ch
Feedback
ፍኖተ- አማራ ሚዲያ (Finote- Amhara ) Midea

ፍኖተ- አማራ ሚዲያ (Finote- Amhara ) Midea

前往频道在 Telegram

የተመሠረተው የአማራን ሕዝብ ለማንቃት፣ ለማደራጀት እና ለማስተባበር ነው። የአማራ ሕዝብን ✅ ፖለቲካዊ ✅ ማህበራዊ ✅ ኢኮኖሚያዊ ታሪካዊ ጥያቄዎችን ለማሰማት እና የአማራን ሕዝብ በማንቃት ሰፊውን ሕዝብ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ይሰራል። ወደዱም ጠሉም የኃላ ታሪካችን በእኛ እጅ ይፃፋል። አማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ( አፋብን)

显示更多
3 279
订阅者
+3924 小时
+3057 天
+69830 天
帖子存档
በአምባሰል ወረዳ በተደረገ ተጋድሎ ፋኖ ስልታዊ ማጥቃት በማድረግ የጠላት አከርካሪን ሰብሮ ድል ተቀዳጀ! በአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ 102ኛ ኮር ስር ከ35ኛ ክ/ጦር እና 104ኛ ኮር ከ24ኛ ክ/ጦር የተወጣጡ የፋኖ አሃዶች ዛሬ መጋቢት 27/2018 ዓ/ም ከረፋድ ጀምሮ እስከ ምሽት በቅንጅት ባደረጉት ውጊያ ከፍተኛ ድል አስመዝግበዋል፡፡ በአምባሰል ወረዳ መነሻቸውን ከአበት እና ከውጫሌ ያደረጉ የአገዛዙ ኃይሎች በወረዳው ሚለዋ ተብሎ ወደሚጠራው ቀበሌ እየተንቀሳቀሱ ባለበት ነው ሊመከት የማይችል ከባድ የቆረጣ ጥቃት የተፈፀመባቸው። ማርፈጃውን የተጀመረው ተጋድሎ እስከ ምሽት 12:30 ገደማ የዘለቀ ሲሆን፡ በዚህም የጠላት ኃይል የተሰነዘረበት ጥቃት መመከት አቅቶት ተፍረክርኮና ተሽመድምዶ ተበታትኗል። በተጋድሎው ለጊዜው ቁጥራቸው በውል ያልታወቀ ወታደሮች ሲደመሰሱ ቀሪው ኃይል ቁስለኛውን እያዝረከረከ ወደ ውጫሌ ከተማ ፈርጥጧል። መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልዉና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል! ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን! አፋብን ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ መጋቢት 27/2018 ዓ/ም    

በ102ኛ ኮር አዴት ላይ በተደረገ የተጠና (የታቀደ) ኦፕሬሽን በርካታ ጠላትን መደምሰ ችለናል። የተገኘ ሰብዓዊ እና ቁሳዊ ምርኮ👇 አዴት ላይ፦  ቁሳዊ ->159 የነፍስ ወከፍ መሳሪያ ->14,800 የብሬን ተተኳሽ ->14,984 የክላሽ ተተኳሽ ጠቅላላ ድምር = 27,784 ->61 የእጅ ቦንብ ->221 የክላሽ ካዘና ->05ኩንታል ከስክስ እና ሚሊታሪ ->24 የደረት ትጥቅ ->12 የወገብ ትጥቅ የተደመሰሰ ጠላት ብዛት እና አይነት ->97 ሚሊሻ ->37 አድማ ብተና ->22 መከላከያ ->206 እስረኞችን ማስፈታት ችለናል። የ የደጋ ዳሞት እና ጎንጅ ቆለላ ዝርዝሩን ይዘን እንመጣለን ድል ለጀግናው አማራ ! ድል ለጀግናው ፋኖ !! ©ማርሸት ፀሐይ የቴዎድሮስ ዕዝ ሕዝብ ግንኙነት

