ch
Feedback
ASTU Network ®️

ASTU Network ®️

前往频道在 Telegram

🛜 ASTU Network ®️ ➲ Join us || @ASTU_Network || || @ASTU_Network_Group || 📚 Library: @ASTU_Network_Library 👁‍🗨 We are here to keep you updated! ➲ Admin 📩 👤 @NS_Nazu Ⓝ Ŋazarene Ŝon [🥷] |➲| @ASTU_Network

显示更多
4 847
订阅者
+824 小时
+587
+31330
帖子存档
#Ethiopia 🇪🇹 — the land of diverse societies and cultures! 🤗😁 .
#Ethiopia 🇪🇹 — the land of diverse societies and cultures! 🤗😁 .

መስከረም 8 ቀን 2018 ዓ.ም ሁሉም ተማሪ ዩኒቨርስቲ የሚገባበት እለት መሆኑ ተነገረ መስከረም 8 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ የቀጣዩ አመት የዩኒቨርስቲ ት/ት ይጀመራል ሲል ትምህርት ሚኒስቴር አስታው
መስከረም 8 ቀን 2018 ዓ.ም ሁሉም ተማሪ ዩኒቨርስቲ የሚገባበት እለት መሆኑ ተነገረ መስከረም 8 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ የቀጣዩ አመት የዩኒቨርስቲ ት/ት ይጀመራል ሲል ትምህርት ሚኒስቴር አስታውቋል። የዘንድሮው የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ የፈተና ውጤት ጳጉሜ ላይ ይፋ ይሆናል በማለት እስከዚያም ድረስ የሚቆየው ፈተና ያልወሰዱና በመጪው ነሐሴ ወር ለፈተና የሚቀመጡ ቀሪ ተፈታኝ ተማሪዎች በመኖራቸው መሆኑን የትምህርት ሚኒስትሩ ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ ተናግረዋል። በተለያየ ምክንያት ዘግይተው ትምህርት የጀመሩ በመኖራቸው ነው ፈተና እኩል ያልወሰዱ ተፈታኞች ያሉት በማለትም በመሆኑም ጳጉሜ ወር ላይ የ12ኛ ክፍል የፈተና ውጤት ከታወቀ በኋላ መስከረም 8 ቀን ሁሉም ተማሪ ዩኒቨርስቲ የሚጀምርበት እለት እንደሚሆን ሚኒስትሩ ገልጸዋል። የትምህርት ካላንደርን በአግባቡ አክብሮ በመስራት የፈተና ጊዜያትንም ላለመሻማት ይሰራል ሲሉ ያከሉት ፕሮፌሰር ብርሃኑ ከመስከረም ጀምሮ ጥብቅ አሰራር እንደሚኖር ገልጸዋል። እንደ ሀገር እኩል ውጤት ተናግሮ በእኩል ትምህርት ለማስጀመር ሲባል ቀሪ ያልተፈተኑ ተፈታኝ ተማሪዎችን ጠብቆ ማስጨረስ እንደሚገባ የተናገሩት የትምህርት ሚኒስትሩ በራሳቸው ፈቃድና ምክንያት አስቀድመው ፈተና ላይ ካልተቀመጡት በቀር ሌሎቹ የመመዘኛ መስፈርቱ አካል መሆናቸውን ገልጸዋል። || @ASTU_Network

