ch
Feedback

不要被骗子欺骗!Telemetrio 会找到并标记这些频道 👉 如果想查看标记,请订阅

️ፈለገ ጥበብ Photography (ፈለገ ጥበብ ፎቶ ማህደር ዘፈለገ ጥበብ ሚዲያ)

️ፈለገ ጥበብ Photography (ፈለገ ጥበብ ፎቶ ማህደር ዘፈለገ ጥበብ ሚዲያ)

前往频道在 Telegram

እንኳን ወደ ፈለገ ጥበብ ሚዲያ የ 🅿🅷🅾🆃🅾🅶🆁🅰🅿🅷 ቻናላችን በደህና መጣቹ። ✔️በፈለገ ጥበብ ሰንበት ትምህርት ቤትም ይሁን በተለያዩ ደብራት የሚነሱ ፎቶግራፎችን በዚህ የፈለገ ጥበብ የፎቶ ማህደር ላይ ያኙታል። መልካም ጊዜ 📸📷📹💽

显示更多
733
订阅者
无数据24 小时
-57 天
-530 天
帖子存档
በደብረዘይት ደብረመዊዕ ቅዱስ ሚካኤል ወደብረ ብስራት ቅዱስ ገብርኤል አብያተክርስቲያናት የመልአኩ የቅዱስ ራጉኤል ክብረ በዓል እና የአዲስ ዓመት ክብረበዓልን ተከበረ። መስከረም 01/2017 ዓ.ም #FTM #ፈለገ_ጥበብ_ሚዲያ

የምሥራቅ ሸዋ ሀገረ ስብከት ሰንበት ት/ቤቶች አንድነት ላስተማራቸው ሚኒስትሪ ተፈታኞች የምርቃትና የሽልማት መርሓ ግብር ብፁዕ አቡነ የምሥራቅ ሸዋ ሀገረ ስብከት ሰንበት ት/ቤቶች አንድነት ላስተማራቸው የሚኒስትሪ ተፈታኞች የምርቃትና የሽልማት መርሓ ግብር ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ የምሥራቅ ሸዋ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ የዝዋይ ሐመረ ብርሃን ቅዱስ ገብርኤል ገዳምና ሥራ አመራር መንፈሳዊ ኮሌጅ የበላይ ጠባቂ ፡ ክቡር መልአከ ምሕረት ቆሞስ አባ ገብረ መድኅን ንጉሤ የምሥራቅ ሸዋ ሀገረ ስብከት ዋና ሥራ አስኪያጅ ፡ የሀገረ ስብከቱ የየመምሪያ ክፍል ኃላፊዎች ፡ የአድባራት አስተዳዳሪዎች ፡ አበው ካህናት ፡ የአንድነቱ ከፍተኛ አመራሮች ፡ ከልዩ ልዩ ወረዳዎችና አጥቢያ አብያተ ክርስቲያናት የተውጣጡ የደረጃ ተማሪዎችና አመራሮች  በተገኙበት በአዳማ ደብረ ታቦር  ምሥራቀ ፀሐይ ቅዱስ እግዚአብሔር አብ  መሰብሰቢያ አዳራሽ አካሄደ፡፡ መርሐግብሩ በብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ መሪነት በጸሎተ ወንጌል የተጀመረ ሲሆን የዝማሬ አገልግሎት በአዳማ ናዝሬት ምሥራቀ ፀሐይ ቅዱስ እግዚአብሔር አብ ቤተ ክርስቲያን ፈለገ ብርሃን ሰንበት ት/ቤት ዘማሪያን የቀረበ ሲሆን በዲ/ን ፍስሐ ታደሰ  የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት ም/ሰብሳቢና የትምህርት ክፍል ኃላፊ በአዲስ መልክ እየተተገበረ በሚገኘው ሥርዓተ ትምህርት ዙሪያና ስለ አፈጻጸሙ ዝርዝር ሪፖርት ቀርቧል፡፡ በመቀጠልም የአንድነቱ ተቀዳሚ ም/ሰብሳቢ መምህር ኢንጅነር ዓለም አንተ አበጀ የሰንበት ት/ቤት መዋቅር በሚል ርዕሰ ጉዳይ ሰንበት ት/ቤት አወቃቀር የሰንበት ት/ቤት ተልዕኮ የሰንበት ት/ቤት አስፈላጊነት ምን እንደሚመስልና የሰንበት ት/ቤት መዋቅር በቤተ ክርስቲያን ላይ መዘርጋቱ ያለው ፋይዳ ምን እንደሚመስል ዘርዘር ያሉ ገለጻዎችን  አቅርቧል፡፡ በመቀጠልም ታላቁ የበረከት አባት ብፁዕ አባታችን አቡነ ጎርጎርዮስ  በወጣት ከተማ የአንድነቱ ፀሐፊ  አቅራቢነት ለደረጃ ተማሪዎች የካርድና ሽልማት የሰጡ ሲሆን ክቡር መልአከ ምሕረት ቆሞስ አባ ገብረ መድኅን ንጉሤ  የሀገረ ስብከቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ  ትምህርተ ወንጌል ሰጥተዋል፡፡ በመጨረሻም ብፁዕ አባታችን አባታዊ መልእክት አስተላልፈዋል። የመርሀግርብሩን ሙሉ ፎቶ ያግኙ👇👇👇 https://t.me/felegetibebimage #ፈለገ_ጥበብ_ሚዲያ ጳጉሜ 2016 ዓ.ም