Musalla App
前往频道在 Telegram
All things about the Musalla App https://onelink.to/quvuv3 Direct contact @ContactMusalla ይህ ቻናል ሙሰላ አፕን የሚመለከቱ መረጃዎች የሚተላለፉበት ነው። መተግበሪያውን ለማግኘት https://onelink.to/quvuv3 በቀጥታ እኛን ለማግኘት @ContactMusalla
显示更多未指定国家未指定类别
📈 Telegram 频道 Musalla App 的分析概览
频道 Musalla App (@musalla_app) 是活跃参与者。目前社区聚集了 11 280 名订阅者,在 其他 类别中位列第 。
📊 受众指标与增长动态
自 невідомо 创建以来,项目保持高速增长,吸引了 11 280 名订阅者。
根据 08 七月, 2026 的最新数据,频道保持稳定运转。过去 30 天订阅人数变化为 370,过去 24 小时变化为 1,整体触达仍然可观。
- 认证状态: 未认证
- 互动率 (ER): 平均受众互动率为 65.89%。内容发布后 24 小时内通常能获得 N/A% 的反应,占订阅者总量。
- 帖子覆盖: 每篇帖子平均可获得 0 次浏览,首日通常累积 0 次浏览。
- 互动与反馈: 受众积极参与,单帖平均反应数为 0。
📝 描述与内容策略
作者将该频道定位为表达主观观点的平台:
“All things about the Musalla App https://onelink.to/quvuv3
Direct contact @ContactMusalla
ይህ ቻናል ሙሰላ አፕን የሚመለከቱ መረጃዎች የሚተላለፉበት ነው። መተግበሪያውን ለማግኘት https://onelink.to/quvuv3
በቀጥታ እኛን ለማግኘት @ContactMusalla”
凭借高频更新(最新数据采集于 09 七月, 2026),频道始终保持新鲜度与高覆盖。分析显示受众积极互动,使其成为 其他 类别中的关键影响点。
11 280
订阅者
+124 小时
+777 天
+37030 天
帖子存档
11 280
አላሁ አክበር! አላሁ አክበር! ላ ኢላሃ ኢለላህ አላሁ አክበር! አላሁ አክበር....
"ተቀበለላሁ ሚና ወሚንኩም ሷሊሐል አዕማል!"
(አላህ ከእኛም ከእናንተም መልካም ሥራዎችን ይቀበል!)
በድጋሚ እንኳን ለ1447ኛው የዒድ አል-አድሃ በዓል በሰላም፣ በጤና እና በፍቅር አደረሳችሁ።
በዓሉን ከቤተሰብዎ እና ከወዳጅ ዘመድዎ ጋር በደስታ ያሳልፉ! ዒድ ሙባረክ! 🎁🐏
11 280
🎉 ዒድ ሙባረክ! | ተቀበለላሁ ሚና ወሚንኩም! 🌙🐑
الله أكــبر، الله أكــبر، الله أكــبر،
لا إلــه إلا الـلــــه،
والـلــه أكــبر، الـلــه أكــبر، ولـلــه الحمــد.
እንኳን ለ1447ኛው የዒድ አል-አድሃ (የአረፋ) በዓል በሰላም አደረሳችሁ! አላህ (ሱ.ወ) የሑጃጆችን ሐጅ፣ ጾመኛውን፣ ኡድሂያ አራጁንና መልካም የሰራውን ሁሉ ስራውን ይቀበለው!
ይህ የዒድ በዓል፡-
✨ የነብዩላህ ኢብራሂምን (ዐ.ሰ) ታዛዥነት የምንማርበት፤
✨ በኡድሂያ (እርድ) ድሆችን የምናስደስትበት፣እና
✨ የቤተሰብ ዝምድናን የምናጠናክርበት በዓል ነው።
ሙሰላ ቲም ለመላው ሙስሊም ማህበረሰብ የተባረከ፣ የደስታ እና የሰላም በዓል እንዲሆን ይመኛል! ዒድ ሙባረክ! 🎈
11 280
🌟የአመቱ ታላቁ ቀን ነገ ነው!
አልሀምዱሊላህ! አላህ (ሱ.ወ) በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎችን ከእሳት ነጻ የሚያወጣበት ታላቁ የዐረፋ ቀን ነገ (ማክሰኞ) ነው! ለዚህ ድንቅ ቀን ከወዲሁ እንዘጋጅ፡-
1. የጾም ቱሩፋት (በረካ)፡ነገን ለመጾም ከወዲሁ ኒያ እናደርግ የዐረፋን ቀን የጾመ ሰው አላህ የሁለት ዓመት (ያለፈውን እና የሚመጣውን) ወንጀል ይምርለታል! ሱብሀነላህ!
