ch
Feedback
ፍኖተ- አማራ ሚዲያ (Finote- Amhara ) Midea

ፍኖተ- አማራ ሚዲያ (Finote- Amhara ) Midea

前往频道在 Telegram

የተመሠረተው የአማራን ሕዝብ ለማንቃት፣ ለማደራጀት እና ለማስተባበር ነው። የአማራ ሕዝብን ✅ ፖለቲካዊ ✅ ማህበራዊ ✅ ኢኮኖሚያዊ ታሪካዊ ጥያቄዎችን ለማሰማት እና የአማራን ሕዝብ በማንቃት ሰፊውን ሕዝብ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ይሰራል። ወደዱም ጠሉም የኃላ ታሪካችን በእኛ እጅ ይፃፋል። አማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ( አፋብን)

显示更多
3 279
订阅者
+3924 小时
+3057 天
+69830 天
帖子存档
✍️ እንኳን ለበዓለ ስቅለቱ በሰላም አደረሳችሁ ♦️ ከዳግማዊ ቴዎድሮስ ፭ኛ ኮር የተሰጠ መግለጫ    እንኳን ለ2018 ዓ.ም የጌታችን መድሃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስቅለት በዓል በሰላም አደረሳችሁ። ሞት የማይገባው ጌታ የድንግል ማርያም ልጅ ለህዝበ ክርስቲያን ነፃነትን ለመስጠት፤ አዳምም የታሰረበትን የኃጢያት ሰንሰለት ለመበጣጠስ ሲል በመስቀል ላይ ዋለ። ይህ ቀን በክርስትና እምነት ልዩ የሆነ በዓል ነዉ። እኛ ፋኖዎችም የህዝባችን ደስታ ደስታችን፤ የህዝባችን መከራ መከራችን ነውና በድጋሚ እንኳን አደረሰን አደረሳችሁ ። ♦️ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እራሱን ዝቅ አድርጎ በሰዉ እጅ ተሰቃየ ፣ታሰረ፣ ተገረፈ፣ ተሰቀለ፣ ህይወቱን ለሰዉ ልጅ ሲል ሰጠ ። የአማራ ፋኖም እራሱን ዝቅ አድርጎ ድንጋይ ተንተርሶ፣ ውርጭ ልሶ ብዙ መከራ እያሰላፈ አንዲት ህይወቱን ሳይሳሳ ለሚወደዉ ለታላቁ የአማራ ህዝብ እየሰጠ ይገኛል።ለዓለም ሕዝብ መከራ መቀበልን አምላካችን አሳይቶናልና እኛም ከእሱ በመማር መከራ እየተቀበልን፣ ለምንወደዉ የአማራ ህዝብ ህይወታችንንም በደስታ እየሰጠን እንገኛለን። ♦️እየሱስ ክርስቶስ በመስቀል ላይ የተሰቀለው ህዝብን ከወደቀበት ለማንሳት ሲል ነበር ። የአማራ ፋኖም ህዝባችን ያለአበሳው ከገባው መከራ ለማዳን ሲል ነፍጥ አንግቦ ጫካ በመውጣት ለአማራ ህዝብ አለኝታ እና ጠበቃ በመሆን እየታገለ ይገኛል። እየሱስ ክርስቶስ ተሰቅሎ እንዳልቀረው በትንሳዔ እንደተነሳው ሁሉ የአማራ ህዝብም ተሰቃይቶ የማይቀር፤ጌታ አምላካችን ሞትን ድል አድርጎ እንደተነሳው ሁሉ ህዝባችንም ድል አድርጎ  ትንሳኤችንን በቅርብ ቀን እንደሚሆን እናረጋግጣለን። ♦️የአማራ ፋኖ የአማራ ህዝብ  እምነቶች፣ ባህሎች፣ ትውፊቶች ጠበቃ ነውና ብዙ መከራ ችሎ ግፉ ሲበዛ እምቢ ያለውን የአማራ ሕዝብን በመያዝ የአብይን ወንበር እየነቀነቅነዉ እንገኛለን። ለህዝባችን እስከ መጨረሻዋ ሰዓት ድረስ በኩራት ፣ በፍፁም ፍቅር ፣በፍፁም ትህትና እንደምናገለግል፤ አገዛዙንም እንደምናስወግድ ስንገልጽ በልበ ሙሉነት ነው። ♦️በተጨማሪም ሁሉም አማራ እንዲሁም ሀገር ወዳድ ኢትዮጵያዊ  በዓሉን ስናከብር የክርስቶስን ምግባር ተላብሰን  ፣በመደጋገፍና በመረዳዳት ፣በመደማመጥና በፍቅር ፣በደስታ አቅመ ደካሞችን በማገዝ እንዲሁም በአገዛዙ የተፈናቀሉ ወገኖችንም ጭምር በማሰብ፤ በዋናነትም ልጆቻቸው የተሰዋባቸውን የፋኖ ቤተሰቦችንም በመጠየቅና በማገዝ ለአማራ ሕዝብ ሲሉ በየጫካው የቀሩት ልጆቻቸው አለመኖር እንዳይሰማቸውም በዓሉንም አብሮ በማክበር እንዲሆን ስንል በትህትና እንጠይቃለን ።                   መልካም በዓል ይሁንላችሁ ‼️                            ኅልውናችን በተባበረ ክንዳችን             አፋብን ጎንደር ጠቅላይ ግዛት በላይ እዝ                    ዳግማዊ ቴዎድሮስ ፭ኛ ኮር                           ሚያዝያ 02/2018 ዓ.ም

