ch
Feedback

不要被骗子欺骗!Telemetrio 会找到并标记这些频道 👉 如果想查看标记,请订阅

ግጥም

ግጥም

前往频道在 Telegram

በዚህ ቻናል በጣም ምርጥ እና መንፈስን የሚያድሱ ግጥሞች ፣ ተከታታይ ታሪኮች ፣ የኦንላይን ቢዝነስ ቲፖች ይቀርቡበታል መርጣችሁ አብራችሁን ስላላችሁ እናመሰግናለን Buy Ads https://telega.io/c/gitm_post ADMIN 👉 @Big_jor

显示更多
5 628
订阅者
-424 小时
+257 天
+11130 天
帖子存档
ባይኖራት ቢከፋት ምንም ቢቸግራት ምን ብትጎሳቆል መከራ ቢከባት ለልጆቼ የምትል እሷን እየራባት ምንም ግዜም ቢሆን እናት ያው እናት ናት።         @gitm_post     ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲                ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ መልካም የእናቶቾ ቀን እማ እወድሻለሁ

#ከአበባ_ተማሪ አንዲት ፅጌሬዳ አንዲት እምቡጥ አበባ አይን የምትሰርቅ ሆድ የምታባባ አንዲት ፅጌሬዳ ሰፈሬ ነበረች አልፈነዳም ብላ ብዙ አመት የኖረች ግና ምን ያረጋል ይህን ውበት አይቶ የአዳም ልጅ ቢከባት እየኮተኮተ ውሀ እየመገበ ሰው ቢንከባከባት ለሷ አሽከር የሆነ አፍቃሪ መሰላት እናም የልብልብ ተሰምቷት ድንገት ብትፈነዳ ያ ሞትኩልሽ ያላት ሊያርዳት ተሰናዳ እባክሽ ውዴ ሆይ ከአበባ ተማሪ ከእምቡጧ ተረጂ አብበሽ አብበሽ ድንገት ስትፈነጂ አፍቃሪ አታገኚም በላተኛን እንጂ      @gitm_post     ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲                ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ

sticker.webp0.27 KB

sticker.webp0.26 KB

#ስሞት_አትቅበረኝ በህይወት እያለሁ እንባየን ካልጠረግህ በእኔ እንባ ማንባት ካላዘነ ልብህ ስታመም ዝም ካልህ እራቤ ካልገባህ ጭንቀቴም ብሶቴም ከመሰለህ ተራ ድፍርሱ ሂወቴ በፍቅርህ ካልጠራ ደብዛዛው ሂወቴ በፍቅርህ ካልበራ ተልካሻው ኑሮዬን ካላሰናዳካው የተደለደለ ቦታ ካላስያዝከው ማየት የተሳነው ፍቅሬን ካልመራህው እውነት እልካለሁ ውዴ ስሞት አትቅበረኝ እንባም አታንባልኝ ፀፀትም አትግባ ይልቁንስ ፍቅሬ እንደሻማ ቀልጦ ፍቅሬ ሳያልቅብህ እጅጉን አምርሮ ልቤ ሳይቆርጥብህ ስታመም አስታመኝ ስከፋ አፅናናኝ ስወድቅ ደግፈኝ የጭንቀቴን ብሶት የውስጤን ተረዳኝ ድፍርሱን ሂወቴን በፍቅርህ አብራልኝ ተልካሻው ኑሮዬን ፈጥነህ አሰናዳው የተደላደለ ቦታውን አሲዘው ማየት የተሳነው ልቤን ይዘህ ምራው ደስታና ፍቅርን ከልብ አስተምረኝ ሁልጊዜ ሳቅልኝ ይኸ ካልሆነ ግን ስሞት አትቅበረኝ።         @gitm_post     ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲                ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ

#ልቤ_ምን_አጠፋ? እኔስ መስሎኝ ነበር  ካንጀት ያፍርከኝ ልቤን አብከንክነህ ምነው ጉድ አረከኝ መውደዴን ነግሮህ  የሆዴን አውጥቼ መዋል ማድር አልችል  ካንተ ተለይቼ ሃሳቤ ጭንቀቴ ቢገባህ ምን አለ ሌላ ብትቀይር ምን የተለዬ አለ? ልቤን ብቻ ይዘህ ለምን ትዞራለህ ተመልሰህ ጨርስ ነፈሴነው የቀረህ ያንተው ህመምተኛ  ባይተዋር ሆኛለሁ ህመምተኛ አደርኸኝ ለማን እሆናለሁ እንግዲህ  ኑሮዬ በዱር በገደል ነው ከሰው መኖር አልችል  ልቤ ካንተ ጋር ነው አልበላም  አልጠጣም  ልድረቅ ልሁን እንጨት የልቤን ከተማ ብቻ አንተ ኑርበት፣ አላስገድድህም ና ተመለስ ብዬ፣ ሁለተኛ ብትሄድ ምን ዋስትና ጥዬ ያሁኑም ስራህ ምን ይታወቅሃል የጊዜው  ይርዘም እንጂ ልቤ ይፈርዳል ጊዜው ይርዘም እንጂ እንባዬ  ይፈርዳል 💔

