ፍኖተ- አማራ ሚዲያ (Finote- Amhara ) Midea
前往频道在 Telegram
የተመሠረተው የአማራን ሕዝብ ለማንቃት፣ ለማደራጀት እና ለማስተባበር ነው። የአማራ ሕዝብን ✅ ፖለቲካዊ ✅ ማህበራዊ ✅ ኢኮኖሚያዊ ታሪካዊ ጥያቄዎችን ለማሰማት እና የአማራን ሕዝብ በማንቃት ሰፊውን ሕዝብ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ይሰራል። ወደዱም ጠሉም የኃላ ታሪካችን በእኛ እጅ ይፃፋል። አማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ( አፋብን)
显示更多2 976
订阅者
+2324 小时
+367 天
+41430 天
帖子存档
የአፋብን ወሎ ቤተ-አማራ ሚኒሊክ ዕዝ 29ኛ ክፍለ ጦር የ3ኛ ዙር ምልምል ፋኖዎችን አስመረቀ!
ሚኒሊክ ዕዝ 105ኛ ኮር ስር የሚገኘው 29ኛ ክፍለ ጦር፣ ለወራት ሲያሰለጥናቸው የቆየውን ምልምል ፋኖዎች ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት ዛሬ በደመቀ ሁኔታ አስመርቋል።
ይህ የ3ኛ ዙር ምልምል ሰልጣኞች ምርቃት ፕሮግራም፣ ከፍተኛ የዕዝ እና የኮር አመራሮች በተገኙበት በታላቅ ወታደራዊ ስነ-ስርዓት ተከናውኗል።
በዚሁ የምርቃት ስነ-ስርዓት ላይ የክብር እንግዳ ሆነው የተገኙት የሚኒሊክ ዕዝ ምክትል የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አርበኛ ኑረዲን አበበ፣ ተመራቂዎቹ ለሕዝብ ህልውና መከበር የሚጠበቅባቸውን ታሪካዊ ኃላፊነት እንዲወጡ አሳስበዋል። የ105ኛ ኮር ዋና ሰብሳቢ አርበኛ ሻለቃ አብነው ታደሰ በበኩላቸው፣ የሰራዊቱ መጠናከር በትግሉ ሂደት ላይ የሚኖረውን ፋይዳ በመግለጽ ስለ ወደፊቱ የትግል አቅጣጫ ሰፊ ገለጻ አድርገዋል።
በምርቃቱ ላይ የዕዝ፣ የኮር እና የክፍለ ጦር ከፍተኛ አመራሮች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ የእድር ዳኞች፣ የጎበዝ አለቆች እንዲሁም የፋኖ ጊዚያዊ መንግስት የቀበሌ አስተዳዳሪዎች ተገኝተዋል። ተጋባዥ እንግዶቹ ስለ ተመራቂዎቹ ብቃትና ስለ ትግሉ ወቅታዊ ሁኔታ በሰፊው የተወያዩ ሲሆን፣ የምርቃት ስነ-ስርዓቱም በተሳካ ሁኔታ ተጠናቋል።
ይህ አዲስ የተመረቀው ኃይል በአሁኑ ወቅት በአማራ ሕዝብ ላይ እየተፈጸመ ያለውን የግፍ ጥቃት ለመመከትና የህልውና ትግሉን ለማፋጠን ትልቅ አቅም እንደሚሆን ተመልክቷል።
ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!
የአፋብን ወሎ ቤተ-አማራ ሚኒሊክ ዕዝ
ሚያዚያ 27 ቀን 2018 ዓ.ም
የመተማ ወረዳ የንግድ ማዕከላት ከአገዛዙ ዘራፊዎች ነፃ መውጣታቸው ተሰማ፤ የፋኖ ኃይሎች በፈጸሙት መብረቃዊ ጥቃት የዘራፊ ቡድኑ ተመትቷል!
