Secrets of Truth - 𝘽𝙮 𝙍𝙚𝙨𝙝𝙖𝙙
前往频道在 Telegram
● ዲናችንና በሚመለከት ወቅታዊ መረጃዎችን ➶ Current information about Muslims and Islam 🔗 ሌሎችንም አንገብጋቢ ጉዳዮችን የምንተዋወስበት Channel ነው‼️ ➞ በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ አጠር ያሉ ስንኞች (በተለይም ስለ ፈለስጢን 🇵🇸) 🎯 አላማዬ:- የእውነትን ሚስጥሮች ማጋለጥ ነው‼️ #Free_Palestine 🇵🇸
显示更多213
订阅者
无数据24 小时
-17 天
-430 天
帖子存档
Advice Regarding Our Brothers in Palestine | Shaykh Sulayman al-Ruhayli حفظه الله
በመቶዎች የሚቆጠሩ ግብፃውያን የራፋህ መሻገሪያ ላይ ዕርዳታ ወደ ጋዛ እንዲገባ እንዲከፈት ጠይቀው፣ “ፍልስጤም ሆይ ነገ 100 ሚሊዮን ይመጣል” በማለት ዘምረዋል።
ኢማማችን ተፈተዋል ‼
.
የአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ የወረዳ 4 መጅሊስ አመራሮች ከበላይ የእስልምና ጉዳዮች አመራር ጋር በጋራ ባደረጉት ጥረት የመሳለሚያ የቢላል መስጂድ ኢማም ተፈተዋል።
.
የሰፈራችን መሳለሚያ የቢላል መስጂድ የሆኑት ሸይኽ አሊዩ ባለፈው ጁሙዐ ፍልስጤም ላይ እየደረሰ ስላለው በደል በኹጥባቸው በመናገራቸው ብቻ በዛሬው ለምርመራ እንፈልጓችኃለን ብለው ተወስደው ታስረው እንደነበር ይታወሳል።
.
አልሀምዱሊላህ ‼
D.r Meksud Shemsu
فـلسـ𓂆ـطين عربية وعاصمتها القدس الشريف
إن فلسطين هي المعيار الأخلاقي، فإذا أردت رؤية الجانب الأخلاقي في إنسان اعرف موقفه من قضية فلسطين. اللَّهُمَّ حرِّر #المسجد_الأقصى
#الأقصى_خط_أحمر
#فـلسـ𓂆ـطين_عربية
https://t.me/falastien
«ነብዩ ﷺ ላይ አብዝቶ ሰለዋት የሚያበዛ ሙስሊም አገልጋይ፤ አላህ ልቦናውን ያበራለታል፣ ኃጢአቱን ይምርለታል፣ ደረቱን ያሰፋለታል፣ ጉዳዩን ያቃልለታል።»
| ኢብኑ አልጀውዚይ|
اللهم صلِ وسلم على نبينا محمد ﷺ 🤍
ቤተሰቦቹ ላይ በወራሪዋ እስራኤል የአየር ድብደባ ቤቱ ሲፈርስ እሱ ሆስፒታል ቁስለኞችን እያከመ ነበር። ድንገት ሴት ልጁ ቁስለኛ ሁና ወደ ሆስፒታሉ ስትገባ አያት💔 በሌላ በኩል አንድ ወንድ ልጁ እንደጠፋ ተነገረው ደነገጠ!! የ7 አመት እድሜ ያለውን የጠፋው ልጁን ታካሚዎች ውስጥ መፈለግ ይጀምራል። ቁስለኞች ውስጥ ቢፈልግ አላገኘውም ወደ ጀናዛ ክፍል ሲገባ ልጁ ከጀናዛዎች መካከል አገኘው! ልቡ💔 የስራ ባልደረቦቹ (ጓደኞቹ) ሊያረጋጉት ከበው ሳለ የአላህን ውሳኔ ወዶ ተቀብሎ አንዲቅ ቃል ተነፈሰ ቃሏም "አልሀምዱሊላህ" የምትል ነበረች!!
