ch
Feedback

不要被骗子欺骗!Telemetrio 会找到并标记这些频道 👉 如果想查看标记,请订阅

ፍኖተ-አማራ ሚዲያ (Finote Amhara Media)

ፍኖተ-አማራ ሚዲያ (Finote Amhara Media)

前往频道在 Telegram

የተመሠረተው የአማራን ሕዝብ ለማንቃት፣ ለማደራጀት እና ለማስተባበር ነው። የአማራ ሕዝብን ✅ ፖለቲካዊ ✅ ማህበራዊ ✅ ኢኮኖሚያዊ ታሪካዊ ጥያቄዎችን ለማሰማት እና የአማራን ሕዝብ በማንቃት ሰፊውን ሕዝብ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ይሰራል። ወደዱም ጠሉም የኃላ ታሪካችን በእኛ እጅ ይፃፋል። አማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ( አፋብን)

显示更多
4 349
订阅者
+17324 小时
+2467 天
+1 36830 天
帖子存档
#ዘመን #የማይሽረው #ጀብድ! ትውልድ ቦታው ከጀግኖች መንደር ጠገዴ አርማጭሆ አዴት አመራ፥ የአርበኛ ጎቤ መልኬ (ዋዋ) የመንፈስ ልጅ የአርበኛ የሲሳይ አሸብር ቀኝ እጅ  የአርበኛ እሸቴ አሸብር ጋሻ አልሞ ተኳሹ(ዋግነር) መልክና ቁመናው ታይቶ የማይጠገብ የወንዶች ቁና ተወርዋሪው ኮከብ አርበኛ #ብርሃኑ #ሙላው #ሙጨ በየተገኘበት ቦታ ሁሉ ለሚገደለው ለሚፈናቀለው ሀብት ንብረቱ ለሚዘረፍበት የአማራ ህዝብ ብሎ ለከፈለው ውድ የህይወት መስዋዕትነት ክብር ይገባዋል!:: አርበኛ ብርሃኑ ሙላው በወርሃ ጥቅምት በ2013 ዓ.ም የብልጽግና መንግስት ዙፋኔን የህወሀት ቡድን ሊቀማኝ ነው ብሎ ጥሪ ባቀረበ ጌዜ ከወንድሞቹ ከነ አርበኛ ሲሳይ አሸብር ጋር በመሆን በማይጋባ ግንባር ተሰልፎ ሊወር የመጣውን ሀይል በመደምሰስ ዲሽቃን ጨምሮ በርካታ የነብስ ወከፍ መሳሪያዎችን ማርኳል:: በወርሃ ሰኔ 2015 ዓ.ም በምዕራብ ኢትዮጵያ ሱዳን ጠረፍ ምድራችን ሊወር የመጣውን የሱዳን እና የህወሃት ታጣቂ ሀይል  ከነ አርበኛ ሲሳይ አሸብር ጋር በመሆን አይቀጡ ቅጣት በመቅጣት ከ15 በላይ የጠላትን ሀይ ከአፈር ጋር ጨምረውታል የቀረው ደግሞ እፍረትን ተከናንቦ ተመልሷል:: በወርሃ ነሀሴ 1/2015 ዓ.ም አማራ ጠሉ የብልጽግናው አገዛዝ የአማራን ህዝብ እንኳን ትጥቁን ቀበቶውን አስፈታዋለሁ ብሎ በተለያዩ የአማራ ግዛቶችና ከተሞች በህዝባችን ላይ ጦርነት ሲያውጅ ጀግናው አርበኛ ብርሀኑ ሙላው ከነ አርበኛ ሲሳይ አሸብርና ደጀን አሸብር(እረመጡ) ጋር በመሆን ሳንጃ ከተማ የጁላን ሰራዊት እራስና እግር አቆላልፈውታል በዚህ የጦር ግንባር ከ200 በላይ የጠላት ሀይል ተደምሷል:: አርበኛ ብርሃኑ ሙላው የጎቤ ክፍለ ጦር መስራች ሲሆን የክፍለ ጦሩ ዘመቻ መምሪያ ሁኖ በብዙ የጦር ግንባሮች ድልን እየተቀናጃ ሲዋጋና ሲያዋጋ የነበረ የጦር ጠበብት ታጋይ ነበር:: አርበኛ ብርሃኑ ሙላው 4ኛ ደጃዝማች ኮር ከተመሰረተ ጊዜ አንስቶ የኮሩ አደረጃጀት መምሪያ ሀላፊ ሆኖ ከዳዋ እስከ አርማጭሆ ከጠገዴ እስከ ሱዳን ጠረፍ ከቋራ እስከ አዳኝአገር ጫቆ የሚሸፍነውን ሰፊ የበርሃማ መሬት በመዘዋወር የፋኖ ሀይል ጥሩ ቁመና እንዲኖረው በጽናት የታገለ ጀግና መሪ ነበር:: አርበኛው ታህሳስ 05/2018 ዓ.ም በመተማ ወረዳ መሸሃ ቀበሌ መሽጎ የነበረውን የጁላ ሰራዊት ከኮሩ በተውጣጡ 3 ክፍለ ጦሮች ከበባ በማድረግ ከጥዋቱ 12:00 እስከ ቀኑ 10:00 ሰዓት በነበረው እልህ አስጨራሽ የጨበጣ ውጊያ የጠላትን ሀይል እንደ ቅጣል አራግፎ ሲዋጋና ሲያዋጋ ቆይቶ ከቀኑ 5:00 ሰዓት ላይ ተሰውቷል:: አርበኛው በተሰዋበት የጦር ግምባር 253 የሞተ 58 የቆሰለ 55 ሰራዊት የተማረከ ሲሆን 83 የነብስ ወከፍ ክላሽን ኮፕ መሳሪያ ከ15 ሽ የተለያዩ ተተኳሾች ጋር 1 ዲሽቃ 2 ብሬን ገቢ ተደርጓል:: "የደጀን ጋሽ የሲሳይ ወንድም ጠላት ሲመጣ ምሽግ አይለቅም ዘማች ማይጋባ ዘማች ሱዳን ዳር ከወንድሞቹ ከነ ሲሳይ ጋር የአርማጭሆው ልጅ የነ ጎቤ ዘር ጠላትን ለይቶ ከአፈር ሚጨምር" ሲል ነበር ወንድማችን አርበኛ ብርሃኑ ሙላው የወንድማችን ነብስ ከደጋጎች ከነ አብርሃም ጋር ያኑርልን ነብስ ይማር!    ድል ለአማራ ፋኖ! ክብር ለሰማዕታት! ታህሳስ 06/2018 ዓ.ም ዘመቻ ሰማዕታት

