ch
Feedback
✝ጽርሐ አርያም✝

✝ጽርሐ አርያም✝

前往频道在 Telegram

ሰላም ✝ጽርሐ አርያም✝ ቻናል ተከታታዮች #የዚህ ቻናል አላማ የእግዚአብሔርን አምላክነት፣ የድንግል ማርያምን አማላጅነት፣ የፃድቃንን ተራዳኢነት ለማስተማር የተቋቋመ ነው:: ለህይወታችን ለሚገጥሙን ፈተናዎች አስተማሪና ጠቃሚ የሆኑ መልእክቶች ይገኙበታል።በታሪኮቹ እየተደሰቱ በመልእክቶቹ እንደምትማሩ ተስፋ እናረጋለን። ✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝ ቻናሉን ለወዳጅ ዘመድዎ ሼር ማረግ አይርሱ። @orthodox26

显示更多
289
订阅者
无数据24 小时
无数据7 天
无数据30 天
帖子存档
ጥያቄ፦ ፩, እመቤታችን በምድር ላይ የኖረችው የእድሜ መጠን ስንት ነበር? ሀ. 74 ለ. 120 ሐ. 81 መ. 64

ጥያቄ፦ ፩, እመቤታችን በምድር ላይ የኖረችው የእድሜ መጠን ስንት ነበር?
Anonymous voting

ድንግል ሆይ ከአይኖችሽ ፈሶ በተወዳጁ ልጅሽ ፊት ላይ የወረደውን መሪር እንባ አሳስቢ እመቤታችንም ከልጇ ከወዳጇ ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር  ትዕማን ወደምትባል አንዲት ከበርቴ ባለሀብት ቤት ሄዳ ቁራሽ እንጀራንና ለልጇም ጥቂት ወተትን ለመነቻት፡፡ ያቺ ክፉ ሴት ግን ልብን በሀዘን የሚሰብር ክፉ ንግግርን ተነጋረቻት፡፡ ጻድቅ ዮሴፍም ‹‹እንግዳን ካለ ይሰጡታል ከሌለ በሰላም ይሸኙታል እንጂ ለምን ክፉ ንግግርን ትናገሪያታለሽ?›› እያለ ሲነጋገሩ አሽከሯ ኮቲባ የእመቤቷን ቁጣ ሰምታ መጥታ ጌታችንን ከመሬት ላይ ጥላ እንደ ድንጋይ አንከባለለችው፡፡ እመቤታችንም እጅግ ደንግጣ እያለቀሰች ልጇን ፈጥና ልታነሣው ስትል ዮሴፍ ‹‹ተይው አታንሽው ኀይሉን ያሳይ›› አላት፡፡ ያንጊዜም ትዕማንን ምድር አፏን ከፍታ ዋጠቻት፡፡ ገረዷ ኮቲባም በለምጽ ተመታች፡፡ በቤታቸውም ውስጥ በሕይወት የቀረ የለምና የሩቅ ቤተሰቦቿም ጦጣ ሆነው ከተራራ ወደ ተራራ ሸሹ፡፡ እመቤታችን ፣ ዮሴፍና ሰሎሜም በትዕማን ቤት 6 ወር ከተቀመጡ በኋላ መልአኩ ተገልጦ ከዚያ እንዲወጡ አዘዛቸውና ወጡ፡፡ አዘክሪ ድንግል አንብዐ መሪረ ዘውኅዘ አምአእይንትኪ ወወረደ ዲበ ገጸ ፍቁር ወልድኪ ድንግል ሆይ ከአይኖችሽ ፈሶ በተወዳጁ ልጅሽ ፊት ላይ የወረደውን መሪር እንባ አሳስቢ ቻናሉን ለወዳጅ ዘመድዎ ሼር ማረግ አይርሱ። @orthodox26 @orthodox26

