Secrets of Truth - 𝘽𝙮 𝙍𝙚𝙨𝙝𝙖𝙙
前往频道在 Telegram
● ዲናችንና በሚመለከት ወቅታዊ መረጃዎችን ➶ Current information about Muslims and Islam 🔗 ሌሎችንም አንገብጋቢ ጉዳዮችን የምንተዋወስበት Channel ነው‼️ ➞ በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ አጠር ያሉ ስንኞች (በተለይም ስለ ፈለስጢን 🇵🇸) 🎯 አላማዬ:- የእውነትን ሚስጥሮች ማጋለጥ ነው‼️ #Free_Palestine 🇵🇸
显示更多213
订阅者
无数据24 小时
-17 天
-430 天
帖子存档
«ንጋት» የተሰኘው የኡስታዝ አሕመድ ኣደም አዲሱ መጽሐፍ ገበያ ላይ ውሏል።
መጽሐፉን በሚከተሉት አድራሻዎች ታገኙታላችሁ። ገዝታችሁ አንብቡ፤ ተጠቀሙ።
🔰 ወላሂ አውፍ ብዬሀለሁ
=============
(በጀማል አህመድ )
ዛሬ ኮልፌ መቃብር ተገኝቻለሁ። በቀብር ስነስርዓት ላይ ነውና የተገኘሁት አስቀብረን ስንመለስ አንድ አባት እንባ እየተናነቃቸው የሚያውቁትን ሰው ስም እየጠሩ ይጮሀሉ። አይናቸው ያረፈው እግርጌያቸው ያለው ቀብር ላይ ነው። ቀብሩ ላይ ለስም መፃፊያ በቆመው ድንጋይ ላይ የሟች ስምና የተቀበረበት ቀን ተጽፎአል።
"ወይኔ ሱሌ፣ ወይኔ ሱሌ እኔ የት ጠፋህብኝ እላለሁ ለካ አንተ እዚህ ነህ? ወላሂ ወላሂ አውፍ ብዬ አለው " እንባቸው እርግፍ ማለት ጀመረ።
"ወይኔ ሱሌ " ይላሉ ደጋግመው።
አብሮኝ የነበረው ሱልጣን ወደ እሳቸው ጠጋ ብሎ "የሚያውቁት ቤተሰብ ነው? " ሲል ጠየቃቸው።
"በስራ አጋጣሚ ነበር የምንተዋወቀው 160 ሺህ ብር አበድሬው ነበር። ለረጅም ጊዜ ጠፋብኝ ደውዬም ማግኝት አልቻልኩም፣ ብድር የወሰደበትን መዝገብ አልፎ አልፎ እየተመለከትኩና ስሙን ከነአያቱ እየጠራሁ የት ገባ እላለሁ? ወይኔ ወንድሜ ለካ እዚህ መጥቶ ነው? ወይኔ ሱሌ ሁሉን ነገር ይቅር ብዬ አለሁ።"
የሰውየው ሁኔታ ሟች የእሳቸው እድ ሳይከፈል በመሞቱ ሲሰቃይ እያዩ ለማስጣል የሚማጠኑ ይመስላሉ "ወላሂ አውፍ ብዬዋለሁ! ወላሂ አውፍ ብዬአለሁ ! " አሉ ደጋግመው።
⌚️ ጎናቸው የቆመው ሱልጣን አይኑ እንባ አቀረረ። ሁላችንም በሁኔታቸው ስሜታችን ተነክቷል።
⭕️ ባለቤትሽ ገንዘቤን ሳይሰጠኝ ሞተ ብሎ እናቴን በሐሰት የከሰታትንና የአባቴን ንብረት በሐራጅ ሊያሸጥ የመጨረሻ ደረጃ ላይ ደረሶ በኋላ አባቴ የከፈለበት ማስረጃ ተገኝቶ ጎዳና ላይ ከመውጣት የተረፍንበት አጋጣሚ ለቅፅበት ታወሰኝ ።
የእኚ ሰው ሁኔታ ደግሞ ፍፁም የተለየ ነው። እንባዬ የአይኔን በር አልፎ ለመውጣት እየተጋለ ነው።
ይባስ ብለው "ያለአባት የቀሩት ልጆቹ በምን ሁኔታ ይሆን ያሉት? ያሉበትን አፈላልጌ እጠይቃቸዋለሁ ኢንሻአላህ! " ቁጢጥ ብለው ከተቀመጡበት ብድግ አሉ።