ዛሬ ቀን 2/8/2018 ዓ.ም የአማራ ፋኖ ብሄራዊ ንቅናቄ (አፋብን) በላይ ዕዝ የሜ/ጀነራል ውባንተ አባተ ኮር (፩ኛ ኮር)የጣና ገላውዲወስ ክፍለጦር ለብዙ ወራት ያሰለጠናቸውን ሰራዊት በደማቅ ሁኔታ አስመርቋል።     ጣና ገላውዲወስ ክፍለጦር እጅግ ተዋጊ ሀይል የተሰባሰበበት፣ ብዛት ያለው የሰው ሀይል ያለበት፣  በርካታ የቡድን እና የነፍስ ወከፍ የጦር መሳሪወችን የታጠቀ ፣ በበሳል እና በአማራ ብሄርተኝነት በማይደራደሩ መሪወች የሚመራ ፣ ከውድቀት ወደ ከፍታ የገሰገሰ በኮራችንም ውስጥ የምንተማመንበት ክፍለጦር ነው።    ከዚህ በፊት በክፍለጦሩ ሰልጥነው የተመረቁት ሰራዊቶች በርካታ ጠላትም ደምሠዋል። በተለይ የካቲት አንድ ቀን የተጀመረው መደበኛ ማጥቃት በደቡባዊ ጎንደር ክፍል ውስጥ የነበረውን ጠላትም ሙሉ በሙሉ በመደምሰስ ማርከው ታጥቀው እና አስታጥቀው ይገኛሉ።    ያልሰለጠነው ትውልድም ይህን በመረዳት መሰልጠን ፣ መደራጀት ፣ መሰባሰብ ፣ ፋኖ ሁኖ መገኘት እና በአማራ ሰማይ ስር ሁኖ መታገል አማራጭ የሌለው ግዴታ መሆኑንም ተገንዝበው ዛሬ በደማቅ ሁኔታ ስልጠናቸውን አጠናቀው መደበኛ ሰራዊት በመሆን ተመርቀዋል።    ዛሬ ጌታችን እየሱስ ክርስቶስ የተሰቀለበት የግፍ፣ የመከራ፣ የስቃይ፣ የግርፋት ቀን መሆኑ ለዛሬው ተመራቂ ለየት ያደርገዋል    ምክንኛት ያለው የፋኖ ትግል ዛሬ ይህን ሰራዊት ስናስመርቅ  ባርነቱን ፣ ድብደባውን፣ በደሉን በደንብ ተገንዝቦ የእውነት በአርብ ቀን ተመርቆ የእውነተኛ አርበኛ መሆኑ ነው።   ፋኖ አመኑ አለም አንተ!!!

#ፍቅሩ_ሙሉዬ የሚባል ወዶ ገብ #በቀቀን በሚዲያ ቀርበ ብልፅግና የፃፈለትን ተውኔት እየተወነ የአመራር ልጆች በወጭ አገር እየተሞላቀቁ እየኖሩ እያለ  ሲቀደድ  አየውት ሰማሁት። የየትኛው የአፋብን አመራር ቤተሰብ ነው ዉጭ ሀገር የሚኖር ❓ ከዚህ በታች ያሉትን አየወቃቸውም ልበል❓ የአፋ--ብን ሊቀመንበር አርበኛ ዘመነ ካሴ ቤተሰቦች። - አርበኛ ዘመነ ካሴ - አርበኛ ንብረቱ ካሴ - አርበኛ ገደፋው ካሴ - አርበኛ ኪሩቤል ዘመነ ካሴ ሌሎች በርካታ ቤተሰቡ በትግል ሜዳ ተገኝተው ዋጋ እየከፈሉ ነው። የአፋ----ብን ምክትል አዛዠ ለወታደራዊ አስተዳደር አርበኛ ዝናቡ ልንገረው ቤተሰቦች። - አርበኛ ልንገረው ደለለ :- ወላጅ አባት -  ፋኖ ዝናቡ ልንገረው ደለለ - ፋኖ ይታይህ ልንገረው ደለለ - ፋኖ ለጌታ ልንገረው ደለለ - ፋኖ ለሰሚ ልንገረው ደለለ - ዋስይሁን ደረጄ በላይ ( ሚያዚያ 15/2016 ዓ.ም የተ--ሰዋ) - አማኑኤል ደረጄ በላይ ( መስከረም 7/2017 ዓ.ም የተ---ሰዋ ) የአፋ---ብን ጎጠግ በላይ ዘለቀ ዕዝ የአባት አርበኞች ምክርቤት ፀሃፊ የሆነው ኮማንደር አረጋ አለባቸው ሶስት ወንድሞቹን ሁለት ልጆቹን እንዲሁም አንድ የወንድም ልጅ እና የእህቱን ልጅ ይዞ እየተ----ዋደቀ ይገኛል። እነሱም፦ - አርበኛ ማርየ አለባቸው  - አርበኛ ጌትነት አለባቸው - አርበኛ ፍቅሬ አለባቸው   - አርበኛ ክንድየ አረጋ አለባቸው - አርበኛ ጌታው አረጋ አለባቸው - የኮማንደር አረጋ አለባቸው የወንድም ልጅ አርበኛ አለሙ ፍቅሬ አለባቸው ( መጋቢት 21/2018 ዓ.ም የ--ተሰዋ ) የአፋ---ብን ጎጠግ በላይ ዘለቀ ዕዝ የአባት አርበኞች ምክርቤት ሰብሳቢ አርበኛ መሳፍንት ተስፉ ቤተሰቦች! - ፋኖ ገብሬ መሳፍንት ተስፉ ( በክብር የተ---ሰዋ) - ፋኖ ጌትነት መሳፍንት ተስፉ ( ጥቅምት 29/2018 ዓ.ም የተ---ሰዋ) - ፋኖ ሰላም መሳፍንት ተስፉ - ፋኖ መከተ ተስፉን ጨምሮ ከ30 በላይ ቤተሰቦቹ በነቂስ እየተሳተፉ ነው። የፋኖው አባት የዋዋ ጎቤ መልኬ ቤተሰቦች። - አርበኛ ፋሲል ጎቤ - አርበኛ  እሱባለው ጎቤ - አርበኛ አንተነህ ጎቤ - አርበኛ ስጦታው መልኬ ሌሎች ያልጠቀስኳቸው የአጎትና የአክስት ልጆች እንዳሉ ልብ ይሏል። የዝምተኛው መብረቅ የሲሳይ አሸብር ወንድሞች! - አርበኛ እሸቴ አሸብር አርበኛ ደጀን አሸብር( በክብር ተሰው---ቷል) የአፋ---ብን ምክትል ወታደራዊ አዛዠ ዋርካው ምሬ ወዳጆ ልጅ ንጉሡ ምሬ ወዳጆ በትግል ሜዳ ነው። ከአንድ ቤተሰብ ለህልውና ትግላችን በክብር የተ--ሰው ፣ የቆ---ሰለ ፣ አሁንም እየተጋሉ ያሉ ያልጠቀስኳቸው እጅግ እጅግ በርካታ ወንድሞች አለ። ከከፍተኛ አመራር እስከታች ድረስ ውድ ዋጋ እየተከፈለልን ነው። ክብር ለሰማእታት!🙏🙏🙏

እንኳን ለጌታችንና ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የስቅለት በዓል በሰላም አደረሳችሁ። ____ የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ (አፋብን) የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት ____ የስቅለት በዓል የሚያስተምረን ጽናትና ለዓላማ መሞት ያለውን ትልቅ ትርጉም ነው።  ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስለ እውነትና ስለ ሰው ልጆች ፍቅር ሲል እስከ ቀራንዮ እንደተጓዘ ሁሉ፣ የአማራን ህዝብ ክብርና ህልውና ለማስጠበቅ የተጀመረው ጉዞ የተፀነሰው በመንገዳችን በድንገት በተቀላቀሉ እና እየወረዱ ባሉት ይሁዳዎች ሳይሆን ውድ ህይወታቸውን ለመክፈል በማይሰስቱ በቁርጠኛ ልጆቹ ልብ ያለ እስከ ቀራንዮ ለመጓዝ የተቆረጠ የማያወላውል ጉዞ ነው። ስቃይና መከራ ለክብር፣ ሞት ደግሞ ለትንሳኤ መንገድ እንደሆኑ ሁሉ፤ ዛሬ የምናልፍበት መከራና የምንከፍለው መሥዋዕትነትም ለታላቅ ድልና ለሕዝባችን ሰላም መሠረት መሆኑ አይቀሬ መሆኑን በመተማን ነው። የአፋብን አመራሮችና መላው የሰራዊት አባላትም ይህ ጉዞ የሕዝባችንን ነጻነትና ደህንነት እስኪያረጋግጥ ድረስ በፅናት እና በሙሉ ልብነት ለማስቀጠል በዚህ ለመላው የሰው ልጆች ሲባል ዋጋ በተከፈለበት ቀን በድጋሜ ቃል እንገባለን። በዓሉን ስናከብር ለአማራ ሕዝብ ህልውና ሲሉ ውድ ሕይወታቸውን የገበሩ ጀግኖቻችንን እና በየበረሃው ደማቸውን ያፈሰሱ ልጆቻችንን ቤተሰቦች በመጠየቅና በመደገፍ፣ በማንነታቸው ምክንያት ከቀያቸው ተፈናቅለው በችግርና በስደት የሚገኙ ወገኖቻችንን በማሰብ፣  "አማራነት ወንጀል" ተደርጎባቸውና በፖለቲካ አመለካከታቸው ምክንያት በየእስር ቤቱ የሚማቅቁ የሕዝብ ልጆችንና ቤተሰቦቻቸውን በማስታወስ፣ ድምፅ በመሆንና በመጠየቅ ከጎናቸው መሆናችንን በማሳየት እንዲሆን ጥሪ እናቀርባለን። በድጋሜ እንኳን ለጌታችን ለመድኃኒታችን እየሱስ ክርስቶስ የስቅለት በዓል አደረሳችሁ! ሚያዝያ ፪ ቀን ፪፼፩፰ ዓ.ም የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ (አፋብን)

