ch
Feedback
ፍኖተ- አማራ ሚዲያ (Finote- Amhara ) Midea

ፍኖተ- አማራ ሚዲያ (Finote- Amhara ) Midea

前往频道在 Telegram

የተመሠረተው የአማራን ሕዝብ ለማንቃት፣ ለማደራጀት እና ለማስተባበር ነው። የአማራ ሕዝብን ✅ ፖለቲካዊ ✅ ማህበራዊ ✅ ኢኮኖሚያዊ ታሪካዊ ጥያቄዎችን ለማሰማት እና የአማራን ሕዝብ በማንቃት ሰፊውን ሕዝብ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ይሰራል። ወደዱም ጠሉም የኃላ ታሪካችን በእኛ እጅ ይፃፋል። አማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ( አፋብን)

显示更多
3 606
订阅者
+6624 小时
+5877 天
+1 04130 天
帖子存档
ከብር ሸለቆ ወታደራዊ ማሰልጠኛ አፍንጫ ስር #ላይ_ብር የሰፈረው ሚኒሻ  በ77ተኛ ክፍለጦር ሻለቃ 4 ሙሉ በሙሉ ተወ--ግ--ዷል! ══════════════💝💝════════════════                       መጋቢት 08/07/2018 ዓ.ም የ77ኛ ክፍለ ጦር አራተኛ ሻለቃ  ምህረት ተሰጥቷቸ ባልተቀበሉ ባንዳዎች የስርዓቱ ሚሊሻ  አገልጋዮች ላይ ከብር ሸለቆ ወታደራዊ ማሰልጠኛ አፍንጫ ስር #ላይ_ብር  ከተማን በሌሌት በመክበብ እርምጃ ተወሰ-ደባቸው፡፡ 109ኛ ኮር የ77ኛ ክፍለ ጦር አራተኛ ሻለቃ በብርሸለቆ ማሰልጠኛ ተቋም ዙሪያ ላይ ብር  ልዩ ስሙ ወታደር ሰፈር ላይ መሽጎ በተቀመጠው የአገዛዙ ሚሊሻ  ላይ እርምጃ በመውሰድ መሳሪያዎችን መማረክ ተችሏል። የ77ኛ ክፍለ ጦር ነበልባሏ አራተኛ ሻለቃ ባደረጉት ውጊያ የአብይ አህመድ አገልጋይ ሚሊሻ ላይ በተደረገው መብረቃዊ ጥቃት ከተፈፀመባቸው መካከል  አበው ወድማለም፣ስለሽ  ሰማህኝ፣መልካሙእና ሌሎች ስማቸው ያልታወቀ ደግሞ 2  በድምሩ 5 ሙት ሲኖሩ ከ10 በላይ  ከባድ ቁስለኛ ሆነዋል ፡፡ ጠላትን በመደምሰስ ሁለት ክላሽ እና 4የእርቀት መሳሪያ አብራራው እና ኤስኬስ የምርኮ መሳሪያዎችን ማግኘት ተችሏል። የ109ኛ ኮር 77ኛ ክፍለ ጦር ምህረት ተደርጎላቸው ምህረት ባልተቀበሉ ባንዳዎች ላይ እርምጃ እየወሰደ ይገኛል።ለቀጣይም ይቀጥላል። 👉ድል ለዐማራ ህዝብ💪 አፋብን ምዕራብ ዐማራ ቀጠና ቴዎድሮስ ዕዝ 109ኛ ኮር 77ኛ ክፍለ ጦር ህዝብ ግንኙነት መምሪያ

ሶስት የፋሽስቱ አገዛዝ ብልፅግና ወታደሮች የፋኖን ትግል ተቀላቀሉ:: የፋሽስቱ ብልፅግና አገዛዝ ሰራዊት እየፈረሰ የፋኖን የህልውና ትግል እየተቀላቀለ ያለ ሲሆን ሁሉት አድማ ብተና እና አንድ የ58ኛ
+2
ሶስት የፋሽስቱ አገዛዝ ብልፅግና ወታደሮች የፋኖን ትግል ተቀላቀሉ:: የፋሽስቱ ብልፅግና አገዛዝ ሰራዊት እየፈረሰ የፋኖን የህልውና ትግል እየተቀላቀለ ያለ ሲሆን ሁሉት አድማ ብተና እና አንድ የ58ኛ ክፍለ ጦር ሞርተር ኦፒ ባጠቃላይ ሶስት የሰራዊቱ አባላቶች ከወልድያ ዙሪያ በመኮብለል ከነ ሙሉ ትጥቃቸው ምኒልክ ዕዝ 101ኛ ኮር 11ኛ ክፍለ ጦርን ተቀላቅለዋል:: የክፍለ ጦር አመራሮችም አቀባበል አድርገውላቸዋል:: መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልዉና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል! ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን! አፋብን ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ መጋቢት 8/2018 ዓ.ም