ውጊያ አንድም አዋጊና ተዋጊ ወታደርህን ሁለትም ደጀን ህዝብህን ይመስላል። ቃላቶች ሁሉ ቢሰደሩ የህዝባችንን አይተኬ ሚና ተዘርዝሮ አያልቅም። ፤ የጎጃምን ምድር ጋራና ሸንተረሩን፣ ቆላና ደጋውን፣ ተራራና ሜዳውን ብጥርጥር አድርገው የሚያውቁ ወታደራዊ አመራሮች ተፈጥረዋል። በወረቀት ድስኩር አልያም በፓወር ፖይንት የተገኘ የስልጠና ንቃት አላገኙም። ከዚያ በተቃረነ ሁኔታ የወንድምን ደም ተራምደው እያለፉ፤ የጠላትን ኮሌታ ከነነፍሱ ጨብጠው እየያዙ፤ የጦርነትን አስከፊ ሁኔታ ዕለት ከዕለት እየተጋፈጡና ሞት ቤተኛ ሁኖ መሽቶ በነጋ ቁጥር እየጎበኛቸው “የተስተማሩትን ቁርጠኝነት” የትኛውም ዓለም ላይ በስኮላር ብትጓዝ ልትሸምተው የማትችለው እውቀት ነው። ከምንም በላይ ያነገቡት ዓላማ ደግሞ የጠራ ኃሳብ ነው። ፤ መምህሩ እንደ ህዝብ የገጠመን የህልውና ስጋት፣ ትምህርት ቤቱ የጎጃም መልከዓምድር፣ ተማሪዎች ራሳችን በመሆን ህዝባቸውን ጠባቂ የነገዋ ኢትዮጵያ “ኮሎኔልና ጀኔራሎች” እየተፈጠሩ ነው። ፤ Red Carpet ተነጥፎልን በአንዴ ፬ኪሎ አይገባም ስንል የዚህ ሂደት አንዱ አካል ነበር። አመራሮቻችን ለአላማቸው ብቻ ሲሉ ፅናትን የተላበሰ ሀገርን የመምራት Exercises ውስጥ ናቸው። 📷 የ102፣ 109ኝና ኮማንዶ ዩኒት አዛዥና ዘመቻ መሪ ናቸው። @ማንችሎት እሱባለው

አፋብን | ቴዎድሮስ ዕዝ ____፩ ጠላት መግቢያ መውጫ እያጣ ነው። 102ኛ ኮር ሁለት ከተማዎች ላይ ጠላትን በመደምሰስ  ወታደራዊ  እና ፖለቲካዊ ድል ተቀዳጄ። 1ኛ. ሰሜን ግጃም ዞን አዴት ከተማ የነበረ አንድ ሻለቃ ሙሉ በሙሉ ተደምስሷል። ጠላት ከአንድ አመት በላይ ማዘዣ ጣቢያ በማድረግ ሲጠቀምበት የነበረው የአዴት ፖሊስ ጣቢያን በመቆጣጠር እና ጠላትን በመደምሰስ በርካታ የቡድን፣ የነፍስ ወከፍ መሳሪያ እና ተተኳሽ መማረክ ተችሏል። 159 የነፍስ ወከፍ መሳሪያ 14,800 የብሬን ተተኳሽ 14,984 የክላሽ ተተኳሽ ጠቅላላ ድምር= 29,784 61 የእጅ ቦንብ 221የክላሽ ካዘና 05 ኩንታል ከስክስ እና ሚሊታሪ 24 የደረት ትጥቅ 12 የወገብ ትጥቅ  መማረክ ሲቻል። 97 ሚሊሻ 37 አድማ ብተና 22 መከላከያ በድምሩ 156 ጠላትን በመደምሰስ 07 ለጠላት አገልግሎት ሲሰጡ የነበሩ ተሽገርካሪዎችን በድጋሜ አገልግሎት እንዳይሰጡ ማድረግ ተችሏል። በዚሁ አዴት ከተማ አገዛዙ በግፍ ለዘመናት ፋኖን ትደግፋላችሁ በማለት ሲያሰቃያቸው የነበሩ 206 የግፍ እስረኞችን ማስለቀቅ ተችሏል። 2ኛ :-ሰሜን ጎጃም ዞን ጎንጅ ቆለላ ከተማ መሽጎ የነበረውን ጠላት መደምሰስ ተችሏል። ነበልባሎቹ 102ኛ ኮር በተመሳሳይ ስዓት ጎንጅ ቆለላ ወረዳ በመግባት 89 ሚኒሻ 24መከላከያ በድምሩ 103 የጠላት ሀይል በመደምሰስ :- 58 የነፍስ ወከፍ መሳሪያ  እና 3480 ተቷኳሽ በመማረክ ታሪክ ሰርተዋል። በአጠቃላይ 102ኛ ኮር አዴት እና ጎንጅ ቆለላ በተደረገ ውጊያ     217 የነፍስ ወከፍ መሳራያ 31264 ተተኳሽ በመማረክ  ታሪክን በእጁ ፅፏል። አዲስ ትውልድ፣ አዲስ አስተሳሰብ ፣አዲስ ተስፋ!         ክፋት ለማንም ፣በጎነት ለሁሉም! አፋብን| ቴወድሮስ ዕዝ ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ            መጋቢት 27/2018 ዓ.ም

