አቡ ፈህድ ዘመናዊ ዐረቢያን መጅሊስና ኳሊቲ የቤት እቃዎች
前往频道在 Telegram
መጅሊስ፣ ምንጣፍ፣ ድጋፍ፣ መጋረጃ፣ ትራስ ልብስ፣ ሁሉንም የሲንጀር ውጤቶችን የተሟሉ ረኮበት ሴቶችንና የተለያዩ ኳሊቲ የቤት እቃዎችን እንዲሁም አስቤዛዎችን በተመጣጣኝ ዋጋ እኛ ጋር ያገኛሉ በታማኝነት ያሉበት ሀገር እንልካለን!
显示更多埃塞俄比亚2 805未指定类别
📈 Telegram 频道 አቡ ፈህድ ዘመናዊ ዐረቢያን መጅሊስና ኳሊቲ የቤት እቃዎች 的分析概览
频道 አቡ ፈህድ ዘመናዊ ዐረቢያን መጅሊስና ኳሊቲ የቤት እቃዎች (@abu_fehd_online_market) 是活跃参与者。目前社区聚集了 12 583 名订阅者,在 其他 类别中位列第 ,并在 埃塞俄比亚 地区排名第 2 805 位。
📊 受众指标与增长动态
自 невідомо 创建以来,项目保持高速增长,吸引了 12 583 名订阅者。
根据 29 十月, 2026 的最新数据,频道保持稳定运转。过去 30 天订阅人数变化为 -560,过去 24 小时变化为 -21,整体触达仍然可观。
- 认证状态: 未认证
- 互动率 (ER): 平均受众互动率为 1.61%。内容发布后 24 小时内通常能获得 0.89% 的反应,占订阅者总量。
- 帖子覆盖: 每篇帖子平均可获得 202 次浏览,首日通常累积 112 次浏览。
- 互动与反馈: 受众积极参与,单帖平均反应数为 1。
📝 描述与内容策略
作者将该频道定位为表达主观观点的平台:
“መጅሊስ፣ ምንጣፍ፣ ድጋፍ፣ መጋረጃ፣ ትራስ ልብስ፣ ሁሉንም የሲንጀር ውጤቶችን የተሟሉ ረኮበት ሴቶችንና የተለያዩ ኳሊቲ የቤት እቃዎችን እንዲሁም አስቤዛዎችን በተመጣጣኝ ዋጋ እኛ ጋር ያገኛሉ በታማኝነት ያሉበት ሀገር እንልካለን!”
凭借高频更新(最新数据采集于 30 十月, 2026),频道始终保持新鲜度与高覆盖。分析显示受众积极互动,使其成为 其他 类别中的关键影响点。
12 583
订阅者
-2124 小时
-1177 天
-56030 天
帖子存档
አካላችሁ የመቋሸሽ ምልክት ያሳያል። ውስጣችሁ ሲፀዳ ደግሞ የንፅህናችሁ ምልክት በመላ አካላችሁ ላይ ይስተዋላል። ሳሊሜም ላይ ያስተዋልኩት ይሄንኑ ነው።" ሲል ድንቅ መልስ ሰጠን።
"አባባ ልባችንን በሻሙና ብናጥበው ይጠላል አይደል?" ስትል የ4 አመቷ ያክስቴ ልጅ ሀያት በሚኮላተፈው አንደበቷ ጠየቀችው። ዕድሜያችን ከሷ በላይ የሆንነው ሁሉ በጥያቄዋ ሳቅን።
"የኔ እንቦቀቅላ! አዎ ይጠራል። ባይሆን የልብ ማፅጃ ሳሙናው ተውበት ነው።"
"ተውበት? ተውበት ማለት አዲሽ የመጣ ሻሙና ነዋ አባባ?" ስትል አሁንም አሳቀችን።
"አይደለም የኔ ቆንጆ! ተውበት ማለት እጃችንን እና ገላችንን የምንታጠብበት አይነት ሳሙና ሳይሆን አላህን ላጠፋነው ጥፋት "ይቅርታ" የምንጠይቅበት ሰፊ በር ነው።" ሲል መለሰላት።
"በሩ ከኛ በር ይበልጣልኣ?" ብላ ከመጠየቋ በፊት፤
"አያያ! አላህ ግን የእውነት ያሳለፍኳቸውን ወንጀሎቼን ይቅር ይለኛል?" ብዬ ጠየቅኩት።
"እንዴታ! አላህ ማለት እኮ ከአዛኝነቱ የተነሳ ባሪያዎቹ ከባህር አረፋ የበዛ፤ ከሰማይና ምድር የሰፋ ወንጀል ቢፈፅሙ ለመማር ቅንጣት ታህል የማይሳሳ ውብ አምላካችን ነው። ደግሞ አትጠራጠር የእውነት ከቶበትክ ልክ ከታላቅ ሽፍታነት ወደ ታላቅ አሊምነት እንደተለወጠው ሰውዬ መሆን ትችላለህ።" አለኝ በተስፋ ቃላት ውስጤን እየገነባልኝ። ከተስፋ ቃሉ ውስጥ ከሽፍታነት ወደ ታላቅ አሊምነት የተለወጠውን ሰውዬ ታሪክ ማወቅ ሻትኩ።
አንዳንዴ ከአንድ ነገር ወደ አንድ ነገር ለመሻገር ካንተ በፊት ወደዛ ነገር የተሻገረ አርዓያ የሚሆንህ ሰው ያስፈልጋል። ከኔ ታሪክ ጋር የሚሄድ አርዓያ ደግሞ አሁን አያቴ ያነሱልኝ ሰውዬ ነው። ስለሆነም አርዓያዬ እንዲሆን ተመኘሁ። አንተንና ሽፍታን ምን አገናኛችሁ የምትሉ እንደማትጠፉ አምናለሁ። አዎ ከሰው እጅ ወይም ኪስ ገንዘብን አልነጠቅኩ ይሆናል። ነገር ግን ከብዙ ሴቶች ላይ እምነትን፣ ክብርን፣ ጊዜን እና ማንነትን ዘርፌያለሁ። ምናልባት ከመንግስት ወይም ከቤተሰብ አልሸፈትኩ ይሆናል። ነገር ግን ከእናት በላይ ከሚያዝንልኝ ፈጣሪዬ ለዘመናት ሸሽቼ ሸፍቻለሁ። ስለሆነም የሽፍታው ሰውዬ ታሪክ ለአርአያነት ይጠቅመኛልና ታሪኩን ለማወቅ ጓጓሁ።
"አያያ! የሽፍታውን ታሪክ ንገረን!" ስትል ጠየቀችው ሪ። አንዳንዴ እኮ ሪ ሳታስበውም ቢሆን ከኔ ጋር በሃሳብ ትገጣጠማለች። ለነገሩ አስተማሪ ታሪኮችን እኔ ጀሮዬን በማሸሽባቸው ጊዜያትም ጭምር መስማት ትወድ ነበር። እኔ ነኝ እንጅ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ባመጣሁት ለውጥ ከሷ ጋር የገጠምኩት። ከኋላ የመጣ... አሉ። ሃሃሃሃ
.
.
ይቀጥላል!
🧕ሂክማ🧕
ክፍል አስራ ስምንት
✍ኢብኑ ኢብራሂም
በቀጥታ ያመራነው ወደኛ ቤት ነበር። የጊቢያችንን በር አልፈን ወደ ውስጥ ስንገባ ማሚ፣ ሪ እና ሀምዱ ቁጭ ብለው እየተጫወቱ አገኘናቸው። ሀምዱ ሁሌም ባይሆን በወር ወይም በ15 ቀን አንዴ እየመጣ ይዘይረናል። ከእኔ ይልቅ እነ ማሚጋ ስለሚቀራረብ የኔ መኖር አለመኖር ግድ አይሰጠውም።
"ጎረምሶቹ ዛሬ ከየት ተከሰታችሁ?" አለችን ማሚ ሶፋችን ላይ እንደተቀመጥን።
"ዛሬ ከእናንተጋ ማሳለፍ ፈልገን ነው። ደስ የሚለው ደግሞ ሀምዱም አለ።" ስል መለስኩላት።
"በሰላም ከሆነስ ይሁን። አሁን እኮ ከሀምዴ ጋር እያነሳንህ ነበር።"
"መቼም እናቴ ባለችበት በክፉ እንደማልነሳ እርግጠኛ ነኝ!" ስል አሳቅኳቸው።
"ሳሊሜ እኔስ ብሆን አንተን በክፉ የማማህ ይመስልሃል?" አለኝ ሀምዱ!
"ኧረ በፍፁም! ባይሆን እችን ሙጢ መጠርጠሩ አይከፋም!" አልኩ ወደ ሪ እየጠቆምኩ።
"ዋ! ስነስርአት ብታደርግ ነው ሚሻልህ ካልሆነ ይሄን ማንደጃ እላይህ ላይ ገልብጬ ነው ክሰል ማስመስልህ!" አለች ሻይ ጥዳ እያራገበችው ወዳለው ማንደጃ እያመላከተች። ሁላችንም ሳቅን።
"እኔ እኮ ይሄ ፀባችሁ ነው ወደ ቤት እንድመጣ ሚያደርገኝ!" አለ ሀምዱ።
"ለዛ ነዋ በየአመቱ ምትዘይረን ኪኪኪ" ማሚ አሸሞረችበት። ሀምዱ ወደኔ እያየ፤
"Boss ከፈቀደማ በየሳምንቱ ነው ምዘይራችሁ!" አለ።
"ቆይ እሱን ደግሞ ማናባቱ ነው ፈቃጅ ያደረገው?" ሪ በንቀት አስተያየት እየተመለከተችኝ።
"ዋ! አንቺ ልጅ እንግዳ አለ ብዬ እንጅ ከሚፈላው ማንቆርቆሪያ ውስጥ ከትቼ ነው እንደ ሻይ ማፈላሽ። ለነገሩ አንች የገባሽበት ሻይ ልክ እንዳንቺ እሬት እሬት ነው የሚለው። ሃሃሃ" ቤት ውስጥ ከሪ ውጭ ያልሳቀ አልነበረም።
"ቆይ ብቻ አሳይሃለው!" ብላ ዛተችብኝ።
"በየትኛው የቲቪ ጣቢያ ነው ሚተላለፈው እንዳያመልጠን!" ስል የባሰ አቀጣጠልኳት።
"ማሚ ይሄን ልጅ ዝም አስብይልኝ ካልሆነ ወጥቼ ነው የምሄደው!" አለች እንደ ማኩረፍ ብላ።
"እስኪ እንግዳ ፊት አንኳን አደብ ግዙ! ምን ያለ ፈተና ነው ባካችሁ!" አለች ማሚ በሂጃቧ አፏን እየሸፈነች።
"የምር ግን ፍቅራችሁ ያስቀናል!" አለ ሀምዱ።
"የማንና የማን?" አልን በአንድ ድምፅም።
"የሁለታችሁ ነዋ! አንዳንድ ፍቅሮች እኮ በፀብ የታሸጉ ናቸው። ይሄ የሚገባችሁ ለጥቂት ጊዜ ስትራራቁ ብቻ ነው።" አለ ሀምዱ።
"በል በል አትፈላሰፍብኝ!" ብየው ውሃ ልጠጣ ወደ ጓዳ ገባሁ። ስመለስ ሪ ሻዩን ቀድታ ጠበቀችኝ። እኔ ሻይ ትንሽ ቀዝቀዝ ካላለ በቀር በትኩሱ መጠጣት ስለማልችል ገና አልቀመስኩትም። ሪ አስሬ
"ኧረ ሻዩ ቀዘቀዘ።" እያለች ትነዘንዘኛለች።
"ቆይ ምነው እንደ ባለሙያ ሻይሽ እስኪቀመስ ቸኮልሽ? ያንች ሻይ እንደ ቂቤ ሲቀዘቅዝ ይረጋል እንዴ?" ብያት አንስቼ አንዴ ፉት ስለው የተጎነጨሁትን ሻይ አፌ ላይ ማቆየት ተስኖኝ እሩጬ ወጥቼ ተፋሁት። ተፍቼ ስመለስ ሁሉም ሆዳቸው እስኪቆስል እየሳቁ አገኘኋቸው። ለካንስ ወደ ውስጥ በገባሁበት ሰዓት ሪ የኔ ሻይ ላይ ጨው ሞጅራበት ነበር።
"የታባህ! አሳይሃለው አላልኩህም ነበር።" ስትል ሸለለችብኝ።
"እንግዲህ ያሳየችህ በአፋር ቲቪ መሆኑ ነው። ሃሃሃ" አለ ሀምዱ በራሱም በሪም ቀልድ ድጋሚ እየሳቀ። ሃሚ አይናፋርነቱ ይዞት እንጅ ከዚህ በላይ እንደሚስቅ አልጠራጠርም። ማሚማ ሆዷን ይዛ አሁን ድረስ እየሳቀች ነው።
ሪሃና "በል እንካ በዚህ አወራርደው።" ብላ ሌላ ሻይ ሰጠችኝ።
"ባክሽ አልፈልግልሽም! ስትፈልጊ ተጋችው።" አልኳት የሰጠችኝን የሻይ ቡሽ እየመለስኩላት።
"ወይ ሪሃናዬ! ከዚህ በኋላ ሻይ የሚጠጣ ይመስልሻል?" አለች ማሚ ሳቋ በረድ ሲልላት።
"ከዚህ በኋላማ አይደለም ሪሃና ያፈላችውን እሷ የገባችበት ካፌ ያፈላውን ሻይ እንኳን አምኜ አልጠጣም!" አልኩ። እንዲህ እየተሳሳቅን እያለ የሰፈራችን አዛን አሱር መድረሱን አበሰረን። ወደ ሃሚ ጠጋ ብዬ በጆሮው፦
"ሻወር መውሰድ ወይም ልብስ መቀየር ምትፈልግ ከሆነ ወደ ውስጥ እንሂድና ተጣጥበህ ቀይር!" አልኩት።
"አይ ወደ ልደቱ ስንሄድ ታጥቤና ልብስ ቀይሬ ነው የወጣሁት።" አለኝ። ሦስታችንም ተያይዘን ወደ ሰፈራችን መስጂድ ሄድን።
*
"ማሻ አላህ! አየህ አይደል የሶላትን ጥቅም? ከአንተም አልፋ በዙሪያህ ያሉትንም የመቀየር ሀይል አላት።" አለችኝ ሂክማ ማታ ላይ የቀኑን ውሎዬን ስነግራት።
"ወላሂ ምን እንደምልሽ አላውቅም። ለዘመናት የታወሩትን አይኖቼን ነው ያበራሽልኝ።"
"ሳሊሜ የመምራትም፤ የማጥመም ስልጣን ያለው በአላህ እጅ ነው። በሰዎች እጅ ቢሆን ኖሮማ ነብዩላህ ኑህ ልጃቸውን፣ ነብዩላህ ኢብራሂም አባታቸውን፤ ነብዩላህ ሉጥ ምስታቸውን፣ ረሱል (ሰ.ዐ.ወ) አጎታቸውን መምራት በቻሉ ነበር።"
"እሱማ ልክ ነሽ። ያው ሰበብ ሆነሽኛል ማለቴ ነው።"
"እንደዛ ልክ ነህ።" አለችኝ። ዛሬ እስከ ዛሬ ፈልጌ ያልተሳኩልኝን ሁለት ነገሮችን አግኝቻለሁ። አዎ የሂክማን "ሳሊሜ" የሚል የቁልምጫ ጥሪና እሷን በሃሳብ መርታት።
ሳሊሜ የሚለው ቁልምጫዋ ልቤ ውስጥ ያዳፈንኩትን ፍቅር ቀስቅሶብኝ ፎቶዋን ላኪልኝ ልላት ብዬ ካፌ መለስኩት። አሁን ላይ የምፈፅማቸው አምልኮዎች ንያቸው የአላህ ፊት ቢሆንም፤ የሂክማን መጨረሻ ለማወቅ ግን ከመቸውም በላይ ጓጉቻለሁ። ብዙ ጠቃሚ ምክሮችን ከተለዋወጥን በኋላ ተሰነባብተን ተለያየን።
የእሁድ ጧት ውሏችን እንደተለመደው ነበር። ጠዋት የሚጠበቅብንን የስራ ድርሻ ከውነን ወደ አያታችን ቤት አቀናን። አሁን ላይ እንደስከዛሬው እየደበረኝ አይደለም የምሄደው። ይልቁንስ የቋሸሸችዋን ነብሴን የማፀዳበት ግሳፄ ለመሸመት እየጓጓሁ ነው የሄድኩት። አንዳንዴ የአንድን ነገር ደረጃ አለማወቃችን በዛ ነገር ላይ ያለንን ምልከታ ያዛባብናል። አሁን ላይ የአለም ሰው የተቸገረው በዚህ አባዜ ነው። የመለኪያ ሚዛናችን ተዛንፎ መጥፎው ጥሩ፤ ጥሩው ደግሞ መጥፎ ሆኖ ተምታቶብናል። ረሱላችንምﷺ "እስልምና ሲጀምር እንግዳ ነበር፤ ወደ ፊትም ወደ እንግዳነት ይመለሳል!" ሲሉ ይሄንን እውነታ እየነገሩን ይመስለኛል።
ለማንኛውም ዛሬም የተለመደውን ስርዓት ከውነን ከአያታችን ስር ተሰብስበን የሳምንት የምክር ቀለባችንን እየሰነቅን ነው።
"ሳሊሜ የምትነግረኝ አዲስ ነገር እንዳለ ፊትህ ይነግረኛል። አዲስ ነገር አለ እንዴ?"
