ch
Feedback
Secrets of Truth - 𝘽𝙮 𝙍𝙚𝙨𝙝𝙖𝙙

Secrets of Truth - 𝘽𝙮 𝙍𝙚𝙨𝙝𝙖𝙙

前往频道在 Telegram

● ዲናችንና በሚመለከት ወቅታዊ መረጃዎችን ➶ Current information about Muslims and Islam 🔗 ሌሎችንም አንገብጋቢ ጉዳዮችን የምንተዋወስበት Channel ነው‼️ ➞ በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ አጠር ያሉ ስንኞች (በተለይም ስለ ፈለስጢን 🇵🇸) 🎯 አላማዬ:- የእውነትን ሚስጥሮች ማጋለጥ ነው‼️ #Free_Palestine 🇵🇸

显示更多
213
订阅者
无数据24 小时
-17 天
-430 天
帖子存档
Eid Khateebs at Masjid Al Haram and Masjid An Nabawi Sheikh Dr. Abdul Rahman Al-Sudais will be leading the Eid al-Adha prayer
Eid Khateebs at Masjid Al Haram and Masjid An Nabawi Sheikh Dr. Abdul Rahman Al-Sudais will be leading the Eid al-Adha prayer at Masjid Al Haram after a gap of 11 years. Sheikh Dr. Khalid Al-Muhanna will be leading the Eid al-Adha prayer at Masjid An Nabawi. Join Our Channel For More Updates : https://t.me/haramainsharif

ስለታማ ሰይፎድ [Sharp Swords] ይቺህ ዱንያማ ምንም እኮ ነች። ትንሽ አስደስታን ብዙ ታስከፋናለች❗️ ምንነቷን ካስተነተንናት እንደ መጥፎ ጥላ ወይም ህልም ናት‼️ በዚህች መጥፎ ጥላ በሆነችው፤ በህልም የተመኘነው ሁሉ ስንባንን እንደ ሚጠፈው በሽርፍራፊ ሴኮዶች ለምትቀያየረው ዱንያ ብለን መጥፎ ነገር አንስራ። በሉ እንደውም ነገ ምን እንደሚገጥመን አናውቅምና ዛሬ ላይ አዎ አሁን በዚሁ ቅፅበት መልካም ስራዎችን እናብዛ❗️ ◆ አላህን ከማመፅ ይልቅ መታዘዝና እሱን (አላህን) መገዛት፣ ◆ ከመጎሻሸም መደጋገፍን፣ ◆ ከመገፋፋት አብሽር በአላህ ፍቃድ እኔ አለሁልህ ብለን ሰዎችን መርዳት አስፈላጊ ነው ብቻ ሳይሆን ግዴታችንም ጭምር ነው።  ✍️ ረሻድ ኢብኑ ሙዘሚል

ከእናቱ ጋር ሐጅ እንዲወፍቀው አላህን «ለምኖታል ... ለአመታት . "የመጅሊስን ማስታወቂያ አየኸው?" አለችው እህቱ ደውላ ... የቱ? አላት ... "የሐጅ" አለችው ... አይቶታል ግን ብር የለውም
ከእናቱ ጋር ሐጅ እንዲወፍቀው አላህን «ለምኖታል ... ለአመታት . "የመጅሊስን ማስታወቂያ አየኸው?" አለችው እህቱ ደውላ ... የቱ? አላት ... "የሐጅ" አለችው ... አይቶታል ግን ብር የለውም "እእእእ" አለ ቀዝቀዝ ብሎ  ... . አስደነገጠችው! . "ዘንድሮ ለእማ ነይቻለው!" . ዘለለ ... ደለቀ ... ፈነደቀ ... አላህ ዱዓውን አሳካለት ... ባላሰበው አቅጣጫ ባላሰበው አመት ጌታው ኒያውን ሞላለት! . እንደዛ ነበር ... ብር አልነበረውም ... በዛ ሰሞን ለቤት ኪራይ ሁላ እየተበዳደረ ነበር ... . ምን ልልህ ነው .... ነይት ... ወጥረህ ዱዓእ አርግ ... አላህ እንደሚያሳካልህ አትጠራጠር!» ©: ቢን ዓልይ

