ch
Feedback

不要被骗子欺骗!Telemetrio 会找到并标记这些频道 👉 如果想查看标记,请订阅

ፍኖተ-አማራ ሚዲያ (Finote Amhara Media)

ፍኖተ-አማራ ሚዲያ (Finote Amhara Media)

前往频道在 Telegram

የተመሠረተው የአማራን ሕዝብ ለማንቃት፣ ለማደራጀት እና ለማስተባበር ነው። የአማራ ሕዝብን ✅ ፖለቲካዊ ✅ ማህበራዊ ✅ ኢኮኖሚያዊ ታሪካዊ ጥያቄዎችን ለማሰማት እና የአማራን ሕዝብ በማንቃት ሰፊውን ሕዝብ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ይሰራል። ወደዱም ጠሉም የኃላ ታሪካችን በእኛ እጅ ይፃፋል። አማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ( አፋብን)

显示更多
4 379
订阅者
-924 小时
+2477 天
+1 42930 天
帖子存档
“ስደተሽ ስደታችን ነው”በደከመኝ ግዜ በረታሁ፤በአዘንኩ ጊዜ ተፅናናሁ፤በጎበዝኩ ጊዜ አስተዋልኩ፤በብዙ ሰው መከበብ ውስጥ ባልሆንኩ ጊዜም አልደነገጥኩም ምክኒያቱም በእጄ ከያዝኩት ነፍጥ ይልቅ በልቤ የ
+1
“ስደተሽ ስደታችን ነው”በደከመኝ ግዜ በረታሁ፤በአዘንኩ ጊዜ ተፅናናሁ፤በጎበዝኩ ጊዜ አስተዋልኩ፤በብዙ ሰው መከበብ ውስጥ ባልሆንኩ ጊዜም አልደነገጥኩም ምክኒያቱም በእጄ ከያዝኩት ነፍጥ ይልቅ በልቤ የያዝኩሽ ስደተኛዋን እናቴን አንቺን አምናለሁ በእውነት እኔን ደካማውን በቤትሽ ስላሳደግሺኝ እድለኛ ነኝ በስደት ያለቺውን ቅድስት ሀገረ-ኢቲዬን እንደምታሳርፊያት አልጠራጠርም። ወገን-የፋኖን ማሸነፍ ለምትጠብቁ ሁሉ እንኳን ለደብረ ፅሀይ ቁስቋም ማሪያም ዓመታዊ ክብረ በዓል በሰላም አደረሰን አደረሳቹሁ።ድሉን ለኛ በይው ሁልጊዜም ቁስቋም ማሪያም ናት ለደጀ ሰላምሽ ያብቃን እናቴ አማላጄ🙏 #ጎንደር_ሂዳር_6_ደብረ_ፅሀይ_ቁስቋም_ማሪያም አንተነህ ወርቁ ከጎንደር ሰማይ ስር

