Tнє Cσmpαrαtσr¹
前往频道在 Telegram
⎛ይህ ቻናል ሙስሊም|ሙእሚን ባልሆኑ አካላት ለሚነሱ ሀይማኖታዊ ጥያቄዎች፤ብሎም በነሱም ላይ ጥያቄ ለማንሳት እና እውነታ ለማስጨበጥ የተከፈተ ነው።⎠
显示更多734
订阅者
无数据24 小时
无数据7 天
无数据30 天
帖子存档
ኢሣ ነውን?(በቪድዮ የተዘጋጀ)
-----------------------------------------------------
©አነፃፃሪው|Comparator
t.me/TheComparator
አኺራ
በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ፥ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው❲بِسْمِ اللَّهِ الرَّحْمَٰنِ الرَّحِيم❳
سَلَٰمٌ عَلَيْكُم بِمَا صَبَرْتُمْ ۚ فَنِعْمَ عُقْبَى ٱلدَّارِ
“«ሰላም ለእናንተ ይኹን፡፡ (ይህ ምንዳ) በመታገሳችሁ ነው፡፡ የመጨረሻይቱም አገር ምን ታምር!» (ይሏቸዋል)፡፡”❲Qūrān 13:24❳
-----------------------------------------------------
▪አኺራ"آخِرة" የሚለው የአረቢኛ ቃል አኸረ"آخَر" ከሚለው ስርወ ቃል የተገኘ ሲሆን"የመጨረሻ"፣"መጨረሻ" ማለት ሲሆን"ከሞት በኋላ""Afterlife" ማለት ነው።ይህ ከሞት በኋላ ያለ አለም ለሁለት ሲከፈል እነሱም፦አንደኛው ጀናህ"جَنَّة" ወይም"ገነት" ማለት ሲሆን ሁለተኛው ጀሀንነም"جَهَنَّم" ወይም"ገሀነም" ማለት ነው።
-----------------------------------------------------
◌ነጥብ አንድ ጀናህ:
ጀናህ"جَنَّة" የሚለው ቃል ጀንነ"جَنَّ" ከሚል ስርወ ቃል የተገኘ ሲሆን"መሸፈን"፣"መደበቅ" የሚል ትርጓሜ አለው ጀናህ ከሰው ልጅ አስተሳሰብ እና ማስተዋል በላይ ናት የሚለውን ሃሳብ ስለምታጎላ ጀናህ"የተሸፈነ"፣"የተደበቀ" ተብላ ተጠርታለች ለዚህም በቁርአን እና በሀዲስ ላይ፦
فَلَا تَعْلَمُ نَفْسٌۭ مَّآ أُخْفِىَ لَهُم مِّن قُرَّةِ أَعْيُنٍۢ جَزَآءًۢ بِمَا كَانُوا۟ يَعْمَلُونَ
“ይሠሩትም በነበሩት ለመመንዳት ከዓይኖች መርጊያ ለእነርሱ የተደበቀላቸውን (ጸጋ) ማንኛይቱም ነፍስ አታውቅም፡፡”❲Qūrān 32:17❳
عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ ـ رضى الله عنه ـ قَالَ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم " قَالَ اللَّهُ أَعْدَدْتُ لِعِبَادِي الصَّالِحِينَ مَا لاَ عَيْنَ رَأَتْ، وَلاَ أُذُنَ سَمِعَتْ، وَلاَ خَطَرَ عَلَى قَلْبِ بَشَرٍ،
አቡ ሁረይራ እንደዘገቡት፦
የአላህ መልእክተኛ❲ﷺ❳ እንዲህ ብለዋል፡- “አላህ እንዲህ አለ፡- “እኔ ለመልካም ባሮቼ በአይን ያልታየ፣በጆሮ ያልተሰማ፣በሰውም ያልታሰበውን ነገር አዘጋጅቻለሁ።”❲Sāhih āl-būkhāri 3244❳
▪ጀናህ በቁርኣን አውድ ውስጥ ውስጥ ዘላለማዊ ህይወት የሚያገኙ አማኞችን የምታኖር መሆኗን ለመግለጽ ጥቅም ላይ ውሏል ለዚህም በቁርአን ላይ፦
وَٱلَّذِينَ ءَامَنُوا۟ وَعَمِلُوا۟ ٱلصَّٰلِحَٰتِ لَنُبَوِّئَنَّهُم مِّنَ ٱلْجَنَّةِ غُرَفًۭا تَجْرِى مِن تَحْتِهَا ٱلْأَنْهَٰرُ خَٰلِدِينَ فِيهَا ۚ نِعْمَ أَجْرُ ٱلْعَٰمِلِينَ
“እነዚያም ያመኑና መልካም ሥራዎችን የሠሩ ከገነት በሥሮቻቸው ወንዞች የሚፈሱባቸውን ሰገነቶች በውስጣቸው ዘውታሪዎች ሲኾኑ በእርግጥ እናሰፍራቸዋለን፡፡የሠራተኞች ምንዳ ምንኛ አማረ!”❲Qūrān 29:58❳
በዚህ የቁርአን አንቀጽ ላይ "ዘውታሪዎች" ለሚለው ቃል የተጠቀመው ኻሊዲን"خَٰلِدِين" የሚለውን ቃል ሲሆን ኻሊድ"خَالِد" ከሚለው ሥርወ ቃል የተገኘ ብዙ ቁጥር ነው ትርጉሙም "የሚቀሩ"፣" የሚቆዩት"፣"ዘለዓለማዊ የሆኑት" ማለት ነው።
ይህች ለዘልአለማውያን ዘልአለማዊ የሆነች ቤት መልካም ለሰሩ ምዕመናን የተዘጋጀች ዝግጅት ነች፦
وَٱلَّذِينَ ءَامَنُوا۟ وَعَمِلُوا۟ ٱلصَّٰلِحَٰتِ لَنُبَوِّئَنَّهُم مِّنَ ٱلْجَنَّةِ غُرَفًۭا تَجْرِى مِن تَحْتِهَا ٱلْأَنْهَٰرُ خَٰلِدِينَ فِيهَا ۚ نِعْمَ أَجْرُ ٱلْعَٰمِلِينَ
“እነዚያም ያመኑና መልካም ሥራዎችን የሠሩ ከገነት በሥሮቻቸው ወንዞች የሚፈሱባቸውን ሰገነቶች በውስጣቸው ዘውታሪዎች ሲኾኑ በእርግጥ እናሰፍራቸዋለን፡፡የሠራተኞች ምንዳ ምንኛ አማረ!”❲Qūrān 29:58❳
-----------------------------------------------------
◌ነጥብ ሁለት ጀሀንነም:
ጀሀንነም"جَهَنَّم" የሚለው ቃል ጌሂኖም"גֵיהִנֹם" ከሚለው የዕብራይስጥ ቃል እንደመጣ ይታመናል።[¹]በአይሁድ እምነት"ጌሄና" ወይም"ጌሂኖም" ክፉዎች ከሞቱ በኋላ ወይም በፍርድ ቀን❲Day Of Judgement❳ የሚቀጡበት እሳታማ ቦታ ነው ብለው የሚያምኑበትን"ሂኖም" የተባለ ከኢየሩሳሌም ውጭ ያለ ቦታ ነው።[²]
▪ጀሀንነም ለጠመሙ ለአጥፊዎችም ምንዳ መቀበያ መኖሪያ መሆኗን በቁርአን አውደ ምንባብ❲Contextual Passage❳ ላይ ውሏል፦
أُو۟لَٰٓئِكَ مَأْوَىٰهُمْ جَهَنَّمُ وَلَا يَجِدُونَ عَنْهَا مَحِيصًۭا
“እነዚያ መኖሪያቸው ገሀነም ናት፡፡ ከርስዋም መሸሻን አያገኙም፡፡”❲Qūrān 4:121❳
لَّيْسَ بِأَمَانِيِّكُمْ وَلَآ أَمَانِىِّ أَهْلِ ٱلْكِتَٰبِ ۗ مَن يَعْمَلْ سُوٓءًۭا يُجْزَ بِهِۦ وَلَا يَجِدْ لَهُۥ مِن دُونِ ٱللَّهِ وَلِيًّۭا وَلَا نَصِيرًۭا
“(ነገሩ) በምኞታችሁና በመጽሐፉ ሰዎች ምኞት አይደለም፡፡ መጥፎን የሚሠራ ሰው በእርሱ ይቀጣል፡፡ ለእርሱም ከአላህ ሌላ ጠባቂንም ረዳትንም አያገኝም፡፡”❲Qūrān 4:123❳
عَنْ عَبْدِ اللَّهِ بْنِ مَسْعُودٍ، قَالَ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ ﷺ " يُؤْتَى بِجَهَنَّمَ يَوْمَئِذٍ لَهَا سَبْعُونَ أَلْفَ زِمَامٍ مَعَ كُلِّ زِمَامٍ سَبْعُونَ أَلْفَ مَلَكٍ يَجُرُّونَهَا " . قَالَ عَبْدُ اللَّهِ بْنُ عَبْدِ الرَّحْمَنِ وَالثَّوْرِيُّ لاَ يَرْفَعُهُ.