The best Dhikr of Dhul Hijjah | Shaykh Abdus Salām Ash-Shuwayr حفظه الله

The Presidency announces His Excellency, Sheikh Abdul Rahman Al Sudais as the Imam of the Eid Al Adha Salat at Masjid Al Hara
+4
The Presidency announces His Excellency, Sheikh Abdul Rahman Al Sudais as the Imam of the Eid Al Adha Salat at Masjid Al Haram and His Eminence, Sheikh Khalid Al Muhanna as the Imam of the Eid Al Adha Salat at Masjid Al Nabawi. رئاسة الشؤون الدينية تعلن: معالي الشيخ عبدالرحمن السديس إمامًا للمسجد الحرام، وفضيلة الشيخ خالد المهنا للمسجد النبوي في صلاة عيد الأضحى.

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የእስራኤልን መንግስት "ጥቁር መዝገብ" ውስጥ ማስገባቱን ገለፀ! ... የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የእስራኤል መንግስት በጦርነት ወቅት ለህፃናት አስፈላጊውን ጥበቃ የማያደርጉ የአለም ሀገራት ስማቸው ከሚሰፍርበት ጥቁር መዝገብ  ማስገባቱን በዋና ፀሃፊው ቃል አቀባይ መግለጫ  ጠቅሷል። . የእስራኤል መንግስት በጋዛ በመፈፀም ላይ ባለው ጥቃት ባለፉት ስምንት ወራት ብቻ 36,000 ንፁሃን ፍልስጤማውያን የተገደሉ ሲሆን ከእነዚህ ውስጥ 15,000 ህፃናት መሆናቸው ይታወቃል። . በዚህ የቅሌት መዝገብ ሀገራቸው መጠቀሷን ተከትሎ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የእስራኤል አምባሳደር " ጊላድ ኤርዳን " እና ጠቅላይ ሚንስትር " ቤኒያሚን ኔታናይሆ" ቁጣቸውን ገልፀዋል። . ©ሀሩን ሚዲያ

أحيوا سنة التكبير وعمِرٌوا بيوتكم #بذكر_الله..  ‏ الله أكبر ، الله أكبر ، الله أكبر  لا إله إلا الله، الله أكبر الله أكبر  ولله الحمد 🪴♥️"‏