የ206ኛ ኮር አዳኝ ቡድን በደብረ ማርቆስ ከተማ ከሌሊቱ 7:45 በፈፀሙት የቦምብ ጥቃት 3 ፖሊሶችና 4 የሚኒሻ አባላት ህይወታቸውን አጠዋል። ሚያዝያ 1/2018 ዓ.ም ===================
የ206ኛ ኮር አዳኝ ቡድን በደብረ ማርቆስ ከተማ ከሌሊቱ 7:45 በፈፀሙት የቦምብ ጥቃት 3 ፖሊሶችና 4 የሚኒሻ አባላት ህይወታቸውን አጠዋል። ሚያዝያ 1/2018 ዓ.ም ======================================= የ206ኛ ኮር አነፋናፊ አዳኝ ቡድን በደብረ ማርቆስ ከተማ ከሌሊቱ 7:45 በፈፀሙት የቦምብ ጥቃት በ10 ሚኒሻና ፖሊሶች ላይ ከፍተኛ ጉዳት ደርሷል። ምሽቱን ተገን አድርገው በአብማ ክ/ከታማ ልዩ ቦታው እነገም አካባቢ ለቅኝት በሚንቀሳቀሱ አንድ ጋንታ የጠላት ኃይል ላይ ጥቃቱ ያነጣጠረ ሲሆን 3 ፖሊሶችና 4 ሚኒሻዎች ሲሞቱ 1 ፖሊስና 2 የሚኒሻ አባላት እንዲሁ ከባድ ቁስለኛ መሆናቸው ተረጋግጧል። የ206ኛ ኮር አዳኝ ቡድን በደብረ ማርቆስ ከተማ እያደረሱት ባለው የቦምብ ጥቃት አደጋ ላይ የወደቁ የአድማ ብተና አባላት እንዲሁ በ24 ሰዓታት ውስጥ 15  የሚሆኑት 206ኛ ኮር 14ኛ ክ/ጦር ጅበላ ሙተራ ሻለቃ መቀላቀላቸው የሚታወስ ነው። አዲስ ትውልድ! አዲስ አስተሳሰብ ! አዲስ ተስፋ! የአፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 206ኛ ኮር ህዝብ ግንኙነት

አፋብን | ቴዎድሮስ ዕዝ ____፩ ምቱ ሲጠነክር  ጠላት በአቅጣጫው  ወደፋኖ እየጎረፈ ነው። የአማራ ባህሉ መሳሪያ ታጥቆ ጠላትን ማጥቃት እንጅ ከጠላት ጋር ማበር አይደለም።  ይህ የተገለጠላቸው የጠላትን መሳሪያ በመያዝ ፋኖን እየተቀላቀሉ ነው። ዛሬም በደብረ ማርቆስ ከተማ ለ45 ቀን የፖራ ኮማንዶ ስልጠና ወስዳችኋል የተባሉ ሚሊሻዎች  አራት የአገዛዙ  አባላት ከእነማይ ወረዳ ወይራ ቀበሌ በመውጣት 64ኛ ክ/ጦር ተቀላቅለዋል። 1ኛ.ሚሊሻ ደስታው መንበሩ 2ኛ.ሚሊሻ ውዱ ውል 3ኛ.ሚሊሻ ተጎዳ ሰውነት 4ኛ.የቻለ ፍሬው የተባሉ ሙሉ ትጥቃውን ይዘው ተቀላቅለዋል። _፪ የ206ኛ ኮር አዳኝ ቡድን በደብረ ማርቆስ ከተማ ከሌሊቱ 7:45 በፈፀሙት የቦምብ ጥቃት 3 ፖሊሶችና 4 የሚኒሻ አባላት ህይወታቸውን አጠዋል። የ206ኛ ኮር አነፋናፊ አዳኝ ቡድን በደብረ ማርቆስ ከተማ ከሌሊቱ 7:45 በፈፀሙት የቦምብ ጥቃት በ10 ሚኒሻና ፖሊሶች ላይ ከፍተኛ ጉዳት ደርሷል። ልዩ ስሙ አባ ብዙነህ ጉርድ ተብሎ በሚጠራዉ ዘራብሩክ አካቢ ከከተማ ወደ እንደገም ለቅኝት ሲንቀሳቀስ በነረ የአብማ ክፈለ ከተማ ሰላም አስከባሪ ሚሊሻ ፓሊስ ላይ ባደረግነዉ የደፈጣ የቦምብ ጥቃት  3 ፖሊሶችና 4 ሚኒሻዎች ሲሞቱ 1 ፖሊስና 2 የሚኒሻ አባላት እንዲሁ ከባድ ቁስለኛ መሆናቸው ተረጋግጧል ። በዚህ ጥቃት ጌታቸው የሚባል መሪ መደምሰሱን አረጋግጠናል። ''ከመካከላችን ያለ ሰው ነው ቦምብ የጣለብን እንጂ ፋኖ አይደለም" ብለው የጠረጠሩትን በማሰራቸው ምክንያት ካምፕ ላይ ከፍተኛ ጥርጥርና ረብሻ ተፈጥሯል። አዲስ ትውልድ፣ አዲስ አስተሳሰብ ፣አዲስ ተስፋ!         ክፋት ለማንም ፣በጎነት ለሁሉም! አፋብን| ቴወድሮስ ዕዝ ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ            ሚያዚያ 01/2018 ዓ.ም

