Secrets of Truth - 𝘽𝙮 𝙍𝙚𝙨𝙝𝙖𝙙
前往频道在 Telegram
● ዲናችንና በሚመለከት ወቅታዊ መረጃዎችን ➶ Current information about Muslims and Islam 🔗 ሌሎችንም አንገብጋቢ ጉዳዮችን የምንተዋወስበት Channel ነው‼️ ➞ በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ አጠር ያሉ ስንኞች (በተለይም ስለ ፈለስጢን 🇵🇸) 🎯 አላማዬ:- የእውነትን ሚስጥሮች ማጋለጥ ነው‼️ #Free_Palestine 🇵🇸
显示更多213
订阅者
无数据24 小时
-17 天
-430 天
帖子存档
ይህን የኢብኑ ዑሠይሚን ስለ አይሁዶች የተናገሩትን ድንቅ ንግግር አዳምጡልኝ'ማ።
متى النصر ؟ / الشيخ :محمد بن صالح #العثيمين رحمه الله
ለሃገሬ ክርስቲያኖች‼
===============
(ምናልባት ባለማወቅ ከሆነና ከገባቸው አድርሱላቸው!)
||
✍ በፍልስጤምና በእስራኤል መካከል ጦርነት በተፈጠረ ቁጥር፤ የሃገራችንን ሚዲያዎች ጨምሮ በርካታ ሚዲያዎች ጉዳዩን ሲዘግቡ በርካታ የሃገራችን ክርስቲያኖች በኮመንት መስጫው ላይ ይገቡና «ዲል ለእስራኤል!» ሲሉ ይደመጣሉ። ከፊሎች ደግሞ አለፍ ሲል በፖስት ደረጃም ጭምር ድጋፋቸውን ለእስራኤል ያሳያሉ። አንዳንድ ትልልቅ የሚዲያ ዘጋቢዎችም ለእስራኤል ያላቸውን ድጋፍ በሚያሳብቅ መልኩ ይዘግባሉ።
ለምን ይሆን⁉️
①) አብዛሃኛው የሃገራችን ክርስቲያን እስራኤል በተደጋጋሚ በባይብል ላይ ስሟ ስለተወሳ የክርስቲያን ሃገር ትመስለዋለች። እውነታው ግን እስራኤል ውስጥ የሚኖሩ ክርስቲያኖች ከ1.9%–2% ብቻ የሚሆኑ ናቸው።
(ይሄው ግቡና አንብቡ። https://www.pewresearch.org/short-reads/2016/03/08/key-findings-religion-politics-israel/)
የእስራኤል አብዛሃኛው ህዝቧ አይሁድ ነው። አይሁዶች ደግሞ የኛ ሃገር ክርስቲያኖች ፈጣሪያችን የሚሉትን ነቢዩ-ል'ሏህ ዒሳን (እየሱስ) እናቱን መርዬምን (ማሪያም) የሚራገሙ ናቸው። እሳቢያቸው ትክክል ባይሆንም እየሱስን የሰቀሉት አይሁዶች ናቸው ብለው አይደል እንደ የሚያምኑት?
ታዲያ እየሱስን አክብረው የአላህ ነቢይ ነው ብለው፣ እናቱን መርዬምንም የሴቶች ቁንጮ ብለው ከሚያወዱስት ሙስሊሞች እነዚህ የአይሁድ ጭራ'ቆች ቀርበዋቸው ነው የሚደግፏቸው?