የአርበኛ ፍሬው አለና የህይወት እና የትግል ታሪክ! "ጀግና ይሰዋል ትግል ይቀጥላል!" አርበኛ ፍሬው አለና የትውልድ ቦታ ራያ ቆቦ ተኩለሽ ነው:: የመጀመሪያ እና የሁለተኛ ደረጃ ትምህርቱን ቆቦ ከተማ ሚሊኒየም ት/ቤት እና ቆቦ ሃይስኩል ተምሯል:: ወጣቱ አርበኛ ፍሬው አለና የ2ኛ ደረጃ ትምህርቱን ካጠናቀቀ በኋላ ፊቱን ወደ ግል ስራ በማዞር የግል ስራዎችን ይሰራ የነበረ ሲሆን ባለ ትዳርና የሁለት ልጆች አባትም ነበር:: አርበኛ ፍሬው አለና በ2013 ዓ.ም የተቀሰቀሰውን የሰሜኑን ጦርነት ተከትሎ ፋኖን በመቀልቀል የዞብል አምባ ክፍለጦር አባል በመሆን በርካታ ተጋድሎዎችን በማድረግ ስሙን በታሪክ መዝገብ አስፍሯል:: የሰሜኑ ጦርነት በፕሪቶሪያው ስምምነትና ድራማ መጠናቀቅ ማግስት የአማራ ህዝብ የዘመናት ጥያቄዎች በብልፅግናው አገዛዝ በኃይል መታፈን ጋር ተያይዞ ፋኖ ወደ ለየለት የፖለቲካ ት ጥቅ ትግል መግባቱ የሚታወቅ ሲሆን አርበኛ ፍሬው አለና ቆቦ ከተማ በህቡ እየተንቀሳቀሰ ስውር ድርጊያዎችን በመፈፀም ትግሉን ቀጠለ:: አርበኛ ፍሬው አለና የፋሽስቱ አገዛዝ ሰዎች እስከሚጠረጥሩና እስከሚነቁበት ድረስ ከአንድ አመት በላይ ጊዜ ቆቦ ከተማ በህቡ በመንቀሳቀስ በርካታ ተጋድሎዎችን በማድረግና ጀብዶችን በመፈፀም ከተማውንና ግንባር ያለውን ፋኖ ድልድይ ሆኖ በማገናኘት የትግሉን ሚዛን በመጠበቅ ጉልህ ሚና ተጫውቷል:: በነበረው ተጋድሎም ቆስሎ ታክሞ ብዙም ሳያገግም ተመልሶ ወደ ትግሉ ገብቷል:: በዚህ ጊዜም ከተማ ውስጥ በፋሽስቱ አገዛዝ መካከል ሆኖ ከሌሎች ጓዶቹ ጋር በመተባበር ከ50 በላይ ክላሾችን ከብልፅግና ሰዎች በመሰብሰብ ፋኖን አስታጥቋል:: አርበኛ ፍሬው አለና ከስውር ድርጊያው በመውጣት ወደ መደበኛው የግንባር ተጋድሎ በመቀላቀል የምኒልክ ዕዝ ልዩ ዘመቻን በመቀላቀል የክፍለጦር ዘመቻ መሪ በመሆን በበርካታ የቤተ-አማራ አካባቢዎችና ግንባሮች የጠላትን አንገት ያስደፋ የወገንን አንገት ቀጥ ያደረጉ ድሎችን ተጎናጽፏል:: አርበኛ ፍሬው አለና ምኒልክ ዕዝ ባወጀውና ከመስከረም 14-30/2018 ዓ.ም በቆየው ዘመቻ አርበኛ አደም አሊ (አባ ናደው) የዕዙ ልዩ ዘመቻ አሃድ የሆነውን ክፍለጦር ዘመቻ መሪ ሆኖ በርካታ ወታደራዊ እና ፖለቲካዊ ብሎም ዲፕሎማሲያዊ ድሎችን ተጎናፅፎ ከዘመቻው መገባደድ በኋላ የነበረውን የጠላት ከባድ ማጥቃት በመመከት ተኩለሽ ግንባር በነበረ ትንቅንቅና ተጋድሎ ከቆቦ ከተማ በቅርብ ርቀት ልዩ ስሙ ጠበለት የተባለ ቦታ ላይ ጥቅምት 6/2018 ዓ.ም ለአማራ ህዝብ ሁለንተናዊ ነፃነት ሲል መስዋዕትነት ከፍሎ አልፏል:: በመጨረሻም እኛ የትግል ጓዶቹ ወጣቱ አርበኛ ፋኖ ፍሬው አለና የተሰዋለትን የአማራ ህዝብ የህልውና ትግል ለድልና ነፃነት እናበቃለን! ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን! የትግል ጓዶቹ ከትግሉ ሜዳ! አፋብኃ ምኒልክ ዕዝ ህዳር 6/2018 ዓ.ም

ታላቅ ስቦ የማስከዳት ዜና የአረመኔው ጡት ቆራጩ የብልፅግና ጦር እየፈረሰ ነው ህዳር 06/2018 ዓ.ም 24ኛ ክ/ጦር ደባይ ጮቄ ሻለቃ በአፋብኃ ምዕ/ አማራ ቀጠና ቴዎድሮስ ዕዝ 206ኛ ኮር 24ኛ
+1
ታላቅ ስቦ የማስከዳት ዜና   የአረመኔው ጡት ቆራጩ የብልፅግና ጦር እየፈረሰ ነው ህዳር  06/2018 ዓ.ም  24ኛ ክ/ጦር ደባይ ጮቄ ሻለቃ በአፋብኃ ምዕ/ አማራ ቀጠና ቴዎድሮስ ዕዝ 206ኛ ኮር 24ኛ ክ/ጦር በደባይ ጮቄ ሻለቃ የአረመኔው የአገዛዙ ሎሌ ሰራዊት ዛሬም በመፍረስ ላይ ነው።በዛሬው ዕለት ስመኘው ቢሰጥ አሰፋ  የተባለ ወጣት የአገዛዙ መከላከያ ሰራዊት አባል 6ኛ ዕዝ 52ኛ ክ/ጦር 1ኛ ሪጅመንት ሻምበል 3 የአፋብኃ ምዕ/አማራ ቀጠና ቴዎድሮስ ዕዝ 206ኛ ኮር 24ኛ ክ/ጦር ደባይ ጮቄ ሻለቃ ፋኖን ተቀላቅሏል።በ24ኛ ክ/ጦር በደባይ ጮቄ ሻለቃ ብቻ በዚህ ሳምንት  በተለያዬ ቀን 4 የመካከያ ሰራዊትና 1ሚሊሻ አባል መቀላቀላቸው ይታወቃል!!! አዲስ ትውልድ አዲስ ተስፋ  አዲስ አስተሳሰብ አፋብኃ ምዕ/አማራ ቀጠና ቴዎድሮስ ዕዝ 206ኛ ኮር 24ኛ ክ/ጦር ህዝብ ግንኙነት