በሰንበት መፍረስ ✨የኢያሪኮ ሰዎች የሠራዊት ጌታ የእግዚአብሔርን ኃይል በመናቃቸው ምንኛ ተጎዱ?!  እርሱ ዓለምን የፈጠረ መሆኑን ስላላመኑ እንዳልተፈጠሩ የሆኑት የኢያሪኮ ሰዎች መጨረሻ እጅግ አሳዛኝ ነበር፡፡ ➡️ቅጥራቸው ከመፍረሱ በፊት እስራኤል የእግዚአብሔርን ታቦት ይዘው ለስድስት ቀናት ያህል በዝምታ ኢያሪኮን ዞሯት፡፡ ዓለምን በስድስት ቀናት የፈጠረውን ጌታ እንዲያስተውሉ ስድስት የዝምታ ቀናት ተሠጧቸው፡፡ በሰባተኛው ቀን ግን ጮኹ የኢያሪኮም ቅጥር ፈረሰ፡፡ ✨ሰባተኛ ቀን የዕረፍት ቀን ነው፡፡ ለኢያሪኮ ግን የመፍረስ ቀን ሆነባት፡፡ ሰባተኛ ቀን ፈጣሪን ለሚያምኑ የተቀደሰ ቀን ነበር ፤ ለኢያሪኮ ግን የመረገም ቀን ሆነባት፡፡ እግዚአብሔር የፈጠረው ሁሉ መልካም እንደሆነ ባየበት ሰባተኛ ቀን ኢያሪኮ ግን ከፉ እንደሆነች ታየባት፡፡ ➡️እግዚአብሔር የሌለበት ሕይወት እንዲህ ነው፡፡ ወዳጄ እግዚአብሔር በሕይወትህ ውስጥ ከሌለ የሰንበት ቀን የነፍስህ ዕረፍት ቀን መሆኑ ይቀርና እንደ ኢያሪኮ የመፍረስ ቀን ይሆናል፡፡ በዚያ ቅዱስ ቀን ቅጥርህን በመጠጥ ፣ በስካር በዝሙት ስታፈርስ ትውልና ታድራለህ፡፡ ራስህን አንድደህ ትሞቃለህ ፤ እያራገብህ ትቃጠላለህ፡፡ ታቦት ይዘው ቢዞሩህም የኃጢአት ግንብን አጥረሃልና አትሰማም፡፡ በላይህ ላይ ቢቀደስብህም እንደ ኢያሪኮ ሰዎች ካህናቱን እያየህ ‘ዝም ብሎ መዞር ምንድር ነው?’ እያልክ ትስቃለህ፡፡ የካህናቱ የቅዳሴ ዜማ ለአንተ የሚያፈርስ ጩኸት ይሆንብሃል፡፡ የኢያሪኮ ሰው ከመሆን ፣ በሰንበት ፈራሽ ከመሆን ያድንህ! ✨ቅዳሴያችን መካከል ካህኑ ዕጣን እያጠኑ ዞረው ሲመለሱ የዚህች አጭር ጽሑፍ መነሻ ሃሳብ የሆነውን ይህንን ጸሎት ይጸልያሉ፦  አምላካችን እግዚአብሔር ሆይ አስቀድመህ በባሪያህ በነዌ ልጅ በኢያሱ እጅ የኢያሪኮን ግንብ እንዳፈረስከው የእኔንና የሕዝብህን የኃጢአታችንን ግንብ አፍርሰው፡፡ ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ ጥቅምት 9 /2012 ዓ.ም. ቪክቶሪያ አውስትራሊያ ቻናሉን ለወዳጅ ዘመድዎ ሼር ማረግ አይርሱ። @orthodox26 @orthodox26