⬆️ ሱልጣን በተቀመጡበት ረስተውት የተነሱትን የመኪናቸውን ቁልፍ አንስቶ ሰጣቸው።
ከዚያ ሰላማዊና ምንም መሆናችን ከሚያስታውሰን
የሙታን ስፍራ ስለነገ ሞታችን እያሰብን ወጣን።
እንዲህም አይነት ሰው አለ።
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
እህት ወንድሞች እስከ መቼ በትናንሽ ስህተቶች ተኮራርፈን እንቆያለን⁉️
እስከ መቼ ወንድም እህቶቻችን እናነውራለን⁉️
እስከ መቼ ነው እርሰበርሳችን የምንባላው⁉️
⭕️ ሞት መጥቶ እስኪይዘን ድረስ ነው⁉️
⭕️ ሯመዳንንስ በዚሁ መኮራረፍ፣ መበላላት፣ ሰዎችን በማነወር፣ የወንድም እህቶቻችንን አይብ በማውጣት ነው የምንቀበለው⁉️
❗️ሁላችንንም እራሳችንን እንጠይቅ❗️
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
❗️ተማሪዎች ይችህን ፅሁፍ ሳታነቧት እንዳታልፉ። አደራዬ ነው❗️
🔰 ወላሂ አውፍ ብዬ አለሁ

❗️ይችህን ፅሁፍ ሳታነቧት እንዳታልፉ። አደራዬ ነው❗️
I ወላሂ! ወቢላሂ! ወተላሂ! ረመዷንን ሳይጠቀምበት ያለፈበት ማንም ሰው ዑዝር የለውም!
ሸይኽ ሱዑድ ሹረይም
ትርጉም ጦለሃ አህመድ
https://t.me/tolehaahmed
"I was asleep. I woke up to someone pulling me out of the rubble," says this little girl who survived an Israeli airstrike targeting her family home last night in Deir el-Balah.
💻 አውፍ በይን አቅሳ 🇵🇸
አንቺ እየቆሰልሽ - እኛ ፈገግ እንላለን፤
አንቺ እያለቀስሽ - እኛ እንስቃለን፣
በማይረባ ነገር - እርሰበርስ እንባላለን፤
ትላንት አዝነንልሽ - ዛሬ ጨክነናል፤
ባለፈ ዱዓ አድርገን - ዛሬ ዘግተናል፤
አውፍ በዪን ፈለስጢን - እኛ ጨክነናል፤
ይህ ሁሉ ሳያንሰን- በወንጀል ተዘፍቀናል፤
አወይ የኛ ክፋት - ምንኛ ጨካኝ ነን⁉️፤
ለወንድሞቻችን ወድቀት - ቀመር እንቀምራለን፤
በእህቶቻችን አይብ - እንሳለቃለን፤
ሰዎችን ለመጣል - ሴራ እናሴራለን፤
በዚያ ግን ትቀጠፋለች - የኛዋ ፈለስጢን።
አቅሳ፣ ፈለስጢንን እያየን - ለሰዎች አናዝንም⁉️፤
አላህ ነስሩን እንዲሰጠን - ማመፅ አናቆምም⁉️፤
ወደ ጌታችን ተመልሰን - የአላህ አንልም⁉️፤
አረ ይበቃናል - በቁማችን ሞትን፤
መቃብር ሳንገባ - አፈርም ለበስን፤
ህይወት አላቸው እንዲሉ - እየተቀሳቀስን፤
ክፋታችን ከፍቷል - ረሳናት ፈለስጢንን፤
ልባችን ጨከነ - ዘነጋናት አቅሳን።
ለአላህ ስትይ - አቅሳ አውፍ በይን፣
አንቺ እየቆሰልሽ - እኛ ፈገግ እንላለን፤
አንቺ እያለቀስሽ - እኛ እንስቃለን፣
ትላንት አዝነንልሽ - ዛሬ ጨክነናል፤
ባለፈ ዱዓ አድርገን - ዛሬ ዘግተናል፤
