Natty's Perspectives
前往频道在 Telegram
1 290
订阅者
无数据24 小时
+27 天
+230 天
正在加载数据
吸引订阅者
十月 '2610月 '26
十月 '26
+336
在2个频道中
九月 '260
在4个频道中
Get PRO
八月 '260
在1个频道中
Get PRO
七月 '260
在1个频道中
Get PRO
六月 '260
在2个频道中
Get PRO
五月 '260
在1个频道中
Get PRO
四月 '260
在6个频道中
Get PRO
三月 '260
在6个频道中
Get PRO
二月 '260
在6个频道中
Get PRO
一月 '260
在2个频道中
Get PRO
十二月 '250
在3个频道中
Get PRO
十一月 '250
在2个频道中
Get PRO
十月 '250
在1个频道中
Get PRO
九月 '25
+10
在1个频道中
Get PRO
八月 '25
+43
在2个频道中
Get PRO
七月 '25
+26
在3个频道中
Get PRO
六月 '25
+71
在8个频道中
Get PRO
五月 '25
+78
在1个频道中
Get PRO
四月 '25
+103
在5个频道中
Get PRO
三月 '25
+30
在0个频道中
Get PRO
二月 '25
+48
在2个频道中
Get PRO
一月 '25
+70
在2个频道中
Get PRO
十二月 '24
+114
在1个频道中
Get PRO
十一月 '24
+68
在0个频道中
Get PRO
十月 '24
+72
在1个频道中
Get PRO
九月 '24
+30
在0个频道中
Get PRO
八月 '24
+25
在0个频道中
Get PRO
七月 '24
+7
在0个频道中
Get PRO
六月 '24
+21
在0个频道中
Get PRO
五月 '24
+29
在0个频道中
Get PRO
四月 '24
+11
在0个频道中
Get PRO
三月 '24
+17
在1个频道中
Get PRO
二月 '24
+14
在1个频道中
Get PRO
一月 '24
+18
在0个频道中
Get PRO
十二月 '23
+18
在1个频道中
Get PRO
十一月 '23
+281
在1个频道中
| 日期 | 订阅者增长 | 提及 | 频道 | |
| 15 十月 | +3 | |||
| 14 十月 | +1 | |||
| 13 十月 | +3 |
频道帖子
ብዙዎቻችን ክርስቲያን በመሆናችን የምናውቀው ተቀይሯል ነገር ግን የምንወደው ነገር አልተቀየረም።
For most of us, when we became Christians, what we knew changed, but what we loved did not.
መንፈስ ቅዱስ ሆይ ፍቅራችንን ቀድሰው!
@Romans148
| 2 | ኢየሱስ አትለፍብኝ
https://www.youtube.com/watch?v=X7kdtL2yCc4&list=PLuwG8LCGZZrK3gDObrmCq-aNK2iibfjZx | 229 |
| 3 | የወጣት ዮርዳኖስን የሞት ዜና አነበብሁ። በጣም ልብ ይሰብራል። የፍቅር ጥያቄዬን ገፋች በሚል መነሳሳት እንዲህ ያለ አረመኔ ተግባር መፈጸም እንስሳነት ነው። እንዲህ ዓይነት በጭካኔ የተሞላ ድርጊት እየተበራከተ መምጣቱ ከአስተሳሰብ ዝቅጠታችን በተጨማሪ፣ የሀገራችንን ህግ መላላት ያንጸባርቃል። ስለዚህ በተገቢ ሁኔታ ፍርድ ካልተሰጠ ነገ ለደኅንነት የበለጠ አስጊ ይሆናል።
እግዚአብሔር ለእህታችን ቤተሰብ መጽናናትን ይስጥ።
@Romans148 | 279 |
| 4 | ጸሎት
ሰላም ወዳጆች፣