አጋልጥ !! ይሔ ሁሉ ፋኖን እና አማራን ሲራገም እና ሲራገጥ የሚውል "አራት እግር አሳማ" ነው ። መሬት ላይ በወታደራዊ ኃይል የተሸነፈው ብልፅግና በማህበራዊ ሚዲያ የፋኖ አመራር ስም ማጥፋት እና አጀንዳ መስጠት ላይ ያሰማራቸው እነዚህ የፌስቡክ ገፆች ናቸው ። የፌስቡክ አካውንቶች ዝርዝር፦ 1. Ethio Mereja 2. ስንቅ 3. ሁሴን ገዳ ከኦሮሚያ 3. Lula Kebede 4. ሀገሬን 5. Sebona Eliyas Tofik 6. Ethio Daily Media 7. ፍቅርተ ይበልጣል 8. Edu Lala 9. Yene Ethiopia 10. Ethio Intercept 11. Ardi Info 12. Meron Tadesse 13. Asmera Press 14. ዲጅታል ኢትዮጵያ 15. Addis Zemen 15. Selam mulugeta 16. ጥቁር አንበሶች 17. Ethio Press 18. Addis view አድስ እይታ 19. Nardos Page 20. Gohe tv ጎህ ቲቪ 21. ወደ ፍቅር ጉዞ ተያይዞ 22. ጎንደር ፋሲለደስ 23. hagere zena 24. የፍቅር መንገድ 25. Fast Mereja ፈጣን መረጃ 26. Solomon Gumba 27. Ethiopiya Adane 28. Sheger press 29. የሰላም ዘብ 30. Melat Bekele 31. Beti Tesfaye 32. Eden Hagose 33. Liya Eshetu 34. Eden Tamerat 35. አማኑኤል አወቀ 36. O U R Raya 37. One Ethiopia 38. Kelemu Taddele 39. ኢትዮፒድያ ዜና 40. Obbo Chidessa  Odda                                41. Sis Press 42. Betty Gullele 43. የበለፀገች ኢትዮጵያ 44.  Ethiopia voice 45. Gullale post 46. Lucy media 47. Maski Bekele 48. Saroon 49. Dz Ethio 50. የኛ info 51. Meri konjoooo 52. Zemed Mekonnen 53. ጧፈኛ 54. Gondar Times 55. ብሌን ሰለሞን 56. Msgei 57. ጉና ክምር ድንጋይ 58. ሰላም ለሃገሬ 59. አቦል መረጃ 60. ሰላም ለኢትዮጵያ 61. Helen Sisay 62. Nafkot Tesema 63. Thomas Jejaw 64. Abiti Ankober 65. ሮዛ ፍቅር 66. Melat Bekele 67. እውነተኛ ፋኖ 68. Wollo Gerado 69. መልህቅ የመረጃ ምንጭ 70. Yordanos Tekeste 71. Ethiopian Insight 72. Hibist Kefyalew 73. Sonan Press 74. Bole Times 75. Assab Ethiopia 76. በጌምድር-ጎንደር 77. Hiwot A Feleke 78. Meles Bisrat 79. Ethio Intercept 80. ብላቴናው ንጉስ 81. Helen Getachew 82. Tesfayehun Seme 83. Amhara Post 84. Beza Kebede 85. Bilen Mesfin 86. ጯሂት ጎርጎራ 87. Selam Alemu 88. ዲጂታል ኢትዮጵያ 89. Sonan press press 90. Pro peace press 91. Eden Nigussie 92. የሸገር ልጆች 93. የመደመር ትውል 94. አርጎባ ወሎ ጀበርቲ 95. ጀበርቲ አርጎባ አገር 96. Meron Tsegaye 97. Selam Adan 98. Medener 99. Mekides Melaku 100. Meri Konjoo 101. Geda Moti 102. ዝምተኛው ንጉስ መደመር 103. Amihara Fano 104. Wubit Seyoum Gashaw 105. አንድ አምሓራ 106. Semira Jamal 107. Tizta Melaku 108. Miser Dagne 109.አገው ነኝ 110. Lasta Agew 111.  Kidist Nega 11. የውብዳር አረጋ 112. Shebelaw Getachew 113 .ዲጂታል ጦቢያ 114. Helen Tesfa 115. ቡሬ ዳሞት ፋኖ 116. Tigist Kefale 117. Tg Love Andebt B Ali 118. እውነታ ሚድያ 119. Ethio press 120. ቀይ ባህር 121. ተዋበች ጎንደር 122. Nigat Nigat 123. አፍሮ ሚድያ 124. Selam Fentie 125. Zemed Mekonen 126. ድጅታል ፋኖ-digital fano 127. ፈጣን መረጃ 128. Dibora Mekonen Atinafu 129. Burie Damot Fano 130. Addis View አድስ እይታ 131. ጎጃሜዋ መቅደስ 132. ብሌን 133. Helina Alebachew 134 .ፀረ ሌባ ፀረ ሌባ 135.GoJam GoJam 136.Dered Der 137.ጣዝማ ማር 138. ኢትዮጵያMekete 139.Endalamawealama 140.Quarite Press 141.Nile Bluile 142.Bekalu Yehuala 143.Yehuala Yehu 144.Mihret Abewa 145.አብዱሮህማን ኢብራሂም 146.ስዩም ይዘንጋው ድንቁ 147.Indo Amhara 148.Amha Mulat 149.Addis Fikrte 150.AlemuTigist 151.Zelalem Sisay 152.Baynesagn Fentie 153.ሀሴት አየለ 154.አባይ ሚዲያ 155.ራያ ራዩማ 156.ወልቃይት ጠገዴ አማራ 157.ጦሳ ሚዲያ 158. Ghone Forces 159. Raya Price ከብልፅግና ገንዘብ የሚከፈላቸው ናቸው ። ሌሎችን ለቅሞ ማጋለጡ ተጠናክሮ ይቀጥላል ። ፍኖተ-አማራ ሚዲያ ወቅታዊና ትኩስ የፋኖ እንቅስቃሴን መረጃን ከግንባር ሁነን በአራቱም ማዕዘን እየሰራን እንገኛለን። ለሁሉም አማራ ተደራሽ እንሆን ዘንድ እየሰራን እንገኛለን የበኩሉዎን አስተዎፆ የቴሌግራም ቻናላችን ጆይን ሸር አድርጉ አድራሻችን👇👇👇👇 ‼️ https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk ‎