በ2018 ዓ.ም የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች የጥራት ቁጥጥር እንደሚጀመር ታውቋል። የኢፌዲሪ ትምህርትና ስልጠና ባለስልጣን፣ በመጪው አመት 2018 ዓ.ም በመንግስት ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ላይ የጥራት
+1
በ2018 ዓ.ም የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች የጥራት ቁጥጥር እንደሚጀመር ታውቋል። የኢፌዲሪ ትምህርትና ስልጠና ባለስልጣን፣ በመጪው አመት 2018 ዓ.ም በመንግስት ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ላይ የጥራት ቁጥጥር እንደሚጀምር አስታወቀ፡፡ የተቋሙ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ውብሸት ታደለ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ቃለመጠይቅ፣ በአሁን ወቅት በግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ላይ እየተካወነ ያለው ዳግም ምዝገባና ምዘና ስራ ሲጠናቀቅ ይኸው እንቅስቃሴ በመንግስት ኮሌጆች፣ የማሰልጠኛ ተቋማትና ዩኒቨርሲቲዎች ላይም በቀጣዩ አመት እንደሚቀጥል ተናግረዋል፡፡ አቶ ውብሸት ታደለ በዝርዝር ምን አሉ ? " አሁን እየተከናወነ ያለውን የመጀመሪያው ዙር የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማትን ምዝገባና ግምገማ እንደጨረስን፣ በሁለተኛውና በሶስተኛው ዙር የመንግስት ከፍተኛ የትምህርት ተቋማትን እንመዘግባለን፣ እንገመግማለን፡፡ በፌደራልና በክልሎች የተከፈቱ ኮሌጆችና የማሰልጠኛ ተቋማት አሉ፡፡ መጀመሪያ የምናየው እነሱን ነው፡፡ ቀጥለን ደግሞ ሁሉንም የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎችን እናያለን፡፡ እስካሁን የግል ተቋማት ላይ ያተኮርነው፣ እዚህ ዘርፍ ላይ የነበረው ችግር ሰፊ ስለሆነ ነው፡፡ ያለንን የሰው ሀይልና ሀብት ወደዚህ ዘርፍ በማዞር ቅድሚያ ሰጥተናል፡፡ ሁሉንም አንድ ላይ ማየት አንችልም፡፡ አሁን የግሎቹን ተቋማት ካጠናቀቅን በኋላ፣ ወደ መንግስት ትምህርት ተቋማት ግምገማ እንገባለን፡፡ የመንግስት የትምህርት ተቋማት በመሰረተልማት በኩል ችግር የለባቸውም፡፡ የራሳቸው ህንፃና ግቢ አላቸው፡፡ ስለዚህ እነሱ ጋ ትኩረት የምናደርገው ጥራት ላይ ነው፡፡ ለምሳሌ ፕሮግራሞቹ/ትምህርቱ በበቂ መምህራንና አኳሀን መሰጠቱን እናያለን፡፡ አካዳሚያዊ የድርጊት መርሀግብራቸው ትክክል መሆኑን እንፈትሻለን፡፡ የተገቢነትና አስፈላጊነት ጥያቄ የሚነሳባቸው፣ ዝም ብለው ያለ በቂ ጥናት የሚከፈቱ ፕሮግራሞች አሉ፡፡ የትምህርት ግብአት እና የላቦራቶሪ ቁሳቁሶች፣ እንዲሁም የዳታ ማዕከላቸው ይታያል፡፡ ለተማሪዎችና ለአስተማሪዎች የሚቀርቡት አገልግሎቶች ደረጃቸውን የጠበቁ ናቸው ወይ የሚለውን እናያለን፡፡ ቀደም ብለው የተቋቋሙት ነባሮቹ ዩኒቨርሲቲዎች የዚህ አይነት ችግር ላይኖርባቸው ይችላል፡፡ አዳዲሶቹ ዩኒቨርሲቲዎች ግን በነዚህ መስፈርቶች በኩል ክፍተት ይኖሩባቸዋል፡፡ በአጠቃላይ ግን ጥራትን እናምጣ ካልን፣ ሁሉንም የመንግስት ኮሌጆችና ዩኒቨርሲቲዎችን መፈተሽ አለብን፡፡ በዳግመ ምዝገባችን፣ በተቋማቱ የሚሰጡትን ሁሉንም ፕሮግራሞቻቸውን እናያለን፡፡ ፋይሎቻቸውን እንዲያስገቡ አድርገን እያንዳንዱን ፕሮግራም እንመዝናለን፡፡ አያስፈልጉም የምንላቸውን ፕሮግራሞች እንዲዘጉ፣ ያስኬዳሉ የምንላቸውን ደግሞ እንዲያስቀጥሉ እናደርጋለን፡፡ የመንግስት ተቋማትን ከግሎቹ በበለጠ ጠንከር ያለ ምዘና እናደርጋለን፡፡ ጠበቅ አድርገን ለማየት እንሞክራለን፡፡ የግሎቹን እንደጨረስን፣ በየክልሉ ያሉትንና በፌደራል ደረጃም ያሉትን ኮሌጆችና የማሰልጠኛ ተቋማትን እናያለን፡፡ ከዛም ወደ ዩኒቨርሲቲዎች እንሔዳለን፡፡ ይህ ስራ በ 2018 ዓ.ም የሚጀመር ይመስለኛል " ብለዋል። ቲክቫህ ኢትዮጵያ አዲስ አበባ #TikvahEthiopiaFamilyAA @tikvahethiopia

