ch
Feedback
WENDE TUTORIAL

WENDE TUTORIAL

前往频道在 Telegram

For any Promotion dm 👉👉 @wende161721 👉History for Grade 12, New curriculum grade 12 history, grade 12 Geography, Grade 12 Economics in Amharic on Youtube

显示更多

📈 Telegram 频道 WENDE TUTORIAL 的分析概览

频道 WENDE TUTORIAL (@wendetutorial) 阿姆哈拉语 语言赛道中的 是活跃参与者。目前社区聚集了 11 892 名订阅者,在 教育 类别中位列第 16 659,并在 埃塞俄比亚 地区排名第 2 836 位。

📊 受众指标与增长动态

自 невідомо 创建以来,项目保持高速增长,吸引了 11 892 名订阅者。

根据 28 九月, 2026 的最新数据,频道保持稳定运转。过去 30 天订阅人数变化为 -190,过去 24 小时变化为 -5,整体触达仍然可观。

  • 认证状态: 未认证
  • 互动率 (ER): 平均受众互动率为 2.04%。内容发布后 24 小时内通常能获得 2.04% 的反应,占订阅者总量。
  • 帖子覆盖: 每篇帖子平均可获得 242 次浏览,首日通常累积 243 次浏览。
  • 互动与反馈: 受众积极参与,单帖平均反应数为 2。

📝 描述与内容策略

作者将该频道定位为表达主观观点的平台:
“For any Promotion dm 👉👉 @wende161721 👉History for Grade 12, New curriculum grade 12 history, grade 12 Geography, Grade 12 Economics in Amharic on Youtube”