ዛሬ የምንችል ሰዎች ሁሉ በያለንበት ሆነን በሀገራችን ጉዳይ በእግዚአብሔር ፊት በጾምና በጸሎት እናሳልፋለን።
የጸሎታችን ትኩረት ማንም ማንንም እንዲያሸንፍ ወይም የሆነን የፖለቲካ አጀንዳ ማገዝ አይደለም። እሱ ላይ ሁላችንም የተለያየ ፖለቲካዊ አቋም ሊኖረን ይችላል። ነገር ግን እንደ ክርስቲያን ደም መፋሰስ እንዲያበቃ፣ ነገሮች በሰለምና በመግባባት እንዲያልቁ መጸለይ ግዴታችን ነው። ስለዚህ በዚህ ልብ ሆነን በሚከተሉትና ሌሎችም እግዚአብሔር በልባችን በሚያኖራቸው አርዕስት እንጸልያለን።
1. እግዚአብሔር ለሀገራችን ሰላምን እንዲያረግ እንጸልያለን፤ በተለይም ለትግራይ፣ ለአማራ፣ ለኦሮምያ፣ ለአፋር ክልልና ሌሎችም አነሰም በዛ በሰላም እጦትና በጦርነት እየተሰቃዩ ላሉ አካባቢዎች እንጸልያለን።
2. በጦርነት እየተሳተፉ ላሉ አካላት፦ የመግግስት አመራሮችና የተቃዋሚ ቡድኖች መሪዎች እግዚአብሔር ማስተዋልንና መግባባትን እንዲሰጣቸው እንጸልያለን።
3. ከላይ በተጠቀሱት አካባቢዎችና በሌሎችም በሰላም እጦትና በጦርነት እየተጎዱ ላሉ የኢትዮጵያ ሕዝቦች እግዚአብሔር ፈውስን እንዲሰጥ እንጸልያለን።
4. በአፍሪካ፣ በተለይም በአፍሪካ ቀንድ (horn of Africa) ሰላም እንዲሆን፣ ለእነዚህ ሀገራት መስማማትና በወንድማማች መንፈስ መያያዝ እንዲሆን እንጸልያለን።
የሰላም ንጉስ ሰላሙን ይስጠን!
@Romans148 | 498 |
| 5 | የሀገራችን ሁኔታ በጣም እያሳሰበኝ ነው። ስለሆነም የምንችል የቻናሉ አባላት ቅዳሜ በያለንበት በጸሎትና በጾም ብንቆይ ብዬ አስቤአለሁ ።ከዛ ደግሞ ከቻልን live ከፍተን ወደ ማታ በጋራ ብንጸልይ ብዬም እያሰብኩ ነው። እስቲ ሀሳባችሁን አካፍሉን?
ተባረኩ!
@Romans148 | 506 |
| 6 | ይህ ደግሞ ሌላኛው ቀኔን የባረከ የኬለር ስብከት ነው። እናንተም ተባረኩበት።
እኔ ስብከት በብዛት አደምጣለሁ። ታዲያ ይህን የማረገው የተለየ ጊዜ መድቤለት አይደለም። ይልቅ ስንቀሳቅስ ወይም ትኩረት የማይፈልግ ስራ ሰራ አሊያም ወክ ሳረግ በearphone እሰማለሁ። እንዲህ በማረግ ብዙ ጊዜ በቀን አንድ ስብከት ልሰማ እችላለሁ። ታዲያ ይህን የምነግራችሁ እናንተንም ተመሳሳይ ነገር እንድታደርጉ ለማበረታታት ነው። ለምሳሌ አዲስ አበባ ያላችሁ ሰዎች፣ የታክሲ ሰልፉ እንዲሁም ታክሲ ውስጥ ሆናችሁ የምትጓዙበት ሰዓት ቀላል አይደለም (አንድ ጥናት እንደሚጠቁመው አዲስ አበባ በአማካይ አንድ ግለሰብ በቀነ ወደ 2 ሰዓት በጉዞ ላይ ይፈጃል:: ይህ ማለት 60 ዓመት ብትኖሩ 5ቱ የሚያልቀው በጉዞ ነው ማለት ነው።)። ሰለዚህ እሱን ጊዜ መጽሐፍ ለማንበብና ስብከት ለመስማት መጠቀም ትችላላቹ ወይም ሌላ ገንቢ ነገሮችን ለታደርጉ ትችላላሁ።
ለዛሬ በዚህ ስብከት ጀምሩ፤
https://youtu.be/cajScztdhJA?si=rNk8YJQJvfI18g8O | 826 |
| 7 | I think this is the second or third time I've listened to this sermon. It's powerful, so I encourage you to listen. It is titled " how to change deeply."
