ፍኖተ-አማራ ሚዲያ (Finote Amhara Media)
前往频道在 Telegram
የተመሠረተው የአማራን ሕዝብ ለማንቃት፣ ለማደራጀት እና ለማስተባበር ነው። የአማራ ሕዝብን ✅ ፖለቲካዊ ✅ ማህበራዊ ✅ ኢኮኖሚያዊ ታሪካዊ ጥያቄዎችን ለማሰማት እና የአማራን ሕዝብ በማንቃት ሰፊውን ሕዝብ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ይሰራል። ወደዱም ጠሉም የኃላ ታሪካችን በእኛ እጅ ይፃፋል። አማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ( አፋብን)
显示更多4 136
订阅者
+724 小时
+2087 天
+1 20130 天
帖子存档
+3
በተግባር ተቋሙን እያፈረስነው ነው‼️
በአገዛዙ ስርዓት አማራ በመሆናችን ብቻ እየተገፋን ስለሆነ በማለት በዛሬው እለት ወደ ፋኖ ተቀላቅለዋል።
ታህሳስ 20/2018 ዓ.ም
1ኛ.እሸት ይመር ይበላል 6ኛ ዕዝ 601ኛ ኮር 52 ኛ ክ/ጦር ሸበል በረንታ መርገጭ ከተማ ከመከላከያ ተቋም ሙሉ ትጥቅ በመያዝ 64ኛ ክፍለ ጦርን ተቀላቅሏል።
2ኛ.ይሁን ብሬ ከሚሊሻ ተቋም 74ኛ ክ/ጦርን ተቀላቅሏል
3ኛ.በለጠ አለማየሁ ከሚሊሻ ተቋም 74ኛ ክ/ጦር የተቀላቀሉ ሲሆን አመራሮችም አቀባበል አድርገውላቸዋል።
ታህሳስ 20/2018 ዓ.ም
አዲስ ትውልድ፣አዲስ አስተሳሰብ፣አዲስ ተስፋ
የቴወድሮስ ዕዝ 201ኛ ኮር ህዝብ ግንኙነት
ቲባግነት ( T-Bagism)
===============
"ፕሪዝን ብሬክ" በተባለው ዝነኛ የአሜሪካ ፊልም ለሐገር ፍቅር የሚከፈልን ዋጋ እና የአላማ ፅናት አንድን ግለሰብ የሚያጎናፅፈውን ክብር በማሳየት በኩል ወደር የለውም።
ለዚህ ፊልም ተወዳጅነት በፊልሙ ማይክል ተብሎ የሚጠራው ድንቅ ተዋናይ ከራሱ በላይ ለሌሎች ፍትህ መረጋገጥ እና ለሐገሩ ሉዓላዊነት የሚከፍለውን ዋጋ ጠንቅቆ በማወቅ ሁሉነገሩን አሳልፎ ሲሰጥ እና ድንቅ ችሎታው ክብርን ሲያጎናፅፈው እንመለከታለን።
ማይክል ለፍትህ እና ለውድ ሐገሩ አሜሪካ ያለውን ቀናይነት ተመልክተው እንደየ ክህሎታቸው የሚያግዙት እና በጋራ ለስኬት የበቁ ብዙ መልካም ዜጎች እንዳሉ እና መኖር እንዳለባቸው በፊልሙ እያዝናና ያስተምረናል።
እነዚህ መልካም ዜጎች ለተቀደሰው አላማ ከማይክል ጋር በመተባበራቸው ራሳቸውን ከአስከፊው እስር ነፃ ሲያወጡ ፣ ሐገራቸውን ከጥፋት ሲታደጉ ብሎም በሐገራቸው ላይ ያንዣበበው አደጋ ለእደገታቸው እንደ መልካም አጋጣሚ ሲጠቀሙት እናስተውላለን።
