ፍኖተ- አማራ ሚዲያ (Finote- Amhara ) Midea
前往频道在 Telegram
የተመሠረተው የአማራን ሕዝብ ለማንቃት፣ ለማደራጀት እና ለማስተባበር ነው። የአማራ ሕዝብን ✅ ፖለቲካዊ ✅ ማህበራዊ ✅ ኢኮኖሚያዊ ታሪካዊ ጥያቄዎችን ለማሰማት እና የአማራን ሕዝብ በማንቃት ሰፊውን ሕዝብ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ይሰራል። ወደዱም ጠሉም የኃላ ታሪካችን በእኛ እጅ ይፃፋል። አማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ( አፋብን)
显示更多3 712
订阅者
+2624 小时
+3797 天
+1 10930 天
帖子存档
ሰበር...ቦምብ እንደ ዳቦ አጉራሽ የተባለላቸው አፈንፋኝ ኮማንዶዎች ገቡ!
በደጃች በላይ ዘለቀ ዕዝ ዳግማዊ ቴዎድሮስ ኮር ስር "አፈንፋኞቹ" የሚል ቅፅል ስም ያላቸው የልዩ ኦፕሬሽን ምድብተኛ ኮማንዶዎች በደብረታቦር ከተማ ምን አልባት በየህንፃ ጣሪያው እና ሌሎች ቦታዎች ላይ ተቆርጦ የቀረ የጠላት ኃይል ካለ ወደ ከተማዋ በመግባት አፅድተው ለፋኖ ሲቪል አስተዳደር ክፍል እንዲያስረክቡ ትዕዛዝ ተሰቷቸው ተሰማርተዋል።
የከተማ መሠረተ ልማት እንዳይጎዳና ንፁኋኖች ለጥቃት እንዳይጋለጡ በከተሞች ብቻ ማጥቃት እንዲችሉ ተደርገው ለወራት በጥንቃቄ ሰልጥነው የተመረቁ የልዩ ኦፕሬሽን ምድብተኞች ስራቸውን ጀምረዋል።
ቀሪው እግረኛው ኃይል ወደፊት እየገሰገሰ መሆኑን የመረብ ሚዲያ የግንባር ዘጋቢዎች ለማረጋገጥ ችለዋል።
አገዛዙ "አይነኬ" በሚል የሚተማመንበት በከተማዋ ኢየሱስ ተራራ ላይ የነበረው የኮንክሪት ምሽግ፡ በልዕለ ኃያሉ ፋኖ ክንድ ሲሰበር የተደመሰሱ የበርካታ ወታደሮች አ*ስ*ከ*ሬ*ን አሁን በዚህ ሰዓት የሰማይ አሞራ እየተራኮተበት ይገኛል።
የአፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 109ኛ ኮር 88ኛ ክ/ጦር በጠላት ላይ ሰብአዊና ቁሳዊ ኪሳራ አደረሰ
*//
በዛሬው ዕለት ጥር 04/2018 ዓ. ም ከምዕ/ጎጃሟ ቡሬ ዙሪያ ወረዳ ቁጭ ከተማ የመሸገው የአገዛዙ ዘራፊና ጨፍጫፊ ሠራዊት ወደ ወምበርማዋ ወረዳ ወይንማ ቀበሌ የተለመደ አርሶ አደሩ ላይ የዘረፋ ተግባሩን ለመፈፀም ከንጋቱ 11:30 ጀምሮ ተንቀሳቅሷል። ነገር ግን የጠላት መቅጫ አይበገሬው አፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ የ109ኛ ኮር 88ኛ ክ/ጦር በፈርጣማ ክንዱ አቅምሶ እና ደቁሶ እያሯሯጠ መልሶ ከቀበሮ ጉድጓዱ ከቶት ተመልሷል።
ወይንማ እና ጭራር በእጅበጅ ተኩስ 1ኛ እና 2ኛ ሻለቃ ጠላትን ሲቆሉት ሽንዲ ከተማ ደግሞ 4ኛ ሻለቃ ከተማ ሰርጎ በመግባትና ተኩስ በመክፈት የጠላትን ትስስር እንዳይፈጥር በማድረግ የጠላትን አከርካሪ መምታት ተችሏል።
#በተያያዘ ጥር 03/2018 የክ/ጦሯ ኮማንዶ ዩኒቷ 5ኛ ሻለቃ ሽንዲ ከተማ የመሸገውን ጠላት ከእኩለ ቀን በኋላ ካምፕ ላይ እያለ ተስባ በመጠጋትና ጥቃት በመክፈት ሙትና ቁስለኛ አድርጋ ተመልሳለች።
በ2ቱ ቀን ግዳጅ ጠላት በርካታ ሠባዊና ቁሳዊ ኪሳራ ከማስተናገዱ ባሻገር በቀጠናችን የኃይል ሚዛኑን ብልጫ ያረጋገጥንበትም እንደነበር የ88ኛ ክ/ጦር ህ/ግንኙነት መረጃውን አድርሶናል።
አዲስ ትውልድ፣ አዲስ አስተሳሰብ፣ አዲስ ተስፋ!
የአፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 109ኛ ኮር ህ/ግንኙነት
የካቲት 4/2018ዓ.ም
ወቅታዊ ትኩስ የፋኖን እንቅስቃሴ ወቅታዊና የዕለት ከዕለት መረጃዎች ለማግኘት ይህንን የፊስቡክ ገፅ ይወዳጁ!!
https://www.facebook.com/share/1ACkV44SXg/
ሰበር!...ባሕርዳር መኮድ ካምፕ!
የሰሜን ምዕራብ ዕዝን ጨምሮ የአገዛዙ ወታደራዊ ኃይል ዋና ማዘዣ ጣቢያ በሆነው መኮድ ካምፕ ውስጥ በተቀሰቀሰ ግጭት በርካታ ወታደሮች ሙትና ቁስለኛ ተደረጉ!
የግጭቱ መነሻ ዛሬ የካቲት 04/2018 ዓ/ም ማርፈጃውን በተካሄደ ወታደራዊ የግምገማ መድረክ "በፋኖ ቁጥጥር ስር እየገቡ በሚገኙ አከባቢዎች ላይ ንፁኋንን ያነጣጠረ የድሮን ጥቃት እንዲፈፀምና በዚህም ሕዝቡ አስመታችሁን በሚል ፋኖን እንዲቃዎም ማስደረግ" የሚል መመሪያ የወረደ ሲሆን፡ "የገጠምነው ከፋኖ ጋር እንጂ ንፁኋኖች ምን አደረጉን?" በሚል መመሪያውን የተቃዎሙ የአማራ ተወላጅ የሆኑ የጦር መኮነኖች ከግምገማ መድረኩ በኋላ መረሸናቸውን የመረብ ሚዲያ ወታደራዊ ምንጮች ተናግረዋል።
ይሄንን ተከትሎ በካምፑ ውስጥ በሚገኘው ሰራዊት መካከል ከባድ የሆነ የእርስ በእርስ ውጊያ ተቀስቅሶ በርካታ ወታደሮች መገደላቸው ተሰምቷል።
በአሁን ሰዓት በካምፑ ውስጥ የአማራ ተወላጅ የሰራዊት አባላትና የጦር መኮነኖች እየተመረጡ ትጥቅ እንዲያወርዱ ተደርገው እየታሰሩ ነው።
ከዚህ በተጨማሪ ፋኖ ወደ ከተማዋ መጠጋቱን ተከትሎ ሊከዱ ይችላሉ በሚል የሚጠረጠሩ የመከላከያ ሰራዊት አባላትን በስውር እያፈነ የሚገድል ስኳድ ቡድን በካምፑ ውስጥ ተዋቅሮ ወደ ስራ ገብቷል።
በካምፑ ውስጥ የተቀሰቀሰቀሰው የእርስ በእርስ ውጊያም ይህ ዜና እስከተጠናቀረበት 8:20 ሰዓት ድረስ ተባብሶ ቀጥሏል።
"አማራዋ እናቴ ላይ የድሮን እሳት ሲዘንብ ከጠላቴ ጋር ተባባሪ አልሆንም" ያሉ በርካታ ወታደሮችም ከነ ሙሉ ትጥቃቸው ለሊቱን ከወታደራዊ ካምፑ ወጥተው ጠፍተዋል።
ደብረታቦር ምሽጎች ሁሉ ተንኮታኩተዋል።
አሁን ሰማዩም ምድሩም የአብይ ቡችሎች አይደለም ። የእሳት ባህር ሁኗል ቀጠናው።የሚያቀልጥ ውጦ የሚበላ።
የሚደርስላቸው የለም ወዳጅ ዘመድ ከሚደመሰሱ እየደወለ እጅ እንዲሰጡ ይምከር።
እስከ አሁን የተማረኩት በደህና ይገኛሉ።ፈጥነው እጅ የሚሰጡ ይተርፋሉ።
እጅ እየሰጡ ይትረፉ!!
