ch
Feedback

不要被骗子欺骗!Telemetrio 会找到并标记这些频道 👉 如果想查看标记,请订阅 👈

ፍኖተ- አማራ ሚዲያ (Finote- Amhara ) Midea

ፍኖተ- አማራ ሚዲያ (Finote- Amhara ) Midea

前往频道在 Telegram

የተመሠረተው የአማራን ሕዝብ ለማንቃት፣ ለማደራጀት እና ለማስተባበር ነው። የአማራ ሕዝብን ✅ ፖለቲካዊ ✅ ማህበራዊ ✅ ኢኮኖሚያዊ ታሪካዊ ጥያቄዎችን ለማሰማት እና የአማራን ሕዝብ በማንቃት ሰፊውን ሕዝብ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ይሰራል። ወደዱም ጠሉም የኃላ ታሪካችን በእኛ እጅ ይፃፋል። አማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ( አፋብን)

显示更多
4 039
订阅者
+6824 小时
+3957 天
+1 39230 天
帖子存档
ትኩረታችን ዋናው ጠላታችን ላይ ብቻ ይሁን!! ዘላለማዊ ባርነትን በመለማመድ የህዝባችንን እጣ ፋንታ ለከፍተኛ ብሔራዊ የህልውና አደጋ የዳረገን የባንዳ ምልክቱ የአማራ ብልፅግና ዛሬም እንደ ወትሮው አድስ ማደናገሪያ ይዞ መጥቷል!! የህልውና ትግላችን ዋና አጀንዳ የአማራን ህዝብ ህልውና ማረጋገጥ እንጅ በየሰፈሩ ሃይል ለመበተንና ከወጣንበት ዓላማ በተፃረረ ሁናቴ ህዝብን እያደናገሩ የአማራ ክልልን የቀውስ ቀጠና ማድረግ ተቀባይነት የለውም!! አስከፊውን ፀረ -ህዝብ አገዛዝ በማስወገድ አድስ ስርዓት ለማንበር የጀመርነው ትግል ጠልፎ ለመጣል የሚደረገው ያልተገባ ትርክት መፍጠር ይበቃል!! ዋናው ጠላታችን እያደረገ ያለውን አማራን ከፋፍሎ እና አደናግሮ የአማራ ፋኖ ትግልን መጥለፍ አይቻልም!! አፋብን የሚመራበት የፓለቲካ ፕሮግራም እና የትግል መስመር የብልፅግናውን አገዛዝ በመገርሰስ በምትኩ አድስ ስርዓት ለመትከል እንጅ በየሰፈሩ እና በየግዛቱ ጠላት በሚሰራቸው አሉታዊ ፕሮፖጋንዳ የሚቀለበስ ትግል የለንም!! ስለሆነም ድርጅታችን አፋብን ትኩረቱን ወደ ደቡብ ግንባር በማድረግ የአገዛዙን እስትንፋስ ለመቁረጥ የጀመረውን ዘመቻ አጠናክሮ ይቀጥላል!! ከዚህ ባለፈ የቀጠናው ቀውስ ጠማቂ የአብይ አህመድ መንግስት ከሰሜን ሃይሎች ጋር የጀመረውን አድስ ውጊያ ምክንያት በማድረግ የአማራን ህዝብ እያደናገሩ መቀጠል ጊዜው አልፏል!! የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ እንደ ድርጅት ሁለንተናዊ ትኩረቱን የጠላት ዋና የስበት ማዕከል የሆነውን የደቡብ ግንባር ዘመቻ አጠናክሮ በመቀጠል ፀረ ህዝብ አገዛዙን ላይመለስ መቅበር እንጅ በሀሰት ትርክት እና በጥቂት ጥቁር አማራዎች ተሳትፎ የሚመለስም የሚቀለበስም የህዝብ ትግል የለም!! ግፋ በለው!! ዝንታለም አማራ ወይራው አማራ