"አዎ አለ። ግን እንዴት አወቅክ?" ስል ተገርሜ ጠየቅኩት።
"አዲሱን ነገር ንገረኝና ያወቅኩበትን መንገድ እነግራችኋለሁ።" አለኝ። በሁለት ሳምንታት ውስጥ የተፈጠረውን ሁሉ ነገርኩት።
"ማሻ አላህ! አላህ ሊመራህ ሲፈልግ ምን እንደሚልክልህ አታውቅም። ይሄው እኛ ክፉ ጎን እንጅ ሌላ እንደሌለው የምናስበው ፌስቡክ ላንተ መቅናት ሰበብ ሆነህ። የተባረከች ልጅ! እንዲያው አላህ ይጠብቃት። ለኛ እንዳላስቸገርክ መቀናትህን በሷ ከትቦት ኖሮ በጥበቡ አቀናህ። እውነትም ሂክማ! ሰው የስሙ ተቃራኒ በሚሆንበት ዘመን እንደ ስሟ ጥበብ የሆነች ባሪያ!..." አያቴ ያልቸራት ሙገሳ፤ ያስቀረባት ምርቃት አልነበረም። ሂክማ ማለት ጥበብ ማለት መሆኑን ለመጀመሪያ ጊዜ አሁን አወቅኩ። ማታ አግኚቻት እስክነግራት ነው የጓጓሁት።
ሪሃና "አያያ! እንዴት ከፊቱ ላይ ማወቅ እንደቻልክ እኮ አልነገርከንም።" ስትል የኔም ጥያቄ የሆነውን ጥያቄ ጠየቀችልኝ።
"ደስታው አስክሮኝ እኮ ስሜቴን መቆጣጠር አልቻልኩም። ለማንኛው የሰው ልጅ ልብ/ቀልብ ልክ እንደ ብርጭቆ ነው። ውስጡ ጥቁር ቀለም ስታስቀምጡበት ጥቁር፤ ነጭ ቀለም ስታስቀምጡበት ነጭ ቀለምን ያስተላልፋል።
ልጆቼ ቀልባችሁ ሲቆሽሽ ግንባራችሁና
ከሆነማ ከአንተ ውሳኔ ውጭ ስንዝር ታህል እንደማልወጣ ታውቃለህ!" አለኝ። በጣም ደስስ አለኝ። በኔ ሰበብ ከእምነቱ ያፈነገጠ ባሪያ በኔው ሰበብ ለመስተካከል በመብቃቱ የድል አድራጊነት ስሜት ተሰማኝ። አልሐምዱ ሊላህ!
.
.
.
ይቀጥላል!
🧕ሂክማ🧕
ክፍል አስራ ሰባት
✍ኢብኑ ኢብራሂም
በመጨረሻም ልደቱ ላይ ለመገኘት ወሰንኩኝ። ቢያንስ አግኝቻቸው አቋሜን መግለፅ እንዳለብኝ ራሴን አሳመንኩ። ቢሆንም ግን ውስጤ ትክክለኛ ውሳኔ እንዳልወሰንኩ ይነግረኝ ይዟል። ሱብሃነላህ! ለአመታት ተዛንፎ የነበረው የውስጤ ሚዛን መስራት ጀምሯል። ለካንስ አላህ መልካምና መጥፎን እንድንፈትሽበት የቸረን ደመነፍሳችን ህያው የሚሆነው እንዲሰራ ስንፈቅድለት ኖሯል። ከዚህ በፊት ወንጀል ከፈፀምኩ በኋላ የማላውቀው ድብርት እና ጭንቀት ይሰማኛል እንጅ ከመስራቴ በፊት ትክክል ነው አይደለም የሚል ስሜት ተሰምቶኝ አያውቅም ነበር። ዛሬ ግን ይሄው ይሄ ስሜቴ ህይወት ዘርቶ ለነብሴ እንደ ትራፊክ መብራት ሆኖ ያስጠነቅቀኝ ጀምሯል።
ከነ ዮኒ ጋር ወደ ልደት ቤቱ ስንገባ ልክ ባለስልጣን የገባ ይመስል በደማቅ ጩኸትና ፉጨት ተቀበሉን። በትላንቱ ማንነቴ ላይ ብሆን ኑሮ ይህ አቀባበል ነብሴን ወደ ሰማየ ሰማያት የሚያመጥቅ ድንቅ አጋጣሚ በሆነልኝ ነበር። ነገር ግን ዛሬ ላይ ሁኜ ሳየው ሸይጧን በፌዝና በሹፈት ሲሳለቅብኝ የሚያሰማው የሳቅ ድምፅ መስሎ ታየኝ። እስከዛሬ ያፈራሁት እውቅና እና ክብርን ሳየው በራሴ አፈርኩ። ወደ መስጂድ ስገባ አይን ውስጥ የማልገባ ተራ ሰው ስሆን መጠጥ ቤት አልያም ሀራም ስፍራ ስገኝ ደግሞ አይንን የምማርክ ታዋቂ መሆኔን ሳይ አላህ ዘንድ በወንጀሌ ቢሆን እንጅ ሚዛን የማልደፋ ተራ ባሪያ፤ ሸይጧን ዘንድ በሀጢያቴ ብዛት አልጋ ወራሹ ለመሆን ምንም የማይቀረኝ ወንጀለኛ እንደሆንኩ አውቄ በውስጤ አነባሁ።
ቤቱ መዋብ የሚችለውን ያህል ተውቧል። ሴቶቹ እርቃናቸውን በሚባል መልኩ ተራቁተው ለብሰው ራሳቸውን ለሰይጣን መሳሪያነት አጭተው ተሰልፈዋል። ሙዚቃው የጆሮ ታንቡር እስኪበሳ ድረስ ይደነክራል። ዙሪያ ገባውን ስቃኝ ብዙ አስደንጋጭ ነገሮችን ቃኘሁ። ትምህርት ቤት ውስጥ ጭምት እንደሆኑ የሚታወቁት እንስቶች ሙሉ ለሙሉ እርቃን ናቸው ለማለት በሚያስደፍር መልኩ ልብሳቸውንም ክብራቸውንም ገፈው ቁመዋል።
በየግል ያመጣንላትን ስጦታ ከሰጠናት በኋላ የተዘጋጀልን ሶፋ ላይ ተቀመጥን። እስካሁን ለይላን አለየኋትም። ለነገሩ እኛ ላይ ያፈጠጡ የሴቶችን አይን መቋቋም ተስኖኝ በሙሉ አይኔ ዙሪያውን ማየት ስላልቻልኩ እንጅ ከሴቶች መሃል አትጠፋም። ዛሬ የሰገድኳት ሱብሂ ስራዋን ሳትሰራ አልቀረችም። ይሄው ዛሬ እስከ ዛሬ ከተሳተፍኩባቸውና ከተደሰትኩባቸው መድረኮች ውስጥ የዛሬው መድረክ ይበልጥ የደመቀ ቢሆንም ነብሴ ልትረጋጋልኝ አልቻለችም። የሙዚቃው ጩኸት እስከዛሬ ያልጨፈርኩበት ይመስል ቀፈፈኝ። እንዲህ ከውስጤ ጋር ግብግብ እየገጠምኩ እያለ አንዲት ሴት እኔ ወዳለሁበት መቀመጫ አመራች። ካጠገቤ የተቀመጠው ሃማድ ተነስቶ ሌላ ቦታ ሄዶ ተቀመጠ። ልጅቷ ሃሚ የተነሳበት ቦታ ተቀምጣ እጇን ዘርግታ አንገቴን አቀፈችኝ። ደንግጬ ሳስተውላት ለይላ መሆኗን ተረዳሁ። ከላይ ትክሻዋንና የጡቶቿን ግማሽ አካል ያራቆተ፤ ከታች እንብርቷ ላይ ሳይደርስ የቆመ ስስ ቦዲ ለብሳለች። ከስር ያደረገችው ቀሚስ ግማሽ ቅልጥሟ ላይ ቀርቶ ከፊት ለፊቱ እስከ ግማሽ ታፋዋ ድረት የተሰነጠቀ ከመሆኑ የተነሳ ቁጭ ስትል ሁለቱን ጭኖቿን አጋልጦታል። ሂጃቧ ቦታው ላይ የለም። በቦታው የተተኮሰ ረጅም ፀጉሯ ተከምሯል።
"ምነው ሌላ ሰው መሰልኩብህ እንዴ?"
"አዎ በጣም!"
"እና አላማረብኝም?"
"አስጠልቶብሻል።" አልኳት ኮስተር ብዬ። ፊቷ በቅሬታ ተሞላ። ቀኑን ሙሉ ሽርጉድ ስትልበት የዋለችው ወጥ እንዳልጣፈጠላት ሴት ውስጧን ከፋው።
"እኔ ግን አለባበሴን ትወድልኛለህ ብዬ ጠብቄ ነበር።"
"እንዳጋጣሚ ሆኖ አልወደድኩልሽም።"
"ሂድ ወደዛ ገገማ። ዛሬ ደግሞ በህይወቴ ለማንም ልሰጠው የማልችል ትልቅ ስጦታ አዘጋጅቼልሃለሁ።" አለችኝ አይኗን እያቁለጨለጨችብኝ።
ክብሯን ልትሰጠኝ አስባ እንደሆነ አላጣሁትም። እንዳለችው ለትላንቱ ሳሊም ይሄ ትልቅ ስጦታ ነው። ለዛሬው ሳሊም ግን ራሱን ሊፈትንበት የቀረበ ትልቅ ፈተና ነበር። ምንም እንኳን ከዚህ በፊት በሁኔታዎች አለመመቻቸት ምክንያት ዋነኛው ዝሙት ላይ ባልወድቅም እንደዛሬው ተመቻችቶልኝ ለዛውም እስከዛሬ ከቀረብኳቸው ሴቶች ውስጥ ልዩ ስሜት እንዲሰማኝ ካደረገችኝ እንስት በኩል እንዲህ ያለ ግብዣ ቀርቦልኝ ማለፉ የማይታሰብ ነበር። ነገር ግን አልሐምዱ ሊላህ በትክክለኛው ሰዓት የአላህ ጥበቃ ታድጎኛል። ዝም ስልባት ወሬዋን ቀጠለች።
"ለስጦታው ተዘጋጅ። ደግሞ ያች ልጅ ትታይሃለች?" ብላ ወደ ፊት ለፊት በከንፈሯ ጠቆመችኝ። ወደጠቆመችኝ አቅጣጫ ስዞር አንዲት በ16 ዓመት ክልል ውስጥ የምትገኝ ቀይ ልጅ ወደ ሃሚ እያየች ስትሽኮረመም አየኋት። ሃሚ አፍሮ ነው መሰለኝ አንገቱን ደፍቶ የዪኒን ስልክ ይጎረጉራል። ዮኒ ከባለ ልደቷ ጋር ተቀምጦ የጦፈ የፍቅር ወሬ እያወራ ነው።
"አዎ አየኋት ማን ናት?"
"በሃሚ ፍቅር ያበደች ልጅ ናት። ዛሬ ሃሚን ከሷ ጋር ልናመቻች እቅድ ነድፈናል።" አለችኝ በጀብደኝነት ስሜት።
"የምን እቅድ?" ስል ጠየቅኳት ውስጤ ቅጥል እንዳለ።
"ሃሚን ዛሬ አስክረን ከልጅቷ ጋር እንዲተኛ የማድረግ እቅድ።"
"እርግጠኛ ነሽ?" አልኳት ፊቴ ከበፊቱ እየቀላ። ለይላ ከገፅታዋ ጋር ስብዕናዋም የተለወጠ መስላ ታየችኝ። የፊቴን ገፅታ ስታይ ደንገጥ አለች።
"አዎ ምነው? ለሱም አይናፋርነቱ ይገፈፍለት ብለን እኮነው።"
"ቆዳችሁ ይገፈፍ!" ብዬ ተስፈንጥሬ ተነስቼ ወደ ሃሚ ሄድኩና ቆጣ ብዬ "ና ተከተለኝ!" አልኩት። በሁኔታዬ ደንግጦ ስለነበር ምንም ሳይል ተነስቶ ተከተለኝ። ዮኒም በርቀት እያየን ስለነበር ሩጦ ተከተለንና
"ምነው ምን ሁናችኋል? ፕሮግራሙ እኮ ሊጀምር አንድ ደቂቃ ብቻ ነው የቀረው ወዴት ልትሄዱ ነው?" ሲል ጠየቀን። ሃሚ የሱም ጥያቄ ስለነበር ምላሼን ለመስማት ወደኔ ዞረ።
"ዮኒዬ ነገ እነግርሃለሁ። አሁን መሄድ አለብን ለነሱ የሆነ ነገር ብለህ አሳምናቸው። ቻው!" ብዬው ሃሚን እየጎተትኩ ከግቢው ወጣሁ። ዮኒ በቅሬታ ተሞልቶ የሰፈሩን መታጠፊያ እስክንታጠፍ ድረስ በቆመበት ሳይንቀሳቀስ ሸኘን።
ግማሽ መንገድ ያህል ስንጓዝ ከሃሚ ጋር ምንም አልተነጋገርንም። እኔ ግን በውስጤ ብዙ ነገር እያወራሁ ነበር።
ከራሴ ህይወት አልፌ የሃሚን ህይወት ላበላሽ እንደነበር ሳስበው ውስጤን ፀፀት ወረረው። የተሳሳትኩ የመሰለኝ ውሳኔ ትክክል መሆኑን የተረዳሁት ገና አሁን ነው። ልደቱ ቦታ ላይ አልመጣም ብዬ ብቀር ኑሮ የሃሚ ህይወት እስከ ወዲያኛው ድረስ ይበላሽ እንደነበር ጥርጥር የለውም።
አልሀምዱ ሊላህ! አላህ መሄዱን እንድወስን አድርጎ የሃሚን ህይወት ስለታደገው እጅግ ተደሰትኩ።
ዝም ብለን ብዙ ከተጓዝን በኋላ
"ሃሚ ከዚህ በኋላ ራሳችንን መለወጥ ይኖርብናል። ሳናውቀው ከአላህ መንገድ ብዙ እርቀን እየተጓዝን ነው።" አልኩት። ዝምታውን ስለሰበርኩለት ደስ ብሎት ሊጠይቀኝ ያሰበውን ጥያቄ ሰነዘረ።
"ሳሊሜ ከዛ በፊት ግን ለምን ከልደቱ ቦታ እንድንወጣ እንደፈለክ ንገረኝ!" አለኝ። የሆነውን ሁሉ ስነግረው በውሳኔዬ በጣም መደሰቱን ነግሮ አመሰገነኝ። የተሸረበበት ሴራ በጣም አናዶት ስለነበረም ያቀረብኩለትን የለውጥ ጥያቄ ካሰብኩት ፍጥነት በላይ ተቀበለኝ።
ሀምዛን (ረ.ዐ) ያሰለመው ቁጣ ሃሚን ሳያስቶብተው አልቀረም!
"ሳሊሜ እውነት ለመናገር እስከዛሬ አብሬህ የማልሰግደው አንተ በጊዜያዊነት መስገድ የጀመርክ ስለመሰለኝ እንጅ፤ በቋሚነት
🧕ሂክማ🧕
ክፍል አስራ ስድስት
✍ ኢብኑ ኢብራሂም
...ፌስቡክ ስከፍት ሂክማ ኦንላይን ላይ የለችም። እስክትገባ ድረስ ከለይላ ጋር ማውራት ጀመርኩ። ለይላ አሁንም እያለቃቀሰችብኝ ነው። የነገው የዮኒ ችክ ልደት ላይ እንዳልቀር እያግባባችኝ ነው። ያው ለሷ ብዬም ባይሆን ለዮኒ ስል መሄዴ ስለማይቀር እንደምገኝ ቃል ገባሁላት። በነገራችን ላይ እኔና ሃሚ ትንሽ ብር አግኝተንለት ለፍቅረኛው እንደ አቅሚቲ ስጦታ ሸምቶላታል። የነገን ቅዳሜ ከሰዓት ልደቱ ቦታ ሄደን ለማሳለፍ አቅደናል።...በዚህ መሃል ሂክማ ኦንላይ ገባች። ተቻኩዬም ሰላምታ አቀረብኩላት። የሚገርማችሁ ከሂክማ ጋር ማውራት ከጀመርኩ አንስቶ ብዙ ነገሮቼ ተቀያይሯል። ከዛ ውስጥ ቀድሜ ሰላምታ ማቅረብና መንሰፍሰፍ ጀምሬያለሁ። እንደበፊቱ ቢሆን ኑሮ እንኳን ለሴት ልጅ ቀድሜ ሰላምታ ላቀርብ፤ ሰላምታ ሲያቀርቡልኝ እንኳን ትዕግስታቸውን ካስጨረስኩ በኋላ ነበር የምመልስላቸው። ለሰላምታዬ ምላሽ ከሰጠችኝና አንዳንድ ወሬዎችን ካወራን በኋላ ወደ ገደለው እንዲህ ስል ገባሁ፦
"ሂኩ ዛሬ ሂሳብ የምታወራርጅበት ቀን ነው።"
"የምን ሂሳብ ነው? እኔና አንተ እስከ መበዳደርም ደርሰናል እንዴ? ኪኪኪኪ"
"ባክሽ ገብቶሻል። እኔ የመስገድ ግዳጄን ተወጥቻለሁ። አንች ደግሞ ቃልሽን ሙይልኝ!"