በምዕራብ ጎንደር ዞን መተማ ወረዳ ከሱዳን ጋር በሚያዋስኑት አምተኮል፣ አምስት ቁጥር እና አራት ቁጥር ተብለው በሚጠሩ አካባቢዎች ተሰማርቶ የነበረው የአገዛዙ ዘራፊ ቡድን በፋኖ ኃይሎች መመታቱ ታወቀ።
የአፋብን ጎንደር ጠቅላይ ግዛት በላይ ዘለቀ ዕዝ 305ኛ ጎቤ ኮር 76ኛ ክፍለ ጦር ወደ ቀጠናው ዘልቆ በመግባት በፈጸመው ጥቃት፣ በወረዳው አስተዳዳሪ አማካኝነት ተደራጅቶ ሲንቀሳቀስ የነበረውን ዘራፊ ቡድን ብትንትኑን አውጥቶታል።
የዕዙ ምክትል ወታደራዊ አዛዥ አርበኛ እሸቴ አሸብር እንደገለጹት፣ በጥቃቱ ወቅት የዘራፊ ቡድኑ አባላት እጅ ከፍንጅ የተያዙ ሲሆን በዝርፊያ ተግባሩ ላይ እንዲሰማሩ በመተማ ወረዳ አስተዳዳሪ ተልዕኮ እንደተሰጣቸው በምርመራ ወቅት መናገራቸውን አረጋግጠዋል። ከ50 በላይ የሚሆኑት የቡድኑ አባላት ወደ መተማ ወረዳ የፈረጠጡ ሲሆን፣ አገዛዙ "ሰላም አስከባሪ" ብሎ የሚጠራቸው ኃይሎችም በዝርፊያ ወንጀሉ ውስጥ እጃቸው እንዳለበት ከቦታው የሚወጡ መረጃዎች ያመለክታሉ።
ከፍተኛ የንግድ እንቅስቃሴ የሚደረግባትና ለንግድ ማኅበረሰቡ ልዩ ስፍራ የሆነችው አምተኮል፣ ለረጅም ጊዜ በአገዛዙ ታጣቂዎችና በዘራፊዎች እንግልት ሲደርስባት እንደቆየች የአካባቢው ማኅበረሰብ ገልጿል።
የቀጠናው የፋኖ አመራሮች እንደገለጹት፣ የኢንተርኔት አገልግሎት ሲገኝ ስለተከናወነው ኦፕሬሽንና ስለተያዙት ምርኮኞች ሙሉ ማስረጃውን ለሕዝብ ይፋ የሚያደርጉ ይሆናል።
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ሽዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው ዕዝ መሀመድ ቢሆነኝ ኮር እና ዓፄ ዘርዓያቆብ ኮር በጋራ በጠላት ላይ በወሰዱት መብረቃዊ ጥቃት ድል ተቀናጁ!!
ሚያዝያ 28/8/2018 ዓም
የአፋብን ሽዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው ዕዝ ግዙፎቹ ሁለት ኮሮች በቀን 27/08/18/ ዓ.ም በኤፍራታና ግድም ወረዳ በተለያዩ ቦታዎች በዓፄ ዘርያቆብ ኮር በስሩ ያሉ ክ/ጦሮች ውጊያ ማድረጋቸውን በትናትናው በዜና ሠአታችን መዘገባችንይታወቃል። በዚህ አውደውጊያ አድማሡን አሥፍቶ በቀጠለው በአንቦበር ወታጋ ቀበሌ አመጃ ገብርኤል በተባለው ቦታ የመሀመድ ቢሆነኝ ኮር አካል የሆነው ደጅ አዝማች ተሠማ እርገጤ ክ/ጦር አሥማረ ደኜ ሻለቃ ጠላትን ምሽጉ ድረሥ ዘልቀው በመግባት በጣላት ላይ ሠባዊና ቁሣዊ ጉዳት ደርሶበታል። ጠላትም የደረሠበትን ጉዳት መቋቋም ሢያቅተው ከፊት ያለውን ምሽግ ለቆ ሌላ ምሽግ ገንብቶ ይገኛል።
ሆኖም የኦህዴድ ብልፅግና አማራ ጠል ወራሪ ሰራዊትን መንገድ እየመራ የመጣው የአረጋ ከበድ ምስለኔ ሚኒሻና መከላከያ ተደምስሰው ለጅብ እራት መሆናቸው በካራ ለጉማ ናዝሩት በተባለ ቦታ ለይ የአይን እማኞች መረጃ አድርሰውናል። በዚህም በካራ ለጉማ ዱልት ቀበሌ ናዝሩት በተባለ ቦታ ከተደመሰሱ የጠላት ሃይል መካከል
1 . ከአምስት በላይ የመከላከያ አስክሬን በአይን የታየ አንድ ቦታ
2. ተፈራ አበባው ምኒሻ የነበረ በማህበረሰብ የተቀበረ
3. ሃብቴ የተባለ ይቀድሞ ልዩ ሀይል የነበረ አሁን ምኒሻ ጽ/በት ላይ የሰላም አስከባሪ አስተባባሪ የሆነ በማህበረሰብ የተቀበረ
4. ስሙ ያልታወቀ ሚኒሻ ጅብ ግማሽ አካሉን በልቶት የተረፈውን አካል በማህበረሰብ የተቀበረ
5. ሶስት ሚኒሻ ስማቸው ያልታወቀ አጣየ አማኑኤል ቤተ ክርስትያን የተቀበሩ
የአሳምነው ዓናብስቶች ዛሬም ከትናንት ያለ ዕረፍት የአብይ አህመድ አየር ወለድ አራዊት ሰራዊት እና ጥምር ጦር ብሎ የሚጠራውን ኃይል እና የኤፍራታ ግድም ወረዳ ምክትል አስተዳዳሪና ሰላምና ደህንነት ኃላፊ በተለይም በኤፍራታ ግድም ወርዳ ህፃናት በማሰር የብአዴን ስራ አስፈፃሚ ሆኖ የአማራን ህዝብ እያስለቀሰ የሚገኘው ባንዳው ወንድሙ ካሳ ጨምር ያስለቀሰ ውጊያ የነበረ ሲሆን የብአዴን ቅጠረኛ ኃይል በገባበት ገብተው በግንባር ድል እያስመዘገቡ ይገኛሉ።
ክብር ለትግሉ ሰማዕታት!"
ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!"
አፋብን ሸዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው ዕዝ ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ!!
ከጠላት ነፃ በወጡ ቀጠናወች ህዝባዊ ውይይቶች ቀጥለዋል፨
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
...ሚያዚያ 27/2018 ዓ.ም
የአፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 201ኛ ኮር 74ኛ ክ/ጦር አመራሮችና የእነብሴ ሳር ምድር ወረዳ ጊዚያዊ መንግስት አመራሮች በጋራ በቅርቡ ከጠላት ነፃ የወጡ የ013 ዝምብቲት ቀበሌና 011 ድቦ ከተማ ነዋሪዎችን አወያይተዋል።
ጠላት ለወራት ተቀምጦባቸው የነበሩትን ቀጠናዎች ሰሞኑን በተጠና መልኩ ተቀጥቅጦ ከተባረረ በኋላ በተለያዩ ቦታዎች ህዝባዊ መድረኮች እየተካሄዱ ሲሆን በድቦ ከተማና ዝምብቲት ቀበሌም ሰፊ ውይይቶች ተካሂደዋል።
* የአፋብንን አሁናዊ ቁመና ማስገንዘብ
* የወቅቱን ቀጠናዊና አለማቀፋዊ ፖለቲካዊ አሰላለፍ ማስገንዘብ
* የጠላትን ወታደራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ድፕሎማሲያዊ ኪሳራ ማስረዳት እና
* በማህበረሰቡና በፋኖ አባላት መካከል ያሉ ግንኙነቶች መፈተሽ ሲሆን ከማህበረሰቡም አንዳን ጥያቄዎች ተነስተው በአመራሮቹ ምላሽ ተሰጦባቸዋል።
ህዝባችንም ምንግዜም ከጎናችን እንደማይለየንና ትግሉ የጋራ እርብርብ የሚጠይቅ በመሆኑ በገንዘብም በጉልበትም እንደሚያግዝ ቃል በመግባት ውይይቱ ተቋጭቷል።
የአፋብን ቴወድሮስ ዕዝ 201ኛ ኮር 74ኛ ክ/ጦር እነብሴ ሳር ምድር ወረዳ ጊ/መ ሚዲያና ኮምንኬሽን
ቅዱስ ሲኖዶስ የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ከመጥፋት እንዲታደጋት የሰዴ ወረዳ የሐይማኖት አባቶች ጥሪ አቀረቡ።
➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺ ሚያዚያ 27/2018 ዓ.ም
የአብይ አህመድ ጀነራሎች በአደባባይ በሰጡት ትዕዛዝ መሰረት የአገዛዙ ሰራዊት አባላት እና የጦር መኮንኖች በቤተ ክርስቲያኗ ቅጥር ግቢ ምሽግ በማድረግ ልዕልናዋን እንደገፋፏት የሰዴ ወረዳ የሐይማኖት አባቶች ተናግረዋል።
በአማራ ህዝብ ላይ በተፈፀመው ወረራ ቤተ ክርስቲያኗ በቀጥታ ጥቃት እየተፈፀመባት ነው ያሉት የሐይማኖት አባቶች በበኩላቸው ካህናት፣ ቀሳውስት ፣ የአብነት ተማሪዎችና ዲያቆናት እየተገደሉ ስርዓተ ቤተክርስቲያን እየተስተጓጎለ ይገኛል ብለዋል። ከዚህ በፊት በድምቀት የሚከበሩት አመታዊ ሐይማኖታዊ በዓላት የአገዛዙ ሰራዊት በቤተ ክርስቲያኗ ላይ በመመሸጉና የሐይማኖት አባቶችን በማሳደዱ በተለመደው መልኩ ማክበር አለመቻሉንም አስታውቀው፤ ቤተ ክርስቲያኗ ቅርሷ እየተዘረፈ፤ ስርዓቷ እየተገፈፈ፤ አገልጋዮቿ እየተገደሉ በመሆኑ ፀበሉን እንደ ውሀ እየቀድ እየጠጡት ሲሆን ቅዱስ ሲኖዶስ ቤተ ክርስቲያኗን ከመጥፋት እንዲታደጋት ጥሪ አቅርበዋል።
በዚህም 201ኛ ኮር በተደራጀ የፖለቲካ ስራ የአማራ ህዝብ ብሔራዊ ንቃት ይዳብራል፤ ህልውናውም ይረጋገጣል!፥
በሚል መሪ ቃል ሰዴ ወረዳ ከኃይማኖት አባቶች ጋር ውይይት እያደረገ ይገኛል።
አዲስ ትውልድ ! አዲስ አስተሳሰብ! አዲስ ተስፋ
የአፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 201ኛ ኮር የህዝብ ግንኙነት