ከሳንጃ ውግ እስከ ክላሽ ጨበጣ ውጊያና ቦምብ ውርወራ የደረሰው ከባዱ ትንቅንቅና የተሰበረው የጠላት ምሽግ‼️ በምስራቅ ዐምሓራ ቀጠና በተሁለ ድሬ ወረዳ ከሐይቅ ከተማ በቅርብ ርቀት ልዩ ስሙ ቆሎ ባቄላ ተብሎ በሚጠራው አከባቢ ላይ የሚገኘውና ከቦታ አቀማመጡ ጋር ተዳምሮ በመዘመናዊ መንገድ ተሰርቶ የነበረው የአገዛዙ ወታደራዊ ምሽግ በፋኖ ቦምብ ድርምስምሱ ወጥቷል። በምሽጉ ውስጥ የነበሩ በርካታ ወታደሮች የእሳት እራት ሆነው ሲቀሩ፡ ሕይወታቸውን ለማትረፍ ሲሸሹ የነበሩ ቁጥራቸው በውል ያልታወቀ በርካቶች ደግሞ ገደል ገብተው አልቀዋል። በአማራ ፋኖ ብሄራዊ ንቅናቄ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒሊክ ዕዝ ልጅ እያሱ ኮር 24ኛ ክ/ጦር ጥር 19 ለጥር 20/2018 ዓ/ም አጥቢያ ሌሊት በፈፀሙት ታአምራዊ ኦፕሬሽን የጠላትን አከርካሪ በመስበር ታላቅ ድል መጎናፀፋቸውን የመረብ ሚዲያ የምስራቅ ዐምሓራ ቀጠና ዘጋቢዎች ለማረጋገጥ ችለዋል። በደቡብ ወሎ ዞን ተሁለደሬ ወረዳ ልዩ ቦታው ቆሎ ባቄላ ተብሎ በሚጠራው ቦታ በነበረው የአገዛዙ ወታደሮች ምሽግ ላይ ነው መብረቃዊው እርምጃ የተወሰደው። ከቦታው መልካአ ምድራዊ አቀማመጥ ጋር ተዳምሮ በመዘመናዊ መንገድ ተሰርቶ የነበረው የአገዛዙ ወታደሮች የኮንክሪት ምሽግ ነው "ተናዳፊዎቹ" በሚል ቅፅል ስም የሚጠሩት በልጅ እያሱ ኮር ስር የ24 ክ/ጦር ፋኖዎች ትናንት አጥቢያ ለሊቱን የጥቃት ዶፍ አውርደውበት ድርምስምሱን ያወጡት። የፋኖ አባላቱ የጥይት ካዝናቸውን እንዳነገቡና የብሬን ሸንሼናቸውን ልክ እንደመቀነት በወገባችው ደግድገው በደረታቸው እየተሳቡ በጠላት ምግሽ ተወርውረው በመግባት በቅድሚያ የምሽጉ ዋርድያዎችን በድምፅ አልባው ሳንጃ ካጋደሙ በኋላ በምሽጉ ውስጥ የነበሩ ወታደሮችን ጭዳ እንዳደረጓቸው የመረብ ሚዲያ የቀጠናው ዘጋቢ ጋዜጠኞች አረጋግጠዋል። የሳንጃ ትንቅንቅን ጨምሮ የክላሽ ጨበጣ ውጊያው የተካሄደው በድቅድቅ ጨለማ በመሆኑ የተገደሉ የአገዛዙ ወታደሮች ቁጥር በውል ባይታወቅም ነገር ግን በርካቶች የአፈር ሲሳይ ሆነው ቀርተዋል። በዚህ መብረቃዊ ኦፕሬሽን ከፋኖ ሳንጃና አፈሙዝ ለማምለጥ ሲሸሹ የነበሩ ቁጥራቸው በውል ያልታወቀ በርካቶች ደግሞ ገደል ገብተው መሞታቸው ነው የታወቀው። የፋኖ አባላቱ፡ ጠላት አይደፈሬ በሚል ሲመካበት የነበረውን ምሽግ ሰዓታትን ባልፈጀ ውጊያ ድርምስምሱን በማውጣት በርካታ ወታደሮችን ከደመሰሱ በኋላ 15 ክላሽንኮቭ መሣሪያዎችን ከነ ተተኳሾቻቸው እንዲሁም ሌሎች ለትግሉ አስፈላጊ የሆኑ ወታደራዊ ግብአቶችን ከበርካታ ወታደሮች ጋር ማርከው በድል ታጅበው ቀጠናውን ለቀው መውጣታቸውን ነው ጣቢያችን መረብ ሚዲያ ለማረጋገጥ የቻለው። ከሐይቅ ከተማ በውስን ኪሎሜትሮች እርቀት ቆሎ ባቄላ አከባቢ በነበረው ምሽግ ላይ ከእኩለ ለሊት ጀምሮ በፋኖ የተከፈተውን ጥብቅ እርምጃ የሰሙ በሐይቅ ከተማ የነበሩ የአገዛዙ ምንጣፍ ጎታች ካድሬዎች አንዳንዶች የለሊት ፒጃማ እንደለበሱ፡ አንዳንዶች ደግሞ በቁምጣና ፓንት ብቻ ሆነው በደረቅ ለሊት ወደ ደሴ ከተማ መሸሻቸው ነው የተነገረው። በከተማዋ መኃል ሸሙሳ ተብሎ በሚጠራው ተራራማ ስፍራ ላይ ሰፍሮ የሚገኘው ቀሪው የአገዛዙ ኃይል፡ ባጠመደው ከባድ መሣሪያ ቆሎ ባቄላ ለነበሩ ጓዶቹ ሽፋን ሲሰጥ ያደረ ቢሆንም፡ ነገር ግን የአንድ ወታደርን ሕይወት ሳይታደግ "የአህያ ባል ከጅብ አያስጥልም" ሆኖ ቀርቷል። 21/ዐ5/2018 ዓ.ም