አፋብኃ ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴዎድሮስ ዕዝ የ24ስዓት ዘገባ   ____፩ የአረመኔው ሰራዊት አባላት ፋኖን በቡድን መቀላቀላቸውን ቀጥለዋል። የአረመኔው ስርዓት የሚነዛው ተራ ፕሮፓጋንዳ ኃይሉን ከመበተን አልታደገውም በስሁት ምኞት 4 ክላሾች ጋር የሰላም ስምምነት አድርጊያለሁ ብሎ ፕሮፓጋንዳ የሚነዛው የአረመኔው ውሸት ከሞት የማያድናቸው መሆኑን የተገነዘቡ አባላቱ ቀን በቀን እየከዱ ትግሉን እየተቀላቀሉ ሲሆን ቻሌ ቤዛው፣ እናውጋው ላቀ የአድማ ብተና አባልና ማስረሻ ሰው አገኝ ፣ይበልጣል ወርቄ የሚባሉ የአረመኔው ሰራዊት የ32ኛ ክ/ጦር አባላት ከደብረ ኤልያስ ከተማ በመውጣት 206ኛ ኮር 14ኛ ክ/ጦር ቀስተ ደመና ሻለቃን ሲቀላቀሉ አበበ ይበልጣል የተባለ የአድማ ብተና አባል ከደብረ ማርቆስ ከተማ በመውጣት ጅበላ ሙተራ ሻለቃን መቀላቀሉ ታውቋል። በተመሳሳይ የመከላከያ ኦፕሬተሩ በአፋብኃ ምዕራብ ዐማራ ቀጠና ቴዎድሮስ ዕዝ 102ኛ ኮር 33ኛ ክ/ጦርን መቀላቀሉ ታውቋል። ከ59ኛ ክፍለጦር 3ኛ ሻለቃ ወጦ ፋኖን የተቀላቀለው ፍትሀለው ዳኛው  የተባለው የመከላከያ ኦፕሬተሩ እንደተናገረው በአሁኑ ሰዓት ራሱን መከላከያ ብሎ የሚጠራው አሸባሪ ሠራዊት ፋኖን የመቋቋም አቅም እንደሌለው ገልፆ፤ ሁሉም የሠራዊቱ አባላት እየተበተነ ወደ ፋኖ መቀላቀል እንደሚፈልግ አስረድቷል።   ___፪ አውዳሚው ዐማራ ጠል ሥርዓት የተጀመሩ የመንገድ ፕሮጀክቶችን አቋረጠ። አውዳሚው ዐማራ ጠል ሥርዓት በምዕራብ ጎጃም ዞን ቋሪት ወረዳ የተጀመሩ የአስፓልት መንገድ ፕሮጀክቶችን ማቋረጡ ተረጋገጠ። በፌደራል መንገዶች ባለሥልጣን ይሁንታ የተጀመረው የጅጋ_ቋሪት_ዓርብ_ገበያ_ግሽ_ዓባይ_ቲሊሊ የአስፓልት መንገድ ፕሮጀክት በቋሪት ወረዳ የብልጽግና ሹማምንት አደናቃፊነት ተቋርጧል። የውስጥ መረጃዎቻችን እንዳሳወቁት ከኾነ መንገዱ የተቋረጠው የቋሪት ወረዳ ገቢዎች ጽ/ቤት ፕሮጀክቱን ሊከፍል ከሚገባው የግዢ እና የሠራተኛ 2% ግብር በላይ ከዘጠኝ ሚሊዮን ብር በላይ ግብር በመጠየቁ ምክንያት ነው። የጤና፣ የትምህርት፣ የግብርና፣ የማኅበራት፣ ወዘተ. ተቋማትን ዘርፎ እና አውድሞ እየጨረሰ ያለው የብልጽግና ሥርዓት አሁን ደግሞ የሕዝቡን ዐይን ይከፍታል ተብሎ ተስፋ የተጣለበትን የአስፓልት መንገድ ፕሮጀክት አቋርጧል። የዐማራን ሕይወት እና የመልማት ተስፋ እየነጠቀ ያለው አረመኔው መዝባሪ የብልጽግና ሥርዓት ነባር የሕዝብ ተቋማትን ሲያወድም መቆየቱ ይታወሳል። አውዳሚው ዐማራ ጠል ሥርዓት ለአንዴ እና ለመጨረሻ ጊዜ ላይመለስ እስካልተነቀለ ድረስ ሕዝባችን የሚፈልገውን ልማት እና ሰላም ማየት እንደማይችል ተገንዝቦ ትግሉን በነበረ ግለቱ ለማስቀጠል ይበልጥ መበርታት እንደሚያስፈልግ የቋሪት ወረዳ ጊዜያዊ መንግሥት አሳስቧል። አዲስ ትውልድ፣አዲስአስተሳሰብ፣አዲስ ተስፋ!   ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን ! አፋብኃ| ቴወድሮስ ዕዝ ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ            ታህሳስ 06/2018 ዓ.ም

የእነማይ ወረዳ ጊ/መንግስት ደጀኑ ህዝባችን ጋር መክሯል።             ታህሳስ 6/2018 ዓ.ም የአማራ ፋኖ ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴወድሮስ ዕዝ 201ኛ ኮር 64ኛ ክፍለ ጦር የእነማይ ወረዳ ጊ/መንግሰት ታህሳስ 05/2018 ዓ.ም በእነማይ ወረዳ ሰቀላ ጉመር ቀበሌ ህዝባዊ ውይይት አካሂዶል። በእነማይ ወረዳ ሰቀላ ጉመር ቀበሌ የቀበሌ አደረጃጀቶችን በመፈተሽ፣ ድርጅቱ ያለበትን ወቅታዊ ቁመና በማስረዳት፣ የአካባቢ መሰረተ ልማት፣ የቀበሌ ፍርድ ሸንጎ አሰራርን እና የቀበሌ ፀጥታ ጉዳይ በተመለከተ ሰፊ ውይይት በማድርግ በስብሰባ መድርኩ ለተገኙ ደጀኑ ሕዝባችን ወቅቱን ያማከለ የፖለቲካ ግንዛቤ ሰጥተዋል። አዲስ ትውልድ ፣ አዲስ አስተሳሰብ፣ አዲስ ተስፋ !                 ታህሳስ 06/2018 ዓ.ም አፋብሃ ቴወድሮስ ዕዝ 201ኛ ኮር 64ኛ ክ/ጦር ሕዝብ ግንኙነት

