FACE THE TRUTH
前往频道在 Telegram
አብዱልከሪም እባላለሁ ! እዚህ ቻናል ላይ እስልምናን የተመለከቱ ፖለቲካዊ ሀሳቦችን , ታሪካዊ ክስተቶችን እንዲሁም የኃይማኖት ንፅፅር መረጃዎችን አቀርባለሁ። [ የትኛውም ማህበር እንዲሁም ፓርቲ አባል አይደለሁም ] --- ዘና በሉ... ፈገግ እያልንን እንማማር አላህ ያግዘን !! (B T G O G).
显示更多📈 Telegram 频道 FACE THE TRUTH 的分析概览
频道 FACE THE TRUTH (@facethetruth22) 阿姆哈拉语 语言赛道中的 是活跃参与者。目前社区聚集了 14 413 名订阅者,在 宗教与灵性 类别中位列第 5 885,并在 埃塞俄比亚 地区排名第 2 349 位。
📊 受众指标与增长动态
自 невідомо 创建以来,项目保持高速增长,吸引了 14 413 名订阅者。
根据 30 八月, 2026 的最新数据,频道保持稳定运转。过去 30 天订阅人数变化为 223,过去 24 小时变化为 10,整体触达仍然可观。
- 认证状态: 未认证
- 互动率 (ER): 平均受众互动率为 20.97%。内容发布后 24 小时内通常能获得 23.59% 的反应,占订阅者总量。
- 帖子覆盖: 每篇帖子平均可获得 3 023 次浏览,首日通常累积 3 400 次浏览。
- 互动与反馈: 受众积极参与,单帖平均反应数为 372。
📝 描述与内容策略
作者将该频道定位为表达主观观点的平台:
“አብዱልከሪም እባላለሁ ! እዚህ ቻናል ላይ እስልምናን የተመለከቱ ፖለቲካዊ ሀሳቦችን , ታሪካዊ ክስተቶችን እንዲሁም የኃይማኖት ንፅፅር መረጃዎችን አቀርባለሁ። [ የትኛውም ማህበር እንዲሁም ፓርቲ አባል አይደለሁም ] --- ዘና በሉ... ፈገግ እያልንን እንማማር አላህ ያግዘን !! (B T G O G).”
凭借高频更新(最新数据采集于 31 八月, 2026),频道始终保持新鲜度与高覆盖。分析显示受众积极互动,使其成为 宗教与灵性 类别中的关键影响点。
14 413
订阅者
+1024 小时
+557 天
+22330 天
帖子存档
14 413
የማስተር ሀሰን ጥያቄ ተቀባይነትአያገኝም
ካስታወሳችሁ Mube media ነገሮችን ወደ ኃይማኖት በማዞር ችግር እየፈጠረ ነበር። 2 ጊዜ ስህተት ሰርቷል ።
መጀመሪያ ከውድድሩ በፊት ሴዶን አስገብቶ ነገሩን የሀይማኖት አስመሰለው ። ከዛ እሱ ሳያንስ ደግሞ ቀጣይ አንድ በኃይማኖት ስሜት ተነሳስቶ የሚናገር ሰው አቀረበ ይህም ሰው ሴዶን አይቼው ተው ብዬው ነበር አሁን ለዲኑ ክብር እበቀላለሁ የሚል ሰው አምጥቶ በሚዲያ ሌላ ነገር ፈጠረ። የምትቀርቡት ሰዎች ንጉሩት የሚቀሳሰር እና የማይቀሳሰር ነገር ይለይ። እስልምና ላይ ጥላቻን የሚዘሩ ሰዎችን ሲከላከል ኃይማኖታዊ ነገሮችን ሲያስተባብር ነው የምናውቀው ነገር ግን ሁሉ ቦታ ኃይማኖታዊ ነገር የለም ማቀሳሰር አቁም በሉት። ለማንኛውም የውድድሩ አዘጋጆች የማስተር ሀሰንን ጥያቄ በጭራሽ እንደማይቀበሉ ዋናው አዘጋጅ በአግራሞት መልኩ ሲናገር አስተባባሪው የሆነ ቪድዮ ስር ጥያቄው ተቀባይነት እንደማያገኝ ፅፏል።