በሆዳቸው ወድቀው ለብልፅግና መገረድን ምርጫቸው ያደረጉ (ትግሉን የከዱ ባንዳወችም፣ ቀድመው የፈረሙቱ የአብን ሰወችም ሆኑ ሌሎች ከህሊናቸዉ የተፋቱ የአብይ አማሮች) የሚግባቡበት የጋራ ቋንቋ አላቸው። ፋኖን በተላላኪነት መፈረጅ። ይህንን ነገር ደጋግመው የሚያጮሁት መደበቂያ ፍለጋ ነው። የዘር ማጥፋት ጦርነት ታውጆበት እየተጨፈጨፈ ያለን ህዝብ በመካዳቸው እርቃናቸውን ቆመዋል። ከሞራል፣ ከህሊና እና ከታሪክ ጥያቄወች የሚሸሸጉበት ዋሻ ፈልገዋል። ይህንን ዋሻ ያጡ ባንዳወች እና የተላላኪነት ምልክቶች ህይወቱን እየሰጠ ህዝቡን ከጥፋት በማዳን ላይ ያለን ታጋይ በማጠልሸት እና አቻ ፍለጋ ላይ በመሰማራት ራሳቸውን ሊያስደስቱ እየደከሙ ነው። እነሱ እርቃናቸውን ስለቆሙ ከትግላችን አነሳስ እና ባህሪ ጋር በማይገናኝ መንገድ ፋኖን የሆነ አካል ይመራዋል ብሎ በመፈረጅ እንደነሱ ህሊናችን እንዲታረዝላቸው ይፈልጋሉ። ፋኖ በታሪክ ፊት በክብር የሚያቆመዉን ፀረ- አገዛዝ ተጋድሎ እያደረገ ነው። መላላክ እና በራስ ህዝብ ላይ መቆመር የባንዳወች የህይወት መመሪያ ነው። ፋኖ የአማራን ህዝብ ከመጥፋት ለመታደግ ክቡር መስዋዕትነት የሚከፍል በዚህ ዘመን ካሉ ግዙፍ የነፃነት፣ የሰብአዊ መብት ታጋዮች ቀዳሚው ነው። የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ የሚያስከትለው ወይም በጋራ የሚያሰልፈው እንጅ ለብልፅግና እንዳደሩቱ የሚገብርለት ወይም ጁኒየር የሚሆንለት አጋር የለዉም። በህልውናችን ላይ በመጣ ግዜ ህወሃትን ጨምሮ የትኛውንም አካል ለመዋጋት የሚቀድመን እንደሌለ ህዝባችን ጠንቅቆ ያውቃል። ይህንን ደግሞ ከአብይ ጉያ ስር ተወሽቀን ሳይሆን በራሳችን መንገድ ያደረግነው፣ ማድረግም የምንችለው እንደሆነ በተግባር አረጋግጠናል። የህልዉና ጦርነት ውስጥ የከተተን የብልፅግና አገዛዝ ፕሮፖጋንዳም የውጊያ መስመርም ሊያዘጋጅልን አይችልም። በUAE ጀት እና ድሮን አማራን ለሚጨፈጭፈው አብይ አህመድ ስልጣን በፈቃደኝነት የሚፈስ የአማራ ደም አይኖርም። መስዋዕትነት የምንከፍለው አረመኔውን አገዛዝ በማስወገድ የህልውና ጥያቄያችንን በምሉዕነት ለማረጋገጥ ነው። የአፍሪካ ቀንድ ሰላም የሚመጣው ብልፅግና ሲወገድ ብቻ ነው። አስረስ ማረ ዳምጤ

አያሌዉ ሞኙ --ሰዉ አማኙ : ከፋኖ ይልቅ -- ኦህዴድ አማኙ: ከወንድሞቹ -- አራጅ አማኙ አያሌዉ ሞኙ -- አቢይ አማኙ ጨብ ጨብ አድርጉላቸዉ እንጂ ለእነ አያሌዉ ሞኙ ---
አያሌዉ ሞኙ --ሰዉ አማኙ : ከፋኖ ይልቅ -- ኦህዴድ አማኙ: ከወንድሞቹ -- አራጅ አማኙ አያሌዉ ሞኙ -- አቢይ አማኙ ጨብ ጨብ አድርጉላቸዉ እንጂ ለእነ አያሌዉ ሞኙ ---

206ኛ ኮር በስቦ ማስከዳት 68ኛ ክላሽ ሲያገኝ ስድስት የአረመኔው ሰራዊት አባላት ትግሉን መቀላቀላቸው ተገለጸ። ጥር 21/2018 ዓ.ም ======================= ዳዊት መሐመድ ፣ ባቱ
+6
206ኛ ኮር በስቦ ማስከዳት 68ኛ ክላሽ ሲያገኝ ስድስት የአረመኔው ሰራዊት አባላት ትግሉን መቀላቀላቸው ተገለጸ። ጥር 21/2018 ዓ.ም ======================= ዳዊት መሐመድ ፣ ባቱ ቱና፣ ጁበዲ አባ ነጋ፣ አብዱ ሀሰን፣ አማረ ፍቃዱ ፣ በቃሉ አንማው፣ የተባሉ የ32ኛ ክ/ጦር አባላት ከተሰማሩበት ደብረ ኤልያስ፣ ማይአንገታም ምሽግ በመውጣት 206ኛ ኮር 14ኛ ክ/ጦርን መቀላቀላቸው ታውቋል። የአረመኔው ሰራዊት አባላት የሚሰጣቸውን ማንኛውም ግዳጅ ለመወጣት የማይችሉ እና የተሰላቸ ኃይል በመሆኑ ከፍተኛ ኪሳራን በማስተናገ በርካታ ወንድሞቻችንን በሞት ተነጥቀናል የሚሉት እነዚህ የስርዓቱ ወታደሮች የተደረገልልን ጥሪ በመቀበል ትግሉን ተቀላቅለናል ብለዋል። የጠላትን ሰራዊት እረፍት በመንሳት እና በተደራጀ መንገድ የአረመኔውን ኃይል እየናደ የሚገኘው ኮሩ ሁሉም ክ/ጦሮችና ሻለቆች ትግሉን የሚቀላቀሉ የጠላት ወታደሮችን እየተቀበሉ በክብር እያስተናገዱ መሆኑ የጠላት ኃይል ቀን በቀን እየፈረሰ የወገንን ኃይል በቡድን መቀላቀላቸው ተገልጿል ። አዲስ ትውልድ ! አዲስ አስተሳሰብ ! አዲስ ተስፋ! የአፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 206ኛ ኮር ህዝብ ግንኙነት