Many students have been asking this... 👇 Which school is better according to the education provided at ASTU? Choose one and share your reasoning in the comments section:
Anonymous voting

ለዚህ እኮ ነው ይሄ ነገር ልክ ይኑረው የሚባለው 😣... ወይ የሀገራችን ኳስ አይደለ 🤷‍♂️😕 ... የራሳችን ቢሆን እንኳ አንድ ነገር ይባላል 😐 ... ኧረ እንደውም እሱም አያስፈልግም! 🙅‍♂️ ጭራሽ ከእኛ ጋር በምንም በማይገናኝ በውጪ ኳስ ይሄን ያክል ነፍስ እስከሚጠፋ ድረስ በዚህ ልክ ያለ ስሜታዊነት ምን ማለት ነው? ጥቅሙስ ምንድን??🤔 ልጁ ቀኑን ሙሉ ከቤተሰቡ ጋር ውሎ ኳስ ለማየት ሄዶ አስከሬኑ ከኳስ ቦታ ሲመለስ ቤተሰቡ (በተለይ እናቱ) የሚሰማቸውን ስሜት አስቡት... 😭💔 ኧረ ጎበዝ ወዴት እየሄድን ነው? ኧረ ነገ ኮ ብዙ ነገር ነው የሚጠብቀን ... ኧረ ይሄ ነገርኮ የራሳችንን ኑሮ አስጥሎን ሁሉ ነገራችንን ቁማር (bet) እና ጊዜ ማባከን ላይ አስደረገን ... ኧረ ለራሳችን ማሰብ ቢያቅተን እና እንደው ህልም ምናምን የምንለው ፣ የምንኖርለት እና የምንጠነቀቅለት ነገር ባይኖረን እንኳን ቢያንስ ዋጋ ለከፈሉልን ቤተሰቦቻችን እናስብ ... ኧረ እንሰብሰብ ... ቅዱስ መጽሐፉም እኮ "ነገርን ሁሉ በልክ አድርግ" ይላል... 😭 በእውነት እጅግ በጣም ያሳዝናል! 😭💔 Bro ነፍስህ በሰላም ትረፍ! 🕊 .