የUAE አየር ኃይል MAMA-T የተባሉ በርካታ የድሮን ተተኳሾችን ባህርዳር በላይ ዘለቀ ኤርፖርት ጥግ ከሚገኘው ምዕራብ እዝ አየር ኃይል ግቢ በብዛት አከማችቷል።
ምሽግ፣ መኪና፣ ታንክ፣ ህንፃ፣ ካምፕ፣ ፋብሪካ እና ድልድይ የማውደም አቅም ያላቸው እነኝህ ቦንቦች 1.4 ሜትር ርዝመት እና 260 ሚሊሜትር ዲያሜትር ወይም ቁመት አላቸው። በትላልቆቹ አካንች ድሮኖች የሚጫኑት ሲሆኑ 94/95 ኪሎ ግራም ይመዝናሉ።
ከፋኖ በተጨማሪ ዋነኛ ዒላማቸው የሱዳን መከላከያ ሎጅቲክስ ማእከል ነው። ከሰሞኑ አሶሳ አቅራቢያ የሚገኘውን አንድ ትንሽ ከተማ ውስጥ ያለ ጤና ጣቢያን ኢምሬቶች የደበደቡት ጉዳዩን በሱዳን መንግስት ጦር በማሳበብ ካርቱምን ለመደብደብ ምክንያት ፍለጋ ነበር። በዚህ ስሌት መሰረትም ከባህርዳር የተነሱት አካንች ድሮኖች ሱዳንን በተደጋጋሚ በመደብደብ ላይ ናቸው። በቅርቡ ደግሞ በትግራይ የሚገኙ ኤርፖርቶች እና ወታደራዊ ቤዞች ላይ ጥቃት ለማድረስ ተዘጋጅተዋል።
የኢትዮጵያን አየር ኃይል ሙሉ በሙሉ የተረከቡት ኤምሬቶች በባህርዳር እና አሶሳ አዳዲስ የመኖሪያ ቤት እንዲገነባላቸዉ አገዛዙ የግንባታ ጨረታ አውጥቷል።
አማፂያንን በመደገፍ የምትታወቀው ኢምሬቶች በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ ያመፀዉን የአብይ አህመድ ቡድን ተሸክማ መቀጠል እንደማትችል የእስከዛሬው ፀረ-ህዝብ የአየር ኃይሏ ዘመቻ በቂ ማሳያ ነው።
አርበኛ አስረስ ማረ ዳምጤ
የአፋብን ቃልአቀባይ
ቅዱስ ሲኖዶስ የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ከመጥፋት እንዲታደጋት የሁለት እጁ እነሴ ወረዳ አስቴሪዮ የሐይማኖት አባቶች ጥሪ አቀረቡ።
➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺ ሚያዚያ 27/2018 ዓ.ም
የአብይ አህመድ ጀነራሎች በአደባባይ በሰጡት ትዕዛዝ መሰረት የአገዛዙ ሰራዊት አባላት እና የጦር መኮንኖች በቤተ ክርስቲያኗ ቅጥር ግቢ ምሽግ በማድረግ ልዕልናዋን እንደገፋፏት የሁለት እጅ እነሴ ወረዳ የሐይማኖት አባቶች ተናግረዋል።
በአማራ ህዝብ ላይ በተፈፀመው ወረራ ቤተ ክርስቲያኗ በቀጥታ ጥቃት እየተፈፀመባት ነው ያሉት የሐይማኖት አባቶች በበኩላቸው ካህናት፣ ቀሳውስት ፣ የአብነት ተማሪዎችና ዲያቆናት እየተገደሉ ስርዓተ ቤተክርስቲያን እየተስተጓጎለ ይገኛል ብለዋል። ከዚህ በፊት በድምቀት የሚከበሩት አመታዊ ሐይማኖታዊ በዓላት የአገዛዙ ሰራዊት በቤተ ክርስቲያኗ ላይ በመመሸጉና የሐይማኖት አባቶችን በማሳደዱ በተለመደው መልኩ ማክበር አለመቻሉንም አስታውቀው፤ ቤተ ክርስቲያኗ ቅርሷ እየተዘረፈ፤ ስርዓቷ እየተገፈፈ፤ አገልጋዮቿ እየተገደሉ በመሆኑ ቅዱስ ሲኖዶስ ቤተ ክርስቲያኗን ከመጥፋት እንዲታደጋት ጥሪ አቅርበዋል።
በዚህም 201ኛ ኮር በተደራጀ የፖለቲካ ስራ የአማራ ህዝብ ብሔራዊ ንቃት ይዳብራል፤ ህልውናውም ይረጋገጣል!፥
በሚል መሪ ቃል በሁለት እጁ እነሴ ወረዳ አስቴሪዮ ከኃይማኖት አባቶች ጋር ውይይት እያደረገ ይገኛል።
አዲስ ትውልድ ! አዲስ አስተሳሰብ! አዲስ ተስፋ
የአፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 201ኛ ኮር የህዝብ ግንኙነት
ዛሬ ይህንን የምጽፍላችሁ ደሜ በሚፍለቀለቅበት፣ ማንነቴ በኩራት በሚሞላበት ሰዓት ነው። እኔ የአሳምነው ልጅ ነኝ፤ ለማንኛውም ግፍ አንገቴን የማልደፋ፣ ለምንም ችግር የማልኮራ፣ የቁርጥ ቀን የአማራ ልጅ!