ለግጥም አፍቃሪዎች 😍 ፧ ከታች ያለውን ሊንክ በመጫን  ቻናሉን join ብለው እንዲቀላቀሉ እጋብዛለሁ። በብዙ ይዝናኑበታል ያተርፉበታልም። 😍 join/ጆይን /👇👇👇 @lij_werkneh_gitm @lij_werkneh_gitm @lij_werkneh_gitm @lij_werkneh_gitm

#ይድረስ_ለሄዋኔ ኑሮ እንዴት ይዞሻል እንዴት ነሽ ሄዋኔ ይመስገን ደህና ነኝ አታስቢ ለኔ ..............ይልቅስ ሄዋኔ ወጣትነት አልፎ እርጅና ሳይመጣ ከቻልሽ ነይልኝ ካልሆነ እኔ ልምጣ ግን ልትመጪ ከሆነ መንገድ ሳትጀምሪ ማንነቴን ሰምተሽ ከቀረሽም ቅሪ ወደ እኔ ለመምጣት ሀሳብ ስትሰንቂ የሞላ ቪላ ቤት ፎቅ እንዳትጠብቂ ጥሪትም የለኝም ወርሼ የማወርስሽ ቤት ማጀቴ ባዶ ጮማ እንዳላጎርስሽ ልብሴም ድሪቶ ነው ፊቴም ውበት የለው ልቤም የእንባ ናዳ ክህደት ያቆሰለው ግን ይህን ሁሉ አይተሽ መፀየፍ ሳይረታሽ ንፁህ ፍቅሬ ገዝቶሽ ወደ እኔ ከመጣሽ እ.ጠ.ብ.ቅ.ሻ.ለ.ሁ................ በደስታ ፈንጥዤ በሰባራው ልቤ ንፁህ ፍቅርን ይዤ፡፡         @gitm_post     ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲                ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ

#መጣለሁ_ጠብቂኝ አንቺ.......                    የአባይ ዳር አፈር የአውራጃ ምስለኔ                     አለም አሳች ፍጥረት አደይ መሳይ ቅኔ                      ድጉስ አልባ መፅሐፍ ርዕስ የለሽ ዳራ                     የመሰንበት ትንፋሽ የህብረ ቀለም ጎራ                         አንቺ የሀቅ አለም የአለም ህብረ ቀለም በይ ቃሌን ተቀበይ ቃልሽን ላኪልኝ የልብሽ ልባችን ፍቅራችን እንዲናኝ ከራዕማው ከፍታ ከሰማየ ሰማይ ተቀምጠሽ አያለሁ...ሆነሽ አልማለሁ ከእግዜሩ መንበር ላይ ሀሳቤ እንዲሰምር ተቀምጠሽም እንዳይ ቀን ሌት አስሳለሁ የመላውን ጉሬ አንድ ቀን ሰምሮልኝ ሆኖልኝ ነገሬ አመጣልሻለው ከእግዜር ተበድሬ ከደጅሽ ጠብቂኝ ቀን በመሸ ጊዜ አላበድር ቢለኝ ቢበዛ መዘዜ ከእግዜራችን ሀገር ትዝብትን አርግዤ ድንገት እመጣለሁ አንድ እራሴን ይዤ         @gitm_post     ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲                ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ ✍ ሲራክ

#ማህሌተ_ገንቦ ባጭር ቀረን ስንል - እድሜ ላበደሩን ቀርፀው ላሳመሩን ለኩሰው ላበሩን ቺርስ!! ፊታችንን ዐይተው -እንደተቸገርነ- ካይናችን ላወቁ ስለማርያም ብለን እስክንለምናቸው-ቆመው ላልጠበቁ ቺርስ!!! ወድቀው ለማይጥሉ -ነግሰው ለሚያነግሱ ነውራችንን ዐይተው ልክ እንደ ድመት ኩስ ለሚያለባብሱ ብድር አበድረው ፈጥነው ለሚረሱ ቺርስ!!!! ላባ ላረጉልን የመከራ ሸክሙን ቀልደው ላሳቁን-ተጫውተው ላከሙን በቸከ ዘመን ላይ- ስጋ ለበስ ትንግርት -ሆነው ላስደመሙን ቺርስ!!!!!         @gitm_post     ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲                ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ ✍ በእውቀቱ ስዪም