"እንዴ ገና ግንባርህ ላይ የመስገድህ ምልክት የሆነውን ኑር ሳታወጣ ሰገድኩ ብለህ ታወራለህ?" ስትለኝ ሃሞቴ ፈሰሰ። ግንባሬ መጥቆር አለመጥቆሩን ለማረጋገጥ የመኝታ ቤቴን መብራት አበራሁና የስልኬን ካሜራ ከፍቼ ግንባሬን አስተዋልኩት። ምንም አይነት ምልክት የለም። "ቆይ ስንት ቀን ብሰግድ ነው የሚወጣው?" ስል አሰብኩ። ይሄን ባሰብኩበት ሰዓት ሪ ሶላት የጀመረች ጊዜ ግንባሯን በድንጋ ፈግፍጋ ያቆሰለችው ትዝ አለኝና ፈገግ አልኩ።
"ዋናው እኮ ሶላት መጀመሬ ነው። አሁን ላይ ሳላቋርጥ መስገድ ጀምሬያለሁ።" አልኳት።
"ኪኪኪ ኑር ያልኩህ ለቀልድ ያህል ነው። ዋናው ኑር (ብርሃን) የልብ ኑር ነው።" አለችኝ።
"እኮ ላኪልኛ!"
"እስካሁን ሶላት መች መስገድ ጀመርክ።"
"እንዴ...ምን ማለት ነው? ይሄው ለአራት ቀናት ሙሉ ሱቢህ እንኳን መስጂድ ውስጥ ስሰግድ አይደል እንዴ የሰነበትኩት?" አልኳት በስጨት ብዬ።
"ሳሊም! ሶላት ከመጥፎና ከቆሻሻ ተግባር እስካላቀበህ ድረስ ሶላት ሊባል አይችልም!"
"እና እኔ የትኛውን ወንጀል ስፈፅም አየሽኝ?"
"ልቦናህ ስለሚያውቀው መናገሩ አስፈላጊ አይመስለኝም።"
"እኔ ግን እንድትነግሪኝ ፈለኩ።"
"እርግጠኛ ነህ?"
"100%" አልኳት። ምን ልትለኝ እንደሆነ ለመስማት ልቤ ጓጓ። ምላሿ እስኪደርሰኝ ድረስ ትዕግስት አጣሁ። ንዴትና ጉጉት ስለተደራረበብኝ ነው መሰል ጉሮሮዬ ደርቆ ውሃ አስፈለገኝ። እስክትመልስ ቁጭ ብዬ ከምጨናነቅ ብዬ ውሃ ለመጠጣት ወደ ጓዳ ሄድኩኝ። ጠጥቼ ስመለስ የሪሃና ክፍል ክፍት ነው። ሪ ከዛን ምሽት ጀምሮ በአቀባዠረኝ ሰበብ ከነማሚ ጋር ማደር ጀምራለች። ዛሬም እነሱጋ ነው ያደረችው። ወደ ክፍሌ ስገባ መልዕክት ገብቶ ጠበቀኝ።
"ይሄንን ባልነግርህ ደስ ይለኝ ነበር። ለማንኛውም እስኪ በዚህ ሳምንት የፈፀምካቸውን ሀጢያቶች አስታውስ! የማትገባህን ሴት ስመሃል፣ ሴቶችን ተላክፈሃል፣ ሙዚቃ አዳምጠሃል፣ ፊልም በማየት ጌዜህን አባክነሃል..." ስትል ጉዴን ሁሉ ዘክዝካ ላከችልኝ። ወላሂ ሂክማ ሁሉም ነገሯ ግራ የሚያጋባ ቢሆንም እንደዛሬ ግራ አጋብታኝ አታውቅም። አሁን ፈፀምካቸው ብላ የጠቀሰችልኝ ወንጀሎችን በሙሉ ፈፅሜያቸዋለሁ። ግራ ያጋባኝ ወንጀሎቼን ማወቋ አይደለም። ከእነዚህ ወንጀሎች ውስጥ ግማሹን ትምህርት ቤት ወስጥ፤ ግማሹን ደግሞ ቤቴ ውስጥ የፈፀምኳቸው ወንጀሎች በመሆናቸው ሁሉንም ማወቋ ነው ያስደነቀኝ። አሁን ሂክማ ማን እንደሆነች ግራ ገብቶኛል። ትምህርት ቤት ውስጥ የሚያውቀኝ ሰው ነው እንዳልል ከትምህርት ቤት ውጭ የፈፀምኩትንም ታውቃለች። የቤት ሰው ናት እንዳልል ቤት ውስጥ ትምህርት ቤት የፈፀምኩትን ሊያውቅ የሚችል ሰው የለም። ምክኒያቱም ሪ ገና የሀይስኩል ተመሪ ናት። ታዲ ማን ናት ልበል?
"ቆይ ግን አንች ማን ነሽ? ማንስ ብትሆኚ ነው ከኔ ውጭ ማንም ሊያውቅ የማይችለውን ሚስጥሬን ሁሉ ልታውቂ የቻልሽው? ማን ነሽ? ማን ነሽ?" ተነጫነጭኩባት።
"ለዚህ ጥያቄ መልስ ማግኘት የምትችለው ሶላትህ ከወንጀል ልታቅብህ የቻለች ቀን ነው።"
"ቆይ እንደምትይው ሶላት ከወንጀል የምትከለክል ከሆነ የኔ ሶላት ለምን እኔን ከወንጀል ለመከልከል አቅም አነሳት?"
"ምክንያቱም ለአላህ ብለህ ስለማትሰግድ ነዋ! ለአላህ ብለህ መስገድ ስትጀምር ሶላትህ ልክ እንደ መኪና ፍሬን ከወንጀልና ከአደጋ የምትከላከልልህ ትሆንልሃለች።" አለችኝ። ያለችው ሁሉ እውነት ነው። ሌላው ቀርቶ ለሰው ብዬ መስገድ የጀመርኩት ሶላት እንኳን በህይወቴ ላይ ያመጣው ለውጥ ቀላል የሚባል አይደለም። ከነገዋ ሱብሂ ጀምሮ ለአላህ ብዬ መስገድ ለመጀመር ወሰንኩ።
"እሽ እንዳልሽው ከነገ ጀምሮ ለአላህ ብዬ መስገድ እጀምራለሁ። ከዚህ በኋላ ፎቶ ላኪልኝ ብዬ አልጠይቅሽም። መላክ አለብኝ ብለሽ ባሰብሽው ሰዓት ራስሽ አስበሽ ላኪልኝ።" አልኳት።
"ማሻ አላህ! አሁን ገና ትክክለኛ ውሳኔ ላይ ደረስክ። አታስብ ፎቶዬን ሳይሆን እኔን በአካል የምታገኝበት ጊዜ ሩቅ አይሆንም።" ብላ ተስፋ ሰጠችኝ። ይሄን ካወራን በኋላ ብዙም አልቆየንም። እኔው እራሴ መተኛት አለብኝ ብዬ ተሰናብቻት ወጣሁ።
ጠዋት ሪ ከመቀስቀሷ በፊት የስልኬን አላርም ሰምቼ ነቃሁ። ሪ እንደለመደችው ውሃ በብርጭቆ ይዛ ወደ ክፍሌ ስትገባ እኔ ልብሴን ለባብሼ የአልጋዬ ጠርዝ ላይ ተቀምጬ ነበር።
"ዛሬ እንቅልፍ እንቢ ብሎህ መሆን አለበት።" አለችኝ።
"አይ መነሳት ከፈለኩ መነሳት እንደምችል ላሳይሽ ስለፈለኩ ነው።" አልኳት
"ዋ! በኋላ ሳልቀሰቅስህ ቀርቼ ዷህዋህን እንዳላሰግድህ!"
"ከፈለግሽ ሌሊት ቀስቅሼሽ የሌሊት ሶላት ላሰግድሽ!" ስል መለስኩላት።
"ሂድ ወደዛ ብላ የያዘችውን ውሃ ፊቴ ላይ ረጭታብኝ ሮጠች። ብከተላትም መኝታ ቤቷ ቀድማኝ ገብታ በሩን ዘጋችብኝ።
ለመጀመሪያ ጊዜ አላህ ፊት ለሱ ብዬ ቆምኩ። ወላሂ የተሰማኝን ስሜት ልገልፅላችሁ አልችልም። ምናልባት ከእናንተ ውስጥ እንደኔ ለዘመናት አፈንግጦ የተመለሰ፤ አልያም ሰልሞ ለመጀመሪያ ጊዜ ጌታው ፊት የቆመ ካለ ስሜቴን ሊረዳው ይችል ይሆናል። ሶላቱ እንደተጠናቀቀ እንደወትሮው ከአባቢ ጋር ወደ ቤት አላቀናሁም። ይልቁንስ አባቢ እንዲሄድ ነግሬ እስከ ረፋድ ድረስ እዛው መስጂድ ውስጥ ጌታዬን ማህርታ ስማፀንና ቁርዓን ስቀራ አረፈድኩ። የምር ነው ምላችሁ ቁርዓንን ከፍቼ መቅራት እንደጀመርኩ ነው ትርጉሙን መረዳት ባለመቻሌ የተፀፀትኩት። ስለሆነም አያቴጋ በሚኖረኝ የ15 ቀን ቆይታ ውስጥ ቂርዓት ለመጀመር እቅድ ነደፍኩ።
ከምሳ በኋላ እነ ዮኒ ወደ ልደቱ ቦታ እንድንሄድ ደወሉልኝ። በህይወቴ ለመጀመያ ጊዜ ከባድ ምርጫ ውስጥ ወደቅኩ። የነ ዮኒን ጥሪ ምላሽ ሰጥቼ አላህን ላሳዝን? ወይንስ ጥሪውን አንቢ ብዬ ቀርቼ አምላኬን ላስደስት? ለመወሰን ቸገረኝ። ምላሼን እየተጠባበቀ ያለው ዮኒ ዝም ስልበት አስሬ "ሄሎ!..ሄሎ!...ሳሊሜ አይሰማም?.." አያለ እየደጋገመ ይጣራል።
.
.
ይቀጥላል
🧕ሂክማ🧕
ክፍል አስራ አምስት
✍ኢብኑ ኢብራሂም
፡
"ቆይ ለምንድን ነው የኛ ታሪክ ይሄን ያህል ሰፍ እንድትሉ ያደረጋችሁ?" ሲል ጠየቀን አባቢ።
"እንዴ የስንቱን ታሪክ ሰፍ ብለን ስንሰማና ስናዳምጥ አይደል ያደግነው። እንዴት የወላጆቻችን ታሪክ ሰፍ አያደርገንም?" አለች ሪ።
"እኔ ግን ያባቴ ልጅ መሆን ስለምፈልግ የማሚ አይነቷን ጉብል እንዴት ማጥመድ እንደምችል ልምድ ለመቅሰም ስለምፈልግ ነው።" ስል ሁሉም ሳቁብኝ።
"ያም ሆነ ይህ ዛሬ ካቆሙኩበት ልቀጥልላችሁ። ምን ላይ ነበር ያቆምኩት?" ሲል ጠየቀን።
"እንዴ አባቢ ምንድን ነው እንደ history መምህር ያቆምንበት ምናምን ምትለው? በዚህ አይነትማ Final Exam ልፈትናችሁ ማለትህ አይቀርም! ኪኪኪኪ" አለች ሪ።
"አባቢ አሷን ተዋት። ያቆምክልን ከማሚ ጋ በስነ ፅሁፍ ምክንያት መግባባት እንደቻላችሁና እሷ ግጥም እየገጠመች አንተ ደግሞ የራስህን ፅሁፎች እየፃፍክ እየሰጣሃት እንደነበር ነግረኸን ነው ያቆምከው።" አልኩት።
"አንተ እውነትም በደንብ ወጥረህ ይዘሃል።" ብሎ ሁላችንንም አሳቀን።
"እናላችሁ ከእናታችሁ ጋር ያለን ቅርርብ እያደገ መጣ እንደናንተው ዘመን ፌስቡክ ቴሌግራም ምናምን ባይኖርም በደብዳቤና በግጥም የሆድ የሆዳችንን እናወራ ነበር። የሚገርመው ግን አሁንም በአካል ማውራት አልጀመርንም። ሱቅ ስትመጣ ልክ እንደማታውቀኝ ሁሉ እቃ ትገዛኝና ወረቀቷን ይዛ ትሄዳለች እንጅ አንድም ቀን ቁማ አዋርታኝ አታውቅም።
እንዲሁ እያልን ለሁለት ወር ያህል እንደቆየን አንድ ቀን ከአንድ የግል ሬዲዮ ጣቢያ የስልክ ጥሪ ደረሰኝ። ከሳምንት በፊት ሲቪዬን ያስገባሁበት ድርጅት ነው። ለኢንተርቪው እንደምፈለግና ነገ ቢሮ ድረስ እንድገኝ ነገሩኝ። በማግስቱ ቢሮ ድረስ ሂጄ ኢንተርቪው ወሰድኩና መስፈርቱን አሟልቼ በሰራተኝነት ተቀጠርኩ።
ይሄንን በደብዳቤ ለእናታችሁ የነገርኳት ዕለት በራቸው ላይ ቁማ ወደኔ እያየች ስታነባ ዋለች። በጣም እንደለመደችኝና ሱቁን ትቼ ሌላ ስራ ስጀምር እንዳልረሳት እንደምትሰጋ በወረቀት ላይ ፅፋ ላከችልኝ። ደብዳቤዋ ላይ የቤት ስልክ ቁጥራቸውንም አብራ ልካ እንድደውልላት አሳሰበችኝ። ይሄን ያህል ውስጧ እንደገባሁ አልገመትኩም ነበር። ለካንስ ከስነፅሁፍ ፍቅሯ ባሻገር የእኔም ፍቅር በውስጧ ሰፍሮ ነበር።" ብሎ ወደ ማሚ ሰረቅ አርጎ ተመለከተ። ማሚ እንደ ሁልጊዜው በሀፍረት ጉንጮቿ ቀልተው አቀርቅራ ቡናዋን በመቁላት ላይ ነበረች። እኔና ሪ ተጠቃቅሰን ፈገግ አልን። አባቢ ግን መተረኩን ቀጥሏል።
"...ሱቁን ለአጎቴ አስረክቤ የሬዲዮ ጣቢያው ውስጥ መስራት ጀመርኩ። መጀመሪያ ላይ ምሽት 3 ሰዓት ላይ የሚተላለፍ የመፅሐፍ ትረካ እንዳቀርብ ነበር ሃላፊነት የተሰጠኝ። ሁሌም ረጃጅም ልብወለዶችን ተርኬ ስጨርስ ሌላ እስኪጀመር የራሴን አጫጭር ፅሑፎችን አቀርብ ስለነበር፤ ከተራኪነትም ባሻገር በድርጅቱ የሚታተመው መፅሔት ላይ አንድ አምድ እንድይዝ እድል ተመቻቸልኝ። በትረካውም ሆነ በመፅሔቱ ላይ በማቀርባቸው ፅሑፎች ምክንያት ብዙ አድናቂዎችን አፈራሁ። የመፅሔቱ አምድ ላይ የአንባቢዎችን አስተያየትና የስነፅሁፍ ስራዎቻቸውን አሰፍር ስለነበር ብዙ ሙገሳዎች ይጎርፉልኝ ጀመር። ከአምዴ ስር ከሚሳተፉት ውስጥ እናታችሁ አንደኛዋ ነበረች። በነገራችን ላይ ከእናታችሁ ጋር ወላጆቿ በማይኖሩበት ሰዓት በመስሪያቤቱ ስልክ እየተደዋወልን እንገናኝ ጀምረናል። ሁሌም ባይሆን በሳምንት ሁለትና ሦስት ቀናቶች እንደዋወላለን። አሁን ላይ ስለትዳርና አብረን ስለመኖር ማውራት ጀምረናል። ቢያንስ ለትዳር የሚያስፈልጉ መሰረታዊ ነገሮችን ሟሟላት ስችል በአንድ ጥላ ስር ለመኖር ቀጠሮ ይዘናል። ታዲያ አንድ ቀን ህይዎቴን የቀየረ አንድ ታላቅ እድል ገጠመኝ፡፡ ከአንድ ኢስላማዊ ማተሚያ ድርጅት በአርታኢነት እንዳገለግል ተጋበዝኩ። ደሞዙ የሬዲዮ ጣቢያው ከሚከፍለኝ እጥፍ ስለነበር በደስታ ተቀበልኩ። በሙያዬ እስልምናን የማገልገል ህልሜንም የማሳካበት እድል ስለነበር ደስታዬ ወደር አልነበረውም። እዚሁ ማተሚያ ቤት እያገለገልኩ ቆየሁ ድርጅቱ የሚያሳትመው ወርሃዊ ጋዜጣ ላይም እሳተፋለሁ። በዚህኛው ዘርፍም አድናቂዎችን ማትረፍ ጀመርኩ። አንዳንዶችም መፅሐፍ እንዳሳትም ይጠይቁኝ ጀመር። የምሰራበት ድርጅትም መፅሐፍ ማሳተም የምፈልግ ከሆነ በነፃ አሳትሞ እንደ ሚያከፋፍልልኝ ቃል ገባልኝ። በ3 ወራት ውስጥ ከዚህ በፊት የፃፍኳቸውንና አዳዲስ ስራዎቼን አሰባስቤ አንድ መፅሐፍ አሳተምኩ። ሽያጩም አሪፍ የሚባል ስለነበር ጥሩ ገንዘብ ማግኘት ቻልኩ። ባገኘሁትም ገንዘብ የቤት ቁሳቁስ ካሟላሁ በኋላ ወደ እናታችሁ ቤተሰብ ሽማግሌ ልኬ እናታችሁን አስጠየቅኩ።
እንደምታውቁት አያታችሁ ማካበድ የማይወድ ስለነበር ስነምግባሬንና ዲን ላይ ያለኝን አቋም ካጣራ በኋላ ቀለል ባለ መህርና ኒካህ እናታችሁን ጀቡኝ። ከዚህ በኋላ ያለውን አያታችሁ ስለነገረቻችሁ የምታውቁት ይመስለኛል።" ሲል ታሪኩን አጠናቀቀልን። የነ አባቢ ታሪክ በጣም ደስ የሚል ታሪክ ነበር ለኛ። የወላጆችን ታሪክ መስማት የሚሰጠውን ሀሴት ያጋጠመው ብቻ ነው ሊያውቀው የሚችለው።
"ማሚ እስኪ አባቢ የዋሸው ወይም የዘለለው ታሪክ ካለ ንገሪን!" አለቻት ሪ ቡናውን ጥዳ ራት በማቅረብ ላይ ላለችው ማሚ።
"ምን ይሄ ጋዜጠኛ አባታችሁ ዜና ሚያነብ ይመስል ሚነገረውንም ማይነገረውንም ነግሮ ጨርሶት የለ እንዴ ምኑን ልንገራችሁ!" አለች የተናደደች ለመምሰል እየጣረች።
"ቆይ ማሚ ግን አባቢን ለመጀመሪያ ጊዜ ስታይው ምን ተሰማሽ?" አልኳት ላሳፍራት ብዬ።
"አይ እንግዲህ ለልጅ ፊት መስጠት እኮ..." ብላ ወደ ጓዳ ገባች። ውይ የኔ አይናፋር እናት እንዴት እኮ ደስስ እንደምትለኝ!...ራት በልተንና ቡና ጠጥተን ስንጨርስ ወደየ መኝታችን ተበታተን። አሁን የሂክማ ፎቶ ጉዳይ ይቀረኛል። እስኪ ከተሳካልኝ የእድሌን ልሞክር
.