🚹ስማኝ ልጄ‼️ 1.ጠንካራ ሰው ሁን ማለት አትውደቅ ማለት አይደለም ወድቀህ መነሳትንም ልመድ ማለት እንጂ!!!! 2. ዝም በል ማለት አትናገር ማለት አይደለም ሌሎችን ለመስማት ጆሮ ስጥ ማለት እንጂ!!!! 3. ሆዳም አትሁን ማለት አትብላ ማለት አይደለም በሰው ሀቅ አትለፍ ማለት እንጂ!!!! 4. አትቆጣ ማለት ስሜት አይኑርህ ማለት አይደለም ከቁጣ ቶሎ ተመለስ ማለት እንጂ!!!! 5. ይቅርታ አድርግ ማለት አልተጎዳህም ማለት አይደለም በሆድህ ቂም መያዝ ሌላ ጉዳት ስለሆነ እንጂ!!!! 6. ጠላትህን ውደድ ማለት ጠላት ጥሩ ነው ማለት አይደለም ከጥላቻ ይልቅ ፍቅር ስለሚያሸንፍ!!! 7. ደስተኛ ሁን ማለት ሁሉ ይኑርህ ማለት አይደለም ባለህ ነገር ደስ ይበልህ ማለት እንጂ!!!! 8. ስራህን ውደድ ማለት የምትሰራው ስራ ጥሩ ነው ማለት አይደለም ነገ ጥሩ ስራ እንዲኖርህ ዛሬ የምትሰራውን ስራ ውደድ ማለት እንጂ!!!! 9. ወረኛ አትሁን ማለት አታውራ ማለት አይደለም ምንም ስለማታውቀው ነገር አታውራ ማለት እንጂ!!!! 10. ትሞታለህ ማለት አትስራ ማለት አይደለም ምንም ቁም ነገር ስትሰራ አትሙት ማለት እንጂ!!!! 11. ብቸኛ አትሁን ማለት ሮጠህ ትዳር ያዝ ማለት አይደለም ልብህን ግዜህን ያለህን ሁሉ አሳልፈ ለመስጠት ዝግጁ ሁን ማለት እንጂ!!!! 12. እውነተኛ ሁን ማለት ሰዎች ባሉበት ብቻ እውነትተናገር ማለት አይደለም ለራስህም የእውነት ኑሮ ኑር ማለት ማለት እንጂ!!!! 13. አትጣላ ማለት ከሰው ጋር አትኑር ማለት አይደለም ቂም ይዘህ አትቆይ ማለት እንጂ!!!! 14. ኩራተኛ አትሁን ማለት አትዘንጥ ማለት አይደለም ሌሎችን አትናቅ ማለት እንጂ!!! 15. ቆንጆ ነህ ማለት ከሌሎች የተሻልክህ ነህ ማለት አይደለም አምሮብሃል ማለት እንጂ!!!! 16. አዋቂ ሁን ማለት እንደገና ት/ቤት ሂድ ማለት አይደለም ብልህ ሁን ማለት እንጂ!!!! እግዚአብሔር አምላክ መልካሙን አዊዋቂዎች ያድርገን🙏🙏🙏 ቻናሉን ለወዳጅ ዘመድዎ ሼር ማረግ አይርሱ። @orthodox26 @orthodox26