(ድብድብ በእስልምና ይቻላል ብዬ ሳይሆን ነገረ ስራቸውን እየተቸው ነው ነገሩ ሲበርድ ከእስልምና አንፃር ያለውን ነገር እናየዋለን )
✍️ Abdulkerim
https://t.me/Facethetruth22
------------------------------------------------------
14 413
🔘 ቀድሜ መድኃኒቱን ሰጥቻችሁ ነበር 🔘
ድብድብ አይቻልም ብዬ እንደ ሌሎች ኡስታዞች ጥግ መያዝ እችል ነበር ግን ክርስቲያኖች ቀድመው ስፖርቱን የኃይማኖት አድርገው ሴዶ እንዴትም ተሸንፎ ፖለቲካቸውን ለመንዛት ተዘጋጅተው እየጠበቁ ስለነበር በጭፍን ስትጋጩ ማየት አልቻልኩም።
ሀሳባቸውን ለማፍረስ ይሆናችሁ ዘንድ ካስታወሳችሁ በሰዓቱ ረቢቅ አሸነፈ ዘሀራም አሸንፋለች ከዛ የቀረው እድሪስ ነው እሱ ካሸነፈ ጨርሰናል የጆኒ ማሸነፍ ችግር አይፈጥርም አሰልጣኙ ኡመር ጀማል ነው ሙስሊም ነው። በምንም ፖለቲካ እንደማትመቱ ስነግራችሁ በቪድዮም ሳሳያችሁ ነበር። ብዙ ሰው ግን እዚህ ቻናል ስለሌለ መድኃኒቱ አልደረሰውም ።
በቃ ጭራሽ ሴዶ ተሸነፈ ብሎው የኃይማኖት ለቅሶ ገቡ። እንበቀላለን ብለው ሌላ ህልም አይቻለሁ ክብር አስመልሳለሁ የሚል ስፖርት እና የኃይማኖት ጦርነት የተምታታበት ሰው አመጡ። ሌላ ስህተት ።
🔘 ለማንኛውም ከላይ በቪድዮ እንደምታዩት ጆኒ አባይ ቲቪ ላይ ከውድድሩ በኃላ አጠገቡ ያሉ አሰልጣኞቹን ሲያመሰግን ያው ኡመር ጀማል አጠገቡ የለም ግን ድሮ ስላሰለጠነው ሲያመሰግነው ይታያል። እኔ ስሰጣችሁ የነበሩትን ቪድዮዎች ይዛችሁ ሁሉንም የማውቀን ያስተማረኝ እሱ ነው ከሚለው ጋ ብታያይዙት የክርስቲያኖችን ፖለቲካ በቀላሉ ታበላሹ ነበር። እንደው እነሱ ያፍሩ ነበር።
✍️ Abdulkerim
https://t.me/Facethetruth22
------------------------------------------------------
14 413
🎙 Abdulkerim
https://t.me/Facethetruth22
------------------------------------------------------
14 413
የሙስሊም ሚዲያዎችን አንድ ልንላቸው ይገባል።
🔘 አንዳንድ የሙስሊም ሚዲያዎች በእስልምና የማይፈቀደውን ድብድብ ሙስሊሙ ህዝብ መሀል በማጋጋል ስፖርቱን ወደ ኃይማኖት በመቀየር ሌላ አይነት ነገር እያስመሰሉት ነው። ይህ የምታዩት ማስተር ሀሰን ይባላል ። በጣም ጠንካራ በቻይና እንዲሁም ሌሎችም ሀገራት ሄዶ በተለያዩ ስፖርቶች በመሳተፍ አሸንፏል። ይህ እንደ ግሉ ስናየው መልካም ሆኖ ሳለ ከፈለገ ራሱን ችሎ ለመወዳደር መግባት ሲገባው ነገሩን የኃይማኖት አድርጎ በማሰብ እና በዛ እልህ ሆኖ ለመግባት ማሰብ ጭራሽ ደግሞ ይህን በአደባባይ መናገር ትክክል አይደለም ።