ስራ መሰከረ👥 ዘመናዊ የፋኖ ሰራዊት በመገንባቱ ሂደት የበኩላቸውን ሙያዊ አስተዋጽኦ በማበርከት ላይ ያሉት የምኒልክ ዕዝ እንቁዎች፣ የአማራ ህዝብ አለኝታዎች እንድሁም የትውልድ መምህራን እነዚህ ናቸ
+1
ስራ መሰከረ👥 ዘመናዊ የፋኖ ሰራዊት በመገንባቱ ሂደት የበኩላቸውን ሙያዊ አስተዋጽኦ በማበርከት ላይ ያሉት የምኒልክ ዕዝ እንቁዎች፣ የአማራ ህዝብ አለኝታዎች እንድሁም የትውልድ መምህራን እነዚህ ናቸው:: እናመሰግናለን ወንድሞቼ:: Yoseph Asmare Et Gechoo Sisay

የአገዛዙ ቅጥረኛ ሚሊሻ መረጃ እና ደህንነት በቁጥጥር ስር ውሏል!! ባንዳ ሞሳው እንዳለው አስታጥቄ ሸበል በረንታ ቃርማ ቀጣፋ ቀበሌ ተወላጅ ሲሆን የአገዛዙን ሚኒሻ መረጃ ደህንነት በመሆን ለ3(ሶስት
+3
የአገዛዙ ቅጥረኛ ሚሊሻ መረጃ እና ደህንነት በቁጥጥር ስር ውሏል!! ባንዳ ሞሳው እንዳለው አስታጥቄ ሸበል በረንታ ቃርማ ቀጣፋ ቀበሌ ተወላጅ ሲሆን የአገዛዙን ሚኒሻ መረጃ ደህንነት በመሆን ለ3(ሶስት) ወራቶች አገልግሏል። ባንዳ ሞሳው በ64ኛ ክ/ጦር 5ኛ ሻለቃ የመረጃ ደህንነት ክትትል አማካኝነት ከአገዛዙ ተልኮ ተቀብሎ በሸበል በረንታ ገብሲት ቀበሌ እናገዞ አቦ አመታዊ ክብረ በዓል የፋኖን እንቅስቃሴ ለመመረጅ ላይ እንዳለ በአፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 201ኛ ኮር 64ኛ ክፍለ ጦር 5ኛ እሬጅመት መረጃ እና ደህንነት ክትትል በቁጥጥር ስር ውሏል። አዲስ ትውልድ፣ አዲስ አስተሳሰብ፣ አዲስ ተስፋ!!             መጋቢት 09/2018 ዓ.ም የአፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 201ኛ ኮር 64ኛ ክፍለ ጦር ሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ

🔥ጀብደኛው 99ኛ ክ/ጦር ‼️ አፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 109ኛ ኮር 99ኛ ክ/ጦር በደምበጫ ከተማ #አርቡቅ በተባለ ቦታ እና በማቻክል ወረዳ #ደብረቀለሞ በተባለ ቦታ ከባድ ትንቅንቅ ሲያደርግ አርፍዷል፣     ጀብደኛው 99ኛ ክ/ጦር በጦር ጠበብቶች  በ10 አለቃ ሁነኛው እና በሻለቃ አባይነህ  የተመራው ይህ ወጊያ በደምበጫ ከተማ እና ማቻክል ደብረ ቀለሞ ሲያስጨንቁት አርፍደዋል ።የብርሃኑ ጁላ ሰራዊት መግቢያ ቀዳዳ፣ ማምለጫ ጣሻ አጥቶ ሲጨነቅ አርፍዷል በዚህም አውደ ውጊያ መጠነሰፊ የቁስ እና የሰራዊት ኪሳራ ደርሶበታል።       የብርሃኑ ሰራዊት በድሮን የታገዘ ውጊያ ቢያደርግም ያሰበውን ማሳከታ አይደለም ምንም ኪሳራ ሳያደርስ ሙት እና ቁስለኛውን ሲጎትት አርፍዷል። በሌላ መረጃ ጀብደኛው 99ኛ ክ/ጦር ይዋጋል በሰላም የመጡትን በሰላም ይቀበላል ዛሬም ማቻክል ደምበጫ እየተዋጋን ባለበት ሰዓት ደጋ ዳሞት ደግሞ 1ኛ.በረከት ገማልቋ -ደቡብ መሰረታዊ ወታደር ጥቁር ክላሽ 120 ፍሬ ጥይት 2 ካዘና 2ኛ.ሙሉጌታ ተሾመ ሲሳይ - ጎንደር ጥቁር ክላሽ 170 ጥይት  ካዘና 2 3ኛ.ዘገየ ገርሱ -ደቡብ ጎፋ ጥቁር ክላሽ 90 ጥይት 2 ካዘና ይዘው ተቀላቅለውና። ©አፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 109ኛ ኮር 99ኛ ክ/ጦር ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ!