106ኛ ኮር 31ኛ ክፍለ ጦር የብልፅግና የምርጫ ቁሳቁስ በተሸከሙ ሎሌዎች ላይ የማያዳግም እርምጃ ወሰደ:: አፋብን ሚኒሊክ ዕዝ 106ኛ ኮር 31ኛ ክፍለ ጦር በደላንታ ወረዳ ፀሀይመውጫ መከለት በተባለ ቦታ የብልፅግናን የምርጫ ኮሮጆ ተሸካሚ ሎሌዎች ላይ የተሳካ ኦፕሬሽን ተፈፅሟል! መጋቢት 27/2018 ዓ/ም ከፀሀይመውጫ መከለት  ሸዋበር ተቀሳቅሶ "ማህበረሰቡን የምርጫ ካርድ አውጡ" በማለት እያስገደደ በነበረ የብልፅግና ተላላኪ ካድሬዎችን የጫነ ፓትሮል ላይ  ደፈጣ በማድረክ  ፓትሯሏን አልሞ ተኳሽ ግስላዎቹ ታርጌት አድርገው ስትመታ፤ የሎሌነት ልክፍታቸውን ሳያሳኩ መሀል መንገድ ላይ ጥቃት በመፈፀም ተሽከርካሪዋ ሲትገለበጥ፤ ከፓትሮሏ ውስጥ የነበሩት ካሚኔዎችና የፓትሮሏ ሹፌር ታጠቅ ሀይለልዑል የተባለው ሆድአደሮችን ጨምሮ  ከሞራል እስከ አካል ጉዳት ድረስ እርምጃ ተወስዷባቸዋል። የብልፅግናን የጥፋት ፕሮጀክት ለማሳለጥ በሚጎብጡ ተላላኪዎች ላይ ክፍለ ጦሯ በወሰደችው ቅስፈታዊ እርምጃ የከባቢዉ ማህበረሰብ እጅጉን የኮራ ሲሆን ተመሳሳይ አይነት ሆድ አደር ተላላኪዎችን ከጥፋት እርምጃቸው የሚገታ ፍቱን ፈውስ ሆኖ ተወስዷል። በክፍለ ጦሯ ዘመቻ መምሪያ ሀላፊ በሆነው በባለ ጥቁሩ እስናይፐር ተኳሽ ሲሳይ ተሾመ(ጨልጤ) የዘመቻ እንቅስቃሲያቸውን እንደ ንብ ተግተው የሚፈፅሙት ግስላዎች ዛሬም በጥላት ሰራዊት ላይ አንገት የሚያስደፋ ተልኮ ተፈፅሟል!!! መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልዉና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል! ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን! አፋብን ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ #106ኛ ኮር ህ/ግ መምሪያ ሀላፊ! መጋቢት 27/2018 ዓ.ም