🔘በነገራችን ላይ በውድድሩ ሙስሊም አሸናፊዎች ነበሩ ለምሳሌ ረቢቅ ሳኒ በዝረራ ሲያሸንፍ በተከታታይ 2ኛ ጊዜ ነው። ዘሀራም አሸንፋለች። ከጆኒ ቡድኖች ውስጥ አንዱ እድሪስ ነው እሱም አሸንፏል። ነገር ግን ግሎ የተነሳው የሴዶ መሸነፍ ነው። ሴዶ ስላልሰራ ተሸነፈ እንጂ በኃይማኖት አይደለም ። ጆኒ ራሱ አስተማሪው ሙስሊም ነው ። ኡመር ጀማል ነው ብለን ብንጮህ ሊሰሙን አይደለም ። በአለም ደረጃ UFC ላይ ራሱ የነገሱት ሙስሊሞች ናቸው። የሙስሊም ሚዲያዎች ህዝቡን አጉል ነገር ውስጥ እየከተቱት ነው።
በነገራችን ላይ ቦክስ አይቻልም በኢስላም ይህን ረስቼ አይደለም ግን መጀመሪያ እየተዘዋወረ ያለው የተዛባ ነገር ላጥራ ብዬ ነው ስተነትንላችሁ የቆየሁት። ከኢስላም አንፃር ያለውን ነገር እነግራችኋለሁ።
✍️ Abdulkerim
https://t.me/Facethetruth22
------------------------------------------------------
14 413
ቢመቸኝ በአካል ተገኝቼ የማየው የእግዚአብሔር እና የያዕቆብን ትግል ነበር።
በመፅሐፍ ቅዱስ ዘፍጥረት 32:28 ላይ ለሊት ሙሉ እንደታገሉ ተቀምጧል ። ፅፌበታለሁ ይህን 👉 (ተጫን) ተጭናች አንብቡ።
🔘 እርግጠኛ ነኝ እናንተም ትገኙ ነበር መገኘት ብቻ ሳይሆን እኔማ ቆምር ነበር ያለኝን ብር አሲዝ ነበር አይቻልም አውቃለሁ ግን ለአምላክ ነውኮ የምመድበው ራሱ ሲጣላ ነውኮ የመደብኩት የሚደብረው አይመስለኝም ። መጨረሻው ግን ተሸንፎ ነው ያለቀው። አስቡት ዜናው ራሱ ምን ሊሆን እንደሚችል
"የፍጥረተ አለሙ ፈጣሪ ከያዕቆብ ጋ ታግሎ እስኪነጋ ድረስ ጥረት ቢያደርግም በመጨረሻ ተሸነፈ።"
🔘 እኛ ሙስሊሞች ነን ከድክመት የጠራውን አላህን ነው የምናመልከው። በአምላክ ላይ የተቀጠፉ ውሸቶችን የያዙ መፅሐፍትን ሳይሆን ስህተት የሌለውን የመጨረሻውን የአምላክ መልዕክት የሆነውን ቁርዓንን ነው የህይወት መመሪያ ያደረግነው። የሚሞት , በትግል የሚሸነፍ አምላክ የለም። ክርስቲያን ኑ ዳኑ !
( ከላይ ያለው ፎቶ ራሳችሁ ክርስቲያኖች የሰራቹት ነው እኔ የሰራውት አይደለም )
✍️ Abdulkerim
https://t.me/Facethetruth22
------------------------------------------------------
14 413
በሴዶ ምክንያት ልባችሁ ለተሰበረ
መከራዬን አየሁኮ እናንተን በማስረዳት 😁
ጆኒ በአስተማሪው ኡመር ጀማል እየታነቀ ነው የተማረው። ዝምሎ ራሱ ለጉብኝት ሲመጣ ያንቀዋል ። ይኸው በቪድዮ መረጃ። ሴዶ አልተማረም ። ሳይማር ገባ ከዛ ታነቀ ። ሴዶ ቴኳንዶ ነው የተማረው ። grappling , jujitsu አልተማረም።በቃ ያለው ነገር ይሄ ነው። እናንተን በማፅናናት ጊዜ ፈጀውኮ ።
እህቶች ደግሞ ተጠንቀቁ ስሜቱ ካለቀቀሽ በቃ 15 ቀን በዚህ መልኩ ከቀጠልሽ 16ኛው ቀን ላይ ሰይዶን ስታይው ነብዩ ዩሱፍ (ዐሰ) አይነት መልክ ያለው ሆኖ ይታይሻል። ያኔ ግን አልቋል መድኃኒት የለንም !!!