ማይክል የብዙ ክፉ ሰወችንም ልብ በፍቅሩ አሸንፎ ለተቀደሰ አላማ ሲያሰልፋቸው እንመለከታለን።
ይሁን እንጅ በዚህ ፊልም ወስጥ ቲባግ የተባለው ግለሰብ ለሐገር እና ለሌሎች ፍትህ ዋጋ ሊከፍል ይቅርና :-
➟ ለእራሱ እንኳን ክብር የሌለው
➟ ከእስርቤቱ አምልጦ ምን እንደሚሰራ ርዕይ አልቦ
➟ ሰወችን ለማበሳቆል ጭካኔውና ክፋቱ ወደር የለሽ
➟ የደስታ ምንጩ በምድር ላይ በርካሽነታቸው የሚታወቁ ነገሮች የሆነ
➟ የራሱን ሐፂያት ለሌሎች የሚያሳብብ
➟ ከቡድኑ ጥፋት እና ስህተት ራሱን ነፃ ለማድረግ የሚላላጥ
➟ ቂመኛ ፣ ምቀኛ ፣ ራስ ወዳድ እና የትልቁ አላማ ህፀፅ ሆኖ እንመለከተዋለን።
ቲባግ በስርቤት ሰበራው ተጋድሎ ሒደት ውስጥ በማይክል እና ጓደኞቹ ትክሻ ላይ ሆኖ ካለማገዙም በላይ ሒደቱን ብዙ ጊዜ አበላሽቷል ፤ የስርቤት ሰባሪ ቡድኑን በተደጋጋሚ ለአደጋ አጋልጧል። የበር ተመልካች ውሻ ያህል እንኳን ሚና አልነበረውም።
በዚህ ሁሉ ጥፋት መሐል እነ ማይክል ለቲባግ ይቅርታ እያደረጉ እድል ቢሰጡትም ባለመቀየሩ ከእነ ማይክል ተጋድሎ ስኬት በሗላ በክፋቱ ብዛት ይቅር የሚለው አጥቶ ወደ አስከፊው እስር ቤት መልሶ ሲወረወር እንመለከታለን።
Moral of The Story ፦
ከከበበን አስከፊ ጭቆና እና የህልውና አደጋ ለመውጣት በሚደረገው የአማራ ብሔራዊ አብዮት ተጋድሎ ሒደት ውስጥ (በሚኖረን ተጋድሎ) ቲባግነት ፀረ-አማራ ብሔርተኝነት ትግል እንደሆነ ታውቆ ሚናችንን በሚጠበቅብን ልክ መወጣት አለብን።
ቲባግነት ብኩንነት ነው!!! ቲባግነት አሞሟቱ እንኳን የከፋ "የውሻ ሞት" የሚያስከትል መሆኑን ማወቅ አስፈላጊ ነው።
አዲስ ትውልድ፣ አዲስ አስተሳሰብ፣ አዲስ ተሰፋ !!!
Kinfemelak N Kassa
አንች አገሬ ኢትዮጲያ እውነት በድየሽ ከሆነ ነፍሴን አይቀበላት! አልበደልኩልሽ ከሆነ ወንድ አይብቀልብሽ ብሏል ደጃዝማች በላይ ዘለቀ( አባኮስተር
ደጃዝማች በላይ ዘለቀ ልጃቸው የሻሽወርቅን ከጣሊያ ካምፕ በሚስጥር ካስመለጠ እና ወደራሱ ካመጣት በኋላ ከገጠማቸው ግጥሞች መካከል
ለገንዘብ የሚሞት የቅጥር ወታደር
እራሱን ያፈቅራል አይሆንም ለሀገር
አይሆንም ለሀገር
አይሆንም ለዘመድ
ለገንዘብ የሚሞት ይቅር አይወለድ
በተግባር ተቋሙን እያፈረስነው ነው‼️