*
②) የኛ ሃገር ከፊል ክርስቲያኖች ለሙስሊሙ ካላቸው የመረረ ጥላቻ ብቻ ተነስተው ነው «የጠላቴ ጠላት ወዳጄ ነው!» በሚል ስሌት አይሁዳውያኑን የሚደግፏቸው። እንጂ'ማ ጠላታቸው መሆናቸው አልተሰወረባቸውም።
*
√ ለማንኛውም የተወሰነ የአማኝነት ጭላንጭል ካላችሁ፤ በእስራኤል ከሚኖሩ ክርስቲያኖች ይልቅ በፈለስጢን የሚኖሩ ክርስቲያኖች በብዙ እጥፍ ይበዛሉ። በፈለስጢን የሚኖሩ ክርስቲያኖች ከ6%–15% ይደርሳሉ ተብሎ የሚገመት ሲሆን፤ ለፈለስጢን ነፃነት አብረው ከሙስሊሞች ጋር ይዋጋሉ። (ከታች ያያዝኳቸውን ፎቶዎች በጥሞና ተመልከቱ።)
እስራኤል የምትገ'ድለው ሙስሊሞችን ብቻ ሳይሆን እነዚህንም ክርስቲያኖች ጭምር መሆኑን ልብ ይሏል። (ይህን የቪድዮ ማስረጃ ተመልከቱ። https://t.me/MuradTadesse/32031)
የሚገርመው ደግሞ እነዚህ በፈለስጢን የሚኖሩ ክርስቲያኖች አብዛሃኛዎቹ የግሪክ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ተከታዮች ሲሆኑ፣ ሌሎች የአርመኒያና የሶሪያ ኦርቶዶክስ ተከታዮች ናቸው። በርግጥ በመካከላቸው በጣት የሚቆጠሩ የሮማን ካቶሊክ ክርስቲያኖችም አሉበት። ታዲያ ምን አስበው ይሆን ለእስራኤል መወገናቸው?
(ስለ ዳታው ይህን አንብቡ። https://culturalatlas.sbs.com.au/palestinian-culture/palestinian-culture-religion)
*
√ የእውነት የሰብዓዊነት ጭላንጭ ውስጣችሁ ላይ ካለ ደግሞ የኃይማኖቱን ጉዳይ ተውትና ንጹሕ ሰው ከሆናችሁ ፈለስጢናዊያን ከ1948 ጀምሮ መሬታቸው በእስራኤል ተወሮ በራሳቸው ሃገር እንደ ስደተኛ ተቆጥረዋል። እስካሁን ድረስ የገንዘቡን ተውትና በርካታ ህፃናትና አረጋዊያን እንዲሁም በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች ተገድለዋል። ሁሌም በማያባራው የእስራኤል ትንኮሳ ሳቢያ ለዘገባ ወደ ዌስት ባንክ፣ ጋዛና ምስራቅ እየሩሳሌም ያመሩ የአልጀዚራና መሰል ዓለም አቀፍ ሚዲያዎች ጋዜጠኞች በእምነታቸው ሙስሊም ያልሆኑትም ጭምር በእስራኤል ተገድ'ለዋል።
ፈለስጢን ስለደረሰባት ግፍ በማስረጃ በዚህ ሊንክ አንብቡ። https://www.aljazeera.com/news/2021/5/18/mapping-israeli-occupation-gaza-palestine
★