እባካችሁ በጥሞና አንብቡት 🙏🙏       + አልቆም ያለ ደም+ "በኋላውም ቀርባ የልብሱን ጫፍ ዳሰሰች፥ የደምዋም ፈሳሽ በዚያን ጊዜ ቆመ" ሉቃ. 8:44 ከአሥራ ሁለት ዓመትም ጀምሮ ደም የሚፈሳት ሴት ነበረች፥ ትዳርዋንም ሁሉ ለባለመድኃኒቶች ከስራ ማንም ሊፈውሳት አልተቻለውም። ደምዋ ፈስሶ አያልቅም ወይ? ዓሥራ ሁለት ዓመት ሙሉ? እንዴት ያለ ሕመም ነው?! ሰው በክፉ ሽታዋ እስኪርቃት ድረስ የማይቆም ደም:: ባለ መድኃኒቶች ሊያቆሙት ያልቻሉትን የደም ጎርፍ የናዝሬቱ ባለ መድኃኒት በቀሚሱ ብቻ አቆመው:: በልብሱ ጫፍ ብቻ:: ሳያያት ሳይነካት እጁን ሳይጭንባት በልብሱ ጫፍ ብቻ የደምዋን ዝናብ እንዲያባራ አደረገው:: የሕመምዋን ማዕበል ገሠጸው:: በልብሱ ጫፍ ብቻ የሚፈውስ ሐኪም እንዴት ያለ ነው?  ቀጠሮ ሳይሠጥህ ሳያናግርህ ቀና ብሎ ሳያይህ ስትነካው ብቻ የምትድንበት ከሆነ እርሱ መድኃኒት የሚያዝ ሐኪም ሳይሆን ራሱ መድኃኒት ነው:: የልብሱን ጫፍ የነካ ከዳነ ሥጋውን የበሉ ደሙን የጠጡማ ምንኛ ይድኑ ይሆን? ሊፈውሳት አስቦ አልነበረም የዐሥራ ሁለት ዓመት ሴት ልጅ ከሞት ሊያስነሣ መንገድ ሲሔድ ግን እግረ መንገዱን የዓሥራ ሁለት ዓመት የቁም ሙትዋን ፈወሳት:: መድኃኔዓለም እንዲህ ነው:: ወደ በሽተኛው ሳይሔድ በቃሉ ብቻ ተናግሮ ይፈውሳል  ፤  በሽተኛው ቤት ገብቶ በአልጋው ላይ ይፈውሳል:: ሊፈውስ ሲሔድም ይፈውሳል:: እናም የሴቲቱ አልቆም ያለ ደም በልብሱ ጫፍ ብቻ ቀጥ አለ:: ጌታዬ ሆይ የእኔንስ ደም የምታቆመው መቼ ነው? ምን ደም ፈስሶህ ያውቃል ካልከኝ ኃጢአት የሚባል ደም ሲፈሰኝ አይታይህም? አንተስ በቃልህ "ኃጢአታችሁ እንደ ደም ብትቀላ እንደ ባዘቶ ትጠራለች" ብለህ የለ?  እንደ ደም የቀላው የእኔ ኃጢአት ነው:: ይኸው ሲፈስ ከሴቲቱ በላይ ቆየ:: ላቆመው ብል አልቆም አለኝ:: ያላሰርኩበት ጨርቅ ፣ ያልሞከርኩት ቅባት ፣ ያልሔድኩበት ባለ መድኃኒት የለም::  ገንዘቤን ከሰርኩ እንጂ ኃጢአቴ ግን መቆም አልቻለም:: እንዲያውም መጠኑ እየጨመረ ነው:: ባሕር ሆኖ ሊያስጥመኝ የደረሰ የኃጢአት ደም ከብቦኛል:: ለእኔ የሚሆን የቀሚስ ጫፍ ታጣ ይሆን? እኔ እንደ ሴቲቱ ታላቅ እምነት የለኝም ቀሚስህ ግን አሁንም ኃይል አለው:: ልትፈውሰኝ ና አልልህም ስታልፍ ግን ልዳስስህና ልዳን:: ጉዞህን ሳላሰናክል ሰው ሳይሰማ በልብስህ ጫፍ ብቻ ደሜን አቁምልኝ::  የእኔን ደሜን መግታት ላንተ ምንህ ነው? ደምህንስ አፍስሰህልኝ የለ? እባክህን ደሜ ሳይቆም ሌላ ዓመት አልሻገር:: እኔ ኃጢአቴን "ያለፈው ዘመን ይበቃል" ማለት ቢያቅተኝም አንተ ግን ይበቃሃል በልልኝ:: በእምነት ማጣት የታጠፈውን እጄን ወደ ልብስህ ጫፍ ዘርጋልኝ:: እኔ ማቆም ያልቻልኩትን የበደል ደም ጸጥ አድርገህ "አንድ ሰው ዳስሶኛል ኃይል ከእኔ ወጥቶአል" በል:: እነ ጴጥሮስም ይደነቁ እኔም በሰላም ልሒድ:: ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ ጳጉሜን 2015 ዓ.ም. ቻናሉን ለወዳጅ ዘመድዎ ሼር ማረግ አይርሱ።        👇👇👇👇👇👇 👉👉 @orthodox26 👈👈 👉👉 @orthodox26 👈👈        👆👆👆👆👆👆

👉 የኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር እንዴት ነው? 👉 ጳጉሜ እንዴት 6 እና 5 ትሆናለች? 👉 ጳጉሜ ሰባት የምትሆነው መች እና እንዴት ነው? 👉 አቆጣጠሩስ እንዴት ነው? ለነዚህ ጥያቄዎች መልስ ይፈልጋሉ?? መልሶ አዎ ከሆነ ከታች ያለውን ቻናል ተቀላቀሉ✅ ቻናሉን ለወዳጅ ዘመድዎ ሼር ማረግ አይርሱ።        👇👇👇👇👇👇 👉👉 @orthodox26 👈👈 👉👉 @orthodox26 👈👈        👆👆👆👆👆👆