.
ይቀጥላል!
🧕ሂክማ🧕
ክፍል አስራ አምስት
✍ኢብኑ ኢብራሂም
፡
"ቆይ ለምንድን ነው የኛ ታሪክ ይሄን ያህል ሰፍ እንድትሉ ያደረጋችሁ?" ሲል ጠየቀን አባቢ።
"እንዴ የስንቱን ታሪክ ሰፍ ብለን ስንሰማና ስናዳምጥ አይደል ያደግነው። እንዴት የወላጆቻችን ታሪክ ሰፍ አያደርገንም?" አለች ሪ።
"እኔ ግን ያባቴ ልጅ መሆን ስለምፈልግ የማሚ አይነቷን ጉብል እንዴት ማጥመድ እንደምችል ልምድ ለመቅሰም ስለምፈልግ ነው።" ስል ሁሉም ሳቁብኝ።
"ያም ሆነ ይህ ዛሬ ካቆሙኩበት ልቀጥልላችሁ። ምን ላይ ነበር ያቆምኩት?" ሲል ጠየቀን።
"እንዴ አባቢ ምንድን ነው እንደ history መምህር ያቆምንበት ምናምን ምትለው? በዚህ አይነትማ Final Exam ልፈትናችሁ ማለትህ አይቀርም! ኪኪኪኪ" አለች ሪ።
"አባቢ አሷን ተዋት። ያቆምክልን ከማሚ ጋ በስነ ፅሁፍ ምክንያት መግባባት እንደቻላችሁና እሷ ግጥም እየገጠመች አንተ ደግሞ የራስህን ፅሁፎች እየፃፍክ እየሰጣሃት እንደነበር ነግረኸን ነው ያቆምከው።" አልኩት።
"አንተ እውነትም በደንብ ወጥረህ ይዘሃል።" ብሎ ሁላችንንም አሳቀን።
"እናላችሁ ከእናታችሁ ጋር ያለን ቅርርብ እያደገ መጣ እንደናንተው ዘመን ፌስቡክ ቴሌግራም ምናምን ባይኖርም በደብዳቤና በግጥም የሆድ የሆዳችንን እናወራ ነበር። የሚገርመው ግን አሁንም በአካል ማውራት አልጀመርንም። ሱቅ ስትመጣ ልክ እንደማታውቀኝ ሁሉ እቃ ትገዛኝና ወረቀቷን ይዛ ትሄዳለች እንጅ አንድም ቀን ቁማ አዋርታኝ አታውቅም።
እንዲሁ እያልን ለሁለት ወር ያህል እንደቆየን አንድ ቀን ከአንድ የግል ሬዲዮ ጣቢያ የስልክ ጥሪ ደረሰኝ። ከሳምንት በፊት ሲቪዬን ያስገባሁበት ድርጅት ነው። ለኢንተርቪው እንደምፈለግና ነገ ቢሮ ድረስ እንድገኝ ነገሩኝ። በማግስቱ ቢሮ ድረስ ሂጄ ኢንተርቪው ወሰድኩና መስፈርቱን አሟልቼ በሰራተኝነት ተቀጠርኩ።
ይሄንን በደብዳቤ ለእናታችሁ የነገርኳት ዕለት በራቸው ላይ ቁማ ወደኔ እያየች ስታነባ ዋለች። በጣም እንደለመደችኝና ሱቁን ትቼ ሌላ ስራ ስጀምር እንዳልረሳት እንደምትሰጋ በወረቀት ላይ ፅፋ ላከችልኝ። ደብዳቤዋ ላይ የቤት ስልክ ቁጥራቸውንም አብራ ልካ እንድደውልላት አሳሰበችኝ። ይሄን ያህል ውስጧ እንደገባሁ አልገመትኩም ነበር። ለካንስ ከስነፅሁፍ ፍቅሯ ባሻገር የእኔም ፍቅር በውስጧ ሰፍሮ ነበር።" ብሎ ወደ ማሚ ሰረቅ አርጎ ተመለከተ። ማሚ እንደ ሁልጊዜው በሀፍረት ጉንጮቿ ቀልተው አቀርቅራ ቡናዋን በመቁላት ላይ ነበረች። እኔና ሪ ተጠቃቅሰን ፈገግ አልን። አባቢ ግን መተረኩን ቀጥሏል።
"...ሱቁን ለአጎቴ አስረክቤ የሬዲዮ ጣቢያው ውስጥ መስራት ጀመርኩ። መጀመሪያ ላይ ምሽት 3 ሰዓት ላይ የሚተላለፍ የመፅሐፍ ትረካ እንዳቀርብ ነበር ሃላፊነት የተሰጠኝ። ሁሌም ረጃጅም ልብወለዶችን ተርኬ ስጨርስ ሌላ እስኪጀመር የራሴን አጫጭር ፅሑፎችን አቀርብ ስለነበር፤ ከተራኪነትም ባሻገር በድርጅቱ የሚታተመው መፅሔት ላይ አንድ አምድ እንድይዝ እድል ተመቻቸልኝ። በትረካውም ሆነ በመፅሔቱ ላይ በማቀርባቸው ፅሑፎች ምክንያት ብዙ አድናቂዎችን አፈራሁ። የመፅሔቱ አምድ ላይ የአንባቢዎችን አስተያየትና የስነፅሁፍ ስራዎቻቸውን አሰፍር ስለነበር ብዙ ሙገሳዎች ይጎርፉልኝ ጀመር። ከአምዴ ስር ከሚሳተፉት ውስጥ እናታችሁ አንደኛዋ ነበረች። በነገራችን ላይ ከእናታችሁ ጋር ወላጆቿ በማይኖሩበት ሰዓት በመስሪያቤቱ ስልክ እየተደዋወልን እንገናኝ ጀምረናል። ሁሌም ባይሆን በሳምንት ሁለትና ሦስት ቀናቶች እንደዋወላለን። አሁን ላይ ስለትዳርና አብረን ስለመኖር ማውራት ጀምረናል። ቢያንስ ለትዳር የሚያስፈልጉ መሰረታዊ ነገሮችን ሟሟላት ስችል በአንድ ጥላ ስር ለመኖር ቀጠሮ ይዘናል። ታዲያ አንድ ቀን ህይዎቴን የቀየረ አንድ ታላቅ እድል ገጠመኝ፡፡ ከአንድ ኢስላማዊ ማተሚያ ድርጅት በአርታኢነት እንዳገለግል ተጋበዝኩ። ደሞዙ የሬዲዮ ጣቢያው ከሚከፍለኝ እጥፍ ስለነበር በደስታ ተቀበልኩ። በሙያዬ እስልምናን የማገልገል ህልሜንም የማሳካበት እድል ስለነበር ደስታዬ ወደር አልነበረውም። እዚሁ ማተሚያ ቤት እያገለገልኩ ቆየሁ ድርጅቱ የሚያሳትመው ወርሃዊ ጋዜጣ ላይም እሳተፋለሁ። በዚህኛው ዘርፍም አድናቂዎችን ማትረፍ ጀመርኩ። አንዳንዶችም መፅሐፍ እንዳሳትም ይጠይቁኝ ጀመር። የምሰራበት ድርጅትም መፅሐፍ ማሳተም የምፈልግ ከሆነ በነፃ አሳትሞ እንደ ሚያከፋፍልልኝ ቃል ገባልኝ። በ3 ወራት ውስጥ ከዚህ በፊት የፃፍኳቸውንና አዳዲስ ስራዎቼን አሰባስቤ አንድ መፅሐፍ አሳተምኩ። ሽያጩም አሪፍ የሚባል ስለነበር ጥሩ ገንዘብ ማግኘት ቻልኩ። ባገኘሁትም ገንዘብ የቤት ቁሳቁስ ካሟላሁ በኋላ ወደ እናታችሁ ቤተሰብ ሽማግሌ ልኬ እናታችሁን አስጠየቅኩ።
እንደምታውቁት አያታችሁ ማካበድ የማይወድ ስለነበር ስነምግባሬንና ዲን ላይ ያለኝን አቋም ካጣራ በኋላ ቀለል ባለ መህርና ኒካህ እናታችሁን ጀቡኝ። ከዚህ በኋላ ያለውን አያታችሁ ስለነገረቻችሁ የምታውቁት ይመስለኛል።" ሲል ታሪኩን አጠናቀቀልን። የነ አባቢ ታሪክ በጣም ደስ የሚል ታሪክ ነበር ለኛ። የወላጆችን ታሪክ መስማት የሚሰጠውን ሀሴት ያጋጠመው ብቻ ነው ሊያውቀው የሚችለው።
"ማሚ እስኪ አባቢ የዋሸው ወይም የዘለለው ታሪክ ካለ ንገሪን!" አለቻት ሪ ቡናውን ጥዳ ራት በማቅረብ ላይ ላለችው ማሚ።
"ምን ይሄ ጋዜጠኛ አባታችሁ ዜና ሚያነብ ይመስል ሚነገረውንም ማይነገረውንም ነግሮ ጨርሶት የለ እንዴ ምኑን ልንገራችሁ!" አለች የተናደደች ለመምሰል እየጣረች።
"ቆይ ማሚ ግን አባቢን ለመጀመሪያ ጊዜ ስታይው ምን ተሰማሽ?" አልኳት ላሳፍራት ብዬ።
"አይ እንግዲህ ለልጅ ፊት መስጠት እኮ..." ብላ ወደ ጓዳ ገባች። ውይ የኔ አይናፋር እናት እንዴት እኮ ደስስ እንደምትለኝ!...ራት በልተንና ቡና ጠጥተን ስንጨርስ ወደየ መኝታችን ተበታተን። አሁን የሂክማ ፎቶ ጉዳይ ይቀረኛል። እስኪ ከተሳካልኝ የእድሌን ልሞክር
.
.
ይቀጥላል!
🧕ሂክማ🧕
ክፍል አስራ አራት
✍ ኢብኑ ኢብራሂም
...ጠዋት የነቃሁት "ይሄ ልጅ አሁንም አልተነሳም እንዴ?" የሚለውን የአባቢን ድምፅ ስሰማ ነበር። ድምፁን አንደሰማሁ በርግጌ ተነሳሁ። ሰዓቱን ሳይ 12:30 ይላል።
"አባቢ ደግሞ መስጂድ ልትሄድ ስትል አትቀሰቅሰኝም ነበር እንዴ?" ስል ተነጫነጭኩበት።
"ስቀሰቅስህ እኮ እሽ እነሳለሁ ብለኸኝ ነበር።" አለኝ አባቢ። ገና ለማጅ ነው ብሎ ስላሰበ መሰለኝ ብዙም ያልተጫነኝ።
"እንቅልፋም አሁን መነዛነዙን ትተህ ፀሀይ ከመውጣቷ በፊት አትሰግድም?" አለችኝ ሪ።
"ሂጂ ሙጢ! እንዲ ከምትለፈልፊብኝ ስትነሽ አትቀሰቅሺኝም ነበር?" አልኳት።
"በቃ አታስብ ነገ ድጋሚ እንዳተኛ አድርጌ ነው ምቀሰቅስህ አሁን ሂድና ዱሓህን ስገድ!" አለችኝ። መጨቃጨቁን ተውኩና ውዱዕ አድርጌ ሰገድኩ። በርግጥ ከትላንቱ ዛሬ እሻላለሁ። ምንም እንኳን በጀመዓ ባልሰግድም ፀሐይ ከመውጣቷ በፊት ነው የሰገድኩት።
ከቁርስ በኋላ እንደተለመደው ወደ ት/ቤት ሄድኩ። ሁል ጊዜ እንደምናደርገው ከነ ዮኒና ሃሚ ጋ ተገናኝተን ክላስ እስክንገባ ድረስ ተሰባስበን እያወራን ነው። እነ ዩኒ ስለ ሂክማ አንስተው ጠይቀውኝ እውነቱን ነገርኳቸው። ጭንቀት ውስጥ የገባሁ ስለመሰላቸው ሁሉን ነገር ትቼ ወደ ድሮው ህይወቴ እንድመለስ ተማፀኑኝ። እኔ ግን መጨረሻውን ሳላይ ወደኋላ እንደማልል አስረግጬ ነገርኳቸውና ወደየ ክፍላችን ገባን።
እረፍት ላይ ለይላን አገኘኋት። ዛሬም እንደ ድሮው ልሆንላት አልቻልኩም። እንዲህ የሆንኩበት ምክኒያት እንኳን ለሷ ለኔም ግልፅ አይደለም። እሷ እያሰበች ያለችው እንደጠላኋትና ልርቃት እንደፈለኩ ነው። ስለሆነም ተንሰቅስቃ እያለቀሰች እንዳልርቃት ትማፀነኝ ይዛለች። በርግጥ ለይላን ስቀርባት ሌሎች ሴቶችን እንደምቀርበው ሁሉ ለጊዜያዊ ቢሆንም ለኔ ያላትን እውነተኛ ፍቅርና ለኔ ስትል የከፈለችውን መስዋትነት ባየሁ ጊዜ መጉዳት እንደሌለብኝ ራሴን አሳምኛለሁ። ቢሆንም ግን ውስጤ ባላወቅኩት ምክኒያት ለሷም ሆነ ባጠቃላይ ለሴት ልጅ ያለኝ ስሜት ተቀዛቅዞብኛል።
ለይላ አሁንም ጭኔ ላይ ጭንቅላቷን አድርጋ እያለቀሰች ነው። እኔ ደግሞ በፍፁም እንደማልርቃት እየገለፅኩ እያባበልኳት ነው። በመሃል ግን ድንገት ብድግ ብላ፦
"ሳሊሜ እውነት የምትወደኝ ከሆነ አሁኑኑ ከንፈሬን ሳመኝ።" አለችኝ። ወላሂ እስከዛሬ ድረስ ዝሙት ላይ ወድቄ ባላውቅም ከዛ በታች የሆነውን ተግባር ሁሉ ፈፅሜያለሁ። ከዛ አኳያ ከንፈሯን መሳም እዚህ ግባ የማይባል ቀላል ተግባር ቢሆንም ዛሬ ግን ከንፈሯን መሳም ከተራራ በላይ ገዝፎ ታየኝ። እንቢ ልላት ፈለኩ። ነገር ግን የተሰበረውን ቅስሟን፣ በሃዘን የተጨማደደውን ፊቷንና ከአይኖቿ የወረዱትን የእንባ ዘለላዎቿን ሳይ እንቢ የማለት ወኔ አጣሁና ከንፈሯን ነካ የማድረግ ያህል ስሜያት ተመለስኩ። ብዙም ባትደሰትም በትንሹ ዘና ማለት ጀመረች። ጥቂት አዋርቻት የዕረፍት ሰዓት ሲገባደድ ተሰናብቻት ወደ ክላስ ገባሁ።
ለምሳ ስንወጣ ከነ ዮኒ ጋር ምሳ በልቼ ወደ መስጂድ ሄድኩ። ዛሬ ተደብቄያቸው አይደለም የሄድኩት። "መስጂድ ደርሼ መጣሁ።" ብያቸው ነው የሄድኩት። ከአይናቸው እስክሰወር ድረስ በአይናቸው ሸኙኝ። ሳላሳዝናቸው አልቀረሁም። የኔ ከመሬት ተነስቶ እንዲህ መቀየር ግራ አጋብቷቸዋል። ሁኔታቸው የሂክማን ምክር አስታወሰኝ። አዎ የምትመዝንበት ሚዛን ሲዛባ እውነታው ሁሉ ይቃረናል። እነ ሃሚ እኔን የሚመዝኑት በበፊቱ ማንነቴ ነው። ከዛ አኳያ ሲያዩኝ እልኸኝነቴ እዚህ ድረስ አድርሶ ያላመንኩበትን ተግባር እያስፈፀመኝ እንደሆነ ሲያስቡ ነው እንዲያዝኑልኝ ያስገደዳቸው። እርግጥ ነው እውነታው ከዚህ የራቀ አይደለም። እኔን የመስጂድ በር ያስረገጠኝም ሆነ ጌታዬ ፊት በሱጁድ ያስደፋኝ እልኸኛነቴና በውስጤ እያንሰራራ ያለው የሂክማ ፍቅርና እሷን የማየት ጉጉት ነው። ቢሆንም ግን ይህ ተግባሬ(ወደ መስጂድ ማቅናቴ) በጤናማ ሚዛን ለመዘነው ይበል የሚያሰኝ እንጅ የሚያሳዝን አልነበረም። እኔም ይሄ ህይዎት የመንፈስ እርካታና ሀይል እየሰጠኝ በመሆኑ እየወደድኩት ነው። ሁሉም ቢቀር ከአሏህ ባሮች ጋር እንደመቀላቀል ምን የሚያስደስት ነገር አለ?
