ch
Feedback
Secrets of Truth - 𝘽𝙮 𝙍𝙚𝙨𝙝𝙖𝙙

Secrets of Truth - 𝘽𝙮 𝙍𝙚𝙨𝙝𝙖𝙙

前往频道在 Telegram

● ዲናችንና በሚመለከት ወቅታዊ መረጃዎችን ➶ Current information about Muslims and Islam 🔗 ሌሎችንም አንገብጋቢ ጉዳዮችን የምንተዋወስበት Channel ነው‼️ ➞ በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ አጠር ያሉ ስንኞች (በተለይም ስለ ፈለስጢን 🇵🇸) 🎯 አላማዬ:- የእውነትን ሚስጥሮች ማጋለጥ ነው‼️ #Free_Palestine 🇵🇸

显示更多
213
订阅者
无数据24 小时
-17 夊
-430 夊
帖子存档
The Messenger of Allāh  said: "When one of you stands to pray, indeed he is speaking privately to his Lord. Therefore, (let
The Messenger of Allāh ﷺ said: "When one of you stands to pray, indeed he is speaking privately to his Lord. Therefore, (let each one of you) look at how he speaks to his Lord privately." 【Sahīh Al-Jāmi' (1538)】

✍🏻 ስለ ሻዕባን ወር አጫጭር ጥቆማዎች ┄┄┉┉✽‌»‌🌼»‌✽‌┉┉┄┄ ☞ በሸይኽ ሙሐመድ ሷሊህ አል ዑሰይሚን «ሙስሊሞች ሆይ ያለነው በሻዕባን ወር ላይ ነውና በዚህ ወር ዙርያ አንድ ስድስት ነጥቦችን በማውሳት ልንከተለው ስለሚገባን ግዴታችን እናብራራለን። 💥የመጀመርያው ነጥብ የሻዕባን ወር ከሌሎች ወራት በተለየ ሁኔታ በፆም ይለያልን? አዎን ይለያል ። ምክንያቱም ነቢዩ [ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም] «በዚህ ወር ፆም ያበዛሉ። ከወሩ ጥቂት ቀናት እስኪቀራቸው ወሩን ይፆሙት ነበርና።» በዚህም ሱና መሰረት የአላህ መልእክተኛን [ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም] በመከተል በዚህ በሻዕባን ወር ፆም ማብዛት አለብን። 💥ሁለተኛው ነጥብ የሻዕባን ወር አጋማሽ ቀን ፆምን የተመለከተው ነው። ይህንን ቀን ለይቶ መፆምን የሚመለከቱ ከነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ያልተገኙና ትክክለኛ ያልሆኑ ደካማ ሀዲሶች ተነግረዋል። በነዚህ ተመርኩዞ ይህንን ዒባዳ መፈፀም ደግሞ አይቻልም። ከነቢዩ ለመተላለፉ ባልተረጋገጠ ማንኛውም ነገር አላህን ማምለክ አይፈቀድም። በመሆኑም የሻዕባን አስራ አምስተኛው ቀንን ለይቶ መፆም የሌለ ነገር ነው። ከመልእክተኛው ለመገኘቱ መረጃ ከሌለ ደግሞ ቢደዐ ነው። 💥ሶስተኛው ነጥብ፤ የሻዕባን ወር አስራ አምስተኛው ቀን ሌሊት ትሩፋትን ይመለከታል። ልክ ቀኑን መፆም የተረጋገጠ መረጃ እንደሌለው ሁሉ ለሌሊቱም ከሌሎች ሌሊቶች በላጭ ነው ተብለው የተነገሩት ሀዲሶች ከነቢዩ [ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም] ለመነገራቸው ትክክለኛ መረጃ የሌላቸው ደካማዎች ናቸው። ስለሆነም የሻእባን አጋማሽ ሌሊት ልክ እንደ ረቢዕ ወር ሌሊት፣ እንደ ረጀብ ወር ሌሊት እንጂ የተለየ ነገር የለውም። ተነገረ የተባለውም መረጃ ቀድሜ እንደገለፅኩት ደካማዎች ናቸው። 