እንግዲህ ልብ ካላችሁ ያለው እውነታ ይህ ነው። ከዚህ በኋላ ከቻላችሁ ከተበደሉት ከፈለስጢናውያን ጎን ለመቆም ሞክሩ። አለበለዚያ ግን ሙስሊም ጠልነታችሁን ለጊዜው ዋጥ አድርጉትና ዝምታን ምረጡ። ይህ ካልሆነ ደግሞ አንዳንድ አይሁድ ትውልደ ኢትዮጵያውያን ለእስራኤል ገረድ ሆነው እንደሚዋጉት ሁሉ ሂዱና ተዋጉ። ከዚያ ውጭ ራሳችሁን ለትዝብት ትዳርጋላችሁ እንጂ እንኳን እንደናንተ ያለው ጭፍን አለቅላቂ ባለ ሚሳኤሎቹ እነ አሜሪካም ምንም አያመጡም። የሁሉም ሚሳኤልና አየር የሚንቀሳቀሰው ከአ-ር'ረሕማን ዐርሽ ስር ያውም ከመጨረሻዋ ሰማይ ስር ነው። ለተበዳይ ደግሞ ከሰባት ሰማይ በላይ ከዐርሹ በላይ ያለው አላህ አለ።
*
✔ እኛ ሙስሊሞች ግን ፈለስጢናውያን ሙስሊም ባይሆኑ ኖሮ እንኳ ተበዳይ ስለሆኑ ብቻ ከተበዳይ ጎን እንድንቆም ፍትሐዊው እምነታችን አዞናል። ሙስሊምነታቸው ሲጨመር ደግሞ ከጎናቸው እንቆም ዘንድ በኛ ላይ ሐቅ አላቸው።
ሌላ ማድረግ ባንችል እንኳ የግንዛቤ ፈጠራ በመሥራትና በዱዓእ የወንድሞቻችንን ህመማቸውን እንጋራለን። ሙስሊም በስጋ ዝምድና ብቻ አያምንም፤ ሙስሊም እስከሆነ ድረስ ዘርና ድንበር ሳይገድበው ወንድማማች ነው።
አላህ እንዲህ ብሎናል፦
(إِنَّمَا الْمُؤْمِنُونَ إِخْوَةٌ…)
«ምእመናኖች ወንድማማቾች ናቸው፡፡…»
[አል-ሑጁራት: 10]
*
ነቢያችን እንዲህ ብለውናል፦
(مثلُ المؤمنين في تَوادِّهم ، وتَرَاحُمِهِم ، وتعاطُفِهِمْ . مثلُ الجسَدِ إذا اشتكَى منْهُ عضوٌ تدَاعَى لَهُ سائِرُ الجسَدِ بالسَّهَرِ والْحُمَّى)
«በመዋደዳቸው፣ በርኅራኄያቸውና በመተዛዘናቸው የሙእሚኖች አምሳያ ልክ አንድ የሰውነት አካል ሲታመም ሌሎቹ እንቅልፍ በማጣትና በስቃይ እንደሚጠራሩት ነው።»
[አል-ቡኻሪይ: 5849፣ 6011
ሙስሊም: 2586]
*
ውዱ ነቢይ እንዲህም ብለዋል፦
(المُؤْمِنَ للمؤمنِ كالبُنْيانِ يشدُّ بَعضُهُ بعضًا)
«ሙእሚን (አማኝ) ለሙእሚም ልክ እንደ ግንብ ነው፤ ከፊሉ ከፊሉን ያጠናክረዋል።»
[አ-ት'ቲርሚዚይ: 1928
አል-ቡኻሪይ: 6026
ሙስሊም: 2585]
♠
አላህ የፈለስጢን ወንድሞቻችንን ከክፉ ነገር ሁሉ ጠብቆ ዲልን ያጎናጽፋቸው። ሽንፈትና ውርደት ለጽዮና'ዊያኑ ወራ'ሪዎች ይሁን። የዓለም ሙስሊሞችንም በሐቅ ላይ አንድ የምንሆንበትና በጠላቶቻችን ላይ ዲል የምንቀዳጅበት ወደ አላህም የምንመለስበት ያድርግልን።
||
ወንድማችሁ፦ ሙራድ ታደሰ
=========
ኦክቶበር 08, 2023 G.C.
ፈገግም እያላቹህ
የስረኛው ፖስት ፀሃፊ ኢዲ ኮሄን ይባላል።የፅዮናዊያኑ ሰራዊት ቃል አቀባይ ነው።እንዲህ ሲል ፃፈ:-
"ቁርአን እስረኛዎቻቹን በክብር ያዙ ሲል አዞ ነበር።ፍልስጤማዊያኑ ታጣቂዎች ግን አንገላቱብን😭" ይላል።
ዳርፉር ሙሐመድ ለኮሄን ምላሽ ሰጠ:-
"እንዴት ነህ ኢዲ..