በአዲስ አበባ በፒኤስጂ እና ቼልሲ መካከል የተደረገውን የዓለም የክለቦች ዋንጫ የፍፃሜ ጨዋታ በዲኤስቲቪ ሲመለከቱ የነበሩ ደጋፊዎች በነበሩበት ሆቴል በተፈጠረ ግጭት የሰው ህይወት አለፈ። ትላንት ምሽ
+1
በአዲስ አበባ በፒኤስጂ እና ቼልሲ መካከል የተደረገውን የዓለም የክለቦች ዋንጫ የፍፃሜ ጨዋታ በዲኤስቲቪ ሲመለከቱ የነበሩ ደጋፊዎች በነበሩበት ሆቴል በተፈጠረ ግጭት የሰው ህይወት አለፈ። ትላንት ምሽት በአሜርካ ኒው ጀርሲ በሚገኘው ሜትላይፍ ስታዲየም በፒኤስጂ እና ቼልሲ መካከል የተደረገውን የዓለም የክለቦች ዋንጫ የፍፃሜ ጨዋታ "ለቡ" አካባቢ በሚገኝ ሆቴል ውስጥ በዲኤስቲቪ እየተመለከቱ በነበሩ ተመልካቾች መካከል በተፈጠረ ግጭት የአንድ ለጋ ወጣት ህይወት አልፏል። በቀብር ስነስርዓቱ ላይ የተገኙ የሟቹ ወዳጆች ፣ ጓደኞች "አሟሟቱ እጅግ የሚያሳዝን ነው" ያሉ ሲሆን "ግለሰቡም ተይዟል" ብለዋል። "እስከ ምሽት 3:00 ሰአት ድረስ ከቤተሰቦቹ ጋር ካመሸ በኋላ ከጓደኞቼ ጋር ትንሽ ልዝናና ብሎ ሆቴሉ እንደገባ ነው ክስተቱ የተፈጠረው" ሲሉ ተናግረዋል። በአሟሟቱ ቤተሰቦቹ እጅግ ከፍተኛ ሀዘን ውስጥ እንደሚገኙ ለመመልከት ችለናል። "ወጣቱ ከኳስ ስሜታዊነት መቆጠብ ወይም የእግር ኳስ ጨዎታዎችን ተሰባስቦ ከማየት መቆጠብ አለበት ካልሆነ ግን የቤተሰብን ሀዘን ማብዛት ነው" ሲሉ ለቀስተኞች ተናግረዋል። "ወጣቶች እባካችሁ ለቤተሰቦቻችሁ ሀዘን አታብዙ፣ ሁሉን በማስተዋል አድርጉ፣ ማታ ማታ አታምሹ፣ በአጭሩ እየተቀጫችሁ ሃዘናችንን አታብዙት" የሚሉ እና ሌሎች ልብ የሚነኩ ሃሳቦች ተሰንዝረዋል። በስልክ ቃላቸውን የሰጡ አንድ እናት ሟቹን ወጣት እንደሚያውቁት ገና በ22 ዓመቱ በተፈጠረው ፀብ እንደተቀጠፈ ገልጸዋል።  "በውጭ ኳስ ምክንያት የለጋ ወጣት ህይወት መጥፋቱ እጅግ ያሳዝናል። ሁሉም ወጣቱ ከስሜታዊነት መራቅ አለበት፣ የሚመለከታቸው አካላትም እንዲህ ያለው ነገር እንዳይፈጠር የራሳቸውን ድርሻ መወጣት አለባቸው" ሲሉ እናታዊ መልዕክታቸውን በሀዘን ስሜት አስተላልፈዋል። || @ASTU_Network

photo content
+1

#EthiopianDefenceUniversity የኢትዮጵያ መከላከያ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያሰለጠናቸውን ተማሪዎች በቢሾፍቱ እያስመረቀ ነው። ዩኒቨርሲቲው በምህንድስና፣ በጤና ሳይንስ እ
#EthiopianDefenceUniversity የኢትዮጵያ መከላከያ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያሰለጠናቸውን ተማሪዎች በቢሾፍቱ እያስመረቀ ነው። ዩኒቨርሲቲው በምህንድስና፣ በጤና ሳይንስ እና በማኅበረሰብ ሳይንስ የትምህርት መስኮች ትምህርታቸውን ተከታትለው ያጠናቀቁ ተማሪዎችን በማስመረቅ ላይ ይገኛል፡፡ የኢትዮጵያ መከላከያ ዩኒቨርሲቲ ከ2018 የትምህርት ዘመን ጀምሮ የተማሪዎች የከፍተኛ ትምህርት ዩኒቨርሲቲ ምርጫ ውስጥ እንደሚገባ በትምህርት ሚኒስቴር መገለፁ ይታወቃል፡፡ @tikvahuniversity