አውፍ በይን ፈለስጢን - እኛ ጨክነናል፤
አውፍ በይን አቅሳ - እኛ ጨክነናል።
🇵🇸 🇵🇸 🇵🇸 🇵🇸 🇵🇸 🇵🇸 🇵🇸 🇵🇸
📙 በረሻድ ኢብኑ ሙዘሚል
🕤 ቀን:- ማክሰኞ/ የካቲት 26/2016 ዓ.ል
ፕሮፌሰር ሸይኽ ዐብዱረዛቅ አልበድር (አላህ ይውደዳቸው) እንዲ ሲሉ በአንድ ወቅት የገጠማቸውን ያጫውቱናል።
የሆነ ወቅት ላይ ደርስ (ትምህርት) ሰጥቼ ከጨረስኩ በኋላ አንድ በዕድሜ ጠና ያሉ ሰው ወደኔ መጡና እንዲህ አሉኝ፦
ያ ሸይኽ፦
"እኔ ከሱረቱል ፋቲሓ እና ኢኽላስ قل هو الله أحد በስተቀር ምንም የሸመደድኩት የቁርኣን ምዕራፍ የለም ፤ እነዚህን ሱራዎች እየቀራሁ ለሊት ላይ ለሰዓታት እሰግዳለሁ።
ከዚያም አለቀሱና እንዲህ አሉኝ፦
"እኔ ከእነርሱ ውጪ ምንም የሐፈዝኩት (የሸመደድኩት) ሱራ የለም ፤ ያ ሸይኽ በዚህ መልኩ ደጋግሞ መስገዱ ይፈቀድልኛልን???
(አጂብ…)
ሸይኽ ዐብዱረዛቅ ይህንን አጋጣሚ ተንተርሰው እንዲህ ይላሉ፦
"ይህን ሰውና አምልኮውን አስተውሉ! ሌላውን ደግሞ ተመልከቱ ሙሉ የቁርኣን ሱራ ሐፍዟል (እንኳን የለሊት ሶላት ሊሰግድ ይቅርና) ሰላተል ፈጅርን ተኝቶ ያሳልፋል።"
📙 شرح أخلاق حملة القرآن الشريط: (12)
እንዴት ነሽ ፈለስጢን
⭕️ አለም ዝም ጭጭ ቢልም አላህ ግን ዝንጉ ጌታም ረሺም አይደለም። ድሉን ያቀርብልናል ኢንሻአላህ!
ፈለስጢኖች በየ ቀኑ እየተቀጠፉ እኛ ደግሞ እዚህ በማይረቡ ነገሮች እንጃጃላለን!
ወደ አላህ እንመለስ፤ ተውበት እናድርግ አላህ አዛኝና ወንጀልን ሚምር ጊታ ነው።❗️
የረመዳን ወር ልቅና!
ረሱል (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦
﴿إِنَّ هذا الشهرَ قدْ حضَرَكُمْ، وَفيهِ ليلَةٌ خَيْرٌ مِنْ أَلْفِ شهْرٍ، مَنْ حُرِمَها فَقَدْ حُرِمَ الخيرَ كُلَّهُ، ولا يُحْرَمُ خيرَها إلّا محرومٌ﴾
“ይህ ወር ለናንተ መጥቶላችኋል። በዚህ ወር ውስጥ ከአንድ ሺህ ወር የምትበልጥ አንድ ሌሊት አለች። የእርሷን መልካም ነገር የተነፈገ ሰው በእርግጥ (መልካም የተባለ ነገር ሁሉ) ተነፍጓል። መልካም ነገር የተነፈገ ደግሞ አይኖርም፤ መልካምን የተነፈገ ቢሆን እንጂ።”
📚 ሶሂህ አልጃሚ: 6647
Israeli airstrikes in Gaza have primarily hit civilian areas, leaving thousands buried under rubble without sufficient equipment for rescue efforts. Thousands of missing Palestinians remain trapped under the rubbles since the war started five months ago.