#የድል_ሐዲድ፤ #የነፃነት_ነጎድጓድ! የ102ኛ ኮር ጥምር ክንዶች (33ኛ 11ኛ እና 22ኛ ክፍለ-ጦሮች) በጠላት ላይ ታሪካዊ ድል ተቀዳጁ _ ወደ 283 ጠላት ተወግዷል። ༻༺༻༺༻༺༻༺ [መጋቢት 27/2018 ዓ.ም፣ ዐፋብን ምዕራብ ዐማራ ቀጠና ቴዎድሮስ ዕዝ 102ኛ ኮር 33ኛ ክ/ጦር ሕዝብ ግንኙነት] የነፃነት ታጋዩ ፋኖ የጭቆናን ቀንበር ለመስበር የጀመረው ግስጋሴ በአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ (ዐፋብን) ምዕራብ አማራ ቀጠና፣ ቴዎድሮስ ዕዝ ስር በሚንቀሳቀሱ የ102ኛ ኮር የቁርጥ ቀን ልጆች አይበገሬነት ደምቆ ውሏል። ዛሬ ንጋት የፋኖ ክንድ በጠላት ምሽግ ላይ እንደ መብረቅ ወርዶባቸዋል። #የጎንጂ_ቆለላ_ድል (33ኛ ክፍለ-ጦር) ከንጋቱ 1፡30 ጀምሮ የነፃነት ፀሐይ በጎንጂ ቆለላ ወጥታለች። 33ኛው ክፍለ-ጦር ከተማዋን በሁሉም አቅጣጫዎች በመቆጣጠር፣ 63 "ጥቁር አማራ" የብልጽግና ተላላኪዎችን እና ከሃያ በላይ የሰልቃጩን ሥርዓት ጠባቂዎችን ከጥቅም ውጭ አድርጓል። #ምርኮኞች፦ 15 በላይ የጠላት ኃይሎች በእጅ ተይዘዋል። #ትጥቅ፦ ወደ 30 የሚጣጠጉ ክላሽንኮቭ መሣሪያዎችና ተተኳሾች ለነፃነት ትግሉ ገቢ ሆነዋል። #እስረኞች፦ ቁጥራቸው ያልታወቁ እስረኞች ተለቀዋል። በሌላ ዜና #የአዴት ከተማ -  (11ኛ እና 22ኛ ክፍለ-ጦሮች) በአዴት ከተማ ደግሞ 11ኛ እና 22ኛው ክፍለ-ጦሮች ባካሄዱት የተቀናጀ ጥቃት የብልጽግናን ኃይል በማነካከት የጠላትን አንጀት የሚያሳርር ድል ተቀዳጅተዋል። #የአዴት_ድል_ ስኬቶች_በቁጥር፦ 🔥 200 በላይ የአድማ ብተና እና የሚሊሻ አባላት ተደምስሰዋል። 🩸 100 በላይ የጠላት ኃይሎች በከባድና ቀላል ቁስል ከውጊያ ውጭ ሆነዋል። 🔓 100 በላይ ያለ በቂ ምክንያት የታሰሩ ንፁሃን ወገኖቻችን ከእስር ተለቀዋል። 🔫 300 በላይ የነፍስ ወከፍ መሣሪያዎች ከጠላት ዕቃ ግምጃ ቤት ተወርሰዋል። 🚒 13 ፓትሮሎች ድባቅ ተመትተው ወድመዋል። 👕 100 በላይ የታሸጉ ወታደራዊ አልባሳት፣ 150 በላይ ካዝናዎችና የብሬን ተተኳሾች ተማርከዋል። ➡ ለይስሙላ ምርጫ ተዘጋጅቶ የነበረው የካርድ ክምርም ሙሉ በሙሉ ወደ አመድነት ተቀይሯል! የጠላት ሴራና የገበሬውን መሣሪያ የመቀማት ግብዝነት በፋኖ ፅናት እና በተቀናጀ ወታደራዊ ጥበብ መክኗል። ✔ ድል ለአማራ ሕዝብ!✊ ✔ ክብር ዐማራ ፋኖ!