አብደላህ ቢን መስዑድ እንዳስተላለፈው የአላህ መልእክተኛ❲ﷺ❳ እንዲህ ብለዋል፡-
“ገሀነም በዚያ ቀን (በትንሳኤ) ትወጣለች ሰባ ሺህ ልጓም ያላት በእያንዳንዱ መያዣም ሁሉ የሚጎትቱት ሰባ ሺህ መላእክቶች አልሉ።”❲Jami` at-Tirmidhi Vol. 4,The Description Of Hell, Hadith 2573❳
-----------------------------------------------------
▪አላህ❲ﷻ❳ በቁርአን እነዚህን ቤቶች እንደየስራችን እንደምናገኛቸው አስረግጦ ይነግረናል፦
يَوْمَئِذٍۢ يَصْدُرُ ٱلنَّاسُ أَشْتَاتًۭا لِّيُرَوْا۟ أَعْمَٰلَهُمْ
“በዚያ ቀን ሰዎች ሥራዎቻቸውን (ምንዳዋን) እንዲያዩ ይደረጉ ዘንድ (እንደየሥራቸው) የተለያዩ ኾነው (ከመቆሚያው ስፍራ) ይመለሳሉ፡፡”❲Qūrān 99:6❳
-----------------------------------------------------
ዋቢ ይመልከቱ:
[¹] https://www.newworldencyclopedia.org/entry/Jahannam
[²] https://www.newworldencyclopedia.org/entry/Gehenna
-----------------------------------------------------
ወሰላሙ አለይኩም
©ከወንድም አህመድ(አነፃፃሪው)
t.me/TheComparator
ከኢሣ በስተቀር?
በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ፥ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው❲بِسْمِ اللَّهِ الرَّحْمَٰنِ الرَّحِيم❳
فَلَمَّا وَضَعَتْهَا قَالَتْ رَبِّ إِنِّى وَضَعْتُهَآ أُنثَىٰ وَٱللَّهُ أَعْلَمُ بِمَا وَضَعَتْ وَلَيْسَ ٱلذَّكَرُ كَٱلْأُنثَىٰ ۖ وَإِنِّى سَمَّيْتُهَا مَرْيَمَ وَإِنِّىٓ أُعِيذُهَا بِكَ وَذُرِّيَّتَهَا مِنَ ٱلشَّيْطَٰنِ ٱلرَّجِيمِ
“በወለደቻትም ጊዜ፡- «ጌታዬ ሆይ! እኔ ሴት ኾና ወለድኋት፡፡» አላህም የወለደችውን ዐዋቂ ነው፡፡ «ወንድም እንደ ሴት አይደለም፡፡ እኔም መርየም ብዬ ስም አወጣሁላት፡፡ እኔም እስዋንም ዝርያዋንም ከተረገመው ሰይጣን በአንተ እጠብቃቸዋለሁ» አለች፡፡”❲Qūrān 3:36❳
-----------------------------------------------------
መግቢያ❲Introduction❳
▪“መብላቷን ሳታውቅ፤እጇን ታጠበች” እንዲሉ አንዳች ተገኘ ተብሎ ወንበር ልቀቁ ማለት ለሰሚውም ያሸማቅቃል፤በሀሳዊ ድምዳሜ❲Fallacy Conclusion❳ መመረቂያ ፅሁፋቸውን ከሰሩ ዕቅበተ ክርስትና❲Christian Apologetics❳ ወገኖቻችን“ጉድ ሳይሰማ” እንዲሉ እስቲ አብረን አጂብ እንበል።
-----------------------------------------------------
أَبِي هُرَيْرَةَ ـ رضى الله عنه ـ قَالَ قَالَ النَّبِيُّ صلى الله عليه وسلم
” " كُلُّ بَنِي آدَمَ يَطْعُنُ الشَّيْطَانُ فِي جَنْبَيْهِ بِإِصْبَعِهِ حِينَ يُولَدُ، غَيْرَ عِيسَى بْنِ مَرْيَمَ، ذَهَبَ يَطْعُنُ فَطَعَنَ فِي الْحِجَابِ“
አቡ ሁረይራ እንደተረከው፡-
“ነብዩ (ሶ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል፡- ‹‹ማንም ሰው ሲወለድ ሸይጣን በሁለት ጣቶቹ ከሥጋው በሁለቱም በኩል ይነካዋል፣ የመርየም ልጅ ዒሳ በስተቀር፣ ሰይጣን ሊነካው ሞክሮ አልተሳካለትምና። በምትኩ የእንግዴ ሽፋኑን ነክቷል።”❲Sāhih Āl-Buhāri 3286❳
-----------------------------------------------------
◌ስንጀምር በዚህ ሀዲስ ላይ ሀሳዊ ድምዳሜ❲Fallacy Conclusion❳ ማድረጉን ያዝ አድርጉት እና በረጋ እይታ እንድትመልከቱ አሳስባለሁ!በዚህ ሀዲሱ ላይ“ማንኛውም ሰው ሲወለድ...” ሲል ከመፈጠሩ ብሎም ከእናቱ ማህፀን በኋላ ያሳያል እንጂ ስንወለድ ሙስሊም የሆነው ሰይጣን ስለነካን አይደለም፤ምክንያቱም የተፈጠርነው በእስልምና ላይ ነውና ለዚህም በቁርአን፦
فَأَقِمْ وَجْهَكَ لِلدِّينِ حَنِيفًۭا ۚ فِطْرَتَ ٱللَّهِ ٱلَّتِى فَطَرَ ٱلنَّاسَ عَلَيْهَا ۚ لَا تَبْدِيلَ لِخَلْقِ ٱللَّهِ ۚ ذَٰلِكَ ٱلدِّينُ ٱلْقَيِّمُ وَلَٰكِنَّ أَكْثَرَ ٱلنَّاسِ لَا يَعْلَمُونَ
ወደ እውነት ተዘንባይ ኾነህም ፊትህን ለሃይማኖት ቀጥ አድርግ፡፡ የአላህን ፍጥረት ያችን አላህ ሰዎችን በእርስዋ ላይ የፈጠረባትን (ሃይማኖት ያዟት)፡፡ የአላህን ፍጥረት መለወጥ የለም፡፡ ይህ ቀጥተኛ ሃይማኖት ነው፡፡ ግን አብዛኛዎቹ ሰዎች አያውቁም፡፡”❲Qūrān 30:30❳
-----------------------------------------------------
◌ስንቀጥል“ይህም ሆነ ያ የመርየም ልጅ ኢሣ ከተወላጅ ሰው በምን ተለየ?” የሚሉም አልጠፉም!ኢስማህ"عِصْمَة" የሚለው ቃል ሶምመ"صَمَّ" ከሚለው ስርወ ቃል የተገኘ ሲሆን "ከስህተት መጠበቅ"፣"መከልከል" ማለት ነው።የመርየም እናት የሆነችው ሐና መርየምን ባረገዘች ጊዜ እንዲህ ስትል ዱኣ አደረገች ለዚህም በቁርአን፦