👉 ዘመናት ሲቆጠሩ ዘመነ ማርቆስ ፣ ዘመነ ማቴዎስ ፣ ዘመነ ሉቃስ እና ዘመነ ዮሐንስ ናቸው። 👉 ሁልጊዜም ወደ ዘመነ ዮሐንስ ስንሸጋገር ጳጉሜ 6 ትሆናለች። 👉 ይህ እንዴት ሆነ?በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን አውሻህር መፅሐፍ ላይ የዘመን አቆጣጠር አባቶች አስቀምጠውታል።3ቱ አመታት 365 ቀን ከ6 ሰአት ይይዛሉ።ስለዚህ የሶስቱ አመታት የ6 ሰዓታት ጥርቅም 18 ይሆናል።ከዛን ዘመነ ሉቃስ ተገባዶ ወደ ዘመነ ዮሐንስ ስንሸጋገር 18+6=24 ሰአት ይሆናል ስለዚህ በየአራት አመቱ ጳጉሜ 6  ሆናለች። በፈረንጆቹ leap year ይሉታል እሱም February ወር 29 ቀናትን ይይዛል ።በእኛ መጠነ ራብኢት ማለትም ዘመነ ዮሐንስ የሚውልበት።ቀደምት አባቶች ጳጉሜ 7 ቀናትን የሚይዝበት አመት እንዳለ ፅፈው አስቀምጠዋል።እሱም በ600 አመት አንዴ ይከሰታል። በቀን ሰዓታት ውስጥ ተጨማሪ 0.4 ሰከንድ አለ።ስሌቷም በብራና መፃህፍት ላይ ተፅፏል።ሪና መአልትና ሪና ሌሊት የሚል ስሌት ነው።በኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር 365 እለት ከ15 ኬክሮስ ከ6ካልኢት ወይንም 365 ቀን ከ6 ሰአት ከ2 ደቂቃ ከ24 ሰከንድ ነው።ስለዚህ 2 ደቂቃ ከ24 ሰከንድ ተጠራቅሞ ጳጉሜን 7 ያደርጓታል።ካልኢት ማለት 24 ሰከንድ ነው።የ5 አመት 30 ካልኢት የ10 አመት 60 ካልኢት ነው።60 ካልኢት ደግሞ 24 ሰከንድ ነው።የ100 አመት 240 ሰከንድ ወይም 10 ኬክሮስ የ200 አመት 20 ኬክሮስ የ300 አመት 30 ኬክሮስ የ400 አመት 40 ኬክሮስ የ500 አመት 50 ኬክሮስ የ600 አመት 60 ኬክሮስ።60 ኬክሮስ 1440 ደቂቃ  ወይም 24 ሰአት ይሆናል።ስለዚህ በ600 አመት አንዴ ጳጉሜ 7 ይሆናል።ይህንን በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የብራና መፃህፍት ላይ ተፅፎ ይገኛል። ቻናሉን ለወዳጅ ዘመድዎ ሼር ማረግ አይርሱ። @orthodox26 @orthodox26