https://youtu.be/DQgxuDl8DXs?is=s2xucq58IeOyWD_s | 725 |
| 8 | እሰይ በይ ነፍሴ እግዚአብሔርን አመስግኚ
ከየት ነው የጠራሽ? ደጋግመሽ ተደሰቺ
ኢየሱስ ባይኖር ሕይወትን ባላገኘሽ
እሱ ባይጠራሽ በክብር ባላጌጥሽ
https://youtu.be/CKEkTU8iGG0?si=Yt9Ibs4XNKg52FkD | 823 |
| 9 | ኒቼና ክርስትና
የቀጠለ…
ባለፈው ሳምንት ኒቼ ክርስትና ላይ የሚያነሳቸውን ሁለት ዋና ዋና ትችቶች ለማተት ሙከራ አድርጌ ነበር። ከሁለቱ ትችቶች የመጀመሪያው፣ ክርስትና ምድር-ጠል ነው የሚል ነበር። ይህ የኒቼ ትችት እንደ ክርስቲያን ካለንበት ዓለም ጋር ያለንን መስተጋብር እንድንቅኝ ይጋብዘናል። መጽሐፍ እንደሚል፣ ከዓልም ባንሆንም በዓለም አለንና ምድርን የምናይበትን እይታ እንድንፈትሽ እንዲህ ያለው ትችት እድል ይሰጠናል።
እንደኔ እይታ፣ እኛ ክርስቲያኖች ከዓለም ጋር ባለን ግንኙነት ሁለት ፈተናዎች ይጋረጡብናል። አንደኛው፣ መጻኢ ተስፋን መዘንጋትና በዚህ ዓለም ሃሳብ መጠመድ ነው። አንዳንድ ጊዜ እንግዶች መሆናችንን በመዘንጋት እንደ ቤተኞች በምድር ላይ ከሚገባ በላይ እንደላደላለን። እንዲህ ያለነውን አማኞች፣ ቅዱስ ጳውሎስ “እኛ አገራችን በሰማይ ነውና፥ ከዚያም ደግሞ የሚመጣ መድኃኒትን እርሱንም ጌታን ኢየሱስ ክርስቶስን እንጠባበቃለን” በማለት ትኩረታችንን እንድናስተካክል ይመክረናል (ፊል 3፡20)።
በሌላ በኩል ደግሞ፣ ከምድር ጋር ላለመጣበቅ በሚል ፍራቻ በዚህ ምድር ያለንን ኃላፊነት እርግፍ አድርገን እንተዋለን። ለዚህ ነው የኒቼ የመጀመሪያው ትችት በተወሰነ መልኩ ከኛ ጋር ተዛማጅነት ያለው። እርግጥ ነው ክርስትና መጻኢ ተስፋ ላይ ይንጠለጠላል። ነገር ግን ክርስትና መጻኢ ብቻ አይደለም፣ አሁናዊም ገጽታ አለው እንጂ። አዲስ ሰማይና አዲስ ምድርን ስንጠብቅ አሁን የምንኖርበትን ዓለም ችላ እያልን አይደለም። ይልቅ እግዚአብሔር በጠራን መንገድ ሁሉ ምድርን እየጠበቅንና እየተንከባከብን እንድንኖር የግዚአብሔር ፈቃድ ነው። ኒቼ እንደሚለው ክርስትና በይፋ ይህን ምድር እንድንጠላና ችላ እንድንል ባያስተምርም፣ ነገር ግን አንዳንዴ ባለማወቅ መጻኢ ተስፋችን ላይ በማላካክ እግዚአብሔር ምድርን እንድንንከባከብ የሰጠንን ኃላፊነት ችላ እንዳንል ልናስተውል ይገባል። እንደ ተሰሎቄ አማኞች “ጌታ ሊመጣ ነው” በሚል ማመካኛ ከስራ እንዳንለጉም ልንጠነቀቅ ገባል። በዚህ ዓለም እስካለን እግዚአብሔር በጠራን መስክ ሁሉ በትጋት ልንሰራና ልናፈራ ተጠርተናል።