فَلَمَّا وَضَعَتْهَا قَالَتْ رَبِّ إِنِّى وَضَعْتُهَآ أُنثَىٰ وَٱللَّهُ أَعْلَمُ بِمَا وَضَعَتْ وَلَيْسَ ٱلذَّكَرُ كَٱلْأُنثَىٰ ۖ وَإِنِّى سَمَّيْتُهَا مَرْيَمَ وَإِنِّىٓ أُعِيذُهَا بِكَ وَذُرِّيَّتَهَا مِنَ ٱلشَّيْطَٰنِ ٱلرَّجِيمِ
“በወለደቻትም ጊዜ፡- «ጌታዬ ሆይ! እኔ ሴት ኾና ወለድኋት፡፡» አላህም የወለደችውን ዐዋቂ ነው፡፡ «ወንድም እንደ ሴት አይደለም፡፡ እኔም መርየም ብዬ ስም አወጣሁላት፡፡ እኔም እስዋንም ዝርያዋንም ከተረገመው ሰይጣን በአንተ እጠብቃቸዋለሁ» አለች፡፡”❲Qūrān 3:36❳
“በንጹሕ አስተዳደር፣ግሩም ባሕርያት፣ በተቃዋሚዎች ላይ ጽኑ አቋም እና መረጋጋት (አስ-ሰኪናህ)፣ኢስማህ በፈጣሪ የተሰጠ መለኮታዊ ጸጋ ነው።”
▪ይህን ከአላህ ዘንድ የሚገኝ ነውና ኢሣን በተሰጠው ከሰይጣን የመጠበቅ ፀጋ ከሌሎች ፍጥረታት መለየት አንችልም ምክንያቱም በፀጋ ከፍጥረታት የተለዩ ብዙሀን ናቸው።
ለምሳሌ፦ሱለይማን❲﵇❳ በምድር ማንም ያላገኘውን ፀጋ አግኝተዋል ነገርግን ከፍጥረታት አንለያቸውም ፀጋው ከአላህ❲ﷻ❳ ነውና፤አደም❲﵇❳ ከኢሣ ባለፈ መልኩ እንኳን ተበጃጅተው ለመንካት ሰይጣንም ከአላህ እዝነት አልተገለለም ነበር ነገርግን አሁንም አደምን ከፍጥረታት አንለያቸውም ከነብያትም አንለያቸውም አልታዘዝንምና ለዚህም በቁርአን፦
ءَامَنَ ٱلرَّسُولُ بِمَآ أُنزِلَ إِلَيْهِ مِن رَّبِّهِۦ وَٱلْمُؤْمِنُونَ ۚ كُلٌّ ءَامَنَ بِٱللَّهِ وَمَلَٰٓئِكَتِهِۦ وَكُتُبِهِۦ وَرُسُلِهِۦ لَا نُفَرِّقُ بَيْنَ أَحَدٍۢ مِّن رُّسُلِهِۦ ۚ وَقَالُوا۟ سَمِعْنَا وَأَطَعْنَا ۖ غُفْرَانَكَ رَبَّنَا وَإِلَيْكَ ٱلْمَصِيرُ
“መልክተኛው ከጌታው ወደ ርሱ በተወረደው አመነ፡፡ ምእምኖቹም (እንደዚሁ)፡፡ ሁሉም በአላህ፣ በመላዕክቱም፣ በመጻሕፍቱም፣ በመልክተኞቹም ከመልክተኞቹ «በአንድም መካከል አንለይም» (የሚሉ ሲኾኑ) አመኑ፡፡ «ሰማን፤ ታዘዝንም፡፡ ጌታችን ሆይ! ምሕረትህን (እንሻለን)፡፡ መመለሻም ወዳንተ ብቻ ነው» አሉም።”❲Qūrān 2:285❳
-----------------------------------------------------
ማጠቃለያ❲Conclusion❳
▪የተፈጠርነው በእስልምና ሆኖ ሳለ ከመፈጠራችን ከጊዜያት በኋላ ከማህፀን ስትወጣ ሰይጣን ነካህና ስለነካህ ሙስሊም ተባልክ የስነ አመክንዮን❲Logic❳ የመጣረስ ዘመቻ ነው።
▪ሆኖም ኢሣ ኢብኑ መርየም ከአላህ ዘንድ የተሰጣቸውን ጥበቃ ጠምዝዞ አምላክነትን ያሳያል ማለት አያስኬድም።
-----------------------------------------------------
“አል-መሲሕ(እየሱስ) የአላህ ባሪያ ከመኾን ፈፅሞ አይጠየፍም...”❲ቁርአን 4:172❳ እናንተም ሆነ እኛ“ሳይጠሩት አቤት...” እንዲሉ ሳይታዘዙ ለአምላክነት እየሱስን መሾም ተገቢ አይደለም!
-----------------------------------------------------
ወሰላሙ አለይኩም
©ከወንድም አህመድ(አነፃፃሪው)
t.me/TheComparator
-----------------------------------------------------
◌ስንቀጥል ይህም ይሁን“ሙስሊሞች ለማምለጥ ሀዲሱን” ለሚሉ ክርስቲያን ተሟጋቾች በሙግት ህግ ለሚቀርብ ማስረጃ ማረጋገጫ በሌለው አፍን ሞልቶ መናገር ክልክል መሆኑን ዘንግተው አይደለም!ቢሆንም አኢሻ የዘገበችው ሀዲስ ላይ የተጠቀሰው አንቀፅ ማለትም“አዋቂን በድንጋይ መውገርና ጡት ማጥባት...” አንቀፅ ካለው ጥቅም አንፃር ጉዳቱ ስላመዘነ አላህ❲ﷻ❳ በንባብ❲ቲላዋ❳ ላይ አንቀፁ በመሻሩ አብሮም በግም ሆነ ፍየል በላው አልበላው በቁርአን ጥራዝ ላይ ሊከተብ አይችልም፤ስለዚህ ይህ አልተከተበም እና የቁርአን አንድ ክፍል ጠፍቷል❲Destructed❳ ብሎ ጮቤ መርገጥ አልባሌ ተግባር ነው።
وَإِذَا بَدَّلْنَآ ءَايَةًۭ مَّكَانَ ءَايَةٍۢ ۙ وَٱللَّهُ أَعْلَمُ بِمَا يُنَزِّلُ قَالُوٓا۟ إِنَّمَآ أَنتَ مُفْتَرٍۭ ۚ بَلْ أَكْثَرُهُمْ لَا يَعْلَمُونَ
“በአንቀጽም ስፍራ አንቀጽን በለወጥን ጊዜ አላህም የሚያወርደውን ነገር አዋቂ ነው፡፡ «አንተ ቀጣፊ እንጂ ሌላ አይደለህም» ይላሉ፡፡ በእውነቱ አብዛኞቻቸው አያውቁም፡፡”❲Qūrān 16:101❳
يَسْـَٔلُونَكَ عَنِ ٱلْخَمْرِ وَٱلْمَيْسِرِ ۖ قُلْ فِيهِمَآ إِثْمٌۭ كَبِيرٌۭ وَمَنَٰفِعُ لِلنَّاسِ وَإِثْمُهُمَآ أَكْبَرُ مِن نَّفْعِهِمَا ۗ وَيَسْـَٔلُونَكَ مَاذَا يُنفِقُونَ قُلِ ٱلْعَفْوَ ۗ كَذَٰلِكَ يُبَيِّنُ ٱللَّهُ لَكُمُ ٱلْءَايَٰتِ لَعَلَّكُمْ تَتَفَكَّرُونَ
“አእምሮን ከሚቃወም መጠጥና ከቁማር ይጠይቁሃል፡፡ «በሁለቱም ውስጥ ታላቅ ኃጢኣትና ለሰዎች ጥቅሞች አሉባቸው፡፡ ግን ኃጢኣታቸው ከጥቅማቸው በጣም ትልቅ ነው» በላቸው፡፡ ምንን እንደሚመጸውቱም (መጠኑን) ይጠይቁሃል፡፡ «ትርፍን (መጽውቱ)» በላቸው፡፡ እንደዚሁ ታስተነትኑ ዘንድ አላህ ለናንተ አንቀጾችን ይገልጽላችኋል፡፡”❲Qūrān 2:219❳
▪እንደ አልኮል እና ቁማር ሁሉ እደግመዋለሁ “አዋቂን በድንጋይ መውገርና ጡት ማጥባት...” አንቀፅ ካለው ጥቅም አንፃር ጉዳቱ ስላመዘነ አላህ❲ﷻ❳ በንባብ❲ቲላዋ❳ ላይ አንቀፁ በመሻሩ አብሮም በግም ሆነ ፍየል በላው አልበላው በቁርአን ጥራዝ ላይ ሊከተብ አይችልም!!!