አሁናዊ የወለጋ ሁኔታ!!! በተደጋጋሚ ጊዜ የአብይ አህመድ ወንበር ጠባቂ እና ጨፍጫፊው የብልፅግና መከላከያ ሰራዊት በነ ሽመልስ አብዲሳ ቀጥታ ትዛዝ ወለጋ የሚኖረውን የአማራ ማህበረሰብ ሲጨፈጭፍ ቆይቷል፡፡ በዚህ አንድ ወር ውስጥ ብቻ ለ8ኛ ጊዜ በድሮን ጭምር የታገዘ ውጊያ አድርጎ የፋኖን ምት መቋቋም ሲያቀተው ወለጋ ውስጥ ያለውን አማራ እንደፈለኩ መጨፍጨፍ አልቻለኩም  ከአቅሜ በላይ ነው በማለት ለላኪዎቹ  ምላሽ  ይሰጣል፡፡ አማራን ከምድረ ገፅ የማጥፋት አጀንዳቸውን ሊያስፈፅምላቸው  ባለመቻሉ  ልዚሁ ፕሮጀከት ማስፈፀሚያንት  ሲባል በገፍ ሲያሰለጥኑት እና ሲያሰታጥቁት የኖሩትን ብዛቱ ከ 5700 በላይ የሚሆን የኦሮሚያ ልዩ ኃይል፣ ገዳ ኮማንዶ፣  ጋቸና ሲርና እና ሚሊሻን በማጣመር   ዘመናዊ መሳሪያ በማስታጠቅ በገፍ ወደ ወለጋ ገባ፡፡ ይህ ፀረ አማራ ጨፍጫፊ ኃይል ወለጋ ምድር እንደገባ በቀጥታ የአማራ ማህበረሰብ በብዛት ወደ ሚኖርባቸው ወረዳዎች ዘልቆ በመግባት ከኋላ የብልጽግና መከላከያ ሰራዊት ዙ-23 ጨምሮ በከባድ መሳሪያ ሽፋን እየሰጠ አማራን መግደል ሲጀምር የህልውና ታጋዩ ፋኖ የመጣውን ኃይል በጀብደኚነት በመመከት ሙትና ቁስለኛ በማደረግ ድል ተጎናጽፏል፡፡ ኪራሙ ወረዳ የገባው የጠላት ኃይል በሻለቃ ሀብታም ጥላሁን የሚመራው በጀብደኛው ይበልጣል መኮነን አዲስ አለም ክፍለ ጦር 2 ሻለቆችን ብቻ በማሳተፍ 160 በላይ የጠላት ኃይል የተደመሰሰ ሲሆን እድል የቀናው እጅ በመስጠት እና በመማረክ ህይወቱን አትርፏል፡፡ ሲቡ ሲሬ ወረዳ የገባው የጠላት ኃይል በሻለቃ አለፈ ሽባባው በሚመራው ጌጤ ግርማ መብረቅ ክፍለ ጦር በስሩ በሚገኙት በአርበኛ በላይ የምትመራው አስር አለቃ ይርጋ እንዳለው  ብሶት ሻለቃ፣ በዘላለም አማረ የምትመራው ታዱ አንተነህ አንድነት ሻለቃ፣በተስፋይ የሻምበል የምትመራው ምስጋን ስራየ ነበልባል ሻለቃ በሰሩት ጀብድ ከ60 በላይ ጠላት የተደመሰሰ ሲሆን 35 ገዳ ኮማነዶ ተማርኳል፡፡ ጊዳ አያና ወረዳ የገባው ኃይል እንዲሁ የፋኖን ውጊያ መቋቋም ሲያቅተው እዶዴ ዲቾ ቀበሌ አሊ ከተማ ላይ ንፁሃንን ባሰቃቂ ሁኔታ ገድሏል፡፡ አሁን ላይ የገባው ኃይል በፋኖ በመመታቱ ተጨማሪ ኃይል  ከነቀምት ከተማ ወደ ሁሉም ወረዳዎች በማሰገባት ላይ የገኛል፡፡ ላንጨርስ አልጀመርንም!!! ድል ለአማራ ፋኖ!!!

የመከላከያ ኦፕሬተሩ ፋኖን ተቀላቅሏል ═══════════❁✿❁════════════ (ታኅሣስ 06/2018 ዓ.ም፣ 33ኛ ክ/ጦር ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ) የመከላከያ ኦፕሬተሩ በአፋብኃ ምዕራብ ዐማራ ቀጠ
+1
የመከላከያ ኦፕሬተሩ ፋኖን ተቀላቅሏል ═══════════❁✿❁════════════ (ታኅሣስ 06/2018 ዓ.ም፣ 33ኛ ክ/ጦር ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ) የመከላከያ ኦፕሬተሩ በአፋብኃ ምዕራብ ዐማራ ቀጠና ቴዎድሮስ ዕዝ 102ኛ ኮር 33ኛ ክ/ጦርን መቀላቀል ታወቀ። ከ59ኛ ክፍለጦር 3ኛ ሻለቃ ወጦ ፋኖን የተቀላቀለው ፍትሀለው ዳኛው የተባለው የመከላከያ ኦፕሬተሩ እንደተናገረው በአሁኑ ሰዓት ራሱን መከላከያ ብሎ የሚጠራው አሸባሪ ሠራዊት ፋኖን የመቋቋም አቅም እንደሌለው ገልፆ፤ ሁሉም የሠራዊቱ አባላት እየተበተነ ወደ ፋኖ መቀላቀል እንደሚፈልግ አስረድቷል። ▶ አዲስ ትውልድ ▶ አዲስ አስተሳሰብ ▶ አዲስ ተስፋ

የደጋው መብረቅ ኮር አሃዶች በጥምረት እያደረጉት ባለው ተጋድሎ ድል ማስመዝገባቸውን ቀጥለዋል:: አፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ሚኒሊክ ዕዝ የደጋው መብረቅ ኮር ታህሳስ 6/2018 ዓ/ም በተለያዩ ወረዳዎች ላይ ፅናት ክፍለ ጦር እና ሰንጥቅ ክፍለ ጦሮች ከጥላት ጋር ባደረጉት አውደ ውጊያ የጥላትን ሰራዊት አከርካሪውን በመስበር ድላቸውን አጠናክረው አስቀጥለዋል:: ፅናት ክፍለ ጦር በተሪ ተራራዎች ላይ በደፈጣ የብርሀኑን ጁላ ሰራዊትን ዶግ አመድ ሲያደርጉት፤ በዳውንት ወረዳ ሰንጥቅ ክፍለ ጦር ጋግቢያ በረሀ ላይ ውሀ ውሀ ያሰኜ ጠንካራ ጥቃትን በጥላት ጥምር ሰራዊት ላይ ፈፅመዋል። ሁለቱ ክፍለ ጦሮች በተለያዩ ቦታዎች በአንድ አስትንፋስ በጥላት ሰራዊት ላይ ባደረሱት የማጥቃት እርምጃ የአብይ አህመድን ድፋታን ከማተርቦሽ  ባሻገር  በርካታ ቁሳዊና አካላዊ ጉዳትን በማስተናገድ እፍረትንና ሽፈትን ተከናንቦ ወዴ መወሸቂያ ካፑ እንዲፈረጥጥ ማድረግ ተችሏል። መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልዉና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል! ህልዉናችን በተባበረ ክንዳችን! የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል (አፋብኃ) የደጋው መብረቅ ኮር ህ/ግ ክፍል ታህሳስ 6/2018 ዓ.ም