ወደ መስጂዱ ግቢ ስገባ እንደ ትላንቱ ሀምዱን አገኘሁት። ውዱዕ እያደረገ ነበር። እኔን ሲያየኝ ፈገግ ብሎ የውዱዕ ውሃ ሊቀዳልኝ ሊነሳ ሲል እንዳይነሳ ምልክት ሰጥቼው እኔ ራሴ ቀድቼ መጣሁና ከጎኑ ተቀመጥኩኝ። እያየብኝ ባለው ለውጥ እንደተደሰተብኝ ነገረኝ። እኔም በዚሁ መፅናት እንድችል ዱዓ አድርግልኝ አልኩት።
"ይሄማኮ ዘንግቼው የማላውቀው የሁል ጊዜ ተግባር ነው።" አለኝ። ሱብሃነላህ ምን አይነት ሰው ነው ግን? ያን ሁሉ ግፍ ፈፅሜበት ቂም ሊይዝብኝ ይቅርና የዱዓው አንድ አካል ማድረጉ አስገረመኝ።
"ሀምዱዬ በአላህ ይሁንብህ እስካሁን ያደረስኩብህን ሁሉ አውፍ በለኝ።" አልኩት።
"እኔ ዘንድ ምንም አይነት ይቅር የሚባል ጥፋት የለብህም። ባይሆን ጓደኛህ እንድሆን ፍቀድልኝ" አለኝ። በስብዕናው ይበልጥ ተማረኩ። ነፃ አውጪዬ እንዲሆንም በራሴ ላይ ሾምኩት። ውዱዕ ስንጨርስ ወደ ውስጥ ገባን። ሰግደንም ወጣንና ብዙ ነገር እያወራን ት/ቤታችን ደረስን። እኔ ተለይቼው ወደነ ሃሚ ስሄድ እሱ ደግሞ የሚፅፈው ፅሁፍ እንዳለው ነግሮኝ ወደ ላይብረሪ ሄደ። የተቀረችውን የረፍት ሰዓት እነ ዮኒ ጋር አሳለፍኩ። እንደ በፊቱ ሰፊ ጊዜ ስላልሰጠኋቸው ቅር ተሰኝተውብኛል። እንግዲህ ምን ማድረግ ይቻላል? ወይ እንደኔ በትክክለኛው ሚዛን ሊመዘኑ፤ አልያም እኔ እንደ ድሮው ማንነቴ በተሳሳተው ሚዛን ልመዘን ግድ ይላል። መጨረሻው ምን እንደሚሆን አሏህ ነው የሚያውቀው።
★
ዛሬ ቀኑ አርብ ነው። በህይወቴ ለመጀመሪያ ጊዜ በራሴ ፍቃድ መስጂድ ሂጄ ጁመዓ የሰገድኩበት ቀን ቢኖር ዛሬ ብቻ ነው። ምንም አንኳን በትምህርት ምክንያት በመስጂድ ውስጥ የሚተላለፈውን ሙሉ ስብከት ለመሳተፍ ባልችልም ወደ መጨረሻ ላይ ደርሼ የተወሰነ ግንዛቤዎችን ጨብጫለሁ። ዛሬ ምሽት ላይ ሁለት አጓጊ ፕሮግራሞች ስላሉኝ እስኪመሽ ጓጉቻለሁ። አንደኛው ፕሮግራም የነአባቢ ታሪክ ሲሆን ሁለተኛው ፕሮግራም ደግሞ ሂክማን ፎቶ የማስላክ ፕሮግራም ነው። በርግጥ የሂክማ ፎቶ የማስላኩ ጉዳይ መሳካቱን እርግጠኛ አይደለሁም። ቢሆንም ግን ለአራት ቀናት ያህል ያለ ማቋረጥ ሶላት መስገድ ስለቻልኩ እንቢ ትለኛለች የሚል ግምት የለኝም። በነገራችን ላይ ሱብሂ ላይ ሪ ውሃ ፊቴ ላይ እየረጨች ስለምትቀሰቅሰኝ ከአባቢ ጋር መስጂድ በጀመዓ መስገድ ጀምሬያለሁ። ከሂክማ ጋርም ጥሩ የሆነ መቀራረብን ፈጥረናል። ምንም እንኳን ብዙ ነገሯን ሚስጥር የማድረግ አባዜ ቢኖርባትም ከቀን ወደ ቀን ግን በደምብ እየተግባባን ነው። ዛሬ ደግሞ ከተሳካልኝ ፎቶዋን የማየት እድል አገኛለሁ።
የማይመሽ የመሰለኝ ቀን መሽቶ ከቤተሰቦቼ ጋር ተሰባስበን ተቀምጠናል። አባቢ በቃሉ መሰረት ሳምንት የጀመረልንን ታሪክ ሊቀጥልልን ፊታችን ተሰይሟል። ማሚ ሳሎን ቤት ውስጥ ሆና ቡና እየቆላች ነው። እኔና ሪ ደግሞ አባቢ ፊት ለፊት ተቀምጠን አይናችንን እያቁለጨለጭንበት እንገኛለን።
.
.
ይቀጥላል!
ሂክማ
ክፍል አስራ ሦስት
...እንደተለመደው አጥንቼ እንደጨረስኩ ሂክማን ፍለጋ ወደ ፌስቡክ መንደር ጎራ አልኩ። የዛሬውን የውሎ ሪፖርት እስክነግራት ቸኩያለሁ። ምናልባትም ከሁለትና ሦስት ቀናቶች በኋላ ፎቶዋን ልካልኝ እንዲህ ልቤን ያንበረከከችውን ጀግና ማንነት ማወቅ እችል ይሆናል።
ሂክማ ኦን ላይን ላይ ነበረች። ቀድሜ ኢስላማዊ ሰላምታ አቀረብኩላት። እሷም አፀፋዊ ምላሽ ሰጠችኝና፤
"ሶላት እንዴት ነበር?" ስትል ጠየቀችኝ።
"ይሄው አንድም ሳላስቀር ስሰግድ ነው የዋልኩት።" አልኳት።
"እስኪ ሳትዋሽ ንገረኝ ሁሉንም በአግባቡ ሰግደሃል?" ስትል ጠየቀችኝ። ምን መመለስ እንዳለብኝ ግራ ገባኝ እንዳልዋሻት ሁሉንም አውቃለሁ ስላለችኝ ምናልባት እንደዋሸኋት አውቃ 'ቃሌን አልሞላልህም!' እንዳትለኝ ሰጋሁ። እውነቱን ብነግራት ደግሞ 'ዛሬ ሙሉ ሶላት ስላልሰገድክ ከነገ ጀምሮ ነው መቆጠር የሚጀምረው።' ብላ የዛሬውን ልፋቴን ከንቱ እንዳታረግብኝና ሶላት የምሰግድበትን ቀናቶች እንዳታራዝምብኝ ፈራሁ። ስላንተ ሁሉንም አውቃለሁ ያለችው ለማስፈራራት ያህል ሊሆን ይችላል ብዬ በማሰብ መዋሸቱን መረጥኩና፤
"አዎ ሁሉንም በሰዓቱና በአግባቡ ነው የሰገድኩት።" አልኳት።
"እሱን እንኳን ተወው! ፈጅርን ፀሐይ ከወጣ በኋላ ነው የሰገድከው። ያው የመጀመሪያ ነው በሚለው ልናልፈው ካልሆነ በቀር!" ብላ አስደነገጠችኝ። እውነት ለመናገር የሂክማ ነገር ከማስበው በላይ ግራ እያጋባኝ ነው። የውጭ ሰው ናት እንዳይሏት የውስጥ ሚስጥሬን ሳይቀር ታውቃለች። የውስጥ ሰው ናት እንዳልል ደግሞ ከቤተሰቦቼ ውስጥ በሷ ደረጃ የሚጠረጠር ሰው የለም። ሪ ስልክ አትይዝም። የማሚ ስልክም ኢንተርኔት የማትሰራ ትንሽዬ ስልክ ናት። አባቢም ቀንም ማታም ቢዚ ስለሆነ ለዚህ የሚሆን ትርፍ ጊዜ የለውም። እንዲያው አንዳቸው ናት ብንል እንኳን፤ ማናቸውም የሷን ያህል በሳልና አቅሜን ሊፈታተን የሚችል የለም። ታዲያ ማን ትሆን? ግራ ተጋባሁ። ሀምዱ ነው ብዬ የጠረጠርኩት ጥርጣሬ ስህተት እንደሆነ አረጋገጥኩ። እሱ ሱቢህ በጊዜ ልስገድ አልስገድ ይቅርና ዙሁር እንኳን መስገዴን ያወቀው ገና መስጂድ ውስጥ ያየኝ ሰዓት ነው።
"ቆይ አንች ግን ማን ነሽ? እንዴትስ የውስጥ ሚስጥሬን ልታውቂ ቻልሽ? መቼም ጠንቋይ መሆን አለብሽ!"
"ጠንቋይ ለራሱ አያውቅም! ሲባል አልሰማህም?"
"እሱም እኮ ስለሰዎች እንጅ ስለራሴ አውቃለሁ አላለም።"
"ከፅንስነቱ ጀምሮ አብሮት ስላለው ራሱ ማወቅ ያልቻለ ስለሰው ያውቃል ብለህ ታስባለህ?" አለችኝ። ከዚህ በላይ ልከራከራት አልቻልኩም።
"አሁን ማረሳሳቱን ተይና የጠየቅኩሽን መልሽልኝ!" አልኳት ትዕግስቴ አልቆ።
"ይሄን ለማወቅ እኮ ብዙ መልፋት አይጠበቅብኝም።"
"እኮ እንዴት??"
"አንድ ለብዙ አመት የሱቢህን ሶላት ያልሰገደ ሰው የመጀመሪያ ሶላቱን በወቅቱ ሊሰግ ያለመቻሉ እድል ሰፊ ነው። አንተ ደግሞ እንቅልፋም ስለሆንክ ከረፈደ ነው ምትነሳው ተሳሳትኩ?" አለችኝ። መቸም እኛ ሰዎች አዕምሯችንን በአንድ ነገር ላይ ካሳመንነው ከዛ አንግል ባለፈ ሊመለከት አይችልም። በዚህ መልኩ ይሆናል ብዬ በጭራሽ አልጠበቅኩም ነበር። አሁን ደግሞ ሀምዱ ላይ የነበረኝ ጥርጣሬ የመጀመሪያ ቦታውን ተቆጣጠረ። አሁንም ግን ሌላ አሻሚ ነገር ንግግሯ ውስጥ አገኘሁ። አዎ እንቅልፋም እንደሆንኩና አርፍጄ እንደምነሳ እንዴት አወቀች? የጥያቄውን አቅጣጫ ወደሷ አዙሬ ጠየቅኳት።
"አምሽቶ የሚተኛ ሰው አረፍዶ መነሳቱ ሳይታለም የተፈታ ጉዳይ እንደሆነ ስለማውቅ ነዋ!" ስትል መለሰችልኝ።
"እና እንደዛ ከሆነ ስልኬን ልስጥሽና ለምን እየደወልሽ አትቀሰቅሺኝም?" አልኳት። ይሄን ያልኳት በስልኳ አማካኝነት ማንነቷን ለማጣራት በማሰብ ነው። ስልኳን ማግኘት ከቻልኩ ሰፈራችን ውስጥ የሚኖር የቴሌ ሰራተኛ ጓደኛ ስላለኝ እሱ በማን ስም እንደተመዘገበና በ GPS አማካኝነት ያለችበትን Location እንዲያጣራልኝ ማድረግ እችላለሁ።
"ኪኪኪ 'እንኳን ሲሸጡን ሲደልሉን እናውቃለን' አለች ዶሮ ካንጀት ካለቀሱ እንባ አይገድም መነሳት ከፈለክ ከስልክ የማይተናነስ አላርም አለልህ ሙላና ተኛ። እንዳትነሳ ምክንያት የሚሆንብህ ዋነኛው ነገር ደግሞ በጊዜ አለመተኛትህ ነው። ስለዚህ በጊዜ መተኛት ልመድ። ነብያችን (ሰዐወ) ከኢሻዕ በኋላ ማምሸትም ሆነ ወሬ ማውራት አይወዱም ነበር።" ስትል ረዘም ያለ ምክር ሰጥታ ተስፋዬ ላይ ውሃ ቸለሰችበት። እንግዲህ ያለኝ አማራጭ ከዚህ በኋላ አንድ ሁለት ቀን ሰግጄ ፎቶዋን ማስላክ ነው። ኡፍፍፍፍ! ያላመኑበትን ነገር መስራት እንዴት ይጨንቃል? ምንም እንኳን አንድ ቀን ኢማነኛ የመሆን ምኞት ቢኖረኝም፤ አሁን ላይ ለዛ ዝግጁ ስላልሆንኩ ለሷ እልህ ስል እንጅ ለአሏህ ብዬ አይደለም የምሰግደው። በዛ ላይ ገና በአንድ ቀን ከነ ዮኒ ጋር መቀዛቀዝ ታይቶብኛል። በዚህ ከቀጠልኩኝ እስከ መጨረሻው መለያየታችን የማይቀር ነው። እኔ ደግሞ እነሱን ማጣት አልፈልግም። በርግጥ ሰው አዋዋሉን ይመስላል እንደሚባለው በዚች በአንድ ቀን ውስጥ በዲን ሰዎች እይታ ጥሩ የሚባሉ ለውጦችን ማሳየት ጀምሬያለሁ። ውስጤም ቢሆን የሆነ የርጋታ አይነት ስሜት ይሰማው ይዟል። ቢሆንም ግን ገና ቦርቄ ሳልጨርስ መመንመን አልፈልግም። ሀምዱና ያጎቴ ልጅ በክሪ ራሱ በዚህ እድሜያቸው ሶላት፤ ሃራም፤ ሃላል እያሉ ሲጨናነቁ ሳያቸው እንዴት እንደሚያሳዝኑኝ! አባ እኔ እንደሆን ዩንቨርስቲ ገብቼ ላይፌን ሳልቀጭማ አላስበውም።
ሂክማን "እና ለምን አንቺ እስከዚህ ሰዓት ታመሻለሽ?" ብዬ ለመጠየቅ አስቤ ተውኩት። ደግሞ "አዎ ልክ ነህ ማምሸት የለብንም!" ብላ ጭራሹኑን ብትጠፋብኝስ? በምትኩም፦
"በቃ እሽ አባቢን እንዲቀሰቅሰኝ አደርጋለሁ።" አልኳት።
"በጣም ጥሩ ሃሳብ ነው። እንዲያውም አባትህ ጋር መስጂድ በጀመዓ ነው መስገድ ያለብህ!" ብላኝ አረፈች። አይ መከራ! ምናለ ያባቢን ስም ባላነሳሁ ኖሮ። አሁን ደግሞ በጀመዓ ሰገድክ አልሰገድክ እያለች ልትነዘንዘኝ ነው? ቆይ ግን አባቢ ሱብሂን በጀመዓ እንደሚሰግድ እንዴት አወቀች? መጠየቅማ አለብኝ።
"ቆይ አባቢ መስጂድ እንደሚሰግድ በምን አወቅሽ?"
"አንዳንድ ጥያቄዎች መልስ የላቸውም!"
"እኮ ለምን?"
"እሱን ሲያጋጥምህ ታውቀዋለህ።" ስትል አድበስብሳ አለፈች። የሆነች ግራ ነገር! ግራ ማጋባት ስትወድ። በምን ቀን ነው ያወቅኳት ባካችሁ?
"በል በቃ እንተኛ ደግሞ ዛሬም ሱብሂን ዱሓ እንዳታረገው!" አለችኝ። ዛሬ ይሄ ዱሓ ሚባል ነገር ሰግጀው እንኳን ሳላውቅ በኔ ምክንያት አስሬ ሲነሳ ዋለ። ሂክማን ተሰናብቻት ወጣሁ። በነገራችን ላይ ከሂክማ ጋር እያወራሁ እግረ መንገዴንም ለይላን እያዋራኋት ነበር። ለይላ ቀን በክላስ ደወል ምክኒያት የተገላገልኩትን ጥያቄ በ 'Fb' ወጥራ ይዛ እየነዘነዘችኝ ነበር። ስታስጨንቀኝ ግዜ ነገ በሰፊው አብሪያት በመሆን እንደምክሳት ቃል ገብቼ አረጋጋኋት። ከሂክማ ጋር እንደተሰነባበትን እሷንም ተሰናብቼ ተኛሁ።
.
.
.ይቀጥላል!
እነ አባቢ በሳቅ ፈረሱ። ትንሽ ወደራሷ መለስ ካለች በኋላ ፊት ለፊቷ የተቀመጠውን የውሃ ብርጭቆ አንስታ ምኝታ ክፍሌ ድረስ አሯሯጠችኝ። ክፍሌ ገብቼ በሩን ስዘጋባት እየተነጫነጨች ተመልሳ ሄደች። ይሄን ቃሪያ ምላሷን እንዲህ በቃሪያ ማቃጠል ካልሆነ በቀር ማን ይችለዋል።
.
.
.
ይቀጥላል...