ሰበር አሳዛኝ የእገታ መረጃ‼️ በኦሮሚያ ክልል አርሲ ዞን መርቲ ወረዳ፡ አቦምሳ ከተማ ለመድረስ ጥቂት ኪ.ሜ ሲቀረው፤ ልዩ ቦታው #አይፋ_ዳገት ላይ 31 ንፁሃን ዜጎች ታግተው ተወስደዋል ። በትናትናው ዕለት በቀን 05/3/2018 ዓ.ም፤ ከናዝሬት ከተማ ወደ አቦምሳ የሚጓዝ የህዝብ ማመላለሻ መኪና ሰዎችን ጭኖ በሚጓዝበት ወቅት አይፋ ዳገት በሚባል አከባቢ ላይ ሲደርስ፤ የታጠቁ ሀይሎች መንገድ በመዝጋት ፥ ተሽከርካሪ መኪናውን በማስቆም 31 ንፁሃንን አፍነው ወደማይታወቅ ስፍራ መወሰዳቸውን እንዲሁም እስካሁን ድረስ በግፍ የታገቱት ንፁሃን ዜጎች የት እንዳሉ ፥ በምን ሁኔታ ላይ እንዳሉ ማወቅ አልቻልንም ሲሉ ሁለት ስማቸው እንዳይጠቀስ የፈለጉ የታጋች ቤተሰቦች ከ ከሰም ሚዲያ ጋር ቆይታ ባደረጉበት ወቅት ተናገረዋል ። አክለውም፤ በኦሮሚያ ክልል በሁሉም ቦታዎች በማንነታችን ምክንያት ንፁሃን ዜጎች እንታገታለን ፥ በአሰቃቂ ሁኔታ እንታረዳለን ፥ እንደላለን ፥ እንፈናቀላለን... ይህ ሁሉ ግፍ ሲፈፀም ግን አንድ ሰሚ አካል ግን ሊገኝ አልተቻለም ። በየጊዜው ዜጎች ይታገታሉ፤ ለመልቀቅ በሚሊዮን የሚቆጠር ገንዘብ ይጠይቃሉ፤ ገንዘቡ ከተከፈለ በኋላ ግን በአሰቃቂ ሁኔታ ይገድሏቸዋል ። ኦነግ ሸኔም ሆነ "መንግስት ነኝ" የሚለው አካልም ለእኛ ልዩነት የላቸውም፤ ሁለቱም እየገደሉን ነው ሲሉም ተደምጠዋል ። በኦሮሚያ ክልል በተለያዩ ቦታዎች መፍትሄ የታጣለት የማንነት ተኮር የሆነ የግድያ እና የእገታ ዜናዎች ዛሬም እንደቀጠሉ ናቸው...።