💥አራተኛው ነጥብ ይህችን የአስራ አምስተኛዋን ሌሊት ለየት አድርጎ ዝግጅት ፈጥሮ ማሳለፍ ቢደዐ ነው። ነቢዩ [ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም] ለየት አድርገው ያሳዩን፣ ሌሊቱን የሚሰገድ አምልኮትም ዝግጅትም የለምና። ስለዚህ ምሽቷ ልክ እንደ ሌሎች ምሽት ናት። አንድ ሰው ከዚያች ሌሊት በፊትም የለይል ሰላት መስገድ ልምዱ ከነበረ በዚያች ሌሊትም ተነስቶ መስገዱ ልክ እንደበፊቱ ነውና ችግር የለውም። ካልሆነና በፊት የማይሰግድ ከነበረ ዛሬ በሻዕባን "ለይለቱ ኒስፍን" ለየት አድርጎ መስገድ የለበትም። ምክንያቱም ከአላህ መልዕክተኛ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ያልተገኘ ተግባር ነውና። ከዚህም የከፋው ደግሞ አንዳንዱ ሰው የሆነ ያህል ረከዓ በዚህ ምሽት ይሰገዳል በሚል ለየት ያደርገዋል። ይሁንና ከነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ይህንን ምሽት ነጥሎ ለየት ማድረግ ስላልተገኘ ይህችን ምሽት በሰላት ልዩ አናደርግም። 💥አምስተኛው ነጥብ የአላህ ሱብሃነሁ ለነገሮች የሚያደርገው ውሳኔ በሻዕባን አስራ አምስተኛዋ (አጋማሽ) ምሽት ነውን❓ ምላሹም አይደለም ሲሆን፤ ምሽቷም የመወሰኛይቱ ሌሊት [ለይለቱል ቀድር] አይደለችምና ነው። ምክንያቱም "ለይለቱል ቀድር" በረመዳን ውስጥ የምትገኝ ምሽት ናት። ሃያሉ አላህ እንዳለው፤ ”إنا انزلناه“ "እኛ አወረድነው" ማለትም ቁርኣንን ለመጀመርያ ግዜ ያወረድነው ማለቱ ነው። ይህም ሙሉ ምዕራፉ ሲነበብ እንዲህ ይላል፤ إِنَّا أَنزَلْنَاهُ فِي لَيْلَةِ الْقَدْرِ ﴿١﴾ وَمَا أَدْرَاكَ مَا لَيْلَةُ الْقَدْرِ ﴿٢﴾ لَيْلَةُ الْقَدْرِ خَيْرٌ مِّنْ أَلْفِ شَهْرٍ ﴿٣﴾ تَنَزَّلُ الْمَلَائِكَةُ وَالرُّوحُ فِيهَا بِإِذْنِ رَبِّهِم مِّن كُلِّ أَمْرٍ ﴿٤﴾ سَلَامٌ هِيَ حَتَّىٰ مَطْلَعِ الْفَجْرِ ﴿٥﴾ Al-Qadr☞ القدر:- [1-5] [እኛ (ቁርኣኑን) በመወሰኛይቱ ሌሊት አወረድነው፡፡ (1)መወሰኛይቱም ሌሊተ ምን እንደ ኾነች ምን አሳወቀህ? (2)መወሰኛይቱ ሌሊት ከሺሕ ወር በላጭ ናት፡፡ (3) በርሷ ውስጥ መላእክትና መንፈሱ በጌታቸው ፈቃድ በነገሩ ሁሉ ይወርዳሉ፡፡ (4) እርስዋ እስከ ጎህ መውጣት ድረስ ሰላም ብቻ ናት፡፡(5)] ይህ ክስተትና ምሽቱም መቼ እንደሆነ ሲገልፅ እንዲህ ይላል፤ (شَهْرُ رَمَضَانَ الَّذِي أُنزِلَ فِيهِ الْقُرْآنُ هُدًى لِّلنَّاسِ وَبَيِّنَاتٍ مِّنَ الْهُدَىٰ وَالْفُرْقَانِ ۚ فَمَن شَهِدَ مِنكُمُ الشَّهْرَ فَلْيَصُمْهُ ۖوَمَن كَانَ مَرِيضًا أَوْ عَلَىٰ سَفَرٍ فَعِدَّةٌ مِّنْ أَيَّامٍ أُخَرَ ۗ يُرِيدُ اللَّـهُ بِكُمُ الْيُسْرَ وَلَا يُرِيدُ بِكُمُ الْعُسْرَ وَلِتُكْمِلُوا الْعِدَّةَ وَلِتُكَبِّرُوا اللَّـهَ عَلَىٰ مَا هَدَاكُمْ وَلَعَلَّكُمْ تَشْكُرُونَ) البقرة:- 185 [(እንድትጾሙ የተጻፈባችሁ) ያ በርሱ ውስጥ ለሰዎች መሪ ከቅን መንገድና (እውነትን ከውሸት) ከሚለዩም ገላጮች (አንቀጾች) ሲኾን ቁርኣን የተወረደበት የረመዳን ወር ነው፡፡ ከእናንተም ወሩን ያገኘ ሰው ይጹመው፡፡ በሽተኛ ወይም በጉዞ ላይ የኾነም ሰው ከሌሎች ቀኖች ቁጥሮችን (በልኩ) መጾም አለበት፡፡ አላህ በእናንተ ገሩን (ነገር) ይሻል፡፡ በእናንተም ችግሩን አይሻም፡፡ ቁጥሮችንም ልትሞሉ አላህንም ቅኑን መንገድ ስለመራችሁ ታከብሩትና ታመሰግኑት ዘንድ (ይህን ደነገግንላችሁ)፡፡ (185)] በዚህም መረጃ መሰረት ለይለቱል ቀድር ማለትም ፈጣሪያችን አላህ ለማንኛውም ነገር ሁሉ አመታዊ ውሳኔ የሚሰጥበት ምሽት በረመዳን ወር ውስጥ የምትገኝ አንዲት ሌሊት መሆኗን እንረዳለን። ምክንያቱም ሌሊቷ ቁርኣን የወረደባት ሌሊት ነች ። ቁርኣን ደግሞ የወረደው በረመዳን ወር ነውና የመወሰኛይቱ ምሽትም የምትገኘው በረመዳን እንጂ በሌላ ወር አይደለም። ስለሆነም የሻዕባን አጋማሽ ሌሊት "ለይለቱል ቀድር" የመወሰኛይቱ ምሽት አይደለችም። በዚያች ሌሊትም ለአመቱ የሚሆን ምንም የሚወሰን ነገር የለም። 💥ስድስተኛው ነጥብ፦ የሻዕባን ወር አጋማሽ ቀን ላይ አንዳንዶች ምግብ አዘጋጅተው ለድሆች በሚል የሚያከፋፍሉትና የእናት እራት፣ የአባት እራት ወይም የወላጆች እራት የሚሉት [እንዲሁም ባገራችን የእህል ዘሮችን ባንድ ላይ ሰብስቦ በመቀቀልና ከዚያም መጀመርያ ግቢ ውስጥና ውጪም በመበተን አመቱ የጥጋብ የርጋታ ይሁንልን የሚሉት] ሁሉ ከነቢዩ ያልተላለፈልን ከሰሃቦችም ሪድዋኑላሂ አለይሂም ያልተገኘ መጤ የሆነ ቢድዐ ነው። 👆 እነዚህን ስድስት ነጥቦች ጠቅሼ ብቆጥራቸውም ሌሎች ላብራራቸው የሚገቡ ሆነው ያለፍኳቸው እንዳሉ ግልፅ ነው። አላህ እኛንም እናንተንም ሱናን የሚያሰራጩ፣ ቢድዐን የሚያስጠነቅቁና ተመርተው የሚመሩ (ቅን ሆነው የሚያቀኑ) ያድርገን። ነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም በጁምዓ ኩጥባቸው ወቅት እንደገለፁት ከምሪቶች ሁሉ በላጩ የሳቸው ምሪት ነውና ቅኑን መንገድ የሚከተሉ፣ በሳቸው አመራርም የሚመሩ ያድርገን። «በማስከተል፤ ከንግግሮች ሁሉ በላጩ የአላህ ኪታብ ነው። ከአመራሮች ሁሉ በላጩም የሙሀመድ ምሪት ነው። መጥፎ ጉዳይ ማለት መጤዎቹ ናቸው። ሁሉም ፈጠራዎች ጥመት ናቸውና።»ብለዋል። 🍀〰〰〰〰〰〰🍀 በታላቁ ፈቂህ ሸይኽ ሙሐመድ ሷሊህ አል ዑሰይሚን [ረሂመሁላህ] __ 3 ሻዕባን 1437/ 11 ሜይ 2016 ትርጉም፦ አቡፈውዛን •┈┈┈•✿❁✿•┈┈┈• www.facebook.com/tenbihat

ድንቅ ሽልማት ~ ነፍል ወይም ግዴታ ያልሆኑ ሶላቶችህን ደበቅ አድርጋቸው። ነብዩ  እንዲህ ብለዋል:- "አንድ ሰው ሰዎች ሳያዩት የሚሰግዳት ግዴታ ያልሆነች ሶላት ከሰዎች እይታ ሾር ሆኖ ከሚሰግዳት ሶላት ሃያ አምስት (እጥፍ) ትስተካከላለች።" አልባኒ ሶሒሕ ብለውታል። [ሶሒሑልጃሚዕ: 3821] ©️©️©️ ይ🀄ላ🀄ሉን👇👇 share👇        tiktok.com/@secretsof_truth Instagram.com/secretsof_truth t.me/Secretsof_Truth Fb.com/SecretsofTruth1 ► ለሀሳብ፣ አስታየት ወይም ጥቆማ 👇👇 t.me/ReshadMuzemil

አላህ እንኳን ወደርሱ ለተጠጉ ባሮቹ ይቅርና ከርሱ ለራቁ እንኳን አዛኝና ሩህሩህ ነው። አላህ ሆይ! ሁሌም አንተን አስታዋሽ ወደአንተም ተመላሽ አድርገን 🤲 ይ🀄ላ🀄ሉን👇👇 share👇        tiktok.com/@secretsof_truth Instagram.com/secretsof_truth t.me/Secretsof_Truth Fb.com/SecretsofTruth1 ► ለሀሳብ፣ አስታየት ወይም ጥቆማ 👇👇 t.me/ReshadMuzemil

#ከእሳት_ለመራቅ_ፆም_አንዱ_መንገድ_ነዉ... "ለአላህ ብሎ አንድ ቀንን የፆመ አላህ ፊቱን ከጀሀነም ሰባ አመት ያርቃል።" ብለዋል ነብያችን() اللهم صل وسلم وباعك على نبينا محمدﷺ ይ🀄ላ🀄ሉን👇👇 share👇        tiktok.com/@secretsof_truth Instagram.com/secretsof_truth t.me/Secretsof_Truth Fb.com/SecretsofTruth1 ► ለሀሳብ፣ አስታየት ወይም ጥቆማ 👇👇 t.me/ReshadMuzemil

ከንፋስ ጥቅም ለማግኘት የሚደረግ ዱዓእ! ከምዕመናን እናት አዒሻ (رضي ﷲ عنها) ተይዞ፡ እንዲህ ትላለች፡ ነቢዩ (ﷺ) ንፋስ ሲነፍስ እንዲህ ይሉ ነበር፦ ﴿اللَّهُمَّ إِنِّي أَسْأَ
ከንፋስ ጥቅም ለማግኘት የሚደረግ ዱዓእ! ከምዕመናን እናት አዒሻ (رضي ﷲ عنها) ተይዞ፡ እንዲህ ትላለች፡ ነቢዩ (ﷺ) ንፋስ ሲነፍስ እንዲህ ይሉ ነበር፦ ﴿اللَّهُمَّ إِنِّي أَسْأَلُكَ خَيْرَهَا، وَخَيْرَ مَا فِيهَا، وَخَيْرَ مَا أُرْسِلَتْ بِهِ، وَأَعُوذُ بِكَ مِنْ شَرِّهَا، وَشَرِّ مَا فِيهَا، وَشَرِّ مَا أُرْسِلَتْ بِهِ﴾ “አላህ ሆይ! መልካሟን፣ በውስጧ የያዘችውን መልካም ነገርና የተላከችበትን መልካም ነገር እጠይቅሃለሁ። ከክፉዋ፣ በውስጧ ከያዘቸችው ክፉ ነገርና ከተላከችበት ክፉ ነገር በአንተ እጠበቃለሁ።” 📚 ሙስሊም ዘግበውታል፡ 899

#ከእሳት_ለመራቅ_ፆም_አንዱ_መንገድ_ነዉ... "ለአላህ ብሎ አንድ ቀንን የፆመ አላህ ፊቱን ከጀሀነም ሰባ አመት ያርቃል።" ብለዋል ነብያችን(ﷺ) اللهم صل وسلم وبارك على نبينا محمدﷺ

* አላዋቂ የሆነ ሰው ዓሊም ባይሆንም በእውቀት ሲገለፅ  መደሰቱ እና ጃህል ጃሂል ከመሆኑ ጋር በጅህልና ሲገለፅ መሸማቀቁ ለዒልም ፈድልና ክብር በቂ ነው!! *አላዋቂነት ሁለት አይነት ሲሆን፡- ከእውቀት የፀዳ መሀይምነት እና  ስራን በመዘንጋት የሚመጣ ጅህልና ናቸው። 🎙ሸይኽ ዐብዱል ከሪም አል– ኹደይር ሐፊዘሁሏህ ©️©️©️

📌 የታላቁ የረመዷን ወር 27 ቀናቶች ገደማ ብቻ ቀሩት! 🔸 አላህ በሰላም ከሚደርሱትና ፁመው ተቀባይነትን ከሚያገኙት ባሮቹ ያርገን 🤲🤲
📌 የታላቁ የረመዷን ወር 27 ቀናቶች ገደማ ብቻ ቀሩት! 🔸 አላህ በሰላም ከሚደርሱትና ፁመው ተቀባይነትን ከሚያገኙት ባሮቹ ያርገን 🤲🤲

(No ! Valentine's Day) Apni Jawani ! Ko Sahi Jagah Invest Karo By: Abdul Aziz Shakeel #Naujawaan #MustWatch #AbdulAzizShakeel #Shortlecture #Language: Hindi Join:- ይ🀄ላ🀄ሉን👇👇 share👇        tiktok.com/@secretsof_truth Instagram.com/secretsof_truth t.me/Secretsof_Truth Fb.com/SecretsofTruth1 ► ለሀሳብ፣ አስታየት ወይም ጥቆማ 👇👇 t.me/ReshadMuzemil

​Celebrating Valentine's Day is HARAM! 🔸Valentine’s Day is a jaahili Roman festival, which continued to be celebrated until after the Romans became Christian. This festival became connected with the saint known as Valentine who was sentenced to death on 14 February 270 CE. The kuffaar still celebrate this festival, during which immorality and evil are practised widely. 💔It is unfortunate that even Muslims have started celebrating this day without thinking. This is not only a festival of non-Muslims, but if we look at the present day, the evils spread through it testify to why this festival should be rejected. 🚨Here are some Qur'anic verses and hadiths on how we are disobeying Allah and His Messenger by participating in this festival in any way. 🔹There is no doubt that this festival is based on pornography and is spreading obscenity through it. 📖Allah سبحان و تعالیٰ says: إِنَّ الَّذِينَ يُحِبُّونَ أَن تَشِيعَ الْفَاحِشَةُ فِي الَّذِينَ آمَنُوا لَهُمْ عَذَابٌ أَلِيمٌ فِي الدُّنْيَا وَالْآخِرَةِ ۚ Indeed, those who like that immorality should be spread [or publicized] among those who have believed will have a painful punishment in this world and the Hereafter. [Al Quran 24:19] 📖وَلَا تَقْرَبُوا الْفَوَاحِشَ مَا ظَهَرَ مِنْهَا وَمَا بَطَنَ ۖ And do not approach immoralities - what is apparent of them and what is concealed. [Al Quran 6:151] ☪Prophet  said: الْحَيَاءَ مِنَ الْإِيمَانِ Haya' is a part of faith. [Bukhari 24] 🔸Muslims should stick to their religion instead of running after the majority and be content with what Allah has given us in the form of Islam. 📖Allah سبحان و تعالیٰ warned us: وَإِن تُطِعْ أَكْثَرَ مَن فِي الْأَرْضِ يُضِلُّوكَ عَن سَبِيلِ اللَّهِ ۚ إِن يَتَّبِعُونَ إِلَّا الظَّنَّ وَإِنْ هُمْ إِلَّا ŮŠŮŽŘŽŮ’ŘąŮŘľŮŮˆŮ†ŮŽ And if you obey most of those upon the earth, they will mislead you from the way of Allah . They follow not except assumption, and they are not but falsifying. [Al Quran 6:116] ☪The Prophet  said, You will follow the ways of those nations who were before you, span by span and cubit by cubit (i.e., inch by inch) so much so that even if they entered a hole of a mastigure, you would follow them.   We said,   O Allah's Apostle! (Do you mean) the Jews and the Christians?   He said,   Whom else? [Bukhari 7320] 🔹When it is clear to us that this is a non-Muslim festival, it is not permissible for anyone to celebrate this day, even if it is a couple! Because قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صَلَّى اللَّهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ:‌‌‌‏  مَنْ تَشَبَّهَ بِقَوْمٍ فَهُوَ مِنْهُمْ  . ☪The Prophet  said: He who copies any people is one of them. [Abu dawood 4031] 🚨Aren't we Muslims?  Don't believe in the Hereafter?  Do they not remember Allah and fear His wrath? 📖 Allah سبحان و تعالیٰ said: لَّقَدْ كَانَ لَكُمْ فِي رَسُولِ اللَّهِ أُسْوَةٌ حَسَنَةٌ لِّمَن كَانَ يَرْجُو اللَّهَ وَالْيَوْمَ الْآخِرَ وَذَكَرَ اللَّهَ ŮƒŮŽŘŤŮŮŠŘąŮ‹Ř§ There has certainly been for you in the Messenger of Allah an excellent pattern for anyone whose hope is in Allah and the Last Day and [who] remembers Allah often.      ‼️Who are you following? Valentine or Allah's Messenger   SayNoTo Valentine's Day! #ValentinesDay #Valentine

ሻዕባን! ረሱል (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦ ﴿شَعْبانُ بين رَجَبٍ ورَمَضانَ، يَغْفَلُ الناسُ عنهُ، تُرْفَعُ فيهِ أَعْمالُ العِبادِ، فَأُحِبُّ أنْ
ሻዕባን! ረሱል (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦ ﴿شَعْبانُ بين رَجَبٍ ورَمَضانَ، يَغْفَلُ الناسُ عنهُ، تُرْفَعُ فيهِ أَعْمالُ العِبادِ، فَأُحِبُّ أنْ لا يُرْفَعَ عملي إلّا وأنا صائِمٌ﴾ “ሻዕባን በረጀብ እና በረመዳን መካከል የሚገኝ ወር ሲሆን ሰዎች ከሱ የሚዘናጉበት ስራዎች ወደ ዓለማቱ ጌታ የሚወጡበት ወር ነው። እኔ ደግሞ ስራዬ ጾመኛ ሆኜ እንዲወጣልኝ እወዳለሁ።” 📚 አልባኒ በሲልሲለቱ አሶሂሃ ውስጥ ሀሰን ብለውታል: 1898

Ibn ul-Qayyim رحمه الله said: لو علم المتصدق أن صدقته تقع في يد الله قبل يد الفقير “If the one giving charity knew that his c
Ibn ul-Qayyim رحمه الله said: لو علم المتصدق أن صدقته تقع في يد الله قبل يد الفقير “If the one giving charity knew that his charity landed in the Hand of Allāh before the hand of the poor person, لكانت لذة المعطي أكثر من لذة الآخذ. the pleasure of the giver would be greater than the pleasure of the receiver.” [مدارج السالكين ١/٢٦]