#ሂክማ
ክፍል 12
...መስጂድ ስገባ ሀምዱ ተንደርድሮ መጥቶ ሰላም አለኝ። ፊቱ ላይ ያየሁትን ፈገግታ መቼም ልረሳው አልችልም።
"ሳሊሜ እንኳን ደህና መጣህ! ቆይ የውዱዕ ውሃ ላምጣልህ።" ብሎኝ ሄደ። ብታምኑም ባታምኑም ይሄ መስጂድ ለት/ቤታችን ቅርብ ቢሆንም አንድም ቀን ገብቼ አይቸው አላውቅም። መስጂዱ በጣም ይመስጣል። ውር ውር የሚሉት ምዕመናኖችን ሳይ ከነሱ መሃል መገኘት የማይገባኝ ቆሻሻ እንደሆንኩ ያህል ተሰማኝ። የመስጂዱን ምንጣፍ በእግሬ ብረግጠው የሚነጀስ መስሎም ታዬኝ።
ሀምዱ በውዱዕ እቃ ውሃ ሞልቶ አመጣልኝ። ሚስኪን! ይሄኔ እምነቴ ሳይሆን አንዲትን ሴት ለማየት ያለኝ እልሄ እዚህ እንዳመጣኝ ቢያውቅ እንዲህ ባልተደሰተብኝ ነበር።
ሂክማ እሱ ሊሆን እንደሚችል ስለጠረጠርኩ ከአሁን አሁን ፍንጭ አገኝበታለው በማለት ንግግሩንና እንቅስቃሴውን በአይነ ቁራኛ መከታተሌን አላቆምኩም። እንዴት ልመጣ እንደቻልኩ ይጠይቀኛል ብዬ ስጠብቅ፤ ስሌላ ጉዳዮች ብቻ ሲጠይቀኝ ቆይቶ ውዱዕ ጨርሰን ወደ መስጂድ ለመግባት ተነሳን። ጫማዬን ተቀብሎ ደህና ቦታ ላይ አስቀመጠልኝና እጄን ይዞ ወደ ውስጥ አስገባኝ። ሀምዱ ምንም ቂም አልያዘብኝም። እንዲያውም ወደ መስጅድ በመግባቴ እጅጉን ደስ ተሰኝቷል።
ዙሁርን ከዘመናት በኋላ በጀመዓ ሰገድኩ። ከመስጅድ ወጥተን ት/ቤታችን እስክንደርስ ሀምዱ አብሮኝ ነበር። ልክ ግቢ እንደገባን እነ ዮኒ እንዳያዩኝ ተሰናብቼ ተለየሁት። ውስጤ አንድ ነገር መጠርጠር ጀምሯል። አዎ! ሀምዱ ወደ መስጅድ እንዴት እንደመጣሁ ለምን ሳይጠይቀኝ ቀረ? ይሄ ጥርጣሬዬን ከፍ የሚያደርግ አንድ ነጥብ እንደሆነ አድርጌ ያዝኩት። እነ ዮኒጋ ስደርስ እየተጫወቱ አገኘኋቸው።
"አንተ የታባህ ሄደህ ነው ይሄን ያህል የቆየኸው? አብረህን ሳትጫወት እኮ የምሳ ረፍታችን ሊያልቅ ነው።" አለኝ ዮኒ። እስካሁን መስጂድ እንደሄድኩ አልነቁብኝም።
"ተረኛህ ደግሞ ፈልጋህ መጥታ ነበር።" አለ ሃሚ።
"ለይላ መጥታ ነበር?" አልኳቸው።
"አዎ አይንህ ሳይርባት አልቀረም ተቅበዝብዛብን ሄደች።" ዮኒ ነበር የመለሰልኝ። ልክ ዮኒ ይሄን እዳለኝ አንድ ቀጠን ያለ መዳፍ ከኋላዬ በኩል አይኔን ጨፍኖ ያዘኝ። ማንነቱን ለማወቅ ጊዜ አልወሰደብኝም።
"ለይላ ነሽ" ስላት አይኔን ለቃ በፊት ለፊቴ በኩል መጥታ እየተጠመጠመችብኝ፤
"አንተ እስካሁን የታባህ ቆይተህ ነው?" አለችኝ።
"ለሆነ ጉዳይ ከግቢ ወጣ ብዬ ነው።"
"እና ደህና ነህልኛ? እንዴት አባህ እንደናፈቅከኝ!" እያለች ይዛኝ በፅድ ወደተከበበው የት/ቤታችን ባንዴራ ወሰደችኝ።"
"እንደናፈቅኩሽ ያስታውቅብሻል።" አልኳት።
"አንተ ደግሞ ሰው ባንተ ናፍቆት ሲሰቃይ ማየት ያስደስትሃል!" አለችን እጆቿን በትከሻዬ በኩል አሳልፋ አቅፋ አንገቴ ውስጥ ጭንቅላቷን እየወሸቀች።
"ብትናፍቂኝ ምን ትሆኛለሽ? መቼም ናፍቆት እደ ኦክስጅን አጥሮ አይገልሽ!"
"ቆይ አንተ ሰሞኑን ምን አይነት ፀባይ ነው እያሳየኸኝ ያለኸው? አስጠላሁህ እንዴ?" አለችኝ ጭንቅላቷን ቀና አድርጋ እየተመለከተኝ።
"እኔ እንደዛ የሚል ቃል ወጣኝ?"
"እና እሽ ያ ሁሉ የፍቅር ቃላት የት ገባ? አልታወቀህም እንጅ ፀባይህ ተቀያይሯል እኮ።" አለችኝ ፊቷን ክስክስ አድርጋ። አይኖቿ ለማንባት እያቆበቆቡ እንደሆነ ያሳብቃሉ። ደግነቱ ምላሽ ሳልሰጣት የመግቢያ ደወል ተደወለና ደስ እንዲላት ብቻ ጉንጯን ስሜ ተለየኋት። የዕለቱ ትምህርት ተገባዶ ወደ ቤት ስንለያይ ዮኒ፤
"በል እንግዲህ መልካም የስብከት ምሽት ይሁንልህ¡" አለኝ።
"እንዴ ዙሁር እኮ አልሰገድክም ልትዋሻት ነው ወይስ ከአሱር ጋር ሰግደህ ሰግጃለሁ ልትላት ነው?" አለ ሃሚ።
"ውይ ሚስኪኪኪኪን! ለካ የ7 ሰዓቱን ስግደት አልሰገድክም። አሁንስ አንጀቴን በላሃኝ። በቃ ለምን አትተዋትም?" ሲል ዮኒ አስተያየቱን ሰነዘረልኝ።
"አዎ ዮኒ እውነቱን ነው በቃ አንዳንዴ እኮ ሽንፈትን አምኖ መቀበል ጥሩ ነው።" ሲል ሃሚ የዮኒን ሃሳብ አጠናከረ።
"አይ ቢያንስ እንኳን ማንነቷን ልወቅ እንጅ!" አልኳቸው።
"እሽ እንደፈለክ።" አለ ዮኒ። በዚህ መልኩ ተለያይተን ወደዬ ቤታችን አቀናን።
ቤት ገብቼ አሱርን ስሰግድ ሰግጄ እስክጨርስ ድረስ ሪሃና ተገርማ ቆማ አየችኝ። ማሚም እንዳላፍርና እንዳልሸማቀቅ ስለሰጋች ችላ ያለች ብትመስልም በሳሎን ቤቱ ባለፈች ቁጥር የደስታ ሳቅ ውስጧን እየተናነቃት በቆሪጥ እያየችኝ ነው። ሰግጄ ስጨርስ ሪሃና፤
"አንተ ልጅ ግን ዛሬ በደህናህ ነው?" ስትል ጠየቀችኝ።
"ምነው ደህና አልመስል አልኩሽ እንዴ?" አልኳት የሰገድኩበትን መስገጃ እያጣጠፍኩ፡፡
"ቀላል! ቆይ የምትሞትበት ቀን ተነገረህ እንዴ?" አለችኝ። ሪ ስለሞት ስታነሳ መሞት የሚባል ጣጣ እንዳለ ትዝ አለኝ። እውነትም ቆይ እንዲህ በተዘናጋሁበት ሰዓት ብሞትስ? የጀነት ነኝ ወይስ የጀሀነም? ለነገሩ ምንም ጥያቄ አያስፈልገውም ጀሃነም ውስጥ VIP ተይዞልኝ እንደሚጠብቀኝ ግልፅ ነው። በሃሳብ ውስጥ ሰምጬ ሳልመልስላት ስቀር ማሚ የተጨነቅኩ መስሏት፤
"አንች ልጅ ምናለበት ባትጨቀጭቂው?" አለቻት።
"እንዴ ማሚ ይሄ ልጅማ በደህናው ከመሬት ተነስቶ ሶላት ሊጀምር አይችልም። ግድ የለሽም አባቢ ይምጣና ቁርዓን ይቅራበት።" አለቻት።
"አስተግፊሩላህ! አንች ልጅ እንዴት እንዴት ነው ምትናገሪው? ካልሽስ አንች ላይ ነበር ማስቀራት!" አለቻት።
"ማሚዬኮ ስወድሽ! አሁን እች ካንች ማህፀን ነው የወጣችው ቢባል ሰው ያምናል?" አልኳት ተነስቼ ግንባሯን እየሳምኩ።
"እናንተማ ቆይ! እኔ ላይ እያበራችሁ አስቸግራችኋል።" አለች ሪ እንደ መቅናት እያረጋት።
"አሁን ጭቅጭቁን ተዉ እና ውሃዋ ሳትሄድ ባልዲውን ሙሉ!" ብላ ስራ ሰጠችን ማሚ።
መግሪብ እና ኢሻዕንም በሰአቱ ሰገድኩ። ማታ አባቢ መጥቶ እራት እየበላን እያለ ሪሃና የዛሬውን ሁኔታዬን ለአባቢ ነገረችው። አባቢም፤
"እንዴ በዱሀ የተጀመረው የሳሊሜ ሶላት እስከ ኢሻዕ ዘለቀ ማለት ነው?" ብሎ ቀለደብኝ።
"ኢንሻ አላህ! ነገ ለሱብሂ ስትነሳ ከቀሰቀስከኝ ሱብሂንም በሰዓቱ እሰግዳለሁ!" አልኩት።
"እንዴ ሳሊሜ ኢንሻ አላህ ሲል ሰማሁት ልበል?" አለች እች ሙጢ ሪሃና። እኔንም ጨምሮ ሁላችንም ሳቅን። ሪሃና እውነቷን ነው። ከዛሬ ውጭ አንድ ተራ ሙስሊም ዘንድ የሚዘወተሩ ሀይማኖታዊ ቃላቶችን እንኳን በንግግሬ መሃል ቀላቅዬ አላውቅም ነበር። እድሜ ለሂክማ ዛሬ አንድ ቃል ለማለት በቃሁ።
"አራት አውቃት ሶላት ሰግዶ ይሄን ያህል ለውጥ ካሳዬማ፤ ነገ ሱብሂን በሰዓቱ ሲሰግድ ሀይለኛ ዳኢ ነው ሚወጣው!" ብላ ቀለደችብኝ ማሚ።
"ማሚዬ አንችም? አንችም እንደነሱ እኔ ላይ ማሾፍ ጀመርሽ?" አልኳት።
"እኔ አላሾፍኩም ሳሊሜ የምሬን ነው። አልተጠቀምከውም እንጅ ፈጣን ጭንቅላት ነው ያለህ።" አለችኝ።
"አይ እንግዲህ ማዕድ ላይ አትሞጋገሱብን!" አለች ሪ።
"አንች ቆይ በኔና በማሚ እንዲህ ሚያስቀናሽ ምንድን ነው? ጡቴን ጠባሽብኝ እንጅ አልጠባሁብሽ?" ስል ነካኋት። ብዙ ጊዜ ታላቅ በታናሹ ሲቀና እንጅ ታናሽ በታላቁ ሲቀና አይቼ ስለማላውቅ ነው እንደዛ ያልኳት። በወሬያችን ዝም ብሎ ሲስቅ የቆየው አባቢ፤
"እናንተ ለማዕድ ክብር ይኑራችሁ እንጅ! ማዕድ እየተበላ አይወራም!" አለን።
በልቼ እንደጠገብኩ በደረቅ እንጀራ ቃሪያ ጠቅልዬ፤
"እስኪ ነይ ላጉርስሽ እኔ እንዳንች ምቀኛ አይደለሁም።" አልኩና ለሪሃና አጎረስኳት። የጎረሰችውን ስታላምጠው ቃሪያው አንገበገባት። ሲጀመርም ቃሪያ አትወድም ነበረና ላብ እስኪያጠምቃት ድረስ ተንገበገበች። እ
ፍራቻ ቢሰግድም፤ ት/ቤት ውስጥ አባቱ የሉምና ሰግዶ አያውቅም።
"በሉ እየተጫወታችሁ ጠብቁኝ መጣሁ።" ብያቸው ትቻቸው ሄድኩኝ። ሃሚ ቅድም ስላሾፈብኝ አብረን እንሂድ ልለው አልደፈርኩም። ለነገሩ እሱ ምን በወጣው አብሮኝ ይሄዳል? እኔም የያዘ ይዞኝ እንጅ እግሬን አላነሳም ነበር
.
.
.
ይቀጥላል...
#ሂክማ
ክፍል አስራ አንድ
..."ቆይ ምን አይነት መስፈርት ነው?"
"ሶላት መስገድ"
"ሶላት መስገድ? ቆይ እርግጠኛ ነሽ ሶላት ብሰግድ ፎቶሽን ትልኪልኛለሽ?"
"አትጠራጠር! በትክክል ሶላት ስገድ እንጅ አይደለም ፎቶዬን እኔን እራሱ በአካል ታገኘኛለህ።" ምን ማለቷ ነው? እኔ ሳሊም እልኸኛ መሆኔን አላወቀችም ማለት ነው። የፈለግኩትን እስካገኝ አይደለም አንድ ሶላትን፤ አንድ ሚሊየን መስፈርቶችን ብትደረድር ከሟሟላት ወደኋላ እንደማልል ብታውቅ እንደዛ አትልም ነበር። ይሄን ሳታውቅ ነው እንዴ ስላንተ አውቃለሁ የምትለው? (ልማድ በተሎ አይለቅም እንደሚባለው ሆኖ እንጅ እንዲህ የሚያሸልል ወኔ እንኳን አልነበረኝም!ሃሃሃ)
"ቃል ግቢልኝና ከነገ ጀምሮ መስገድ እጀምራለሁ።"
"በጣም ጥሩ! በአላህ ስም ቃል ገብቸልሃለው። አንድ ነገር ግን ማወቅ አለብህ እንደ ነገርኩህ ስላንተ ብዙ ነገር አውቃለሁ። ልታታለኝ ብትሞክር ቃሌን እንደማልሞላልህ ልብ በል!"
"ችግር የለውም።"
"እሽ እንደዛ ከሆነ ነገ ሱብሂ ስላለብህ በጊዜ እንድትነሳ አሁን ተኛ!"
"እሽ በቃ ደህና እደሪ!"
"ደህና እደር ወሰላሙ አለይኩም ወረህመቱላህ"
"wa wr wb"
ከፌስቡክ ወጥቼ ስለ ሂክማ ማሰላሰል ጀመርኩ። ከሷ ጋር ማውራት ከጀመርኩባቸው ቀናቶች አንስቶ ማንነቴ ሙሉ ለሙሉ ተለውጧል። ለራሴ ያለኝ ግምትና ቦታ ከሚባለው በላይ ወርዷል። ምንም የማይሳነኝና የፈለግኩትን ነገር ማግኘት እንደምችል አስብ እንዳልነበር፤ የፈለግኩትን ነገር በቀላሉ እንደማላገኝ አረዳችኝ። ከሴቶች ውስጥ ወንድን የሚያንበረክኩ ጠንካራና ብርቱ ሴቶች መኖራቸውን ከሂክማ አንድ ብዬ መቁጥር እንድጀምር ተገደድኩ። ለካስ የኔ ኩራት ከንቱ የገለባ ክምር፣ የእንቧይ ካብ ኖሯል!