🌻እንኳን ለጳጉሜን ወር አደርሰን አደርሳችሁ !!! ✨፩፥ ጳጉሜ ፩ #የማዕተብ ቀን። ✨፪፥ ጳጉሜ ፪ የክብረ ክህነት ቀን። ✨፫፥ ጳጉሜ ፫ የቅዱስ ሩፋኤል ቀን። ✨፬፦ ጳጉሜ ፬ የፊደል ገበታ ቀን። ✨፭፦ ጳጉሜ ፭ የሰንደቅ ዓላማና የቅድስት ቤተ        ክርስቲያን ቀን። ✨፮፦ ጳጉሜ ፮ ከሱስ ሁሉ የመላቀቂያ ቀን። ✳️በመጀመሪያ የዛሬውን የማዕተብ ቀንን እንዴት አክብረን ማሳለፍ እንዳለብን በጥቂቱ እንመልከት። ➡️ጳጉሜን ፩ ፦ የማዕተብ ቀን፥ የአንገት ማዕተብ የማሰር ቀን፥ ነገ ቴሌግራማችን :ፌስቡካችን በአንገት ማዕተብ ክር ተጥለቅልቆ ይውላል። ማዕተቤን አልበጥስም ስንል እንውላለን። ወዳጄ መጪው ዘመን ዘመነ ሰማዕታት ነው። ማዕተብህን የምታጠብቅበት። ማዕተብ ማሰር ማለት ቀላል መስሎ እንዳታየው። ማዕተብ ማለት ከቅድስት ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ሃይማኖትህ ጋር ላትፋታ ቃልኪዳን የመግባትህም ምልክትም ነው። ማዕተብ ማሰር ማለት ማንነትህን፣ ማን መሆንህን ሳትናገር በሰው ሁሉ ፊት መመስከርህን የምታውጅበት ነው። እኔ ኦርቶዶክስ ነኝ። እኔ የተዋሕዶ ልጅ ነኝ ብለህ በአፍህ መናገር ሳይጠበቅብህ አንገትህ በራሱ ጮሆ የሚናገርልህ ማለትህ ነው። ማዕተብ የሌለው አንገት የኦርቶዶክሳዊ አንገት አይደለም። እሱ የአህዛብ አንገት ነው። የተዋሕዶ ልጅ አንገት በማዕተብ ያሸበረቀም ነው። ማዕተብ ከሰባኪ በላይ ጮሆ የሚሰብክልህ ሰባኪ ነው። “ እላችሁማለሁ፥ በሰው ፊት የሚመሰክርልኝ ሁሉ፥ የሰው ልጅ ደግሞ በእግዚአብሔር መላእክት ፊት ይመሰክርለታል፤ በሰውም ፊት የሚክደኝ በእግዚአብሔር መላእክት ፊት ይካዳል። ሉቃስ፣ 12 8-9 እናም ነገ ጳጉሜን አንድ ቀን ብፁዓን አባቶቻችን ወደ ቤተ መንግሥት መብታችንን ሊያስከብሩ ይሄዳሉ። አንታረድም፣ አንቃጠልም። አንከፋፈልም ለማለት ቤተ መንግሥት ይሄዳሉ።እኛ ደግሞ ፌስቡኩን በአንገት ማዕተብ ክር አጥለቅልቀነው እንውላለን ማለት ነው። ቀኑም የማዕተብ የ ማሰር ቀን ሆኖ ይውላል ማለት ነው። የማዕተብ ክር የሌላችሁ ነገ ጠዋት ከቤተ ክርስቲያን ደጃፍ ማዕተቡን ከነመስቀሉ ግዙ። ገዝታችሁም ለካህን አስባርኩ። ያልተባረከ የማዕተብ ክርም አትሠሩ። ነገ ቀኑ ከዚህ ቀደም በአንድም በሌላም ምክንያት ማዕተባቸውን የበጠሱ የተዋሕዶ ልጆች ደግመው ማዕተባቸውን የሚያስሩበት ቀን ይሁን። ወዳጄ ወርቅና ብር የሀብት መግለጫ እንጂ የማዕተብ ክርን አይተኩም። እንደ ማዕተብ ክርም አይቆጠርም። ማነሽ አንቺ ቆንጆዬዋ የእኔ ኦርቶዶክሳዊቷ እህቴ ከዚያ መለሎ መቃው አንገትሽ ላይ ማዕተብሽን እሰሪበት። ማነህ ወንድም ጋሼ አንተ ጎበዝ በአንገትህ ላይ ያጠለቅከውን የውሻ ማሠሪያ የሚመስለውን ሰንሰለት አውልቀህ ጣለውና በማዕተብ ክርህ ተካው። በሠርጋችሁ ዕለት ላይ ፕሮቶኮል ያበላሻል እያስባለ አጅሬ ሰይጣን ከስንት እህቶች አንገት ላይ ማዕተባቸውን አስበጠሰ? ገዳይ ቢመጣ እንኳን ሰማዕትነት የምትቀበለው አንገትህ ላይ ባለው ማዕተብህ ታይቶ ነው። አሁን ሁሉም በቁጥር ብዙ ነን የሚለው አንገትህ እንደነሱው ሌጣ መሆኑን ስላየ ነው። ወዳጄ ፋራ ልትባል ትችላለህ፣ ዘመናዊ አይደለሽም ልትባይ ትቺያለሽ፣ ነገር ግን አንተ አንቺም የጥንታዊቷ፣ በዘመናት መካከል ማርጀት የሌለባት የጥንታዊቷ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ልጆች ናችሁ። ታድለን በእመቤቴ። ተመስገን አምላኬ ሆይ ከሀገር መርጠህ ኢትዮጵያ የፈጠርከኝ። ከዜግነት መርጠህ ኢትዮጵያዊ ያደረግከኝ። ከሃይማኖት መርጠህ የኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ልጅ ያደረግከኝ በድጋሚ ተመስገንልኝ። ✨እኔ ኢትዮጵዊ ነኝ ያውም የተዋህዶ ልጅ  እምነቴ በልቤ መስቀሉ በአንገቴ።