እውነት ነው፣ ትናንትና ተረግጦ፣ ተጠልቶ፣ ተንቆ የነበረውን አማራ ሲዘፈዝፉት፣ ከካዲያሙ ያረጋል ጎን ተሰልፈው ሲያጠቁት የነበሩ ሰዎች ዛሬ በፊቴ ሲቆሙ አያለሁ። ትናንት አርዳኝ ብለው እግሬ ላይ የወደቁ፣ ዛሬ ግን በየስርቻው እኔን ለማደን፣ መኖርያዬን ለማፈራረስ የቆሙትን ሳያቸው የሚታየኝ የትግል አድማስ ነው።
ግና... አንድ ነገር በደንብ አውቁ። እናንተ በምትከፍቱት በየአቅጣጫው ያለው አፈና፣ በየመንገዱ የምትዘረጉት ወጥመድ ለእኔ ማፈግፈጊያ ሳይሆን፣ ለጀግንነቴ ማሳያ ነው። እኔን ለማሳደድ በምትገፋፉ ቁጥር፣ የምበልጠው በእውቀት፣ የምጠነክረው በጽናት፣ የምገነባው በአማራው ህዝብ አንድነት ነው። ዛሬ እኔን ታሳድዳላችሁ፤ ነገ ግን የህሊና ቁስል ይዟችሁ ትፈራርሳላችሁ። እናንተ በቆፈራችሁት የጥላቻ ጉድጓድ ውስጥ የራሳችሁን ውድቀት እየቀበራችሁ እንደሆነ እንዴት አትረዱትም? ለእኔማ፣ ይህ ሁሉ ጥቃት ከብርት እንዲጠነክር፣ የሰላም መንገድ እንዲኖረኝና የአማራን ህዝብ ክብር ወደ ነበረበት ለመመለስ የምጓዝበትን አዲስ መንገድ እየከፈትኩልኝ መሆኑን አትርሱ።
የቁርጥ ቀን ልጅ መሆን ማለት አውሎ ነፋስ ሲነፍስ መፍራት ሳይሆን፣ ያንን ነፋስ ተገን አድርጎ ወደፊት መገስገስ ነው። ዛሬ የምትዘሩት መከፋፈል፣ ነገ የአማራን አንድነት ታላቅ ግንብ ይገነባል።
ያለፈው አልፏል፤ የነገው ደግሞ በእጃችን ነው።
+1
አንድ ጥይት፣ ለአንድ ጠላት! የዘመኑ የጀግንነት መሪ ቃላቱ በልቡ ያተመው!!
በሸዋ ደጋማና ቁልቁለታማ ተራራዎች አናት ላይ፣ ነፋሱ ስለ ነጻነት፤ ድንጋዮቹ ስለ ጀግንነት የሚያወሩበት ምድር ላይ፣ ያሉ ሁሉ የጀግንነቱን ወኔ የሚናገሩለት አርበኛ ኢሳያስ ደመቀ የአማራን ሕዝብ ህልውና ለመጠበቅ፣ ነጻነቱ ተነጥቆ ከምድረ ገጽ እንዳይጠፋ "ከህዝቤ በፊት እኔ!" ብሎ ደረቱን የሰጠ፣ የጀግና ልጅ። አብይ አህመድ የላከው የአየር ወለድ ኮማንዶ በሸዋ ተራራዎች ሲገባ፣ የሚያርበደብደው ኢሳያስ ደመቀ ቁርጠኝነት የአሳምነው ልጆችን ጽናት ተምሳሌት በተግባር ይነገርለታል።
የአርበኛው ኢሳያስ ደመቀ የውጊያ ስልት አጭር ነው፤ ግን ለጠላት ገዳይ ነው። በጦር ሜዳ ላይ ንግግር አያበዛም፤ የእርሱ ትእዛዝ በአይኑ ጥቅሻ ብቻ ነው። ያ የኢሳያስ ጥቅሻ የሰራዊቱን ወኔ ያነሳሳል፣ የጠላትን ሰፈር ያናውጣል፤ የድልንም ብስራት አበሳሪ ነው። ዛሬም አዲስ አበባን በአይነ ቁልቁል እያየ፣ የሽዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው እዝ ምክትል ወታደራዊ አዛዥ ሆኖ፣ በታላቅ የትግል ጽናት የነጻነትን እየቀደደ ወደ ፊት የአብይ አህመድ አየር ወለድ አራዊት ሰራዊት በገባበት ገብቶ እያዳፋው ከትግል ጓዶቹ ጋር በመሆን ይገኛል።
ጀግናው አርበኛ ኢሳያስ ደመቀ፤ የሸዋው የነጻነት ፋና። ፈጣሪ የጀግናውን ወኔ፣ የሰራዊቱን ጥንካሬና የትግሉን ጉዞ ይጠብቅ! #Dawit Amhara ከንጉሶች መንደር!!!