በሸበል በረንታ ወረዳ 64ኛ የክ/ጦሩ አመራር እና የወረዳው ጊ/መንግስት ከቀበሌ ጊ/አስተዳደሮች ጋር ውይይት አካሂዶል። ➧➧➧➧➧➧➧➧➧➧➧➧➧➧➧➧➧➧➧➧➧➧➧➧➧➧➧➧➧ ጥር 21/2018 ዓ.ም በውይይ
+3
በሸበል በረንታ ወረዳ 64ኛ የክ/ጦሩ አመራር እና የወረዳው ጊ/መንግስት ከቀበሌ ጊ/አስተዳደሮች ጋር ውይይት አካሂዶል። ➧➧➧➧➧➧➧➧➧➧➧➧➧➧➧➧➧➧➧➧➧➧➧➧➧➧➧➧➧ ጥር 21/2018 ዓ.ም በውይይቱ መድረኩ ➣የአፋብን ምስረታን በተመለከተ ➣የድርጅቱ አሁናዊ ቁመና በተመለከተ ➣የሀብት አሰባሰብን በተመለከተ ➣የመልካም አስተዳደርን በተመለከተ በክፍለ ጦሩ አመራር እና በወረዳ ጊ/መንግስት አመራሮች የአመራርነት ስልጠና በመስጠት የቀጣይ የስራ አቅጣጫ ተሰጥተዋል። አዲስ ትውልድ፣ አዲስ አስተሳሰብ፣ አዲስ ተስፋ! ጥር 21/2018 ዓ.ም አፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 201ኛ ኮር ህዝብ ግንኙነት

የደጋው መብረቅ ኮር አሃዶች በመቄትና ቋና በሁለት ግንባር በጥላት ሰራዊት ላይ መጠነ ሰፊ ማጥቃት በማድረግ ታላቅ ድል አስመዘገቡ:: የደጋው መብረቅ ኮር አሀድ የሆኑት አንሻ ክፍለ ጦርና ቀኝአዝማች
+1
የደጋው መብረቅ ኮር አሃዶች በመቄትና ቋና በሁለት ግንባር በጥላት ሰራዊት ላይ መጠነ ሰፊ ማጥቃት በማድረግ ታላቅ ድል አስመዘገቡ:: የደጋው መብረቅ ኮር አሀድ የሆኑት አንሻ ክፍለ ጦርና ቀኝአዝማች ተበጀ ወርቁ ክፍለ ጦር በሁለቱ ግባሮች ላይ በርካታ የብርሀኑ ጁላን መከላከያ ሰራዊት ሙትና ቁስለኛ ተደርገዋል! አፋብን ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ የደጋው መብረቅ ኮር አሀዶች ጥር 20/2018 ዓ/ም በሁለት ግባር ከሶስት ወረዳዎች ለከበባ በመጣ የብርሀኑ ጁላ መከላከያ ሰራዊት ላይ ከባድ ጥቃት ተፈፅሟል። ከመቄት፣ከጋሸናና ከኮን በሶስት አቅጣጫ ለከበባ የመጣው የጥላት ሰራዊት የከበባ ጥቃት የከፈተ ቢሆንም ፤በፋኖዎቹ በተወሰደ አፀፋዊ የመልሶ ማጥቃት እርምጃ በሁለቱም ግባር ከ15 በላይ የጥላት ሰራዊት ሲደመሰሱ፤ዘጠኙ ከባድ ቁስለኛ ተደርገዋል። ከዚሁ ጋር ተያይዞ በርካታ የቁስና የሞራል ኪሳራን ያስተናገደው የጥላት ሰራዊት ወደመጣበት ሲመለስ በንፁሀኖች ላይ የፈሪ በትሩን አሳርፎ በርካቶች የከባቢውን ንፁሀኖችን በገፍ ጨፍጭፏል። በፋኖዎቹ የመልሶ ማጥቃት ጥቃት ክፉኛ የተከፈተበት የፋሽስቱ ሰራዊት እግሬ አውጭኝ በማለት ወደየመጣበት ምሽጉ ተመልሷል። መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልዉና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል! ህልዉናችን በተባበረ ክንዳችን! የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ (አፋብን)የደጋው መብረቅ ኮር ህ/ግ ክፍል ጥር 20/2018 ዓ.ም

ጥር 20/05/2018 ዓ.ም ተስፋ ምሳው የተባለ የአረመኔዉ አገዛዝ 6ኛ ዕዝ 605ኛ ኮር 14ኛ ክ/ጦር ሬጅመንት 5 አባል ፋኖን ተቀላቅሏል። የአማራ ፋኖ አንድነት ምስረታ በፈጠረበት ደስታ ወደፋኖ
ጥር 20/05/2018 ዓ.ም ተስፋ ምሳው የተባለ የአረመኔዉ አገዛዝ 6ኛ ዕዝ 605ኛ ኮር 14ኛ ክ/ጦር ሬጅመንት 5 አባል ፋኖን ተቀላቅሏል። የአማራ ፋኖ አንድነት ምስረታ በፈጠረበት  ደስታ ወደፋኖ ለመቀላቀል መወሰኑን የገለፀዉ ተስፋ ምሳዉ ከኦሮሚያ ክልል በመነሳት ቀናትን የወሰደ ጉዞ ተጉዞ 206ኛ ኮር 34ኛ ክ/ጦርን ተቀላቅሏል። የአረመኔው ሰራዊት አባል ሁኘ በህዝባችን ላይ የሚደርሰውን ግፍና በደል ተመልክቻለሁ ያለው አባሉ ጥር ዘጠኝ የተሰማውን የአማራ ፋኖ አንድነት ብስራት ተከትሎ ከአረመኔዉ ሰራዊት በመዉጣት በግንባር  ድርጅቱን ለመቀላቀል ረጅም መንገድ በእግሩ በመጓዝ ወደ ጎጃም ሊገባ እንደቻለ አክሎ ገልጿል። መከላከያዉ ከተቋቋመለት አላማ በተቃራኒው በራሱ ህዝብ ላይ በመዝመት ፀረ -አማራ ዘመቻ ላይ በመሆኑ የአብይ አህመድን የጭካኔ ተልዕኮ የተቀበሉ የአረመኔው ሰራዊት አባላት ወደ ህዝባቸው መተኮሱን አቁመው የፋኖን ትግል እንዲቀላቀሉ ጥሪ አቅርቧል። ጌትነት እውነቱ / የ206ኛ ኮር 34ኛ ክ/ጦር ኢንዶክትሪኔሽን ኃላፊ

ሰበር...ከሐይቅ ከተማ በቅርብ ርቀት የሚገኘውና ከቦታው አቀማመጡ ጋር ተዳምሮ በመዘመናዊ መንገድ ተሰርቶ የነበረው የአገዛዙ ወታደሮች ምሽግ ዛሬ አጥቢያ ለሊቱን በፋኖ ቦምብ ድርምስምሱ ወጥቶ አድሯል
+1
ሰበር...ከሐይቅ ከተማ በቅርብ ርቀት የሚገኘውና ከቦታው አቀማመጡ ጋር ተዳምሮ በመዘመናዊ መንገድ ተሰርቶ የነበረው የአገዛዙ ወታደሮች ምሽግ ዛሬ አጥቢያ ለሊቱን በፋኖ ቦምብ ድርምስምሱ ወጥቶ አድሯል! በምሽጉ ውስጥ የነበሩ በርካታ ወታደሮች የእሳት እራት ሆነው ሲቀሩ፡ ሕይወታቸውን ለማትረፍ ሲሸሹ የነበሩ ቁጥራቸው በውል ያልታወቀ በርካቶች ደግሞ ገደል ገብተው ማለቃቸውን የምስራቅ ዐምሓራ ቀጠና ዘጋቢዎች ለማረጋገጥ ችለዋል። ይሄንን የሰሙ በሐይቅ ከተማ የነበሩ ካድሬዎች አንዳንዶች የለሊት ፒጃማ እንደለበሱ፡ አንዳንዶች ደግሞ በቁምጣና ፓንት ብቻ ሆነው በደረቅ ለሊት ወደ ደሴ ከተማ ሲሸሹ ታይተዋል። መረብ

የ 99ኛ ክ/ጦር ከፍተኛ አመራሮች ከ ሶስተኛ ሻለቃ አባላት ጋር ሠፊ ግምገማና ውይይት አድርገዋል። የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ቴዎድሮስ ዕዝ በ109ኛ ኮር የ99ኛ ክ/ጦር ከፍተኛ አመራሮች የአንድ
+9
የ 99ኛ ክ/ጦር ከፍተኛ  አመራሮች ከ ሶስተኛ ሻለቃ አባላት ጋር ሠፊ ግምገማና ውይይት አድርገዋል። የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ቴዎድሮስ ዕዝ በ109ኛ ኮር የ99ኛ ክ/ጦር ከፍተኛ አመራሮች የአንድ ወር የስራ አፈፃፀም ከሶስተኛ ሸለቃ አመራሮች እና አባላት ጋር ሠፊ ውይይት አድርገዋል:: የሻለቃ አመራሮች እና አባላት ትግሉን ሊያሻግር የሚቻል ሀሣብ አንስተዋል። በዚህ ውይይት የሻለቃ ሶስት አመራሮች እና አባላት የአማራ ፋኖ አንድነት አማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ያስደሠታቸው መሆኑን ተናግረው ከዚህ በኋላ የምንሞተው ሞት የደስታ እና የፍስU ነው ሲሉ ተናግረዋል።   የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ  ቴዎድሮስ ዕዝ በ109ኛ ኮር የ 99ነኛ ክ/ጦር ምክትል ሠብሳቢ አርበኛ አዲሲ ጥበቡ የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ  ቴዎድሮስ ዕዝ በ109ኛ ኮር የ 99ነኛ ክ/ጦር  ወታደራዊ አሥተዳደር ሳጅን ዘለለም አፈወርቅ እና የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ  ቴዎድሮስ ዕዝ በ109ኛ ኮር የ 99ነኛ ክ/ጦር  ፲/ አለቃ ቀሬ ምናለ ከውይይቱ በተነሱ ጥያቄዎች ምላሽ ሠጥተው የቀጣይ አቅጣጫ አስቀምጠዋል::

ትግሉ ሴቶችንም ወንዶችንም የመላው አማራን ህዝብ ብቻ ሳይሆን የምስራቅ አፍሪካን ቀጠናዊ ሀይል በሙሉ የሚያነቃንቅ እንደሆነ መገንዘብ ይኖርብናል!!!!!!
ትግሉ ሴቶችንም ወንዶችንም የመላው አማራን ህዝብ ብቻ ሳይሆን የምስራቅ አፍሪካን ቀጠናዊ ሀይል በሙሉ የሚያነቃንቅ እንደሆነ መገንዘብ ይኖርብናል!!!!!!

19/5/2018ዓም የደባይ ጥላት ግን ወረዳ ጊዚያዊ መንግስት ከኋላ ደጀን ጦር አባላት ጋራ በወቅታዊ የፀጥታ ጉዳይ ሰፊ ውይይት ተደርገ። በውይይቱም የአማራ ፋኖ ብሄራዊ ንቅናቄ አንድ ድርጅት በመመስ
+3
19/5/2018ዓም የደባይ ጥላት ግን ወረዳ ጊዚያዊ መንግስት   ከኋላ ደጀን ጦር አባላት ጋራ በወቅታዊ የፀጥታ ጉዳይ ሰፊ ውይይት ተደርገ። በውይይቱም የአማራ ፋኖ ብሄራዊ ንቅናቄ አንድ ድርጅት በመመስረቱ የኋላ ደጀን ጦር አባላት መደሰታቸውን ገልፀዋል። ለየትኛውም ግዳጅ ዝግጁ መሆናቸውን ተናግረዋል። በውይይቱ መጨረሻም የኋላ ደጀን ጦር በተጠንቀቅ ለግዳጅ ዝግጁ መሆኑን ጊዚያዊ መንግስቱ  በማረጋገጥ የቀጣይ የግዳጅ ተልኮ በአደረጃጀቱ መሰረት አቅጣጫ በመሰጠት የዕለቱ መድረክ ተጠናቋል። አሌክስ አወቀ የደባይ ጥላት ግን ወረዳ ጊዚያዊ መንግስት ሚዲያ ግንኙነት ክፍል