凭借高频更新(最新数据采集于 29 九月, 2026),频道始终保持新鲜度与高覆盖。分析显示受众积极互动,使其成为 教育 类别中的关键影响点。

11 892
订阅者
-524 小时
+27 天
-19030 天
帖子存档
@WENDETUTORIAL #ሰው ብዙ ይላል ስላንተ ምንም ሊባል ይችላል፣ ማንም ምንም ሊል ይችላል። የሰዎች ስም ማውጣትና ስላንተ ተግባር ደጋግሞ ማውራት የሚያሳስብህ ከሆነ አንድም የሚያወሩብህን ሰዎች ተከታትለህ አፋቸውን አዘጋ አሊያም አንተ የምታደርገውን አቁም። እነዚህ ሁለቱም እርምጃዎች ትርፍ እንደሌላቸው ደግሞ ጠንቅቀህ ታውቃለህ። ስንቱን አፉን ታዘጋለህ? እስከመቼስ ለሚያወሩብህና የማይሆን ስም ለሚለጥፉብህ ሰዎች ብለህ እራስህን ትገድባለህ? አንድ ነገር አስታውስ ማንም ሰው ያላንተ ፍቃድ አናትህ ላይ መውጣት አይችልም፤ ማንም ሰው ያላንተ ይሁንታ ከግብህ ሊያቆምህ፣ አላማህን ሊያስትህ አይችልም። ያንተ ተሽሎ መገኘት፣ ያንተ እራስህን መሆን፣ ያንተ በእራስህ ቀለም መድመቅ፣ መፍካት፣ መዋብ ሊያስቀናው፣ ሊያበሳጨው፣ ሊያናድደው ይችላል፤ እርሱ ግን ያንተ ችግር ያንተ ጉዳይ አይደለም። ሰው የፈለገውን ማየት ይችላል፤ በመረጠው መንገድ መጓዝ ይችላል፤ ያሰኘውን መናገር ይችላል። ችሎታውን ለክፉና መጥፎ ነገር ከተጠቀመውም ነፃ ፍቃዱ ነውና ምንም ማድረግ አይቻልም። ሰው ብዙ ይላል! በተለይ ደግሞ የሚቀናብህ፣ ያንተን ቦታ አብዝቶ የሚመኝ ነገር ግን አንተ የምታደርገውን ለማድረግ፣ ያለህበት ስፍራ ለመገኘት ያልቻለ ሰው ስላንተ ከማውራት አያርፍም። ብዙ አስተያየት መስጫ ሰጥኖችን ተመልከት ስድብ፣ ነቀፋ፣ ጥላቻ፣ ትቺት ይበዛባቸዋል። በሚያስገርም ሁኔታ የነዚህ ስድብና ነቀፋ አስተያየት ሰጪዎች በህይወታቸው ምንም ጠብ የሚል ነገር ማድረግ ያልቻሉ፣ ማንነታቸውን ያልተረዱ፣ በውስጣቸው ያለው እምቅ ሃይል ያልገባቸው ምስኪን ሰዎች ናቸው። የሚሰሩ ሰዎች ላይ የጥላቻ ቃል በመወርወር፣ መንገዳቸው ላይ እንቅፋት በማስቀመጥ፣ እየተከተሉ በስድብ በማከናነብ የእነርሱ ህይወት የሚቀየር ይመስላቸዋል፤ ማንም ከእነርሱ በልጦና ተሽሎ እንዲገኝ አይፈልጉም። እነርሱም መሔድና ረጅም ርቀት መጓዝ እየቻሉ የሚሔደውን ጎትተው ለማስቀረት ይጥራሉ። ማለት የሚፈልግ ያሰኘውን ይላል፤ የሚናገርም ይናገራል። ነገር ግን አለም የተቀየረችው በሚናገሩት ሳይሆን በሚያደርጉት ሰዎች ነው። የሚዘልፍ፣ የሚተች፣ የሚያጠለሽ፣ የሚሳደብ ሰው ሁሉ የሚችለውን ብቻ ማድረግ ቢችል አለም በብዙ እጥፍ ባደገችና በተመነደገች ነበር። ማንም እቅድህን አያውቅም፣ ቀጣይ እርምጃህ አይገባውም። ስታደርገው ብቻ ማወቅ የሚገባው ከለ በተግባር አሳየው። ከተግባርህ ምላስህን አታስቀድም። ስንቱ ሊጠልፍህ በመንገድ እንደሚጠብቅህ አስተውል። ያለምክንያት፣ ያለምንም ትርፍ፣ አንድ አይነት ሆኖ የወረደን ህይወት ለመኖር ብቻ ሰው ለሰው አይተኛም። አንተም ለእራስህ ብለህ አትተኛና። ብዙ የሚቃወሙህ ቢኖሩም ጥቂት የሚደግፉህ፣ በሒደትም የሚበዙ፣ የሚያበረቱህ ሰዎች አሉና በእራስህ ተስፋ እንዳትቆርጥ። የተባለው ይባል አንተም የምታደርገውን አድርግ፤ የሚገባህ ስፍራ ተገኝ፤ በሚመጥንህ ፍጥነት ተጓዝ፤ ግብህን ምታ፤ ህልምህን ያዝ። 🥳ALL IN ONE🥰 🏆WENDE TUTORIAL  ይለያል 🥇❤️

ጆሴፍ ስታሊን ፈላጭ ቆረጭ የሆነ ከእራሱ ሀሳብ ዉጭ የማይሰማ ጨካኝ መሪ ነበር ይላሉ ። የኮሚኒስትን ፓሊስ በሚቀርፀዉ ኮሚቴ (politeburo) ስብሰባ ላይ በህይወት ያለችን ዶሮ ይዞ ወደ ስብሰባ
ጆሴፍ ስታሊን ፈላጭ ቆረጭ የሆነ ከእራሱ ሀሳብ ዉጭ የማይሰማ ጨካኝ መሪ ነበር ይላሉ ። የኮሚኒስትን ፓሊስ በሚቀርፀዉ ኮሚቴ (politeburo) ስብሰባ ላይ በህይወት ያለችን ዶሮ ይዞ ወደ ስብሰባ ይገባል።በተሰብሳቢዎቹ ፊት በመቆም  ሙሉ በሙሉ ቆዳዎ እስከሚታይ ድረስና ደም በደም እስክትሆን ድረስ የዶሮዎን ላባ በጨካኔ ይነቃቅለዋል።ዶሮዎም በስቃይ ውስጥ ሆና ብትጮህም፣ስታሊን ከምንም ነገር ሳይቆጥር አንድም ላባ ሳይቀር ባዶ እስክትሆን ድረስ ይነቃቅለዋል።ላባዎንም ነቅሎ ከጨረሰ በኋላ ከኪሱ ጥሬ በማዉጣት ለዶሮዋ ይሰጣታል።ሚስኪኗ ዶሮም በስቃይም ዉስጥ ሆና ስታሊን እየተከተለች፣ እግሩ ስር የበተነላትን ጥሬ መለቃቀም ጀመረች። ሰታሊንም ወደ ተሰበሰበዉ የፓለቲካ አመራር አየተመለከተ "ይቺ ዶሮ ህዝቡን ነዉ የምትወክለዉ።ህዝቡን ልትደበድቡት፣ልታሰቃዩት፣ሀይሉን ልታሳጡት ይገባል።ይህን ካደረጋችሁ በኋላ ፣ኪሳችሁ ገብታችሁ የሚበላዉን ነገር ትወረዉሩለታላችሁ።ያኔ ይህ ህዝብ በምትሄዱበት ሁሉ ይከተላችኋል፣ያመልካችኋል።መጨቆኑን ረስቶ ለዘላለም ጀግና ያደርጋችኋል።"በማለት ነበር  ታዳሚያን የተናገረዉ። @WENDETUTORIAL

Who Invented Exams ? Henry Fischel, an American educator of the late 19th century, is credited with inventing formal exams. H
Who Invented Exams ? Henry Fischel, an American educator of the late 19th century, is credited with inventing formal exams. He was the first to bring structured testing in order to systematically evaluate the students' knowledge. However, this concept finds its deeper roots in history. The first ever known examination system was the Imperial Examination in ancient China, initiated during the Sui Dynasty, from 581 to 618 CE. It had been devised to pick out government officials based on merit, mainly through rigorous written tests on Confucian texts. Fischel's work modernized this concept, creating a framework that standardized exams today use around the world. Though exams remain the painful part of education, they still are an important method of knowledge assessment and help develop other critical skills, such as time management and problem-solving. @WENDETUTORIAL @WENDETUTORIAL

@WENDETUTORIAL "ጽናት!!!...በዓለም ላይ የጽናትን ቦታ የሚተካ ምንም ነገር የለም። ብቃትም  አይደለም።  እንደውም ብቃት ያላቸው ስኬታማ እንዳልሆኑ ብዙ ቁጥር ያለው የለም።  የረቀቀ ዕውቀትም አይደለም እንደውም ሰዎች እንደማወቃቸው ስኬታማ አለመሆናቸው ቢታይ አስገራሚ   ትዕይንት ነው። መማርም አይደለም። ዓለማችን በተማሩና በማይሰሩ ሰዎች የተሞለች ናት። ጽናትና ቁርጠኝነት ግን ሁሉንም ነገሮች ናቸው።የአላማ ፅናት ያለቸው ሰዎች ከየትኛውም ቦታ ተነስተው  ያሰቡት ቦታ ለመድረስ ሊያቆማቸው የሚችል ነገር የለም።"                          - ካልቬን ኮሌጅ "እያንዳንዱ ታላላቅ  የስኬት ታሪክ የትልልቅ ውድቀቶች ውጤት ነው ። ልዩነቱ ተሸናፊዎች በወደቁበት ተኝተው ሲቀሩ አሸናፊዎች ግን ከያንዳንዱ ውድቀታቸው በኀላ ዳግመኛ በታላቅ ብርታት መነሳተቸው ነው"                          -ፊዮዶር ዶስቶቭስኪ 🥳ALL IN ONE🥰 🏆WENDE TUTORIAL  ይለያል 🥇❤️

@WENDETUTORIAL #ህመሙን ተቀበሉት! ፨፨፨፨////////፨፨፨፨ የትኛውም ውሳኔ የራሱ ተመጣጣኝ ዋጋ አለው፤ የትኛውም ተግባር የራሱ ግብረመልስ፣ የራሱ ውጤት አለው። ለውሳኔያችሁ መታመን፣ ተግባራችሁን እስከመጨረሻው ማስኬድ፣ ጥረታችሁንም መቀጠል አምናችሁ መቀበል ላለባችሁ ህመም ያጋልጣችኋል። ህመሙን እንደ ጥፋት፣ ስቃዩንም እንደ ቅጣት የምትመለከቱ ከሆነ ግን ዳግም አዲስ ውሳኔ መወሰንና እንደገና አዲስ ተግባር የመሞከር ድፍረት እያጣችሁ ትመጣላችሁ። የምትችሉት አንድ ነገር ነው፦ ጥፋቱን ሳይሆን ህመሙን መቀበል፣ ውጣውረዱን እንደ ቅጣት ሳይሆነ ነገ ውጤት ሊያመጣ እንደሚችል ግበዓት መውሰድ። የሞከራችሁት ነገር በሙሉ ባልተሳካ ቁጥር እራሳችሁን ጥፋተኛ ማድረግ ተነሳሽነታችሁን እየገደለ፣ አቅማችሁን እያሳነሰና ዋጋ እያሳጣችሁ እንደሚመጣ አስተውሉ። አዎ! ጥፋቱን ተውት ህመሙን ተቀበሉት! የሚያሳድጋችሁን ህመም፣ የሚቀይራችሁን ህመም፣ ደረጃችሁን የሚጨምረውን ህመም ተቀሉት። ሃሳባችሁ ትልቅ ሲሆን ህመማችሁም ትልቅ ይሆናል፣ ተግባራችሁ ፈታኝ ሲሆን ጥረታችሁና ድካማችሁም እንዲሁ ፈታኝ ይሆናል። በጥረታችሁ መሃል የምታጠፉትን ጥፋት፣ የሚያጋጥማችሁን ውድቀት፣ የሚደርስባችሁን ጫና፣ የምታጡትን ሰውና የምትከስሩትን ገንዘብ እንደመማሪያ እንጂ እንደ ሌላ የስጋት ምንጭ አትውሰዱት። ምንጊዜም የጥፋተኝነት ስሜት እስረኛ ያደርጋችኋል፤ በስህተታችሁ በተፀፀታችሁ ቁጥር ወደፊት መጓዝ ያቅታችኋል፣ ሃሳባችሁ እንዲሁ ያስፈራችኋል፣ ምኞታችሁ ከንቱ ሆኖ ይቀራል፣ የራሳችሁ እንቅፋት እራሳችሁ ትሆናላችሁ፣ ሳታውቁት ለዘመናት በተመሳሳይ አስተሳሰብ ተመሳሳይ ስፍራ እራሳችሁን ታገኙታላችሁ። አዎ! ጀግናዬ..! ጥፋቱ እንደጥፋት፣ ስህተቱም እንደስህተት ይቀመጥ፣ ይልቅ ከጥፋቱ ቦሃላ ከደረሰብህ ህመም፣ ከስህተቱ ቦሃላ ካጋጠመህ ስቃይ በሚገባ ተማር። ትሞክራለህ ትሳሳታለህ፣ አዲስ ነገር ትጀምራለህ ታጠፋለህ፣ ነገር ግን በሂደቱ ውስጥ መማር ከቻልክ ነገሮች ሁሉ የማይቀየሩበት ምክንያት አይኖርም። በህመም ውስጥ ተምሮ መውጣት፣ በስቃይ መሃል እራስን ፈልጎ ማግኘት መቻል የትልቁ አላማህ አካል መሆን ይኖርበታል። ስቃይ የመኖር እጣፋንታ ነው፣ ህመም የህይወት አንድ አካል ነው። ነገር ግን ለምን እየተሰቃየህ ነው? ለምን ብለህ እየታመምክ፣ ዋጋ እየከፈልክ ነው? የሰዎችን ኢምፓየር ለመገንባት ወይስ የእራስህን ለመመስረት፣ ሰዎችን ለማበልፀግ ወይስ እራስህን ከእስር ነፃ ለማውጣት? ምክንያትህን በሚገባ እወቀው፣ ባወከው ልክ ለላቀቀው ህመም እራስህን አዘጋጅ፣ ሁሌም ከርሱ ተማር፣ እራስህንም አብቃበት። 🥳ALL IN ONE🥰 🏆WENDE TUTORIAL  ይለያል 🥇❤️

@WENDETUTORIAL #አይንህን ግለጥ ወደኋላ ዞረህ እራስህን ስትመለከት ምን ይታይሃል? ብዙ ርቀት ወደፊት ተጉዘሃል ወይስ እዛው አካባቢ በቅርብ ርቀት ነህ? ሃሳቦችህን በሚገባ አሳክተሃል ወይስ ከነጭራሹ ትተሃቸዋል? አምስት አመታትን ወደኋላ ስትቆጥር የነበሩ ችግሮችህ ዛሬም አሉ ይሆን? ያኔ ሲያስጨንቁህ የነበሩ ጉዳዮችስ ከምን ደረሱ? በጊዜ ፍጥነት ነገሮች በቶሉ ይቀያየራሉ። የሆነ ጊዜ እራስን ማወቅ፤ እራስ ላይ መስራት፣ እራስን ማዳን፤ ከእራስ በላይ ለሰዎች መኖር የሚባለውን ነገር አናውቀውም ነበር። ዛሬ ግን ህይወት በእራሷ በተግባር እያስተማረችን ነው። ዝም ብሎ በዘፈቀድ መኖር፣ ያለምንም እቅድና አላማ ምድር ላይ መመላለስ ህይወትን የባሰ ከባድና ውስብስብ እንደሚያደረግው እራሷ ህይወት በሚገባ አስረድታናለች። አይንህን ግለጥ፤ በአፅንዖት መመልከት ጀምር፤ እራስህን በሚገባ መርምር። ከአመታት በፊት የነበርክበት ስፍራ ነህ ወይስ እየተጓዝክ ነው? ዛሬም ባለፉት አመታት ችግሮችህ ተከበሃል ወይስ ከእንቅስቃሴህ ጋር ከተቀየሩ አዳዲስ ችግሮችህ ጋር ነህ? የት ነበርክ? የትስ አለህ? ምን ይዘሃል? ከምንስ ደርሰሃል? እድሜ እስከጨመረ ድረስ የፊት ገፅታ፣ የሰውነት አቋምና ድምፅ መቀየሩ አይቀርም። ዋናው ቁብነገር ግን እርሱ አይደለም። በግል ስብዕና፣ በአመለካከት፣ በአስተሳሰብ ልኬት፣ በማስተዋል ችሎታ እራስህ ላይ የተመለከትከው ለውጥና እድገት ምንድነው? ምናልባት በቻልከው መጠን ትጥር ይሆናል፤ ብዙ ስራ እየሰራህ፣ ብዙ ወዳጆችህን አፍርተህም ይሆናል። ሂደቱ ካልሰራህ ግን እራስህ ቆም ብለህ ማሰብ ይጠበቅብሃል። ምንም ቢሆን አንተን የማይቀይር፣ እሴት የማይጨምርብህ፣ ዋጋህን ከፍ የማያደርግ፣ ካለህበት ቦታ ፈቀቅ የማያደርግህ ጥረት ምንም ትርጉም የለውም። ከፍጥነቷ የተነሳ ህይወትን ትናንት ብለን ዛሬ ለማለት ጊዜ ልናጣ እንችላለን፤ ያለምንም ቁብነገርና አለማ የሚደረግ ሩጫ ደግሞ ጠዓም እያሳጣት በብዙ እጥፍ ያሳጥራታል። የመኖርህን ትርጉም ለመረዳት ጊዜ አታጥፋ፤ አይንህን በቶሎ ግለጥ፤ እርሱን ለማወቅ ማድረግ የሚጠበቅብህን ሁሉ አድርግ። በዚህ ጉዳይ ቀጠሮ ሰጠህ ማለት ህይወትህን ሙሉ፣ ትርፋማ፣ አስደሳችና በእግዚአብሔር የተወደደ ለማድረግ እያቅማማህ እንደሆነ እወቅ። ህይወትህን መቀየር እንደምትችል፣ የተሻለ ስፍራ ማድረስ እንደምትችል ማወቅህ ብቻ በቂ አይደለምና ውስጥህ የሚመላለሰውን ግሩም ሃሳብ በመተግበር በመግለፅ እውቀትህን ተግባራዊ አድርገው። 🥳ALL IN ONE🥰 🏆WENDE TUTORIAL  ይለያል 🥇❤️

ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለጌታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል በሰላም እና በጤና አደረሳችሁ!🙏🙏 መልካም የገና በዓል❤️
ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለጌታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል በሰላም እና በጤና አደረሳችሁ!🙏🙏 መልካም የገና በዓል❤️

ቪድዮ ፦ በዱለቻ ወረዳ ዶፋን ተራራ ላይ የእሳተ ገሞራ ፍንዳታ ተከሰተ። ሰሞኑን የመሬት መንቀጥቀጥ ሲስተዋልባቸው ከነበሩት አካባቢዎች አንዱ በሆነው ዱለቻ ወረዳ ዶፋን ተራራ ላይ ዛሬ የእሳተ ገሞራ ፍንዳታ ተከስቷል፡፡ ይህን ተከትሎም በአካባቢው ነዋሪዎች ላይ ጉዳት እንዳይደርስ ርብርብ እየተደረገ መሆኑን በአፋር ክልል የጋቢ ረሱ ዞን ዋና አሥተዳዳሪ አብዱ ዓሊ ተናግረዋል። በዚሁ መሠረት " በተቀናጀ ሁኔታ ወደ ጊዜያዊ መጠለያ የማጓጓዝ ሥራ እየተሠራ ነው " ብለዋል፡፡ የመሬት መንቀጥቀጡ አሁንም በተደጋጋሚ መቀጠሉን ጠቅሰው " የእሳተ ገሞራ ፍንዳታ ዛሬ ተከስቷል፤ ንዝረቱም ከሰሞኑ ከፍያለ እና ጠንካራ ነበር " ብለዋል፡፡ መረጃው የፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን (FMC) ነው። @WENDETUTORIAL

@ZOO ብዙዎቻችሁ START ብቻ ነው ያላችሁት ነገር ግን ከላይ እንደነገርኩዋችሁ TASK ገብታችሁ ስሩ የሚሰጣችሁን CLAIM አድርጉ በፎቶ ላይም ያሉትን ታስኮች ጨርሳችሁ ስሩ ነቃ በሉ እንጂ ወገን START ማለታችሁ እኛን ብቻ ነው እሚጠቅመው ። http://t.me/zoo_story_bot/game?startapp=ref6499012001

zoo ላይ 3819 ገብታቹ ውሰዱ 3 Min Only

#ZOO ሰላም ስንቶቻችሁ ናችሁ ስለዚህ Airdrop የምታውቁት አሰራሩ ቀላል የሆነና 29 ቀን ብቻ የቀረው ነው Tap Tap ምንም የለውም እየገባችሁ ብቻ ታስኮቹን መስራት እናም እንስሳትን መግዛት
#ZOO ሰላም ስንቶቻችሁ ናችሁ ስለዚህ Airdrop የምታውቁት አሰራሩ ቀላል የሆነና 29 ቀን ብቻ የቀረው ነው Tap Tap ምንም የለውም እየገባችሁ ብቻ ታስኮቹን መስራት እናም እንስሳትን መግዛት ነው ። ከወር በኋላ መንበሽበሽ ነው ወገን። ፍጠኑ ጀምሩት እና ቶሎ ስሩ 👉http://t.me/zoo_story_bot/game?startapp=ref6499012001

#ZOO ሰላም ስንቶቻችሁ ናችሁ ስለዚህ የምታውቁት አሰራሩ ቀላል የሆነና ቀን ብቻ የቀረው ነው ምንም የለውም እየገባችሁ ብቻ ታስኮቹን መስራት እናም እንስሳትን መግዛት ነው ። ከወር በኋላ መንበሽበሽ ነው ወገን። ፍጠኑ ጀምሩት እና ቶሎ ስሩ 👉http://t.me/zoo_story_bot/game?startapp=ref6649520121

#WENDETUTORIAL ሰላም ተማሪዎች እንዴት ናችሁ CLASS አሪፍ? EXAM እየደረሰ ነው እና ዝግጅት እንዴት እየሄደ ነው❓🤔 ባለፈው እንደነገርናችሁ ቻናላችን 1200 Subscriber ቢደርስም ዋጋ የለሽ ነው የሆነብን ምክንያቱም ኔትዎርካቹ VPN ጋር መገናኘት አለበት። እኛም ቪዲዮ የመስራት ሆነ የተሰሩትን የመልቀቅ አቅማችን ነው የተዳከመው።😔 እውነት የቱቶርያል ቪዲዮ እና የENTRANCE EXAM ጥያቄዎች እንዲቀጥል ከፈለጋችሁ እና ከጠቀማችሁ ቀላል ነገር ነው VPN እያበራችሁ ቪዲዮዎቹን ተመልከቱ።🙌 #WENDETUTORIAL

