Secrets of Truth - 𝘽𝙮 𝙍𝙚𝙨𝙝𝙖𝙙
前往频道在 Telegram
● ዲናችንና በሚመለከት ወቅታዊ መረጃዎችን ➶ Current information about Muslims and Islam 🔗 ሌሎችንም አንገብጋቢ ጉዳዮችን የምንተዋወስበት Channel ነው‼️ ➞ በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ አጠር ያሉ ስንኞች (በተለይም ስለ ፈለስጢን 🇵🇸) 🎯 አላማዬ:- የእውነትን ሚስጥሮች ማጋለጥ ነው‼️ #Free_Palestine 🇵🇸
显示更多213
订阅者
无数据24 小时
-17 天
-430 天
帖子存档
🇵🇸 ትዝብቴንና ግርምቴን በብዕር
ለእርሱም ትክክለኛ ቦታውን መስጠት ያስቸግራል፡፡
............................. ረሺ ነና!
◆ ስንት ስንመኛቸው እንቅልፍ የነሱን ነገራቶች ከእጃችን ሲገቡ ዘንግተናቸዋል፡፡
በእጅህና በአንተ ላይ ያሉትን መልካም ነገራቶች ደጋግመህ ማሰብህ ህይወትህን ለማጣፈጥ ከሚጠቅሙ ወሳኝ ቅመሞች መካከል ቀዳሚው ነው፡፡
እስቲ ያለንን እናስታውስ!_......_እኔ ልጀምር!
ummalife.com/ReshadMuzemil
«ጁመዓህ ጀለብያ ለብሼ ፏ ብዬ… …!» አላለችም! እነዚህ ሰዎች ሲበጠረቁ ትንሽ እንኳን አያፍሩም? ተከታያቸውን ምን ያክል ቢንቁት ነው ሰብስበው ተረት የሚነግሩት?
ካነበብኩት ላካፍላችሁ [[➊]]
የብቸኝነት ጎዳና
አንዳንድ ጊዜ ብቻችሁን የምትሄዱባቸው ጎዳናዎች እንዳሉ አትርሱ፡፡ የብቸኝነት ጎዳና ማለት በዙሪያችሁ አብረዋችሁ ያሉ ሰዎች አብሮነታቸውን ለማሳየት የማይፈልጉበት ወይም የማይችሉበት ሁኔታ ሲከሰት ማለት ነው፡፡
እነዚህ ጎዳናዎች ሰዎች ሊገነዘቧችሁ የማይችሉት ሁኔታ ላይ ስትሆኑ፣ አንዳንድ የተሳሳተ ውሳኔ ላይ ራሳችሁን ስታገኙትና ያንን ለማስተካከል እንኳን ጊዜ አልሰጥ ሲሏችሁ፣ ለማንም የማትነግሩት አይነት ችግር ሲያጋጥማችሁ፣ ለሕይወታችሁ አዲስ ምእራፍ ፈልጋችሁ ለውጥን ማምጣት ስትጀምሩ፣ አንዳንድ ጊዜ ደግሞ ምክንያቱን በማታውቁት ሁኔታ የብቸኝነትን ጉዞ እንድትያያዙት ትገደዳላችሁ፡፡
እንደዚህ አይነት ሁኔታ ላይ ራሳቸሁን ስታገኙት . . .
1. ሁኔታው ጊዜያዊ ነውና የከረሩ ውሳኔዎች ውስጥ እንዳትገቡ ተረጋጉ፡፡
2. ሰዎች ገለል የማለታቸው ምክንያት ለምን እንደሆነ መነሻ ሃሳባቸውን ተወት አድርጉትና ውሳኔያቸውን አክብሩና ለቀቅ አድርጓቸው፡፡
3. ራሳችሁን እንድትመለከቱ እድል የምታገኙበት አስገራሚ ጊዜ ስለሆነ በቂ ጊዜን ከራሳችሁ ጋር አሳልፉ፡፡
4. ከሰዎች ጋርም ሆነ ከሰዎች ውጪ፣ ከችግር ጋርም ሆነ ከችግር ውጪ መኖር የምትችሉበት አቅማችሁ የሚፈተሸበት ጊዜ መሆኑን አትርሱ፣ ያንንም አዳብሩ፡፡
5. ሁል ጊዜ ፈጣሪያችን ከእናንተ ጋር እንደሆነና ሁሉን ነገራችሁን እንደሚገነዛባችሁ በማሰብ ወደ እሱ የምትጠጉበት አጋጣሚ በማድረግ ተጠቀሙበት፡፡
አይዟቸሁ! አላህ አለ!
▬▬▬▬▬▬▬▬
ካነበብኩት ላካፍላችሁ [[❷]]
በፍጹም ተስፋ እንዳትቆርጡ!
“አንድ እድሜ ልኩን ማየት የተሳነው ሰው አይኑ ሲበራለት መጀመሪያ የሚጥለው እድሜ ልኩን ምርኩዝና ምሪት ሆኖ ያገለገለውን በትር (ዱላ) ነው” ይባላል፡፡
“አንድ ሕጻን ጥርስ ሲያወጣ መጀመሪያ የሚነክሰው ያለፉትን ወራት ሲመግበው የነበረውን የእናቱን ጡት ነው” ይባላል፡፡
በጎ ነገር በማድረጋችሁና ጨዋ ማንነት በመያዛችሁ ምክንያት በሰዎች የደረሰባችሁ ነገር ምንም ያህል ቢጎዳችሁና ስሜቱ ደስ ባያሰኝም፣ እናንተ ላይ ብቻ የደረሰና አዲስ ነገር ግን አይደለም፡፡
ከደረሰባችሁ ሁኔታ የተነሳ ጨዋ ማንነታችሁን አትጣሉ!
©️ Toleha Ahmed
Join:-
YouTube: YouTube.com/@SecretsofTruth
Tiktok: tiktok.com/@secretsof_truth
Instagram: Instagram.com/secretsof_truth
Telegram: t.me/Secretsof_Truth
Facebook: Fb.com/SecretsofTruth1
Ummalife: ummalife.com/ReshadMuzemil
ለአስታየት
👇👇👇
t.me/ReshadMuzemil
ፈገግ በሉ
~
የአናቱን አምስት ብር ያነሳው ልጅ "ማነው ብር የወሰደው?" ሲባል "እኔ አምስት ብር አላየሁም" አለ አሉ። አንዳንዶች ባልታሰበ ሰዓት ወንጀላቸውን ይናዘዛሉ። ያያያዝኩት በዒራቅ ላይ ወረራ የፈፀመ ጆርጅ ቡሽ የተሰኘው የአሜሪካ መሪ ነው። የዩክሬንን ወረራ ሊያወግዝ ፈልጎ ምላሱ አጋለጠው።
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://t.me/IbnuMunewor
ሀጅ ለማድረግ ለተነሳችሁ ወንድም እህቶች የሐጅ እና ዑምራን ድንጋጌዎችን ለመማር የሚረዳ ጠቃሚ አፕሊኬሽን ስለሆነ አውርዳችሁ ተጠቀሙበት።
@ahmedin99
ሪያእ
🎙 ኡስታዝ አብዱረዛቅ
۩ ۩ ۩ ۩ ۩ ۩ ۩
☀ ሁዳ መልቲሚዲያ
----------------------
በቴሌግራም
t.me/huda4eth
በፌስቡክ
fb.com/huda4eth
በዩትዩብ
https://goo.gl/WK5K5N
በ ቲክ ቶክ
@huda4eth
ያግኙን
اِنَّ الَّذِيْنَ اٰمَنُوْا وَا لَّذِيْنَ هَا جَرُوْا وَجَاهَدُوْا فِيْ سَبِيْلِ اللّٰهِ ۙ اُولٰٓئِكَ يَرْجُوْنَ رَحْمَتَ اللّٰهِ ۗ وَا للّٰهُ غَفُوْرٌ رَّحِيْمٌ
"Indeed, those who have believed and those who have emigrated and fought in the cause of Allah - those expect the mercy of Allah. And Allah is Forgiving and Merciful."