✍️ Abdulkerim
14 413
እግዚአብሔር በትግል ተሸንፎ ያውቃል ።
🔘 መፅሐፍ ቅዱስ ላይ እንደተፃፈው እግዚአብሔር ከያዕቆብ ጋ ለሊት ሙሉ ሲታገል እንደነበር እና ቆይቶ በመጨረሻ ግን ያዕቆብ እንዳሸነፈው መፅሐፍ ቅዱስ ይናገራል።
📕ዘፍጥረት 32:24-27
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
²⁴ ያዕቆብ ግን ለብቻው ቀረ፤ አንድ ሰውም እስከ ንጋት ድረስ ይታገለው ነበር።
²⁵ እንዳላሸነፈውም ባየ ጊዜ የጭኑን ሹልዳ ነካው፤ ያዕቆብም የጭኑ ሹልዳ ሲታገለው ደነዘዘ።
²⁶ እንዲህም አለው፦ ሊነጋ አቀላልቶአልና ልቀቀኝ። እርሱም፦ ካልባረክኸኝ አልለቅቅህም አለው።
²⁷ እንዲህም አለው፦ ስምህ ማን ነው? እርሱም፦ ያዕቆብ ነኝ አለው።
²⁸ አለውም፦ ከእንግዲህ ወዲህ ስምህ እስራኤል ይባል እንጂ ያዕቆብ አይባል፤ ከእግዚአብሔር ከሰውም ጋር ታግለህ አሸንፈሃልና።
🌐 እንኳን ሴዶ እግዚአብሔርም ተሸንፎ ያውቃል ሴዶ ፍጡር ስለሆነ ራሱን አሻሽሎ ይገባል ። እግዚአብሔር ተሻሽሎ ይሆን ??
🔘 የፕሮቴስታንት ምሁራንን ማብራሪያ ብታዩ
ነገሩ Christophany እንደሆነ ይናገራሉ።
ለምሳሌ Joseph Benson ሲያብራራ ያዕቆብ ሲታገል የነበረው ሰው የእግዚአብሔር ልጅ ዘላለማዊ ቃል በሰው መልክ ተገልጦ እንደሆነ ይናገራል።ዞሮ ዞሮ ያው ኢየሱስ ጋ ነበር ያዕቆብ የታገለው ማለት ነው። ኢየሱስ ተሸነፈ ነው የሚሆነው ።
✍️ Abdulkerim
https://t.me/Facethetruth22
------------------------------------------------------
14 413
🎙 Abdulkerim
ድብድብ አይፈቀድም ብዬ
ላስረዳ አስቤ መጀመሪያ በሴዶ መሸነፍ የተሰበሩትን ላፅናና😂
https://t.me/Facethetruth22
------------------------------------------------------
14 413
+3
ሴዶ ተሸንፏል ጆኒ አሸንፏል ::
የጆኒ አሰልጣኝ የሆነው ኡመር ጀማል ማን ነው ?
በአፍሪካ አሉ ከሚባሉ MMA መምህራን አንዱ የሆነው ኡመር ጀማል ተፅዕኖ ፈጣሪ የሆኑ ተማሪዎችን አፍርቷል። ኬኒያ ያሉት እያሸነፉ ሲገኙ በኢትዮጵያ ላይ ደግሞ በስፖርቱ ተፅዕኖ እየፈጠረ የሚገኘው ጆኒ አንዱ የእሱ ተማሪ ነው። ኡመር ጀማል በዚህ ልክ በአፍሪካ ደረጃ ተፅዕኖ ለመፍጠር እዚህ ለመድረስ ምን እንዳነሳሳው በሚዲያ ቀርቦ ሲናገር ከላይ በቪድዮው እንደምታዩት ሁሌም መሪ መሆን ይፈልግ እንደነበር ከመሆኑ በፊት እንኳን የውሸት ራሱ እንደመሪ ይሆን እንደነበር ዙሪያው ያሉ ሰዎች ላይ ተፅዕኖ መፍጠር አላማ እንደነበረው ይናገራል ።
ይኸው ዛሬ እሱ ያስተማራቸው ልጆች ህዝብ እየዘረሩ ነው። በነገራችን ላይ ለጆኒ ትልቅ ክብር አለኝ አስተማሪውን አልረሳም። አንዳንዴ ሰዎች ከፍ ካሉ በኃላ credit ለመስጠት ይቸገራሉ። ኩራት ይገላቸዋል።
ሴዶ ተሸነፈ ብላችሁ የምታዝኑ ሰዎች ሴዶ ጠንካራ ነው ግን Jujitsu grappling አልሰራም የተሸነፈው በዚህ እንጂ የጥንካሬ ችግር አይደለም ። 2ቴ እጁ ሊሰበር ተይዞ ባለው ጥንካሬ ችሎ ይዟል ሌላ ቢሆን አልቆለታል። ግን በቃ grappling jujitsu ዜሮ ነው። ጆኒ ደግሞ በተቃራኒው በአፍሪካ ደረጃ ስሙ የገነነው መምህር ኡመር ጀማል ስር ነው ሲማር ነው የነበረው።
🔘ኡመር ጀማል ሙስሊም ስለሆነ ብዙም የሚዲያ ሽፋን አይሰጠውም።ያው ለዝና ያህል እንጂ ሊወዳደር አይደለም። በአፍሪካ ደረጃ አሰልጣኝ ነው። መንደር አይወርድም።
🌐COACH OMAR JEMAL🌐
✍️ Abdulkerim
https://t.me/Facethetruth22
------------------------------------------------------
14 413
+3
ሴዶን ተሸንፏል ጆኒ አሸንፏል
የጆኒ አሰልጣኝ የሆነው ኡመር ጀማል ማን ነው ?