የቆቦ ከተማ ውሀና ፍሳሽ አገልግሎት ቢሮን (የውሀ ልማት) ካዝና በብልፅግና ከመበዝበዝ ማን ይታደገው?? ይህ መስሪያ ቤት ከትላንት እስከ ዛሬ ድረስ ከተፈራረቁ የመንግስት ስርዓቶች እንደ ብልፅግና የፓርቲ ስርዓት ሆኖ ካዝናውን ያራቆተውና የመዘበረው የለም። ይህ ቢሮ የቆቦ ከተማ ብልፅግና በትንሽ በትልቁ ለሚያደርጋቸው የፓርቲ ድግሶች ከፊት ሆኖ በርካታ የህዝብን ገንዘብ እያወጣ ስርዓቱን ለማስቀጠል የሚያደርገው ከልክ ያለፈ ማሽቃበጥ ወደር አይገኝለትም። በከተማው ከንቲባ የቦርድ ሀላፊነትና በታናሽ ወንድሙ የበላይ እንደራሴነት የሚዘወረው ይሄ ተቋም በማንኛውም አጋጣሚ የሚያባክነው ከፍተኛ ገንዘብ ከውሀ ጥምም በላይ ጉሮሮን ከማድረቅ አልፎ አንገትን ቆርጦ ይጥላል። ለስሙ እንደ ተንቀሳቃሽ አሻንጉሊት ያስቀመጡት 'ገበያው አማረ' የተባለ 'Useful Ediot' ቢሮው ውስጥ ሀላፊ ሆኖ ቢቀመጥም ብልፅግና የሚፈልገውን ሲያደርግ ሆን ብሎ አይለማም አይሠማም! ሠውየው በራሱ ፈቃድ የደነቆረና የደነዘዘ አስገራሚ ፍጡር ነው። አድርግ ሲባል ማድረግ፣ አውራ ሲሉት ማውራትና ዝም በል ሲሉት ዝም የሚል ዘመናዊ ፓሮት ነው። ቢያንስ ለራሱና ለቤተሠቦቹ ሲል እንኳ ተጠያቂነት አያሳስበውም። በሠው አምሳል የተቀረፀ ቆንጆ ድንጋይ ነው!! ከተማው ውስጥ ባንድም ይሁን በሌላ መንገድ የአብይ አማራዎች ለሚያደርጉት ትንሽም ይሁን ትልቅ ዝግጅቶች ሆን ተብሎ ከየትኛውም ተቋም በተለየ መልኩ ስፖንሰር እንዲሆን የሚፈለገው ይሄ ቢሮ ነው። 'ባለቤቱን ካልናቁ አጥሩን አይነቀንቁ' እንደሚባለው ብሂል 'ገበያው' የሚሉትን የደነዘዘ ግለሠብ ማንም ከቁብ ሳይቆጥረው ገንዘብ ሲወጣ ብቻ ለፊርማ ያቀርቡታል።ተቋሙ ምንም እንኳ ጠንካራና ሞጋች ሠራተኞች ቢኖሩትም ብልፅግና አስርጎ ባስገባቸው የውስጥ ደህንነትና የመረጃ ሠዎች እንዲሁም አፍቃሪ-ብልፅግናዎች ምክንያት ዝምታን ከመረጡ ሠነባብተዋል። አበበ አሸነፍ፣ሠዒድ አበበ፣ሞላ ወዳጆና ንጉስ አያሌው የተባሉ የከንቲባውና የዞኑ ከድር ሙስጠፋ የውስጥ መረጃ አቀባዮች ምክንያት ሁሉም ተፈራርቶ ከተቀመጠ ቆይቷል። የከተማው የብልፅግና ካድሬዎች ከቆቦ ጀምሮ እስከ አዲስ አበባ ፌደራል ውሀና ኢነርጂ ቢሮ ድረስ እየተሽከረከሩ በተቋሙ ገንዘብ አላስፈላጊ ድግስ፣ስጦታና እጅ መንሻ ሲያጎርፉ የሚገላምጣቸውም ይሁን ሀላፊነት ተሠምቶት የሚያስቆማቸው የጫካም ይሁን የከተማ እንደራሴ የለም። በተለያየ ጊዜ ለፋኖ አመራሮች ይሄ ሀቅ ቢነገራቸውም እስካሁን ድረስ ግን ህዝቡንና ተቋሙን የታደገው ወገን የለም። ሁሌም ምላሹ ውሀ-ጥም ነው!! ስለዚህ መ/ቤት'እናውቃለን፣ ብንናገር እናልቃለን' በማለት በሩን በፍርሀት ዘግቶ የተቀመጠው ህዝብ ቁጥሩ ቀላል አይደለም። ራሱን የመፍትሄ አካል በማድረግ ለኗሪው ህዝብ ሁነኛ መፍትሄ ሊያመጣ የሚሞክርም አካል በተመሣሣይ አልመጣም። በፍየል፣በባህል ልብስ፣በፕላስቲክ ውሀና በተጋነነ የካድሬ አበል ወጭ ስም እየተመዘበረ እዚህ የደረሠው ቢሮ አሁን ደግሞ ደረጃው ከፍ ብሎ በኮሪደር ልማትና በምርጫ ቅስቀሳ ስም ማሟሟቅ ጀምሯል። ግን እስከ መቼ ድረስ በህዝብ ላይ መጫወት??? ብልፅግና It's already dead! የፋኖ ተቋም የት ነው ያለው? ጊዜ መግዛት ለምን አስፈለገ?