በአገዛዙ ስርዓት አማራ በመሆናችን ብቻ እየተገፋን ስለሆነ በማለት በዛሬው እለት ወደ ፋኖ ተቀላቅለዋል።
ታህሳስ 20/2018 ዓ.ም
1ኛ.እሸት ይመር ይበላል 6ኛ ዕዝ 601ኛ ኮር 52 ኛ ክ/ጦር ሸበል በረንታ መርገጭ ከተማ ከመከላከያ ተቋም ሙሉ ትጥቅ በመያዝ 64ኛ ክፍለ ጦርን ተቀላቅሏል።
2ኛ.ይሁን ብሬ ከሚሊሻ ተቋም 74ኛ ክ/ጦርን ተቀላቅሏል
3ኛ.በለጠ አለማየሁ ከሚሊሻ ተቋም 74ኛ ክ/ጦር የተቀላቀሉ ሲሆን አመራሮችም አቀባበል አድርገውላቸዋል።
ታህሳስ 20/2018 ዓ.ም
አዲስ ትውልድ፣አዲስ አስተሳሰብ፣አዲስ ተስፋ
የቴወድሮስ ዕዝ 201ኛ ኮር ህዝብ ግንኙነት
ለተወርዋሪ ሀይሎች ስልጠና ተሰጠ
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
በቀን 19/04/2018 ዓ/ም
ቴወድሮስ ዕዝ 201ኛ ኮር 74ኛ ክ/ጦር አመራሮችና የጎንቻ ሲሶ እነሴ ወረዳ ግዚያዊ መንግስት አመራር በወረዳው ከሚገኙት በአምስት ቀበሌወች የሚገኙትን ተወርዋሪ ሀይሎችና የቀበሌ አስተዳደሮችን ስልጠና ተሰጥቷል ።
በስልጠናውም፦
_ ስለፍትህ አሰጣጥ
_ ስለቀበሌ አደረጃጀት
_ ስለአዲሱ ኮርና ክፍለ ጦር አደረጃጀት
_ ስለግዚያዊ መንግስት አደረጃጀት
_ ትግሉ ስለደረሰበት ደረጃ ግንዛቤ የተፈጠረ ሲሆን
ስልጠናውን የወሰዱ የየቀበሌው ተወርዋሪ ሀይሎችና የየቀበሌው አመራሮች ከዚህ በኋላ በቁርጠኝነት ፣በግልፀኝነትና በታማኝነት ድርጅታቸውንና ህዝባቸውን እንደሚያገለግሉ ቃል ገብተዋል።
አዲስ ትውልድ፣አዲስ አስተሳሰብ፣አዲስ ተስፋ
ታህሳስ 20/2018 ዓ.ም
የቴወድሮስ ዕዝ 201ኛ ኮር ህዝብ ግንኘነት
ሰበር ዜና!!
ሜጀር ጀነራል ውባንተ አባተ ፩ኛ ኮር ምርጥ ሥብሥብ
ታሕሣሥ 19/2018ዓ.ም
በሰማዕቱ አርበኛ ሜጀር ጀነራል ውባንተ አባተ ሥም የተሰየመው ፩ኛ ኮር 04 ብሬኖችን፣ ክላሾችንና ብዛት ያለው ተተኳሽ ከጠላት ማርኳል።
ይህ ድል የተገኘው ከ04ቱም ክፍለ ጦሮች በተውጣጣ ዕንቁ የተዋጊ ስብስብ ነው።
ተጨማሪ የተማረከ ተተኳሽን በቁጥር፣ የተማረከ ነፍሥ ወከፍና ቡድን መማሪያዎችን በቁጥር እንዲሁም በጠላት ላይ የደረሰውን ድምሰሳና ቁሳዊ ኪሣራ በቁጥር እናሥቀምጣለን።
ኅልውናችን በተባበረ ክንዳችን✊
አፋብኃ ሰ/አ/ቀ በላይ ዕዝ
ሜጀር ጀነራል ውባንተ አባተ ፩ኛ ኮር
ኃቅአለው ፀጋ አለባቸው
ትላንትም ዛሬም ነገም አንድ ነን!!
