Secrets of Truth - 𝘽𝙮 𝙍𝙚𝙨𝙝𝙖𝙙
前往频道在 Telegram
● ዲናችንና በሚመለከት ወቅታዊ መረጃዎችን ➶ Current information about Muslims and Islam 🔗 ሌሎችንም አንገብጋቢ ጉዳዮችን የምንተዋወስበት Channel ነው‼️ ➞ በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ አጠር ያሉ ስንኞች (በተለይም ስለ ፈለስጢን 🇵🇸) 🎯 አላማዬ:- የእውነትን ሚስጥሮች ማጋለጥ ነው‼️ #Free_Palestine 🇵🇸
显示更多213
订阅者
无数据24 小时
-17 天
-430 天
帖子存档
ይህ ዘመን ዛሬም አለ⁉️
================
«እኔ በህይዎት እያለሁ በሰፈራችን የአዛን ድምፅ መስማት አልፈልግም!»
||
✍ በፊት ነበር በአጼው ዘመን እንዲህ አይነት እብሪት ስንሰማ የነበረው። አሁን ባለንበት በብልፅግና መንግስት ዘመን ደግሞ እንደ እያሱ ኢሊያስ (ፕሮፌሰር) አይነት የፓርላማ አባላት በጣት የሚቆጠሩ ሰዎችን ፒቲሽን አስፈርመው «በሰፈራችን መስጅድ ማየት አንፈልግም!» ብለው ለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አቤቱታ አቅርበዋል።
የሚገርመው ይሄ አይደለም። እነ እያሱ ይህን ለማድረግ ሲያሴሩ ቅንጣት ኃፍረት አልያዛቸውም። ይህን ቅሬታ ያቀረቡለት የከተማው አስተዳደር ቅሬታቸውን ተቀብሎ መስጂዱን አስቁሞታል።
በኮልፌ ቀራኒዮ ክ/ከተማ ወረዳ 05 ዘነበ ወርቅ አካባቢ 72 ባጃጅ ተራ የሚገኘው «አግራው» በመባል የሚታወቀው መስጅድ በነ እያሱ ሙስሊም ጠልነት ሳቢያ ተከልክሏል።
በነገራችን ላይ… እያሱ ኢለያስ የወንጌላዊያን ቁልፍ ሰው ነው።
በብዛት ሙስሊም አለበት በሚባልበት ቤተል አካባቢ «አንድ ቸርች ለአንድ አማኝ» የተባለ መርህ የተላለፈ ይመስል ባዶ ቦታ አለ የሚባለውን ሁሉ በህገ ወጥነት አጥረው ይገኛሉ የሚል መረጃ ደርሶኛል።
ሙስሊሙ እንደ ሌሎች ያገኘውን ባዶ ቦታ ሁሉ በጉልበት አጥሮ ስጡኝ ማለት ጠፍቶት አይደለም። እንዳውም ቢያደርግ አግባብ አለው፤ ምክንያቱም የማይገባውን ስለማይጠይቅ።
ግን ይህ ሁሉ ያገኘውን ማጠሩ ለሁከትና ብጥብጥ ይዳርጋል፣ ስርዓት አልበኝነት ይነግሳል፣ ሰላሟ በየቦታው ለምትናወጥ ሃገር «በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ!» ይሆናል ብለን በህጋዊ መንገድ የመስጅድ ቦታ ይሰጠን ዘንድ ጠይቀናል። እንደ ሌሎች በሄክታር አልጠየቅንም።
እምቢ ብላችሁ ወደ ስርዓት አልበኝነት እንድንገባ አትገፋፉን።
ለምነናችሁ ካልሰማችሁን ግን ሁሉንም እናውቅበታለን። እናንተም ታውቃላችሁ!