ህዝቡ እንደዘጋው ሁሉ አገዛዙም ሊዘጋው የማይፈልገው ዶሴ! ምንም እንኳ ሁሉም ነገር ካለፈ በኃላ ጥቂቶች '' በወልቃይት ጉዳይ ከጳጳሱ በላይ ቄስ እንሁን አላችሁ!'' ሲሉ በወልቃይት ዙሪያ አማራውን ''ጳጳስ ፣ ቄስና ዲያቆን'' ደረጃ ሲሰጡት ብናስተውልም ቅሉ ፣ ወልቃይት በየት አቅጣጫ እንደምትገኝ የሚያውቀውም የማያውቀውም ፣ ''ክተት'' ሲባል ተሞ የከተተውም ያልከተተውም ፣ በሀገር ውስጥም ከሀገር ውጭ ያለውም ፣ ለአስርት አመታት ''ወልቃይት ብረሳሽ ቀኜ ትርሳኝ'' ሲል ያልጮኸ ያልታገለ አማራ የለም። የሚገርመው እኛ ወሎ አካባቢ ያለነው እንኳ በልቦናችን ታትሞ የቀረው ''ወልቃይት ብረሳሽ ቀኜ ትርሳኝ'' የሚለው መፈክር (ሞቶ) ብቻ ነው። የራያን ጉዳይ ከማውሳት በላይ የወልቃይት ጉዳይ ይቀናናል። ምናልባትም በርግጥ በትግሉ ሂደት ''ወልቃይትና ራያ ብንረሳችሁ ቀኛችን ትርሳን'' የሚል ሞቶ በስፋት ስላልተለመደም ይሆናል። ይህ የአስርት አመታት የአማራ ህዝብ ትግል ደምና አጥንት ተከስክሶበት ፣ መላው አማራ ተሳትፎበት ፣ ዋጋ ከፍሎበት ወደታሪካዊ ባለቤቱና ማንነቱ ተመልሷል። ፋይሉ እንዲዘጋ ያልፈለገው አገዛዙ እንጂ የአማራ ህዝብ መዝገቡን ከዘጋው ቆይቷል። እዚህ ላይ ''የፕሪቶሪያ ስምምነት'' በተባለው አማራው የማያውቀውና ያልተሳተፈበትን ድራማዊ ትእይንት ተከትሎ ፤ ጦርነቱ ''የዜሮ ድምር'' ሆኖና ሚሊየኖችን በልቶ ፥ ያለአንዳች ውጤት በተጠናቀቀ ማግስት ፣ የሀገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስቴር '' ራያ የእናንተ ነው ብዬ በይፋ መግለፅ ስለማልችል በወረራ መልክ ጦራችሁን አስገብታችሁ ተቆጣጠሩት። ወልቃይትን ግን ብዙ ተያያዥ ነገሮች ሊያስከትል ስለሚችል ለጊዜው ባለበት ይቆይና ወደፊት እየተነጋገርን የምንወስነው ይሆናል!'' በማለት ፥ ወልቃይትን ለፖለቲካዊ ቁማር መጫወቻ ካርድነት ሲያጫት የነበራችሁ ሰዎች ፣ ''..የእናንተን አካባቢ ግን ምንም ማድረግ አልችልም!'' ስትባሉ '' እሺ ጌቶችዬ!'' ያላችሁ አድርባዮች ሁሉ ፤ ዛሬ ባይሆን እድሜ ሰጥቶን ከኖርን ወደፊት በራሳችሁ አንደበት በአደባባይ እንደምትመሰክሩ ቅንጣት አልጠራጠርም! ምንም እንኳ ከዚህ ቀደም አማራውን ''በጳጳስና በቄስ'' ምድብ በደለደሉት ፈራጆች ፤ '' ወልቃይትን አሳልፎ የሚሰጥ እና ወልቃይትን የሚጠብቅ '' የሚል ሌላ የመደብ ድልድል ተሰጥቶት እየሳቅንም እየተሳቀቅንም ብንገኝም ፤ የወልቃይትን ጉዳይ በተመለከተ የአማራ ህዝብ መዝገቡን ዘግቶ ፣ የራሱን አስተዳደርና መዋቅር ዘርግቶ መተዳደር ከጀመረ አመታት ተቆጥረዋል። የአብይ አገዛዝ በስፍራው ጦር ያሰፈረው መቼም '' ወያኔ ወልቃይትን ከአማራው እንዳይወስድበት እየጠበቀለት ነው!'' የሚል የፖለቲካ ድንክ አይኖርም ተብሎ ባይታበልም ፣ አገዛዙ የፖለቲካዊ ቁማር መጫወቻ ካርዱ መሆኗን አለመረዳት የጤና ሊሆን አይችልም። አገዛዙ ላለፉት አመታት ''ወልቃይት በደምና በአጥንት የተመለሰች የአማራ አፅመ እርስት ናት'' ብሎ ቢያምንማ አመታትን በጀት ሳይበጅትላትና እውቅና ሳይሰጣት ተንሳፋፊ ግዛት ሆና አትቀጥልም ነበር። ወልቃይት የተመለሰችው በአማራው ልብ ውስጥ ብቻ ነው። ለአገዛዙ በሁለቱም አቅጣጫ እንደጆከር የምትገባ የቁማር ካርድ ናት። እስኪ አገዛዙ የአማራ ህዝብ ደምና አጥንት ገብሮ (መከላከያም ጭምር) ከሰላሳ አመት በኃላ በጉልበት እንደወሰዱት በጉልበት ማስመለሱን ካመነ ዘንዳ ፣ ወልቃይት በአማራ ክልላዊ አስተዳደር ስር መካተቷን በይፋ አውጆ በጀቷንም ይበጅትላት? ያኔ ጦር ማስፈር አይጠበቅበትም ። ሰራዊቱንም ሲፈልግ ያስወጣ። ወልቃይትን ባለቤቱ ህዝብ ይጠብቃታል! ነገርግን በፍፁም አያደርገውም! አዎ! ሀረርን ፣ ድሬዳዋን ፣ ጅግጅጋንና ሌሎችን አካባቢዎችም እንደወልቃይት አይነት የፖለቲዊ ቁማር መጫወቻ ካርድ ሊያደርጋቸው እየሰራ ያለው ፤ ከእልቂትና ከግጭት አትራፊው አገዛዝ ይህን በፍፁም አያደርገውም! ህወሓት ከአገዛዙ ጋር ለመስራትና ለአብይ ለመገበር ቢስማማ ፣ ሶስት ቀን ሳይፈጅበት ''በስምምነታችን አንቀፅ ...ብላብላ..'' ብሎ ከጦርነቱ በፊት የነበረውን አስተዳደራዊ መዋቅር ሪስቶር እንደሚያደርግ የስሜን ያህል እርግጠኛ ሆኜ እናገራለሁ! በዚህ መሀል ግን በጥቂት የአስተሳሰብ መቀንጨር የሚያናውዛቸው ቡድኖች ፥ ደምና አጥንቱን ከከፈለው የአማራ Faኖ ይልቅ ፣ የህወሓት የማደጎ ልጆቹ እነአብይ አህመድ የወልቃይት ዘብ ተደርገው ሲቆጠሩ ፤ ያኔ ''ወልቃይት ብረሳሽ ቀኜ ትርሳኝ'' የሚል ባነር ይዘን አደባባይ ከወጣነው ይልቅ ፣ አደባባይ በወጡት አማራዎች ላይ ስናይፐር ሲተኩሱና ሲያስተኩሱ የነበሩት ተቆርቋሪና ጠበቃ ተደርገው መታየታቸው እጅግ አሳፋሪውና ምናልባትም በታሪክ ብዙ የሚያባብለን አሁናዊ ክስተት ነው! የወልቃይትን መሬት በማወቅ ወይም ባለማወቅ ፣ ከወልቃይት አንጡራ የተፈጥሮ ፀጋ በመጠቀምና ባለመጠቀም ደረጃ '' ጳጳስ ፣ ቄስ ፣ ዲያቆን ፣ ...ወዘተ'' ልንባል እንችል ካልሆነ በስተቀር ፣ በወልቃይት የአማራ የወሰንና የማንነት ትግል ዙሪያ ትናንትም ፣ ዛሬም ሆነ ወደፊት ማንም ምንም ስላለ የሚለወጥ አቋም አይኖረንም! እኩል ታግለን እኩል እንሞታለን! ምክንያቱም ከአማራ ህዝብ የህልውና ትግል ቅንጣቶች መካከል አንደኛው ''የወልቃይት ፣ የራያ ፣ የደራ ፣ የመተከል ፣ ...ወዘተ የማንነትና የወሰን ጥያቄ'' አንደኛው በመሆኑ ነው! በብልፅግና የቁማር ጨዋታ ውስጥ ግን ማንም አይገባም! አብሮ ማቋመር የሚፈልግም ፥ የአገዛዙ አደግዳጊና ዙፋን ጠባቂ እንጂ የወልቃይት የማንነትና የወሰን ተቆርቋሪ ሊሆን ፈፅሞ አይችልም! ቦ ጊዜ ለኩሉ ....!