-----------------------------------------------------
◌ስንሰልስ የቁርአን መወረድ በሆነ ጊዜ የነቢዩ ሙሀመድ❲ﷺ❳ ሰሀቢዮች በቃል ያጠኑት እንደነበር እሙን ነው፤አንድ ክፍል በቃል ተጠና[➾]ለፅሕፈት በቃ[➾]በግ በላችው ከዚህም በኋላ አይፃፍም ማለት ስነ አመክንዮ❲Logic❳ አያሟላም!ምክንያቱም ቀድመው እንደ ፃፉት ይፅፉታልና ስለዚህ“የቁርአን ሙሉ መፅሐፍ በሚፃፍ ጊዜ ክፍሉ ጠፍቷልና” እያሉ መዘባረቃችሁን ብታቆሙ!
-----------------------------------------------------
ማጠቃለያ❲Conclusion❳
▪ሙግት❲premise❳ አንድ ሀዲሱ ይሄ ነው የሚባል ማረጋገጫ የሆነ ማስረጃ የለውም፤ሙግት❲premise❳ ሁለት ሀዲሱ የተጣራ ብንለው እንኳ ጥቅሱ የተሻረ❲Abrogated❳ ወይም ነስኽ"نَسْخ" ስለሆነ ቢበላም አለማስፈለጉ፤ሙግት❲premise❳ ሦስት ቢያስፈልግ እንኳ ጥቅሱ ተመልሶ መፃፍ ይቻላል ስለዚህ ቁርአን በምንም ሁኔታ አልጠፋም።
-----------------------------------------------------
አላህ ቅኑን መንገድ እንዲመራችሁ፤መልካሙን መመለስ እንዲመልሳችሁ ዱዓ፣ፀሎታችን ነው።
-----------------------------------------------------
ወሰላሙ አለይኩም
©ከወንድም አህመድ(አነፃፃሪው)
t.me/TheComparator
የተበላው አንቀፅ?
በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ፥ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው❲بِسْمِ اللَّهِ الرَّحْمَٰنِ الرَّحِيم❳
مَا نَنسَخْ مِنْ ءَايَةٍ أَوْ نُنسِهَا نَأْتِ بِخَيْرٍۢ مِّنْهَآ أَوْ مِثْلِهَآ ۗ أَلَمْ تَعْلَمْ أَنَّ ٱللَّهَ عَلَىٰ كُلِّ شَىْءٍۢ قَدِيرٌ
“ከአንቀጽ ብንለውጥ ወይም እርሷን ብናስረሳህ ከርሷ የሚበልጥን ወይም ብጤዋን እናመጣለን፤ አላህ በነገሩ ሁሉ ላይ ከሃሊ (ቻይ) መኾኑን አታውቅምን?”❲Qūrān 2:106❳
-----------------------------------------------------
መግቢያ❲Introduction❳
▪ማንም ያልደፈረው ከባለቤቱ ዋስትና ያለውን ቁርአንን የጠፉ ክፍሎች አሉት በማለት ለብዙዎች የክፍርና መንገድ ጠርገዋል!ለዚህ “በሬ ወለደ” መሰል ለጆሮ የማይጥም ዲስኩር ይዘው አዛ ማድረጉን ከያዙት ሰነባብተዋል፤ለዚህም ቱሪናፋነታቸው መልስ እንዲሆን ጥርስና ምላሱን እየያዝን እየነቀዝን እንቃኝ።
-----------------------------------------------------
▪አላህ❲ﷻ❳ ለነብያችን❲ﷺ❳ ቁርአንን ሲያወርድ ለዚህ ለአላህ ፈራህያን መመሪያ የሆነው ኪታብ የጥበቃ ዋስትና ሰጥቶታል፤ይህም የጥበቃ ዋስትና ያለው መመሪያ ሆኖ ከአላህ ዘንድ ሊወረድ ችሏል፦
إِنَّا نَحْنُ نَزَّلْنَا ٱلذِّكْرَ وَإِنَّا لَهُۥ لَحَٰفِظُونَ
“እኛ ቁርኣንን እኛው አወረድነው፡፡ እኛም ለእርሱ ጠባቂዎቹ ነን፡፡”❲Qūrān 15:9❳
ۛ هُدًۭى لِّلْمُتَّقِينَ
“ለፈራህያን መሪ ነው፡፡”❲Qūrān 2:2❳
-----------------------------------------------------
ነስኽ"نَسْخ" የሚለው ቃል"መሻር" ከሚለው የአማርኛ አቻ ትርጉም ሊተረጎም ይቻላል።ነስኽ የቁርአን መለኮታዊ አመጣጥ ማስረጃ ነው ማለትም እንችላለን ምክንያቱም አላህ በተለያዩ ጊዜያት ውስጥ ሊተገበሩ የሚችሉ ተገቢ ህጎችን በማውጣቱ እስልምና በሁሉም ጊዜ፣ ቦታዎች እና ሰዎች ላይ ተፈፃሚ እንዲሆን የሚያደርግ የፈጣሪን ጥበብ ያንፀባርቃል።
▪መሻር የሚከሰተው በአላህ❲ﷻ❳ ፈቃድ እና ጥበብ ነው፣ እሱም ሰዎች የሚያስፈልጋቸውን በሚፈልጉበት ቅጽበት ያውቃል። በተለያዩ መለኮታዊ መጻሕፍት ጥቅሶች መካከል በወረዱት ማለትም በተውራት❲ኦሪት❳ በመዝሙረ ዳዊት❲ዘቡር❳ በወንጌል❲ኢንጅል❳ ውስጥ ሊከሰት ይችላል፤ለምሳሌ፦
▪ለአይሁዳውያን ሰንበትን ቅዳሜ ሲፈፅሙ፣ክርስቲያኖች እሁድ ያደርጉታል እኛ የነብያችን❲ﷺ❳ ኡማዎች ሶላት አል ጁሙአ በአርብ እንሰግዳለን ለዚህም ነው“መሻር የሚከሰተው በአላህ❲ﷻ❳ ፈቃድ እና ጥበብ ነው...”ያልኩት ምክንያቱም አንድ እና ግትር የሆኑ ህጎች ቢኖሩ ለዘመናችን ሰዎች ይቅርና ቀደምት ሙስሊሞች በሕይወታቸው ውስጥ የሱን መመሪያ ለመከተል በጣም ከባድ ሊሆን ይችል ነበር፤ለዚህም ቁርአን፦