ድል ለአማራ ሕዝብ! 🙏🏾
#አርበኛ #ፋኖ #ኢሳያስደመቀ #የሸዋአንበሳ #ነጻነት #የአማራ_ጀግና #ኢትዮጵያ
ሰበር ዜና!
ምኒልክ ዕዝ ለሁለት ሳምንታት ያክል ጥልቅ የስራ ግምገማና ተሃድሶ አደረገ::
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ (አፋብን) ወሎ ቤተ-አማራ ምኒልክ ዕዝ ለሁለት ሳምንታት ያክል ጥልቅ የስራ ግምገማና ተሃድሶ በማድረግ በህልውና ትግሉ ያሉ ጠንካራና ደካማ ጎኖችን በመለየት ላሉ ድክመቶች የመፍትሄ አቅጣጫዎችን በማስቀመጥና ያሉ ጠንካራ ጎኖችን የበለጠ አጎልብቶ የህልውና ትግሉን ለድል ማብቃት በሚቻልበት ሁኔታ ላይ በከፍተኛ ደረጃ የመከረ ሲሆን በተጨማሪም የአማራ ህዝብ መሪ ድርጅት አፋብን ባወረደው መመሪያ መሰረት የዕዙን ሙሉ የአመራር መዋቅር በመስራትና ወደ ድርጅቱ የሚላኩ አመራሮችን በመመልመል ዛሬ ሚያዚያ 27/2018 ዓ.ም ስብሰባውን በስኬት አጠናቋል::
በመሆኑም ምኒልክ ዕዝ የአማራ ህዝብ መሪ ድርጅት አፋብን ያወረደውን መመሪያ ተግባራዊ በማድረግ መዋቅሩን መስራቱ ድርጅቱን መሰረት ከማስያዝና ከመትከል አንፃር ያለው ሚና ከፍተኛ መሆኑን በፅኑ በማመኑ የቤት ስራውን ለመስራት የበቃ ሲሆን ያለንበት ጊዜ የህልውና ትግሉ የሽግግር ወቅት በመሆኑ ፊታውራሪ ድርሳን ብርሃኔን የምኒልክ ዕዝ ሰብሳቢ በማድረግ ሾሟል::
ከዚህ ጋር ተያይዞም የምኒልክ ዕዝ የስራ አስፈፃሚ አመራር የሚከተሉት ናቸው፦
1. ሰብሳቢ.... አርበኛ ድርሳን ብርሃኔ
2. ምክ/ሰብሳቢ... አርበኛ ረዳ ዉበቱ
3. ወታደራዊ አማካሪ... ኮ/ል ሞገስ ዘገዬ
4. ወታደራዊ አዛዥ አርበኛ ወንድሙ ማሩ
5. ምክ/ወታደራዊ አዛዥ አርበኛ ሃብታሙ ደምሴ
6. ወታደራዊ እቅድና ስትራቴጅ መምሪያ... ኮ/ል ተስፋዬ አየለ
ምክ/ወታደራዊ እቅድና ስትራቴጅ መምሪያ... ኃላፊ ኮ/ል ፈንታው መኩየ
7. ዘመቻ መምሪያ... አርበኛ በለጠ ሸጋዉ
ምክ/ዘመቻ መምሪያ... አርበኛ ሙላቱ ሰጠ
8. ወታደራዊ አስተዲደር መምሪያ... አርበኛ ትዝታ በዛብህ
ምክ/ወታደራዊ አስተዳደር.. አርበኛ መስፍን አያሌው
9. ሎጂስቲክስ መምሪያ... ሻለቃ ኢሳይያስ መለሰ
ምክ/ሎጅስቲክ መምሪያ... አርበኛ ሽመልስ አቦል
ስንቅና ስርጭት... አርበኛ ሞላ ሰማው
10. ወታደራዊ ሥልጠና መምሪያ... አርበኛ አሌክስ ገርባው
ምክትል የሥልጠና መምሪያ... ፶ ዓለቃ አበበ አጋዡ
11. ወታደራዊ መረጃና መገናኛ መምሪያ አርበኛ × × × × × × ×
ወታደራዊ መረጃ መምሪያ አርበኛ × × × × × × ×
ወታደራዊ መገናኛ መምሪያ አርበኛ × × × × × × ×
መኃንዲስ ክፍል አርበኛ × × × × × × ×
12. ወታደራዊ ኢንዶክትሪኔሽን መምሪያ... አርበኛ አክሎግ ሲሳይ
ምክ/ወታደራዊ ኢንዶክትሪኔሽን... አርበኛ አለሙ ገላው
የኪነትና መዝናኛ ክፍል... አርበኛ ኪሮስ ደርቤ
13. ልዩ ዘመቻ መምሪያ... ሰብሳቢ አርበኛ ተሾመ ፈንታዬ
14. የመካናይዝድ ጦር መምሪያ... አርበኛ ሙሉቀን አያልነህ
ምክ/የመካናይዝድ ጦር መምሪያ.... ሻለቃ ወንድሙ ተሾመ
15. ጤና መምሪያ... ዶ/ር ኡስማን ሰይድ