በውስጥ መስመር የደረሰንን መርጃ ልናደርሳችሁ ነው። የብልፅግናው አብይ አህመድ እና የሳይበር ታማኞቻቸው (ደጋፊዎቻቸው)፤ የፋኖ አንድነት መጠናከርን ተከትሎ፣ ከቤተ-መንግሥት እስከ ክልል መዋቅሮች ድረስ እርስ በእርስ መተማመን በማጣታቸው የተጠያቂነት 'ዱላ ቅብብሎሽ' ላይ ይገኛሉ።" ​፩. የፋኖ አንድነት እና የመንግሥት ስጋት የፋኖ ኃይሎች በተለይም በአማራ ክልል ያላቸውን ቅንጅት ማጠናከራቸው እና በጋራ መንቀሳቀሳቸው፣ መንግሥት ቀደም ሲል የነበረውን "የመከፋፈል" ስልት እንዳይጠቀም አድርጎታል። ይህ አንድነት በመንግሥት የፀጥታ መዋቅር ላይ ከፍተኛ ጫና ፈጥሯል። ​፪. የመተማመን መሸርሸር (ከቤተ-መንግሥት እስከ ክልል) የጦርነቱ መራዘም እና የሚፈለገው ወታደራዊ ውጤት አለመገኘት በመንግሥት ባለሥልጣናት መካከል ጥርጣሬን ፈጥሯል። ​በክልል ደረጃ፡ የክልል አመራሮች "መንግሥት ጥበቃ ሊያደርግልን አልቻለም" በሚል ስጋት ውስጥ ሲገቡ፤ ​በፌዴራል ደረጃ፡ "መረጃዎች ወደ ፋኖ እየፈሰሱ ነው" የሚል ጥርጣሬ በከፍተኛ አመራሮች ዘንድ ተፈጥሯል። ይህ ሁኔታ አንዱ ሌላውን እንደ "ሰላይ" ወይም "ደካማ" እንዲያይ አድርጎታል። ​ ከመከላከያ ​ወታደራዊ አመራሩ ፖለቲከኛውን "ችግሩን በውይይት አልፈታህም" ሲል ይወቅሳል። ​ፖለቲከኛው ደግሞ ወታደሩን "ውጤታማ አይደለህም" ይላል። ​የክልል ባለሥልጣናት ደግሞ "ፌዴራል መንግሥቱ ትኩረት አልሰጠንም" በሚል ጣታቸውን ይቀስራሉ። ​፬. በማኅበራዊ ሚዲያ (ሳይበር) ላይ መንግሥትን የሚደግፉ አካላትም በዚህ ውጥረት ውስጥ ግራ ተጋብተዋል። ቀደም ሲል በአንድ ድምፅ ይሟገቱ የነበሩት አካላት፣ አሁን ላይ የትኛውን የመንግሥት ክንፍ መደገፍ እንዳለባቸው በማጣት እርስ በእርሳቸው መካሰስና መከፋፈል ውስጥ ገብተዋል። ​ባጠቃላይ፣ የፋኖ እንቅስቃሴ መሬት ላይ እያሳየ የመጣው ለውጥ በመንግሥት መዋቅር ውስጥ ያለውን ነባር ስንጥቅ አጉልቶታል። ይህም በአብይ አህመድ ባለሥልጣናት መካከል ያለውን መተማመን አጥፍቶ፣ አገራዊ ችግሩን ከመፍታት ይልቅ አንዱ በሌላው ላይ ጥፋት የማላከክ (ዱላ ቅብብሎሽ) ሥራ ላይ እንዲጠመዱ አድርጓቸዋል።