በአፉብን ቴዎድሮስ ዕዝ ውስጥ እረፍት አልባ ቀናቶች እንደ ነጎዱ ናቸው። ሁሌም ስልጠና፣ ሁሌም ውጊያ፣ ሁሌም ህዝብን ማስተዳደር፣ ሁሌም ወዳጅን የማብዛት ዲፕሎማሲ፣ ሁሌም ዓለም ሀቃችንን እንዲረዳው
በአፉብን ቴዎድሮስ ዕዝ ውስጥ እረፍት አልባ ቀናቶች እንደ ነጎዱ ናቸው። ሁሌም ስልጠና፣ ሁሌም ውጊያ፣ ሁሌም ህዝብን ማስተዳደር፣ ሁሌም ወዳጅን የማብዛት ዲፕሎማሲ፣ ሁሌም ዓለም ሀቃችንን እንዲረዳው የማድረግ ስራዎች ያለመታከት እየተሰሩ ነው። ፤ ከንጋት ጀምሮ እየተደረገ ባለው የወገን ሀይል የማጥቃት እንቅስቃሴ በ102ኛ ኮር 11ኛና 33ኛ ክፍለ ጦር አዴትና ጎንጅ ላይ፤ በ109ኛ ኮር 99ኛና 77ኛ ክፍለ ጦር ክፍለ ጦር ደጋዳሞት ፈረስቤት ላይ የጠላትን አከርካሪ የሰበረ ውጊያ እየተካሄደ ነው። ፤ የታክቲካል ውጊያ አውዶች ሰፍተው ስትራቴጂካል ድል እጃችን ላይ እስኪገባ የአብይ ወታደር መሰረታዊ ቤዞችን በከፍተኛ ድምፅ እየተንኳኩ ነው። በሩም በግዱ ይበረገዳል፣ ጠላትም እንዳይፀና ሁኖ ይናዳል። ፤ እንበርታ! 📷 ጀኔራል ዝናቡ ልንገረው ከወታደራዊ መምሪያ፤

▪የአፋብን ቴወድሮስ እዝ 109ኛ ኮር እና የእዙ ኮማንዶ ዩኒት በጋራ ባደረጉት ውጊያ የምስራቅ እዝ ነባር መኮንኖች የረገፉበት ምድር ደጋ ዳሞት ላይ አንድ ሌተናንት ኮሎኔልን ጨምሮ በርካታ ሰራዊት ተማርኳል። የጠላትን ሎጅስቲክስ ሙሉ በሙሉ ተረክበናል። ▪102ኛ ኮር በታቀደ እና በተቀናጀ ውጊያ በቦታው የነበረውን ጠላት በመደምሰስ የአዴትን እና የጎንጅን የጠላት የመሳሪያ እና የተተኳሽ ግምጃ ቤቶች በሙሉ ተረክባለች። ገና ጅምር ላይ ነን፣ ይቀጥላል... ▪በነገራችን ላይ የአብይን ኮሎኔል ማርከው እጅ ወደ ላይ አስብለው "ፋኖ ይችላል" እንዲል ያሰኙት ሁለቱ ጀግኖች ከምርኮኛው ኮሎኔል ደመላሽ ቆጭቶ በቀኝ በኩል የ109ኛ ኮር አዛዥ ሻለቃ ታዘበው ስዬ፤ በግራ በኩል የእዙ ኮማንዶ ዩኒት አዛዥ መቶ አለቃ አጃናው ጥላሁን ናቸው።

+1
#ሰበር_የምርኮ_ዜና‼️ ሌተናል ኮሎኔል ደመላሽ አሰፋ የተባለ የክ/ጦር ሎጀስቲክስ ኃላፊ አመራር በደጋ ዳሞት በአፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ ልዩ ኮማንዶ ተማርኳል💪 ግፋ ፋኖ💪 27/ዐ7/2018 ዓ.ም

#ጥንቃቄ_አይለየን‼️ አፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ በዛሬው ዕለት በተለያዩ ቦታዎች #ከባድ_ማጥቃት እያደረገ ሲሆን በዚህ ተጋድሎ ነፃ የወጡ ወረዳዎች ይገኛሉ። በእግረኛ ያልቻለው አገዛዝ በአየር ኃይል ቅኝት
#ጥንቃቄ_አይለየን‼️ አፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ በዛሬው ዕለት በተለያዩ ቦታዎች #ከባድ_ማጥቃት እያደረገ ሲሆን በዚህ ተጋድሎ ነፃ የወጡ ወረዳዎች ይገኛሉ። በእግረኛ ያልቻለው አገዛዝ በአየር ኃይል ቅኝት እያደረገ ስለሆነ ሰራዊታችንና ህዝባችን እንቅስቃሴ ሲያደርጉ ለአየር ኃይል ጥቃት በማይመች መልኩ እንዲሆን ንስር አማራ መልዕክቷን ታስተላልፋለች‼️ 27/ዐ7/2018 ዓ.ም

#የጥንቃቄ መልክት #የኦህዴድ ብልፅግና መከላከያ በእግረኛ አልችል ሲል አሁን በዚህ ሰአት 5:10 ላይ ከባህር ዳር #የጀት እንቅስቃሴ እያደረገ ሲሆን የወገን ሀይል ጥንቃቄ ይደረግ። #ሸርርርርር ©ዮሴፍ ሐረገወይን መጋቢት 27/7/2018ዓም

አነደድ ላይ የአብይ ሚኒሻ በጧት ነዷል በአነደድ ወረዳ በተደረገ ውጊያ አንድ የሻለቃ አዛዥን ጨምሮ 30 የአገዛዙ ወታደሮች ተገደሉ‼️ በአፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 206ኛ ኮር ስር የሚገኘው 34ኛ ክ/ጦር ትላንት መጋቢት 26/2018 ዓ/ም በአነደድ ወረዳ ጃማ እና ታላቅአምባ የሚገኙ የፍኖ አባላትን ለማፈን የተንቀሳቀሰ የአገዛዙ ሰራዊት ላይ ባደረጉት የተኩስ ልውውጥ 30 የአገዛዙ ወታደሮች እስከወዳኛው የተሸኙ ሲሆን በርካቶች ቁስለኛ መሆናቸው ተገልጿል ጀብደኛውና አይበገሬው 34ኛ ክ/ጦር  ቃኝና መሀንዲስ ከቀኑ 8:00-12:30 ባደረጉት እልህ አስጨራሽ ውጊያ ወገንን ሲያሰቃይ የነበረ የአድማ ብተና አዛዡ ሲገደል መገናኛ ሬድዮዉ መማረኩ የተገለፀ ሲሆን ከዚህም በተጨማሪ የባሶ ሊበን ካድሬ የሚተማመንበት ባንዳው ሻለቃ ወርቁ አጃቢ እስከወዳኛው ተሸኝቷል። ይህን ውጊያ ያደረጉት ነበልባሎቹ የ34ኛ ክ/ጦር ቃኝና መሀንዲስ 12 ክላሽንኮቭ ፦ በርካታ ካዘና እንድሁም እጅግ ብዙ ቁጥር ያለው ተተኳሽ የተማረከ ሲሆን ለማፈን የመጠው የጠላት ሀይል አስከሬኑን ተሸክሞ በመሄድ ድንኳን ጥሎ እያለቀሰ ይገኛል ። በሌላ በኩል በአዋባል ወረዳ ለጋ ላይ የሚገኝ አንድን የጎበዝ አለቃ አፍኖ ለመውሰድ የተንቀሳቀሰው የጠላት ሀይል በተደረገበት ደፈጣ ሳይሳካለት ወደመጣበት ፈርጥጧል። በአፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 206ኛ ኮር 34ኛ ክ/ጦር ሕዝብ ግንኙነት ክፍል! 27/ዐ7/2018 ዓ.ም