በአፍሪካ አሉ ከሚባሉ MMA መምህራን አንዱ የሆነው ኡመር ጀማል ተፅዕኖ ፈጣሪ የሆኑ ተማሪዎችን አፍርቷል። ኬኒያ ያሉት እያሸነፉ ሲገኙ በኢትዮጵያ ላይ ደግሞ በስፖርቱ ተፅዕኖ እየፈጠረ የሚገኘው ጆኒ አንዱ የእሱ ተማሪ ነው። ኡመር ጀማል በዚህ ልክ በአፍሪካ ደረጃ ተፅዕኖ ለመፍጠር እዚህ ለመድረስ ምን እንዳነሳሳው በሚዲያ ቀርቦ ሲናገር ከላይ በቪድዮው እንደምታዩት ሁሌም መሪ መሆን ይፈልግ እንደነበር ከመሆኑ በፊት እንኳን የውሸት ራሱ እንደመሪ ይሆን እንደነበር ዙሪያው ያሉ ሰዎች ላይ ተፅዕኖ መፍጠር አላማ እንደነበረው ይናገራል ።
ይኸው ዛሬ እሱ ያስተማራቸው ልጆች ህዝብ እየዘረሩ ነው። በነገራችን ላይ ለጆኒ ትልቅ ክብር አለኝ አስተማሪውን አልረሳም። አንዳንዴ ሰዎች ከፍ ካሉ በኃላ credit ለመስጠት ይቸገራሉ። ኩራት ይገላቸዋል።
ሴዶ ተሸነፈ ብላችሁ የምታዝኑ 3 ወር ሰርቶ ጆኒን ካሸነፈኮ በቃ ኡመር ጀማል በሚዲያ በአፍሪካ በዚህ ልክ የተሰጠው ደረጃ ወሬ ነው ማለት ነውኮ። በነገራችን ላይ ኡመር ጀማል ሙስሊም ስለሆነ ብዙም የሚዲያ ሽፋን አይሰጠው ይኼኔ ሌላ ኃይማኖት ተከታይ ቢሆን የት በደረሰ።
🌐COACH OMAR JEMAL🌐
✍️ Abdulkerim
https://t.me/Facethetruth22
------------------------------------------------------
14 413
ሰይዶ ተሸንፏል። ጆኒ አሸንፏል።
ጆኒኮ ተናግሯል። እኔን የሚያሸንፈኝ አስተማሪዬ ብቻ ነው። ኡመር ጀማል አለኮ።
ሴዶ 3 ወር ሰርቶ ስንት አመት ኡመር ጀማል ስር የተማረውን ጆኒን ካሸነፈ ታድያ ኡመር ጀማል አይችልም ማለት ነውኮ
ኡመር ጀማል ከባድ ሰው ነው ማለት ነው ።
14 413
ጨርሰናል ሰዎች ተኙ ። 3ቱ ሙስሊሞች አሸንፈዋል።የቀረው ሴዶ ነው። ጆኒ ካሸነፈም
የአሰልጣኝ ኡመር ጀማል ውጤት ነው ።
ሴዶ ካሸነፈም ችግር የለውም።
መረጃ በቪድዮ ። ከራሱ ከጆኒ አፍ ስሙ ።
14 413
+1
እድሪስ በመጀመሪያው ዙር ጨዋታውን ጨረሰው። አሸንፏል።
ዘሀራ አሸነፈች
ረቢቅ ሳኒ አሸነፈ
እድሪስ አሸነፈ
🌐 ሴዶ ካሸነፈ 100% ዘጋን ማለት ነው።
ባያሸንፍ ራሱ ጨርሰናል ።
ጆኒ ካሸነፈ አስተማሪው ኡመር ጀማል ነው ብለን እንጨርሳለን ። 😁
14 413
መንግስት ይወዳል እንዲህ አይነት ዝግጅት ?