አሏህ በጀነት ያገናኛቸው። በነገራችን ላይ ፈለስጢን ውስጥ አብዛህኛው ህይወታቸው እያለፈ ያለው ህፃናት ናቸው። ለወላጆቻቸው የጀነት መግቢያ ሰበብ ከእሳት ግርዶሽ አላህ ያርግላቸው።
ትላንት መግሪብ ላይ ኢማሙ አሰግዶ እንደ ጨረሰ አንድ ወንድማችን ከኢማሙ ማይኩን ተቀብሎ እንዲህ አለ
ወንድሞቼ እህቶቼ ወገኖቻችን በጋዛ እያለቁ ነው ። ህጻናት በግፍ እየተጨፈጨፉ ነው ። እጃችንን ወደ አላህ አንስተን እያለቅስን ዱዓ እናድርግላቸው ። ይህን ሁሉ ግፍ እያየን እንደ ሌላው ቀን ዝም ብለን ምንም ሳይመስለን የምንኖር ከሆነ ልባችንን ታሟል ። የከፋ አደጋ ላይ ነን '' ብሎ ንግግሩን መጨረስ አልቻለም ። አለቀሰ ።
መልእክቱ መልእክቴ ነው !
Abdurahim Ahmed
ለፍልስጤማውያን ድምፃቸውን ያሰሙት የመስጂድ ኢማም ታሰሩ!
-------------------
ሳምንት ጁሙዓ በፍልስጤማውያን ላይ እየደረሰ ያለውን ግፍና በደል በመቃወም ኹጥባ ላይ የተናገሩት የመሳለሚያው ቢላል መስጂድ ኢማም ሸኽ አሊዩ ኢብራሂምን ዛሬ አስረዋቸዋል።
ከአሱር በኋላ አጠና ተራ ወረዳ 10 ማቆያ ለጥያቄ እንደሚፈለጉ በመግለፅ የወሰዷቸው ሲሆን ከዛ በመቀጠል ከአጠና ተራ ወደ መርካቶ አራተኛ ፖሊስ ጣቢያ አዛውረዋቸዋል።
ሸኽ አሊ በእለተ ጁሙዓ ያሰሙት ንግግር በግፈኛው በፅዮናውያን አይሁዶች በግፍ እየተጨፈጨፉ ላሉ ፍልስጤማውያን ሁላችንም ድምፅ ልንሆን እንደሚገባና ምንም እንኳ አለሙ ባጠቃላይ ለግፈኞቹ አይሁዳውያን እያገዘ ቢሆንም ይህ ግን ፍፁም ስህተት መሆኑንና እንደ ሰብአዊነት ራሱ ፍልስጤማውያን በግፍ መጨፍጨፋቸው ሁላችንንም ሊያሳዝነን የሚገባ የነበረ የግፍ ጭፍጨፋ መሆኑን ያስገነዘቡበት ነግግር ነበር።
የሸኹ መታሰር በሀገራችን ስለ ንፁሀን ደም እንኳ ማውራት ወንጀል እንደሆነና በሀገሪቱ በአመራር ደረጃ በግልፅ የግፈኞቹ ፅዮናውያን ጭፍን ተከታይ መሰግሰጉን ያሳየን ተግባር ነው!
ኢማማችን ምንም ወንጀል ያልፈፀሙ ስለሰብአዊነት ሲሉ የንፁሀንን መገደል ያወገዙ የእውነት ሰው ናቸው!! ዛሬ ነገ ሳይባል ሊፈቱልን ከመገባቱም በላይ ሰብአዊነት በሀገራችን መቀነሱንና ስለ ንፁሀን ደም በከንቱ መፍሰስ መቆም ያለበት የግፍ ተግባር መሆኑን ይበልጥ መስበክ እንዳለብን በተግባር ያሳዩንም ሆነዋል!
ጥቅምት 08 2016
ሁዳ መልቲሚዲያ