በየቦታው ሰላሟን አደፍራሽ ኃይል ለበዛባት ሃገር አዝማች ያዥ አንሆንም ብለን እንደተለመደው በሆደ ሰፊነት እያሳለፍን እንገኛለን።
ለአንድ ግለሰብ ተብሎ ካርታ አምክነናል… ገለመሌ የሚል አግባብ የሌለው ኮተታችሁን ትታችሁ የሚሊዮኖችን ድምፅ የምትሰሙ ከሆነ ሳይውል ሳያድር የመስጂዱን ቦታ ወደነበረበት መልሱ። ይሄ ንቀትና እብሪታችሁ ባይደጋገም ጥሩ ነው።
ወይንስ መሰል ርዕስ እያስነሳችሁ እንደተለመደው የንፁሐን ደም ጥማታችሁን ልታረኩ ነው?
ተመሳሳይ ገድሎ በዝምታ መታለፍ ይኖራል መስሏችሁ በየ ሆነ ኢንተርቫሉ የተለያዬ የግጭት ነጋሪት እየጎሰማችሁ ሰላማችንን አትነሱን።
ይሄው ነው!
♠
Cc:
===
Adanech Abiebie- አዳነች አቤቤ
Office of the Prime Minister-Ethiopia
Mayor Office of Addis Ababa
||
t.me/MuradTadesse
fb.com/MuradTadesseOfficial
ummalife.com/MuradTadesse
🔰 ያለ ምላሽ
የሳር ድርቆሽ ውስጥ መርፌ (💉) የመፈለግን ያህል ከባድ ነገር የለም፤ ነገር ግን ከውስጣችን ፍላጎት ካለንና ጥረት ካደረግን በሳር ድርቆሽ ውስጥ እኳን ቢሆን መርፌውን እናገኘዋለን።
አንድ ነገርም ጠንቅቀን እናውቃለን መርፌውን በምንፈልግ ወቅት መርፌው ሊጎዳን እንደ ሚችል። ይህ ሁሉ ሆኖም ተባብረን፣ ከውስጣችን ፍላጎት ኖሮና ጥረት ከታከለበት መርፌው ሳይጎዳንም ልናገኘው እንችላለን።
ይህን የምናውቀው መርፌውን በሳር ድርቆሽ ውስጥ እናገኘዋለን ብለን በሙሉ እምነት ስንፈልግ ብቻ ነው።
የትኛውም ነገር ጥረት ይጠይቃል።
➻ይህ ጥረታችን ብዙ የሆኑ እኛን ሊፈታተኑን የሚችሉ እንቅፋቶችም ሊኖሩት ይችላሉ ነገር ግን ጥረታችን ከጧጧፍነውና ብዙ ሆነን በአንድነት ከተባበርን ምንም ያህል የህይወት ጉዞአችን ከገለባው ያልተለየ እንክርዳድ ቢበዛበት፤ አብሮነታችንና ቅንነታችን እነዚህን እንቅፋቶች የመቋቋም ኃይል ይኖረዋል።
ጠንካሮች ሆነን በአንድነት እንዲሳካልን የፈለግን እንደሆነ ብዙ ጥንካሬን የሚሹ ጥረቶችን ማድረግ ይኖርብናል።
➻ ጥንካሬን ከሚሹ ሲታዩ ግን ቀላል ከሚመስሉ ነገሮች ብንጀምር......
ያለ ምላሽ ማፍቀርን
ያለ ምላሽ ደግ መሆንን
ያለ ምላሽ ሰዎችን ማገዝና መርዳትን
ያለ ምላሽ ማገልገልን
ያለ ምላሽ ሰዎችን ማክበር
ያለ ምላሽ ሰዎችን መውደድን ልማዳችንና ማንነታችን ማድረግ‼️
አዎ እንደ መልካም ስራ ጥንካሬን የሚፈትን ምን ነገር አለ?