“እግዚአብሔርም ባረካቸው፥ እንዲህም አላቸው። ብዙ፥ ተባዙ፥ ምድርንም ሙሉአት፥ ግዙአትም፤ የባሕርን ዓሦችና የሰማይን ወፎች በምድር ላይ የሚንቀሳቀሱትንም ሁሉ ግዙአቸው።” (ዘፍጥረት 1፡28)
ይህንን ሃሳብ በተሻለ ሁኔታ ለማሰብ የሚረዳ ነገረ መለኮታዊ ማዕቀፍ በሚቀጥለው ሳምንት አጋራለሁ።
@Romans148 | 821 |
| 10 | ኒቼ (Friedrich Nietzsche)ና ክርስትና
ከሰሞኑ የእውቁን ፈላስፋ ኒቼን ሶስት መጽሐፍትና ከሱ ጋር የተያያዙ አካዳሚያዊ ጽሑፎችን እያነበብኩ ነበር። The Gay Science, Twilight of The Idols, እና The Anti-Christ የሚሉትን መጽሐፍት ነበር ለማንበብ እድል ያገኘሁት።
በመጽሐፎቹ ሁሉ ላይ ክርስትናን እጅግ አጥብቆ ይተቻል። ከሚያቅርባቸው ትችቶች መካከል ዋነኞቹ ክርስትና የምንኖርበትን ዓለም/ምድር የሚጠላ፣ እንዲሁም ደካማነትን የሚሰብክ ነው የሚሉ ናቸው።
ክርስትና ይህን ዓለም ይጠላል የሚልበት ምክኒያት፣ ክርስትና መጻኢ ዓለምን አጥብቆ ስለሚሰብከ ላለንበት ለዚህ ዓለም ትኩረት አይሰጥም በማለት ነው። እንደሱ እይታ፣ ክርስትና የዚህን ዓለም እውነታ ተቀብሎ ተግዳሮትን ለመርታትና ሰው የተሻለ ዓለምን ለመፍጠር እንዲጥር አያበረታታም። ይልቅ የሰውን እይታ ምናባዊ በሆነ ዓለም ላይ በማድረግ አሁን ያለበትን ዓለም ችላ እንዲል ምክኒያት ሆኖታል ብሎ ይሞግታል፣ ኒቼ።
ሁለተኛው ወቀሳው ደግሞ ክርስትና የደካሞች አበረታች እንደህነ ነው። እንደሱ እይታ፣ የሕይወት ትርጉም በዓለም ላይ ያሉ ተግዳሮቶችን ማሸነፍ መቻል ነው። ይህ ከሚጠይቃቸው ባሕርያት መካከል ዋነኞቹ ጥንካሬና ኃይል ናቸው። ዓልም እየተሻሻለች የምትሄደው የሰው ልጅ ለማሸነፍና ለመግዛ በሚያደርገው ትግል ነው። ያ ማለት፣ ደካሞች ለኃያላኑ መገዛታቸው ተፈጥሯዊ ነው ማለት ነው። ነግር ግን፣ ለኒቼ፣ ክርስትና ደካሞችን በማወደስ የዚህ ጥንቅ ሆኗል። እንደ እሱ እምነት፣ በክርስትና እምነተሰ በራሱ አቅም የሌለው ደካማ ይሞገሳል፣ የዘላልም ሕይወት ተስፋ ይሰጠዋል። ስለዚህም፣ ለኒቼ ክርስትና የባሪያዎች ኃይማኖት ነው። በማንቋሸሸም፣ ክርስትና ሲጀምር የጀመረው በባሪያዎችና በማህበረሰብ ቦታ በሌላቸው ሰዎች ነው በማለት ይናገራል።
ከነዚህ ትችቶቹ ጥቂት ነገሮችን ልንማር እንችላለን ብዬ አምናለሁ። ነገር ግን ጽሑፉ እንዳይረዝም፣ ይህን በሚቀጥለው ክፍል አቀርባለሁ።
ይቀጥላል....