የበላይ ዘለቀ ዕዝ ከላይ እስከ ታች ትላንትም ዛሬም ነገም አንድ ነን።
በጦር ያልተፈታ በወሬ ይፈታል ስልት የተለሙ የወሬ ወረርሽኝ ደዌ የአልጋ ቁራኛ ያደርገን ይመስል ከንቱ የወሬ ወረርሽኝ ሰደድ እያራገቡ መሆኑን ተገንዝበናል።
መልሱ ግን በላይ ዕዝ ብቻ አይደለም መላ አማራ አንድ ይሆናል ነው።እየተሰራጨ ያለው የወሬ ወረርሽኝ ያሳሰባችሁ ወዳጆቻችን የወሬ ወረርሽኝ ልክፍት እንዳያወዛግባችሁ እንላለን!!
ዮሐንስ ንጉሱ ሙጨ
የምኒልክ ዕዝ ከፍተኛ የድርጅትና የኮር አመራሮች በተለያዩ ቀጠናዎች የሰራዊት አደረጃጀትና አጠቃላይ ፖለቲካዊና ወታደራዊ ግንባታ እየሰጡ ይገኛሉ::
በዚህም በቅርቡ የኮሩ ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት ጥልቅ ግምገማና ውይይት በማድረግ የአመራር ጥገና ያደረገው የምስራቅ አማራ ኮር አንዱ ሐውጃኖ ክፍለ ጦር ሰራዊትን በተለያዩ ወታደራዊና ፖለቲካዊ ጉዳዮች ዙሪያ መሰረታዊ የሚባል ግንባታ ሰጥተዋል::
ከፍተኛ አመራሮቹ ትኩረት ያደረጉባቸው ነጥበችም የሚከተሉት ናቸው፦
1ኛ.የድርጅቱን ቀጠናዊ ትስስር እና ፖለቲካዊ ግንባታ
በአርበኛ አበበ ቀዮ
2ኛ.የሲቪል አስተዳደር መዋቅር
አስፈላጊነት እና ዘመናዊ የሰራዊት አደረጃጀትና ውህደትን በተመለከተ
በአርበኛ አሰፋ መሰለ (አሳምነው)
3ኛ.ስለ ድርጅቱ አሁናዊ ቁመና እና አንድነትን እንድሁም አጋርነትና ትብብርን በተመለከተ
በአርበኛ እስራኤል እሸቴ
4ኛ.የወታደራዊ አቅም ግንባታ
በአርበኛ ደባሽ መምሬ (አባ ነጋ)
እነዚህን እና ሌሎች ቀጠናዊና አለማቀፋዊ ጉዳዮችን ጭምር በመዳሰስና በማንሳት ለሰራዊቱ ግንባታና የግንዛቤ ፈጠራ ስራ ሰርተዋል::
መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!
ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!
አፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ
ታህሳስ 20/2018 ዓ.ም
የክፍለ ጦሩን ወታደራዊ እና መዋቅራዊ ቁመና ወደ ላቀ ደረጃ የሚያሸጋግር ምክክር ተደረገ
══════════════❁✿❁══════════════
(ታኅሣስ 20/2018 ዓ.ም፣ 33ኛ ክ/ጦር ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ)
ዐፋብኀ 102ኛ ኮር የ33ኛ ክፍለ ጦርን ወታደራዊ እና መዋቅራዊ ቁመና ወደ ላቀ ደረጃ የሚያሸጋግር ምክክር አደረገ።