🔖ወርቃማ የዙል-ሒጃ 10 ቀናትና መልካም ስራ ላይ መበርታት بسم الله الرحمن الرحيم فضل عشر ذي الحجة ووصايا لمن أدركها ምስጋናና ውዳሴ ለዓለማቱ ጌታ ለአላህ ይሁን ሰላትና ሰላም የሰው ልጆች ሁሉ ምርጥ በሆኑት በነቢዩ ሙሐመድ ላይ ይስፈን አላህ በእዝነቱ ለባሮቹ የተለያዩ ወደርሱ የሚያቃርቡ ልዩ የመልካም ስራ እድሎችን ፈጥሯል በዚህም ተፎካካሪዎች እንዲፎካከሩ፣ ተሽቀዳዳሚዎችም እንዲሽቀዳደሙ ገፋፍቷል የስው ልጅ ነፍስ ሁሌ አንድ አይነት ሁኔታ ላይ ስትሆን ትሰለቻለች አዲስ ነገር ስታገኝም ትነቃቃለች ይህንም ባህሪይ ሽሪዓችን ለነፍሲያ በሚገባ ጠብቆላታል ነቢያችን ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም በሐዲሳቸው የሚከተለውን ብለዋል " ነፍስ፥ አንዳንዴ ለመልካም ስራ ትነቃቃለች አንዳንዴም ትሰለቻለች ንቃትና ከፍተኛ ፍላጎት ባላት ጊዜ ኸይርን ስራ በሚገባ አሰሯት በታከተችና በሰለቸች ጊዜ ግዴታ ለሆኑ ነገሮች እንጂ አትጫኗት" ብለዋል 🔹ይህ በጌታው በሚገባ የሚያምንና ስሜቱንም የማይከተልን ሰው ነፍስ ለማለት እንጂ በመሰረቱ ስሜቱን የሚከተልና የጌታውን ህግ የሚጥስን ሰው ነፍስ አይመለከትም! 🔸መንፈስን ለማደስና ነፍስንም መልካም ነገር ላይ ለማነቃቃት አላህ በየጊዜው በመጠነኛ ልፋትና ጥረት ከፍተኛ ምንዳ የሚያስገኙ እድሎችን አስገኝቷል ይህንንም እድል ፈጥነን እንድንጠቀም ትሩፋቱን ገልጿል ☄ከነዚህም እድሎች መካከል አንዱ የዙል-ሒጃ የመጀመሪያ 10 ቀናቶች ናቸው ቡኻሪይና ሌሎችም ባስተላለፉት ሐዲስ ነቢዩ ሰለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም የሚከተለውን ብለዋል [ما من أيام العمل الصالح فيها أحب إلى الله من هذه الأيام يعني أيام العشر .... الحديث] "ከዙል ሒጃ 10 ቀናት የበለጠ መልካም ስራ ከመቼውም በላይ አሏህ ዘንድ ውድ የሚሆንበት ቀን የለም" 🔸እነሆ አዱኒያ አጭር ናት እድሜያችንም አጭር ነው ከአጭሯ ዱኒያ የቀረውም በጣም አጭር ከአጭሯ ዱኒያ የአንተ ድርሻ ደግሞ እጅግ በጣም አጭር ነው ይህም እውነታ ቀደም ሲል በቁርኣን ተነግኖራል [قُل متاعُ الحياةِ الدنيا قَليل والآخِرةُ خَيرٌ لِمَن اتَقى....] النساء 77 " ነቢዩ ሙሐመድ ሆይ ንገራቸው፥ የዱኒያ ህይወትና መጠቃቀሚያዋ አጭርና ጥቂት ነው የአኼራ ህይወትም (አሏህን ለሚፈሩ) ከዱኒያ የተሻለ ነው" "ሱረቱንኒሳእ 77" አጭርና ጥቂት ከሆነችዋ የዱኒያ ህይወት የቀረው ጥቂቱ መሆኑንም ሲነግረንም አሏህ እንዲህ ብሏል (اقتَرَبَت الساعةُ وانشَقَّ القَمَر) " ቂያማ ተቃረበች ጨረቃም ለሁለት ተከፈለች “ ሱረቱልቀመር 1 (اقتَرَبَ للنَّاسِ حِسابُهم) “ የሰው ልጆች መተሳሰቢያና መመርመሪያ ጊዜያቸው ተቃረበ እነሱ ግን ቸልታና መዘናጋት ላይ ናቸው ” ሱረቱል አንቢያ 1 ▪️አጭሩ እድሜያችን መች እንደሚቋጭ አናውቅምና ሁሌም ራስን ለሞት ማዘጋጀት ብልህነት ነው ለሞት መዘጋጃትም፥ መልካምን ስራ ተሽቀዳድሞ በመስራት ከወንጀል በመራቅ አኼራን በመናፈቅ ነው ▪️ጊዜያችንን በአግባቡ እንጠቀም የውርደትም ይሁን የስኬት ሰበቡ የጊዜ አጠቃቀም ነው፣በዱኒያም በአኼራ በማይጠቅም ነገር ጊዜና ገንዘባችንን የምናባክን ሰዎች:- ☄ቀጣይ ምርጥ 10 የዙልሒጃ ቀናትን በአግባቡና ወደ አላህ በሚያቃርብ ስራ ለማሳለፍ ከወዲሁ ነፍሲያችሁን አሸንፉ! ሌት-ከቀን በኔት ጊዜ፣ ገንዘብና አይናችሁን የምታቃጥሉ፥ አሏህን ፍሩ እራሳችሁንም ፈትሹ ከማይጠቅም ወሬና ተግባርም ራቁ መለከል_መውት ከመምጣቱ በፊትም ከእንቅልፋችሁ ንቁ! የአኼራው ድልድይ/ ሲራጥ ላይ እንዳትወድቁ አላህ ከሚጠላው ስራ በሙሉ በመራቅ ቁርኣን ቅሩ ዘክሩ የኔትና የወሬን ፍቅር በአላህ ውዴታ ቀይሩ! 