የአፋብኃ ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ አፄ ዘራዓ ያዕቆብ ፩ኛ ኮር ሰባት ለሰባ ክፍለጦር ለተከታታይ ሶስት ቀናት በወሰደ ውይይት የክፍለጦሩን አመራሮች የማተካካት ስራ ሰራ!! የአማራን ሕዝብ ከምድረ ገፅ ለማጥፋት ወደ አማራ ክልል የገባው የዐቢይ አሕመድ ዙፋን አስጠባቂ ሠራዊት አሁንም በአማራ ምድር እየተቀበረ ይገኛል። መውጣት እንደ መግባት ቀላል ያልሆነለት የኦሮሙማው ብልፅግና መራሽ የጥፋት ሠራዊት "ሰማዩም ምድሩም የእኔ ነው" በማለት ለአማራ ሕዝብ እልቂትን ደግሶ ከመጣ እነሆ 3 ዓመታትን አስቆጥሯል። ሁኖም የዓፄ ዘርዓ ያዕቆብ ፩ ኮር የሰባት ለሰባ ክፍለ ጦር በስሩ ያሉትን  ሻለቃዎች ከበፊቱ በጠነከረና በተሻለ መንገድ ትግሉን ከፋ በማድርግ የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ደቡብ አማራ ቀጠና  የአሳምነው ዕዝ ምክትል አዛዥ ለሎጅስቲክ መምሪያ ኃላፊ ሻለቃ ሞገስ፣የአሳምነው ዕዝ ምክትል ፖለቲካ ዘርፍ ሀላፊ አርበኛ ኤፍሬም ባዩ፣ የአሳምን ዕዝ ምክትል የሰው ሀብት አስተዳደር መምሪያ ሀላፊ አርበኛ ተፈሪ ወንዶሰን እና የዓፄ ዘርዓ ያዕቆብ ፩ኛ ኮር ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት የፖለቲካ እና የትጥቅ  ትግሉን በሚመጥን መልኩ የመዋቅር ሪፎርም  ለተከታታይ ሶስት ቀናት  ጥልቅ ግምገማ በማድርግ የተወሰኑ የክፍለጦሩ አመራሮችን በማንሳት እና የሚቀጥሉትን በነበሩበት እንዲቀጥሉ በማድረግ ሪፎርም ተሰርቷል ። በዚህም መሰርት 1.ዋና መሪ =አርበኛ አረጋ ሙሉነህ 2.ወታደራዊ አዛዥ=አርበኛ ጌታሁን ሻረው 3.ም/አዛዥ ለኦፕሬሽን=አርበኛ መላኩ ምኒል 4.ዘመቻ : አርበኛ ነጋ ንጉሴ 5.ም/አዛዥ ለሎጀስቲክ=አርበኛ ዘመድ ማንደፍሮ 6.ድርጅት ጉዳይ =አርበኛ እሸቱ በቀለ 7.ፕርሰኔል=አርበኛ ኤፍሬም እሸቴ እና ሌሎች አመራሮች በነበሩበት እንዲቀጥሉ ተደርጓል። በዚህ መሠረት የተመረጡ የክፍለ ጦር የሥራ ኃላፊዎችም በበላይ አመራሮችና በአባላት ፊት ቀርበው ቃለ መኃላ የፈፀሙ ሲሆን በአዲስ ወኔና መንፈስ ተሞልተው በታማኝነትና በቁርጠኝነት የኅልውና ትግሉን እንደሚያስቀጥሉ ዝግጁነታቸውን ገልፀዋል። በመጠርሻም አማራ ጠሉን የአብይ አህመድ አረመኔያዊ ስርዓት በተባበረ ክንዳችን አብርን በአንድነት እንመክራለን፣እንወያያለን፣እንደራጃለን፣እናቅዳለን፣ጠላትን በገባበት ገብተን ድባቅ እንመታለን። መረጃው የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ የዓፄ ዘርዓ ያዕቆብ ፩ኛ ኮር ህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አማር ታዘዘ ነው። " ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን" ‎አፋብኃ ደቡብ  አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ የህዝብ ግንኙነት ዜና ክፍል" ‎      ታህሳስ 06/ዐ4/2018 ዓ.ም

ልጅ እያሱ ኮር 23ኛ ክፍለ ጦር አምባሰል ዙሪያ ተጋድሎ በማድረግ ድል አደረገች:: ምኒልክ ዕዝ ልጅ እያሱ ኮር 23 ክፍለ ጦር ታህሳስ 5/2018 ዓ/ም ማለትም በትናትናዉ እለት አምባሰል አባላ ተራራ ላይ ሰፍሮ ያለውን የጥላት ሃይል ድባቅ በመምታት ድል አደረገች። ልጅ እያሱ ኮር 23ኛ ክፍለጦር ደቡብ ወሎ አምባሰል ጅጎዶ አባላ ተራራ ላይ ሰፍሮ የነበረዉ የብልፅግና አራዊት ሰራዊት ጋር ብርቱ ፍልሚያ እያደረጉአይቀጡ ቅጣት እየቀጡት ይገኛሉ። አሁንም ዛሬ ታህሳስ 6/2018 ዓ/ም አድማሱን በማስፍት ዉጊያው እንደቀጠለ ሲሆን አባላ ተራራ እና ጊሸን ማርያም ገዳም መሽጎ የነበረዉ የአገዛዙ ሰራዊት ወደ ተለያየን እና ዚሀ ጥቁር አስፓልት ወርዶ እየተንቀሳቀሰ በነበረበት ጊዜ 23ኛ ክፍለ ጦር መብረቃዊ ጥቃት በመክፈት ድባቅ እየመታችዉ ትገኛለች።   አናብስቶቹ 23 ክፍለ ጦሮች ከደሴ ደላንታ የሚወስደዉን ጥቁር አስፍልት በመዝጋት ዉጊያ እያደረገች ሲሆን አሁንም ከስከ ተሪ ያለዉን ቀጠና በመሸፈን ዙፋን ጠባቂ ሰራዊቱን መዉጫ መግቢያ በማሳጣትና ሃይል እንዳይጨመረው በማድረግ ቁጥሩ በዉል ያልታወቀ ሙት እና ቁስለኛ በማድረግ ድል ተጎናፅፈዋል:: መዳረሻዉ ድል እና ነፃነት የሆነዉ የአማራ ህዝብ የህልዉና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል! ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን! አፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ የልጅ እያሱ ኮር ህዝብ ግንኙነት ክፍል ታህሳስ 6 ቀን 2018 ዓ.ም