የኦህዴድ /ብልፅግናን ሴራ ያክሽፉ!!
ዮሐንስ ንጉሱ ሙጨ
የአፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 109ኛ ኮር 88ኛ ክ/ጦር በጠላት ላይ ሰብአዊና ቁሳዊ ኪሳራ አደረሰ
*//
በዛሬው ዕለት ጥር 04/2018 ዓ. ም ከምዕ/ጎጃሟ ቡሬ ዙሪያ ወረዳ ቁጭ ከተማ የመሸገው የአገዛዙ ዘራፊና ጨፍጫፊ ሠራዊት ወደ ወምበርማዋ ወረዳ ወይንማ ቀበሌ የተለመደ አርሶ አደሩ ላይ የዘረፋ ተግባሩን ለመፈፀም ከንጋቱ 11:30 ጀምሮ ተንቀሳቅሷል። ነገር ግን የጠላት መቅጫ አይበገሬው አፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ የ109ኛ ኮር 88ኛ ክ/ጦር በፈርጣማ ክንዱ አቅምሶ እና ደቁሶ እያሯሯጠ መልሶ ከቀበሮ ጉድጓዱ ከቶት ተመልሷል።
ወይንማ እና ጭራር በእጅበጅ ተኩስ 1ኛ እና 2ኛ ሻለቃ ጠላትን ሲቆሉት ሽንዲ ከተማ ደግሞ 4ኛ ሻለቃ ከተማ ሰርጎ በመግባትና ተኩስ በመክፈት የጠላትን ትስስር እንዳይፈጥር በማድረግ የጠላትን አከርካሪ መምታት ተችሏል።
#በተያያዘ ጥር 03/2018 የክ/ጦሯ ኮማንዶ ዩኒቷ 5ኛ ሻለቃ ሽንዲ ከተማ የመሸገውን ጠላት ከእኩለ ቀን በኋላ ካምፕ ላይ እያለ ተስባ በመጠጋትና ጥቃት በመክፈት ሙትና ቁስለኛ አድርጋ ተመልሳለች።
በ2ቱ ቀን ግዳጅ ጠላት በርካታ ሠባዊና ቁሳዊ ኪሳራ ከማስተናገዱ ባሻገር በቀጠናችን የኃይል ሚዛኑን ብልጫ ያረጋገጥንበትም እንደነበር የ88ኛ ክ/ጦር ህ/ግንኙነት መረጃውን አድርሶናል።
አዲስ ትውልድ፣ አዲስ አስተሳሰብ፣ አዲስ ተስፋ!
የአፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 109ኛ ኮር ህ/ግንኙነት
የካቲት 4/2018ዓ.ም
+1
ደብረታቦራችን...
አፋብን ጎንደር ጠቅላይ ግዛት እዝ እና በላይ ዕዝ በጥምረት ጠላትን እያርበደበዱት ነው ደብረታቦር ውጊያው እንደቀጠለ ነው እስካሁኑ ሰዓት ድርስ የጠላት ድሮኖች ወይብላ ማሪያም አየር ማረፊያ አካባቢ እንዲሁም ቄራ ኡራኤል ቤተክርስቲያን አካባቢ በተጨማሪ እየሱስ በታች ልዩ ስሙ ወርቄን እሚባል ቦታ በተጨማሪም እብናት መውጫ ልዩ ስሙ ርብ ላይ ከውጊያ ቀጠና ውጭ ድሮን የተጣለ ሲሆን ንፁሃን ገበሬዎችን ጨፍጭፏል ይህ በእንዲህ እንዳለ ከባህርዳር የተንቀሳቀሰው የጠላት ሰራዊት አለምሳጋ ላይ በቆረጣ ዱቄት ሆኖ ወደ መጣበት እየፈረጠጠ ነው።
በወገን ጥምር ጦር በኩል ምንም አይነት ጉዳት አልደረሰም
ዮሐንስ ንጉሱ ሙጨ
#ለሰማዕታት_ክብር_ለቀጣዩ_ግብ_ፅናት‼️
አፋብን ምስራቅ አማራ ቀጠና ምንሊክ ዕዝ
ምስራቅ አማራ ኮር 1 ሐውጃኖ ክፍለ ጦር ንጉስ ቸኮለ ሻለቃ የተደረገው የመታሰቢያና የቃል ኪዳን ፕሮግራም!