በምክክሩ ከሻለቃ እስከ ክፍለጦር በየዘርፉ የታዩ ዝንፈቶች በዝርዝር ተገምግመዋል። ታይተዋል ለተባሉ ተግዳሮቶችም በተገኙ የድርጅቱ አመራሮች በቂ የማስተካከያ ሀሳብ ተሰጥቶባቸዋል።
በማስተካከያ ሀሳብና አቅጣጫዎች የተግባባው ኹሉም የድርጅቱ አመራር እና መላ የምክክሩ ተሳታፊ የሥራ ስምሪት ወስዶ ምክክሩ ተደማድሟል።
የተደረገው ምክክር፣ ግምገማ እና ውይይት አባላትንና አመራሩን በማመጋገብ የተናበበ ውጤት ያስመዘግባል ተብሎ ታምኖበታል።
ከዐፋብኀ የቴዎድሮስ ዕዝ ወታደራዊ አስተዳደር አርበኛ ኢንጂነር ማንችሎት እሱባለው፣ የቴዎድሮስ ዕዝ ጤና መምሪያ ሓላፊ ዶክተር እንዳላማው ጤናው፣ የቴዎድሮስ ዕዝ ሴቶች ጉዳይ ም/ሓላፊ አርበኛ አትጠገብ አጥናፉ፣ የቴዎድሮስ ዕዝ ልዩ ዘመቻ ም/አዛዥ ፶ አለቃ መኰንን ይፍሩ፣ የ102ኛ ኮር ሰብሳቢ አርበኛ ዘውዳለም አዱኛ እና ሌሎች የኮሩ አመራሮች እንዲሁም የ33ኛ ክፍለ ጦር አመራሮች እና የክፍለ-ጦሩ ጊዜያዊ መንግሥት አስተዳዳሪዎች ተሳታፊዎች ነበሩ።
በቢቸና ከተማ የሚገኘው የአገዛዙ ቅጥረኛ ሚሊሻ የእስልምና እምነት ተከታይ የነበር ንፁሃንን በአሰቃቂ ሁኔታ ገደለ!!
ታህሳስ 20/2018 ዓ.ም
ሲራጅ ኢብራሂም የትውልድ ቦታ ሸበል በረንታ ወረጎ ቀበሌ ተወላጅ ሲሆን በቢቸና ከተማ 04 ቀበሌ ኖሪ ነበር። በመሆኑም ሲራጅ ኢብራሂም ባላቤቱን ከአረብ ሀገር ስደት መልስ በመቀበል የእለት ከእለት ህይወታቸውን የሚመሩበት ገንዘብ በእጁ እንደያዘ ቢቸና ከተማ የሚገኘው ቅጥረኛ ሚሊሻ ገንዘቡን በመዝርፍ ታህሳስ 16/2018 ዓ.ም ከምሽቱ 1:30 ቢቸና ከተማ በአሰቃቂ ሁኔታ ገድለው ጥለውታል።
በቢቸና ከተማ ተስፋ የቆረጠው የአገዛዙ ቅጥረኛ ሚሊሻ በቢቸና ከተማ በሁለቱ የእምነት ተቋማትን ለማጋጨት የእስልምና ተከታይ የሆኑ ወንድሞቻችንን በመግደል ፋኖ ገድሏል በማለት የሐሰት ፕሮፖጋንዳ እያሰራጨ ይገኛል።
በቢቸና ከተማ የምትገኙ የእስልምና ተከታይ አማራዎች በሙሉ የአገዛዙ አረመኔዊ ሰራዊት በሁለቱም እምነት ተቋማት እና የሁለቱ እምነት ተከታዩች ላይ እያደረሰባቹህ ያለውን ግፍ እና በደል በቃን በማለት አገዛዙ በቢቸና ከተማ ልታወግዙ ይገባል።
አዲስ ትውልድ፣ አዲስ አስተሳሰብ፣ አዲስ ተስፋ!!
የቴወድሮስ ዕዝ 201ኛ ኮር ህዝብ ግንኙነት
ታህሳስ 20/2018 ዓ.ም
አርበኛ ብሩክ ስለሺ እንደከተበው
"በእነርሱ ውስጥ የሞቱት በእኛ ውስጥ ህያዋን ናቸው"
ነበር!