ከደብረ ታቦር ወሮታ ያለው መስመር ለ10 ቀናት ዝግ እንደሚሆን ተገለፀ አፋብሀ በላይ እዝ ሜጄር ጄኔራል ውባንተ አባተ ክፍለጦር ከወሮታ ደብረ ታቦር ያለው መንገድ ከነገ ጀምሮ ለተሽከርካሪ ዝግ እንደሚሆን አስታውቋል። በላይ እዝ ያወጀውን ሌባን እና ወንጀለኛን የማፅዳት ስራ ለማከናወን ያስችል ዘንድ ነው የመንገድ መዝጋቱ የተላለፈው። በፋኖ ስም ተደራጅተው ህዝብ እያስመረሩ ያሉ ወንጀለኞችን እስክናፀዳ ህዝባችን በትግስት ይጠብቀን ሲል የክፍለ ጦሩ ህዝብ ግንኙነት መምሪያ አስታውቋል። ተሽከርካሪዎች ራሳቸውን ከጉዳት ለመከላከል የ እንቅስቃሴ ገደቡን እንዲያከብሩ ተጠይቋል።

ኢሄ ምርኮኛ የኦሮሚያ ልዩ ሀይል እዛው ኦሮሚያ ወለጋ ላይ የተማረከ የሽመልስ አብዲሳ ጥሬስጋ ተቀላቢ ወታደር ነው። በቢዛሞ ፋኖ ተማርኮ እየተማፀነ ነው። ምን ብሎ እየተማፀነ ይመስላችኋል እስኪ ገምቱ
ኢሄ ምርኮኛ የኦሮሚያ ልዩ ሀይል እዛው ኦሮሚያ ወለጋ ላይ የተማረከ የሽመልስ አብዲሳ ጥሬስጋ ተቀላቢ ወታደር ነው። በቢዛሞ ፋኖ ተማርኮ እየተማፀነ ነው። ምን ብሎ እየተማፀነ ይመስላችኋል እስኪ ገምቱ!?

ይህ ፎቶ ለእውነተኛ አማራ ትልቅ ደስታ ነው የወሎ ፈርጦች ❤ ኮሎኔል ፈንታው ሙሀባ (የአፋሕድ ም/ሊቀመንበር እና ወታደራዊ አዛዥ እንድሁም የወሎ ጠቅላይ ግዛት ዕዝ አዛዥ) ኮሎኔል ፈንታው መኩዬ (የ
ይህ ፎቶ ለእውነተኛ አማራ ትልቅ ደስታ ነው የወሎ ፈርጦች ❤ ኮሎኔል ፈንታው ሙሀባ (የአፋሕድ ም/ሊቀመንበር እና ወታደራዊ አዛዥ እንድሁም የወሎ ጠቅላይ ግዛት ዕዝ አዛዥ) ኮሎኔል ፈንታው መኩዬ (የአፋብኃ ምኒልክ ዕዝ ዘመቻ መምሪያ ም/ኃላፊ) ሻለቃ ክንዱ ሰውነት (የምኒልክ ዕዝ ወታደራዊ ባለሙያ) መቶ አለቃ ታደሰ አስፋው (የምኒልክ ዕዝ ሜካናይዝ ኃይል አሰልጣኝ) በላይነህ ሰጥአድርጌ እኛ አማሮች የፋኖ ታጋይ ወሰን ፣ ድርጅት ፣ ጎጥ ፣ ሀይማኖት ፣ ጾታ ሳይለይ አንድ እንዲሆን ተቀራርቦ እንዲሰራ እርስ በርስ እንዳይተኳኮስ ምኞታቸን ነበር ያ ሆኖ ስላየነው ደስ ብሎናል ደስ ይበላችሁ ፖለቲከኛ ቢገፋፋ ቢጨቃጨቅ ግድ የለም ጠመንጃ ያነገተ ታጋይ ግን ልዬነት ከፈጠረ ብዙ ነብስ ስለምናጣ መቀራረባቸው ግድ ይለን ነበር በዚህ ፎቶ አንጀትህ የሚያር ካለህ አንተ አማራ አይደለህም እና መልካም የመቃጠል ዘመን ይሁንልህ ገና መከታው እና ምሬ በአንድ ተቀምጠው እናያለን ገና እስክንድር እና ዘመነ ተቀራርበው ሲሰሩ እናያለን ደረጀ እና ደሳለኝ በአንድ መአድ ሲቋደሱ እንመለከታለን ሀብቴ እና ዝናቡ በአንድ ላይ እንመለከታቸዋለነሰ በቅርቡ ጀነራል ተፈራ እና ኮረኔል ፈንታው እናያቸዋለን ይህ የንጹህ አማራ ምኞት ነው ከመሀል የሚራገፍ ካለ እየተንጠባጠበ ይቀራል አንድነት የሚፈልጎ እስከ ቀራኒዎ ይዘልቃል ይሄው ነው አማራነት ያሸንፋል ❗️