💥 ውድ የአሏህ ባሮች አላህ ዘንድ ውድ የሆኑ 10 ቀናትን:- ▪️አምስት ወቅት ሰላቶችን በወቅታቸው፣ ከፊትና ከኋላ የሚሰገዱ ሱናችን ከመጠበቅ ጋር፣ ወንዶች በጀማዓ በመስገድ፣ ▪️ቁርኣን በመቅራት፣ ዚክር፣ ዱዓ እንዲሁም ተክቢራ በማብዛት፣ ▪️የተቸገሩ ሰዎችን በመርዳትና የታመሙን በመጠየቅ፣ ▪️ከዙልሂጃ 1 ጀምሮ እስከ 9ኛው ቀን በመጾምና የጾሙ ሰዎችንም በማስፈጠር ወዘተ አሏህ የሚወዳቸው መልካም ስራዎችን በመስራት እናሳልፋቸው ☄ከላይ እንደተጠቀሰው የሰው ልጅ እድሜ በጣም አጭር ነው አሏህ ኸይርን የሻለት ሰው ግን በአጭር ጊዜ ብዙ ቁም ነገር መስራት ይችላል:: በነዚህ ውድ ቀናት ለአኼራችን ስንቅ እንሸምት በጣም ድንቅና የተከበሩ ቀናት ናቸው አሏህ በተከበረው ቁርኣኑ በነዚህ ቀናት ምሏል አሏህ ትልቅ ነው በትልቅና ጠቃሚ ነገር እንጂ አይምልም! ነቢያችንም ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም በነዚህ ቀናት መልካም ስራ ላይ እንደንበረታ ገፋፍተውናል እራሳቸውም ቀናቱን በመልካም ስራዎች ያሳልፏቸው እንደነበረ ተዘግቧል ☄እነሆ ኢማሙ አሕመድና ሌሎችም ዘግበውት አልባኒይ ሰሒህ ባሉት ሐዲስ የምእምናን እናት ሐፍሳ ረዲየላሁ ዐንሃ እንዲህ ብለዋል "ነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም የዓሹራ፣ የዙልሒጃ 10 ቀናትና በየወሩ 3ቀን መጾምን አይተውም ነበር" ብላለች ▪️እዚህ ላይ ልብ መባል ያለበት ነጥብ ቢኖር እናታችን ዓኢሻ ረዲየላሁ ዐንሃ " ነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም የዙልሒጃ10 ቀናትን ጾመው አያውቁም" ብላ የተናገረችበት አጋጣሚ አለ ይህ ማለት እሷ እስከ ምታውቀው ድረስ ለማለት ነው ምክንያቱም ነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ዘጠኝ ሚስቶች ነበር ያሏቸው እሷ ቤት በሚያድሩበት እለት ጾመው አለማየቷን ነው የሚያሳየው እንጂ በጭራሽ አይጾሙም ነበረ ማለት አይደለም።ኡመታቸውን ወደ መልካም ነገር አመላክተው እራሳቸው ወደ ኋላ አይቀሩም! ይህ በእንዲህ እንዳለ የኡሱል ትምህርት ዘርፍ ዑለሞች እንደጠቀሱት አንድን ጉዳይ በተመለከተ ነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም አድርገዉታል ወይስ አላደረጉትም የሚል ውዝግብ ከተነሳ ማድረጋቸው የተጠቀሰው በትክክለኛ ሰነድ መሆኑ ከተረጋገጠ ቅድሚያ የሚሰጠውና ተቀባይነት የሚያገኘው እሱ ነው ምክንያቱም አላደረጉም ያለው አካል የማያውቀውን ነገር እርሱ በማወቁ ጉዳዩ ላይ ይበልጥ አዋቂው ቅድሚያ ይሰጠዋል:: በመሆኑም ከነቢዩ ባለቤቶች መሀል አንደኛዋ ጾመዋል ስትል ሌላኛዋ ደግሞ አልጾሙም ካለች ተቀባይነትና ቅድሚያ የሚያገኘው ጾመዋል ያለችዋ ሃሳብ ይሆናል ማለት ነው። ሰሓቦችና ተከታዮቻቸው እንዲሁም ፈለጋቸውን ይከተሉ የነበሩ ደጋግ ቀደምቶች ትልቁ ጭንቃቸውና የህይወት ዓላማቸው "ዒባዳ" ወይም መልካም ስራ ላይ መሽቀዳደም ነበር ለዚህም ነው ከነሱ መካከል አንዱ እንዲህ ያሉት ☄" በዱኒያ ጉዳይ አንድ ሰው ሊቀድምህ ቢፈልግ መንገዱን አስፋለት በአኼራ ጉዳይ ግን ማንም እንዳይቀድምህ! " አሁን አሁን እየዘነጋን ኖሮ እንጂ አላህም በተከበረው ቃሉ እንዲህ ሲል መክሮን ነበር (سابقوا إلى مغفرة من ربكم وجنة) " ተሽቀዳደሙ……..ወደ ጌታህቹ ምህረትና ወደ ጀነት" ሱረቱልሀዲድ 21 አላህ መልካሙን ሁሉ ካገራላቸው እርሱ ከሚጠላው ነገር በሙሉ ከጠበቃቸው ባሮቹ ያድርገን! ✍ኡስታዝ አሕመድ  ሸይኽ ኣደም