አፋብን ምን ላይ ነው? የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ሲመሠረት፣ ሕዝቡ የተጋረጠበትን የህልውና አደጋ የሚቀለብስለት ጠንካራ የጋራ ቤት አገኘሁ ብሎ በታላቅ ተስፋ ደጀንነቱን አረጋግጦ ነበር። ይህ የሕዝብ አደራ እጅግ ክቡርና በጥንቃቄ ሊያዝ የሚገባው ዋጋ ያለው ስጦታ በመሆኑ፣ ንቅናቄው ይህንን ተስፋ ጠብቆ የማስቀጠል ታሪካዊ ኃላፊነት አለበት። ሆኖም አሁን አሁን የሚስተዋሉ አንዳንድ የአመራር መዘግየቶችና የውስጥ መሻኮቶች፣ ትግሉ ከተመሠረተበት ታላቅ ዓላማ እንዳይዘናጋ ስጋት የሚፈጥሩ ናቸው። ባለፉት ወራት ወጥ የሆነ ዕዝ ከመገንባትና ብቃት ያላቸውን መሪዎች በጋራ ስምምነት ከመሰየም ይልቅ፣ በአንዳንድ አካባቢዎች የሚታዩት ልዩነቶች ጊዜን በአግባቡ ካለመጠቀም ጋር ተዳምረው የሕዝቡን ሞራል ሊፈትኑ ይችላሉ። የህልውና ትግል ስኬት የሚለካው በመቻቻልና በጋራ ዓላማ ላይ በማተኮር እንጂ፣ በውስጣዊ የስልጣን ፍላጎቶች ላይ ጊዜ በማጥፋት ባለመሆኑ አመራሩ ትኩረቱን ወደ ዋናው ግብ ሊመልስ ይገባል። ከአለም አቀፍ የትጥቅ ትግል ታሪክ እንደምንማረው፣ ማንኛውንም ንቅናቄ ክፉኛ የሚፈትነው የጠላት የጦር መሣሪያ ብልጫ ሳይሆን የውስጥ መከፋፈል ነው። በደቡብ ሱዳን የነበረው የሱዳን ሕዝብ ነፃነት ንቅናቄ (SPLM) ንቅናቄ በውስጥ ሽኩቻ የተነሳ የከፈለውን አላስፈላጊ መስዋዕትነት መለስ ብሎ ማየት፣ ከስህተት እንድንማርና ራሳችንን እንድናርም ይረዳናል። እነዚህ የውስጥ ልዩነቶች በአስቸኳይ በውይይትና በመግባባት ካልተፈቱ፣ ንቅናቄው የህዝብን አመኔታ ሊያጣ፣ ለስርዓቱ የስለላ መዋቅር ሰርጎ መግባት በር ሊከፍት፣ እንዲሁም ትግሉን ወደተበታተነ የጦር አበጋዝነት አቅጣጫ ሊወስደው ይችላል የሚሉ ስጋቶችን ቀድሞ መዝጋት የብልህ መሪዎች ቀዳሚ ተግባር ሊሆን ይገባል። በተለይም አሁን ላይ ለፋኖ ወታደራዊ እንቅስቃሴ የተፈጥሮ ጋሻ የሚሆነው ክረምት አፋፍ ላይ እንገኛለን። ይህንን ወርቃማ ጊዜ በአግባቡ ለመጠቀም፣ ጠንካራና የተባበረ ስትራቴጂካዊ ዕዝ መገንባት እጅግ ወሳኝ ነው። መሪነት ትልቅ ኃላፊነትን መሸከምና ራስን ዝቅ አድርጎ ለሕዝብ ዓላማ መገዛትን የሚጠይቅ የክብር ቦታ እንጂ፣ የዝና መሻሚያ መድረክ አይደለም። ስለሆነም፣ የንቅናቄው አመራሮች ይህንን ከባድ አደራ በማሰብ፣ ጥቃቅን ልዩነቶችን ወደ ጎን በመተውና የሕዝቡን የህልውና ጥያቄ በማስቀደም አንድነታቸውን ሊያጠናክሩ ይገባል:: የትግሉ ዋነኛ ባለቤትና ደጀን የሆነው ሕዝብም፣ ከመቼውም ጊዜ በላይ አንድነቱን አጠናክሮ ትግሉን መደገፍና አመራሩንም ወደ ትክክለኛው መስመር እንዲመጣ በጥበብ በጎ ተፅዕኖ መፍጠር አለበት። ክረምቱ ከመግባቱ በፊት የትግሉን መሰረት አጠንክሮ የሕዝብን ተስፋ ማለምለም ጊዜ የማይሰጠው የቤት ሥራ ነው፤ ትግሉ የጋራ ነው፣ በአንድነት ከተቆመ ደግሞ የማይታለፍ ፈተና የለም! #የአማራ_ፋኖ #ህዝባዊ_ትግል #አንድነት_ለህልውና

በደብረ ማርቆስ ከተማ ለ45 ቀን የፖራ ኮማንዶ ስልጠና የወሰዱ አራት የአገዛዙ ፖራ ኮማንዶ አባላት ከእነማይ ወረዳ ወይራ ቀበሌ በመውጣት 64ኛ ክ/ጦር ተቀላቀሉ!! 64ኛ ክ/ጦር ሚያዚያ 01/2018
+2