- እየተጠሉ መወደድ፤
- እየተዋረዱ ክብር መስጠት፤
- በጥላቻ መንፈስ እየታዩ ፍቅርን መስጠት
- እየተገፉ አለሁኝ ማለት፤ ጠንካራ ማንነትን ይጠይቃል። ይህ ጠንካራ ማንነት ደግሞ ከየትም አይመጣም ከኛው ድግግሞሽ ያለበት ሙከራና ጥረት ነው።
⛔ ትዕግስትን አንደ ፍርሃት፣
⛔ ይቅር ባይነት እንደ ውርደት፣
⛔ አክብሮት እንደ ማስመሰል የሚቆጥሩ ሰዎች ብዙ ናቸውና የነሱን ተቃውሞ፣ ዛቻና ትችት የሚችል አቅም መገንባት ይኖርብናል። ይህ አቅም ደግሞ የሚመጣው ምንንም ነገር ያለ ምላሽ ስናደርግ፤ ድርቆሽ ላይ መርፌ የመፈለግን ያህል ከባድ ነገሮችን በአንድነት ስንደፍር ነው!!
በረሻድ ኢብኑ ሙዘሚል
tiktok.com/@sharpswords1
https://t.me/SharpSwords1
www.youtube.com/@SharpSwords1
Instagram.com/sharp_swords1
https://ummalife.com/ReshadMuzemil
አስቸኳይ መረጃ‼
=============
(ለሁሉም ይሰራጭ!)
||
✍ «ፕሮፌሰር ኢያሱ ኢሊያስ በተባለ የፓርላማ አባል አስተባባሪነት ህጋዊ የመስጂድ ካርታ እና የግንባታ ፍቃድ ያለው የመስጂድ ቦታ ግንባታ እንዳይደረግ ያለምንም ህጋዊ ምክንያት ታገደ ።
በኮልፌ ቀራኒዮ ክ/ከተማ ወረዳ 5 አግራዉ በሚል ስያሜ የሚታወቀው መስጂድ በትላንትናው እለት ግዚያዊ የመስጂድ አጥር ግንባታ ለማድረግ እንቅስቃሴ በሚደረግበት ወቅት የወረዳው አመራሮች ከከንቲብ ጽ/ቤት ተደውሎልናል በሚል ግንባታው እንዲቆም አድርገዋል ።
ያለ ህግ አግባብ እንዲታገድ ስለተደረገበት ሁኔታ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ ጽ/ቤት መረጃ ሲጠይቁ የአከባቢው ማህበረሰብ ቦታው ላይ መስጂድ እንዳይገነባ ፒትሽን ፈርሞ ስላስገባ ነው ካርታውን አምክነን ሌላ ተለዋጭ ቦታ እንሰጣቹሃለን የሚል ምላሽ ተሰጥቷል ።
ፕሮፌሰር እያሱ የተባለው የፓርላማ አባል መኖሪያ ቤቱ ከመስጂዱ አጠገብ ሲሆን « እኔ እዚህ እያለው በፍፁም አጠገቤ መስጂድ አይሰራም ‼ » በሚል በተለያየ ግዜ በአከባቢው ሙስሊሞች ላይ እንደሚዝትና በአከባቢው ላይ የሚገኙ ከ 90 የማይበልጡ የሌላ እምነት ተከታዮችን አስተባብረው ፒትሽን ማስገባቱን ለማወቅ ተችሏል ።
ያለምንም የህግ አግባብ የመስጂዱ ግንባታ በመታገዱ ማህበረሰቡ በጊዚያዊነት የመስጂዱ ቅጥር ግቢ ውስጥ ድንኻን በመወጠር ሰላቱን በማከናወን ላይ ይገኛል።»
መላው ህዝበ ሙስሊም በነገው ዕለት ዘነበ ወርቅ አካባቢ 72 ባጃጅ ተራ አግራው ሰፈር በመገኘት የጁሙዓህ ሶላትን በህብረት በመስገድ መስጂዱን እንዲያስከብር ጥሪ ተላልፏል።