በሐውጃኖ ክፍለ ጦር ስር የሚገኘው ሶስተኛ ሻለቃ (ንጉስ ቸኮለ) ሻለቃ፤ በታላቅ ወታደራዊ ስነ-ስርዓት ላለፉት ሶስት አመታት ለአማራ ህልውና ሲሉ ውድ ህይወታቸውን የገበሩ የጀግኖችን ዝክረ-ሰማዕት አካሂዷል። ይህ ፕሮግራም የሀዘን መግለጫ ሳይሆን፣ "ጀግና ይሰዋል፣ ትግል ይቀጥላል!" የሚለው የጸና እምነት በተግባር የተረጋገጠበት የታሪክ መድረክ ሆኖ ውሏል።
የጀግኖች ገድል እና የከፈሉት ዋጋ ባለፉት ሶስት አመታት በየመድረኩና በየውጊያ አውደ-ግንባሩ ለአማራ ህዝብ ክብርና ማንነት ሲሉ የወደቁ ሰማዕታት፣ በደማቸው የፃፉት ገድል ዛሬም በሻለቃው አባላት ዘንድ በከፍተኛ አክብሮት ተነስቷል።
"ሰማዕታቱ የከፈሉት ዋጋ ለዛሬው ጥንካሬያችን መሰረት ነው" በሚል መንፈስ፣ ሻለቃው የእነሱን አደራ ለመሸከም ያለውን ዝግጁነት አሳይቷል። እያንዳንዱ ሰማዕት የወደቀው ለትልቅ አላማ መሆኑንና ያ አላማ ዛሬ በጓዶቻቸው ትከሻ ላይ በፅናት መቀጠሉ ተገልጿል።
አዲስ መንፈስ እና የቃል ኪዳን መታደስ
የመታሰቢያ ፕሮግራሙ ዋነኛ ኩነት ሻለቃው የገባው አዲስ ቃል ኪዳን ነው። "ጀግና ይሰዋል፣ ትግል ይቀጥላል!" በሚለው የትግል መርህ መሰረት፣ የሰማዕታቱ አላማ ግቡን ሳይመታ እንደማይቀርና የጓዶቻቸው ደም በከንቱ እንዳይቀር ለመስራት መላው የሻለቃው አባላት ተማምለዋል።
ዋነኛ የቃል ኪዳኑ ነጥቦች፦
✅የአላማ ፅናት፦ ሰማዕታቱ የወደቁለትን የአማራነት ግብ ዳር ለማድረስ እስከ መጨረሻው መታገል!
✅አዲስ መንፈስ፦ ካለፈው ትግል ልምድ በመቅሰም፣ በአዲስ ወታደራዊ ወኔና ስነ-ልቦና ወደ ቀጣዩ ምዕራፍ መሸጋገር!
✅መስዋዕትነት፦ ለአማራ ህዝብ ነጻነትና ህልውና ሲባል አስፈላጊውን ዋጋ ሁሉ ለመክፈል ዳግም ራስን ማዘጋጀት!
"የጓዶቻችንን አላማ ግብ እናደርሳለን!"