በቀን 18/04/2018ዓ.ም በአገዛዙ በደረሰው ጥቃት በደረሰው ጉዳት ትልቅ አባታችንን ጨምሮ ባጣናቸው ወንድሞቻችንን የተሰማንን ጥልቅ ሃዘን እየገለፅን።
ተስፋዬ መካሻ ሀብተወልድ ግፋወሰን ዕድሜ ያልበገረው ቅን እና ጀግና አባት ነበር። ለመጀመሪያ ጊዜ ወደ ትግል ሜዳ ሲመጣ ወደ ትውልድ ቀዬው መርሐቤቴ በመግባት መሬት ላይ ያለውን የኃይል አሰላለፍ በሚገባ የራሱን ጥናት ሰራ። በወቅቱ በሸዋ ላይ የሚንቀሳቀሱት የፋኖ ኃይሎች በሶስት መዋቅር ስር የነበሩ ናቸው። ይኼንን መመልከቱ ከምንም ነገር በፊት እና በላይ አንድነት ላይ መስራት እንዳለበት ስላስገነዘበው ለዚህም እጅግ ከባድ የሆነውን የሸዋ መልክዓምድር በጠንካራ ወታደራዊ ዲሲፕሊን በኖረበት ወታደራዊ የአካል ብቃት የነበሩትን ልዩነቶች ደግሞ በአስተዋይ የአባትነት መንፈሱ በመጠቀም ለአንድነቱ የሚጠበቅበትን ለመወጣት እንቅስቃሴውን ጀመረ። በመርሐቤቴ ከአንድ አማራ ፋኖ ጋር ያደረገውን ውይይት ተከትሎ ወደ ይፋት በመጓዝ ከአማራ ፋኖ አንድነት ምክር ቤት በሸዋ ጋር በመድገም በመቀጠል በዚያው በይፋት ከሚገኘው የአማራ ፋኖ ነፃ ህዝብ ንቅናቄ ዋና መሪ አርበኛ እና ደራሲ አሰግድ መኮንን ጋር በማድረግ የሸዋን የአንድነት ጉዞ ጀመረው። በመቀጠል በሸዋ ላይ እጅግ ረጅም እና ጥልቅ ውይይት በማመቻቸት የአቅሙን የተወጣው ጋሽ ተስፋዬ በየወቅቱ ይፈጠሩ የነበሩ ችግሮችን ለመፍታት የሽምግልና ወጉን በመወጣት ያላሰለሰ ጥረት ሲያደርግ ቆየ።
"ደክሞት አይቆምም የሸዋ ፈረስ
ከአንኮበር ዘልቆ ሀማሴን ድረስ" እንዲል ዜመኛው በሸዋ መወሰን ያልበቃው ጋሽ ተስፋዬ መሰል ወንድሞቹን በመያዝ የአማራን አንድነት ለማምጣት በዚያ በክረምት ወራት ታላቁ የአባይ ወንዝ እንኳን የሚሻገረውን በሩቅ የሚያየውን በሚያስፈራበት ወቅት ወደ ጎጃም በመሻገር በመቀጠልም ወደ ወሎ እና ጎንደር በመሄድ የአማራን አንድነት ለማምጣት ማንም ያልቻለውን ችሎ አሳይቷል። የምን ጊዜም ምኞቱ የነበረው፤ የዘወትር ጸሎቱ የነበረው "የአማራን አንድነት ሳላይ እንዳልሞት" የሚለውን ቃሉን ነፍሱን በማይፀፅታት መንገድ ኖሮታል።
ጋሽ ተስፋዬ ሌሎች ሊኖራቸው የሚያልሙትን የቅንጦት ህይወት በመተው ከሀገር ውጭ የነበራቸውን ኑሮ እና ቢዝነስ ከአማራ ህዝብ ህልውና አንፃር ምንም እንዳልሆነ በማመን ይኼንን ትግል ከተቀላቀሉ ወዲያ ለአንድ አባት እጅግ ከባድ የሆነው ልጅን የማጣት መከራ በዕድሜያቸው ማባሪያ ጊዜ ደረሰባቸው። ይኽንን መከራ ተሸክመው የአባትነት ፍቅራቸው የጫነባቸውን ሀዘን ለነፃነት ባለቸው ፍቅር መክተው ቆይተዋል።