ሁሉም ሼር በማድረግ ላልሰማ ያሰማ።
መልዕክቱን ለሁሉም በማድረስ መስጅዳችንን እናስጠብቅ።
ኢማሙ አል አውዛዒይ እንዲህ ይላሉ፡
ዋናው ነገር ከሱናው ባቡር ላይ ተሳፈር! “አደራህን!የቀደምቶችን ፋና አጥብቀህ ያዝ! ሰዎች ጀርባቸውን ቢሰጡህም! ከሰዎች አስተያየት ተጠንቀቅ!በቃላት ቢያሸበርቁልህም እንኳ፣ አንተ ቀጥ ያለው መንገድ ላይ ከሆንክ ነገሩ በሒደት ይገለጣል።”
[አሸሪዓ ሊል አጁሪይ “(1/138)]
🔰 እወድቃለሁ የሚል ፍርሃት
● ውድቀት የሚባል ነገር የለም ፣ ትምህርት ቢሆን እንጂ፤ እነዚህ ትምህርቶችም ለማደግ እና ወደ ስኬት ጎዳና ለመራመድ ትምህርት ይሆኑናል።
አንድን ነገር መጨረሻውን ውድቀት ብቻ አድርገን የሳልነው እንደሆነ ውድቀት ብቻ ይከሰታል እናም መሞከር ለማቆም ምክንያት ይሆነናል። ልንወድቅ የምንችልበት ሁኔታ ለመሞከር ፈቃደኛ ያልሆነው ቀድሞውኑ ውድቀት ነው።
➽ በኛ በሰው ልጆች ህይወት ውስጥ፣ የተከናወነው እያንዳንዱ ታላቅ ክንዋኔ ወይም ድርጊት የጀመርነውን በ*መሳሳት ነው። ግን ያ ላለመሞከር በቂ ምክንያት አይሆነንም። መሞከር ነው ዛሬ ወይም ነገ ሁላችንም ለምናከብረው ስኬት ምክንያት ሊሆነን የሚችለው።
➽ በዚህ ህይወት እየተባለ በሚጠራው ጉዞ ውስጥ ስታልፍ፣ ከጊዜ ወደ ጊዜ ትወድቃለህ፣ ትሳሳታለህ፣ ልትደበደብና ልትወቀስም ትችላለህ ነገር ግን እነዚህን ፈተናዎች በትዕግሥት ያለፍካቸው እንደሆነ የሆነ ደረጃ ለይ መድረስህ አይቀሬ ነው።
📒 ብዙዎቻችን ወደ ሜዳው ሳንወርድ አስቀድመን የምንሸነፍበት ምክንያት ውድቀትን ፍራቻ ነው። ግን እኮ ከመሸነፉ በፊት መሸነፉን ያመነ፤ እሱ ወደ ሜዳ የመውረድ መብት የለውም።
➻ አዎ ሽንፈት ከስኬት ውጪ ሳይሆን በሉ እንደውም የስኬት አንዱ አካል ነው።
⚙️ ቀኑን ያለ ሌሊት እንደማናሳልፈው ሁሉ ፣ እንዲሁ እያንዳንዱ ታላቅ ስኬት ከብዙ ውድቀቶች ጋር ነው የሚመጣው። እንዲሳካልህ በሞከርክ ቁጥር የበለጠ ውድቀት ሊያጋጥምህ ይችላል፣ ነገር ግን አንድ ስኬት ብቻዋን የውድቀቶችህን ሁሉ መዝገብ ለማጥፋት የሚያስችል የተፈጥሮ ሃይል አላት።
➝ ስለዚህ የውድቀቶቻችን መዝገብ እስኪጠፋ ድረስ እንሞክር፣ እኮ አዎ ውድቀት መጨረሻ አይደለም፣ በሀሴት ወደፊት ለመኖርና ለመቀጠል ድፍረት ነው እንጂ።
⚙️ ውድቀቶቻችንን እንጋፈጥ ፣ ትምህርቶችን እንማርባቸው ፣ እንደገና ደጋግመን መሞከርን እንልመድ ፣ ይህን ያደረግን እንደሆነ የበለጠ ጠንካራ እና የተሻለ እንሆናለን!!
