ch
Feedback

不要被骗子欺骗!Telemetrio 会找到并标记这些频道 👉 如果想查看标记,请订阅

Addis Ababa Communication Bureau

Addis Ababa Communication Bureau

前往频道在 Telegram
3 954
订阅者
-124 小时
-67 天
-630 天
帖子存档
12ኛውና ከፍተኛ የአፍሪካ ደህንነት ጉባኤ የሆነው ጣና ፎረም ከመጀመሩ አስቀድሞ፣ የሞዛምቢኩን ፕሬዝዳንት ዳንኤል ቻፖን በደስታ ተቀብያለሁ። ትብብራችንን ማጠናከር እና የጋራ ጥቅሞችን ማሳደግ በሚቻል
+3
12ኛውና ከፍተኛ የአፍሪካ ደህንነት ጉባኤ የሆነው ጣና ፎረም ከመጀመሩ አስቀድሞ፣ የሞዛምቢኩን ፕሬዝዳንት ዳንኤል ቻፖን በደስታ ተቀብያለሁ። ትብብራችንን ማጠናከር እና የጋራ ጥቅሞችን ማሳደግ በሚቻልባቸው ጉዳዮች ዙሪያም የሁለትዮሽ ውይይት አካሂደናል። It was a pleasure to welcome Mozambique’s President Daniel Chapo, ahead of the opening of the 12th Tana High-Level Forum on Security in Africa. We also held bilateral talks on strengthening our cooperation and advancing matters of shared interest. ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር)

City transformation as a driving force of African Progress: The Experience from Addis Ababa Addis Ababa hosted the 2026 Afric
+9
City transformation as a driving force of African Progress: The Experience from Addis Ababa Addis Ababa hosted the 2026 African Mayoral Leadership Initiative (AMALI) Reunion this week. The city has shared its experiences in various developmental interventions. The city has demonstrated its undivided attention for Early Childhood Development (ECD) for the mayors and governors during the field visits. As Mayor Adanech Abiebie underscored during the opening of the reunion, Addis Ababa has integrated the thought of Medemer Government in its human-centered developmental interventions. As a result, the city has achieved direct and equitable benefit of its residents through which changes in the everyday life of the people is https://www.facebook.com/share/p/1Bz9L5ziJu/

"IMEX America 2026" የማይስ ቱሪዝም ኤክስፖ በላስ ቬጋስ ኔቫዳ በይፋ ተከፍቷል! አዲስ አበባ ለመጀመሪያ ጊዜ የተሳተፈችበት "IMEX America 2026" የማይስ ቱሪዝም ኤክስፖ በላስ ቬ
+5
"IMEX America 2026" የማይስ ቱሪዝም ኤክስፖ በላስ ቬጋስ ኔቫዳ በይፋ ተከፍቷል! አዲስ አበባ ለመጀመሪያ ጊዜ የተሳተፈችበት "IMEX America 2026" የማይስ ቱሪዝም ኤክስፖ በላስ ቬጋስ፣ ኔቫዳ በደማቅ ሁኔታ ተከፍቷል:: ይህ የኮንፍረንስ ቱሪዝም ንግድ ኤክስፖ፣ በአለም ቀዳሚ ከሆኑ የኮንፍረንስ ቱሪዝም ኤክስፖ አንዱ ሲሆን፣ ከ150 በላይ የአለም ሀገራት የተውጣጡ ከ3,700 በላይ ተሳታፊ ድርጅቶችን ተገኝተዋል:: የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በዚህ ታላቅ የማይስ ቱሪዝም ኤክስፖ ላይ በመተሳተፍ የከተማዋን የቱሪዝም ኢንቨስትመንት ዕድሎች እና የቱሪዝም ሀብቶችን ለዓለም እያስተዋወቀ ይገኛል:: አዲስ አበባ ከቅርብ አመታት ወዲህ በርካታ አለም አቀፍ እና አህጉር አቀፍ ኮንፍረንሶችን በማስተናገድ በአፍሪካ ግንባር ቀደም ከሆኑ የኮንፍረንስ ቱሪዝም መዳረሻዎች መካከል አንዷ መሆኗን ተከትሎ፣ እንዲህ አይነቱ የቱሪዝም ንግድ ኤክስፖ ይበልጥ የከተማዋን የቱሪዝም ሀብት ለማስተዋወቅ እና በዘርፉ ካሉት ተዋናዮች ትስስር ለመፍጠር ያግዛል::