በዕለቱ የክፍለ ጦር አመራሮች ፣የሻለቃው አመራሮችና አባላት በጋራ በገቡት ቃል፣ የሰማዕታቱን መንፈስ ተላብሰው ለቀጣይ ተልዕኮ ዝግጁ መሆናቸውን አረጋግጠዋል። "እነሱ የወደቁት እኛ እንድንቆም ነው፤ እኛ የምንቆመው ደግሞ ህዝባችን እንዲከበር ነው" በሚል መሪ ቃልና በታላቅ የቆራጥነት መንፈስ ፕሮግራሙ ተደምድሟል።
ይህ በንጉስ ቸኮለ ሻለቃ የተካሄደው መርሃ-ግብር፣ የአማራ ህዝብ የህልውና ትግል በፅኑ መሰረት ላይ መቆሙንና ተተኪው ትውልድና ጓዶቻቸው አደራውን ለመረከብ ቆርጠው መነሳታቸውን ለወዳጅም ለጠላትም ያስመሰከሩበት አጋጣሚ ሆኖ አልፏል።
ጀግና ይሰዋል፣ ትግል ይቀጥላል!
መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልዉና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!
ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!
አፋብን ምኒልክ ዕዝ ምስራቅ አማራ ኮር 1 ሐውጃኖ ክፍለ ጦር ህዝብ ግንኙነት ፋኖ አሰፋ መለስ
04/ዐ6/2018 ዓ.ም
#አዛምቱት
ከባህርዳር ከተማ በመውጣት ወደ አባይማዶ መስመር ወይም ወደ ጎንደር መውጫ እየተንቀሳቀሰ ያለ የኦነግ/የብልፅግና/ ወታደር አለ ተብሏል ለጥንቃቄም ሆነ ለአቀባበል ያመች ዘንድ መረጃውን አጋሩት ቻናላችንም ይወዳጁን
የጠላት ሀይል በኮሮቹ ጥምር ጦር እየተራገፈ ነው ‼️
#በጃዊ ወረዳ ሙሉ ቀጠናዎች ኔትወርክ አጥፍቶ ከተለያዩ ቦታዎች አሰባስቦ በርካታ ወራሪ ሰራዊቱን ወደ ተለያዩ ቀጠናዎች ለመንቀሳቀስ ቢሞክርም ብዙ ርቀት ሳይሄድ ባምቡልክ ቀበሌ ጀግኖች አምባ ተራራ ላይ ተከቦ በጀግኖች ክንደ ብርቱ፣ የአማራ ኩራት፣የእሳት ነበልባሎች የአፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 105ኛ ኮር 66ኛ ክ/ጦር፣ 44ኛ ክ/ጦር፣109ኛ ኮር፣206ኛ ኮር፣የቴዎድሮስ ዕዝ ተወርዋሪ ኮማንዶ ክ/ጦር የተዉጣጣዉ ጥምር ጦር የተሳተፈበት አዉደ ዉጊያ የጠላትን ሀይል ሙት እና ቁስለኛ አድርገዉታል።
ለ8 ተከታታይ ቀናት ከበባ ዉስጥ የነበረዉ የጠላት ሃይል ወደ መጣበት ለመመለስ ተደጋጋሚ ጥረት ቢያደርግም ከባድ ምት እየደረሰበት አሳሩን ሲበላ ሰንብቷል።
በጥምር ጦሩ የተመታው የጠላት ሀይል በ03/06/2018 ዓ.ም ሌሊት አስከሬኑን በየቦታዉ እየቀበረ እና እየጣለ ወደ ዳንጉር ወረዳ የልፍኝ ቀበሌ ፈርጥጧል ሲል የ66ኛ ክ/ጦር ህ/ግንኙነት ዘግቧል።
አዲስ ትዉልድ፣አዲስ አስተሳሰብ፣አዲስ ተስፋ !!!
የአፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ የ105ኛ ኮር ህ/ግንኙነት
+1
አፋብን በላይ ዕዝ ደጃዝማች 4ኛ ኮር
በማዕ/አርማጭሆ ወረዳ ማሰሮደንብ
ሚሊሻ፣ፖሊስ አድማ ብተና እና የብአዴን ሹመኞች ወደ ቀልባችሁ ተመለሱ...
እራሳችሁን አትርፉ
የዓብይ አህመድን ሴራ አክሽፉ!!