#Ad > LinkedIn rental በመከራየት በየሳምንቱ 20$ (3000ብር) ተከፋይ ይሁኑ! 💰 > ከተከፈተ አንድ አመት የሆነውና ከ 100 በለይ connection ያለው Linkedin > አካውንት ያላቹ ማከራየት ትችላላችሁ። ማወቅ ያለባችሁ የናንተን LinkedIn  አካውንት email እና password  መስጠት አለባችሁ ለማከራየት ፣ ነገርግን ያለ እናንተ ፈቃድ email ወይም password  መቀየር ስለማንችል አካውንታችሁ አደጋ ላይ አይወድቅም። >በአሁኑ ጊዜ፣ ለማስታወቂያ ብዙ ተከታዮች ያሏቸው በርካታ የLinkedIn አካውንት እንፈልጋለን። ● *ዓላማ:* > የማስተዋወቂያ እና ህጋዊ የንግድ አላማዎችን ብቻ ማገልገል > የመለያውን ደህንነት ያረጋግጡ > እናንተ አካውንት ውስጥ ላሉ friendoch/ ጓደኞች መልእክት አይላክም ● *መስፈርቶች:* > ከ 100 በላይ ግንኙነቶች (connection )  እና ከተኸፈተ ቢያንስ 1 አመት የሆነው አካውንት > የLinkedIn መለያዎን ለመከራየት ፍላጎት ካሎት እባክዎን በቴሌግራም @linkedin_rentalll ያውሩን

#Update The student portal is now reopened. If you have anything to check or edit, please do so before it closes. 🔗 Link 🔗
https://estudent.astu.edu.et
|| @ASTU_Network

#ዜና ኢትዮጵያ የራሷን የዋትስአፕ፣ ጂሜይል እና ዙም ስሪቶች እያበለፀገች እንደሆነ መገለጹን፣ ስፑትኒክ ዘገበ። በኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር (ኢንሳ) አማካኝነት የተገነቡት የዲጂታል ቴክ
#ዜና ኢትዮጵያ የራሷን የዋትስአፕ፣ ጂሜይል እና ዙም ስሪቶች እያበለፀገች እንደሆነ መገለጹን፣ ስፑትኒክ ዘገበ። በኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር (ኢንሳ) አማካኝነት የተገነቡት የዲጂታል ቴክኖሎጂ መድረኮች የሳይበር ደህንነትን ለማሻሻል እና ከኢትዮጵያ የቁጥጥር ማዕቀፍ ውጪ በሆኑ የውጭ ኩባንያዎች ላይ ያለውን ጥገኝነት ለመቀነስ የታለሙ መሆናቸውን የሃገር ውስጥ ሚዲያዎችን ጠቅሶ ዘግቧል። ለጂሜል አማራጭ ሆኖ የቀረበው “እርጋሜል” ከወዲሁ በመንግሥት ተቋማት ሥራ ላይ መዋል እንደጀመረ ተነግሯል፡፡ "ሰርኩትኒ" የዋትስአፕ እና ቴሌግራም ምትክ እንዲሆን የሚጠበቅ ሲሆን ገና በትግብራ ላይ ነው የሚገኘው፡፡ ለቨርቹዋል ግኑኝነቶች እንዲሆን በኢንሳ የበለጸገ የተባለው የዙም ምትክ “ደቦ” ደግሞ የሙከራ ደረጃ ላይ እንደሚገኝ ዘግቧል። ምንጭ:- Zehabesha || @ASTU_Network