@Romans148 | 955 |
| 11 | በፈተና ላሉ ማጽናኛ (Comfort for the Tempted) የ Charles H. Spurgeon ስብከት በ 1ኛ ቆሮንጦስ 10፡13 ላይ እጣሬ (መስከረም 27፣ 1883 እ.አ.አ)
"ለሰው ሁሉ ከሚሆነው በቀር ምንም ፈተና አልደረሰባችሁም፤ ነገር ግን ከሚቻላችሁ መጠን ይልቅ ትፈተኑ ዘንድ የማይፈቅድ እግዚአብሔር የታመነ ነው፥ ትታገሡም ዘንድ እንድትችሉ ከፈተናው ጋር መውጫውን ደግሞ ያደርግላችኋል።" (1 ቆሮ 10፡13)
1. ለብቻችንን አይደለንም
- የትኛውም የምታልፉበት ፈተና ሌሎች አማኞች ያለፉበት ወይም እያለፉበት ያለ ነው።
- አንዳንዴ ጠንካራ የሚመስሉ አማኞችን ስንመለከት በፈተና ያላለፉ ይመስለናል። ነገር ግን አማኞች ብዙ ጊዜ ጠንካራ በሆኑበት በዛው ጉዳይ ተፈትነው ይወድቃሉ። ለምሳሌ፣ ያዕቆብ እዮብ ታጋሽ እንደሆነ ይነግረናል። ታዲያ እስቲ አስቡ ስለ ኢዮብ እለመታገስ ሰምታችሁ አታውቁምን?
- ታዲያ ያሽነፉት ሁሉ ያሸነፉት በእግዚአብሔር መንፈስ እርዳታና በጌታ በኢይሱስ ደምና ጽድቅ ነው።
- ሌላው፣ ጌታ ሆኖ ያላለፈበት አዲስ ፈተና አልገጠማችሁም።
- ስለዚህ የምታልፉበት ፈተና እናንተ ብቻ የምታልፉበት እንደሆነ ታስቡ። እንዲህ ያለው ሃሳብ በናልፍበት ፈተና ላይ ተጨማሪ ሸክም ይሆናል።
2. እግዚአብሔር ታማኝ ነው
- እግዚአብሔር የሰጠንን ተስፋ ለመፈጸም ታማኝ ነው።
- አረሳችሁም አልጥላችሁም ያለውን ተስፋ ሊፈጽም ታማኝ ነው።
- እግዚአብሔር ታማኝ ብቻ ሳይሆን፣ ተስፋው ሊፈጽም ባለንበት ሁኔታ ላይ የበላይ ተቆጣጣሪ ነው።
3. እግዚአብሔር ለፈተናችን ገደብን ያበጃል
- እግዚአብሔር በማንችለውን ፈተና እንድናልፍ አይፈቅድም።
- እግዚአብሔር የሚገጥሙን ፈተናዎች የጊዜ እርዝማኔ ክምንችለው በላይ እንዳይሆን ይገድባቸዋል።
4. እግዚአብሔር ከምናልፍበት ፈተና መውጫ መንገድ ያዘጋጃል
- ከፈተና መውጫ አንድ ብቸኛ መንገድ ነው ያለው፣ እርሱም የእግዚአብሔር መንገድ ብቻ ነው። የራሳችን መውጫ መንገድ ለበለጠ ፈተና ነው የሚያጋልጠን።
- ስለዚህ አንዳንድ ጊዜ በፈተና ውስጥ ሆነን ልናድርገው የምንችለው በጣም ጥሩ ነገር ምንም አለማድረግ ነው።
5. እንታገሥ ዘንድ የእግዚአብሔር መውጫ መንገድ ከፈተና ማምለጥ ሳይሆን በፈታና ውስጥ በጽናት ማለፍ ነው
- ስለዚህ አንዳንዴ በፈተናው ውስጥ ማለፋችን የግዚአብሔር ሃሳብ ከሆነ ጸሎታን መሆን ያለበት እንድንታገስ እግዚአብሔር እንዲረዳን ነው።
- በፈትና እንድናልፍ ሲፈቅድ እግዚአብሔር በፈተና ውስጥ የምናልፍበትን አቅም ይሰጠናል።
- በእኛ ውስጥ ያለውን የእግዚአብሔር ሕይወት ፈተና ሊያጠፋው አይችልም።
@Romans148 | 1 684 |
| 12 | https://youtu.be/5ej-lo0gLgA?is=a1ec4GiM7oULxhNY
@Romans148 | 998 |
| 13 | አባ፣ ለአንተ ታማኝ እንድሆን እርዳኝ!
@Romans148 | 1 132 |
| 14 | ኃጢአት ለእግዚአብሔር ያለንን ቦታ ይገልጣል
በቅዳሴ መጽሐፋችን ውስጥ እንዲህ የሚል የንስሃ ጸሎት ይገኛል፤"I acted if God did not matter." ይህ በጣም ትክክለኛ የኃጢአት ልምምድ አገላለጽ ነው።
በኃጢአት መመላለስ ለእግዚአብሔር ያለንን ቦታ ያሳያል። መስበክ፣ መዘመር፣ መጸለይና መንፈሳዊ ቋንቋዎችን መናገር መቻላችን ብቻውን ለእግዚአብሔር ያለንን ቦታ አይገልጥም። እግዚአብሔር በእኛ ዘንድ ያለው ቦታ እኛ ለኃጢአት ያለንን ንቀት ያህላል።
1 ተሰሎንቄ ሰዎች 4:2-5, 8 አማ54
[2] በጌታ በኢየሱስ የትኛውን ትእዛዝ እንደ ሰጠናችሁ ታውቃላችሁና። [3] ይህ የእግዚአብሔር ፈቃድ እርሱም መቀደሳችሁ ነውና፤ [4-5] ከዝሙት እንድትርቁ፥ እግዚአብሔርን እንደማያውቁ አሕዛብ በፍትወት ምኞት አይደለም እንጂ፥ ከእናንተ እያንዳንዱ የራሱን ዕቃ በቅድስናና በክብር ያገኝ ዘንድ እንዲያውቅ፤
[8] እንግዲህ የሚጥል ሰውን የጣለ አይደለም፥ መንፈስ ቅዱስን በእናንተ እንዲኖር የሰጠውን እግዚአብሔርን ነው እንጂ።
በቁጥር ስምንት ላይ "የሚጥል" ተብሎ የተተረጎመው የግሪኩ ቃል "የሚቃወም፣ የሚሽር" ተብሎ ሊተረጎም ይችላል። ስለዚህ ቅዱስ ጳውሎስ እንደሚለው ይህንን የቅድስናን ጥሪ መግፋት እግዚአብሔርን መሻር ነው።
የኃጢአት ልምምድ እኛን ሊቀድሰን በውስጣችን እየሰራ ካለው ቅዱስ መንፈስ በተቃርኖ መቆም ነው፤ ኃጢአትን ሊያስወግድ የተገለጠውን ጌታ መናቅ ነው።
ነገር ግን ድካማችንን አምነን፣ በተሰበረ ልብ ወደ ፊቱ ብንቀርብ የሚያስፈልገንን ጸጋና የሚቀድሰንን መንፈሱን ሊሰጠን የታመነ አባት አለን።
@Romans148 | 2 049 |
| 15 | የኖርኩትን ዘመን ስቃኝ ከዚህ ውጪ ምን እልሃለሁ:-
"እግዚአብሔርን። አንተ ጌታዬ ነህ አልሁ፤ ከአንተ በቀር በጎነት የለኝም።"
~ መዝ 16:2 ~
"I say to the Lord, “You are my Lord; I have no good apart from you.”
~ Psalm 16:2 ESV ~
በእኔ ሕይወት ለተገኘውና ለሆነው በጎ ነገር ሁሉ ብቸኛው ማብራሪያ አንተ ነህና ተመስገን!
@Romans148 | 1 306 |
| 16 | ጌታ ሆይ፣ ደክሞናል፤ እባክህ ቶሎ ና!