የድል ዜና የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ደቡብ አማራ  ቀጠና አሳምነው ዕዝ ዓፄ ዘርዓ ያዕቆብ አንደኛ ኮር የበፍቃዱ በላይ ክፍለ ጦር ድልን ተቀናጀ! በትላንትናው ዕለት በቀን 05/03/2018 የአብይ አህመድ አገዛዝ ዓፄ ዘርዓ ያዕቆብ አንደኛ ኮር በፍቃዱ በላይ ክፍለ ጦር አናብስቶች አሉበት ወደ ተባለው ቀጠና የጠላት ኃይል ዘልቆ በመግባት ከበባ ለማድረግ ቢሞክርም በክንደ ነበልባሎች ሙትና ቁስለኛ ሆኗል። በመሆኑም ጠላት በሰፊው ከጉንዶ መስቀል በመነሳት ከግራኝ ሙቀጫ እስከ ሀንቁ ባለው ቀጠና  ከስድስት ስዓት  በላይ የወሰደ ውጊያ በማድርግ  የጡት ቆራጩ ኃይል ሶስት መኪና አስከሬን በመያዝ አይቀጡ ቅጣት በመቀጣት እንዲሁም የበፍቃዱ በላይ ክፍለ ጦር  ትግስት ይርሳው ብርጌድ በማከፍታ ቀጭኔ ቀጠና በአደረጉት ውጊያ በጠላት ላይ ከፍታኛ ኪሳራ ማድረስ ተችሏል። በመሆኑም የአብይ አህመድ ተላላኪ ባንዳና ወራዳ መከላከያ በዚህ አካባቢ ፋኖን አጠፋለሁ በማለት በዘጠኝ ሪጅመት በሜካናይዝድ የታገዘ ውጊያ ቢያደርግም በአሳምነው አናብስቶች ከጥዋቱ አስራ አንድ ስዓት እስከ ቀኑ ሰባት ሰዓት በመደበኛ ውጊያ ሲዋጉት ውለዋል።  እንደለመደው አሁን የማህበረሰብ የሰብል መሰብሰቢያ ወቅት በሞሆኑ አማራን ከምድረ ገፅ እንዲጠፋ ስልጣን ከያዘበት ቀን ጀምሮ በደራ አማራ ያላደረገው ያልሰራው ስራ የለም ነገር ግን ጀግኖች የአማራ እናት የወለደቻቸው የበፍቃዱ  በላይ ክፍለ ጦር በአስደማሚ ሁኔታ ሙትና ቁስለኛ በማድረግ ድልን ተቀናጅተዋል። አማራ በታሪክ ጀምሮ ያልጨረሰው የትግል ምዕራፍ የለም አባቶቻችን ብዙ ጥበብን፣ ፅናትን፣ አይበገሬነትን አስተምረውን አልፈዋል። እኛም የአባቶቻችን ፈለግ ተከትለን በጥበብ፣ በፅናትና በአሸናፊነት መንገድ የጀመርነውን የአማራን ህዝብ ከመጥፋት የህልውና አዳጋ የማዳንን ሂደት በማይታመን ፍጥነት ወደ ፊት እየገሰገሰ በጠላት ላይ የበላይነት በመውሰድ ዳር ለማድረስ ጠንክረን እየሰራን እንገኛለን ። መረጃውን ያደረሰን የአፋብኃ  ደቡብ አማራ ቀጣና አሳምነው ዕዝ አፄ ዘርያዕቆብ  ፩ኛ ኮር  የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አርበኛ አማረ ታዘዘ ነው። " ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን"      አፋብኃ ደቡብ  አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ  የህዝብ ግንኙነት ዜና ክፍል ህዳር 06/03//2018 ዓ.ም

አስፈሪው እና ጠላቱን ማርኮ ታጣቂው" አዲሱ የዐማሓራ ሃይል እየመጣ ነው!

ሆሮ ጉዱሩና ምስራቅ ወለጋ ዞኖች የተለያዩ አማራ የሚኖርባቸው ወረዳዎች አማራው ትጥቁን እንዲፈታ እዬተደረገ በዞንና በወረዳ አመራሮች የሚሰለጥኑ ቄሮች የክልሉ መንግስት ከሚያቀርብላቸው መሳርያዎች በተ
+5
ሆሮ ጉዱሩና ምስራቅ ወለጋ ዞኖች የተለያዩ አማራ የሚኖርባቸው ወረዳዎች አማራው ትጥቁን እንዲፈታ እዬተደረገ በዞንና በወረዳ አመራሮች የሚሰለጥኑ ቄሮች የክልሉ መንግስት ከሚያቀርብላቸው መሳርያዎች በተጨማሪ የአማራውን መሳርያ በሀይል በመቀማት እያስታጠቋቸው ይገኛሉ። የህልውና ስጋት አለብን ህጋዊ መሳርያችንን አንፈታም ያሉ አማሮች በመከላከያ እዬተከበቡ ትጥቅ እንዲፈቱ ከተደረጉ በኋላ ወደ ዞንና ወረዳ ማጎርያ ቤቶች እዬተወሰዱ ከፊሉ አድራሻቸው እዬጠፋ ይገኛል። በወረዳና በከተማ አስተዳደር እንዲሁም በዞኖች የሚሰጠው የቄሮ ስልጠና ተጠናክሮ የቀጠለ ሲሆን ይህ ከቻች በምስሉ ላይ የሚታዩት ምስራቅ ወለጋ ዞን አንገር ጉትን ከተማ አስተዳደር ደረጀ በየነ፣ምክተሉ ፈቀደ ደሬሳና በጸጥታ ዘርፍ ሀላፊው ሰኝ ነጋ የሚሰለጥንና ለሚሰጠው ግዳጅ ብቁ እንዲሆን እዬተሰራበት ያለ በአማራ ጥላቻ ያበደ የአማራውን ሀብት ንብረት ለመዝረፍ ብሎም አማራውን ከወለጋ ምድር ለመንቀል ሌት ተቀን እንቅልፍ አጥቶ የሚሰለጥን ሀይል ነው።