As Africa, Ethiopia makes us proud. Addis Ababa is a city transforming it's self. we have seen the capacity of Mayor Adanech Abiebie's transformative leadership. :-Mamphela Ramphele; Advisor of AMALI project

የአፍሪካ ከተሞች ከንቲባዎችንና ባለድርሻ አካላትን በመስክ ሥራዎቻችን በማስጎብኘት፣ የከተማችንን የለውጥ ተሞክሮ አካፍለናል። We shared Addis Ababa’s transformation journey
+9
የአፍሪካ ከተሞች ከንቲባዎችንና ባለድርሻ አካላትን በመስክ ሥራዎቻችን በማስጎብኘት፣ የከተማችንን የለውጥ ተሞክሮ አካፍለናል። We shared Addis Ababa’s transformation journey with mayors from across Africa and other stakeholders through field visits showcasing our development initiatives. ከንቲባ አዳነች አቤቤ

አዲስ አበባ ለአፍሪካ ከተሞች ተምሳሌት መሆን ጀምራለች! ዛሬ አዲስ አበባ ለሁለተኛ ጊዜ ያስተናገደችውን የአፍሪካ ከተሞች ከንቲባዎች አመራር ኢኒሼቲቭ (AMALI) የ2026 የአመራሮች ፎረም ተሳታፊዎ
+9
አዲስ አበባ ለአፍሪካ ከተሞች ተምሳሌት መሆን ጀምራለች! ዛሬ አዲስ አበባ ለሁለተኛ ጊዜ ያስተናገደችውን የአፍሪካ ከተሞች ከንቲባዎች አመራር ኢኒሼቲቭ (AMALI) የ2026 የአመራሮች ፎረም ተሳታፊዎችን ተቀብለናል። ይህ መድረክ ልምድ ለመለዋወጥ፣ እርስ በርስ ለመማማርና ከተማችን እያካሄደች ያለውን የለውጥ ጉዞ ለማካፈል ጠቃሚ ዕድል ፈጥሯል። የከተማችን የለውጥ ጉዞ በጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ አርቆ አሳቢነትና ለከተማዋ ባስቀመጡት ራዕይ የተቃኘ ነው። ይህንን ራዕይ ወደ ተጨባጭ የልማት ውጤቶች እየቀየርን ነው። በትራንስፖርት፣ በቤቶች ልማት፣ በቴክኖሎጂ የተደገፉ አገልግሎቶችና በትውልድ ግንባታ ላይ በምናከናውናቸው ሥራዎች የነዋሪዎቻችንን ተጠቃሚነት እያረጋገጥን ነው። በራሳችን የፋይናንስና የዕውቀት አቅም ላይ ተመሥርተን በመሥራታችን፣ የአዲስ አበባ ተሞክሮ ለሌሎች የአፍሪካና የዓለም ከተሞች ጠቃሚ ትምህርቶችን እያበረከተና አዳዲስ የልማት ዕድሎችን እያመላከተ መሆኑ ያስደስተናል። በተለይም አዲስ አበባን በአፍሪካ ህፃናትን ለማሳደግ ምርጥ ከተማ ለማድረግ ያለንን ጽኑ ቁርጠኝነት እያሳየን ነው። በሕፃናት እድገት (ECD) ላይ ያተኮሩ ተግባራትን በማጠናከር፣ የሕፃናትን ደህንነት፣ ትምህርትና የወደፊት ሕይወት በከተማችን የልማት አጀንዳ ማዕከል ላይ አስቀምጠናል። ከየአፍሪካ ከተሞች ከንቲባዎች አመራር ኢኒሼቲቭ (AMALI) መሪዎችና የፎረሙ ተሳታፊዎች ጋር በመሆን፣ በከተማችን በልዩ ሁኔታ የተገነባውንና ለፕሮግራሙ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ባደረገችው ክብርት ሊዛ ዲዬጎ መታሰቢያ የተሰየመውን የሕፃናት እንክብካቤ ማዕከል መርቀን ለአገልግሎት ከፍተናል። ለዚህ መርሐ ግብር https://www.facebook.com/share/p/1Md74sj417/

የከንቲባ አዳነች አቤቤ መልዕክት *********** የአንደኛ ሩብ ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም ግምገማ አጠናቀናል! ለተከታታይ ሁለት ቀናት ስናካሂድ የነበረውን የከተማ አስተዳደራችንን የአንደኛ ሩብ ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም ግምገማ አጠናቀናል። በግምገማችንም በአንደኛው ሩብ ዓመት የከተማችን ነዋሪዎች የጣሉብንን እምነትና የሰጡንን ኃላፊነት በታማኝነት ለመወጣት በገባነው ቃል መሠረት፣ በነዋሪዎቻችን የኑሮ ሁኔታና ተጠቃሚነት ላይ ለውጥ ያመጡ፣ ለቀጣይ ሥራዎቻችንም መሠረት የጣሉ ውጤታማ ተግባራትን መፈጸም መቻላችንን ገምግመናል። ለአፈጻጸማችን ስኬት መሠረት የሆኑት በከተማችን የተፈጠረው የሥራ ትጋት፣ በታማኝነት የማገልገል ባህል፣ በመደመር መርህ በፍጥነትና በጥራት የመፈጸም ልምድ እንዲሁም ጊዜን ሳናባክን ዕቅድን ወደ ተግባር የመቀየር አቅማችን ናቸው። የመደመር መንግሥት ሥራዎችን አዲስ የፖለቲካ ባህል በሚፈጥር መልኩ ከመፈጸም ባሻገር፣ ወቅቱ የሚጠይቀውን አደረጃጀት በማሻሻልና ውጤትን መሠረት በማድረግ አዳዲስ የአመራር ስምሪቶችን ማከናወን ችለናል። በ90 ቀናት ዕቅዳችን የክረምት በጎ ፈቃድ ሥራዎችን፣ የአረንጓዴ ዐሻራ ሥራዎችን፣ የቤቶች ግንባታንና የተጎሳቆሉ አካባቢዎችን የማሻሻል ሥራዎችን አከናውነናል። የቤት ችግር ያለባቸውና በልማት ምክንያት ከመኖሪያቸው የተነሱ ዜጎች ንጹሕና የዜጎችን ክብር የሚጠብቁ ቤቶች እንዲያገኙም ሠርተናል። ዝቅተኛ ገቢ ያላቸውን ነዋሪዎች የኑሮ ጫና ለመቀነስ የማዕድ ማጋራት ሥራዎችን አከናውነናል። በተጨማሪም፣ በክረምት ግንባታ አይከናወንም የሚለውን የቆየ አስተሳሰብ በመቀየር በርካታ ፕሮጀክቶችን ማከናወን ችለናል። በትራንስፖርት መሠረተ ልማት ዘርፍም አራት ትላልቅ የመኪና ማቆሚያና ተርሚናል ማዕከላትን ወደ ሥራ አስገብተናል። አዳዲስ መንገዶችን፣ የእግረኛና የብስክሌት መንገዶችን፣ የውሃ ማስወገጃና የፍሳሽ መስመሮችን በመገንባት በክረምት ወቅት የሚከሰቱ የጎርፍ አደጋዎችን ለመቀነስና በሰው ሕይወት ላይ ይደርስ የነበረውን የሞት አደጋ ለመከላከል ተጨባጭ ሥራዎችን ሠርተናል። በክረምት ወቅት የሚኖረውን የኑሮ ጫና ለመቀነስ በሰባት የገበያ ማዕከላት ሰፊ የምርት አቅርቦት ወደ ከተማችን እንዲገባ በማድረግ የኑሮ ውድነቱን ለመቀነስ ሠርተናል። የቅዳሜና እሁድ ገበያዎችንም ደረጃ ማሳደግ ችለናል። እነዚህን ጨምሮ በሰው ተኮር ልማት ዘርፎች ያከናወንናቸው ተግባራት ማኅበራዊ ፍትሕን ከማስፈን አንጻር ጉልህ ሚና ነበራቸው። በተመሳሳይ፣ በተቋማትና በግለሰቦች መካከል የሚታዩ የአፈጻጸም ልዩነቶችን በድጋፍና በክትትል ሂደታችን ከመሠረቱ ለመፍታት እንሠራለን። የምንሠራቸው ሥራዎች ሁሉ ከተቋም ግንባታ አንጻር ትኩረት የሚሹ ናቸው። የተበታተነ አቅም ራዕይን አያሳካም፤ ሀገርንም አይገነባም። ስለዚህ እያንዳንዱ ሠራተኛ በግልጽ የተለየ የሥራ ድርሻና ተጠያቂነት ኖሮት፣ በመደመር መርህ ተቀናጅቶ የሚሠራበትን አሠራር ማጠናከር ይጠበቅብናል። የሕዝብን ጥቅም የሚያስቀድም፣ የዜጎችን ክብር የሚጠብቅና ተጨባጭ ውጤት የሚያመጣ ሥራ እንሠራለን!