وَأَنزَلْنَآ إِلَيْكَ ٱلْكِتَٰبَ بِٱلْحَقِّ مُصَدِّقًۭا لِّمَا بَيْنَ يَدَيْهِ مِنَ ٱلْكِتَٰبِ وَمُهَيْمِنًا عَلَيْهِ ۖ فَٱحْكُم بَيْنَهُم بِمَآ أَنزَلَ ٱللَّهُ ۖ وَلَا تَتَّبِعْ أَهْوَآءَهُمْ عَمَّا جَآءَكَ مِنَ ٱلْحَقِّ ۚ لِكُلٍّۢ جَعَلْنَا مِنكُمْ شِرْعَةًۭ وَمِنْهَاجًۭا ۚ وَلَوْ شَآءَ ٱللَّهُ لَجَعَلَكُمْ أُمَّةًۭ وَٰحِدَةًۭ وَلَٰكِن لِّيَبْلُوَكُمْ فِى مَآ ءَاتَىٰكُمْ ۖ فَٱسْتَبِقُوا۟ ٱلْخَيْرَٰتِ ۚ إِلَى ٱللَّهِ مَرْجِعُكُمْ جَمِيعًۭا فَيُنَبِّئُكُم بِمَا كُنتُمْ فِيهِ تَخْتَلِفُونَ
“ወደ አንተም መጽሐፉን ከበፊቱ ያለውን መጽሐፍ አረጋጋጭና በእርሱ ላይ ተጠባባቂ ሲኾን በእውነት አወረድን፡፡ በመካከላቸውም አላህ ባወረደው ሕግ ፍረድ፡፡ እውነቱም ከመጣልህ በኋላ ዝንባሌዎቻቸውን አትከተል፡፡ ከእናንተ ለሁሉም ሕግንና መንገድን አደረግን፡፡ አላህም በሻ ኖሮ አንድ ሕዝብ ባደረጋችሁ ነበር፡፡ ግን በሰጣችሁ ሕግጋት ሊሞክራችሁ (ለያያችሁ)፡፡ በጎ ሥራዎችንም (ለመሥራት) ተሽቀዳደሙ፤ መመለሻችሁ በጠቅላላ ወደ አላህ ነው፡፡ በእርሱም ትለያዩበት የነበራችሁትን ነገር ይነግራችኋል፡፡”❲Qūrān 5:48❳
▪ሆኖም ይህ ህግጋትን የመተግበር ሂደት ከጊዜ፣ሁኔታ አንፃር አመቺ መልኩ ለመፍጠር አላህ አንቀፆችን ይሽራል፤ከርሱ የተሻለውንም ይተካል!
مَا نَنسَخْ مِنْ ءَايَةٍ أَوْ نُنسِهَا نَأْتِ بِخَيْرٍۢ مِّنْهَآ أَوْ مِثْلِهَآ ۗ أَلَمْ تَعْلَمْ أَنَّ ٱللَّهَ عَلَىٰ كُلِّ شَىْءٍۢ قَدِيرٌ
“ከአንቀጽ ብንለውጥ ወይም እርሷን ብናስረሳህ ከርሷ የሚበልጥን ወይም ብጤዋን እናመጣለን፤ አላህ በነገሩ ሁሉ ላይ ከሃሊ (ቻይ) መኾኑን አታውቅምን?”❲Qūrān 2:106❳
-----------------------------------------------------
◌ይህን በወፍ በረር እይታ ካየን አላህ❲ﷻ❳ ለቁርአን ዋስትና ሲሰጥ ከመበረዝ❲Corruption❳ ከመጥፋት❲Destruction❳ ጭምር ነው፤ነገርግን ከዲናችን ሙዕሚኖችን ለማስፈንገጥ ይህን ሀዲስ ያነሳሉ በሱነን ኢብን ማጃህ ቅፅ.3 መፅሐፍ.9 ሀዲስ.1944 ላይ፦
حَدَّثَنَا أَبُو سَلَمَةَ، يَحْيَى بْنُ خَلَفٍ حَدَّثَنَا عَبْدُ الأَعْلَى، عَنْ مُحَمَّدِ بْنِ إِسْحَاقَ، عَنْ عَبْدِ اللَّهِ بْنِ أَبِي بَكْرٍ، عَنْ عَمْرَةَ، عَنْ عَائِشَةَ، . وَعَنْ عَبْدِ الرَّحْمَنِ بْنِ الْقَاسِمِ، عَنْ أَبِيهِ، عَنْ عَائِشَةَ، قَالَتْ لَقَدْ نَزَلَتْ آيَةُ الرَّجْمِ وَرَضَاعَةُ الْكَبِيرِ عَشْرًا وَلَقَدْ كَانَ فِي صَحِيفَةٍ تَحْتَ سَرِيرِي فَلَمَّا مَاتَ رَسُولُ اللَّهِ ـ ﷺ ـ وَتَشَاغَلْنَا بِمَوْتِهِ دَخَلَ دَاجِنٌ فَأَكَلَهَا .
አኢሻ (ረዐ) እንዳስተላለፉት፡-
“አዋቂን በድንጋይ መውገርና ጡት ማጥባት የሚለው አንቀጽ ወረዷል ወረቀቱም ከእኔ ትራስ ስር ነበር። የአላህ መልእክተኛ (ﷺ) ሲሞቱ እኛ በእርሳቸው ሞት ተዋክበን አንዲት ለማዳ በግ ገብታ በላችው።”❲Sunan Ibn Majah Vol. 3 Book 9 Hadith № 1944❳
◌ሲጀመር ይህ የአኢሻ ላይ የ“በግ ገብታ በላችው” ዘገባ ከሌሎች ተመሳሳይ የሀዲስ ዘገባዎች አንፃር ስንመልከት በኢማሙ ማሊክ የሀዲስ ስብስብ ስራ የሆነው"አል-ሙወታዕ" ኪታብ አል-ሪዷዕ"كِتَاب الرِضَاع" ቅፅ 30 ሀዲስ 17 ላይ በኢማሙ ማሊክ፤በዚህ ተመስርቶ በኢማሙ ሙስሊም የሀዲስ ስብስብ ስራ በሶሒሕ አል ሙስሊም ሀዲስ 1452 ላይ በያህያ ኢብኑ ሰኢድ አል-አንሷሪ፤በኢማሙ አህመድ የሀዲስ ስብስብ ስራ "ሙስነድ"...ስለ እነዚህ የተሻሩ ትዕዛዛት የሚናገሩ ዘገባዎች ቢሆኑም እንኳ ስለ የቤት እንስሳ አለመግለፃቸው ብሎም በአውደ ምንባቡ"Contextual Passage" አለማካተታቸው ሀዲሱን ተጓዳኝ የሌለው ደካማ ሀዲስ ወይም ደኢፍ ያደርገዋል።
ኢሣ ነውን?
በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ፥ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው❲بِسْمِ اللَّهِ الرَّحْمَٰنِ الرَّحِيم❳
ٱللَّهُ لَآ إِلَٰهَ إِلَّا هُوَ ۚ وَعَلَى ٱللَّهِ فَلْيَتَوَكَّلِ ٱلْمُؤْمِنُونَ
“አላህ ከርሱ በቀር አምላክ የለም፤ በአላህም ላይ አማኞቹ ይመኩ።”❲Qūrān 64:13❳
-------------------------------------------
መግቢያ❲Introduction❳
▪ዘመነኛ አዋቂ ነን ባዮች ከራሳቸው የቀን ከሌት ውርደት አልፎ “አተርፍ ባይ አጉዳይ” እንዲሉ ጭራሽኑ ቁርአንን ይዘው መቦዘን በማያውቁት ነገር ማላዘን ከጀመሩ ሰነባብተዋል “ስራ ለሰሪው...” እንዲሉ የሚከተለውንም የቁርአን አንቀፅ በማስከተል ያለኝን ማካፈል ልጀምር፦
لَّن يَسْتَنكِفَ ٱلْمَسِيحُ أَن يَكُونَ عَبْدًۭا لِّلَّهِ
“አልመሲሕ (ኢየሱስ) ለአላህ ባሪያ ከመኾን ፈጽሞ አይጠየፍም።”❲Qūrān 4:172❳
-------------------------------------------
▪በሱረት አል-ተውባህ 9:31 ላይ የሚገኘውን የኢሣን ማንነት በሚያብራራ የቁርአን አንቀፅ ላይ፦
ٱتَّخَذُوٓا۟ أَحْبَارَهُمْ وَرُهْبَٰنَهُمْ أَرْبَابًۭا مِّن دُونِ ٱللَّهِ وَٱلْمَسِيحَ ٱبْنَ مَرْيَمَ وَمَآ أُمِرُوٓا۟ إِلَّا لِيَعْبُدُوٓا۟ إِلَٰهًۭا وَٰحِدًۭا ۖ لَّآ إِلَٰهَ إِلَّا هُوَ ۚ سُبْحَٰنَهُۥ عَمَّا يُشْرِكُونَ
“ከእርሱ በቀር ሌላ አምላክ የሌለውን አንድን አምላክ ሊገዙ እንጂ ያልታዘዙ ሲኾኑ ሊቃውንቶቻቸውንና መነኮሳታቸውን፣ የመርየምን ልጅ አልመሲሕንም ከአላህ ሌላ አማልክት አድርገው ያዙ፡፡ ከሚያጋሩት ሁሉ የጠራ ነው።”❲Qūrān 9:31❳
◌ስንጀምር በዚህ የቁርአን አንቀፅ ላይ ኢትተኸዙ"ٱتَّخَذُوٓا۟" ማለትም "ያዙ" እያለ በሶስተኛ መደብ❲الشَّخْصُ الثَّالِثُ❳ በሀላፊ ጊዜ❲الْمَاضِي❳ የሚናገር ግስ❲فَعَلَ❳ ሲሆን ሆኖም ይህ ቃል አሕባረሁም"أحْبَارَهُم" ከሚለው ተሳቢ ተውላጠ ስም❲حَالَةُ النَّصْبِ❳ መምጣቱ የመፅሐፉ ባለቤቶች፣የክርስቲያን መነኮሳት እና ሊቃውንት አምላክ አድርገው ስለያዙት ማንነት እያመላከተ ነው።
◌ስንቀጥል የአንቀፁ አረፍተነገር ቀጠል ብሎ ሚን"من" ከሚል መስተዋድድ❲حَرَفَ الْجَرّ❳ ቀጥሎ አላህ"اللَّهِ" በሚል አገናዛቢ❲الجَر❳ መምጣቱ አላህን እነሱ አምላክ አድርገው ከያዙት የተለየ ያደርገዋል።
ለምሳሌ፦
“የአነፃፃሪው መጣጥፍ” ብዬ ስናገር የ- የሚለው መስተዋድድ መነሻ ቅጥያ ሆኖ መምጣቱ አነፃፃሪው የመጣጥፉ ባለቤት የሆነ ከመጣጥፉ የሚለይ ህላዌ ያለው ማንነት መሆኑን ሲያስጨብጥ፤ልክ እንደዚሁ ሁሉ ክርስቲያኖች አምላክ አድርገው የያዙት ማንነት እና አላህ ሚን"مِن" በሚል መስተዋድድ❲حَرَفَ الْجَرّ❳ መለየቱ አላህን በአውደ ምንባቡ❲Contextual Passage❳ ከተገለፀው ኢየሱስ❲اَلْمَسِيحَ ٱبْنَ مَرْيَم❳ ይለየዋል።
◌ስንሰልስ አላህ"اللَّهِ" ከሚለው ቀጥሎ ወ"وَ" በሚል መስተፃምር"Conjunction" ወልመሲሀ-ኢብነ-መርየም"اَلْمَسِيحَ ٱبْنَ مَرْيَم" መምጣቱ የአማርኛ አቻ ትርጉሙን ከ“የመርየምን ልጅ አልመሲሕንም ከአላህ ሌላ አማልክት አድርገው ያዙ፡፡” ወደ “አላህን እና የመርየምን ልጅ አልመሲሕንም” በማለት አይተረጎምም!
▪ምክንያቱም ሁወ"هُو" ማለትም "እርሱ" የሚለው ቃል በሶስተኛ መደብ❲الشَّخْصُ الثَّالِثُ❳ ለአንድ ማንነት ከሱም አልፎ ለአላህ መግባቱ ኢሣን ከዚህ አያጠቃልለውም፤ሆኖም ይህን ሚዛን የማይደፋ ሙግት ይዞ ያዙኝ ልቀቁኝ ፍፁም የለየለት ጤና ማጣት ነው።
-------------------------------------------
αυτη δε εστιν η αιωνιος ζωη ινα γινωσκωσιν σε τον μονον αληθινον θεον και ον απεστειλας ιησουν χριστον
“እውነተኛ አምላክ ብቻ የሆንህ አንተን የላክኸውንም ኢየሱስ ክርስቶስን ያውቁ ዘንድ ይህች የዘላለም ሕይወት ናት።”❲የዮሐንስ ወንጌል 17፥3❳
◌ስንረብብ ይህን ጥቅስ በአንፃራዊነት ብናየው እራሱ በዚህ ጥቅስ ላይ አሌቲኖን"αληθινον" የሚለው ቃል ቴኦን"θεον" ለሚለው ስም❲Noun❳ ገላጭ❲Adjective❳ ሆኖ ሲመጣ ካይ"καὶ" በሚል መስተፃምር❲Conjunction❳ “ὃν ἀπέστειλας Ἰησοῦν Χριστόν.”|“ሖን አፐስቴይላስ ኤስኡን ኽሪስቶን”
“የላክኸውንም ኢየሱስ ክርስቶስን...”በማለት ይለያያቸዋል።
▪ምክንያቱም፦
αλλ ημιν εις θεος ο πατηρ εξ ου τα παντα και ημεις εις αυτον και εις κυριος ιησους χριστος δι ου τα παντα και ημεις δι αυτου
“ለእኛስ ነገር ሁሉ ከእርሱ የሆነ እኛም ለእርሱ የሆንን አንድ አምላክ አብ አለን፥ ነገር ሁሉም በእርሱ በኩል የሆነ እኛም በእርሱ በኩል የሆንን አንድ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ አለን።”❲1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 8፥6❳
ማጠቃለያ❲Conclusion❳
▪ሆነም ቀረ አወቅን ከሚሉ የቁም ቅዠት ከዋጣቸው መሪዎቻችሁ ገለል በሉና የዘልአለማዊ ህይወት መንገድን ፈልጉ አለማወቅ አይተርፍም!