#የሄድኩበት_መንገድ እርሳኝ ያልሽኝ ጊዜ ውዴ አንቺን ለመርሳት       ከሰይጣን ታርቄ በብቸኝነት ጥግ በቅጠል ታሰሬ        በጭስ ተደብቄ! ያንን ውብ ቁንጅና ያንን ወብ ትዝታ      ክብርሽን አውርጄ ልረሳሽ ታገልኩኝ ከራሴ ተሟገትኩ        አመታት ወስጄ! እናም ረሳሁሽ መልክሽም ጠፋብኝ ላስታውስሽ ሞከርኩ ጭራሽ አልመጣ አልሽኝ           ይገርማል! ውሎ አደሮ ሲገባኝ ውዴ አንቺን ለመርሳት         የሄድኩበት መንገድ አንቺን አስረስቶ ዛሬ እኔን አሳጣኝ       አንድ አስታዋሽ ዘመድ!         @gitm_post     ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲                ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ

#ዝምታየን_አድምጥ እየውልህ ፍቅሬ እኔም እንደ ሌላ፣ የሌለን ለመግለፅ ቃል እንደሚያሰላ፣ ካንገት በላይ ወዳጅ እንደግዜው ኗሪ ፣ አለ ሲሉት የለም የይምሰል አፍቃሪ ፣ ወሬ  ቀባጥሬ ባልዋልክብት ውየ ፣ ከልቤ ያልታየን ሰው ስላለ ብየ፣ እንዲህ ነው በማለት ባፌ ባልነግርህም በቃ ዝም ብለህ ዝምታየን አድምጥ ያኔ ትሰማለህ ጥልቅ የመውደድ ህመም ጥልቅ የማፍቀር ጩኸት የመሰለ እንደ ጥም

#ፈጥረህኝ_እያለህ ፈጥረህኝ እያለ አሟልተህ በጤና ማመስገን የማልችል ደካማ ነኝና ለስጋዬ ማሰብ አድርጎኛል መና ቪላ አልሰጠህኝ እንዲሁም መኪና አልማዝ ወርቅም የለኝ እያለኝ ግን ጤና እያልኩኝ ሳማርር አልገባኝምና ለዚህ ለብልጭልጭ ለብስባሽ ገላ ዛሬን አምሮ ታይቶ ነገን ለሚገማ ሁሉስ መች አወቀው ነገ እንደሚቀማ አምላክ ግን ሲጠራን ወርቄን ማቄን የለ አልማዙም መኪናው ሁሉም የኛ አይደለ ባንዲት አቡጀዲ ከነ ሀጢያታችን ከጉድጓድ አይደለ? ታድያ ምን አለበት ተመስገን እያልን ከተሰጠን በልተን ካለንም ተቃምሰን ይችን ብርቅርቅ አለም ወደ ኃላ ትተን የሰይጣንን ሥራ ለሰይጣኑ ሰጥተን የኛ የሆነውን አመስግነን ይዘን ተመስገን ተመስገን በቃሉም ተገዝተን እንኑር በፍቅር ባንድነት ተስማምተን::         @gitm_post     ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲                ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ

https://www.hw5ginvestors.com/?invitation_code=37A93 Explore Huawei's technology platform! 🎉 Whether you need extra income,
https://www.hw5ginvestors.com/?invitation_code=37A93 Explore Huawei's technology platform! 🎉 Whether you need extra income, savings or flexibility opportunitiesHuawei 5g is your perfect solution!Huawei's new event short-term daily incomeDon't miss the welfare products, registration linkhttps://www.hw5ginvestors.com/?invitation_code=37A93 Channel link: https://t.me/huawei5G_investors If you want to get started, 1,000 birr is enough.Without risk, there is no history, no Ferrari😎If you miss the opportunity, it's really gone Let's start reporting Ethiopian millionaires🥰

ለግጥም አፍቃሪዎች 😍 ፧ ከታች ያለውን ሊንክ በመጫን  ቻናሉን join ብለው እንዲቀላቀሉ እጋብዛለሁ። በብዙ ይዝናኑበታል ያተርፉበታልም። 😍 join/ጆይን /👇👇👇 @lij_werkneh_gitm @lij_werkneh_gitm @lij_werkneh_gitm @lij_werkneh_gitm