የመንግሥት ሠራተኞች "የ5 ሚሊዮን የኢትዮጵያ ኮደርስ ኢንሼቲቭ ነጻ ስልጠና" የግድ ሊወስዱ እንደሆነ ተሰማ። የበይነ መረብ ስልጠናውን ለመውሰድ ፈቃደኛ ያልሆኑ ሠራተኞች የሥራ እና የደምወዝ እድገት
የመንግሥት ሠራተኞች "የ5 ሚሊዮን የኢትዮጵያ ኮደርስ ኢንሼቲቭ ነጻ ስልጠና" የግድ ሊወስዱ እንደሆነ ተሰማ። የበይነ መረብ ስልጠናውን ለመውሰድ ፈቃደኛ ያልሆኑ ሠራተኞች የሥራ እና የደምወዝ እድገት እንዲሁም የዝውውር ዕድል እንደማያገኙ ተሰምቷል። ስልጠናውን ያጠናቀቀ የመንግሥት ሠራተኛ የምስክር ወረቀቱ ከግል ማህደሩ ጋር እንደሚያያዝ ዋዜማ ምንጮቿን ጠቅሳ ዘግባለች። የምስክር ወረቀቱን መያዝ እንደ አንድ መስፈት መቀመጡን የጠቀሰው ዘገባው፤ ሁሉም የመንግሥት መዋቅሮች ማሠልጠን ያለባቸውን የሠራተኛ ኮታ እንደተቀመጠላቸው ታውቋል። አንድ ሠራተኛ ፈተናውን ወስዶ የሚያልፈው ከ20 ከሚያዘው ነጥብ 12 እና ከዚያ በላይ ካመጣ እንደሆነ ተገልጿል። ማንኛውም ኢትዮጵያዊ ዓለም አቀፍ ተቀባይነት ያለው ሰርትፍኬት ማግኘት የሚያስችለውን ስልጠና ባለበት ሆኖ መውሰድ ይችላሉ። ለመመዝገብ 👇 https://www.ethiocoders.et/ የስልጠና ዘርፎች፦ ► ዌብ ፕሮግራሚንግ ► አንድሮይድ ማበልፀግ ► ዳታ ሳይንስ ► አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ፋንዳሜንታልስ @tikvahuniversity

የአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ የ2017 ዓ/ም ሀገር አቀፍ የ12ኛ ክፍል የማህበራዊ ሳይንስ ትምህርት ተፈታኝ ተማሪዎችን እየተቀበለ ይገኛል ========================== የአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ  የ2017 ዓ/ም የ12 ክፍል ሀገር አቀፍ የማህበራዊ ሳይንስ ትምህርት ተፈታኝ ተማሪዎችን  እየተቀበለ ነዉ:: ከሰኔ 23- ሀምሌ 8 /2017 ዓ/ም በሀገር አቀፍ ደረጃ የሚሰጠዉን የ12ኛ ክፍል ተፈታኝ ተማሪዎች  በዩኒቨርሲቲዉ የበላይ አመራሮችና የጸጥታ አካላት አቀባበል እየተደረገላቸዉ ነው::  በዚህ በሁለተኛዉ ዙር  የማህበራዊ ሳይንስ 5140 ተማሪዎች በወረቀት እንዲሁም 897 ተማሪዎች ደግሞ በበየነ-መረብ ለፈተናዉ እንደሚቀመጡ በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ የአካዳሚክ ፕሮግራም  ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር የሆኑት ፕሮፌሰር ተገኔ ደሳለኝ ገልፀዋል ። || @ASTU_Network