ምክ/ጤና መምሪያ... አርበኛ ረብሶ ይላቅ
16. የፖለቲካ መምሪያ አርበኛ ሞገስ አባራው
የፖለቲካ መምሪያ ምክ/ኃላፊ... አርበኛ ስንታየሁ ተስፉ
17. የፖሊሲና ስትራቴጅክ ጉዳዮች መምሪያ... አርበኛ ደርብ ተፈራ
ምክ/የፖሊሲና ስትራቴጅክ ጉዳዮች መምሪያ... አርበኛ ገብረመስቀል ዘለቀ18. የአደረጃጀት መምሪያ... አርበኛ አሰፋ መሰለ
ምክ/የአደረጃጀት መምሪያ... አርበኛ ሲሳይ ሳተናው
19. የሕዝብ ግንኙነት መምሪያ... አርበኛ ብርሃን አረጋ
ምክ/የሕዝብ ግንኙነት መምሪያ... አርበኛ ሽመልስ ትዛዙ
ሚዲያና ኮሚኒኬሽን ኃላፊ... አርበኛ ደርብ መኮንን
ምክ/ሚዲያና ኮሚኒኬሽን ኃላፊ... አርበኛ ደምሴ ጋሻው
20. የሴቶች ጉዳይ መምሪያ... አርበኚት ዚነት አደም
ምክ/የሴቶች ጉዳይ መምሪያ... አርበኚት አበበች ሲሳይ
21. ትምህርትና ስልጠና መምሪያ... አርበኛ ፍቅሩ ፈንታው
ምክ/ትምህርትና ስልጠና መምሪያ... አርበኛ ዘሪሁን ደምሴ
22. ማሕበራዊ ጉዳዮች መምሪያ... አርበኛ ኑረዲን አበበ
ምክ/ማህበራዊ ጉዳዮች መምሪያ... አርበኛ ሚካኤል ጋሻው
23. የሕግና ስነ ምግባር መምሪያ... መቶ አለቃ ፈለቀ ጌትነት
ምክ/የሕግና ስነ ምግባር መምሪያ... አርበኛ አብዱ አያሌው
24. የድርጅት ጽ/ቤት ኃላፊ... አርበኛ አለምነው መብራቱ
ምክ/የድርጅት ጽ/ቤት ኃላፊ... አርበኛ ቃለአብ ወርቅየ
25. የፋይናንስና ግዥ አስተዳደር መምሪያ... አርበኛ ንጉስ አዳነ
ምክ/የፋይናንስና ግዥ አስተዳደር መምሪያ ኃላፊ... አርበኛ አዘዘው ጌትነት
አካውንታንት... አርበኛ ዮሃንስ ከልክሌ
ገንዘብ ያዥ... አርበኛ አዲሴ ጌታሁን
ግዥ ክፍል... አርበኛ አቢይ ቀፀላ
የውስጥ ኦዲተር... አርበኛ ፀጋዬ ብርሃኑ
26. የሐብት አፈላላጊ መምሪያ... አርበኛ ምኒልክ ፋንታሁን
ምክ/የሐብት አፈላላጊ መምሪያ... አርበኚት መሰረት ጫኔ
27. የሕዝብ አስተዳደር መምሪያ... አርበኛ አበበ ቀዬ
ምክ/የሕዝብ አስተዳደር መምሪያ... አርበኛ ጋሻው ሙሉጌታ
28. የሰው ሃብት አስተዳደር መምሪያ... አርበኛ እስራኤል እሸቴ
ምክ/የሰው ሃብት አስተዳደር መምሪያ... ሃምሳ አለቃ ሸዋነው አዲል
29. እቅድ ዝግጅትና ግምገማ መምሪያ... አርበኛ አራጋው ያለው
ምክ/እቅድ ዝግጅትና ግምገማ መምሪያ ኃላፊ... አርበኛ ጌታቸው እሸቱ
30. የመረጃና ደህንነት መምሪያ አርበኛ × × × × × × ×
ምክ/የመረጃና ደህንነት መምሪያ አርበኛ × × × × × × ×
መረጃ መምሪያ አርበኛ × × × × × × ×
ፀረ መረጃ መምሪያ አርበኛ × × × × × × ×ስውር ድርጊያ መምሪያ አርበኛ ×
በመጨረሻም መላ ሰራዊታችንና ህዝባችን ለዚህ ትልቅ አላማ መሳካት ላበረከታችሁት ሁለንተናዊ አስተዋጽኦ የላቀ ምስጋናችንን እያቀረብን እንደ ህዝብ መስዋዕትነት የከፈልንበትና እየከፈልንበት ያለው አላማችን የአማራን ህዝብ ህልውና መረጋገጥ እና የሃገራችን ኢትዮጵያ ባለቤት የመሆን የመጨረሻ ተጋድሎ የተለመደው አበርክቷችሁ ተጠናክሮ ይቀጥል ዘንድ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን!
መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!
ህልውናችን በተባባረ ክንዳችን!
አፋብን ወሎ ቤተ-አማራ ምኒልክ ዕዝ
ሚያዚያ 27/2018 ዓ.ም
ሰበር ዜና
አፋብን ሸዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው ዕዝ አፄ ዘረያዕቆብ ኮር ናደው ክፍለ ጦር ልዩ ተወርዋሪዎች በጠላት ላይ ከፍተኛ ድል ተቀናጁ
ሚያዚያ 27 ቀን 2018 ዓ.ም
በሸዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው ዕዝ ስር የሚንቀሳቀሰው የአፄ ዘርያዓቆብ ፩ ኮር፣ የናደው ክፍለ ጦር ልዩ ተወርዋሪ ኃይሎች በጠላት ላይ መብረቃዊ ጥቃት በመሰንዘር ከፍተኛ ድል ተቀናጅተዋል።
በመርሐቤቴ አካባቢ ምርጫን አስገዳጅ በሆነ ሁኔታ እንዳሳልጡ የተመደቡ አመራሮችን በሁለት አምቡላንሶች በማጀብ ወደ ለሚ ከተማ በመጓዝ ላይ የነበረው የአገዛዙ የ101ኛ አየር ወለድ ኮማንዶ ኃይል፣ በጀግኖቹ ብርቱ ጥቃት ከጥቅም ውጭ ሆኗል።
ጥቃቱ የተፈጸመው "ዱፋ" ተብሎ በሚጠራው ስልታዊ ቦታ ላይ ሲሆን፣ በልዩ ኦፕሬሽን የተካኑት የናደው ክፍለ ጦር አባላት በተለመደው የውጊያ ጥበባቸው ጠላት ከመኪና ሳይወርድ ባለበት እንዲደመሰስ አድርገዋል።
በጠላት ላይ የደረሰ ኪሳራ
በዚህ የተቀናጀ ኦፕሬሽን በአንደኛው መኪና ላይ የነበረው የጠላት ኃይል ሙሉ በሙሉ ተደምስሷል። እስካሁን ባለው መረጃ መሠረት፦
✔ቁጥራቸው በውል ያልታወቁ የጠላት ወታደሮች ተገድለዋል።
✔8 ከፍተኛ ቁስለኞች ወደ ሆስፒታል ገብተዋል።
✔የጠላት ተሽከርካሪ በደረሰበት ከፍተኛ ምት መንቀሳቀስ የማይችል ሆኖ በቦታው ላይ (ዱፋ) ቆሞ ይገኛል።
ጠላት ጉዳት የደረሰባቸውን አመራሮች ለማውጣት ከሁሉም አቅጣጫ ቢረባረብም፣ የናደው ክፍለጦር ልዩ ተወርዋሪ ኃይሎች ያለ ምንም ጉዳት ግዳጃቸውን በስኬት አጠናቀዋል።
የኦፕሬሽኑ መሪ እንደገለጹት፣ ይህ ድል የናደው ክፍለ ጦር ልዩ ተወርዋሪዎች ያላቸውን የውጊያ ብቃትና የጠላትን እንቅስቃሴ አስቀድሞ የመመከት አቅም ዳግም ያስመሰከረ ነው። በተጨማሪም ጠላት የአምቡላንስ ሽፋን በመጠቀም ለማለፍ የነበረው ስልት በጀግኖቹ ንቁ ክትትል ሊከሽፍ ችሏል ብሏል።
"ክብር ለትግሉ ሰማዕታት!"
"ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!"
የሸዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው ዕዝ ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ