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በዛሬው ዕለትም እንጂነር ሽመልስ እሸቱን የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር ዋና ዳይረክተር አድርገው ሾመዋል። Prime Minister Abiy Ahmed (PhD)
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በዛሬው ዕለትም እንጂነር ሽመልስ እሸቱን የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር ዋና ዳይረክተር አድርገው ሾመዋል። Prime Minister Abiy Ahmed (PhD) has also appointed Engineer Shimelis Eshetu as the Director General of the Ethiopian Roads Administration today. #PMOEthiopia #የመደመርመንግሥት

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በዛሬው ዕለት ለሚከተሉትን አመራሮች ሹመት ሰጥተዋል፦ 1. አብዱልዋሳ አብዱላሂ (ዶ/ር) - የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ኢንስቲትዩት (IFA) ዋና ዳይሬክተር 2.
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በዛሬው ዕለት ለሚከተሉትን አመራሮች ሹመት ሰጥተዋል፦ 1. አብዱልዋሳ አብዱላሂ (ዶ/ር) - የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ኢንስቲትዩት (IFA) ዋና ዳይሬክተር 2. ካፒተን ተፈራ ካሳ - የኢትዮጵያ የባሕር ትራንስፓርት እና ሎጂስቲክስ ዋና ስራ አስፈጻሚ #PMOEthiopia #የመደመርመንግሥት

ዛሬ ማለዳ ከከተማችን ነዋሪዎቻና አመራሮች ጋር በመሆን ስፖርታዊ እንቅስቃሴ አካሂደናል። በአእምሮና በአካል ብቁ፣ በአስተሳሰብ ንቁ የሆነ ሕዝብ በመደመር ተምሳሌት ከተማ እንገነባለን! ለላቀ ውጤት፣
+9
ዛሬ ማለዳ ከከተማችን ነዋሪዎቻና አመራሮች ጋር በመሆን ስፖርታዊ እንቅስቃሴ አካሂደናል። በአእምሮና በአካል ብቁ፣ በአስተሳሰብ ንቁ የሆነ ሕዝብ በመደመር ተምሳሌት ከተማ እንገነባለን! ለላቀ ውጤት፣ የተደመረ አቅም፤ ለኢትዮጵያ ብልጽግና! ፈጣሪ ኢትዮጵያንና ሕዝቦቿን ይባርክ! ከንቲባ አዳነች አቤቤ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በዛሬው ዕለት የሚከተሉትን የተቋማት አመራሮች ሾመዋል፦ #PMOEthiopia
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በዛሬው ዕለት የሚከተሉትን የተቋማት አመራሮች ሾመዋል፦ #PMOEthiopia