ደጋግመን ሞክረን እንደገና ካልተሳካ፤ አሁንም ደጋግመን እንሞክር። የድግግሞሽ ሙከራዎቻችን እኛን እየጠነከሩን ይሄዳሉ የበለጠ ጠቢብ እንድንሆን ይረዱናል፤ እኛ ድሮ እንደነበርነው ተመሳሳይ ሰው አንሆንም የተሻለ እንጂ።
በረሻድ ኢብኑ ሙዘሚል
tiktok.com/@sharpswords1
https://t.me/SharpSwords1
www.youtube.com/@SharpSwords1
Instagram.com/sharp_swords1
https://ummalife.com/ReshadMuzemil
አንተ አማኝ ነህ!
ረሱል (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦
﴿إذا سَرَّتْكَ حَسَنَتُكَ، وساءَتْكَ سَيِّئَتُكَ، فَأنتَ مُؤْمِنٌ﴾
“መልካም ስራህ ካስደሰተህ፣ መጥፎ ስራህ ካስከፋህ አንተ አማኝ ነህ።”
📚 ሲልሲለቱ አሶሂሃ: 551
﴿جاء رجلٌ إلى حذيفة، فقال: يا أبا عَبْد
الله، إني أخشى أن أكون منافقًا، قال: تُصَلِّي
إذا خلَوتَ، وتستغفرُ إذا أذنبـت؟ قال: نعم،
قال: اذهب، فما جعلك الله منافقا﴾
“አንድ ሰው ወደ ሁዘይፋ መጣና እንዲህ አላቸው፦ አንቱ የአብደላህ አባት ሆይ! እኔ ሙናፊቅ እንዳልሆን እፈራለሁ ሲላቸው። አሉት፦ ብቻህን ስትሆን ሶላት ትሰግዳለህ ወንጀልስ ሰርተህ ምህረት ትጠይቃለህ? አዎ! አለ። አሉት፦ ሂድ በቃ አላህ ሙናፊቅ አላደረገህም።”
📚 ኢብኑ አካሲር ታሪኹ ዲመሽቅ ላይ ዘግበውታል: 1/251
tiktok.com/@sharpswords1
https://t.me/SharpSwords1
www.youtube.com/@SharpSwords1
Instagram.com/sharp_swords1
https://ummalife.com/ReshadMuzemil
ታላቁ ዓሊም ሸይኽ ሷሊሕ ኢብኑ ፈውዛን አልፈውዛን አላህ ይጠብቃቸውና እንዲህ ይላሉ:–
"የማህበራዊ መገናኛ መንገዶች ለናንተ ልትጠቀሙባቸው የሚገቡ ጥሩ እድሎች ናቸው። ለተንኮለኞችና ለጥመት ሰባኪዎች እንዳትተዋቸው።"
📚(አሀምይየቱል ዐቂደቲ አስሶሒሐህ)
tiktok.com/@sharpswords1
https://t.me/SharpSwords1
www.youtube.com/@SharpSwords1
Instagram.com/sharp_swords1
https://ummalife.com/ReshadMuzemil
♦️ከጁሙዓ ቀን ሱናዎች
▪️ገላን መታጠብ
▪️ጥሩ ልብስ መልበስ
▪️ሽቶ መቀባት(ለወንዶች ብቻ)
▪️በጊዜ ወደመስጂድ መሄድ
▪️በነብዩ - ﷺ - ላይ ሰለዋት ማብዛት
▪️ሱረቱል ከህፍን መቅራት
▪️ዱዓ የሚያገኝበትን ሰአት መጠባበቅ
_
🔻በተጨማሪ አርፍደው ከመጡ የሰው ትከሻ ላይ እየተረማመዱ ሶፍ ውስጥ ከመግባት መቆጠብ, ኹጥባን በጥሞና ማዳመጥ, ሌላ ሰው ቢያወራም ዝምበል አለማለት እና ሶላት ካለቀ በኋላ ያመለጣቸውን ሰዎች ሶላት ሳይቆርጡ ረጋ ብሎ መውጣት ያስፈልጋል።