ድንግል ሆይ ! 👉 አንቺን የወለደ ማህጸን እንዴት ያለ ብሩክ ነው 👉 አንቺን የታቀፉ ክንዶችስ እንዴት ያሉ ድንቅ ናቸው ! 👉 አስራ ሁለት ዓመት ወደ ቤተመቅደስ የተመላለሱ እግሮችሽስ እንዴት የከበሩ ናቸው ! 👉 የቅዱሱን መልአክ ብሥራት የሰሙ ጆሮዎችሸስ እንዴት ያሉ ንቁ ናቸው ! 👉 የቃልን ሰው መሆን ያመነው ልብሽ እንዴት ያለ ንጹሕ ነወ ! 👉 ዘጠኝ ወር ከአምስት ቀን ጌታን የተሸከመው ማሕፀንሽ እንዴት ያለ ግሩም ነው ! 👉 ይህን ታላቅ አምላክ የታቀፉ ክንዶችሽስ እንዴት ያሉ ጽኑ ናቸው ! 👉 ጌታዬን ያጠቡት ጡቶሽን እንዴት የለመለሙ ናቸው ! 👉 ድንግል ሆይ ክብርሽ ከፍ ያለ ነውና አከብርሻለሁ 👉 ሰላሳ ሶስት ዓመት ከሶሶት ወር ከጌታ ጋር ያኖረሽን እምነት እኔ ልጅሽ ለአንድ ሰዓት እንኳ የለኝምና እጅግ ጎስቋላ ነኝ። 👉 አስራ ሁለት ዓመት ከወንጌላዊው ዮሐንስ ቤት ያኖረሽን ልበ ሰፊነት እኔ ደካማው ልጅሽ ለአንድ ሰዓት እንኳ ከምወደው ጋር ለመሆን አልታደልኩምና እጅግ ደካማ ነኝ ! 👉 ቅድስት ሆይ የምልጃሽ በረከት የእግዚአብሔርን እገዛ ይላክልኝ ። 👉 ፍልሰትሽ መጪውን የምዕመናንን ትንሳኤ ጎልቶ ያሳያል ። 👉ዕርገትሽ መጪውን የምዕመናን ዕርገት በግልጥ ያስተምራል ። 👉 ከሚታስበው በላይ  ቅድስት ፣ ከሚነገረው በላይ ትሁት ፣ ከምሰማው በላይ ቡሩክት ፣ ከጻፉልሽም በላይ ንጽህት ፣ ከተረኩሽም በላይ ልዕልት ነሽና ልቤ ታመሰግንሻለች ! ዲያቆን እስጢፋኖስ ደጀኔ ነሐሴ 16 ቀን 2015 ዓ.ም. በማርያም ይህን ጽሁፍ ለኦርቶዶክሳውያን ሼር ሼር ሼር አድርጉት 🙏🙏🙏

እባካችሁ በጥሞና አንብቡት 🙏🙏🙏 👉 ለአራት ቀናት ብቻ ለሞተው አልዓዛር ያለቀሰ ጌታ ለዘመናት በኃጢአት ለሞትን ለእኛ ምንኛ ያለቅስ ይሆን? 👉 ሰውነታች በበደል ለረከሰ ፣ በምኞት መቃብር ለተቀበርን ፣ በዝሙት ለተበላሸን ፣ በጥላቻ ለሸተትን ለእኛ ክርስቶስ ምንኛ ያለቅስ ይሆን? 👉 የኃጢአት ድንጋይ ተጭኖን ፣ የፍትወት መግነዝ ተጠምጥሞብን ላለን ለእኛ የጌታ ዕንባ ምን ያህል ይፈስስልን ይሆን? 👉 አልዓዛርስ ውጣ ቢባል ይወጣል ፣ ካለንበት ኃጢአት መቃብር መውጣት ለማንፈልግ ለእኛ ጌታ እንደምን ያለቅስ ይሆን? 👉 የእኛ ሞት ከአልዓዛር ሞት በላይ ዘልቆ የማይሰማው ይመስላችኋል? 👉 እንዴት አይሰማውም? ለአልዓዛር ዕንባውን ያፈሰሰው ጌታ ለእኛ እኮ ያፈሰሰው ደሙን ነው ።       ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ ቻናሉን ለወዳጅ ዘመድዎ ሼር ማረግ አይርሱ። @orthodox26 @orthodox26