ዛሬ አንድ ምት ቢያርፍብህ የቁርአን አያ ትዝ አለህ?ሌላ ምት ቢጨመርማ ከሰሒሀል-ቡኻሪና ሙስነድ ኢማም አሕመድ ሐዲስ ትነግረን ነበር😅"
ሳዑዲ ዓረቢያ ከሰዓታት በፊት በውጭ ጉዳይ ሚኒስተሯ በኩል ባወጣችው መግለጫ፤ በፍልስጤምና እስራዔል መካከል የተከሰተውን ጦርነት በንቃት እየተከታተለች እንደሆነ ገልፃ ሰላም እንዲወርድና ንጹሐን እንዳይጎዱ አሳስባለች።
ለዚህ ግጭት መነሻም የፍልስጤማዊያን ህጋዊ መብት መገፈፍ፣ ያልተቋረጠ ወረራና በመስጂደል አቅሷ ላይ ስልታዊ የሆነ ተደጋጋሚ ትንኮሳ መፈጸሙ መሆኑን አንስታለች።
ፈለስጢን በዓለም ሙስሊሞች ልብ ውስጥ ናት።
ሁሉም ሙስሊም ፈለስጢንን አርግዟል።
ያ ረብ! ይህን ወቅት መወለጃዋ ያድርግልን! የሙእሚን ዱዓእ ከአረመኔዎች ኒኩሊዬር የበለጠ ኃይል አለውና በመልካም ዱዓችን አንርሳቸው።
The Kingdom has also recalled its repeated warnings from the dangers of the explosion of the situation as a result of the continuation of the occupation, the deprivation of the Palestinian people of their legitimate rights, and the repetition of systematic provocations against its sanctities.
المملكة العربية السعودية في #بيان:
تحذر المملكة العربية السعودية من إنفجار الاوضاع في فلسطين نتيجة استمرار الاحتلال وحرمان الشعب الفلسطيني من حقوقه المشروعة وتكرار الاستفزازات الممنهجة ضد مقدساته 🌿🕋
|| Murad Tadesse
በቱርኪያ በኢስታንቡል ከተማ ከአሱር ሶላት ብኋላ በጋዛ ያለውን ጦርነት ጋዛን በመደገፍ የአንድነትና ሰልፍ አድርገዋል ። በርካቶች ዱዓ ሲያደርጉም ተስተውሎል ።
ሒጃብ እከለክላለሁ ብላ ዝግጅቷን ጨርሳ የነበረችው ፈረንሳይ ሒጃብ በግዴታ የሚያስለብስ የትኋን ወረርሽኝ ለቆባታል።
"ኢሬቻ ባህል እንጂ ሃይማኖት አይደለም" የሚሉ ሙስሊሞችን ማየት በጣም ልብ የሚያደማ ነው።❗️
ከላይ ሃለውን ቪዲዮ ተመልከቱ ለዛፉ ሲሰግዱ! ተመልከቱ የሚሰሩትን።❗️
🩸ሙስሊም ወንድምና እህቶቸ ሆይ❗️ የብሄር አጀንዳ አቅላችንን አስቶ ጀሃም እንዳይከተን እንጠንቀቅ። አላህን እንፍራ።!!
መስቀልን የምንቃወመው የአማራ ስለሆነ አይደለም።የኩፍር በአል ስለሆነ እንጂ።!
ኢሬቻ የኦሮሞ ስለሆነ በተለየ አይን አናየውም። የኩፍር ቡላና ዳለቻ የለውም። ሁሉም ኩፍር ነው። ሁሉም የጣኦት አምልኮ ነው። ሁሉም ተውሒድን በጥብቅ ከሚያስተምረው ኢስላም ጋር ፈፅሞ የሚፃረር ነው። ሁለቱም ከኢስላም ጠርጎ የሚያስወጣ የለየት ክህደት ነው።