ይህ ከላይ የምታዩት ወንድሙ ካሳ ይለባላል በኤፍራታ ግድም ወርዳ ነው ተወልዶ ያደገው ይህ ሰው በቅርቡ በኤፍራታ ግድም ወርዳ የፋኖ ቤተሰቦችን ከአገዛዙ ጋር በመሆን ህፃናትን ያሳግታል አልፎም ተርፎሞ ከአብይ አህመድ መከላከያ ጋር አብሮ በአጣዬ እና በዙሪያው ባሉ ቀበሌዎች ሴቶች እህቶቻችን ያስደፍራል ወንድሞቻችንን ከመከላከያ ጋር በመመሳጠር ከብልፅግና ማጎሪያ ቤት አጉሮ ከሞት የተረፉት እስከ ሚሊዮን ገንዘብ እየተቀበለ የአማራን ህዝብ እየዘረፈ ለግል ጥቅሙ እየሰራ እንደሚገኝ የሚታወቅ ሃቅ ነው። ይህ በ እንዲህ እንዳለ በአጣዬ ዙሪያ በሚኖሩት ማህበረሰብ ውስጥ እየገባ የፋኖ እህል አስቀምጣችኋል በማለት እየዘረፈ ይሸጣል ሆኖም ይህ ሆድ አምላኩ ወንድሙ ካሳ በአማራ ፋኖ የነፃነት ጦርነት በአማራ ህዝብ ላይ ያልሰራው ያላስረሸነው የአማራ ወጣት የለም ብንል ማጋነን አይሆንም ። ዛሬ እንደምታዩን የውጭ አገር ፕሮሰሲንግ ጨርሶ ወደ ውጭ ለመውጣት ዝግጅት ላይ ነው ያለው ሆኖም የአማራ ፋኖ የህዝብ ልጅ ነው ስንል በምክንያት ነው የአማራን ህዝብ በሆዳቸው የሸጡ ሌት ከቀን እየሰሩ ያሉ እንደዚህ ሰው አይነት ባንዳዎች በጣም ብዙህ ናቸው። ዛሬ ላይ ለአማራ ህዝብ የሰላም አባሳደር መስለው ከብልፅግና ጋር ያላቻ ጋብቻ ተጋብተው የሚኖሩ እንደ ተመስገን ጥሩነህና ቀንድ አውጣው የመሳሰሉ ደናቁርት ዛሬ ላይ ውኃ ሞልቶባቸው መሸጋገሪያ አጠው የተቸገሩበት መሆኑን ከእርሱ ከዚህ ከአማራው ባንዳ ከወንድሙ ካሳ የቅርብ ጓዶቹ መስማት ችለናል አጣዬ ከተማ ከአስራ አንድ ግዜ በላይ በአገዛዙ ቅጥረኞች ስትቃጠልና ስትደበደብ ወንድሙ ካሳ የጡት ቆራጩ ኃይል ጋር በመሆን የማህበርሰቡን ትጥቅ በማስፈታትና አገዛዙን ከፊት ሆኖ በመምራት ግንባር ቀደመው ባንዳ ነው። ሆኖም በየትኛውም አለም የምትኖሩ የአማራ ህዞቦች የአብይ ወንበር አስጠባቂ ብአዴኖች ግባተ መሬታቸውን የምፈፅምበት ቅርብ ነው ስለዚህም በየትኛውም አለም የምትኖሩ አማራዊያ እኛ የዚህን ባንዳና ወራዳ ሌባ ከመጀመሪያው እስከ መጨረሻው ተከታታለን በሔደበት ሔደን ለፍርድ የምናቀርብበት ስዓት ስለሆነ ሁላችንም በአይን ቁራኛ አብረን እንድንከታተለው ስንል በአክብሮት እንገልፃለን ሞት ለአብይ አልመድና ወንበርና አስጠባቂ ብአዴን ካድሪዎች። የአገዛዝ ወነበር አስጠባቂ በሞትና በህይወት ሞቶ በሃሳበ በመወተርተር ላይ ያለው የቀንድ አውጣው ነፍስ ገዳይ  ሚኒሻና የብርሃኑ ጁላ መከላከያ እያሰቃዩት ያለውን ህዝባችን ነፃ የምናወጣበት ግዜ ቅርብ ነው። መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!! ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን         ህዳር 6/03/2018 ዓ.ም