▪እውነት እንደ ቅንድብ እናንተም እንደ አይናችሁ ሳትተያዩ ፈጣሪ እንዳይወስዳችሁ ለመንኩ...ቅኑን መንገድ ይምራችሁ።
-------------------------------------------
ትርጉም አልባ የሆነን መንገድ መምረጣቹ ሳያንስ ስህተት አለባችሁ ማለት “ሙት መውቀስ፤ድንጋይ መንከስ”እንዲሉ ለውጥ የሌለው ጊዜ ፈጅ ሂደት ነው፤አላህ❲ﷻ❳ሂዳያን ይስጣችሁ።
-------------------------------------------
ወሰላሙ አለይኩም
©ከወንድም አህመድ(አነፃፃሪው)
t.me/TheComparator
▪ይህች መንገድ ደግሞ የእግዚአብሔር መንገድ ብሎ የዘረጋት የሰዎች መንገድ ነች፤ስለዚህም ነው፦
כִּֽי־גָבְה֥וּ שָׁמַ֖יִם מֵאָ֑רֶץ כֵּ֣ן גָּבְה֤וּ דְרָכַי֙ מִדַּרְכֵיכֶ֔ם וּמַחְשְׁבֹתַ֖י מִמַּחְשְׁבֹתֵיכֶֽם
“ሰማይ ከምድር ከፍ እንደሚል፥ እንዲሁ መንገዴ ከመንገዳችሁ አሳቤም ከአሳባችሁ ከፍ ያለ ነው።”❲ትንቢተ ኢሳይያስ 55፥9❳
▪አዎ ነች በትንቢተ ኢሳይያስ ምዕ55፥9 ላይ ደራካይ "דְרָכַי֙" ማለትም የኔ መንገድ ብሎ የገለፀው በትንቢተ ኤርሚያስ ምዕ6፥16 ላይ ደረኽ "דֶּרֶךְ" ማለትም "መንገድ" ከሚለው የቃል ስር የተገኘ ሲሆን እግዚአብሔር መንገድ የሚለው ትክክለኛውና ነብያት የሄዱበት መንገድ መሆኑን ማስገንዘቡ ነገሩን እንድናስተውል ቀልባችንን ይስበዋል፤ሆኖም በዚህ መንገድ ላይ መሪው አምላክ ነው፦
ٱهْدِنَا ٱلصِّرَٰطَ ٱلْمُسْتَقِيمَ
“ቀጥተኛውን መንገድ ምራን፡፡”❲Qūrān 1:6❳
▪ይህንም ተደግፎ ባይብል፦
לֵ֣ב אָ֭דָם יְחַשֵּׁ֣ב דַּרְכּ֑וֹ וַֽ֝יהוָ֗ה יָכִ֥ין צַעֲדֽוֹ
“የሰው ልብ መንገዱን ያዘጋጃል፤ እግዚአብሔር ግን አካሄዱን ያቀናለታል።”❲መፅሐፈ ምሳሌ 16፥9❳
▪ይህችን መንገድ ህግን እስካልጠበክ አትሄድባትም ምክንያቱም ለመንገድህ ታዛዥ መሆን አለብህ፦
נֵר־לְרַגְלִ֥י דְבָרֶ֑ךָ וְ֝א֗וֹר לִנְתִיבָתִֽי
“ሕግህ ለእግሬ መብራት፥ ለመንገዴ ብርሃን ነው።”❲መዝሙረ ዳዊት 119፥105❳
▪ኢየሱስም ይህን ተመስርቶ፦
εαν αγαπατε με τας εντολας τας εμας τηρησατε
“ብትወዱኝ ትእዛዜን ጠብቁ።❲ዮሐንስ ወንጌል 14፥15❳
▪ምክንያቱም ትዕዛዙ ከፈጣሪው ነውና፦
οτι εγω εξ εμαυτου ουκ ελαλησα αλλ ο πεμψας με πατηρ αυτος μοι εντολην εδωκεν τι ειπω και τι λαλησω
“እኔ ከራሴ አልተናገርሁምና፤ ነገር ግን የላከኝ አብ እርሱ የምለውን የምናገረውንም ትእዛዝ ሰጠኝ።”❲ዮሐንስ ወንጌል 12፥49❳
ማጠቃለያ(Conclusion)
▪ኢየሱስ፣ነብያት፣የእግዚአብሔር ቧለሟሎች የሄዱበት መንገድ ክርስትና አልነበረም፤ስላልተጓዙበትም ክርስቲያን አልተባሉም ነገርግን አንድ ነገር አለ...
▪ይህ መንገድ የፈጣሪን ትዕዛዛት ብሎም ህግጋት መተግበር ከሆነ ይህም “ለፈጣሪ ፍቃድ ራስን መስጠት” ከነበር እኚህ አካላት ሙስሊሞች ነበሩ።
-------------------------------------------
ወገኖቻችን እኛ ከአላህ፣ለአላህ ብሎም ወደ አላህ ነን በሰዎች ጉባኤ ተመስርቶ በሰዎች ጉባኤ በሚበታተን እምነት ከሚኖሩ ኖረውበትም ከሚሞቱ በመሆን የጀሀነም ዘውታሪ አትሁኑ፤በዱዓችን ከናንተ ጋር ነን እንሆናለንም ኢንሻአላህ።
-------------------------------------------
ወሰላሙ አለይኩም
©ከወንድም አህመድ(አነፃፃሪው)
t.me/TheComparator
መልካሚቱ መንገድ
በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ፥ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው❲بِسْمِ اللَّهِ الرَّحْمَٰنِ الرَّحِيم❳
أَلَا لِلَّهِ ٱلدِّينُ ٱلْخَالِصُ ۚ وَٱلَّذِينَ ٱتَّخَذُوا۟ مِن دُونِهِۦٓ أَوْلِيَآءَ مَا نَعْبُدُهُمْ إِلَّا لِيُقَرِّبُونَآ إِلَى ٱللَّهِ زُلْفَىٰٓ إِنَّ ٱللَّهَ يَحْكُمُ بَيْنَهُمْ فِى مَا هُمْ فِيهِ يَخْتَلِفُونَ ۗ إِنَّ ٱللَّهَ لَا يَهْدِى مَنْ هُوَ كَٰذِبٌۭ كَفَّارٌۭ
“ንቁ! ፍጹም ጥሩ የኾነው ሃይማኖት የአላህ ብቻ ነው፡፡ እነዚያም ከእርሱ ሌላ (ጣዖታትን) ረዳቶች የያዙት «ወደ አላህ ማቃረብን እንዲያቀርቡን እንጅ ለሌላ አንገዛቸውም» (ይላሉ)፡፡ አላህ በዚያ እነርሱ በእርሱ በሚለያዩበት ነገር በመካከላቸው ይፈርዳል፡፡ አላህ እርሱ ውሸታም ከሓዲ የኾነን ሰው አያቀናም።”❲Qūrān 39:3❳
-------------------------------------------
መግቢያ❲Introduction❳
ኢስላም "إسْلَٰم" የሚለው ቃል አል-ሲልም "السِلْم" ከሚል ስርወ-ቃል የተገኘ ሲሆን "መታዘዝ፣እጅ መስጠት" የሚል ትርጉም ይይዛል፤ይህ "ለአላህ❲ﷻ❳ ፍቃድ እጅ መስጠት" የሆነውን ሃይማኖት በነብያችን ሙሀመድ❲ﷺ❳የተጠነሰሰ ነው በማለት ሚሽነሪዎች ይህን ጥቅስ ያነሳሉ፦
لَا شَرِيكَ لَهُۥ ۖ وَبِذَٰلِكَ أُمِرْتُ وَأَنَا۠ أَوَّلُ ٱلْمُسْلِمِينَ
«ለእርሱ ተጋሪ የለውም፡፡ በዚህም (በማጥራት) ታዘዝኩ፡፡ እኔም የሙስሊሞች መጀመሪያ ነኝ» (በል)።❲Qūrān 6:163❳
◌ሲጀመር በዚህ ጥቅስ ላይ የሙስሊሞች መጀመሪያ "أَوَّلُ ٱلْمُسْلِمِينَ" አውወሉል-ሙስሊሚን ብሎ የተቀመጠው ከጥቅሱ አውደ ምንባብ❲Contextual Passage❳ነብያችን ሙሀመድ❲ﷺ❳የሙስሊሞች መጀመሪያ የተባሉት ትዕዛዝ ከመቀበል አንፃር ከዚህ ኡማ የመጀመሪያ በመሆናቸው ነው ለዚህም ነው ቁርአን፦