ዛሬ የብሄር አጀንዳ እራሱን የቻለ ጣኦት ሆኗል። ሰዎች ለብሄር ሲሉ ካፊርን ይወዳሉ። ሙስሊምን ይጠላሉ። ለብሄር ሲሉ ለመስቀል፣ ለኢሬቻ ወግነው ይሟገታሉ። የኩፍር በአል ያከብራሉ።
የሚያሳፍረው ሸይኾችና ዱዓቶች ጭምር በዘረኝነት መለከፋቸው ነው። እስኪ የመስጂድ ኢማም ሆኖ፣ ጥምጣም ጠምጥሞ የኦርቶዶክስ ሰልፍ የሚያደምቅ፣ በዘራቸው የተነሳ ሙስሊም ትግሬዎችን ጭምር የሚያጥላላ፣ ለኢሬቻ "የእንኳን አደረሳችሁ" መልእክት የሚያስተላልፍን ልክፍተኛ አስቡ። ዘረኝነት አደዛዥ እፅ ነው።❗️ በዚህ በሽታ የተለከፈ ሰው እይታው ጠበብ ነው። አርቆ ማሰብ አይችልም። ይህንን ሀሺሽ፣ ይህንን ጣኦት አጥብቀን ካልተዋጋነው ብዙ ነገር ያሳጣናል።❗️
የያዝኩት ቪዲዮ ኢሬቻ የሚያከብሩ ሰዎችን ድርጊት ነው።
🩸ሁላችንም ሼር እናድርገው ሼር ሼር ሼር❗️
ታሪኩ ብዙ ነው ፤ ያስታወስነው ግን እኛ ብቻ ነን‼️
እኛ ሞኝ መስለናቸው ይደልሉናል በእውነታው ግን እኛን ወደውን አያውቁም የእነሱን እምነት እስከምንከተል ድረስ።
አላህም ይህንን እውነት በተከበረው ቃሉ ነግሮናል።
▲ ታዲያ እውነተኛው ታሪክ ይህ ከሆነ፤ አኛ እነሱ ይወዱናል በሚል ወራዳ አስተሳሰብ ከአላህ ለምን እንርቃለን!?
◉ የእነሱን ውዴታ እናገኛል በሚል የዘቀጠ አስተሳሰብ ሙስሊም ወንድሞቻችንና እህቶቻችንን ለምን እንበድላለን!?
◉ የእነሱን ክብር ለማግኘት በሚል፤ ከሙስሊሞች ሊመነጭ የማይችልን አስተሳሰብ እያመነጨን በዲናችን ለምን እንቀጥፋለን፣ ድንበርስ ለምን እናልፋለን!?
ወንድም እህቶቼ እኛ ምንም ብንዘቅጥላቸው እነሱ አይወዱንም የነሱን እምነት እስካልተቀበልን ድረስ። ስለዚህ ያማረና ውብ የሆነ ማንም የሚቀናበት ምነው ሙስሊም ባረገኝ ብሎ የሚቆጭበት ዲን አለን።
ከዘር፣ ከብሄር፣ ከጎሳችንና ከነብሳችንም ጨምሮ ሊነፃፀር በማይች ውዴታ አስበልጠን የምንወደው ዲናችንን (እስልምናችንን) ነው መሆን ያለበት!
መጎራበትም ካለብን፣ መጨነቅ መጠበብም ካለብን፣ መደገፍ ለክብራቸው ዘብ መቆምም ካለብን ለሙስሊም እህት ወንድሞቻችን ነው መሆን ያለበት። መተናነስም ካለብን ለሙስሊሞች ነው መሆን ያለበት!!
በዱኒያ ጉዳይ ሲሆን ሙስሊም ካልሆኑ አካላትም እስልምናችንን በማይጋጭ መልኩ ከነሱ ልንውል ልናመሽ እንችላለን። ከዛ ውጭ ግን ዲናችንን ልናስደፍር አይገባንም! በኛው ጥፋት፣ በኛ ወንጀል፣ በኛ አላዋቂነት፣ በኛ ችኮላ፣ ለስልጣን ባለን ጥማትና ጉጉት ምንም አይነት ሙሲባ ከመጣብን በኛ ይምጣ እንጂ በዲናችን መሆን የለበትም።
⭕️ ዲናችን ነው የኛ ህይወት!!
⭕️ እስልምናችን ነው የህይወት መርሆዎችን!!
⭕️ የአላህ መልዕክተኛ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰልም) ብዙ መስዋዕትነት የከፈሉለት ዲን ነው። ሶሀቦች የቆሰሉለት፣ የተሰቃዩለት ዲን ነው። ዲኑን ያከበሩ ይከበራሉ፣ ዲኑን ለማዋረድ የሚሞክሩ ደግሞ በዱኒያም ከአኺራም ይዋረዳሉ። አላህ ይጠብቀን።
〽️〽️▬▬▬▬〽️〽️
► የትላንቱ ታሪክ ዛሬም እንደዛው ነው!!