በዚህች ምድር ላይ እንደ አንተ የታደለ ማን አለ⁉️ እናንተ የመካ ሰዎችና በውስጧ ያላችሁ ይህን አዳምጡ። ከእስልምናና ከሸሃደተይን በኋላ እነዚህን ወርቃማ የዱንያ ቀናት መድረስን የሚያክል ጸጋ የለም። በርግጥ ይህን በህይዎት ያለ መላው የዓለም ሙስሊም ታድሎታል። ግን አንተን ለየት የሚያደርግህ እነዚህን የዱንያ ወርቃማ ቀናት ያገኘሃቸው በምድር ላይ እጅግ በጣም ጽዱና የተባረከች በሆነችው የምድር እምብርት መካ ላይ ሆነህ ከሆነ፣ በካዕባ ዙሪያ ጠዋፍ እያደረግክ፣ ዓይንህን ካዕባህ ላይ ፊት ለፊት ደቅነህ ተመስጠህ እያጣጣምክ ከሆነ፤ እንዳንተ ያለ እድለኛ ማን አለ? አስበው! ያለኸው ከቀናት ሁሉ በተከበሩት ወርቃማ የዙል ሒጃህ ቀናት ላይ ነው፣ እነዚህን ቀናት እያሳለፍክ ያለኸው ደግሞ በተከበረው ቤት ነው። ምንኛ መታደል! ስለሆነም ያ ዐብደ-ል'ሏህ! ያለህበትን የተከበረ ወቅትና ቦታ ታሳቢ አድርገህ አላህ በሚወደው ተግባርና ንግግር ላይ እንጂ ከዚያ ውጭ በሌላ እንዳያገኝህ። ما من نعمة بعد الإسلام والشهادتين تمر على عبدٍ مسلمٍ على الكوكب هذه الليلة كمثل أن من الله عليه فبلغه هذه الأيام … ثم ماذا؟! ትናንት ካደረገው ሙሐደራው የተወሰደ ነው። በዚሁ አጋጣሚ ሐጅ የተወፈቃችሁ ወንድምና እህቶች፤ ዶ/ር ሐሰን ቡኻሪይ የሐጅ ተግባር ከመጀመሩ በፊት ኮርስ ከሚሰጡት መካከል አንዱ ስለሚሆን እጅግ መሳጭ ምክር ስለምታገኙበት ወደ መሊክ ፈህድ በማቅናት ፎቅ ላይ በ74 ቁጥር ብትገቡ በቤተ መጽሐፍቱ ፊት ለፊት ባለው ኩርሲይ ላይ ከመጝሪብ በፊት ወይም በኋላ ታገኙታላችሁ። ስኬጁል ስለሚኖር እዛ አካባቢ ተመልከቱ። እንኳን የማላውቀውን የማውቀውም በርሱ አንሰበት ሲገለፅ ይማርከኛል። ሌሎችም ታላላቅ መሻይኾች አሉ። || t.me/MuradTadesse

