ch
Feedback
ኢት-መጽሐፍት | ETHIO-BOOKS

ኢት-መጽሐፍት | ETHIO-BOOKS

前往频道在 Telegram

👉 "የምታነበው መጽሐፍ ለአንተ የሚያስብልህ ሳይሆን አንተ እንድታስብ የሚያደርግ ነው።" ሃርፐር ሊ Fiction (ልቦለድ), History (ታሪክ), Politics (ፖለቲካ), Psychology (ስነልቦና), Biography (ግለ-ታሪክ), Self-help(ራስ አገዝ),& Philosophy(ፍልስፍና) የሀገር ውስጥ & የውጪ ሀገር መጽሐፎችን ያገኛሉ!አስተያየትዎን እዚህ @Desutech_bot ያድርሱን

显示更多
1 991
订阅者
-124 小时
-67
-5330
帖子存档
➳➳➳ ሼር ያድርጉ!! ➢➢➢    👉 @et_books1 👉 @et_books1

➳➳➳ ሼር ያድርጉ!! ➢➢➢    👉 @et_books1 👉 @et_books1

ፍቅር ምን፣ መሰስሽ?......... እንደ ፅጌረዳ እንደ ሱፍ አበባ በመልካም ጠረኑ መንፈስ እያዛባ አጥብቀው ሲይዙት ሊሰበር ያዘማል ትተው እንዳይሄዱ በመዓዛው ያስራል። ፍቅር ምን መሰለሽ?.... ዕ
ፍቅር ምን፣ መሰስሽ?......... እንደ ፅጌረዳ እንደ ሱፍ አበባ በመልካም ጠረኑ መንፈስ እያዛባ አጥብቀው ሲይዙት ሊሰበር ያዘማል ትተው እንዳይሄዱ በመዓዛው ያስራልፍቅር ምን መሰለሽ?.... ዕድሜን ማባበያ ዘመን መሸንገያ ህልምን ማሳጠሪያ የአምላክ ስጦታ ብዙ መሻቶችን አስሮ የሚገታ፡፡ ይህን አላውቀውም.... ከማውቀው ነገር ላይ የምነግርሽ ነገር አበባ ታቅፌ ዘላለም እንድኖር ወይም ጣቴ መሃል አበባ እንዲሰበር፡፡ ትዝታስ ምንድ ነው?.... ትዝታ ቅዠት ነው..... የሆኑትን ነገር ባልሆንኩት የሚሉት ወይም አሁን ቢሆን ብለው የሚመኙት           ግን............ .....ይህን አልፈልግም የዘመን አስታዋሽ የአበባ እርጋፊ ደራርቆና ወድቆ ተመልከት እንዳይለኝ ..ውበትሽ ላይ ስቆ አንቺ ላይ ተሳልቆ፡፡ ይህ ሁሉ ቢሆንም…..... ውበትዋ ለከዳት ጠውላጋ አበባ ውሃ እሆናለሁ የሕይወትን ንፋስ እተነፍሳለሁ....... እርጅናን ለመግደል ውቢቱን አበባ መፃፍ እችላለሁ............ ➳➳➳ ሼር ያድርጉ!! ➢➢➢    👉 @et_books1 👉 @et_books1

✍️✍️ ጉንዳን✍️✍️ ✍️ ጉንዳን የክብደቱ 50 እጥፍ መሸከም እና 30 እጥፍ መጎተት ይችላል::አንድ ጉንዳን 250,000 የአንጎል ህዋሳት አሉት:: ከአካላቸው ክብደት አንፃር ትልቅ አንጎል ያላቸው
✍️✍️ ጉንዳን✍️✍️ ✍️ ጉንዳን የክብደቱ 50 እጥፍ መሸከም እና 30 እጥፍ መጎተት ይችላል::አንድ ጉንዳን 250,000 የአንጎል ህዋሳት አሉት:: ከአካላቸው ክብደት አንፃር ትልቅ አንጎል ያላቸው ፍጥረታት ጉንዳኖች ናቸው:: ✍️ ጉንዳኖች በምድር ጥልቀት ውስጥ ያለን ውሀ በማሽተት ለይተው ያውቃሉ:: ንግስቲቱ ጉንዳን እስከ 15 አመት እድሜ ትቆያለች:: ጉንዳኖች ውሀ ውስጥ እንደሰመጡ አየር ሳያገኙ ለሁለት ቀናት መቆየት ይችላሉ:: ✍️ጉንዳን ከተፈጠረበት ጊዜ ጀምሮ እስከሚሞትበት ሰአት ድረስ በፍፁም አያንቀላፋም:: በ 1 የጉንዳን መንጋ ውስጥ ግማሽ ሚሊዮን ጉንዳኖች ሊኖሩ ይችላሉ:: ✍️ ብታምኑም ባታምኑም በምድር ላይ  ያሉ ጉንዳኖች በሙሉ ተሰብስበው ክብደታቸው ቢለካ ከአለም ህዝብ አጠቃላይ ክብደት ይበልጣል:: ምንጭ:- National Geographic ➳➳➳ ሼር ያድርጉ!! ➢➢➢    👉 @et_books1 👉 @et_books1

.......ሹመቴን መልሱ......... ጎራዉ ያለ እንደሆን ባለምባራስ ደስታ ዘራፍ ያለ እንደሆን ባለምባራስ ደስታ ጠላት ይጠፋዋል መደበቂያ ቦታ ፊታዉራሪ ፍላቴ ግራዝማች በሀፍቴ አዛዥ ለጥ ይበሉ ቀኝ አዝማች በአካሉ ዣንጥራር ባያለዉ ደጃዝማች እንዳለዉ እንዲህ ነዉ ካልቀረ አንጀት አርስ ሹመት ለድል የሚያበቃ ጦር ይዞ ቢዘምት የጣሊያን ጄኔራል ኮከቡን ደርድሮ በለጋባሞ ዜር ስንት አሳሩን ቆጥሮ ድል አርጎት የኛ ሰዉ ፎከራን በኩራት እንደተመለስን ስልጣኔ መስሎን የሱን ስም ወረስን ሟቹ ጄኔራልነዉ ገዳይ ፊት አዉራሪ ስም እንዴት ይዋሳል ደፋር ሰዉ ከፈሪ በጠላት ሬሳ ላይ ቆመን እያቅራራን በድላችን ማግስት የኛን ሹመት ንቀን ከሆንን ኔተራል: ባናዉቀዉ ነዉ እንጅ የዛን ቀን ሙተናል ኮኔሌል አይበሉን ያገሩን ያገሩን አርበኛ ጄኔራል አይበሉን ያገሩን አርበኛ ፈረንጅ አይደለም ሀበሻ ነን እኛ የሟች ስም አይደለም የገዳይ ሰዉ ምሱ በደም ተበላሽቷል ባለ ኮከብ ልብሱ ገድየዉ ሳበቃ ባስታጠቁኝ ወኔ በሱም አይጥሩኝ ቆሞ እንዲሄድ በኔ ጄኔራል ድል ሆኖ ስላለፈች ነፍሱ ይበሉ ጃንሆይ ሹመቴን መልሱ ፊት አዉራሪ ካታካምቦ ሊጋባ ዴሊቦ አዛዥ ለጥ ይበሉ ቀኝ አዝማች አካሉ ዣንጥራር አበጋዝ እንዲህ ነዉ አንጀት አርስ ሹመት ለድል የሚያበቃ ጦር ይዞ ቢዘምት ፈቃድወ ከሆነ ግርማዊ ተፈሪ እንዳገሬ ሹመት በሉኝ ፊት አዉራሪ በሟች ከመጠራት ስለሚሻል እሱ ይበሉ ጃን ሆይ ሹመቴን መልሱ     ቴዲ_አፍሮ                                                                                                        

አ ላ ዋ ቂ ነ ት ━━✦━━ «ከመላው ዓለም ውስጥ እንደ ሰው በምድር ላይ ስንመላለስ የምናውቀው ጥቂት ሰበዞችን ነው። ክበቡ እጅግ በጣም ሰፊ ነው። የምናውቀው ከማናውቀው ነገር ያንሳል፣ ይበዛልም። ዓለም እንደ እይታችን መጠን ትልቅ፣ ትንሽም ነው። ይህን የሚያውቅ ሰው ግን በቁጥር በጣም ውስን ነው። ዓለምን ያህል ነገር ቀርቶ በውስጧ የያዘችውን ረቂቅና ግዙፍ ፍጥረታት ሳይቀር በዘርፍ ከፋፍለን በቅንጣት ነው የምናጠናው። ለምሳሌ ሥነ-ነርቭ (Neurology)፣ ሥነ-አዕምሮ (Psychiatry)፣ ሥነ-ቆዳ (Dermatology)፣ ሥነ-መሬት (Geology)፣ ፍልስፍና (Philosophy)፣ ሥነ-መለኮት (Theology)፣ ሥነ-ሕይወት (Biology) ... እያልን የምናጠናው ከባሕር ላይ በማንኪያ ሰፍረን ነው። ስለዚህ ሁሉም ነገር ይግባን ብንል ከጥልቀቱ የተነሳ እንባክናለን። ስለምንኖርበት ምድር የምናውቀው ዕውቀት በአንድ ጀምበር የተሰበሰበ አይደለም። በእጃችን ያለው መረጃ በትውልድ ቅብብል የተላለፈ ነው። ከኋለኞቹ የተቀበልነውን ሃይማኖታዊም ሆነ ሳይንሳዊ ድርሳን ለሚመጣው ዘመነኛ ከማስተላለፋችን በፊት እናጤነዋለን። እውነት በዓመታት ብዛት አያረጅምና የማይቀየረውን ባለበት፣ የተገደፈውን ነቅሰን እያስቀረን ያልተደረሰበትን እየገለጥን... መዝገብ እናከማቻለን። ያለፈውን ነገር እንደ ታሪካዊ እውነታ እያወቅን፣ በጊዜ ሂደትም አዲስ ነገርን እያወቅን መሄዳችን አይቀርም። በመማራችን ውስጥ የዕውቀት ፍርሃት አለ። ምናልባትም ማወቅ ትካዜን ስለሚጨምር ይሆናል። ትንሽነታችንን ስንረዳ መታበያችንን እናቆማለን። አቅምን አውቆ መኖር እንዴት ይገላግላል መሰላችሁ? አንጠቀምበትም እንጂ ልክን ማወቅ ትልቅ ችሎታ ነው። ‹አላውቅም፣ አልገባኝም› ማለት ረፍት ሰጪ ቃል ነው። ከመርበትበት፣ ከመጨነቅ ይገላግላል። ስለሞትና ስለሕይወት ሁሉን አናውቅም። ምክንያቱም ሞትን በፅንሰ ሐሳብ እንጂ በድርጊት አናውቀውም። ስለ ሞት የሚያውቀው በሕይወት ያለው ግለሰብ ሳይሆን በሞት የተሰናበተው ነው። ይህ ማለት ግን ሕያዋን ሳለን ስለ ሞት የምናውቅበት ዕድል የለም ማለት አይደለም። የምናውቀውን ያህል መደንገጥ፣ የማናውቀውን ያህል ደግሞ አለመደንገጥ ላይኖርብን ይችላል። ራቪ እንደሚለው የአንድን ነገር መሠረት (Origin)፣ ትርጉም (Meaning)፣ ግብረ-ገብ (Morality)፣ ዕጣ-ፈንታ (Destiny) ሰው ሁሉ እየጠየቀና መልስ ለማግኘት እየሞከረ መጓዝ አለበት። ሰው 'ወደዚህ ምድር እንዴት መጣሁ? ከሞትኩ በኋላስ ወደ የት እሄዳለሁ?' ብሎ መጠየቅ አለበት።» >>> ━━━━━━━━ 📔 አልገባኝም ✍ ዮናስ ዘውዴ ከበደ 📄 27 - 29 🗓 ፳፻፲፪ ዓ.ም. 📖 📖 📖 📖 📖 ➳➳➳ ሼር ያድርጉ!! ➢➢➢    👉 @et_books1 👉 @et_books

➳➳➳ ሼር ያድርጉ!! ➢➢➢    👉 @et_books1 👉 @et_books

ፈ ገ ግ ታ ━ 😁 ━ >>> «በዚህ ዓለም ላይ ጥሩ ወይም መጥፎ ነገር የለም። ያንን የሚፈጥረው ግን ሃሳባችን ነው።» ብሏል ሼክስፒር። ጥንታውያን ቻይኖች ሲበዛ ጥበበኞች ነበሩ። ምንጊዜም ሊረሱት የማይገባ አንድ አባባል አላቸው። እሱም «ፈገግታ የሌለው ሰው ሱቅ መክፈት የለበትም።» ይላል። ፈገግታዎ የመልካም ፈቃድ መልዕክተኛ ነው። ፈገግታዎ የሚመለከተውን ሕይወት ሁሉ ብሩህ ያደርጋል። ብዙ የተኮሳተሩና የተጨማደዱ ፊቶች ያየ ሰው የእርስዎን ፈገግታ ሲመለከት ፀሐይ ከደመና ውስጥ ብቅ እንዳለች ያህል ነው።... ፈገግታ ሁሉም ተስፋ ቢስ እንዳልሆነ እንዲረዳ በዓለማችን ውስጥ ደስታም እንዳለ እንዲገነዘብ የሚረዳ ኃይል ነው። ከጥቂት ዓመታት በፊት ኒውዮርክ ሲቲ ውስጥ አንድ የዲፓርትመንት ስቶር ባገኘው የጥድፊያ ገበያ ሳቢያ በሽያጭ ሠራተኞቹ ላይ የሚከሰተውን ጫና አስመልክቶ ስለ ፈገግታ ጠቃሚነት ለአንባቢያን የሚከተለውን ማስታወቂያ አውጥቶ ነበር።           የፈገግታ ዋጋ → ዋጋ አያወጣም ግን ብዙ ደስታን ይፈጥራል። → ፈገግታ የሚለገሳቸውን ሰዎች ያበለጽጋል፣ ሰጪውንም አያደኸይም። → ከመቅጽበት ስሜትን የሚያድስና ትዝታው አንዳንድ ጊዜ እስከ ወዲያኛው የሚዘልቅ ነው። → በፈገግታ የሚኖሩ ያን ያህል የታደሉና ሀብታም አይደሉም። በፈገግታ የሚኖሩት ያን ያህል ያልታደሉና ደሃ ሳይሆኑ በጠቃሚነታቸው የበለጸጉ ናቸው። → በቤት ውስጥ ደስታን ይፈጥራል፣ በቢዝነስ ውስጥም በጎ ፈቃድን ያጠናክራል፣ እንዲሁም የወዳጆች የይለፍ ቃል ነው። → ለተዳከሙ ረፍት፣ ብርታት ላነሳቸው የቀን ብርሃን፣ ላዘኑ የመጽናኛ ብርሃንና ለችግር የተፈጥሮ መድኃኒት ነው። → ያም ሆኖ ግን ፈገግታ የሚገዛ፣ የሚለመን፣ የሚበደሩት ወይም የሚሰረቅ አይደለም። → ስለሆነም በገና የጥድፊያ ሰዓት ሊገዙ ሲመጡ የሽያጭ ሰዎቻችን ደክመው ፈገግታ ሊሰጡዎ ባይችሉ የእርስዎን ፈገግታ ትተውልን እንዲሄዱ ብንጠይቅዎትስ? >>> ━━━━━━━━ 📔 የመኖር ክህሎት ✍ ዴል ካርኔጊ ትርጉም ➢ በፋንታሁን ኃይሌ 📄 57 - 58 📖 📖 📖 📖 📖 ➳➳➳ ሼር ያድርጉ!! ➢➢➢    👉 @et_books1 👉 @et_books

➳➳➳ ሼር ያድርጉ!! ➢➢➢    👉 @et_books1 👉 @et_books

📚ቄሳርና አብዮት ✍አምባሳደር ብርሃኑ ድንቄ ➳➳➳ ሼር ያድርጉ!! ➢➢➢ 👉 @et_books1 👉 @et_books
📚ቄሳርና አብዮት ✍አምባሳደር ብርሃኑ ድንቄ ➳➳➳ ሼር ያድርጉ!! ➢➢➢    👉 @et_books1 👉 @et_books

የኔ ውብ ከተማ ══✦══ ✍ በዓሉ ግርማ ' ከጎራው ዘልቄ እስኪ ልነጋገር ካለሰው ቢወዱት ምን ያደርጋል አገር? የኔ ውብ ከተማ ህንፃ መች ሆነና የድንጋይ ክምር የኔ ውብ ከተማ መንገድ መች ሆነና የ
የኔ ውብ ከተማ ══✦══ ✍ በዓሉ ግርማ ' ከጎራው ዘልቄ እስኪ ልነጋገር ካለሰው ቢወዱት ምን ያደርጋል አገር?      የኔ ውብ ከተማ ህንፃ መች ሆነና የድንጋይ ክምር      የኔ ውብ ከተማ መንገድ መች ሆነና የድንጋይ አጥር      የኔ ውብ ከተማ የኔ ውብ አገር የሰው ልጅ ልብ ነው የሌለው ዳርቻ የሌለው ድንበር። ህንፃው ምን ቢረዝም ምን ቢፀዳ ቤቱ መንገዱ ቢሰፋ ቢንጣለል አስፋልቱ ሰው ሰው ካልሸተተ ምንድን ነው ውበቱ? ═══════ 📔 ኦ ሮ ማ ይ 📖 📖 📖 📖 ➳➳➳ ሼር ያድርጉ!! ➢➢➢    👉 @et_books1 👉 @et_books

➳➳➳ ሼር ያድርጉ!! ➢➢➢    👉 @et_books1 👉 @et_books

➳➳➳ ሼር ያድርጉ!! ➢➢➢ 👉 @et_books1 👉 @et_books
➳➳➳ ሼር ያድርጉ!! ➢➢➢    👉 @et_books1 👉 @et_books

📚ርዕስ=ዕንባና ሳቅ(ልቦለድ) ✍ደራሲ=ገበየሁ አየለ 📄የገፅ ብዛት= 223 ➳➳➳ ሼር ያድርጉ!! ➢➢➢    👉 @et_books1 👉 @et_books

.... ይህችን ዓለም በበላይነት የሚያስተዳድራት ፍርሃት ነው፤ ከሥልጣን መውረድን መፍራት፣ ውርደትን መፍራት፣ እጦትን መፍራት... ፍርሃት፣ ፍርሃት፣ ፍርሃት...ብዙ መልኮች ያሉት ፍርሃት። . . .
.... ይህችን ዓለም በበላይነት የሚያስተዳድራት ፍርሃት ነው፤ ከሥልጣን መውረድን መፍራት፣ ውርደትን መፍራት፣ እጦትን መፍራት... ፍርሃት፣ ፍርሃት፣ ፍርሃት...ብዙ መልኮች ያሉት ፍርሃት። . . .       በ325 ዓ.ም በኒቂያ ጉባኤ "ክርስቶስ ሰው እንጂ አምላክ አይደለም" የሚለው የአርዮስ አስተሳሰብ ተወገዘ።      ከሁለት ዓመታት በኋላ የጳጳሱ አቡነ እስክንድርን ህልፈት ተከትሎ፣ አቡነ አትናቲዮስ መንበረ ሥልጣኑን ተረከቡ።      ጥቂት ዓመታት ቆይቶ አርዮስ የነገሥታቱን ይሁኝታ በማግኘት አቡነ አትናቲዮስን ለብቻቸው በደሴት ውስጥ አሳሰራቸው።      በዚህ ወቅት ከአንድ ወዳጃቸው "The whole world is against you" በሚል ለተላከላቸው መልእክት አቡነ አትናቲዮስ ሲመልሱ "If the world goes against the truth, then Athanasius will goes against the world" ብለዋል። "ዓለም ዕውነቱን መቃወምን ከመረጠ አትናቲዮስ ዓለምን ይቃወማል" እንደማለት። የብርሃኑ ድንቄ 'አልቦ ዘመዳዊ' "እምቢ አሻፈረኝን ካልተለማመድክ መኖርን አታውቃትም።" ገደምዳሜ ምክር እዚች ጋር በገቢር ይሠራል።         ግን ስንቶቻችን መላው ዓለም ቀርቶ በቅርብ አለቆቻችን፣ አስሮ ባስቀረን ፍርሃታችን ላይ 'እምቢ!' 'አሻፈረኝ!' እንላለን? . . ከባዶ ላይ መዝገን (በያዕቆብ ብርሃኑ) ➳➳➳ ሼር ያድርጉ!! ➢➢➢    👉 @et_books1 👉 @et_books

+1
📚"የብርሃን ፈለጎች" ✍የአለማየሁ ገላጋይ ➳➳➳ ሼር ያድርጉ!! ➢➢➢    👉 @et_books1 👉 @et_books

----ሴት ብቻ ናት እንዴ---- በመከዳት ሀገር በመጎዳት መንደር በፍቅር ቀበሌ ልቧን ሠብራ ምትኖር ሴት ብቻ ናት እንዴ እውነት እንናገር -ቤት ይቁጠረው እንጅ _ _ ለነጋችን በሚል ዛሬው በረሳ እ
----ሴት ብቻ ናት እንዴ---- በመከዳት ሀገር በመጎዳት መንደር    በፍቅር ቀበሌ ልቧን ሠብራ ምትኖር     ሴት ብቻ ናት እንዴ እውነት እንናገር              -ቤት ይቁጠረው እንጅ                    _                    _ ለነጋችን በሚል ዛሬው በረሳ    እርሱን እዬጣለ እርሷን እያነሳ ሄዋን ሞልቶ ሳለ በዝቶ ተትረፍርፎ     የሂዎት ገፁ ላይ እሷን ብቻ ፅፎ      ባመነው ልክ ያህል ክደትን አትርፎ አለቺኝ በሚላት የለህም ተብሎ     ልኑርልሽ ባላት ተገፍቶ ተጥሎ         ዕልፍ አዳም እኮ አለ ከመውደድ ካብሮነት ከፍቅር ተኳርፎ    የኔነቱን ህመም በውስጡ ቆልፎ               ሠው በበዛበት አለም ተገሎ የሚኖር ብቼኝነትን አቅፎ 👤👤👤 ➳➳➳ ሼር ያድርጉ!! ➢➢➢    👉 @et_books1 👉 @et_books

📚ወንጀልና ቅጣት ( Crime And Punishment ) ✍ደራሲ : ፊዮዶር ሚክሀያሎቪች ዶስቶዮቭስኪ 📝ተርጓሚዎች : አምባሳደር ካሳ ገ/ህይወት & ፋንቱ ካሳ 📖ዘውግ : ልብ ወለድ 📜ማዕረግ : Classic ( ዘመን አይሽሬ ) ➳➳➳ ሼር ያድርጉ!! ➢➢➢    👉 @et_books1 👉 @et_books

+1
📖ርዕስ= አካል አዕምሮ ✍️ደራሲ=ኦሾ 🔍ዘውግ= ስነህይወታዊ ➳➳➳ ሼር ያድርጉ!! ➢➢➢    👉 @et_books1 👉 @et_books