በየማዕዘኑ የምናስመርቃቸው የአፋብን ኮማንዶወች ማርከው የሚታጠቁ ናቸው። ከወራት በፊት አዴት ላይ የተመረቁት ኮማንዶወች ከነባሩ የ102ኛ ኮር ሰራዊት ጋር በመቀናጀት አዴት የሰፈረውን ጠላት በጠዋቱ ጨብጠውታል። በአሁኑ ሰዓት አዴት እና ጎንጅ የነበረውን ምሊሻ የአካባቢው አርሶ አደር የደጀን ኃይላችን በተበታተነበት እየተከተለ ትጥቁን እየተቀበለው ነው። መደበኛው ሰራዊታችን ጠላት ባህርዳርን ለመከላከል ካሰፈረው ጠንካራ ኃይል ጋር ትንቅንቅ ላይ ነው። ብዙ ድል ብዙ ገድል አለ። የአፋብን ቴወድሮስ ዕዝ 102ኛ ኮር ጀብዱን በዝርዝር እንመጣበታለን። በሌላ በኩል የአፋብን ቴወድሮስ ዕዝ 109ኛ ኮር እና የቴወድሮስ እዝ ኮማንዶ ክፍለ ጦር በቅንጅት ባደረጉት ውጊያ ፈረስ ቤትን ከጠላት ሰራዊት በማፅዳት የነዱትን የጠላት ምርኮ ከዚህ ተንቀሳቃሽ ምስል ተመልከቱ። ለቅምሻ ነው። ዝርዝር አለ ገና። ይቀጥላል...

ደጋ ዳሞት ላይ ጀብደኛው109ኛ ኮር በ Nibret Dessie ፣ በአባይነህ፣በደመላሽ እና በአብራራው እየተመራ በዚህ መልኩ ሆሳዕናን እያከበረ ይገኛል።
ደጋ ዳሞት ላይ ጀብደኛው109ኛ ኮር በ Nibret Dessie ፣ በአባይነህ፣በደመላሽ እና በአብራራው እየተመራ በዚህ መልኩ ሆሳዕናን እያከበረ ይገኛል።

#መብቱን_ያላስከበረ_ዜጋ_ባሪያ_ሆኖ_ይገዛል!!! ጀግናው የመዘዞ ከተማ ህዝብና ዕድሚያቸው ከ18ዓመት በላይ የሆኑ ተማሪዎች ለተቃውሞ ሰልፍ አደባባይ ወጥተዋል👏 ✍️ት/ቤቱ በድሮን እየወደመበት ያለው ዕድሜው የደረሰ ተማሪ ተቃውሞውን ማሰማቱ ተገቢ ነው። 👉ትምህርታችንን እንማርበት! 👉ት/ቤታችን በድሮን እየወደመ ነው! 👉እኛም እየቆሰልን እየሞትን ነው!

-----------ሰበር------------ ጎንጅ እና አዴት ላይ ዉርዉር አትበሉ፣ 102ኛ ኮር ነብር ሁኖል አሉ💪 ----ዝርዝሩን ጠብቁን‼️