► የትላቱ አግላይነት ዛሬም በዘመናዊነት ቀጥሎዋል።
► የትላንቱ ሙስሊም ጠልነት ዛሬም በዘመነ መልኩ እየተጧጧፈ ነው።
► የትላንቱ ሙስሊምን መጨፍጨፍ ማሰቃየት ዛሬም በዘመነ መንገድ እየተካሄደ ነው።
► የትላንቱ ሙስሊም እህቶችን ሂጃብ የማስወለቅ ሴራ ዛሬም በትምህርት ሴኩላሪዝም በሚል በወደቀ አስተሳሰብ እንደቀጠለ ነው።
▲ ይህ ሁሉ እየሆነ እኛ ለሙስሊሙ ማህበረሰብ በመታገል ፋንታ ሌላ ዝባዝንኬ ነገር ያምረናልን!?
〽️ ይህ ሁሉ እየሆነ እኛን (ሙስሊሞችን) ስልጣንና ገንዘብ ይሸውደናልን!?
〽️ ይህ ሁሉ እየሆነ አውቀንም ሆነ ሳናውቅ ሙስሊም ጠል ከሆነው ከአግላይና ከግፈኛው ጋር ማበራችን አላህ እኛ ላይ በላዕ (መዓት) እንዳያመጣብን አንፈራምን!? *እንደው በአላህ፡ ቆም ብለን አናስብምን።*
*ትላንትናም እኮ እንደዚሁ ነበር፤ ዛሬም ልክ እንደዛው ነው።*
ወንድም እህቶች የተቀየረ ነገር የለም፣ የሙስሊም ጠላቶች ተላንትም ነበሩ ዛሬም አሉ።
⭕️ የተቀየረ ነገር ቢኖር እኛ ነን። በስልጣን፣ በገንዘብ፣ ጠፊ በሆነችው ዱኒያ እየተሸነገልን ሙስሊም ወንድም እሆቶቻችን ላይ በደል ሲፈፀም በዝምታ እናልፋለን። ይባስ ብለን *«ልወደድ ባይ እርኩስነታችን»* ብዙ ነገር ያስለፈልፈን ጀምሯል!!
ለታማኝነታቸው፣ ለእውነተኝነታቸው፣ ለንፁህ ልብ ባለቤትነታቸው፤ አላህ፣ መላኢኮች፣ ሰሃቦች የመሰከሩላቸውን የአላህን መልዕክተኛ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰልም) ከአላህ የታዘዙባቸውን ትዕዛዞችናና ሰሒሕ ማስረጃዎችን ችላ ብለን እኛ በስሜት ያለ እውቀት መቀባጠሩንም ተያይዘነዋል።
⭕️ ዛሬ ላይ “*« ተግባራቶች ሁሉ ለስልጣንና ለገንዘብ ሲባል የሚደረጉ ናቸው »*” የሚል ወራዳ ስሜት ውስጣችን ላይ ያለ ይመሥላል።
◆ አላህን ልንፈራ ይገባል፤ ለገንዘብ ለስሜት፣ ለስልጣን ስንል በሙስሊሙ ማህበረሰብ በተለይም የአላህን ውዴታ ፍለጋ ሂጃብ በለበሱ እህቶቻችን (ሱመያዎቻችን) ላይ በደል አንፈፅም። ⭕️*ክብራቸውን የሚነካ፣ ለሙስሊም ጠል አካላቶች ቀዳዳን የሚያበጅና ሙስሊሙን የሚጨርስ ሚሳኤል የሆነ ንግግር ከምላሳችን እንዳይወጣ።* ‼️
በወንድማችሁ ረሻድ ኢብኑ ሙዘሚል
ቀን:- መስከረም 25/2016 አ.ል
Join:-
YouTube.com/@SecretsofTruth
tiktok.com/@secretsof_truth
Twitter.com/Secretsof_Truth
Instagram.com/secretsof_truth
t.me/Secretsof_Truth
Fb.com/SecretsofTruth1
ለየትኛውም ለአስታየትና ድጋፍ:-
t.me/ReshadMuzemil
ኢማም አን-ነወዊ ረሂመሁሏህ ቲብያን በሚባለው መፅሀፋቸው ውስጥ እንዲህ ይላሉ
"ከ አላህ መፅሐፍ (ከቁርዓን) ጋር ከሚኖረን ስነ ስርዓት መካከል ይቆጠራል ይህን ይመስል አንቀፅ በምናነብበት ጊዜ
[وَقَالَتِ الْيَهُودُ يَدُ اللَّهِ مَغْلُولَةٌ ۚ]
(አይሁዶችም «የአላህ እጅ የታሰረች ናት» አሉ፡፡...)