በደብረ ማርቆስ ከተማ ለ45 ቀን የፖራ ኮማንዶ ስልጠና የወሰዱ አራት የአገዛዙ ፖራ ኮማንዶ አባላት ከእነማይ ወረዳ ወይራ ቀበሌ በመውጣት 64ኛ ክ/ጦር ተቀላቀሉ!!      64ኛ ክ/ጦር ሚያዚያ 01/2018 ዓ.ም 1ኛ.ሚሊሻ ደስታው መንበሩ 2ኛ.ሚሊሻ ውዱ ውል 3ኛ.ሚሊሻ ተጎዳ ሰውነት 4ኛ.የቻለ ፍሬው ፓራ ኮማዶ ሲሆኑ በደብረ ማርቆስ 45 ቀን የፖራ ኮማንዶ ስልጠና ወስደው በእነማይ ወረዳ የሚገኘው ቅጥርኛ የሚሊሻ ሰራዊት አባል ሲሆኑ በአገዛዙ አሰራሮች ተስፋ በመቁረጥ አፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 201ኛ ኮር 64ኛ ክፍለ ጦር ከእነ ሙሉ ትጥቃቸው ተቀላቅለዋል።         ሚያዚያ 01/2018 ዓ.ም አፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 201ኛ ኮር 64ኛ ክ/ጦር ሕዝብ ግንኙነት

ነፃ በወጡ ቀጠናወች በቢቡኝ ወረዳ ወይንውሀ ከተማ ላይ ህዝባዊ ውይይቶች ተካሄደ ➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺ ሚያዚያ 01/2018 ዓ.ም በ201ኛ ኮር 54ኛ ክፍለ ጦር በሚያስተዳድራቸው በቅርቡ ነፃ
+8
ነፃ በወጡ ቀጠናወች በቢቡኝ ወረዳ ወይንውሀ ከተማ ላይ ህዝባዊ ውይይቶች ተካሄደ ➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺ ሚያዚያ 01/2018 ዓ.ም በ201ኛ ኮር 54ኛ ክፍለ ጦር በሚያስተዳድራቸው በቅርቡ ነፃ በወጡ ቀጠናወች የኮሩ አመራሮች እና የ54ኛ ክፍለ ጦር የወረዳው ጊዜያዊ መንግስት አመራሮች ህዝባዊ ውይይቶች በማካሄድ የህዝቡን አለኝታነት በሞራል የመገንባት ስራ ተሰርቷል። የቴወድሮስ ዕዝ 201ኛ ኮር ህዝብ ግንኙነት

የአብይ አህመድ ዘራፊ እና ጨፍጫፊ ሰራዊት በእነማይ ወረዳ ወይራ ቀበሌ ውድመት ፈፅሟል። 64ኛ ክ/ጦር ሚያዚያ 01/2018 ዓ.ም የአብይ አህመድ ጨፍጫፊ እና አውዳሚ ሰራዊት በእነማይ ወረዳ ወይራ ቀበሌ ለ16 ወራት መሽጎ የነበረበትን ካንፕ መጋቢት 28/2018 ዓ.ም በ64ኛ ክ/ጦር ወታደራዊ እንቅስቃሴ ስጋት በመግባት ካንፑን በመልቀቅ ብቸና ከተማ የገባ ሲሆን በዚህ ቅፅበት የፋኖ ኃይሎች ጠላት ይጠቀምበት የነበረውን ካንፕ በማሰስ በወይራ ቀበሌ በርካታ ውድመቶች የአገዛዙ ሰራዊት መፈፀሙን በማስረጃ ይዘው ወጥተዋል። የአማራን ህዝብ ከምድር ገፅ አጠፋለሁ ብሎ ጦርነት የከፈተው አማራ ጠሉ የብልጽግና ቅጥረኛ ሰራዊት በወይራ ቀበሌ ለ16 ወራት በቆየበት ወቅት በርካታ ውድመቶችን እና ጥፋቶችን መፈፀሙን በማስረጃ አርጋግጠዋል። አገዛዙ በወይራ ቀበሌ የእርሻ ሰብል መሬቶችን ምሽግ እና የጃምላ መቀበሪያ አድርጓል። በወይራ ቀበሌ የሚገኝ የህብረተሰብ ክፍል በአገዛዙ ኃይሎች ከፍተኛ ስቃይ እና መከራ ተዳረጓል። በቀበሌ የሚገኙ ት/ቤቶች ውስጥ የሚገኙ መገልገያ ማቴሪያሎች ወንበሮችን፣ ጠረቤዛዎችን እና መፃፍትን ጨምሮ ሙሉ የት/ት መገልገያ እቃዎች ተዘረፈዋል ወድመዋል። ትውልዱ ትምህርት ይቀስምበት የነበረው የት/ት ተቋማት በሙሉ ወድመዋል። በወይራ ቀበሌ የሚገኙ የህብረተሰብ ክፍል መኗሪያ ቤታቸው የሚጠቀሙባቸው ቁሳቁሶች በሙሉ ወድመዋል ተዘርፈዋል። ህፃናት፣ እናቶችን፣ በአገዛዙ ሰራዊት ተገደው ተደፍረዋል። ወጣቶች፣ አዛውንቶች፣ የቀበሌ ኖሪዎች በአገዛዙ ሰራዊት በግፍ ተደብድበው ተገድለዋል። በእነማይ ወረዳ ወይራ ቀበሌ የት/ት ተቋማትን ካንፕ አድርጎ ይገኝ የነበረው የአገዛዙ ሰራዊት በርካታ ንብርቶችን ማውደሙን እና በቀበሌው ይኖሩ የነበሩ የማህበረሰብ ክፍል በአገዛዙ ዘራፊ ኃይሎች ሀብት ንብረታቸውን ማዘዝ እንደማይችሉ፣ አገዛዙ ሀብት ንብረታቸውን በየቀኑ እንደሚዘረፍቸው እንደሚታሰሩ እንዲሁም የት/ት ተቋማት መውደማቸውን በቦታው ለተገኘ የእነማይ ወረዳ ጊ/መንግስት የሚዲያ ክፍል ኃላፊ በአካል አስረድተዋል። ይህ ከታች የምትመለከቱት ቪዲዩ በእነማይ ወረዳ ወይራ ቀበሌ አነገዛዙ ካንፕ አድርጎ የሚጠቀምበት ት/ቤት እና የአርሶ አደሮች የቤት ዕቃ ሲሆን በአምባ ገነኑ አብይ አህመድ አገዛዙ ሰራዊት የት/ት ተቋሙ ውስጥ የሚገኙ መገልገያ ቁሳቁሶች በሙሉ መውደማቸውን በቪዲዩው ዳሰሳ እውነቱን ህዝባችን እና የትግሉ ደጋፊ እውቅና እንዲኖርው እናቀረባለን። ሚያዚያ 01/2018 ዓ.ም የአፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 201ኛ ኮር 64ኛ ክፍለ ጦር ሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ

ሚያዚያ 1/2018 ዓ.ም የህልውና ትግሉ ችቦ የተለኮሰበት ሶስተኛ አመት መታሰቢያ! ሚያዚያ 1/2015 ዓ.ም የምስራቅ አማራ ፋኖ አብሪ ኮከብ አርበኛ ሻምበል ዳንኤል አለሙ ስለ አማራ ህዝብ ህልዉና መስዋዕትነትን የተቀበለበት ዕለት ነው! አርበኛ ሻምበል ዳንኤል አለሙ የአማራን ህዝብ ሁለንተናዊ የህልዉና አደጋ ለመቀልበስና የአማራን ህዝብ እንደ ህዝብ "ሕልው" ለማድረግ ዉድ ህይወቱን የሰዋበት ይህንን ቅዱስ የህልዉና ትግል "ሀ" ብሎ ያስጀመረበትና ችቦ የለኮሰበት ቀን ነው:: ገና በለጋ እድሜው የቀድሞዉን የሃገር መከላከያ ሰራዊት በመቀላቀል ትግል የጀመረው አርበኛ ሻምበል ዳንኤል አለሙ ከእግረኛ እስከ ሻምበልነት ማዕረግ ድረስ እንዲሁም የቀድሞው አግዓዚ ኮማንዶ አባል በመሆን ከሃገር ዉስጥ እስከ ዉጭ አገር ሰላም ማስከበር ተልዕኮ ድረስ ወጣትነቱን ለሃገሩ ገብሯል:: አርበኛ ሻምበል ዳንኤል አለሙ ከሃገር መከላከያ ሰራዊት ባጋጠመው ከባድ ቁስል ምክንያት በጡረታ ያገለለ ሲሆን ከ 2010 ዓ.ም ህዝባዊ እምቢተኝነት ቡሃላ ወጣቶችን በስፖርት በአካል ብቃትና በስነ ልቦና የማንቃት ስራ እየሰራ በኋላም ከነ ዋርካው ምሬ ወዳጆ ጋር የራያ ፋኖን በመመስረትና በመቀላቀል ፀረ ወያኔ ትግሉን ተቀላቅሎ ሁሉንም ተጋድሎዎች በመሪነትና በአሰልጣኝነት በድል ተወጥቷል:: የቀድሞው ምስራቅ አማራ ፋኖ ስልጠና መምሪያን እየመራ በመካነሰላም በደሴ በሃይቅ በወልድያ በቆቦና በራያ አላማጣ በርካታ ታጋዮችን ያሰለጠነና ያፈራ ሲሆን የአሁኑን የአማራ ህዝብ የህልዉና ትግል በሰራዊትና በመሪነት ላይ ያሉ በርካታ ጀግኖችን አፍርቷል:: በርካታ ጀግኖችን እያሰለጠነና እያስታጠቀ መሆኑን ያየው አገዛዙም በጥላቻ አይን ያየው ጀመረ:: የሰሜኑን ጦርነት እነ አብይ አህመድና በድኑ ብአዴን በፕሪቶሪያው የድራማ ስምምነት ከቋጩት በኋላ የአማራ ፋኖን ህግ ማስከበር በሚል ሽፋን ትጥቅ ለማስፈታት በፌደራልና በክልል ደረጃ መከላከያ በማዝመት ዘመቻ በጀመሩበት ጊዜ ግጭቶች መጀመራቸው ይታወቃል:: በዚህም በተለያዩ ጊዜያት የምስራቅ አማራ ፋኖ ሰራዊትና አመራሮችን ቀዳሚ ኢላማ ያደረገ እንቅስቃሴ ተጠናክሮ ቀጠለ:: አርበኛ ሻምበል ዳንኤል አለሙ ከነዚህ የፖለቲካ ጥያቄ ካነገቡ ግጭቶች ጋር ተያይዞ የብርሃኑ ጁላ መከላከያ ሰራዊት ላይ ይመለከት በነበረው ፀረ-ህዝብ ተግባርና ነዉር እጅግ ይበሳጭና ያዝን ስለነበር በአንድ ከአብይ አህመድ ጀኔራሎች ጋር ቆቦ ከተማ ሁለገብ አዳራሽ በተደረገ ስብሰባ የህዝብ ናችሁ ወይስ የብልፅግና? በሚል ይጠይቃቸዋል:: ያ ከራሱ ህዝብ አልፎ ሰላም ማስከበር ጎረቤት አገር ሄዶ ረሽኑን ለህዝብ ሰጥቶ ቅጠል በልቶ የሚያድር ሰራዊት የት ገባ? ሲል በመጠየቅ እስከ ሰላም ማስከበር በደረሰ ተልዕኮው የነበረዉን ህዝባዊነት በመጥቀስ የግፈኞች