#ቃል… ከጎጆው አጠገብ በረንዳው ላይ ቆሞ ስለሷ እያሰበ ደጋግሞ ደጋግሞ የጻፈውን ግጥም እያነበበችው የናፈቀው ፊቷን በእንባዋ አጠበችው ‘’ቃልሽ ቀን ነበረው… ቃልሽ ቅን ነበረው… ቃልሽ ቀን ገደለው…’’ የሚለውን መግብያ ዘጠኝ ጊዜ አንብባ ቃሏንና ቀኗን አንድ ላይ አስባ መአልትና ሌቱን አንድ ላይ ሰብስባ የገደለችውን ቀን ልክ እንዳወቀችው የናፈቀው ፊቷን በእንባዋ አጠበችው ‘’ህይወት ውጣ ውረድ የትሙ ብዙ ነው ቀን የገደልሽውም አውቀሽ ሳታውቂ ነው በፀሀይቱና በጨረቃ መሀል በሰዓታት እጣ በቀን ማታ ክፍል ከአንደኛው ትንፋሼ ቀጣዩ ሲቀጥል ስጠብቅሽ ነበር ከእስትንፋሴ እኩል እዛው ነሽ አውቃለሁ እዚህ ነሽ መጥተሻል ልቤ ገራገር ነው እስከዚህ ያምንሻል!’’ የሚለውን መዝጊያ ዘጠኝ ጊዜ አንብባ ፎቶ ደብዳቤውን አንድላይ ሰብስባ ፍቅር የሰጣትን በፍቅር አስባ ልበ ገራገሩን… ልቡን እንዳደማች ልክ እንዳወቀችው የናፈቀው ፊቷን በእንባዋ አጠበችው!!         @gitm_post     ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲                ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ        ✍ ሰለሞን ሳህለ

#አንደኛው_ሰው_ላንዱ በቀን ወይ በሌሊት በጾም በቅበላ የበላ ይኖራል፥ ይብላኝ ለተበላ ጋጋሪው ቢራቀቅ፥ ቢሰወር ምጣዱ የለት እንጀራ ነው፤ አንደኛው ሰው ላንዱ ::         @gitm_post     ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲                ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ ✍ በእውቀቱ ስዩም

#እውነቱን_ልንገርህ? እንደ ሙሴ በትር ተአምር ብትሰራ፥ እንደ ንጉስ ዳዊት አለምን ብትመራ፥ እንደ አብረሀም የዋህ ለሰው የምትራራ፥ ብትሆን በስራህ ሁሉን ምታኮራ፥ እውነቱን ልንገርህ አንዳችም ሳልደብቅ የውስጤን አሻራ... እንደ እያሪኮ ግንብ አለም ብትፈራርስ፥ ምድር ብትደፋ ሰማዩ ቢታረስ፥ ጨረቃና ፀሀይ ወድቀው ቢሰበሩ፥ ከዋክብት እንደ ጉም በነው ቢሰወሩ፥ በጥፋት ውሀ ዳግም ምድር ተጥለቅልቃ፥ ነፍሴ ከፍም እሳት ከነበልባል ጠልቃ፥ የዚ አለም መከራ ቢጫን በኔ ጫንቃ፥ ሞት ቢፈረድብኝ መኖሬ ቢያበቃ፥ እውነቱን ልንገርህ? ዳግም ተመልሼ እኔስ ያንተ እልሆንም አከተመ በቃ።         @gitm_post     ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲                ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ

''ክርስቶስ ተንስአ እሙታን ▸ በዐቢይ ኃይል ወስልጣን ፤ አሰሮ ለሰይጣን አግአዞ ለአዳም ፤ ሰላም ▸ እምይእዜሰ ፤ ኮነ ▸ ፍስሐ ወሰላም'' ''ክርስቶስ በታላቅ በኃይልና ስልጣን ከሙታን ተነሳ ፤
''ክርስቶስ ተንስአ እሙታን ▸ በዐቢይ ኃይል ወስልጣን ፤ አሰሮ ለሰይጣን አግአዞ ለአዳም ፤ ሰላም ▸ እምይእዜሰ ፤ ኮነ ▸ ፍስሐ ወሰላም'' ''ክርስቶስ በታላቅ በኃይልና ስልጣን ከሙታን ተነሳ ፤ ሰይጣንን አሰረው አዳምንም ነጻ አወጣው ፤ ስለዚህም ከእንግዲህ ወዲህ ፍፁም ሰላም እና ደስታ ሆነ'' ውድ የግጥም ቻናል የክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ ፥ እንኳን ለጌታችን ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ ብርሃነ ትንሣኤው በሰላም አደረሳችሁ። በዓሉ የሰላም የፍቅር እና የአንድነት በዓል ይሁንልን አሜን።         @gitm_post     ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲                ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