____
Repost from Sharp Swords // ስለታማ ሰይፎች
🇵🇸🤲 ታገስ!! ታገሡ ተባበሩ፡ ትድኑም ዘንድ አላህን ፍሩ፡ እርሱም የነገሮች በላጭ ነው፡
🇵🇸👇🇮🇱
የእኛ ወንድም እህቶች እየገደሏቸው ለፈጣሪ የሚሰጡ እና ታግሰው የአላህ ነስር የሚጠብቁ ምርጥ የፈጣሪ ህዝቦች ሲሆኑ ወ&ራሪ*ዎቹ ልባቸው በጥጋብ ያበጠ እርጉም ህዝቦች ናቸው!!
ጥጋብ እና እብሪት ክፉ ነው!!
አለም አይኑን ተክሎ ድርጊታቸውን እየተከታተለ በሚገኝበት በዚህ ሰአት የወንድሞቻችን ደም ሳይደርቅ ሰፋሪዎች ስለማስፈር እየመከሩ ነው!
ባወቁት መስራት!
ረሱል (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦
﴿لا تزولُ قدَما عبدٍ يومَ القيامةِ حتّى يُسألَ عن أربعٍ: وذكَر منها: وعن علمِهِ ماذا عمِلَ بهِ؟﴾
“አንድ ባሪያ በቂያማ እለት ስለ አራት ነገሮች ሳይጠየቅ እግሩ አይንቀሳቀስም። ከጠቀሱት ውስጥ፦ ‘በአውቅከው ነገር ምን ሰራህበት’ ተብሎ ይጠየቃል።”
📚 አልባኒ በሶሂህ አተርጊብ ወተርሒብ ውስጥ ሶሂህ ብለውታል: 3592
አቡ ደርዳ (رضي ﷲ عنه) እንዲህ ይላሉ፦
«إنّ أخوفَ ما أخافُ إذا وُقفتُ على الحساب أن يقال لي: قد علِمتَ فماذا عمِلتَ فيماَ علِمتَ؟»
“በጣም የሚያሰፈራኝ ነገር ለምርመራ ቆሜ አውቀህ ነበር በአወቅከው ነገር ምን ሰራህበት? መባሌ ነው።”
📚 ሐጢብ አልባግዳዲ ኢቅተዳ አልዒልሙ አልዓመል ውስጥ ዘግበውታል: 41
tiktok.com/@sharpswords1
https://t.me/SharpSwords1
www.youtube.com/@SharpSwords1
Instagram.com/sharp_swords1
https://ummalife.com/ReshadMuzemil
አቡ ሁረይራ (ረ.ዐ) እንዳስተላለፉት ነቢዩ (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦ «ከብርቱ መከራ፣ ከዕድለ-ብስነት፣ ከመጥፎ ዕጣ ፋንታ፣ የጠላት መደሰቻ ከመሆን፣ በአላህ ተጠበቁ።
📚(ቡኻሪና ሙስሊም)
📚ሪያዱ አስ-ሷሊሒን [1471]
በሌላ ዘገባ ሱፍያን ፦ አንዱን እኔ እንዳልኩት እገምታለሁ፤ ብለዋል።
ከሐዲሡ የምንማራቸው ቁምነገሮች
=› የአላህ መልዕክተኛ (ﷺ) ይህን ዱዓ እንድናደርግ ያዘዙን ሁለንተናዊ ዱዓ በመሆኑ ነው። በዚህችም ሆነ በመጭው ዓለም ከሚያጋጥም እኩይ ነገር በአላህ መጠበቅን ያስተምራል።