2. በላጩ ዱዓ፡
ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) "ከዱዓዎች ሁሉ በላጩ የዐረፋ ቀን ዱዓ ነው፤እኔ እና ከኔ በፊት ያሉት ነብያቶች ካሉት ሁሉ በላጩ ደግሞ ፤ ላኢላሃ ኢልለሏሁ ወሕደሁ ላሸሪከ ለሁ ፤ ለሁልሙልኩ ወለሁል ሓምዱ ወሑው ዓላ ኩሊ ሸይኢን ቀዲር" የሚለው ነው። ብለዋል።
ነገ አላህን ማንኛውንም ነገር ከመጠየቅ ወደኋላ እንዳንል! ለዱንያችንም፣ ለአኼራችንም፣ ለጤናችን ፣ ለትዳራችን፣ ለቤተሰባችን ... ከልብ አልቅሰን እንለምነው ። ማንም የማያውቀውን የልባችንን ስብራት እንንገረው። ለአላህ የሚከብደው ምንም ነገር የለም፤ ስለዚህ ትላልቅ ነገሮችን በሙሉ እንጠይቀው! የትኛውንም ዱዓ እንዳትረሱ ዛሬ ማታ የዱዓ ዝርዝር (ሊስት) ጻፉ!
በተለይ ነገ ከዓስር እስከ መግሪብ ያለውን ወርቃማ ሰዓት ለማንም አትስጡ። ክፍል ገብታችሁ፣ በር ዘግታችሁ፣ ስልክ አጥፍታችሁ እጃችሁን ወደ ሰማይ በማንሳት አላህን በግል አናግሩት። "ጌታዬ ሆይ! እኔ ደካማ ነኝ፣ አንተ ግን ሀያል ነህ... ማረኝ!" በሉት።
አላህ የነገውን ቀን ጾመው፣ ዱዓቸው ተቀባይነት አግኝቶ ከእሳት ነጻ ከሚወጡት ባሮቹ ያድርገን! አሚን! 🤲
11 280
🕋 ለበይከሏሁመ ለበይክ! የአመቱ ታላቁ ቀን ደረሰ!
በእነዚህ ቀናት የዓለማችን ልዩ ስፍራ በሆነችው መካ፣ ሚሊዮኖች "ለበይከሏሁመ ለበይክ" እያሉ የሐጅ ስነ-ስርዓትን ለመፈጸም እየተዘጋጁ ነው። በአካል እዚያ መገኘት ባንችልም፣ ልባችን እዚያው ነው!
ያልደረስነውን አላህ (ሱ.ወ) በቅርቡ ከሚያስተናግዳቸው እንግዶቹ (ሑጃጆች) እንዲያደርገን፣ ዘንድሮ ለሄዱት ደግሞ ሐጃቸውን "ሐጅ አል-መብሩር" (ተቀባይነት ያለው ሐጅ) እንዲያደርግላቸው ከልብ ዱዓ እናድርግ! 🤲
እኛስ?
የአመቱ ታላቁ ቀን ከነገ ወዲያ ነው! የፊታችን ማክሰኞ የዙል-ሒጃ 9ኛ ቀን፣ ማለትም የዐረፋ ቀን ነው! የዐረፋ ቀን አላህ (ሱ.ወ) ባሮቹን ከእሳት ነጻ የሚያወጣበት፣ ዱዓዎች ተቀባይነት የሚያገኙበት፣ እና ዲናችን ሙሉ የሆነበት ታላቅ ቀን ነው! ለዚህ ቀን ከወዲሁ ልዩ ዝግጅት ያስፈልገናል፡-
• መጾም (ያለፈውን እና የሚመጣውን የ2 ዓመት ወንጀል ያስምራል)
• ዱዓን ማብዛት
• ተክቢራ ማብዛት
አላህ ቀኑን በአግባቡ ከሚጠቀሙት ያድርገን🤲
11 280
🪨 ሸይጧንን መውገር - የውስጥን ፈተና ማሸነፍ
ሑጃጆች በሚና የ"ጀመራት" ስነ-ስርዓትን ሲፈጽሙ (ጠጠር ሲወረውሩ) የምናየው፣ አባታችን ነብዩ ኢብራሂም (ዐ.ሰ) ልጃቸውን ሊያርዱ ሲሄዱ ሸይጧን ሊያሳስታቸው በመጣ ጊዜ ጠጠር በመወርወር ያባረሩበትን ታሪክ ለማስታወስ ነው።
አባታችን ኢብራሂም ሸይጧንን ጠጠር ወርውረው አባረሩት። የኛስ ሸይጧን? ወደ መስጊድ ስንሄድ፣ ሰደቃ ልንሰጥ ስናስብ፣ ወይም ሱናን ልንተገብር ስንል ሸይጧን "ይቀርብሃል፣ ጊዜ የለህም፣ ሰዎች ምን ይሉሃል" እያለ ያዘናጋናል።
የአባታችን ኢብራሂምን ፈለግ በመከተል እኛም በውስጣችን የሚመጣውን የሸይጧን ጉትጎታ በእምነትና በቁርጠኝነት "ጠጠር ወርውረን" (እምቢ ብለን) እናባርረው! አላህ ያግራልን 🤲
11 280
"አባቴ ሆይ የታዘዝከውን ስራ!" - የልጁ ታዛዥነት
ነብዩ ኢብራሂም (ዐ.ሰ) አላህ ያዘዛቸውን ለልጃቸው ለእስማዒል ሲነግሩት፣ የልጁ ምላሽ እጅግ አስገራሚ ነበር!