በመሶብ የአንድ ማዕከል ዲጅታል የመንግስት አግልግሎት ፈጣንና ተደራሽ አገልግሎት በመስጠት 99.6% የተገልጋይ እርካታ ማስመዝገብ ተችሏል። የከተማ አስተዳደራችን የህዝብ ተሳትፍንና ቴክኖልጂን መሰረት
+7
በመሶብ የአንድ ማዕከል ዲጅታል የመንግስት አግልግሎት ፈጣንና ተደራሽ አገልግሎት በመስጠት 99.6% የተገልጋይ እርካታ ማስመዝገብ ተችሏል። የከተማ አስተዳደራችን የህዝብ ተሳትፍንና ቴክኖልጂን መሰረት ያደረገ ቀልጣፋ አስተዳደር በመዘርጋት፣ የነዋሪዎቿን ሁለንተናዊና ፍትሃዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በበጀት ዓመቱ አንደኛ ሩብ ዓመት ጠንካራ የተቋም ግንባታን ቁልፍ ስራ አድርጎ በመስራት ውጤቶች ተመዝግበዋል፡፡ የአገልግሎት ጥራት እና ተደራሽነታቸው እየተመዘነ አገልግልት በሚበዛባቸው ተቋማት ላይ የሪፍርም ስራ ተተግብሯል። በዚህም ስራና ሰራተኛን በማገናኘት፣ በአገልግሎትት አሰጣጡ ላይ ቀጣይነት ያለው ለውጥ እየተመዘገበ ይገኛል። ተገልጋዮችም በአገልግሎት አሰጣጡ ላይ ቀጥተኛ ተሳትፍና ባለቤትነት እንዲኖራቸው በተዘረጋው አሰራር ሌብነትንና ብልሹ አሰራርን በመቀነስ ግልጽነትና ተጠያቂነትን የሚያሰፍን መሠረት ተጥሏል። የስታንዳርዳይዜሽን ትግበራ በ78 ተቋማት ላይ ክትትል እና ደጋፍ በማድረግ በተገኙ ክፍተቶች ሊይ በግብረ-መልስ እየታረመ ይገኛል፡፡ የአዲስ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ዋና መስሪያ ቤቱን ጨምሮ በ11 ክፍለ ከተሞች ቀልጣፋ አገልግሎት እየተሰጠ ይገኛል። በመሶብ የአንድ ማዕከል እስካሁን ለአንድ ሚሊዮን ተገልጋዮች ፈጣንና ተደራሽ አገልግሎት በመስጠት 99.6% ከፍተኛ የተገልጋይ እርካታ ማስመዝገብ ተችሏል። ከዚህ በፊት ዲጅታል ተደርገው የነበሩ 392 አገልግሎቶችን የማጥራት ስራ በመስራት በተገቢ ሁኔታ እየተሰጡ ነው። ወደ አዲስ መሶብ ዲጅታል የአንድ ማዕከል አገልግሎት መስጫ እንዲገቡ 324 አገልግልቶች ተለይተዋል። በሩብ ዓመቱ ወደ አዲስ መሶብ ማዕከለ ገብተው አገልግልት እንዱሰጡ ከተለዩት 30 ዋና አገልግልቶች ሙሉ በሙሉ ወደ ትግበራ እንዱገቡ ተደርጓል።

በኢትዮጵያ የመጀመሪያው የወርቅ ማጣሪያ ፋብሪካ ከአፍሪካ ግዙፍ የውድ ማዕድናት ማጣሪያ ተቋማት አንዱ ለመሆን እና ወርቅ ማጣራትና ተጨማሪ እሴት ለመፍጠር ቀጣናዊ ማዕከል የመሆን ዓላማን ሰንቋል። ‎ ‎🔹 ዓመታዊ አቅም፦ በመጀመሪያው ምዕራፍ ሙሉ አቅሙን ሲይዝ በዓመት ከ600 ቶን በላይ ውድ ማዕድናትን የማጣራት አቅም አለው። ‎🔹 የተገመተ ዓመታዊ እሴት፦ በግምት 80 ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር ገቢ ይኖረዋል። #EthiopiaDelivers #PMOEthiopia #ኢትዮጵያታከናውናለች