ዙፋን ጠባቂ መሆናቸዉንና ነውራቸዉን ነገራቸው:: አይቀሬዉን ጦርነት የተገነዘቡትና የተረዱት የአማራ ህዝብ የቁርጥ ቀን ልጆች ከወሎ ምስራቅ አማራ ፋኖ ከሸዋ ከጎጃምና ከጎንደር ፋኖዎች ጋር በመሆን ጎንደር ሱዳን ጠረፍ የአማራ ፋኖ አንድነት ምክር ቤትን በመመስረት አርበኛ ሰፈር መለሰን ዋና አዛዥ እና ዋርካው ምሬ ወዳጆን ምክትል አዛዥ አድርጎ በመምረጥ እንቅስቃሴ ጀመረ:: ምስራቅ አማራ ፋኖ አጠቃላይ የትግል ጉዞዉን የሚዘክር ታላቅ የተሃድሶ ዝግጅት የምክር ቤቱ ዋና አዛዥ አርበኛ ሰፈር መለሰ እንዲሁም ከፍተኛ የመከላከያ፣ የልዩ ሃይል፣ የብልፅግና አመራሮች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ እና የሃገር ሽማግሌዎች እንዲሁም መላ ሰራዊቱና ህዝብ በተገኙበት በደማቅ ሁኔታ አከበረ:: በዝግጅቱም ምስራቅ አማራ ፋኖ የአማራ ህዝብ በክልሉና በተለይ ከክልሉ ዉጭ እየደረሰበት ያለዉን ግፍና ጭፍጨፋ በማንሳትና በማስታወስ የአማራ ህዝብ የህልዉና አደጋ ተጋርጦበታል "ትግል ይቀጥላል" የሚል መልዕክት ለታዳሚው ለሰራዊቱና በዉስጥም በዉጭም ላለው መላው የአማራ ህዝብ በህዝብ ግንኙነቱ አርበኛ አበበ ፈንታው በኩል መልዕክት አስተላለፈ:: ይህንን ተከትሎም ከተሃድሶ ቡሃላ ትጥቅ ያስረክቡናል ይበተናሉ ስንል እንዴት "ትግል ይቀጥላል" ይላሉ በሚል የአገዛዙ ሹማምንት ከፍተኛ ንዴትና ብስጭት ብሎም ድንጋጤ ዉስጥ ገቡ:: ይህንን ተከትሎም አገዛዙ የምስራቅ አማራ ፋኖ ቁስለኞችን ሳይቀር ሰራዊቱን ባገኘበት ምቹ አጋጣሚ ሁሉ መረሸን ጀመረ:: የለየለት ግጭትም ተጀመረ:: ጥቃት የማይወደው አርበኛ ሻምበል ዳንኤል አለሙም ሰራዊቱን በተጠንቀቅ እንዲቆምና ለሚመጣው ሁሉ ነገር ተመጣጣኝ አፀፋ እንዲሰጥ ድርጅቱና መሪው ዋርካው ምሬ ወዳጆ ያወረደዉን መመሪያ በመቀበል በአንድ ወቅት ምስራቅ አማራ ፋኖ ካምፕ ድረስ ከነ አጃቢዎቹ በፓትሮል የመጣን ኮሎኔል ከመኪናው ወርዶ እስኪፈረጥጥ ድረስ ቆፍጠን ያለ እርምጃዉን ጀመረ:: ምስራቅ አማራ ፋኖም ሰራዊቱን በምዕራብ በኩል ከራያ ቆቦ ጮቢ በር እስከ በላጎ እንዲሁም ወልድያ ዙሪያ ሳንቃና መቻሬ እንዲሁም ሙጃ ድረስ ገዥ መሬቶች ላይ በማስፈር ለአይቀሬው ፍልሚያ ተዘጋጀ:: በበርካታ አካባቢዎች ከነበረው ግጭት ጋር ተያይዞ የነበረዉን ከፍተኛ ዉጥረትና የአማራ ልዩ ሃይል በበድኑ ብአዴን እና በነ አብይ አህመድ ሴራ መፍረሱን ተከትሎ ሚያዚያ 1/2015 አ.ም ረፋድ ላይ ቆቦ ከተማ በተጀመረ ከባድ ዉጊያ የአሁኑን የአማራ ህዝብ የህልዉና ትግል ጅማሮ ችቦ ለኩሶ አርበኛ ሻምበል ዳንኤል አለሙ መስዋዕትነት ተቀበለ:: የህልዉና ተጋድሎዉም ሸዋ በነበሩ የምስራቅ አማራ ፋኖ አሃዶችና የሸዋ ፋኖ አናብስቶች ተቀጣጥሎ ዛሬ በመላው አማራ የደረሰበት ደረጃ ደረሰ:: አርበኛ ሻምበል ዳንኤል አለሙ ስለ አማራ ህዝብ ህልዉና ቀይ መስመር ያለፈዉን በምድርም ይሁን በሰማይ ዘመኑ ያፈራዉን ጦር መሳሪያ እስከ አፍንጫው የታጠቀዉን ጨፍጫፊና ግፈኛ ፋሽስታዊ ስርዓት እስከ መጨረሻው ህቅታ ተናንቆ በጀግንነት ተሰዉቶ ችቦ ለኩሶና አስጀምሮ ይህንን የአማራ ህዝብ ቅዱስ የህልዉና ትግል ለዛሬ ካበቁ ጀግኖች መካከል ግንባር ቀደም ሆኖ አልፏል:: መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል! የተሰዋህለትን አላማ ከግብ እናደርሳለን! ክብር ለትግሉ ሰማዕታት! አፋብን በወሎ ቤተ-አማራ ምኒልክ ዕዝ ሚያዚያ 1/2018 ዓ.ም