(QS. Al-Baqara 2: Verse 218)
የዑለሞች ድንቃድንቅ ንግግሮች
───────────
ኢማሙ_ሻፊዒይ ረሒመሁሏህ እንዲህ ይላሉ : -
«ሁሉንም ሰው እንዲወዱህ ማድረግ አትችልም። በአንተና በአላህ መካከል ያለውን ጉዳይ አስተካክል። ከዚያም የሰዎች ጉዳይ አያስጨንቅህ!።»
📚 ۞ تولى التأنيث لابن رجب【168】۞
───────────
@fenot_jenet
﴿أَمْ جَعَلُوا لِلَّهِ شُرَكَاءَ خَلَقُوا كَخَلْقِهِ فَتَشَابَهَ الْخَلْقُ عَلَيْهِمْ ۚ قُلِ اللَّهُ خَالِقُ كُلِّ شَيْءٍ وَهُوَ الْوَاحِدُ الْقَهَّارُ﴾
[ الرعد: 16]
{رَبِّ اجْعَلْنِي مُقِيمَ الصَّلَاةِ وَمِن ذُرِّيَّتِي ۚ رَبَّنَا
وَتَقَبَّلْ دُعَاءِ} [ابراهيم : 40]
«ጌታዬ ሆይ! ሰላትን አዘውትሬ የምሰግድ አድርገኝ ከዘሮቼም (ሰላትን አዘውታሪ አድርግ)፡፡ ጌታችን ሆይ! ጸሎቴንም ተቀበለኝ» ኢብራሂም : 40
@Darul_Islam_channal
@Darul_Islam_channal
በጀመርከው ኢባዳ (አምልኮ) ላይ መፅናት!
ከአብደላህ ቢን ዐምሩ (رضي ﷲ عنه) ተይዞ: ረሱል (ﷺ) እንዲህ አሉኝ አለ፦
﴿يا عَبْدَ اللَّهِ، لا تَكُنْ مِثْلَ فُلانٍ؛ كانَ يَقُومُ اللَّيْلَ، فَتَرَكَ قِيامَ اللَّيْلِ﴾
“አንተ አብደላህ ሆይ! እንደ እከሌ እንዳትሆን። የሌሊት ሶላት ይሰግድ ነበር። የሌሊት ሶላቱን መስገድ መልሶ ትቶታል።”
📚 ቡኻሪ (1152) ሙስሊም (1159) ዘግበውታል
ጆይን፦ https://t.me/BuhariMuslimAmharic
ማን እንደ እናት!
ከአቡ ሁረይራ (رضي ﷲ عنه) ተይዞ: አንድ ሰው ወደ አላህ መልእክተኛ (ﷺ) ዘንድ መጥቶ እንዲህ አላቸው፦
﴿يا رَسولَ اللَّهِ، مَن أحَقُّ النّاسِ بحُسْنِ صَحابَتِي؟ قالَ: أُمُّكَ، قالَ: ثُمَّ مَنْ؟ قالَ: ثُمَّ أُمُّكَ، قالَ: ثُمَّ مَنْ؟ قالَ: ثُمَّ أُمُّكَ، قالَ: ثُمَّ مَنْ؟ قالَ: ثُمَّ أبُوكَ﴾
“አንቱ የአላህ መልዕክተኛ ሆይ! ማነው ለኔ ከሰዎች ጥሩና እውነተኛ ወዳጅ አድርጌ ልይዘው የሚገባ? “እናትህን” አሉት። ከዛስ በመቀጠል አላቸው: “እናትህን” አሉት። ከዛስ በመቀጠል አላቸው: “እናትህን” አሉት። ከዛስ በመቀጠል አላቸው: “አባትህን” አሉት።”
📚 ቡኻሪ (5971) ሙስሊም (2548) ዘግበውታል
ጆይን፦ https://t.me/BuhariMuslimAmharic
🔰 ባሮችህ ረገፉ
በፈለስጢን ምድር - በአላህ ቤት
በመስጂደል አቅሳ - ነብዩ ባረፉበት
በካኃዲዋ እስራኤል - ረገፉ ህፃናት
ቦምብ ዘነበባቸው - እንቅልፋቸውን በተኙበት
ዓለምም ችላ አለው - ይህን የዘር ማጥፋት
ያረቢ የአላህ - ሰማዩ ሰማይህ
ያራህማን ያራሂም - ምድሩም ምድርህ
ድረስላቸው ጌታችን - ጀባሩ ያአላህ
ሙስሊም የሆኑ - ኢባዱ ራህማን ናቸው
ሰው ናቸውና ያራሂም - ካጠፉም ማራቸው
መንገድ ስተው እንደሆን - መንገድ አሳያቸው
ሙስሊሞቹም ያንተ - ህፃኖች ያንተው
ካንተ ውጭ ሌላ መጠጊያም ዬላቸው!
አዎ ወጀለኞች ነን - ነብሳችንን በዳይ
ድንበር አላፊዎች ነን - በሰጧን አታላይ
ለብልጭልጭ ህይወት - በርከክ ባይ
ለዚህች ለቀን ጤዛ - ደሞም ለዱንያ
ላትሆነን መንገድ - ጀነትን መዝለቂያ
እያጠለቀችልን - የአዛብ ሜዳሊያ
ግን አንገሰፅም - ከዚህ ሁሉም ነገር
በኛ ወንጀል የተነሳ - ሙስሊሙ ሲሸበር
ጠላት ተጠራርተው - ሁሉም ባአንድ ሲያብር
እኛ ስንባላ - በጎሳ በብሄር
እኛ ስንከፋፋል - በቋንቋ በዘር
አስክሬኖች በርክተው - አፈር ሲለብስ በዶዘር
እኛ ቆይ የት ገባን - ቆይ የትስ አለቅን!?
ቆይ ምን ዋጠን - ምንስ ላይ ሰመጥን!?
ሙስሊም ረገፈ እኮ - እኛ በቁም እያለን
ጂሃዱስ አይሳካ - ያአላህ ማለት አቃተን!
የሙስሊም መሣሪያው - ዱዓ ነው እየተባልን፤
ያራህማን ያራሂም - እኛስ ቀሽሞች ነን፤
ሙስሊሞች ነንና - እባክህን ማረን
አዛኝ ነህና - ያአላህ እዘንልን
ውስጣችን ቆሰለ - ደም ዘነበ ከዓይን
ወንድሞቻችን አለቁ - በከሃዲዎች ረገፉብን
እነዛ የሰው አውሬዎች - ያንተን ቤት ደፈሩብን።
ያረቢ የአላህ - ሰማዩ ሰማይህ
ያራህማን ያራሂም - ምድሩም ምድርህ
ያአላህ ያ! ራህማን - ቤቱም ቤትህ
ድረስላቸው ጌታችን - ጀባሩ ያአላህ
ከጭንቅ ጠብቃቸው - ከጭንቅ አውጪ ነህ
ብዙዎች ቆሰሉ - ብዙዎች አለፉ
በህይወት እያሉ - ባሮችህ ደም ተፉ
በዘረጋሃው ምድርህ - ሙስሊሞች ተገፉ
እነዛ አውሬዎች - ሬሳን አሰለፉ
ሴትም አልቀራቸው - ህፃንም ቀጠፉ
ገደልን እያሉ - በደስታም ደነፉ
⭕️ በባረከው ምድርህ - *ባሮችህ ረገፉ* ።
በረሻድ ኢብኑ ሙዘሚል
ቀን: ጥቅምት 20/2016 E.C [Oct 31/2023 G.C]
Join:-
YouTube.com/@SecretsofTruth
tiktok.com/@secretsof_truth
Twitter.com/Secretsof_Truth
Instagram.com/secretsof_truth
t.me/Secretsof_Truth
Fb.com/SecretsofTruth1
https://ummalife.com/ReshadMuzemil
t.me/ReshadMuzemil
በራስ መደነቅ ብዙ መጥፎ ሥነ ምግባራትን እና ባሕርያትን ያመነጫል፤ በዋናነት ሌሎችን መናቅ!
|| 7122 SMS