"ለምን?" ብሎ አልጠየቀም፤ አልተቆጣም፤ ለመሸሽም አልሞከረም። ይልቁንም "አባቴ ሆይ የታዘዝከውን ስራ፤ አላህ ቢሻ ከታጋሾቹ ሆኜ ታገኘኛለህ" በማለት አስደናቂ ታዛዥነትን አሳየ!
የእስማዒልን ታሪክ ስናወሳ፣ ለወላጆቻችን ያለንን ክብርና ታዛዥነት ራሳችንን እንጠይቅ። ወላጆቻችን የሚያዙን ወደ መልካም ነገር ሆኖ ሳለ ስንቶቻችን ነን "እሺ" ብለን በታዛዥነት የምንቀበለው? አላህ የወላጆቻችንን ሐቅ የምንወጣ ያድርገን! 🤲
11 280
ታላቁ ፈተና - በጣም የምንወደውን ለአላህ መስጠት
ነብዩ ኢብራሂም (ዐ.ሰ) በእርጅና ዘመናቸው ያገኙትን፣ ብቸኛ እና እጅግ የሚወዱትን ልጃቸውን (እስማዒልን) እንዲያርዱ በሕልም ታዘዙ። የአላህ ነብያት ሕልም ደግሞ ራዕይ (ወህይ) ነው።
ይህ ፈተና በታሪክ ውስጥ ከታዩት ፈተናዎች እጅግ ከባዱ ነበር! ኢብራሂም ግን የልባቸው ቁራጭ የሆነውን ልጃቸውን ለአላህ ትዕዛዝ ሲሉ አሳልፈው ለመስጠት አላመነቱም።
እኛ ልጃችንን እንድናርድ አልታዘዝንም። ነገር ግን አላህን ለማስደሰት ስንል የትኛውን የምንወደውን ነገር (ምቾታችንን፣ መጥፎ ጓደኛን፣ የተከለከለ ፍላጎትን) መስዋዕት አድርገናል? ሁላችንም አላህ ይቀበለን 🤲
11 280
💧ጥረት እና እምነት - (የሶፋ እና መርዋ ትምህርት)
ህጻኑ እስማዒል በውሃ ጥም ሲያለቅስ፣ እናታችን ሀጀር ዝም ብላ አልተቀመጠችም። ውሃ ለመፈለግ በሶፋ እና መርዋ ተራራዎች መካከል ሰባት ጊዜ ተመላለሰች (ሮጠች)። አላህም ጥረቷን ተመልክቶ በህጻኑ እስማዒል እግር ስር ልዩ የሆነውን የዘምዘም ውሃን አፈለቀላት!
ተወኩል ማለት ቁጭ ብሎ መጠበቅ ማለት አይደለም። አላህን ማመን እና የራስን ጥረት (ሰበብ) ማድረስን ይጠይቃል። ሀጀር ሰበብ አደረሰች፣ አላህ ደግሞ ተዓምር ሰጣት!
ሁላችንም ለዱኒያም ሆነ ለአኼራ ስኬታችን የራሳችንን ጥረት እናድርግ! አላህ ተዓምሩን ያሳየን! 🤲
11 280
🏜 ታላቁ መመካት - የእናታችን ሀጀር ታሪክ
የዙል-ሒጃ ቀናት እና የሐጅ ስነ-ስርዓቶች የነብዩላህ ኢብራሂም (ዐ.ሰ) እና የቤተሰባቸውን ታላቅ መስዋዕትነት የምናስታውስባቸው ቀናት ናቸው።
ነብዩ ኢብራሂም ባለቤታቸውን ሀጀርን እና ህጻኑን እስማዒልን ሰውም ሆነ ውሃ በሌለበት በረሃ (መካ) ትተዋቸው እንዲሄዱ በአላህ ታዘዙ። እናታችን ሀጀርም "ይህን እንድታደርግ አላህ አዞሃልን?" ብላ ጠየቀች። "አዎ" ሲሏት፣ "እንግዲያውስ አላህ እኛን መቼም አይጥለንም!" በማለት አስገራሚ የሆነ እምነቷን አሳየች።
እንደ እናታችን ሀጀር በአላህ ላይ ሙሉ ተወኩል ይኑረን፤እርሱ መቼም አይጥለንም!
11 280
የተረሳውን ሱና ህያው እናድርግ!
የዙል-ሒጃ አስርት ቀናት የዚክር ቀናት ናቸው! ሰሃባዎቹ ኢብኑ ዑመር እና አቡ ሁረይራ (ረ.ዐ) በእነዚህ ቀናት ወደ ገበያ ሲወጡ ድምጻቸውን ከፍ አድርገው ተክቢራ ይሉ ነበር፤ ሰዎቹም አብረዋቸው ተክቢራ ያደርጉ ነበር።
በመንገድ ላይ፣ በቤታችን፣ በስራ ቦታችን ይህንን እንበል፡-
"አላሁ አክበር፣ አላሁ አክበር፣ ላ ኢላሃ ኢለላህ፣ ወላሁ አክበር፣ አላሁ አክበር፣ ወሊላሂል ሐምድ!
11 280
🌟 ከአለም ቀናት ሁሉ በላጮቹ ቀናት ነገ ይጀምራሉ።
እነዚህ 10 ቀናት አላህ (ሱ.ወ) በቁርኣን የማለባቸው ታላላቅ ቀናት ናቸው። የረመዳን የመጨረሻዎቹ 10 ሌሊቶች በአመት ውስጥ በላጭ ሲሆኑ፣ የዙል-ሒጃ የመጀመሪያዎቹ 10 ቀናት ደግሞ ከቀናት ሁሉ በላጭ ናቸው!
ከነገ ጀምሮ ጾም፣ ቁርኣን፣ ሰደቃ እና ዚክር እናብዛ! አላህ ከሚጠቀሙት ያድርገን!
11 280
⏳ ወደ በላጮቹ 10 ቀናት መግቢያ ላይ ነን!
ከአመቱ ቀናት ሁሉ ታላቅ ወደሆኑት የዙል-ሒጃ (የሐጅ ወር) የመጀመሪያዎቹ 10 ቀናት ልንገባ የ ቀናት ዕድሜ ብቻ ቀርቶናል! አሁን የምንገኝበት የተከበረው የዙል-ቂዕዳ ወር ማሳረጊያ ላይ ነው።
በዚህ ሰዓት በሚሊዮን የሚቆጠሩ ምዕመናን ከየአለማቱ ወደ ተከበረችው መካ ጉዟቸውን ጀምሯል። አካላችን እዚያ መገኘት ባይችልም፣ ልባችን እና ዱዓችን ግን ከእነርሱ ጋር ነው! 🕋✨
ረመዳን ሲመጣ ቤታችንን እና ልባችንን እንደምናጸዳው ሁሉ፣ ለእነዚህ "ወርቃማ 10 ቀናት" ዝግጅት አላህ (ሱ.ወ) ካከበራቸው ወራት ውስጥ ነንና ከወንጀል ርቀን በኢስቲግፋር (ምህረትን በመጠየቅ) እንቀበላቸው!
አላህ ሆይ! ያንን የተከበረ ቤት ለመዘየር፣ በካዕባ ዙሪያ ጠዋፍ ለማድረግ፣ በዐረፋ ተራራ ላይ መቆመን በቅርቡ ወፍቀን! አሚን 🤲
11 280
🎉 Bayyinah TV Subscription Giveaway Round 3! 🎉
Do you want to understand the Quran deeply and learn Arabic? We are giving away a FREE 3-month Bayyinah TV subscription to three people!
This opportunity is prepared only for those who genuinely seek knowledge.
To enter, send us a message with the following:
* How do you plan to utilize a 3-month Bayyinah subscription to deepen your understanding of the Quran and Arabic language?
Deadline: April 03, 2026
Send it here: @ContactMusalla
11 280
🌟 የአንድ ሙሉ ዓመት የጾም አጅር ማግኛ
የረመዳን ወር አልፎ የዒድ በዓልን በደስታ አሳልፈናል፤ አልሀምዱሊላህ! አሁን ደግሞ ሌላ ታላቅ እድል ከፊታችን አለ። እሱም የሻዋልን 6 ቀናት መጾም ነው!
6ቱን ቀናት በተከታታይ ወይም በሻዋል ወር ውስጥ ከፋፍሎ (በተለያዩ ቀናት) መጾም ይቻላል።
የሻዋልን ጾም መቼ ለመጀመር አሰባችሁ? አላህ መልካም ስራችንን ሁሉ ይቀበለን! 🤲
11 280
አላሁ አክበር! አላሁ አክበር! ላ ኢላሃ ኢለላህ አላሁ አክበር! አላሁ አክበር....
"ተቀበለላሁ ሚና ወሚንኩም ሷሊሐል አዕማል!"
(አላህ ከእኛም ከእናንተም መልካም ሥራዎችን ይቀበል!)
በድጋሚ እንኳን ለ1447ኛው የዒድ አል-ፊጥር በዓል በሰላም፣ በጤና እና በፍቅር አደረሳችሁ።
በዓሉን ከቤተሰብዎ እና ከወዳጅ ዘመድዎ ጋር በደስታ ያሳልፉ! ዒድ ሙባረክ! 🎁🎈
11 280
🌙 ስንብት እና ተክቢራ!
አላሁ አክበር! አላሁ አክበር! ላ ኢላሃ ኢለላህ...
30 የረመዳን ቀናትን ጾመን፣ አልቅሰን፣ ዱዓ አድርገን እነሆ አጠናቀቅን። ልባችን በረመዳን መሄድ ቢያዝንም፣ አላህ ባዘጋጀልን የኢድ በዓል ደግሞ እንደሰታለን!
ከአሁኑ ሰዓት ጀምሮ እስከ ኢድ ሶላት ድረስ "ተክቢራ" ማድረጋችንን (አላህን ማላቅ) አናቋርጥ። ጌታችን ሆይ! ጾማችንን፣ ሶላታችንን እና ዱዓችንን ተቀበለን!
🎉 ዒድ ሙባረክ! | Eid Mubarak! 🌙✨
11 280
🌅 የመጨረሻው የረመዳን ቀን! (ቁጥሩን መሙላት)
ጨረቃ ባለመታየቷ ምክንያት፣ ነገ የ1447 ዓ.ሂ ረመዳን 30ኛ እና የመጨረሻ ቀን መሆኑ ተረጋግጧል። አላህ (ﷻ) በቁርኣኑ "...ቁጥሩንም ልትሞሉ..." እንዳለው፣ ይህንን የተከበረ ወር በነገው እለት በጾም አጠናቀን እንሰናበታለን።
በዚህች የመጨረሻ ቀን ውስጥ ሆነን እስካሁን የሰራነውን ኢባዳ አላህ እንዲቀበለን፣ በስንፍና ያሳለፍነውን ጊዜ ደግሞ እንዲምረን ከልብ ዱዓ እናድርግ። አላህ ጾማቸውን ከተቀበላቸው ባሮቹ ያድርገን! አሚን!🤲
11 280
🏁 የመጨረሻዋ የጎዶሎ ሌሊት - አትዘናጉ!
ዛሬ የረመዳን 29ኛ ሌሊት ናት! አንዳንዶቻችን ደክሞን ሊሆን ይችላል፤ ነገር ግን "ሥራዎች የሚመዘኑት በፍጻሜያቸው ነው ወሩ ሊያልቅ ነው ብለን አንዘናጋ። እስከ መጨረሻው ሰከንድ በኢባዳ እንበርታ።
11 280
🌾 የጾማችን ማጥሪያ - ዘካተል ፊጥር!
ረመዳን ሊያልቅ ቀናት ብቻ ቀሩት! ጾማችንን ከማናውቀው ስህተትና ከማይረባ ንግግር የሚያጠራልን ዘካተል ፊጥር ነው። በተጨማሪም በኢድ ቀን ድሆች እንዳይራቡ ያደርጋል።
ዘካተል ፊጥርን አውጥታችኋል? ከኢድ ሶላት በፊት መድረስ ስላለበት፣ ከወዲሁ የቤተሰባችንን እናውጣ !🌾