@Romans148 | 1 563 |
| 17 | የዓለም ኀጢአተኞች እንኳን ደስ ያላችሁ፣
ኢየሱስ ክርስቶስ መጥቷል ሊድናችሁ፤
የዓለም ኀጢአተኞች እንደኔ ያላችሁ፣
ኢየሱስ ያድናል በእርሱ ተስፋ አላችሁ።
ኢየሱስ ሠርቶል- በእርሱ ተስፋ አላችሁ፣
አየሱስ ሆኖታል- በእርሱ ተስፋ አላችሁ።
ኢየሱስ ችሎታል - በእርሱ ተስፋ አላችሁ።
ወዳጆቼ፣ ግድ የለም ኢየሱስ አለላችሁ። ተነሱ፤ ወደቤቱ ሂዱ፤ በተስፋውም ታደሱ።
መልካም የጌታ ቀን!
@Romans148 | 2 210 |
| 18 | ያው እንደምታውቁት የምጠቀመው social media telegram ብቻ ነው (ያው linkdin ከነዚህ ጎራ አይጠራም ብዬ ነው እንጂ እሱም አለኝ😁)። ይህንንም አሁን ከምጠቀመው በብዙ እጥፍ ቀንሼ መጠቀም እንዳለቦኝ አምኛለሁ። በሳምንት አንድ ቀን install ከተደረገ ከዛ በኋላለ ሳምንቱን በሙሉ መልሶ ማጥፋት መልካም እንደሆነ አስቤአለሁ።
ይህን ማውራቴ በሁለት ምክንያት ነው፤ አንድም፣ በdirect messageም ሆነ በinbox ቶሎ ባልምስላችሁ ይህን ከግንዛቤ እንድታስገቡ ለመጠየቅ ነው።
ሌላው ደግሞ እናንተም ስራችሁ የሚያስገድዳችሁ ካልሆነ በቀር social media ለመቀነሰት እንድሞክሩ ለማበረታታት ነው። እዚህ መክረም አእምሮን ያቀጭጫል፣ superficial ያደርጋል፣ መሬት ላይ ያለውን ማህበራዊ ግንኙነት ያሳሳል፣ ትኩረት የማድረግ አቅማችሁን ያደክማል፣ ውጤታማነታችሁን ይቀንሳል፣ የምናባዊ ዓለም እስረኛ ያደርጋችኋል፣ ብቻ ምን አለፋችሁ ያልታወቀበት ትልቅ በሽታ ነው። ስለዚህ ቆም ብላችሁ እንድትቃኙ፣ ሲያስፈልግም እረፍ እንድትወስዱ ለማሳሰብ ነው።
ክበሩልኝ!
@Romans148 | 1 460 |
| 19 | የዮሐንስ ወንጌሎ ጥናት
ወዳጆች፣ ባለፈው ባሳወቅኳችሁ መሰረት የዮሐንስ ወንጌል የምናጠናበትን Group ከፍቻለሁ። ተሰጥታችሁ ለማጥናት ፈቃዳችሁን የገለጣችሁ ሰዎች ከታች ያለውን ሊንክ ተጭናችሁ join አድርጉ። ግሩፑ ለሚያጠኑ ሰዎች ብቻ የሚሆን private group ነው። በየሳምንቱ ለማጥናት የሚረዱን ጥያቄና ጽሑፎችን እዛ ላይ አጋራችኋለሁ።
https://t.me/+8339PM6iuPswNGQ5 | 1 041 |
| 20 | ክርስቶስን ለብሼ ከኩነኔ ባላመልጥ ኖሮ ምን ይውጠኝ ነበር?! በምንስ ድፍረት ፊትህ እቀርብ ነበር?!
"ከክርስቶስ ጋር አንድ ትሆኑ ዘንድ የተጠመቃችሁ ሁሉ ክርስቶስን ለብሳችኋልና።"
- ገላትያ 3፡27 -
"እንግዲህ በክርስቶስ ኢየሱስ ላሉት አሁን ኵነኔ የለባቸውም።"
- ሮሜ 8፡1 -
@Romans148 | 1 136 |