=› «ብርቱ መከራ» የሚለው ቃል የትኛውንም ችግር የሚያጠቃልል ቢሆንም ኢብኑ ዑመር ስለዚህ ቃል ተጠይቀው፣ «ሀብት ሳይኖር ቤተሰብ መብዛቱ ነው ብርቱ መከራ» በማለት ተናግረዋል። ይህ ትርጉም ድህነትና በችግር መቆራመድ በኢስላም ምን ያህል የማይደገፍ እንደሆነ ያሳያል። የአላህ መልዕክተኛ ﷺ ዘወትር ጠዋትና ማታ አላህን ከድህነት ይጠብቃቸው ዘንድ አዘውትረው ይለምኑት ነበር። ድህነትን ከክህደት ማቆራኘታቸው ምን ያህል የከበደ መከራ እንደሆነ ጠቋሚ ነው። ኢስላም ለዱንያዊ ስኬት አዎንታዊ አመለካከት እንዳለው ይህን መሰል ሐዲሦች ያመለክታሉ።
=› ድህነት መከራ እንጅ ጸጋ አይደለም። መወገድ ያለበት በሽታ እንጅ የጤና አይደለም። ሙስሊሞች በዓለማዊ ሥራዎች ላይ በትጋት መሳተፍ ከድህነት ራሳቸውን ለማላቀቅ መሥራት እንዳለባቸው፣ መጽዋች እንጅ ተመጽዋች መሆን እንደሌለባቸው ዲናቸው አበክሮ ያስተምራቸዋል።
የአላህ ስጦታ
► ጤና ይሰጠናል በዚህም ወንጀል እንሰራበታለን።
► ገንዘብ ይሰጠናል ሐራም ነገር እንሰራበታለን።
► እውቀት ይሰጠናል አላህ ባላዘዘን መንገድ እናውለዋለን።
► ዘር ፣ ጎሳ፣ ቤተሰብ ይሰጠናል በሱም እንኩራራበታለን።
እነዚህን ሁሉ የሰጠን አላህ መሆኑን ማስተዋል በቻልንና ወደ-አላህም በተመለስን። ወደ አላህ መመለሳችንም ግዴታችን ነው!
ስለዚህ አላህን ምህረት በመጠየቅ ፀፀትና ቁጭት ያለባትን ተውበት ልቶብት ግድ ይለናል። ተውበት ደግሞ የአላህ ምርጥ ስጦታ ነው‼️
ሀሳቡ ከኡስታዝ አህመድ ሼይኽ አደም « ወደ አላህ እንመለስ » ከተሰኘ ሙሐደራ የተወሰደ!
Join:-
YouTube.com/@SecretsofTruth
tiktok.com/@secretsof_truth
Instagram.com/secretsof_truth
t.me/Secretsof_Truth
Fb.com/SecretsofTruth1
https://ummalife.com/ReshadMuzemil
t.me/ReshadMuzemil
🆕⚠️ DID YOU KNOW?
Israel has dropped more than 22,000 American bombs in the first 45 days of the aggression on the besieged #Gaza Strip.
⭕ - That’s 480 bombs a day, 20 bombs an hour!
⭕ - During that time, the United States transferred at least 15,000 bombs, including 2,000-pound bunker busters, and more than 50,000 155mm artillery shells.
Source: The Washington Post
🇹🇷 Gazze Şeridi'ndeki saldırıların ilk 45 gününde 22.000'den fazla Amerikan bombası atıldı.
⭕ Yani günde 480 bomba, saatte 20 bomba!
⭕ Bu süre zarfında ABD, 2.000-pound bunker avcıları ve 50.000'den fazla 155mm top mermisi de dahil olmak üzere en az 15.000 bomba transfer etti.