قُلْ أَغَيْرَ ٱللَّهِ أَتَّخِذُ وَلِيًّۭا فَاطِرِ ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلْأَرْضِ وَهُوَ يُطْعِمُ وَلَا يُطْعَمُ ۗ قُلْ إِنِّىٓ أُمِرْتُ أَنْ أَكُونَ أَوَّلَ مَنْ أَسْلَمَ ۖ وَلَا تَكُونَنَّ مِنَ ٱلْمُشْرِكِينَ
“«ሰማያትንና ምድርን ፈጣሪ ከኾነው አላህ እርሱ የሚመግብ የማይመገብም ሲኾን ሌላን አምላክ እይዛለሁን» በላቸው፡፡«እኔ መጀመሪያ ትእዛዝን ከተቀበለ ሰው ልኾን ታዘዝኩ፡፡ ከአጋሪዎችም ፈጽሞ አትኹን (ተብያለሁ)»በላቸው፡፡”❲Qūrān 6:14❳
◌ሲቀጥል ይህ ትዕዛዝ የጠራ ሲሆን ለአጥሪዎችም ጭምር የተሰጠ ነው ቁርአንም ይህን አስረግጦ፦
َلَا لِلَّهِ ٱلدِّينُ ٱلْخَالِصُ ۚ
“ንቁ! ፍጹም ጥሩ የኾነው ሃይማኖት የአላህ ብቻ ነው፡፡”❲Qūrān 39:3❳
▪በዚህ የቁርአን አንቀፅ ላይ "ፍፁም-ጥሩ"ለሚለው ቃል አል-ኻሊሡ "الْخَالِصُ" የሚለው የአረቢኛ ቃል የገባ ሲሆን ኸለሰ "خَلَصَ"ከሚል የቃል ሥር የተገኘ ነው ይህም "አጠራ"የሚለውን ትርጓሜ ይይዛል በዚሁ መልኩ በሌላው የቁርአን አንቀፅ፦
وَمَآ أُمِرُوٓا۟ إِلَّا لِيَعْبُدُوا۟ ٱللَّهَ مُخْلِصِينَ لَهُ ٱلدِّينَ حُنَفَآءَ وَيُقِيمُوا۟ ٱلصَّلَوٰةَ وَيُؤْتُوا۟ ٱلزَّكَوٰةَ ۚ وَذَٰلِكَ دِينُ ٱلْقَيِّمَةِ
“አላህን ሃይማኖትን ለእርሱ ብቻ አጥሪዎች፣ ቀጥተኞች ኾነው ሊግገዙት፣ ሶላትንም አስተካክለው ሊሰግዱ ዘካንም ሊሰጡ እንጅ ያልታዘዙ ሲኾኑ (ተለያዩ)፡፡ ይህም የቀጥተኛይቱ (ሃይማኖት) ድንጋጌ ነው፡፡”❲Qūrān 98:5❳
▪በዚህ የቁርአን አንቀፅ አጥሪዎች ለሚለው ሙኽሊሲን "مُخْلِصِين" የሚል የአረቢኛ ቃል የተጠቀመ ሲሆን የ ሙኽሊስ "مُخْلِص"ብዙ ቁጥር(Plural Form)ሲሆን ነው፤
ቁርአን "ኢስላምን" ለመግለጽ በአውደ ምንባቡ(Contextual Passage)ይህን ቃል ተጠቅሞበታል።
إِلَّا ٱلَّذِينَ تَابُوا۟ وَأَصْلَحُوا۟ وَٱعْتَصَمُوا۟ بِٱللَّهِ وَأَخْلَصُوا۟ دِينَهُمْ لِلَّهِ فَأُو۟لَٰٓئِكَ مَعَ ٱلْمُؤْمِنِينَ ۖ وَسَوْفَ يُؤْتِ ٱللَّهُ ٱلْمُؤْمِنِينَ أَجْرًا عَظِيمًۭا
“እነዚያ የተመለሱ (ሥራቸውን) ያሳመሩም፤ በአላህም የተጠበቁ፤ ሃይማኖታቸውንም ለአላህ ፍጹም ያደረጉ ሲቀሩ፡፡ እነዚያስ ከምእምናን ጋር ናቸው፡፡ ለምእምናንም አላህ ታላቅን ምንዳ በእርግጥ ይሰጣል፡፡”❲Qūrān 4:146❳
▪በዚህም አንቀፅ ላይ በብዙ ቁጥር ሶስተኛ መደብ "እነርሱ" ማለትም አኽለሱ "أخْلَصُو" ያሳምራሉ እያለ የሚገልጸው ሙስሊም ምዕመናንን ከሆነ ነብያት አማኝ ናቸው ስለዚህ የነብያችን ሙሀመድ❲ﷺ❳ሃይማኖት ከቀደምት ነብያት አይለይም፦
ءَامَنَ ٱلرَّسُولُ بِمَآ أُنزِلَ إِلَيْهِ مِن رَّبِّهِۦ وَٱلْمُؤْمِنُونَ ۚ كُلٌّ ءَامَنَ بِٱللَّهِ وَمَلَٰٓئِكَتِهِۦ وَكُتُبِهِۦ وَرُسُلِهِۦ لَا نُفَرِّقُ بَيْنَ أَحَدٍۢ مِّن رُّسُلِهِۦ ۚ وَقَالُوا۟ سَمِعْنَا وَأَطَعْنَا ۖ غُفْرَانَكَ رَبَّنَا وَإِلَيْكَ ٱلْمَصِيرُ
“መልክተኛው ከጌታው ወደ ርሱ በተወረደው አመነ፡፡ ምእምኖቹም (እንደዚሁ)፡፡ ሁሉም በአላህ፣ በመላዕክቱም፣ በመጻሕፍቱም፣ በመልክተኞቹም ከመልክተኞቹ «በአንድም መካከል አንለይም» (የሚሉ ሲኾኑ) አመኑ፡፡ «ሰማን፤ ታዘዝንም፡፡ ጌታችን ሆይ! ምሕረትህን (እንሻለን)፡፡ መመለሻም ወዳንተ ብቻ ነው» አሉም።”❲Qūrān 2:285❳
-------------------------------------------
➢ነገርግን “የራሷ እያረረ...” እንዲሉ መፅሐፍ ቅዱስን የስራቸው ደብቀው እያሞቁ ለመክረም ቢታትሩም ባይብል፦
και ευρων αυτον ηγαγεν αυτον εις αντιοχειαν εγενετο δε αυτους ενιαυτον ολον συναχθηναι εν τη εκκλησια και διδαξαι οχλον ικανον χρηματισαι τε πρωτον εν αντιοχεια τους μαθητας χριστιανους
“ባገኘውም ጊዜ ወደ አንጾኪያ አመጣው። በቤተ ክርስቲያንም አንድ ዓመት ሙሉ ተሰበሰቡ፥ ብዙ ሕዝብንም አስተማሩ፤ ደቀ መዛሙርትም መጀመሪያ በአንጾኪያ ክርስቲያን ተባሉ።”❲የሐዋርያት ስራ 11፥26❳
◌ሲሠልስ ይህ ክርስትና የተሾመ ከሆነ በመፅሐፍ ቅዱስ የነበሩ የእግዚአብሔር ነብያት ምንድን ነበሩ?
כֹּ֣ה אָמַ֣ר יְהוָ֡ה עִמְדוּ֩ עַל־דְּרָכִ֨ים וּרְא֜וּ וְשַׁאֲל֣וּ׀ לִנְתִב֣וֹת עוֹלָ֗ם אֵי־זֶ֨ה דֶ֤רֶךְ הַטּוֹב֙ וּלְכוּ־בָ֔הּ וּמִצְא֥וּ מַרְגּ֖וֹעַ לְנַפְשְׁכֶ֑ם וַיֹּאמְר֖וּ לֹ֥א נֵלֵֽךְ
“እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ በመንገድ ላይ ቁሙ ተመልከቱም፥ የቀደመችውንም መንገድ ጠይቁ፤ መልካሚቱ መንገድ ወዴት እንደ ሆነች እወቁ፥ በእርስዋም ላይ ሂዱ፥ ለነፍሳችሁም ዕረፍት ታገኛላችሁ፤ እነርሱ ግን፦ አንሄድባትም አሉ።”❲ትንቢተ ኤርምያስ 6፥16❳