ይህን የሚያነበው አካል ድምፁን ዝቅ አድርጎ ቀንሶ በማንበብ ከአላህ ጋር ስነስርዓትን መጠበቅ መቻል ይኖርበታል
ኢማም አን-ነኻኢ በዚህ መልኩ ነበር የሚያነቡት"
.......................................
የመካ ሀረም ኢማም የሆነው ቃሪዕ ሸይኽ አብደላህ አል-ጁሃኒ በዚህ ባማረ እና ስነ ስርዓቱን በጠበቀ መልኩ ይህን አንቀፅ አንብቦታል
©️ Toleha Ahmed
Join:-
YouTube.com/@SecretsofTruth
tiktok.com/@secretsof_truth
Twitter.com/Secretsof_Truth
Instagram.com/secretsof_truth
t.me/Secretsof_Truth
Fb.com/SecretsofTruth1
ለየትኛውም ለአስታየትና ድጋፍ:-
t.me/ReshadMuzemil
አሕመዲን ጀበል ይናገራል‼
ቪድዮው የቆዬ ቢሆንም ካለንበት ተጨባጭ ጋር መልዕክቱ ስለገጠመ፤ እስኪ ለነዛ ያጠፋ አይታረምም ብለው ለሚያስቡ በጭፍን ለሚከተሉት አድርሱላቸው።
ሰሞኑን በኢኽዋን ቡድን በኩል "መዳኺላ መዳኺላ" የሚሉ ጩኸቶች በዝተዋል። የዚህ ቡድን አባላት የጋራ በሽታ የሚጮሁትን ሆኖ አለመኖር ነው። "ስም እየሰጣችሁ አትከፋፍሉን" ይልና ዞሮ "ጃሚያ" "መድኸሊያ" እያለ ይወነጅላል። "ዑለማእ አትሳደቡ" እያለ የሱና ዑለማዎችን ግን "የቤተ መንግሥት ቅጥረኞች" እያለ እጅግ ፀያፍ ውንጀላ ይወነጅላል።
ከሰሞኑ ያደረጉትም ይህንኑ ነው። ምንም ዓይነት ቡድናዊ ይዘት በሌለው ጉዳይ ላይ ከብዙ ጩኸት መሃል ነጥለው "መዳኺላ" እያሉ ቡድናዊ ታርጋ መለጠፍ ላይ ተጠምደው አይተናል። አንዱ ኢኽዋኒም ስለ መዳኺላ ሊያብራራ እየተዘጋጀ እንደሆነ ፅፎ አይቻለሁ። ይህንን ካየሁ በኋላ ይህንን የዲን ነጋዴ ቡድን በተከታታይ ለመቆንጠጥ እያሰብኩ ነው። እነሱ ውንጀላቸውን በለቀቁ ቁጥር እየተከተሉ መከላከል አልታየኝም። ከዚያ ይልቅ የቡድኑንና የቁንጮ አካላቱን ጉዳጉድ በድምፅ ትምህርት ለመዘርዘር እያሰብኩ ነው። ሸይኽ ሙቅቢል - ረሒመሁላህ - "እኔ ማጥቃት ነው ደስ የሚለኝ። እንጂ መከላከል አይደለም" የሚሉት ወደው አይደለም። ባይሆን ጊዜየን ብዙም በነሱ ላይ ማጥፋት ስለማልፈልግ አለፍ አለፍ እያልኩ በሚመቸኝ ጊዜ ነው የማቀርበው፣ ኢንሻአላህ።
Ibnu Munewor
=