+።።። ተሸክሜህ ነው ።።።።።+ ... በበርሃ ይሄድ የነበረ ሰው ወደ ኋላው ዞሮ ሲያይ ከእርሱ ሌላ አንድ ጥላ ይመለከታል:: የዚህም ጥላ ነገር አሳስቦት የማን እንደ ሆነ ያመለክተው ዘንድ ወደ እግ
+።።። ተሸክሜህ ነው ።።።።።+ ... በበርሃ ይሄድ የነበረ ሰው ወደ ኋላው ዞሮ ሲያይ ከእርሱ ሌላ አንድ ጥላ ይመለከታል:: የዚህም ጥላ ነገር አሳስቦት የማን እንደ ሆነ ያመለክተው ዘንድ ወደ እግዚአብሔር ጸለየ። እግዚአብሔርም :- "ከኋላህ የተመለከትከው ጥላ የእኔ ነው። አንተን እየጠበኩህ እንደሆነ ታውቅ ዘንድ ይህን ምልክት አሳየውህ" አለው። ያም ሰው ፈጣሪው ከእርሱ ጋር እንዳለ በመስማቱ እጅግ ደስ እያለው ጉዞውን ቀጠለ። ጥቂትም እንደተጔዘ ወጣ ገባ የሆነ በጣም አስቸጋሪ መንገድ አጋጠመው:: ሰውየውም ያን አስቸጋሪ መንገድ እንደ ምንም ብሎ ለመውጣት ታገለ። በትግሉ መካከል ግን ወደ ኋላው ዞር ብሎ ቢመለከት ቀድሞ ያየውን ጥላ አጣው። ከዚያም ፈታኝ መንገድ እንደ ምንም ብሎ ከወጣ በኋላ፣ በታላቅ ኃዘን ሆኖ እየተበሳጨ ፈጣሪውን እንዲህ ሲል ጠየቀው :- "ምንም ችግር ባልገጠመኝ በሰላሙ ጊዜ "ከአንተ ጋር ነኝ ስትል ጥላህን አሳየኸኝ፣ የአንተ እርዳታ በሚያስፈልገኝ ጊዜ ግን ራስህን ሰወርክብኝ:: ይከተለኝ የነበረውን ጥላም ዘወር ብዬ ባየው አጣኹት። ለምን ተውከኝ ?" :: እግዚአብሔርም :- "በመከራህ ጊዜ ጥላዬን ያጣኸው ትቼህ እኮ አይደለም። ተሸክሜህ ነው!" ብሎ መለሰለት። ክፉውን ዘመን በክንፈ ረድኤቱ ተሸክሞ የሚያሻግረን እግዚአብሔር ነው። እርሱ አይተወንም፤ አይንቀንም። እኛም ከእርሱ ውጭ ተስፋ የምናደርገው የለንም። ጌታ ሆይ ስንት ዘመን ተሸክመኸኝ ምነው ተውከኝ ብዬህ ይሆን? ደካማው ልጅህን ይቅር በለኝ።

መልስ ፩, ሐ ፪, ሐ ፫, 👉 ምሥጢረ ጥምቀት     👉 ምሥጢረ ሜሮን     👉 ምስጢረ ቁርባን     👉 ምሥጢረ  ክህነት     👉 ምሥጢረ ተክሊል     👉 ምሥጢረ ንስሀ     👉 ምሥጢረ ቀንዲል ፬, ቅዱስ ዮሐንስ በእውነት ጥሩ ተሳትፎ ነበር ለሁላችሁም ቃለ ሕይወት ያሰማልን በርቱልኝ 🙏🙏🙏

፬, ከአርዕባቱ ወንጌላውያን ውስጥ በንስር የተመሰለው ቅዱስ ማነው?

፫, ሰባቱ(፯) ምሥጢራተ ቤተ ክርስቲያን የሚባሉትን ዘርዝሩ?

፪, በይሁዳ ምትክ ከዐሥራ አንዱ ጋር የተቆጠረው ሐዋርያ ማን ነው? ሀ.ማቴዎስ ለ.ሉቃስ ሐ.ማትያስ መ.ቀለዮጳ

፩, አማኑኤል ማለት ምን ማለት ነው?      ሀ.እግዚአብሔር ብርሃን ነው      ለ.እግዚአብሔር ፍቅር ነው      ሐ.እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ነው      መ.እግዚአብሔር ፈጣሪ ነው