ባለፈው አንድ ዓመት የነበራቸው ጊዜ ለአንድ ይኼን ሁሉ መስዋዕትነት ለከፈለ አባት የማይገባ ቢሆንም ሁሉንም ተቋቁመው እስከ ትናንትናዋ ሌሊት ከትግል ሜዳው ሳይወጡ ኖረው አገዛዙ ባደረሰው የድሮን ጥቃት ትናንት የህይወታቸው ምዕራፍ ከነሙሉ ታማኝነታቸው በመስዋዕትነት ተቋጭቷል።
የጋሽ ተስፋዬ ህይወትም ሆነ መስዋዕትነት የአንድ ግለሰብ ኑሮ እና ፍፃሜ ሳይሆን የአማራ አባቶች ህልም፤ ፍላጎት፤ ቁጭት፤ አላማ፤ ወግ፤ ክብር የሚነበብበት መፅሐፍ ነው። የአማራ አባቶችን የአማራ አያቶችን ከሞቀ ጎጇቸው አውጥቶ ከልጅ ልጆቻቸው ጋር የሚያታግላቸው በገዛ ሀገራቸው የታወጀባቸው የሞት አዋጅ ነው። የሚቀለበሰውም አባቶቻችን አውግተውን ሰምተን፤ ከትበውልን አንብበን፤ ባገኘነው ታሪክ እና መንገድ ብቻ ሳይሆን ኖረው አሳይተውን በዘረጉት የዘለዓለማዊ ህያውነት መንገድ ጭምር ነው።
በትናትናው እለት አገዛዙ ባደረሰው የድሮን ጥቃት ንፁሃንን ጨምሮ የተሰው ወንድሞቻችን የተሰማንን ጥልቅ ሃዘን መግለፅ እንወዳለን።
የስኬት ክብደቱ
የምቾት አይነቱ
የነገ ውበቱ
ባሻው ቋት ቢለካ በምንም ቢሰፈር
ባሻው ቃል ቢነገር
ጀግና ልጅ አትወልድም
አያቶቿን ገድላ የምትሸልል ሀገር!
ክብር ለተሰዉት!
ድል ለአማራ ህዝብ!
+2
👉ራሱን የሀገር መከላከያ ሰራዊት ብሎ በሚጠራው ኃይል በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን የ-ተ-ቃ-ጠ-ለ የአርሶ አደሮች የበቆሎ ሰብል ነው።😭
ወደ አማራ ክልል የገባው ወ-ራ-ሪ ኃይል አ-ው-ዳ-ሚ ነው ስንል በምክንያት ነው።
"አስቸኳይ መልዕክት"!
ጃቢጠናን ወረዳ በተለይም ማክሰኝን ዙሪያ የድሮን ቅኝት ስላለ የወገን ሀይልና ማህበረሰባችን ጥንቃቄ ይደረግ።
አንድነት ናፋቂው አባት አርበኛ ተስፋዬ መካሻ አረፉ
የለፉህበት እና ዋጋ የከፈሉበት አንድነት ሳታይ በግዞት ሆነው ማረፋቸው በጣም ያንገበግባል።
ከሽዋ እስከ ጎጃም፣ ከጎንደር እስከ ወሎ የአማራን ትግል አንድ ለማድረግ በደከመ ጉልበታቸው፣ በዛለ ሰውነታቸው፣ በመጦሪያቸው እድሜያቸው ሲወጡ ሲወርዱ የነበሩት አንድነት ናፋቂው አባት አርበኛ ጋሽ ተስፋዬ መካሻ ለምን አንድነት ሰበክ ተብለው ታስረው ላለፈው አንድ አመት ሲሳቀዩ ቆይተው በዛሬው ዕለት ከታሰሩበት ቦታ በአገዛዙ የድሮን አረር ከበርካታ ታሳሪዎች ጋር መገደላቸውን ሰማን።
ያሳዝናል😭 አባታችንን
ነፍሳቸውን በአፀደ ገነት ያኑርልን