አሁን ላይ ልክ እሷ እንዳለችው እሷን ለማግኘት የአቡበክር ኢማን፣ የዑመር ጀግንነትና የሰላሃዲን አል አዩቢ ወኔ መላበስ ሳይጠበቅብኝ አይቀርም። እሱ ደግሞ የማይታሰብ የህልም እንጀራ ነው። ለማንኛው እውነቷን ከሆነ እንደምንም ሶላቱን ጎንብስ ቀና ብዬ ፎቶዋን ላግኝና የሚፈጠረውን አያለሁ። ለነገሩ ፎቶዋን አየሁ አላየሁ የሚፈጥረው ለውጥ አይኖርም። ከመልኳ በፊት ማንነቷና ጀግንነቷ ማርኮኛል። "ወይኔ ሳሊም 'መራጭ ምራጭ ላይ ይወድቃል' የሚባለው ባንተ አውነት ሊሆን ነው ማለት ነው? እውነት አሁን ሂክማ የማታምር ብትሆንም ኩራተኛ ልብህን አሳልፈህ ትሰጣለህ?" ለራሴ የጠየቅኩት ጥያቄ መልሶ እኔን አስገረመኝ። በዚህ ሳምንት ውስጥ በራሴ ላይ ስለተከሰቱት ለውጦች ማሰቤን አቁሜ ተከናንቤ ተኛሁ።
ጠዋት የተነሳሁት እስከዛሬ በምነሳበት ሰዓት ነው። 1፡15 ሆኖ ፀሐይ በጠዋት ውር ውር የሚሉትን ፍጡራን ሁሉ vitamin መመገብ ጀምራለች። ማሚም እንደተለመደው ቁርሳችንን አብስላ በማቀራረብ ላይ ናት። ሪ ዩኒፎርሟን ለባብሳ ከማሚ ጋር ቁርስ በማቀራረብ ላይ ተወጥራለች። ተነስቼ ከክፍሌ ስወጣ ኮሊደራችን ላይ ሪን አገኘኋት።
"አንተ እንቅልፋም እስኪ እንደተማሪዎቹ በጧት መነሳት ልመድ!" አለችኝ።
"እስኪ አንችም እንደ ምላስሽ ትልቅ ሰው ለመሆን ጣሪ! እስኪ አሁን በስተርጅና ወላጆችን በመኝታ ማጣበብ ምን ይባላል?" አልኳት። ተረባየን አልችለው ስትል በያዘችው ጭልፋ ለመምታት ማሯሯጥ ጀመረች።
ውጭ ወጥቼ ፊቴን ለመታጠብ የውዱዕ እቃ ሳነሳ ለሂክማ ቃል የገባሁላት ሶላት ትዝ አለኝ።
"ሰዓቱ ሂዷል። መቼም በዚህ ሰዓት ብሰግድ አላህ አይቀበለኝም። ስለዚህ ሱብሂ ይለፈኝ።" ብዬ ካሰብኩ በኋላ፤
"ሲጀመር መች ለአላህ ሆነና ነው ምትሰግደው! ለሂክማ ብለህ አይደል እንዴ ለመስገድ የወሰንከው? ስለዚህ አላህ ተቀበለህም አልተቀበለህ፤ ቢያንስ ስትጠይቅህ አዎ ለማለት እንዲያመችህ ቶሎ ላጥ ላጥ አድርግ!" የሚል ሌላ ሃሳብ መጣልኝ። በዚህኛው ሃሳብ ተስማምቼም ውዱዕ አድርጌ ወደ ቤት ገባሁ። መስገጃ አነጥፌ ስቆም ቁርስ ለመመገብ የቀረቡት ቤተሰቦቼ በሙሉ ተገርመው አፈጠጡብኝ። ከቁብ ሳልቆጥራቸው ሁለት ረከዓ ሰገድኩና ወደ ማዕዱ ተቀላቀልኩ።
"አንተ ሶላት እንዴት እንደሚሰገት ታውቃለህ እንዴ? ቆይ ሱብሂ ሳይሰግዱ ዷህዋ መስገድ ምን ይባላል?" ስትል ወረፈችኝ ሪ።
"ተይ እንደሱ አይባልም አላህ ያዝልቅልህ ነው የሚባለው።" አላት አባቢ።
"ኡኡቴ! ልናይ አይደል¡" ስትል አሁንም አፌዘችብኝ።
"ቆይ አንች ምናለበት ደግ ደጉን ብትመኝለት?" አለቻት ማሚ። እድሜ ለማሚና አባቢ አፍ አፏን ባይሉልኝ ኖሮ አትተወኝም ነበር። እኔ ምንም የምመልሰው ምላሽ ስለሌለኝ ዝምታን መርጫለሁ። በሷ ቤት እኮ የቅድሙን ተረባ መመለሷ ነው። ቆይ አገኛት የለ!
እነ ዮኒን ት/ቤት ውስጥ አገኘኋቸው። ሰላምታ ከተለዋወጥን በኋላ የማይቀርልኝን ጥያቄ ጠየቁኝ። የሆነውን ሁሉ ስነግራቸው ማመን አልቻሉም። በተለይማ የሶላቱን ጉዳይ ሳነሳላቸው ሆዳቸው እስኪቆስል ድረስ ሳቁብኝ። እኔም አብሬያቸው የሃፍረትና የሽንፈት ሳቅ ሳቅኩኝ።
"ሃሃሃ ሃሚ ባለፈው 'ሸኪ መሆን ሳይኖርብህ አይቀርም!' ያልከው እውነት ሊሆን ነው መሰለኝ!" አለ ዮኒ።
"እና አታየውም እንዴ ነገ ከነገወዲያ እኮ አባቢን ሳያስንቅ አይቀርም! ሃሃሃሃ ዮኒ አስበኸዋል ከቤት ያባቢ ስብከት አዝጎኝ ሳሊሜጋ ስመጣ እሱም አባቢ ካቆመበት ሰበካውን ሲቀጥልልኝ? ሃሃሃ" ሃሚም በተራው አሾፈብኝ። በሰዓቱ አልተናደድኩባቸውም ምክንያቱም እኔም የያዘኝ ይዞኝ እንጅ የኔ እጣ ፈንታ በሌላ ላይ ደርሶ ባይ ከነሱ የባሰ ነው የማላግጥበት።
አንዳንዴ ማንኛውም ነገር ግልፅ የሚሆንልን በራሳችን ላይ ደርሶ ስናየው ብቻ ነው። በሌላ ሰው ጫማ ውስጥ ሁነን ስቃዩን ካላስተወልነው በቀር ስቃዩ ሊሰቀን አይችልም። ዛሬ እነ ዮኒ ሲያሾፉብኝ ከዚህ በፊት ሀምዱ ላይ አብሬያቸው ያሾፍኩበት ታወሰኝ። እንደነገርኳችሁ ሀምዱ እጅግ በጣም ዲነኛ ልጅ ነው። አይደለም ዝምድና ያለው ሰው ሆኖ ይቅርና ዝምድና ባይኖረው እንኳን ሰው ከጥፋቱ እንዲመለስ ከመምከር ወደኋላ የማይል ቅን ልጅ ነው።
ታዲያ እኔን እና ሃሚን ለማስተካከል በማሰብ አራተኛችን ሆኖ ተጎዳኘን። መሃላችን ሆኖ ስናማ አላሳማ፣ ስንላክፍ አላስለክፍ፣ ሴቶች ሲቀርቡን አላስጠብስ ብሎ እንቅፋት ሆነብን። ይሄ አካሄዱ ስላልተመቸን እንዲርቀን ብዙ ግፎችን ፈፀምንበት። ሲቀላቀለን በሱ ላይ በህብረት ማሾፍ፣ ሆነ ብለን ሴት በማናገር እንድትፈታተነው በማድረግ፤ ለመቅረብ የማንመች አራስ ነብር ሆንበት። ብዙ ጥሮ ሲያቅተው እርግፍ አድርጎ ተወን። እናም ዛሬ ላይ ሁኜ የሱን ህመም ሳስበው ብዙ እንደቻለን ታወቀኝ። ምስኪን ሀምዱዬ!
ብዙ ሲያላግጡብኝ ቆይተው ወደ ክላስ መግቢያ ሰዓት ደርሶ ተለያየን። ለምሳ ስንወጣ ተገናኝተን በአንድ ላይ ምሳችንን በላን። ልክ እንደጨረስን ከት/ቤታችን አቅራቢያ የሚገኘው መስጊድ ዙሁር መድረሱን በአዛን አበሰረ። (ለኔ እንኳን አረዳ ቢባል ይቀላል!) ለካ እኛ ሰዎች ለመስማት ራሳችንን ዝግጁ ካላደረግን በቀር በጆሮ የሚነገረንን ሹክሹክታ እንኳን መስማት አንችልም። ከአራተኛ ክፍል ጀምሬ እዚህ ት/ቤት ስማር ልብ ብየው የማላውቀው አዛን ዛሬ ለመስማት ዝግጁ ስሆን ተሰማኝ። ሀሚ በኔ ምክንያት የገባበት የእንቅልፍ አለም ውስጥ ስለነበር ዛሬም እኔ የነበርኩበት ዝንጋታ ውስጥ ነው። ሃሚ ቤት አባቱ ፊት ሲሆን ቁጣቸውን
ልሁን?" ለነገሩ የጄን ነው ያገኘሁት። እኔኮ የሚገርመኝ እንደዚህ እየተናገረችኝ ልጠላት ሲገባ እየወደድኳትና እያከበርኳት መምጣቴ ነው። ለካስ ሴቶች
"ወንዶች ስትባሉ ሲንቋችሁ እንጅ ሲወዷችሁ አይወድላችሁም!" የሚሉት እውነታቸውን ኖሯል። ግን ለምናባቷ ነው የኔ ፎቶ አይገባህም ያለችኝ? መጠየቅ ስላለብኝ ጠየቅኳት።
"ቆይ ምን ለማለት ነው? አንች ማነሽና ነው ፎቶሽ ለኔ የማይገባው?"
"ምክንያቱም ሂክማ ስለሆንኩ ነዋ!"
"እኮ ሂክማ ማን ናት?"
"ሂክማ ማለት የራሷ የሆነ ፎቶ የሌላት ናት። ለነገሩ ፎቶ እንኳን ቢኖረኝ እንዳንተ ላለው ሶላት ለማይሰግድ ሰው አልክም።"
እችን ይወዳል! ኧረ እች ሰው ማናት? ጭራሽ ሶላት አትሰግድም አለችኝ እኮ! እውነትም ስለኔ ብዙ ሚስጥር ሳታውቅ አትቀርም። እንደምንምማ ማንነቷን ማጣራት አልያም ፎቶዋን ማየት አለብኝ!
"ደግሞ እንደማልሰግድ እንዴት አወቅሽ?"
"ከዚህ የበለጠ ስለማውቅ አይግረምህ።"
"እሽ ልለምንሽ አይቼ እሰርዘዋለሁ አንድ እንኳን ፎቶ ላኪልኝ!"
"እሱን እንኳን ይሆናል ብለህ አታስበው። ቢሆን እንኳን አንድ መስፈርት ምታሟላ ከሆነ ብቻ ነው የምልክልህ።"
"ቆይ ምን አይነት መስፈርት ነው?"
.
.
ይቀጥላል
#ሂክማ
ክፍል አስር
ከህሊናዬ ጋር የገጠምኩትን ሙግት አቁሜ ለሂክማ ኢስላማዊ ሰላምታ ላኩላት።
"ወአለይኩሙሰላም ወረህመቱላሂ ወበረካቱህ! ዛሬ ጎብዘሀል¡" አለችኝ። ኢስላማዊ ሰላምታ ስላቀረብኩላት መሆኑ ነው።
"ጎበዝ ተማሪ ነኝ አላልኩሽም?"
"ጎበዝ ጉረኛም ጭምር ነህ።"
"እሱንም ካንች ተምሬው ነዋ!"
"ተው እንጅ! ለማንኛውም ደህና ነሃ?"
"ደህና ነኝ አንችስ?"
"አልሀምዱ ሊላህ ደህና ነኝ። ለወደፊቱ አልሃምዱ ሊላህ ማለትን አትርሳ!"
"እሽ ኡስታዜ¡ እኔ ምልሽ?"
"እኔ ምሰማህ?"
"ዛሬ አንድ ጨዋታ ባጫውትሽ ምን ይመስልሻል?"
"ምን አይነት ጨዋታ ነው?"
"በግጥም የማውራት።"
"ግጥም ትችያለሽ ወይ? ብሎ መጠየቁ አይቀድምም?"
"ሁሉን አውቃለሁ ባይ ነሽ ብዬ ነዋ!"
"ዛሬ እኔን ለመሳደብ ስትሸርብ ነው እንዴ የዋልከው? ለማንኛውም እሽ ልሞክር።"
"በአንች ጨዋታ ህግ መሰረት ጀማሪው እኔ መሆን አለብኝ አይደል?"
"አዎ ጨዋታውን አንተ አይደል ያመጣሃው? ቅድሚያ ለባለቤቱ ነው። ጀምር!"
"እሽ!
.
.
ያኔ መጀመሪያ የተገናኘን ለት
የውስጥ ውበት ነው ውበት ብሎ ማለት
ያልሽኝን ንግግር ላንዱ ጓደኛዬ አንስቼ ብነግረው
ከትከት ብሎ ሳቀ እጅጉን ቢደንቀው
'ስማ' ብሎም አለኝ 'ስማ የኔ ወንድም
በንዲህ አይነቱ ሰበብ ፈፅሞ አላምንም
ሲያዩት ያላማረ ሲበሉት አይጥምም
በእንዲህ አይነት ሰበብ ራሱን ሚሸውድ
ወይ መልከ ጥፉ ነው ለአይን ማይወደድ
አልያም ጉረኛ ነው የበላይነትን አብዝቶ የሚወድ።'
ብሎ መልስ ሰጥቶ ከልብ አስደነቀኝ
እንችስ ምን ትያለሽ እስኪ መልሽልኝ?"
.
.
ይሄንን ፅፌላት ቶሎ ልትመልስልኝ እንደማትችል እርግጠኛ ስለነበርኩ ተጨናንቃ እስክትገጥም ድረስ ሽንቴን ለመሽናት ስልኬን አስቀምጬ ወጣሁ።
ከክፍሌ ስወጣ የሪሃና ክፍል በሩ ክፍት ሆኖና መብራቱ በርቶ ተመለከትኩ። ሪ እስከዚህ ሰዓት እንደማታመሽ ስለማውቅ በሩን ክፍት ትታ ተኝታ ይሆናል ብዬ ወደ ክፍሏ ስገባ፤ ሪሃና ክፍሏ ውስጥ የለችም። በጣም ደነገጥኩ። በዚህ ለሊት የት ሂዳ ነው? ብዬም አሰብኩ። ወደ ውጭ የሚያስወጣውን የቤታችንን በር ሳይ በውስጥ በኩል እንደተዘጋ ነው። ማሚና አባቢ ተኝተዋል። ልቀሰቅሳቸው ባልፈልግም የግድ ቀስቅሼ መጠየቅ ስላለብኝ በሩን አንኳኳሁ። ከውስጥ በኩልም አባቢ፦
"ማን ነው?" አለኝ።
"አባቢ እኔ ነኝ ሪሃናን መኝታ ክፍሏ ውስጥ አጣኋት" ስል ነገርኩት።
"ሳሊሜ አትጨነቅ ፈርቻለሁ ብላ እኛጋ ተኝታለች።" አለችኝ ማሚ። ማሚ ይህን ስትል የሪሃና ቀጭን ሳቅ ከታፈነበት መዳፏ አፈትልኮ ተሰማኝ።
"አንች ቦቅቧቃ! በስተርጅናሽም ትፈሪያለሽ? ይሄኔ እኮ ጡትም እየጠባሽ ይሆናል!" አልኳት። ማሚና አባቢ ከልባቸው ሳቁ።
"ቀንተህ ከሆነ አልጋው ይበቃናል ና ተኛ!" አለችኝ ሪ እሷም እየሳቀች።
"ኧረባክሽ! ወንድ የወንድ ልጅ መሆኔን በደንብ ታውቂያለሽ!"
"በቃችሁ በቃ! እንተኛበት አትረብሹን።" አለ አባቢ። የሪሃና እና የወላጆቼ እስከዚህ ሰዓት አለመተኛት ግራ እንደገባኝ ትቻቸው ሽንቴን ለመሽናት ወጣሁ።
ሸንቼ ስመለስ ስልኬ ያልጠበቅኩትን ነገር አዘጋጅታ ጠበቀችኝ። ሂክማ የአፀፋ ምላሽ በግጥም መልኩ መልሳልኝ አገኘሁ። ከመግጠሟ በላይ ያስደነቀኝ ምላሹን የላከችልኝ እኔ ከላኩ ከአንድ ደቂቃ በኋላ መሆኑ ነው። የፈራሁት አልቀረም። ልጅቷ እልም ያለች ገጣሚ ናት። የላከችልኝ ግጥም እንዲህ የሚል ነበር፦
.
.
"እንዲህ ብሎ ላለህ ይሄን ንገርልኝ፦
እንቧይ ምንም ቢያምር ሲቀምሱት መራር ነው
ጊሽጣም ምን ቢያስጠላ ሲበሉት ጣፋጭ ነው
የመልክ ጉዳይ ቢሆን እንቧይ በጣፈጠ
ጊሽጣም መራራ እንጅ ማራኪ ባልሆነ
አየህ የኔ ወንድም ጥሩ ፀባይ ካለህ
ጎረቤት ጓደኛ ዘመድም ሊያደርጉህ
ሰዎቹ እርስ በርስ ሲሻሙህ ታያለህ።
የውበት ጥግ ሆነህ ፀባይ ግን ከሌለህ
እንኳንስ ሊቀርቡህ ዞረውም አያዩህ!"
ግጥሙም ይዘቱም በጣም የሚደንቅ ሆኖ ነው ያገኘሁት። ግጥሙ የሆነ ነገሩ ከማሚ የግጥም ዘይቤ ጋር የሚመሳሰል መስሎ ተሰማኝ። እንግዲህ በግጥም በኩልም የማሸነፉን እድል ማግኘት አልቻልኩም። የሰጠችኝም ምላሽ የማያፈናፍን እንደመሆኑ በክርክሩ መግፋት አልፈለኩም። ስለሆነም ለተወሰነ ጊዜ በግጥም አዋርቼ ወደሌላ ርዕስ ለመዞር በማሰብ እንዲህ ብዬ መለስኩላት፦
"ያልሽኝን በሙሉ ለሱ እነግረዋለው
ምላሽም ከሰጠ ወዳንች አደርሳለው
ግና ያንች ጉዳይ ግራ ነው ያጋባኝ
እስኪ ከራስሽ ጋር ጥቂት አስተዋውቂኝ!"
"ስለኔ ማወቁ ምን ይፈይድሃል?
ለትውውቅ ያህል ስሜ ይበቃሃል።"
"መልክ የውስጥን ውበት አይገልፅም የምትል
ስሜ ማንነቴን ለማወቅ ይበቃል
ስትል ሰው ቢሰማ ምን ሊያስብ ይችላል?"