የንግድ ባንክ ዲጅታል መታወቂያ እና የአብቁተ ብድር ማስመለስ እንቅስቃሴን በተመለከተ ከአፋብኃ ምራብ አማራ ቀጠና ቲዎድሮስ ዕዝ የተሰጠ መግለጫ። አረመኔው አገዛዝ በፈጠረው የሕዝባችን ደካማ ጎን ስም በድጋሚ ተቋማዊ ጅምላ ግድያ (genocide ) እንዲፈጸም አንፈቅድም!! ።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።። የአማራ ሕዝብ እያደረገ ያለው ትግል ሁለንተናዊ የህልውና ትግል ነው። ሁለንተናዊ የህልውና ትግል ላይ ነው ስንል በሐይወት ከመኖርና ካለመኖር የህልውና ፈተና በተጨማሪ ኢኮኖሚያዊ፣ፖለቲካዊ፣ማህበራዊ፣ባሕላዊና አቻ  ነፍስያወቹም የህልውና ፈተና ውስጥ ወደቀዋል  ማለታችን ነው። ሕዝባችን የደረሰበት ኢኮኖሚያዊ የህልውና ፈተና ከእጅ ወደ አፍ  አገዛዛዊ የአኗኗር ዘይቤው ተስፈንጥሮ በልኩ ይለማባቸውና ነገውን ታሳቢ ያደረገ የኢኮኖሚ ቋት ይፈጥርባቸው ዘንድ የሚያስችሉት ደጁ ላይ ያሉ ፀጋወቹን ሆን ተብለው እንዳያዘመንም እንዳይጠቀምም በተሰራ ስርዓት ወልድ የፖሊሲ ትግበራ ነው። ከዚህ የኢኮኖሚ ስብራት ሊያወጡት የሚገባቸው አንድም በያንዳንዱ ሕዝባችን ቅሪት ሁለትም በሕዝባችን ባድማ ላይ የተቋቋሙ የኢኮኖሚ ተቋማትም አፈጣጠራቸው አገዛዛዊ በመሆናቸው እና አላማቸውም የአገዛዙን ስትራቴጅክ ግብ ማሳካት እንደመሆኑ መጠን የአማራ ሕዝብ  የአገዛዙ ህገ መንግስታዊ  ጠላት ተደርጎ የተሳለ ስትራቴጅካሊ እንዲጠፋ እየተደረገ ያለ ሕዝብ በመሆኑ እስካሁን በኢትዮጵያ ምድር ላይ የተቋቋሙ የኢኮኖሚ ተቋማት ሁሉ አገዛዙ እኛኑ የሚያጠፋበትን ስልት በአስቻይነት ሲደግፉ የኖሩ የአገዛዙ ማስፈጸሚያ በትሮች ሆነው ኖረዋል ብለን እናምናለን። ከነዚህ የኢኮኖሚ ተቋማት መካከልም የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና የአማራ ብድርና ቁጠባ ተቋም (አብቁተ)ወይም ፀደይ ባንክ ይገኙበታል። እንደ ፋኖ  እነዚ ተቋማት የአገዛዙ  የእጅ ስራወችና የእቅዱም ማስፈጸሚያወች እንደሆኑ ብናምንም እስካሁን በምናደርገው የህልውና ተጋድሎ ውስጥ  የትግላችን ዋና ተተኳሪ ጠላት እራሱ አገዛዙ ነው ብለን ስለምናምን የነዚህን ተቋማት ከአቢወቱ ያፈነገጠ እንቅስቃሴ ከመታገስ ልዩ ስነ ምግባርን የተላበሰ  ጥበቃና ከለላ እያደረግን የቆየን መሆኑ እራሳቸው ተቋማቱና ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ህያው ምስክሮች ናቼው ። ይሁንጅ በስም የጠቀስናቸው ሁለቱ የኢኮኖሚ ተቋማት እንዲሁም ሌሎች ባንኮች በዚህ ሳምንት :- 1ኛ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ድጂታል መታወቂያ ያልያዘ የባንኩ ደንበኛ መሆን ስለማይቻል ሁላችሁም ወደ ድጂታል መታወቂያ ሲስተም መግባት አለባችሁ በሚል አገዛዙን በስሙ ደብቆ በይፋ የአገዛዙን እኩይና የቀጣይ መጨፍጨፊያ  አላማ ለማስፈጸም በእንቅስቃሴ ላይ እንዳለ ከተቋሙ የቀኘ አባሎቻችን  ለማወቅ ችለናል። 2 አብቁተ(ፀደይ ባንክ)ሕዝባችን ከዚ በፊት የወሰዳችሁትን ብድር  አለና መልሱ በማለት በአረመኔው አብይ አሕመድ ከማምረት ታግዶ 3 ዓመት የሞላውንና በድሮን፣ በመድፍና ታንክ መካክል ያመረታትን  ሆን ተብሎ በቡድን መሳሪያ እየተቃጠለበት ቤተሰቡን ያጎርስ ያለብስበት አጥቶ ቆዝሞ የሚገኘውን ሕዝባችን ተጨማሪ ሰቀቀን ይዞ በየደጁ ለመዞር በዝግጅት ላይ እንዳለ ከውስጥ አርበኞቻችን(ቀኘ) ለመረዳት ችለናል። በመሆኑም የኢትዮጵያ ንግድ ባንክም ሆነ አብቁተ(ፀደይ ባንክ) እንዲሁም ይህን ድርጊት ለመፈጸም በእንቅስቃሴ ላይ ያላችሁ መሰል የኢኮኖሚ ተቋማ እና ሁሉም ባንኮች ከዚ  ድርጊታችሁ ባስቸኳይ እንድታቆሙ እያሳሰብን በተዋረድ ለምትገኙ አመራሮቻችንም ይህን ድርጊት ማስፈጸም ፈጽሞ የተከለከለ መሆኑን እንገልጻለን። መላው ሕዝባችን ከእንዲህ አይነት እንቅስቃሴ እራሱን እንዲጠብቅ በዚሁ አጋጣሚ ማሳሰብ እንወዳለን። ሁሉም ባንኮችና የኢኮኖሚ ተቋማት ከዛሬ ጀምሮ ከዚ ድርጊታችሁ የማትታቀቡ ከሆነ ማንኛውንም ተቋማዊ እርምጃ ለመውሰድ የምንገደድ መሆኑንም በጥብቅ እናሳስባለን!!! አዲስ ትውልድ አዲስ አስተሳሰብ አዲስ ተስፋ !! በአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴዎድሮስ ዕዝ ታህሣሥ 06 / 2018 ዓ.ም

#የኢትዮጵያ_ሕዝብ_እውነቱን_ያውቀዋል #ተሸናፊው_አገዛዙ_አልቆለታል።ከፈለገ ቅንብር ነው ይላል።የጨነቀለት የታባክ በፌስቡክ አንደኛ ናችሁ ወንድ አጠገብ ስትደርስ "መንግስት አስገድዶን ነው የመጣነው"
#የኢትዮጵያ_ሕዝብ_እውነቱን_ያውቀዋል #ተሸናፊው_አገዛዙ_አልቆለታል።ከፈለገ ቅንብር ነው ይላል።የጨነቀለት የታባክ በፌስቡክ አንደኛ ናችሁ ወንድ አጠገብ ስትደርስ "መንግስት አስገድዶን ነው የመጣነው" ትላላችሁ😁አልቃሻ ብቻ😁ልክ ለልክ እንተዋወቃለን።ባንክም ታንክም በእጃችሁ ነው። እኛ እየተራብን ምንም የለንም ባዶ እጃችን ነን።ዘንድሮ በቀላል አንፋታም ወንድና ወንድ መሳይ ይለይልናል።