አሸባሪው መንግስት የጠራው ስብሰባ በፋኖ ኃይሎች ተበተነ! መጋቢት 08/2018 ዓ.ም የፋሽስታዊና የጅምላ ጨፍጫፊነት ባሕርይውን ሕጋዊ እውቅና ለመስጠትና ሕጋዊ ከለላ ባለው መልኩ የጭፍጨፋ ተግባሩን
አሸባሪው መንግስት የጠራው ስብሰባ በፋኖ ኃይሎች ተበተነ! መጋቢት 08/2018 ዓ.ም የፋሽስታዊና የጅምላ ጨፍጫፊነት ባሕርይውን ሕጋዊ እውቅና ለመስጠትና ሕጋዊ ከለላ ባለው መልኩ የጭፍጨፋ ተግባሩን አጠናክሮ ለመቀጠል የብልጽግናው አገዛዝ እያደረገ ስላለው የምርጫ ዝግጅት በትናንትናው ዕለት በጎዛምን ወረዳ ሊባኖስ ቀበሌ ላይ ወሬውን ለመንዛት የጠራውን ስብሰባ ጀግኖቹ የ206ኛ ኮር 14ኛ ክፍለ ጦር የበረኸኛው ጅበላ ሙተራ ሻለቃ የሠራዊት አባላት በትነውታል። የአገዛዙን ቀጣይ የማደንዘዣ ሴራ የምርጫ ፕሮፓጋንዳ እየፈጸመ ላለው የአውዳሚነት ተግባር ሕጋዊ እውቅና ለመስጠት የሚያደርገውን መንደፋደፍ የተረዳው የቀበሌው ማሕበረሰብም የፋኖ ሠራዊታችን በወሰደው እርምጃ መደሰታቸውን ማወቅ ተችሏል። የአማራ ሕዝብ የሚያዋጣውንና የሚያስፈልገውን ምርጫ ከመረጠ ቆይቷል። እርሱም አፈሙዙ ነው። ድል ለአማራ ሕዝብ! የ206ኛ ኮር 14ኛ ክፍለ ጦር ሕዝብ ግንኙነት ክፍል