Increase In Good Deeds During These Ten Days Al-'Allaamah Ibnul-'Uthaymeen, may Allaah have mercy upon him Join the telegram channel: t.me/FruitsOfKnowledge

ذُو الحِجَّةِ Dhuʻl-Hijjah - Shaykh Ibn Uthaymeen رحمه الله تعالى

🕋🕋🕋 🎗 أقبلت العشر 🎗 الشيخ: محمد بن عثيمين ✨ أيامٌ معدودة ▪ ودقائق محدودة ✨ وأعمالّ بأجور ممدودة الله أڪبر الله أكبر الله أكبر لا إله إلا الله በአማርኛ ትርጉም የዙልሂጃ 10ቱ ቀናት 📌ይህች 10 ቀን ነብዩ  ﷺ ስለሷ ይህን ብለዋል አንድም ቀናት የለም መልካም ስራ አላህ ዘንድ ይበልጥ ተወዳጅ የሚሆንባት በዚህች 10 ቀናት ቢሆን እንጅ በአላህ መንገድ ላይ መታገልም ቢሆን? ሲባሉ አዎ እሱም ቢሆን በነፍሱ በገንዘቡ ጂሃድ ወጥቶ ከዚያም ነገር በምንም ያልተመለሰ ሰው ሲቀር ቢሆን እንጂ አሉ 📌በዚህም ታላቅ ሐዲስ ላይ ተመርኩዘን በነዚህ በ10ቱ ቀናት ውስጥ በመልካም ስራዎች በፆም በዚክር በቁርዓን በሰላት በሰደቃ ለሰዎች በጎ በመዋልን በማብዛት እና በሌሎችም ወደ አላህ የሚያቃርቡን በሆኑ መልካም ስራዎች ላይ መበርታት መጠናከር አለብን 📌በነዚህ 10 ቀናት ውስጥ የሚሰሩ መልካም ስራዎች፤ በረመዳን የመጨረሻዎቹ 10ቱ ቀናት ውስጥ ከሚሰሩት መልካም ስራዎች የበለጡ ናቸው 📌የዲን ዕውቀት ተማሪ የሆናችሁ ሰዎች ስለነዚህ ቀናት ትሩፋቶች ሰዎች ዘንድ ግንዛቤን በመፍጠር ማስታወስ እና ማንቃት ይገባቹዋል ብዙሃን ሰዎች ከነዚህ ቀናት ትሩፋቶች የዘነጉ ስለሆኑ ማስታወስን ስለሷ ማወቅን ይሻሉ 📌ከነዚህ ቀናት መፆሙ ይበልጥ የተወደደ የሆነው 9ኛው የአረፋ ቀን ነው ነብያችን ﷺ ስለ አረፋ ቀን ፆም ሲጠየቁ ይህን ቀን በመፆሜ ያለፈውን እና የሚመጣውን ዓመት ወንጀል እንዲማር ከአላህ እከጅላለሁ ብለዋል ✍ طلحة أحمد