ሁለት የሀገር በቀል ጥቁሩ ፋሽስት ከፍተኛ አመራሮች የሆኑት ተደመሰሱ! አፋብኃ ምስርቅ አማራ ቀጠና ሚኒሊክ ዕዝ የደጋው መብረቅ ኮር አንሻ ክፍለጦር በትናንትናው አውደ ውጊያ የአድማበትን ሁለት ከፍተ
ሁለት የሀገር በቀል ጥቁሩ ፋሽስት ከፍተኛ አመራሮች የሆኑት ተደመሰሱ!    አፋብኃ ምስርቅ አማራ ቀጠና ሚኒሊክ ዕዝ የደጋው መብረቅ ኮር አንሻ ክፍለጦር በትናንትናው አውደ ውጊያ የአድማበትን ሁለት ከፍተኛ አመራር ተደምስሰዋል ህዳር 5/2018 ዓ/ም  ከወቂታ እስከ ፍላቂት    በነበረው አውደ ውጊያ  የጥላት ሰራዊት ሙሉ በሙሉ በሚያስብል ደረጃ መደምሰሱን የዘገብን ሲሆን። ከዚህ ጋር ተያይዞ የአማራን ህዝብ በከርሳቸው ፍጆታ የሸጡ አብርሀምና ጌታቸው የተባሉ የአድማበትን የውህድ ምክትል አዛዥ እና ከፍተኛ አመራር በአውደ ውጊያው ተደምስሰዋል። የቀብር ስርዓታቸው ዛሬ ህዳር 6/2018 ዓ/ም እደሚፈፀምም ያገኘነው መረጃ ያሳውቃል። የሶስት ሻለቃ ውህድ ምክትል አዛዥ የሆነው ጌታቸው የሚባል ባንዳ በትናንትናው እለት አውደ ውጊያው ላይ ሲሸኝ፤አብርሀም የሚባለው ከፍተኛ አመራር ግን ከባድ ቁስለኛ ሆኖ ወደ ሆስፒታል ቢገባም የአብይ አህመድ የከርስ መሙያ ብር ህቅታውን ሊታደጋት አልተቻለውም ነበር።በባንዳነት ህዝባቸውን ክደው ለፋሽስቱ ሲያጎበድዱ የነበሩት ሁለቱም ወደ አምላካቸው ተሸኝተዋል። መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልዉና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል! ህልዉናችን በተባበረ ክንዳችን! የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል (አፋብኃ) የደጋው መብረቅ ኮር  አንሻ ክፍለ ጦር ህዳር 6/2018 ዓ.ም

የአዲሱ " ረመጡ ደጀን" ክጦር አመራሮች... አርበኛ እሸቴ አሸብር አድማሱ ...ዋና አዛዥ አርበኛ ደሳለኝ ተቀባ በላይነህ ...ም/አዛዥ
የአዲሱ " ረመጡ ደጀን" ክጦር አመራሮች... አርበኛ እሸቴ አሸብር አድማሱ ...ዋና አዛዥ አርበኛ ደሳለኝ ተቀባ በላይነህ ...ም/አዛዥ

ዛሬ ኅዳር 5 ቀን ከአዳማ ወደ አርሲ አቦምሳ ሲሄድ የነበረን ቅጥቅጥ ባስ ሙሉ ሕዝብ አሸባሪዎቹ አግተዋል ተባለ፡፡ ከተጓዦቹ ውስጥ ምን ያህል አፍነው እንደሚወስዱ አልታወቀም ተብሏል፡፡ ፍትሕ ለአርሲ ኦርቶዶክሳውያን

"የመንግስት መገናኛ ብዙሀን እንደዛሬው ትክክለኛ መረጃ ካቀረቡ የሚጣልብንን ግብር በራሳችን ተነሳሽነት እንከፍላለን። ዛሬ በጣም ነው ያስደሰቱኝ።" አለኝ አንዱ ወዳጄ ከአዲስ አበባደውሎ። "ምን ዝግጅት አቅርበው ነው ያስደሰቱህ?" እለዋለሁ፤ ምን ብሎ ቢመልስልኝ ጥሩ ነው፦ "በቴክኒክ ምክንያት ስርጭታቸው በመቋረጡ!"