#የድሮን_ቅኝት‼️ በአፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 109ኛ ኮር 99ኛ ክፍለ ጦር ቀጠና ማለትም (ደምበጫ ወረዳናና አካባቢው ፣ ማቻክል ወረዳና አካባቢው) የድሮን አሰሳ እየተደረገ ስለሆነ የወገን ኃይልና ማህ
#የድሮን_ቅኝት‼️ በአፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 109ኛ ኮር 99ኛ ክፍለ ጦር ቀጠና ማለትም (ደምበጫ ወረዳናና አካባቢው ፣ ማቻክል ወረዳና አካባቢው) የድሮን አሰሳ እየተደረገ ስለሆነ የወገን ኃይልና ማህበረሰቡ ጥንቃቄ አይለየው‼️ 08/ዐ7/2018 ዓ.ም

የዝምታው ንጉሥ ​ብዕሬን ይዤ ከወረቀቱ ፊት ለፊት ስቀመጥ የዛሬዋ ንጋት እንደ ሌላው አልነበረም። እስካሁን ጽፌ አላውቅም፤ ምናልባትም ቃላትን ሰድሮ ስሜትን መግለጽ ለኔ ብርቅ ሆኖብኝ ይሆናል። ዙሪያዬን ባይ ሰው የለም። ብቻዬን ነኝ። ነገር ግን በውስጤ የሚመላለሰው ስሜትና የሚሰማኝ የህዝብ ሰቆቃ ዝም አትበል ይለኛል። ዛሬ ግን የውስጤን ልፅፍ ወሰንኩ። ​በሃሳብ ሰረገላ ተጭኜ ወደ ኋላ ስመለስ፣ በአይነ ህሊናዬ አንድ ሰው ድቅን አለብኝ። የሰሞኑን የልቤን በር ያንኳኳው፣ የውስጤን ስሜት የቀሰቀሰው ያ አርበኛ ኢንጂነር ደሳለኝ ሲያስብ ሽዋ ስሙን ሳስበው የሚታየኝ የሸዋ ምድር ያ ዳገትና ቁልቁለቱ ነው። ​እሱ ዝምተኛ ነው። ነገር ግን የእሱ ዝምታ እንዲሁ ባዶ አይደለም። ዝምታው እንደ ወርቅ የከበረ፣ እንደ ስጦታም የታደለ ነው። ዝም ብሎ ሲያልም፣ ዝም ብሎ ሲያቅድ፣ ዝም ብሎ ሲመክት... ዝምታው ውስጥ ሺህ ቃላት አሉ። ​በልብወለዱ አለም ውስጥ አርበኛ እንጅነር ደሳለኝ ሲያስብ ሽዋ የሸዋው መብረቅ የአማራው ኩራት የነ አስራት ወልየስ አደራ በክንድህ ላይ አርፏል። ከአበቀለችው ማህፀን የወጣኸው የአንበሳ ደቦል፣ የንጉሱ ልጅ ሆይ! አንተ 'ከእኔ በፊት ህዝቤ!' ብለህ የራስህን ምቾት የናቅህ የቁርጥ ቀን ልጅ ነህ። ​ወረቀቱ ላይ ጠብ የሚለው የቀለም ነጥብ የልቤን ትርታ ይወክላል። ዙሪያዬን ማንም ባይኖርም፣ እንደ ኢንጂነሩ ሁሉ እኔም በጽናት ቆሜያለሁ። ዝምታው ቢያይልም፣ የውስጥ ድምፃችን ግን እንደ ነጎድጓድ ያስገመግማል። ዛሬ ብዕሬን የጨበጥኩት ላንተ ነው፤ ለዛ ጸጥታህ፣ ለዛ ጽናትህ፣ እናም ለዛ 'ህዝቤ ይቅደም' ለሚለው የላቀ የውስጥ አስተሳሰብህ! ክብር ይገባሃል አርበኛ እንጅነር ሲያስብ ሽዋ የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ ዋና ሰብሳቢ Dawit Amhara ከንጉሶች መንደር