ፍኖተ-አማራ ሚዲያ ወቅታዊና ትኩስ የፋኖ እንቅስቃሴን ጎልጉሎ በማውጣት ግንባር ቀደም ሁናለች። ከታች ባለው የቴሌግራም ሊንካችን ጆይን በማለት ይወዳጁን!! አድራሻችን👇👇👇👇 ‼️
https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk
#አስቸኳይ_መረጃ_ለደብረታቦር_አካባቢው‼️
አገዛዙ አየር ሀይል ድሮንና ካስፈለገም ጀት እንዲጠቀም ትዕዛዝ ወርዷል። ደብረታቦር ላይ እየተጠቀመ ካለው ድሮን በተጨማሪ ሁለት ድሮኖች ከደብረዘይት ተነስተው ወደ ሰሜን አቅጣጫ ወጥተዋል። አንድ የጦር ሄሊኮፕተር ባህርዳር ላይ እየተዘጋጀ ነው።
ከኦሮሚያ ክልል ተጭኖ የመጣው መከላከያም ወደ ደብረታቦር እየተቃረበ በመሆኑ አገዛዙ ኔትወርክ ሊያጠፋ ስለሚችል መረጃውን አሁንኑ ለወገን ኃይል ይድረስ‼️
መረጃው ሼር ይደረግ‼️
04/ዐ6/2018 ዓ.ም
ዛሬ 04/05/2018/ከሰሜን ጎንደር ደባርቅ ዞን ጧት ብዛት ያለው መከላከያ እና አድማ ብተና እንዲሁም ከባህርዳር ወደ ጎንደር ።ብር ታቦር ተጭኗል መረጃውን አድርሱልን ለወገን ጦር
ከውስጥ አርበኞች የተላከ
ሰበር የድል ዜና !!
6 ቀኑን ያስቆጠረው የጉና ክፍለ ጦር የተጋድሎ አውደ ውጊያ የብልፅግናን አገዛዝ ጥምር ጦር ደብረ ታቦር ላይ አከርካሪው ተመታ !!
ሰበር ዜና!
ጀግናው የፋኖ ሰራዊት ከትናንት ጀምሮ ባደረገው ከባድ ውጊያ ጥንታዊቷንና ታሪካዊቷ ደብረታቦር ከተማን ተቆጣጠረ!
በተለይ ከትናንት የካቲት 03/2018 ዓ/ም ለዛሬ አጥቢያ ለሊት ጀምሮ በከተማዋ ልዩ ስማቸው ግራር ሰፈር፣ መሎ፣ ማረሚያ ቤት፣ ጎንደር በር፣ አባረጋይ፣ ወይብላ ማርያም፣ በተባሉ አከባቢዎች በተደረገ ውጊያ ትላልቅ የተባሉ የጠላት ምሽጎችን የሰበረው ጀግናው የሕዝብ ልጅ ፋኖ፡ ከንጋት በኋላ ከተማዋን በቁጥጥሩ ስር ማስገባቱን የመረብ ሚዲያ የግንባር ዘጋቢዎች ለማረጋገጥ ችለዋል።
በመሃል ከተማዋ ህብረት ሆቴል ላይ ለጊዜው ስሙና ማዕረጉ በውል ያልተለየ አንድ ከፍተኛ ወታደራዊ አዛዥ ሲገደል፡ በከተማዋ እየሱስ ተራራ ላይ የነበረውና የጠላት ብልፅግና ኃይል "አይነኬ" በሚል የሚተማመንበት የኮንክሪት ምሽግ ተሰብሮ በርካታ የአገዛዙ ወታደሮች ተደምስሰዋል፡ ገሚሱ እጃቸውን ሰጥተዋል።
ጥንታዊቷንና ታሪካዊቷ ደብረታቦር ከተማን በቁጥጥሩ ስር ያደረገው ጀግናው የሕዝብ ልጅ ፋኖ፡ አዲስ ዘመንና ወረታን ነፃ ለማውጣት ወደፊት እየገሰገሰ እንደሚገኝ የፍኖተ-አማራ ሚዲያ የግንባር ዘጋቢዎች አረጋግጠዋል።
ባህርዳር ላይ በብልፅግና ቤት ከባድ ትርምስትና ሽብር ተፈጥሯል። ካድሬው በጭንቀት ተውጧል።
ከባህርዳር አፍንጫ ስር ጭስ አባይ በፋኖ ቁጥጥር ስር መግባቷን መረብ ሚዲያ ተመልክቷል።
መረበኞች ነን መረጃ አጥማጆች!