206ኛ ኮር በደጀን በፈፀመው ታላቅ ጀብድ የሟቾች ቁጥር እየጨመረ ይገኛል። ህዳር 5 2018 ዓ.ም የ206ኛ ኮር 34ኛ ክ/ጦር በጠላት ካም ላይ ባደረገው የከበባ ጥቃት ሁለት የፖለቲካ አመራሮችን ጨ
+1
206ኛ ኮር በደጀን በፈፀመው ታላቅ ጀብድ የሟቾች ቁጥር እየጨመረ ይገኛል። ህዳር 5 2018 ዓ.ም የ206ኛ ኮር 34ኛ ክ/ጦር በጠላት ካም ላይ ባደረገው የከበባ ጥቃት ሁለት የፖለቲካ አመራሮችን ጨምሮ በርካቶች የተደመሰሱ ሲሆን ከፍተኛ ጉዳት ደርሶባቸው ህክምና ሲደረግላቸው የነበሩ የፖሊስ አመራር የሆነው ም/ኢንስፔክተር ሀብቴን ጨምሮ፣ 1 .እንደግ ጤናው 2 .አስረሱ አባትነህ 3. አበባው መኩ የተባሉ የሚኒሻ ጠርናፊና አመራሮች መሞታቸው ተረጋግጧል። የ34ኛ ክ/ጦር ዛምበረሃ ሻለቃ ባደረገችው ጥቃት የተደናበረው ጠላት ከደጀን እስከ ደብረ ማርቆስ ባሉ ከተሞች ያሉ ካድሬዎች በከፍተኛ ጭንቀት የተዋጡ ሲሆን የጦር አመራሩ በማረጋጋት ስራ ተጠምዷል ። አዲስ ትውልድ! አዲስ አስተሳሰብ! አዲስ ተስፋ የአፋብኃ ቴዎድሮስ ዕዝ 206ኛ ኮር ህዝብ ግንኙነት

የደጋው መብረቅ ኮር ከወቄታ እስከ ፍላቂት ባለው ቀጠና በርካታ የጥላት ሃይል በመደምሰስ ድል ተጎናፀፈ:: አፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ሚኒሊክ ዕዝ የደጋው መብረቅ ኮር አንሻ ክፍለ ጦር በጥላት ላይ በወሰደችው ከፍተኛ ጥቃት በመቄት ወረዳ ታይቶ የማይታወቅ ታሪክ ሰራች። ከማለዳው 4:00 ሰዓት ጀምሮ እስከ ምሽት አንድ ሰዓት በዘለቀው እልክ አስጨራሽ አውደ ውጊያ ከወቄታ እስከ ፍላቂት ቀጠናውን ዘርግቶ ሲለበለብ ውሎ ያመሸው የጥላት ሰራዊት ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ ተደመሰሰ። የፋሽስቱ ሰራዊት ሙትና ቁስለኛውን በስምንት ፓትሮል ሲያጎጉዝ የዋለ ሲሆን ሶስት ፓትሮል ሙት፤አምስት ፓትሮሎች ቁስለኛን ጭነው ሲያመላልሱ ውለዋል።የጥላት ጥምር ሰራዊት ተብየው ጣረሞቱን አፋጥኖ ሞቱን ተረክቧል። ከአፍንጫው ዳር ሞትን እያነፈነፈ ያለው ስርአት በመቄት ወረዳ በግስላዎቹ ሞትን እድጎርሳት ተደርጓል። የደጋው መብረቅ ኮር የፋሽስቱን ሰራዊት ከመሀል አስገብቶ  ቅንድብ ቅንድቡን በመቀንደሽ ወደማይቀረው አለሙ እየሸኘው ለምስጥ ሲሳይ አድርጎታል። ፎክሮና ፎግሮ አማራ ክልል የገባው የጥላት ሰራዊት እና በሆዱ የተገዛው ባንዳ በአንሻ ክፍለ ጦር አመርቂ አሸኛኜት ተደርጎለታል። መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልዉና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል! ህልዉናችን በተባበረ ክንዳችን! የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል (አፋብኃ) የደጋው መብረቅ ኮር  አንሻ ክፍለ ጦር ህዳር 5/2018 ዓ.ም

ትግላችን ከዳር እንዲደርስ የአማራው ወንድምህን አቅም ተቀበል ተጠቀምበት ጠብቀውም እርስ በራሳችን እንዋደድ የሀሳብ ልዩነቶችን ወደ ጎን በመተው የተገፋውን ማሕበረሰባችንን ከስቃይ እንታደገው ። የዕለ
ትግላችን ከዳር እንዲደርስ የአማራው ወንድምህን አቅም ተቀበል ተጠቀምበት ጠብቀውም እርስ በራሳችን እንዋደድ የሀሳብ ልዩነቶችን ወደ ጎን በመተው የተገፋውን ማሕበረሰባችንን ከስቃይ እንታደገው ። የዕለቱ መልዕክቴ ነው Dega Damot Timely * አንድነት ኃይል ነው 💪 * የሀሳብ የበላይነትን እናክብር 💪 * አማራነት ይለምልም 💪 # አዲስ ትውልድ # አዲስ አስተሳሰብ # አዲስ ተስፋ ፎቶ ደጋ ዳሞት በሰዓቱ - ሻለቃ ዝናቡ ልንገረው - ሻለቃ ሙላቱ ሲሳይ