ጀብድ ሰርተው ፋኖን ለተቀላቀሉ ለአድማ ብተና አባላት ሽልማት ተሠጠ‼️ መጋቢት 08/2018 ዓ/ም መጋቢት 01/2018 ዓ/ም የአገዛዙ 4/አራት የአድማ ብተና አባላት አዲስ ቅዳም ከመሸገው የጠላት ካፕ በመውጣት 105ኛ ኮር የ44ኛ ክፍለ ጦርን ሲቀላቀሉ 12 /አስራ ሁለት/ መሳሪያዎችንና 12 ትጥቆችን አስከነ ሙሉ ተተኳሻቸው ይዘው የፋኖ አባላትን መቀላቀላቸው ይታወሳል። 1ኛ.እስራኤል እየሱስ አድማ ብ/አባል 2ኛ.ሞገስ እሸቱ አድማ ብ/አባል 3ኛ.አበበ መልካሙ አድማ ብ/አባል 4ኛ.ሞገስ ክንዱ አድማ ብ/አባል በጋራ በመሆን፣ በሰሩት ጀብዱ ከአፋብን ሊቀ መንበር ከአርበኛ ዘመነ ካሴ የአርበኝነት የምስክር ወረቀትን ጨምሮ የገንዘብ ሽልማትም ተበርክቶላቸዋል። ሽልማቱን በውክልና ያበረከቱት የአፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ አመራር፣የ44ኛ ክ/ጦር አመራርና የ55ኛ ክ/ጦር አመራሮች በተገኙበት ተካሄዷል። በሽልማቱ ላይ ተገኝተው መልክት ያስተላለፉት የፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ የዘመቻ መምሪያ ምክትል ኃላፊ ፻ አለቃ ማርቆስ አሞኘ ከጠላት ጎን ወግናችሁ የአማራን ህዝብ የምትወጉ የአማራ ተወላጆች እንደወንድሞቻችሁ በየትኛውም አጋጣሚና ስዓት ብትመጡ ቤታችን ክፍት ነው።ከዚህ ውጭ ግን ምህረትና ርህራሄ እንደሌለን እንድታውቁት እንፈልጋለን ብለዋል። ሌላኛው በሽልማቱ ወቅት መልክት ያስተላለፉት ቴዎድሮስ ዕዝ 105ኛ ኮር የ44ኛ ክ/ጦር የአደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ አርበኛ በላይ አሠፋ የሠራችሁት ጀብድ ለሌሎች ሆዳም አማራዎች ትምህርት የሚሰጥ ስለሆነ፣ሌሎች በተሳሳተ መንገድ ሄደው ወገናቸውን የሚጨፈጭፉ አማራዎች ከናንተ ብዙ መማር አለባቸው ብለዋል። አዲስ ትውልድ፣ አዲስ አስተሳሰብ፣ አዲስ ተስፋ‼️ አፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ የ105ኛ ኮር ሕዝብ ግንኙነት

አማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ አፋብን ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ ከሰም ኮር ኃለማርያም ማሞ ክፍለጦር የተሰጠ ጥብቅ ማስጠንቀቂያ!  መጋቢት 7 2018 ዓ/ም የአማራን ህዝብ ትጥቁንም ቀበቶውንም አስፈትቼ እቀልድበታለሁ በሚል ንቀት ጦርነት የከፈተብን ጠላታችን ዛሬ ደሞ ምርጫ ምረጡ እያለን ነው። እኛ ጦርነት የታወጀብን አማሮች የእልውና ትግል ላይ ነን! ይህ ዛሬ ምርጫ እያለ የሚቀልድ እና በአማራ ህዝብ ላይ የእልውና አደጋ የሆነን ኃይል ፆታ ሳይለይ ሴቱንም ወንዱንም ጨፍጭፏል እድሜ ሳይመርጥ ህፃናትንም አዛውንቶችንም ረሽኗል የትምህርት ደረጃ የስራ ሁኔታ ሳይመርጥ አማራን አሳዷል ገድሏል ሌላው ቀርቶ የኃይማኖት አባቶችን ቀሳውስት ዲያቆናትን በግፍ ረሽኗል።  ይህ የአማራ ህዝብ ጠላት በህዝባችን ላይ ያልፈፀመው ምንም አይነት ምድራዊ ግፍ የለም። እንግዲህ ይህ የአማራ ህዝብ ጠላት ዛሬ ምርጫ ምረጡኝ እያለን ነው። እኛ መልሳችን ልንጥልህ እየታገልንህ ነው የሚል ነው። እያሸነፍነውም ነው። በዚህ ምርጫ በሚል ስላቅ ምክንያት ስንት ወንድሞቻችንን የሰዋንበትን ትግላችን ላይ እንቅፋት የሚሆን ሁሉ ጠላት ነው!! በሰማዕታት ደም አንቀልድም!! እየተሸነፈ ያለ የህዝብ ጠላት ኃይል ምርጫ የሚሉት ቀልድ አይሉት ቁምነገር ጀምሯል። ምረጠኝ የሚለውም እየገደለው እና እያሳደደው ያለውን የአማረን ህዝብ ነው እየገደለን መልሶ ምረጡኝ ማለት ግዳያውን እና ጭፍጨፋውን እንድቀጥል ፍቀዱልኝ ማለት ነው። የኃይለማርያም ማሞ ክፍለጦር በሚቆጣጠራቸው እና በሚያስተዳድራቸው ከዚህ በታች በስም በተዘረዘሩ የከሰም ሀገረማርያም ወረዳ ቀበሌዎች እና ከተሞች ውስጥ ምንም አይነት የምርጫ እንቅስቃሴ እንደማይደረግ ምርጫም እንደማይካሄድ እናሳስባለን።  ፩) ሾላ 01ሀገረማሪያም ከሰም ወረዳ ፪) ቱለፋ ንዑስ ወረዳ ቡልጋ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ፫) ንፋስ አባ ቀበሌ ፬) ሰኮሩ ቀበሌ ፭) ጉርፎ ቀበሌ ፮) አክርሚት ቀበሌ ፯) ስቻት ቀበሌ ፰) ይርማታገር ቀበሌ ፱) ውሃ ሜዳ ቀበሌ ፲) ዛላ ዘባባ/መስኖ/ቀበሌ ፲፩) ቅዱስጌ ቀበሌ ፲፪)/የወላት ቀበሌ ፲፫)ኮረማሽ ንዑስ ቀበሌ ፲፬) የነቾህ ቀበሌ ፲፭) ሀገረማሪያም አቦ ቀበሌ ፲፮) አባ ቡኖ ቀበሌ ፲፯) የለጥ ቀበሌ ፲፰) ሰበሌጥ ቀበሌ ፲፱) ሶስት አባ ቀበሌ ፳) ሸረር ቀበሌ ፳፩) የናጉር ቀበሌ ፳፪) እንኮይ ቀበሌ ፳፫) ንብጌ ቀበሌ ፳፬) ደብረ ፅጌ ይህ ማሳሰቢያ ተቃዋሚ ድርጅቶንም የሚመለከት ሲሆን ከላይ በስም በተዘረዘሩት አካባቢዎች ላይ ምንም አይነት የምርጫ ቅስቀሳም ሆነ ምርጫ አይደረግም ስለሆነም:-  ፩ኛ) የአማራ ህዝብ ጠላት ከሆነው "ብልፅግና" ከሚባል ፀረ አማራ ድርጅትጋ በመሰለፍ በወረዳው የምርጫ ቅስቀሳ የምታደርጉ የጠላት ተወካዮች በመሆናችሁ የማያዳግም እርምጃ እንዳምንወስድ ለዚህም ተጠያቂዎቹ እናተው ራሳችሁን ከጠላትጋ የተጠጋችሁ እንደምትሆኑ እናሳውቃለን።  ፪ኛ) "ተቃዋሚ ድርጅት" በዚህ ወቅት የአማራ ህዝብ ለምርጫ ፖለቲካ ዝግጁ አይደለም ህዝባችን የተከፈተበትን ጦርነት እየመከተ እና ጠላትን ልክ እያገባ ባለበት በዚህ ከባድ ወቅት በምርጫ ሰበብ ፈተና ባትሆኑብን መልካም ነው። ሆኖም ግን በማን አለብኝነት ወይም በግዴለሽነት ተወካዮቻችሁን ልካችሁ የምርጫ ቅስቀሳ እንቅስቃሴዎችን ካደረጋችሁ ተወካዮቻችሁን በቁጥጥር ስር አውለን በእስር እንደምናቆይ ንብረትም እንደምወርስ እያሳወቅን በዚህም ሂደት ለምናወጣው ወጪ በተወካዮቻችሁ ላይ ለሚደርሰው ማንኛውም ጉዳት በሙሉ ተጠያቂዎች እንደምትሆኑ እናሳስባለን። አማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ አፋብን ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ ከሰም ኮር ኃይለማርያም ማሞ ክፍለጦር።