በቦሌ ለሚ ልዩ የኢኮኖሚ ቀጣና የተገነባው ብሔራዊ የውድ ማዕድናት ማጣሪያ ፋብሪካ፤ ኢትዮጵያን ብቻ ሳይሆን ሰፊውን የምሥራቅ አፍሪካና አጠቃላይ የአፍሪካ ገበያን የማገልገል አቅም አለው። ‎በአፍሪካ ውስጥ ዓለም አቀፍ ተዓማኒነት ያለው የማጣራትና የፍተሻ አገልግሎት በመስጠት፤ ጎረቤት ሀገራትና በቀጣናው የሚገኙ የማዕድን ኩባንያዎች ወርቃቸውን ከአህጉሪቱ ውጭ መላክ ሳያስፈልጋቸው፤ ለላቀ ማጣራት፣ ለዕውቅና ማረጋገጫ ሰርተፊኬት፣ ለተጨማሪ እሴትና ለሽያጭ ወደ ኢትዮጵያ እንዲያመጡ ያስችላል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በዛሬው ዕለት የሚከተሉትን አመራሮች በሚኒስትር ዴዔታነት ሾመዋል፦
+2
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በዛሬው ዕለት የሚከተሉትን አመራሮች በሚኒስትር ዴዔታነት ሾመዋል፦

ዛሬ የከተማ አስተዳደራችንን የ2019 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ሩብ ዓመት የሥራ አፈጻጸም ግምገማ ጀምረናል። ባለፉት አምስት ዓመታት ከገባነው ቃል በላይ በመፈጸም ያስመዘገብነውን ስኬት መነሻ በማድረግ
+8
ዛሬ የከተማ አስተዳደራችንን የ2019 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ሩብ ዓመት የሥራ አፈጻጸም ግምገማ ጀምረናል። ባለፉት አምስት ዓመታት ከገባነው ቃል በላይ በመፈጸም ያስመዘገብነውን ስኬት መነሻ በማድረግ፣ በቀጣዮቹ አምስት ዓመታት ከበፊቱ የላቀ ዉጤት ለማምጣት የ5አመት እና የ2019 በጀት አመት እቅድ አዘጋጅተንየላቀ ለዉጥ ለማምጣት ተዘጋጅተናል። የሥራችን ስኬት የሚመዘነው በተሠሩ ሥራዎች ብዛት ብቻ አይደለም። ዋናው መመዘኛ የሕዝባችንን የኑሮ ጫና ምን ያህል እያቀለልን ነዉ፣ አገልግሎቶችን ምን ያህል አሻሽለናል፣ ለወደፊትስ የሚቀጥል ምን ዓይነት ተቋማዊ አቅም ገንብተናል የሚለው ነው። የመደመር መንግስት እንደ መሆናችን የተቋማትን፣ የሀብቶችንና የእውቀትን አቅም በማቀናጀት፣ የዛሬን ውጤት ወደ ነገ አቅም፣ የዛሬን ስኬት ወደ ዘላቂ ብሔራዊ ብቃት እየቀየርን የጋራ ሀገር ግንባታ ላይ ትኩረት አድርገን እንሰራለን። አዲስ አበባ ለኢትዮጵያ ከተሞች ምሳሌ፣ ከዓለም ከተሞች ጋር ተወዳዳሪና ለሕዝቧ የተሻለ ኑሮ የምታረጋግጥ ከተማ መሆን አለባት። ይህንንም የምናረጋግጠው በተቀናጀ አመራር፣ በጠንካራ ተቋማትና በሰዉ ተኮር አፈጻጸም ነው። የዛሬ ሥራችን የነገ አቅማችን ነው፤ የዛሬ ውጤታችን የነገ የኢትዮዽያ ሥልጣኔ መሠረት ነው! ፈጣሪ ኢትዮጵያንና ሕዝቦቿን ይባርክ! ከንቲባ አዳነች አቤቤ