photo content
+7

መልካም ዕድል የ85 ዓመቱ አባት የአርባምንጭ ዩኒቨርሲቲን መንገድ ያዙ! የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ለመውሰድ ወደ አርባምንጭ ዩኒቨርሲቲ ጉዞ የጀመሩት አቶ ማኖ ማገሶ የዘንድሮውን ፈተና ከምን
መልካም ዕድል የ85 ዓመቱ አባት የአርባምንጭ ዩኒቨርሲቲን መንገድ ያዙ! የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ለመውሰድ ወደ አርባምንጭ ዩኒቨርሲቲ ጉዞ የጀመሩት አቶ ማኖ ማገሶ የዘንድሮውን ፈተና ከምን ጊዜውም በተለየ መልኩ ታሪካዊ አድርገውታል። የ85 ዓመቱ አባት የካቻ ካሻሶ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ተማሪ ሲሆኑ፣ በዚህ ዕድሜያቸው ፈተና መፈተናቸው በእርግጥም ትልቅ አርአያነት ነው። አቶ ማኖ ማገሶ * የአምስት ወንዶችና * የስድስት ሴቶች፣ በድምሩ የአስራ አንድ ልጆች አባት ናቸው። ቀደም ሲል በጋሞ ጎፋ ክፍለ ሀገር ጋርዱላ አውራጃ የገበሬ ማኅበር ጽ/ቤት ኃላፊ ሆነው ሰርተዋል። ከዚህም በላይ በገረሴ ወረዳ ጌዣ ደንን በማስተካከል የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብርን ከጀመሩት መካከል አንዱ ናቸው። የካሻሶ ትምህርት ቤትን በማቋቋም እና ለመምህራንና ለአካባቢው ህብረተሰብ ምቹ እንዲሆን ማኖ ገበያን (ወይም ካሻሶ ገበያን) በመክፈት ትልቅ አስተዋጽኦ አድርገዋል። ልጆቻቸውን በማስተማርም አርባ ምንጭ፣ አዲስ አበባ አልፎ ተርፎም ቻይና ድረስ በትምህርት እንዲደርሱ የረዱ ታላቅ አባት ናቸው። የቦንኬ ወረዳ መንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት እንዳስታወቀው፣ የአቶ ማኖ ማገሶ ለ2017 ዓ.ም ሁለተኛ ዙር ማህበራዊ ሳይንስ የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ሀገር አቀፍ ፈተና መፈተን እጅግ ልዩና ታሪካዊ ክስተት ነው። መልካም ዕድል ለአቶ ማኖ እና ለሁሉም ተፈታኞች! 🙏 Via የቦንኬ ወረዳ መንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot ➡️ https://t.me/atc_news

photo content

photo content
+1

#NationalExam🇪🇹 ፆታዊ ትንኮሳ የፈፀሙ ሦስት ተማሪዎች ከሀገር አቀፍ ፈተና ታገዱ። በሀገር አቀፍ ደረጃ እየተሰጠ ባለው የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ለመፈተን ወደ መቱ ዩንቨርስቲ ከገቡት
+1
#NationalExam🇪🇹 ፆታዊ ትንኮሳ የፈፀሙ ሦስት ተማሪዎች ከሀገር አቀፍ ፈተና ታገዱ። በሀገር አቀፍ ደረጃ እየተሰጠ ባለው የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ለመፈተን ወደ መቱ ዩንቨርስቲ ከገቡት ተማሪዎች ውስጥ ሦስት ተማሪዎች በሴት ተማሪዎች ላይ ዕፆታዊ ትንኮሳ በመፈፀማቸው ከፈተናው መታገዳቸውን የመቱ ዩንቨርስቲ አስታወቀ። ዩኒቨርስቲው ፕሬዚዳንት አለሙ ድሳሳ (ዶ/ር) ለቲክቫህ ኢትዮጵያ " በርካታ ተማሪዎች ወደ ግቢ ከገቡ በኃላ ወጣ ያለ ፀባይ እያሳዩ ነበር " ብለዋል። ዩኒቨርስቲውም ለፈተናው ከተቋቋመ ኮማንድፖስት ጋር በመሆን የመቆጣጠር ሥራ ሲሰራ እንደነበር በማንሳት፤ ሦስቱ ተማሪዎች በሴት ተማሪዎች ላይ ሰኔ 22 ቀን 2017 ዓ.ም አደባባይ ላይ ትንኮሳ መፈፀማቸውን ተበድለናል ብለው በመጡ ሴቶች ቅሬታ እና ዩንቨርስቲውም ባደረገው ማጣራትብ ድርጊቱን መፈፀማቸውን አረጋግጧል። " ትንኮሳ አድራጊዎቹ በአደባባይ ሴቶችን በግድ መሳም፤ ልብሳቸውን መገለብ እና መንካት የማይፈቀድ የአካላቸውን ክፍል በመንካታቸው ሴቶቹ ባቀረቡት አቤቱታ መሰረት ህጋዊ እርምጃ ተወስዶባቸዋል " ብለዋል። በዚህ የተነሳ የትንኮሳ ወንጀል በፈፀሙ ወንዶች ላይ ከዘንድሮው አመት ፈተና እንዲታገዱ መደረጉን ገልጸዋል። ተማሪዎቹ አንዱ ከኢሉ አባቦር ዞን በቾ ወረዳ ሁለቱ ደግሞ ከምስራቅ ወለጋ የመጡ መሆናቸውን ፕረዝዳንቱ አክለዋል። እርምጃ ከተወሰደ በኃላ በግቢው ሲስተዋል የነበረው የተማሪዎች ሥነ ምግባር መሻሻሉንም ተናግረዋል። ወደፊትን ተመሳሳይ ችግሮች እንዳይፈጠር ትምህርት ቤቶች የፈተና ሥነ ምግባር ላይ ለተማሪዎች ግንዛቤ መስጠት እንዳለባቸው የገለፁት አለሙ ድሳሳ (ዶ/ር) ሴት ተማሪዎችም ራሳቸውን እንዲጠብቁና ለትንኮሳ ራሳቸውን እንዳይጋብዙም ጠይቀዋል። የመቱ ዩንቨርስቲ በዘንድሮው ለ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ከ14,000 በላይ ተማሪዎችን ለመፈተን መቀበሉንም ዩንቨርስቲው ፕሬዝዳንት ዶክተር አለሙ ድሳሳ አክለው ገልፀዋል። ቲክቫህ ኢትዮጵያ ነቀምቴ #TikvahEthiopiaFamliyNekemte @tikvahethiopia