#ከልካይ የሌለበት  የብል*ና ኤጀንቶች ስውር እጅ????# የፋኖ   የመረጃ፣ የስንቅና ትጥቅ ዋና ሀብቱ የወጣበት ማህበረሰብ መሆኑ ግልጽ ነው። ፋኖም የሚታገለው #ለዚሁ ማህበረሰብ ነውና። ነገር ግን ከዚህ# መሰረታዊ መርህ ባፈነገጠ መልኩ ህዝብን የሚያማርሩ፣ የሚሳደቡ ፣የሚደበድቡ፤ መኪና አስቁመው ይህን ያህል ክፈሉ የሚሉ  ሰወች በዝተዋልና _በላ ቢበጅበት። ችላ ከተባለ ግን ፋኖ ነን እያሉ ሲዘረፋ ቆይተው። በመጨረሻ ወደ ጠላት መግባታቸው አይቀርም ።     ለጠላት መረጃ የሚሆኑትም እንደነዚህ አይነት #ንዋይ አምላኪዎች ናቸውና  መፍትሔ ቢሰጠው። ስሞኑን በቴዎድሮስ እዝ #ማንኩሳ አካባቢ  82 ዓመት ሽማግሌን ጨምሮ ሌሎችንም ተሳፋሪዎች _ሁለት ሽህ  ብር አምጡ ተብለው መከራቸውን አሳይተዋቸዋል። ለአብነት ይሄን አነሳሁ እንጅ በዙ በታዎች #በአምስቱም እዞች ችግሮች ያሉ ቢሆንም በቴዎድሮስ እዝ ና በበላይ እዝ ጎልተው ታይተዋል።ይህ ስል ግን ህዝቡ ማገዝ የለበትም ማለቴ አይደለም_አቅምን ያማከለ ፤ ለሠራዊቱ በሚድረስና በደረሰኝ ቢሆን ለማለት እንጅ       # የዚህ አይነት ዘረፋ ዋናአላማ 1) ህዝብን በማማረር  አማራጭ ማሳጣት እና የድሮው ብአዴን ይሻለኛል እንዲል ፤ 2)ፋኖ ብልጽግና እንደ ሚለው # ለዘረፋ  የተሰባሰበ እንጂ አላማ የለውም እንዲባል፤በዚህ ቀዳዳ ገብቶ ህዝብ ሊሸውድ ወይም ፕሮፓጋንዳ ለመስራት 3)እውነተኛ ታጋዮችም በእነዚህ #ሌቦች ምክንያት ሞራላቸው እንዲላሽቅና ከትግል እንዲወጡ። እነዚህን እና መሰል ቁማሮችን ለማድረግ ነውና እንደነዚህ አይነት #ተኩላወችን  የዘረፋ ሰንሰለታቸውን መበጠስ እና የእርምት እርምጃ መውሰድ ቢቻል። ይህ ካልሆነ ግን የዘረፉትን ገንዘብ ይዘው :-አላማ የሌለው ጦርነትን ነው፤ ሰላምና ይሻለናል፤ ፋኖ በዘረፋ ተሰማርቷል  ማለታቸው አይቀርምና #ለጠላት ማጭበርበሪያ ሳይሆኑ በጊዜ ተለቅመው ቢታረሙ። #(ለሚመለከተው ቢደርስ ለፋኖ ትልቅ ክፍተት ነው።)

ደጃዝማች 4ኛ ኮር ጠላትን ደመሰሰ!!   በመተማ ወረዳ መሸሃ ቀበሌ የቁም ምሽግ ሰርቶ ህዝብ ሲያንገላታና ሲዘርፍ የሰነበተው የጠላት 78ኛ ክ/ጦር አካል ሬጅመንቶች ተደምስሰዋል።     ታህሳስ 05/2018 ዓ.ም በልዩ ወታደራዊ ዕቅድ የማጥቃት ውጊያ የከፈተው ልማደኛው በላይ ዕዝ ደጃዝማች ፬ኛ ኮር ጎቤ ክ/ጦር ፣አርበኞች ክ/ጦርና ረመጡ ደጀን ክ/ጦሮች የተወጣጣ ደምሳሽ ፈጣን ተወርዋሪ ኃይል ጠላት የመሸገባቸውን ከፍተኛ ቦታዎች በመዝለቅ ከንጋቱ 12:00 ሰዓት እስከ ቀኑ 10:00 ሰዓት ከባድ የጨበጣ ውጊያ በማድረግ ጠላትን የደመሰሰ ሲሆን ከመተማ ተነስቶ በነጋ ውኃ አድርጎ መሸሃ በመድረስ የውጊያ ድጋፍ ለማድረግ ከምዕራብ ወደ ሰሜን ምስራቅ አቅጣጫ የተንበሳቀሰው ጠላት በደጃዝማች 4ኛ ኮር አጣናው ዋሴ ክ/ጦር ምት ደርሶበት ተልዕኮው እንዲከሽፍበት ተደረገ። ከምዕ/አርማጭሆ አብርሃ ጅራ በመነሳት መሸሃ ደርሶ ከድምሰሳ ሊታደግ የተንቀሳቀሰው የዓብይ ፋሽስት ሰራዊት ቀድሞ ስምሪት በተሰጣቸው በደጃዝማች 4ኛ ኮር ዘራይ ክ/ጦርና ተከዜ ክ/ጦሮቻችን መተላለፊያ መንገዱ በእሳት መታጠሩን በማረጋገጥ መሸሃ ለተከበበው ጠላት ሊደርስለት አልቻለም ሁሉም መንገዶች የገሞራ ባህር ተደርገዋል።   በቀበሮ ጉድጓዱ ተወሽቆ የሰው ሀይሉንና የመሳሪያ ክምችቱን ተጠቅሞ እጅግ ከፍተኛ ቋሚ መከላከል ሲሞክር ቢውልም ልማደኞቹ  በክላሽና በስናይፐር ግንባር እየነደሉ በጨበጣ በቦምብ እያቃጠሉ በሳንጃ  እየተረተሩ የተማመነበትን ምሽግ በመስበር በወርቅ ቀለም የሚከተብ እጅግ አኩሪ የጀብዱ ታሪክ ፅፈዋል። የጠላት 78ኛ ክ/ጦር ሁለት ሻለቀ ጦር ሙሉ በሙሉ ተደምስሷል። *253 የተደመሰሰ ጠላት *58  የቆሰለ *55   እጅ የሰጠ የተማረከ *83 የተማረከ ክላሽ * 02 የተማረከ ብሬን * 1 ድሽቃ *15 ሽህ ልዩ ልዩ ተተኳሽ ጥይት ተማርኳል። በማጥራትና ማብቃት ተሞርዶ የተሰናዳው ደጃዝማች 4ኛ ኮር በመተማና አርማጭሆ የነበረውን ጠላት እያፈረሰው ይገኛል።       ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!!    አፋብኃ ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዘለቀ ዕዝ          ታህሳስ 06/2018 ዓ.ም

ገሞራው አማራ እንዲህ ይናገራል!! አንድ አማራ ለሁሉም አማራ፣ ሁሉም አማራ ለአንድ አማራ፣ አይበገሬው ትውልድ ያሸንፋል ስንል 100% በመተማመን ነው። ነፍራቃውን እና ለዓላማው ያልታመነውን ሁሉ እየጠረግነው እንጓዛለን🙏🙏 በታሪክ አጋጣሚ ከ50 ዓመት በሗላ የተሰባሰበው ሃይላችን የህዝባችን የመኖር መብት ሳይረጋገጥ የሚያስቆመው ምን ዓይነት ምድራዊ ሃይሌ እንደሌለም የተረጋገጠ ሃቅ ነው!!