በቅርብ ቀን የተዋቀረው የጊዜያዊ መንግስት የህዝብ ውይይቱ እያካሄደ ይገኛል። ህዳር 05/2018 ዓ.ም በእነማይ ወረዳ 3 ቀበሌወችጊዜያዊ መንግስት አስተዳደር ህዝባዊ ውይይት በማካሄድ ከውጊያው ጎን
+5
በቅርብ ቀን የተዋቀረው የጊዜያዊ መንግስት የህዝብ ውይይቱ እያካሄደ ይገኛል። ህዳር 05/2018 ዓ.ም በእነማይ ወረዳ 3 ቀበሌወችጊዜያዊ መንግስት አስተዳደር ህዝባዊ ውይይት በማካሄድ ከውጊያው ጎን ለጎን የስርአተ መንግስት ተከላ ስራ ተጠናክሮ የቀጠለ ሲሆን ደብር፣ ደንሳ እነቆራ እና አዲስ አለም ቀበሌዎች ላይ ህዝባዊ ውይይቶች ተካሂደዋል። የእነማይ ወረዳ ጊዜያዊ መንግስት አመራሮች በሶስቱም ቀበሌዎች ህዝብ ያመነባቸውን የቀበሌ አስዳደር፣ ም/አስተዳደሪ፣ ፀሀፊ፣ ፀጥታ ዘርፍ፣ የፍትህ አካላት፣ ገቢና ሀብት አሰባሰብ፣ ወጣት ተጠሪ እና በሶስቱም ቀበሌዎች የህዝብን ችግር ለመፍታት ህዝብ ያመነባቸው ችግር ፈች ሽማግሌዎችን አዋቅሯል። አፋብኃ ቴወድሮስ እዝ 201ኛ ኮር ህዝብ ግንኙነት ፋኖ ሐብታሙ የሱፍ አዲስ ትውልድ፣አዲስ አስተሳሰብ፣አዲስ አስተሳሰብ!      ህዳር 05/2018 ዓ.ም

የአፋብኃ ሰሜን አማራ ቀጠና #በላይ ዕዝ ሜጀር ጀኔራል ዉባንተ አባተ ፩ኛ ኮር ድልን ተቀዳጀ። በዛሬዉ እለት ህዳር 05/2018 ዓ.ም ሜጀር ጀኔራል ዉባንተ አባተ ፩ኛ ኮር ጉና ክ/ጦር አርበኛ ገብረመስቀል ደርብ ብርጌድ #ጋፋት ሻለቃ፣ #ኮከብ ሻለቃ እና #ታቦር ሻለቃ በመቀናጀት ከደብረታቦር ወደ እብናት ሲጎዝ በነበረ የስርአቱን ቅጥረኛ ከ12፡00 ሰአት ጀምሮ እስከ ቀኑ 6፡40 ሰአት ልዩ ቦታዉ ቡሮ ተብሎ በሚጠራዉ ቦታ ደፈጣ በመጣል የጠላት ሀይልን በሚገባ አስተናግደዉታል። ከደብረታቦር 18 መኪና ጠላትና ሬሽን የጫነ ሲሆን ከእብናት የወረደው አመራር ከ10 መኪና በለይ ታጅቦ ሲመጣ አናብስቶቹ ምን ዉስጥ ገባሁ ብሎ ሲርበተበትና ነብሱን ለማትረፍ ሲፍጨረጨር ዉሏል። በአዉደ ዉጊያዉም የተገኙ ድሎችም የሞተ 14 እና ቁስለኛ ደግሞ ከ20 በላይ አድርጎ በሁለት መኪና ጭኖ ሙትና ቁስለኘውን ወደ ደብረታቦር ይዞ ተመልሷል። በጥቃቱ ከፍተኛ መደናገጥ ውስጥ የገባው ሰራዊቱ ቁስለኛውንና አስከሬኑን በመያዝ ወደ ደብረታቦር ገብቷል። በዚህም የተነሳ ቁስለኛውንና አስከሬኑን ለማንሳት ተጨማሪ የጠላት ኃይል ከደብረታቦር ከተማ ተነስቶ ውጊያው ከተካሄደበት ቦታ በመድረስ በወገን ሃይል ላይ ተኩስ የከፈተ ሲሆን ነበልባሎቹ ፋኖዎች የለመደውን የሽንፈት ካባ አከናንበዉታል ሲል የብርጌዱ ህዝብ ግንኙነት ሀላፊ አርበኛ በላይነዉ ልብሱ ተናግራል። ኅልውናችን በተባበረ ክንዳችን። አፋብኃ ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዘለቀ እዝ ህዳር 05/2018 ዓ.ም