በጣም በደስታ ። ህዝቡን ያዘናጋል ። እንደው የጥንቷ የስልጣኔ ሀገር ሮም መሪዎቿ ህዝብ እንዳያምፅ ለማዘናጋት ነፃ ዳቦ እና በተደጋጋሚ ሰርከስ ይዘጋጅ ነበር።
"ሮም ስትወድቅ ሰርከስ ነበር " ሲባል
ከሰማችሁ ለዛ ነው ።
🌐 ፋኖ ነህ ?
ወንድሜ ተረጋጋ እኔ ደቡብ ነኝ ወንድሜ 3ቱ ብሄር ውስጥ መስዬህ ነው 😁:: የትኛውም መንግስት የሆነ ችግር ይኖራል ያንን እስኪፈታ ህዝብ ቢዘናጋለት ደስ የሰለዋል ለማለት ነው ።
14 413
እድሪስ እንዳይሸነፍ እንጂ
እድሪስ ካሸነፈ በቃ ጨረስንኮ
የሴዶ እና ጆኒ ድብድብ
ማንም ያሸንፍ የእኛ ነጥብ ነው።
ከተሸነፈ ለራሱ ነው እኛን ምን አገባን
እኛ ጆኒን ያሰለጠነው ኡመር ጀማል ነው ብለን ቪድዮ እናሳያለን ። ጆኒ አለኮ ማውቀውን ሁሉ ያስተማረኝ እሱ ነው አለኮ ።አሸናፊው ኡመር ጀማል ነው ። አለቀ። እድሪስ ከተሸነፈ ነው ችግር የሚሆንብን
14 413
ልጁን ገላገለው
Rebik sani kedir.
( ቦክስ እንደ ስፖርት አይቻልም ነግሬሃለሁ:: ነገሩ ካለቀ በኃላ ነግራቹሃለሁ አብራርቼ)
🌐 ውድድሩን ኢስላም ከክርስቲያን አይነት ሲጫወቱ አናደውኝ እንዘግብ እስከጥግ ነገሩን ብዬ ነው ።😁
2 ሙስሊሞች አሸንፈዋል እስካሁን ።
14 413
Rebik sani kedir አሸንፏል።
ይህ ቪድዮ የአሁን አይደለም just ልጁን እንድታስታውሱት ነው ያመጣሁት። በዛሬው ዘርሮ አሸንፏል።
ያው መዝናኛ በሚል ድብድብ ደም ማፍሰስ አይቻልም ብንል ይኸው ሳንፈልግ አላሁ አክበር እያሉ ሱጁድ እያደረጉ በደካማ ጎናችን ይመጣሉ ግራ ገባንኮ ወገን 😁😁
14 413
🌐ህዝቤ የሴዶ እና ጆኒ ድብድብ የኃይማኖት ሲያረጉት ሳይ ኦኦ አልኩና ... እኔ ቀድሜ መድኃኒት አዘጋጅቻለሁ። ሴዶ ካሸነፈ አሸነፈ ነው።
ጆኒ ካሸነፈ መድኃኒቱ ከላይ በቪድዮ እንደምታዩት አስተማሪው ኡመር ጀማል ነው። ማቀውን በሙሉ እሱ ነው ያስተማረኝ እሱ ነው አለኮ በአንደበቱ። የኡመር ጀማልን ጥበብ ነው የምናደንቀው አለቀ !!
አሪፍ መድኃኒት አይደል 😁😁
14 413
Zehara አሸንፋለች ።
የድብድብ ደም የማፍሰስ መዝናኛ በኢስላም አይቻልም ። ግን ወንጀል ላይ ገብታችሁም ተሸንፋችሁም ከተመለሳችሁ ከባድ ነው። ሰይጣን 2-0 እየመራህ ነው ማለት ነው። አሸንፋ ሱጁድ ስትወርድ በቃ ወይኔ ...
ልብሷ አጭር ,ለህዝብ መዝናኛ ድብድብ ሄዳ , ወንዶች መሀል ....ቁጠር ..😁... ግን ያው ስህተቶች እንዳሉ ቢያንስ አሸንፋለች ።