نصائح تتعلق بشهر شعبان ከ ሸዕባን ወር ጋር የተያያዙ አንዳንድ ምክሮች📜 أولا : يجـب قضـاء الصـــــوم لمن أفءع أياما من رمضان الماضي قبـل أن يدخل رمضان القادم. አንደኛ፦ ከዚህ በፊት የረመዳን ቀዷዕ ያለበት አካል በዚሁ በሸዕባን ወር ውስጥ መጪው ረመዳን ሳይገባበት ቀዷዕ ሊያወጣ ግድ ይለዋል። ثانيا : يجب تعلم أحكام الصيـــــــام قـبـل دخـــــــول  رمـضـــــــان القـــــــادم. ሁለተኛ፦ መጪው ረመዳን ከመግባቱ በፊት  የፆም ህግጋቶችን መማር ግድ ይላል። ثالثا : مـن السنة الإكثـار مـــن الصيــــام فـي شـعبـــــــان ሶስተኛ፦ በሸዕባን ወር ፆምን አብዝቶ መፆም ከነብያችን ሱና ይመደባል። عابؚا: من هدي السلف الإكثار من قـــراءة القرآن في شعبــان. አራተኛ፦ ከቀደምት ሰለፎች ተግባር ውስጥ ቁርዓንን በዚህ በሸዕባን ወር ውስጥ አብዝቶ ማንበብ ነው። خامسا : لايجـوز تخصيـص يوم أو ليلة النصف من شعبان بعبــادة خاصـة አምስተኛ፦ በሸዕባን አጋማሽ ላይ የዚያን ቀንንም ሆነ ሌሊትን ለየት ባለ ኢባዳ መለየት አይቻልም። سادسا: لايـجــوز صيــام يــــوم الشـــــــك وهـو يـــــوم الثـلاثين من شعبان ስድስተኛ፦ አጠራጣሪ ቀን የሸዕባን 30ኛ ቀንን መፆም አይቻልም። 👉(አንዳንድ ምክንያቶች ካሉ ግን የሚበቃ ይሆናል) سابؚا : الدعـاء بأن يبلغك الله رمضـــــــان وان يوفـقـك فيـه للعمـل الصالـح. ሰባተኛ፦ አላህን ረመዳንን እንዲያደርስህ በረመዳን ውስጥም መልካም ሾል መስራትን እንዲያስችልክ መለመን። ثامنا : ينبغي إنهاء الأشغال الدنيوية قبل رمضان للتفـرغ للعـبـــادة في رمضــــــــــان ስምንተኛ፦ በረመዳን ውስጥ በዒባዳ ለማሳለፍ ከረመዳን በፊት በዱንያ መወጠርን መተው ይገባል። تاسؚا : من ؚاد؊ السلف إخـراج الزكاة في شعبان. ዘጠነኛ፦ ከቀደምት ሰለፎች ልማድ: በዚህ በሸዕባን ወር ውስጥ ዘካን ማውጣት ነበር። ✍ ጦለሃ አህመድ

إِنَّ أَنْسَابَكُمْ هَذِهِ لَيْسَتْ بِسِبَابٍ عَلَى أَحَدٍ وَإِنَّمَا أَنْتُمْ وَلَدُ آدَمَ لَيْسَ لِأَحَدٍ عَلَى أَحَدٍ فَضْلٌ إِلَّا بِالدِّينِ أَوْ عَمَلٍ صَالِحٍ የአላህ መልዕክተኛ (ﷺ) እንዲህ ብለዋል «በእርግጥ ዘራችሁ ከማንም በላይ እንድትሆኑ አያደርጋችሁም፣ ሁላችሁም የአዳም ልጆች ናችሁና። በሀይማኖት እና በመልካም ሥራ ካልሆነ በቀር ማንም ከማንም አይበልጥም።» (📗Sahih Al-targhib by Albani 2962)

የቀናት ፍጥነት እጅግ አስፈሪ ሆኗል አሁን ፈጅር ሰግደህ ሳታስበው ይመሻል ፤ መሸ ብለህ ትራስህ ላይ እንዳረፍክ ፈጅር አዛን ይሰማል አጀብ ነው ሀቂቃ። ቀናት በዚህ መልኩ ያለማቋረጥ ይጓዛሉ፤ በእውነ
የቀናት ፍጥነት እጅግ አስፈሪ ሆኗል አሁን ፈጅር ሰግደህ ሳታስበው ይመሻል ፤ መሸ ብለህ ትራስህ ላይ እንዳረፍክ ፈጅር አዛን ይሰማል አጀብ ነው ሀቂቃ።  ቀናት በዚህ መልኩ ያለማቋረጥ ይጓዛሉ፤ በእውነት ደስተኛ ሰው ማለት መፅሀፉን በመልካም የሚሞላ ብቻ ነው ፤ አደጋዎች በዝተዋል ፤ አህባቦች በየጊዜው ሞት ይጠልፋቸዋል ፤ እኛም ተራችንን እንጠብቃለን፤ አሁንም የሚያዋጣን መልካም መስራት ብቻና ብቻ ነው። ©️ ©️