Have you read Surah Al Kahaf? --- #ياسر_الدوسري Prophet ﷺ said: "Whoever reads Surah Al-Kahf on Fridays will be adorned with light from that Friday to the next." ● (صحيح جامع الصغير ٢/٦٤٧٠) ‎Prophet ﷺ said: "Whoever recites Surah Al-Kahf on Friday will have a light for him between this Friday and the next." ‎ ‎● {السنن الكبرى ٥٨٥٦} Prophet ﷺ said: "Whoever recites Sūrat Al-Kahf on Friday, it will illuminate him with light from one Friday to the next." ● [المستدرك على الصحيحين ٣٦٨/٢] Prophet ﷺ said: "Whoever recites Sūrat Al-Kahf as it was revealed, it will be a light for him on the Day of Resurrection." ● [السنن الكبرى ٢٤٩/٣]

በሃገረ ሳዑዲ ዐረቢያ የወርሃ ዙል-ሒጃህ ጨረቃ ዛሬ ሐሙስ ስለታየች ነገ ጁሙዓህ ግንቦት 30, 2016 E.C. የዙል-ሒጃህ ወር የመጀመሪያው ቀን ይሆንና ወርቃማዎቹ የዙል-ሒጃህ 10 ቀናት ከነገ ይጀ
በሃገረ ሳዑዲ ዐረቢያ የወርሃ ዙል-ሒጃህ ጨረቃ ዛሬ ሐሙስ ስለታየች ነገ ጁሙዓህ ግንቦት 30, 2016 E.C. የዙል-ሒጃህ ወር የመጀመሪያው ቀን ይሆንና ወርቃማዎቹ የዙል-ሒጃህ 10 ቀናት ከነገ ይጀምራሉ። ስለሆነም ቅዳሜ ጁን 15, 2024 (ሰኔ 08, 2016 E.C.) የዕለተ ዐረፋህ ቀን ሲሆን እሁድ ጁን 16 (ሰኔ 09) ዒደ-ል-አዽሓህ ይሆናል። አላህ በሰላም ያድርሰን‼ እነዚህን ወርቃማ ቀናቶች በዒባዳህ ለማሳለፍ ከወዲሁ ዝግጅት አድርጉ። ቀናቶቹን ከምታሳልፉባቸው ዒባዳዎች መካከል፤ ጾም፣ ዚክር፣ ቁርኣን መቅራት፣ ሶደቃ፣ ለቻለ ሰው ሐጅና መሰል በጎ ተግባራትን ማከናወን ይገኙበታል። አላህ ያበርታን። ሌሎችንም አስታውሱ! The Dhul Hijjah Crescent was SIGHTED today, hence Dhul Hijah.1445 will begin tomorrow Friday, 7th June 2024. || t.me/MuradTadesse x.com/MuradTadesse fb.com/MuradTadesseOfficial fb.com/MuradTadesseOfficialPage tiktok.com/@MuradTadesse ummalife.com/MuradTadesse

አስርቱ ቀናት 🎙በኡስታዝ አብዱልዋሲዕ ሸይኽ ነስሩ ከተንዒም መስጂድ ኹጥባ የተወሰደ ክፍል  1   ኑር ሚድያ Telegram] 👇 https://t.me/Mahfuzmuhdin               [Tik Tok] 👇 https://vm.tiktok.com/ZM6C7vsw2/

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ለሀገራዊ ምክክር የአጀንዳ ዝግጅት የምሁራን ኮሚቴን አዋቅሮ ሰፋ ያለ ጥናት ሲያስጠና ቆይቶ፤ ለኢትዮጲያ ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን በሚከተለው መልኩ አቅርቧል።

★አስርቱ የዙል-ሒጃ ቀናት★