Repost from ASTU Network ®️
✨ Calling all Frontend & Backend Web Developers! Are you skilled in React, Express, or other web tech but feeling stuck? 🤔💻
✨ Calling all Frontend & Backend Web Developers! Are you skilled in React, Express, or other web tech but feeling stuck? 🤔💻 Want to join a team where you can work on real projects and earn money, even with zero experience? 💼💰 We’re starting a new company Zema Web Solutions and we’re building a passionate team of developers like YOU! 👨‍💻👩‍💻 🤝 Together, we will: 🔹 Work on real, paid projects 💻💸 🔹 Support each other as a team 🤝 🔹 Build something impactful from scratch 🚀 No GitHub? No problem just bring your skills and drive! Frontend, backend, or fullstack if you're ready to work and grow your career, we want you on board! ⚡️💪 📲 Send your name + GitHub (optional) on Telegram: 👉 @Zema_websln 📩 Let’s create opportunities and build something BIG together! 💥🔥 #ZemaWebSolutions #WebDevelopers #React #Express #Frontend #Backend #WorkAndEarn #StartupTeam

✨ Calling all Frontend & Backend Web Developers! Are you skilled in React, Express, or other web tech but feeling stuck? 🤔💻
✨ Calling all Frontend & Backend Web Developers! Are you skilled in React, Express, or other web tech but feeling stuck? 🤔💻 Want to join a team where you can work on real projects and earn money, even with zero experience? 💼💰 We’re starting a new company Zema Web Solutions and we’re building a passionate team of developers like YOU! 👨‍💻👩‍💻 🤝 Together, we will: 🔹 Work on real, paid projects 💻💸 🔹 Support each other as a team 🤝 🔹 Build something impactful from scratch 🚀 No GitHub? No problem just bring your skills and drive! Frontend, backend, or fullstack if you're ready to work and grow your career, we want you on board! ⚡️💪 📲 Send your name + GitHub (optional) on Telegram: 👉 @Zema_websln 📩 Let’s create opportunities and build something BIG together! 💥🔥 #ZemaWebSolutions #WebDevelopers #React #Express #Frontend #Backend #WorkAndEarn #StartupTeam