"ስም ባህሪን አይገልጽም አዎ ትክክል ነህ
ስለ አንድ ሰው ግን በንግግሩና በቆይታ ብዛት ልታውቅ ትችላለህ"
"እስኪ እስካሁን ባለው ስለኔ ምን አወቅሽ
ምን አይነት ነው ብለሽ ትገምችኛለሽ?"
"ውበቱን የሚያመልክ የወንድ እልኸኛ
ሽንፈቱን የማያምን እጅግ ኩራተኛ"
ልክ ልኬን ስትነግረኝ በንዴት ቦግ አልኩ። መልሶ ደግሞ ንዴቴ አስገረመኝ። "እውነትም ሽንፈትን የማልወድ እልኸኛ ነኝ። የተናገረችው በሙሉ ፈፅሞ እውነት ነው። ታዲ ምን ያናደኛል? " አልኩኝ ለራሴ። አሁን በንዴቴ ምትክ ለሷ ያለኝ አግራሞት ውስጤን ሞላው። እንዲህም ስል ጠየቅኳት፦
"ቆይ አንች ግን ምን አይነት ሰው ነሽ? ሳይኮሎጂስት ነሽ እንዴ?"
"አንተ ይሄ ነው ሚገርምህ? ከዚህ በላይ ስላንተ የማውቀውን ብነግርህ ምን ልትል ነው?"
"ስለኔ ደግሞ ምንድን ነው ምታውቂው?" ስል ጠየቅኳት። አሁን አሁን ከማውቃቸው ሰዎች ውስጥ አንዷ ልትሆን እንደምትችል መጠርጠር ጀምሬያለሁ። ግን ደግሞ እስከዚህ ደረጃ ገራሚ የሆነች ሴት ፈፅሞ አላውቅም። እና እንዴት ስለኔ ልታውቅ ትችላለች?
"የቤተሰብህ የመጀመሪያ ልጅ ነህ። አንድ እህት እና ሁለት ወላጆች አሉህ..." አለችኝ፡፡ አሁን በቅርበት ከሚያውቁኝ ሰዎች ውስጥ አንዷ ልትሆን እንደምትችል እርግጠኛ ሆንኩ።
"ግን ማን ልትሆን ትችላለች?" ራሴን በጥያቄ አጣደፍኩት። የሚያውቁኝን ሰዎች በሙሉ በህሊናዬ አሰልፌ በሂክማ መለኪያ እለካቸው ጀመርኩ። ሁሉም ግን ፈፅሞ መስፈርቱን ሊያሟሉ አልቻሉም። አንዳንዶቹ ግማሽ ላይ ደርሰው ይወድቃሉ። አንዳንዶቹ ደግሞ በአንድ እና በሁለት መስፈርቶች ከተጠርጣሪነት ነፃ ይወጣሉ። ከሁሉም ተጠርጣሪዎች ውስጥ ከፍተኛ ውጤት ያስመዘገበው ሀምዱ ነው። በነገራችን ላይ ወንድ ሁኖ በሴት ማሊያ እየተጫወተብኝ ይሆናል ብዬ ስለጠረጠርኩኝ ከተጠርጣሪዎች ውስጥ ወንዶችንም አካትቻለሁ።
ሀምዱ ማለት ከእኔ ጋር የርቀት ዝምድና ያለው የትምህርት ቤት ጓደኛዬ ነው። ብዙ ጊዜ ሊቀርበኝ ሞክሮ በስነ ምግባሬ ምክንያት የተወኝ ጓደኛዬም ዘመዴም ነው። በዲኑ ጠንካራ ነው፣ በእውቀትም ቢሆን አይታማም። ግጥም መቻሉን እርግጠኛ ባልሆንም ስነ ፅሁፍ ነገር እንደሚሞክር አውቃለሁ። አብዛህኛውን መስፈርት ቢያሟላም፤ የሴት ለዛ ያለው ንግግር መናገር ይችላል ብሎ ለመደምደም ግን ቸገረኝ። ለማንኛውም ማንነቱን ወይም ማንነቷን እንደምንም ማረጋገጥ መቻል አለብኝ። ይሄን በማስብበት ሰዓት እንዲህ ብላ ላከችልኝ፦
"እርግጠኛ ነኝ ይሄኔ ማን እንደሆንኩ ለማወቅ እየደከምክ ነው። ወንድሜ አትድከም እኔ ሂክማ እንጅ ከምትጠራጠራቸው አንዷ አይደለሁም።"
"ይሄን ያህል በራስሽ እርግጠኛ ከሆንሽ ፎቶሽን ላኪልኛ!"
"ፎቶዬ የሚገባህ ሰው አይደለህማ!" አለችኝ። በዚህ ንግግሯ በጣም ተበሳጨሁ። "ወይኔ ሳሊም! በስንቱ ሴት ላይ እንዳልተጫወትኩ ዛሬ መጫወ
#ሂክማ
ክፍል ዘጠኝ
.
.
ዛሬ የሳምንቱ የመጀመሪያ ቀን ነው። ቁርሴን በልቼ በጣም የምወዳቸውን ጓደኞቼን ወደማገኝበት ት/ቤታችን በጧቱ አቀናሁ። ዮኒና ሃሚ በጣም ናፍቀውኛል። ለአንድ ቀን ሳይሆን ለአንድ አመት ያህል እንዳልተገናኘን ነው እየተሰማኝ ያለው። ሲበዛ ንፍቅ ብለውኛል። እነሱንም እንደናፈቅኳቸው ያወቅኩት ቀድመውኝ ት/ቤት ሳገኛቸው ነው።
"ሳሊሜ...!" እያሉ ተሽቀዳድመው አቀፉኝ። እኔም ወደ ደረቴ ጭምቅ አድርጌ እያቀፍኩ ናፍቆቴን ተወጣሁ።
"በቃ እሁድ አፍንጫ ሆነችብና?" አለ ዮኒ። ዮኒ እሁድን አፍንጫ እያለ ነው የሚጠራት። አፍንጫ ሁለት አይኖች እንዳይተያዩ መሃል ላይ እንደተደነቀረው ሁሉ፤ እሁድም በእኛ መሃል ተደንቅሮ ስለሚገኝ።
"ቀላል አፍንጫ ሆነች ምናለ ህይዎትን እንደ ቪዲዮ በሪሞት ማሳለፍ ቢቻልና እሁድን next ብዬ ባሳለፍኳት።" ስል ሃሳቤን ሰነዘርኩ።
"ይቅርታ አድርጉልኝና ለኔ ግን እንደ እሁድ ባለውለታዬ የሆነ የለም።" አለ ሃሚ።
"እንዴት?" ስንል ጠየቅነው።
"ምክንያቱም እሁድ ባይኖር ኖሮ ምን ያህል እንደምንዋደድ፣ ምን ያህል አንዳችን ለአንዳችን እንደምናስፈልግ ባላወቅን፣ አንደዚሁም ባልተነፋፈቅን ነበር። አባቴ ብዙ ጊዜ ሲል የምሰማው አባባል እወነት መሆኑን የተረዳሁት በእሁድ ነው። አባቴ እዲህ ይላል፦
'ፀጋ የሚታወቀው ከእጅ ሲወጣ ነው።'" የሃሚ ሃሳብ ሁላችንንም ገዛን። ብዙ ጊዜ የሚያነሳቸው ሃሳቦች አሳማኝ ናቸው። ልጁ ከኛ ጋር መሆን አይመጥነውም አላልኳችሁም?
"ስማ እንጅ የሂክማን ነገር ምን ላይ አደረስከው?" ሲል ዮኒ ጠየቀኝ።
"እኔ እንጃ ግራ ገብቶኛል።" አልኩት።
"ትከብድሃለች አላልኩህም ነበር?" አለ ሃሚ።
"እስኪ የሁለት ቀን ሪፖርትህን አቅርብልን።" ዮኒ ነበር የጠየቀኝ።
"ትላንት ደክሞኝ ስለነበር አልተገናኘንም።"
"እሽ የቅዳሜ ምሽትን ንገረን።" አለ ሃሚ። የሆነውን ሁሉ አጠር አድርጌ ነገርኳቸው።
"ውውው ሳሊሜ ሸኪ መሆን ሳይኖርብህ አይቀርም።" አለ ሃሚ።
"እኔ ግን አንድ መንገድ ይታየኛል።" ዮኒ።
"ምን አይነት መንገድ?" ስል ጠየቅኩት ለመስማት ቸኩዬ። ሂክማን ለብቻዬ ማንበርከክ እንደማልችል አውቃለሁ። ስለሆነም የጓደኞቼ እገዛ ያስፈልገኛል።
"አየህ እስካሁን በሷ ሜዳ ላይ ነው ስትጫዎት የነበርከው። ለምን በራስህ ሜዳ ላይ አታጫውታትም?" መፍትሄ ብሎ ያሰበውን ሃሳብ ሰነዘረ።
"አንተ ደግሞ እንዴት ነው ምታስበው? ዘፈን እንዝፈን ይበላት ወይስ የፍቅር ታሪክ እናውራ? መቼም ሳሊም ከዚህ ውጭ ሌላ የሚችለው ነገር የለ!" አለው ሃሚ።
"እስኪ ምናለ እስክጨርስ ብትታገሰኝ?"
"እሽ እስኪ እንስማህ ጨርስ።"
"ሳሊሜ ምን መሰለህ እስካሁን እሷ በፈለገችው መንገድ እየመራችህ አልሸነፍ ብላሃለች። አሁን ግን አንተ በፈለግከው መንገድ እንድትጓዝ አድርጋትና እጅ አስሰጣት።"
"ዩኒዬ አልገባኝም ምን አድርጊ በላት ነው የምትለኝ?" ስል ግራ ገብቶኝ ጠየቅኩት።
"ከናትህ በወረስከው የግጥም ተሰጥኦህ አንበርክካት። በግጥም እናውራ በላት። እርግጠኛ ነኝ ትረታልሃለች።"
"እኔ ምለው? ምላስ ሲረዝም ጭንቅላት ባዶ ይሆናል ሚባለው ነገር ቀረ እንዴ? አሁን ይሄ ሃሳብ ዮኒ ነው ያፈለቀው ቢባል ማን ያምናል?" አለ ሃሚ።
"እኔ ደግሞ አንድ የሀገራችን አባባል እውነት መሆኑን ባንተ ማረጋገጥ ችያለሁ። 'አንገት ደፊ አገር አጥፊ' የሚባለውን። አሁን እስኪ እንዲህ ምላሰኛ መሆንህን ለሰው ብንናገር ማን ሊያምነን ይችላል?" ሲል የመልስ ምት ሰነዘረ። ጭቅጭቅ ከጀመሩ ስለማያቆሙ ጣልቃ ገብቼ አስቆምኳቸው። ወሬ ለማስቀየርም፤
"ዮኒዬ አዲሷ ፍቅረኛህ እንዴት ናት?" ስል ጠየቅኩት።
"በጣም ተመቻችተናል። ግን ቀጣይ ቅዳሜ ልደቷ ስለሆነ ምን እንደማደርግ አላውቅም።" አለ ትክዝ ብሎ።
"ምኑ ነው ያሳሰበህ ንገረንና መፍትሄ እንፈልግለት።" አለው ሃሚ። ሃሚ ሲከፋን አይወድም። ቅድም ሲጨቃጨቀው ስለነበረው ጓደኛው አሁን አንጀቱ ተንሰፈሰፈለት።
"ያው የልደትን ጣጣ ታውቁት የለ። ስጦታ ምናምን ግድ ይላል። በተለይ ደግሞ ፍቅረኛ ከሆንክ ትንሽ ከበድ ያለ ስጦታ መጠበቁ አይቀርም።"
"ገባን ገባን በቃ አታስብ ገና ስድስት ቀናት አለን እስከዛው ገንዘቡን አፈላልገን ማግኘት አያቅተንም።" ስል አፅናናሁት። በዚህ መሃል አንዲት ቀጭን ችክ በአጠገባችን እየተውረገረገች አለፈች። በዚህን ጊዜ ምላሱ የማያርፈው ዮኒ፤
"እእ ችኳ ንፋሱ እንዳይወስድሽ ከጎንሽ ልሁና!" ሲል ለከፋት። ልጅቷ ከሱ የባሰች ምላሰኛ ነበረችና ሦስታችንንም አይናችን እስኪያነባ ድረስ ያሳቀንን ምላሽ ሰጥታ ሳሚን አፉን አዘጋችው።
"መቼም ቀድሜ በንፋስ በመወሰድ መስዋት ልሁንልሽ እያልከኝ መሆን አለበት?" ነበር ያለችው። ማለት የፈለገችው አንተ ከኔ የባስክ ቀጫጫ ነህ ነው። እውነቷን ነበር ዮኒ ሲበዛ ቀጭን እና ረጅም ልጅ ነው። ዮኒ በልጅቷ ምላሽ ተገርሞ አብሮን ሳቀ። ልጅቷም በመጀመሪያው አረማመዷ እየተውረገረገች መንገዷን ቀጠለች። ብዙም ሳንቆይ ወደ ክፍል መግቢያ ሰዓት ደረሰና ተለያየን።
የሰኞን የትምህርት ውሎ ጨርሰን ወደየ ቤታችን ስንለያይ ዮኒና ሃሚ፦
"ነገ ጥሩ ዜና ይዘህልን እንደምትመጣ ተስፋ አለን!" አሉኝ።
"እናያለን።" ስል መለስኩላቸው እርግጠኛ ባልሆነ መንፈስ ውስጥ እንደሆንኩ። ምን ይታወቃል ከኔ የባሰች ገጣሚ ሆና ድጋሚ ድል ትነሳኝ ይሆናል። ግን ምን አይነቷ ልጅ ናት የገጠመችኝ?
እንደነገርኳችሁ ከእሁድ እስከ አርብ ድረስ ያሉት ምሽቶች በጊዜ እራት በልተን ለጥናት ወደ መኝታ ክፍላችን የምንገባባቸው ምሽቶች እንደመሆናቸው፤ የተጀመረልንን የወላጆቻችን የፍቅር ታሪክ የመቀጠል እድል አይኖረንም። ታሪካቸውን ለመጨረስ የግድ አርብ ምሽትን በጉጉት መጠበቅ ይጠበቅብናል። እኛም ይሄንን ስለምናውቅ አልተጨቃጨቅናቸውም። እኔና ሪ ማሚና አባቢን ሳሎን ቤት ትተናቸው ወደዬ ክፍላችን ገባን።
የዛሬውን ጥናቴን በግማሽ ልብ ነበር የጨረስኩት። አስሬ 5 ሰዓት መሙላት አለመሙላቱን ስልኬን እያበራሁ በማየት ሳጠና ቆየሁና፤ ሰዓቱ ሲደርስ ደብተርና መፀሐፍቶቼን ከድኜ ወደ ፌስቡክ መንደር ጎራ አልኩ።
ሂክማ ኦን ላይን ናት። ለምን እንደሆነ ባላውቅም ልቤ ከቁጥጥር ውጭ ሆኖ መምታት ጀመረ። መላ አካላቴንም አንዳች የኤሌክትሪክ ሀይል የመሰለ ንዝረት ተሰማኝ። እንደወደዱኝ የነገሩኝ ሴቶች ሲያዩኝ ይህ አይነት ስሜት እንደሚሰማቸው ይነግሩኝ ነበር። "ምናልባትም እኔም እንደዛ ሆኜ ይሆን? አይ! አይ! አይሆንም! አዎ በፍጹም ሳሊም ፍቅር ሊይዘው አይችልም። ለዛውም መልኳ ምን እንደሚመስል ለማያውቃት፣ ወንድ ትሁን ሴት፤ ወጣት ትሁን አሮጊት ምንም መረጃ ሳይኖረኝማ ፍቅር ሊይዘኝ አይችልም! ለዛውም ለሴት ልጅ! እንዴት ሆኖ?" ከህሊናዬ ጋር የገጠምኩትን ሙጉት አቁሜ ለሂክማ ኢስላማዊ ሰላምታ ላኩላት።
.
.
.
ክፍል 10 ይቀጥላል!
ቤት ገብተን እራት በላንና ለጥናት ወደየ ክፍላችን አመራን። የቀኑ ስራ አድክሞኝ ስለነበር ለጥናት ደብተሬን እንደከፈትኩ ብርድ ልብስ እንኳን ሳልለብስ እንቅልፍ ይዞኝ ሄደ።
ጠዋት ከእንቅልፌ የነቃሁት በሪሃና ቀጭን የሳቅ ድምፅ ነበር።
"እሽ የኛ ጀግና አንተ እኮ አታፍርም እንዲህ ተዘርረህም አሸነፍኩኝ ብለህ ትሸልል ይሆናል።" አለችኝ የመኝታ ክፍሌን በር በእጇ ይዛ።
"ሂጂ ወደዛ መዥገር!" ብዬ ትራሴን ወረወርኩባትና አባረርኳት። በጊዜ ስለተኛሁ ነው መሰል ነቃ ብዬ ነው የተነሳሁት። ማታ ከሂክማ ጋር ባለማውራቴ ቅር አለኝ። እየለመድኳት ሳልመጣ አልቀርም። ስጠፋ መልዕክት ትታልኝ ከሆነ ብዬ ፌስቡክ ስከፍት ብዙ መልዕክቶች የተላኩልኝ ቢሆንም፤ ከሷ በኩል ግን ምንም አይነት መልዕክት አልደረሰኝም። ለመጨረሻ ጊዜ የወጣችበትን ሰዓት ሳይ 5:15 ይላል። "እስከ ዛሬ ምታመሸው ለኔ ብላ ነበር ማለት ነው?" ስል አሰብኩ። ማረጋገጫ ባይኖረኝም 'ይሆናል!' የሚለው ተስፋ ብቻ ማለዳዬን ትንሽ ደመቅ አደረገልኝ።
.
.
.
ይቀጥላል....