የናይጄሪያ ምክትል ፕሬዝዳንት ካሺም ሺቲማ የአዲስ አበባ ከተማ የቀዳማይ ልጅነት ፕሮግራም ልምድ ልውውጥ ላይ ያስተላለፉት መልዕክት

በቦሌ ለሚ ልዩ የኢኮኖሚ ቀጣና የብሔራዊ የውድ ማዕድናት ማጣሪያ ፋብሪካ መመረቅ በኢትዮጵያ የኢንዱስትሪ ልማት ርዕይ ውስጥ ትልቅ ምዕራፍ ነው። ‎ ‎በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ እና በሳም ፕ
+9
በቦሌ ለሚ ልዩ የኢኮኖሚ ቀጣና የብሔራዊ የውድ ማዕድናት ማጣሪያ ፋብሪካ መመረቅ በኢትዮጵያ የኢንዱስትሪ ልማት ርዕይ ውስጥ ትልቅ ምዕራፍ ነው። ‎ ‎በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ እና በሳም ፕሬሺየስ ሜታልስ ዓለም አቀፍ ኢንቨስትመንት አጋርነት የተቋቋመው ይህ ማጣሪያ ፋብሪካ፤ የማዕድን ዘርፉን ለማጠናከር እና በሀገር ውስጥ ምርት ላይ እሴት ለመጨመር የተያዘውን ዓላማ ለማሳካት ትልቅ እመርታ ነው። ‎የማዕድን ዘርፍ ለኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ቅድሚያ የሚሰጠው አምራች ዘርፍ ሲሆን፤ በተለይም ወርቅ ከፍተኛ ውጤት እያስመዘገበ ይገኛል። ይህ ተነሳሽነት የሀገሪቱን ሀብቶች ከሀገር ውስጥ ማቀነባበሪያ፣ ከኢንዱስትሪ አቅም እና ዘላቂ እሴት ፈጠራ ጋር ለማስተሳሰር የመደመር መንግሥት ያለውን ቁርጠኝነት ያሳያል። ‎ ‎ፋብሪካው ሙሉ በሙሉ ወደ ሥራ ሲገባ በዓመት ከ600 ቶን በላይ ውድ ማዕድናትን የማጣራት አቅም ያለው ሲሆን፤ የወርቅ ጥራትን ለመለካት፣ ለማንጠር እና ለውጭ ገበያ ዝግጁ ወደሆኑ ንጹህ ወርቆች ለመቀየር፣ እንዲሁም በተለያዩ የጥራት ደረጃዎች የተሰናዱ የወርቅና የብር ጡቦች ለማምረት ታስቦ የተገነባ ነው። ‎ ‎ማጣሪያ ፋብሪካው በውድ ማዕድናት ማጣራትና ማምረት ረገድ ኢትዮጵያን የቀጣናው ማዕከል ለማድረግ መሠረት የሚጥል ሲሆን፤ የወርቅ ዋጋ አተማመን ላይ ግልጽነትን፣ የጥራት ማረጋገጫን እና እምነትን ያሳድጋል። በተጨማሪም የኢትዮጵያን የተፈጥሮ ሀብት ወደ ላቀ የሀገር ውስጥ እሴት፣ ጠንካራ የኢንዱስትሪ አቅም እንዲሁም በቀጣናዊ እና በዓለም አቀፍ ገበያዎች ሰፊ ዕድሎችን ለመፍጠር የሚረዳ ስትራቴጂካዊ እርምጃ ነው። ‎ ‎ብሔራዊ የውድ ማዕድናት ማጣሪያ ፋብሪካ ግልጽ የሆነ ትልቅ ርዕይ ያነገበ ነው፤ ይህም ጥሬ ማዕድናትን ዝም ብሎ ከመቆፈር https://www.facebook.com/share/p/1bSpyGnorc/