#M.r Endalew Dereje የልባችሁን ምረጡ እውነት እውነቱን አውሩ፣ ግልፅ ግልፁን አስቀምጡ። አሁን ላይ ተስፋችሁ ማነው? ያኖረኛል ብላችሁ የምታስቡት አካል ማነው? ሁሉነገራችሁን ብታጡ እንኳን ያ አካል አብሯችሁ ስለሆነ ብቻ ሙላትና እረፍት የሚሰማችሁ ማነው? ሰውን ተስፋ የሚያደርግ በርሱም ላይ የሚተማመን እርሱ የተረገመ ይሁን እንዲል መፅሐፍ። ይሔን እንኳን እያወቃችሁ በሰው ተደግፋችኋልን? ይሔን እየሰማችሁም ሰውን ተስፋ አድርጋችኋልን? ለማን ምንያህል ቦታ መስጠት እንዳለባችሁ ካላወቃችሁ መቼም ቢሆን ልባችሁ ሊያርፍ አይችልም። የሚያኖራችሁ ፈጣሪ ሆኖ ሳለ የማያኖራችሁ የሰው ልጅ ላይ አትጣበቁ፤ ብትወድቁ የሚያነሳችሁ፣ ብትሳሳቱ የሚያርማችሁ፣ ብትጠፉም የሚመልሳችሁ እግዚአብሔር ሆኖ ሳለ ሰውን ከልክ በላይ በሰው ወይም ባላችሁ ነገር ላይ አትደገፉ። አፈጣሪ ውጪ ሌላው ምድራዊ ነገር ጠፊና አጥፊ ነው። ሲታይ ራሱ የማይጠፋ ይመስላል ነገር ግን ይጠፋል፣ ሲታሰብ ብዙና ሀይለኛ ይመስላል ሲጨበጥ ግን ምንም ነው። ሳይጨልም ንቁ፣ ጊዜው ሳያልፍ ተማሩ። ጨለማ በብረሃለን ይጠፋል፣ ብረሃን ለጨለማ እጁን ይሰጣል። ተፈጥሮ ፈረቃ አላት። ያለምንም ፈረቃ፣ ያለምንም የጊዜ ገደብ፣ ያለምንም እርከን የሚሰራ ግን ፈጣሪ ብቻ ነው። ዓለምን ከጥግ እስከ ጥግ አይታችኋታል፣ ባታዩአትም ስለርሷ ብዙ ሰምታችኋል፣ የምድር ምርጫ ምን አንደሆነ፣ ከእናንተ ምን እንደምትፈልግ፣ ማንስ ደግሞ እንደሚያዋጣችሁ በሚገባ ታውቃላችሁ። የልባችሁን ምረጡ፣ ለሚያሳርፋችሁ ቦታ ስጡ፣ የሚያኖራችሁን አጥብቃችሁ ያዙ። በራሳችሁ ብርታት ብቻ ዛሬ ያላችሁበት ስፍራ አልደረሳችሁም፤ በዙሪያችሁ ባሉ ሰዎች እርዳታ ብቻ አሁን ያገኛችሁትን ነገር አላገኛችሁም። ባፈራችሁት ንብረት ወይም በገነባችሁት ዝና ብቻ ነፃ አልወጣችሁም። አወቃችሁትም አላወቃችሁትም፣ አስተዋላችሁትም አላስተዋላችሁትም፣ የሚገባውን ቦታና ክብር ሰጣችሁት አልሰጣችሁትም በእያንዳንዱ ጥቃቅን እርምጃዎቻችሁ ውስጥ ፈጣሪ ነበረ፣ ዋናው የእርሱ ስራ ነበረ። ብትረሳ ብትረሳ እስከዛሬ ያኖረህን፣ እዚህ ያደረሰህን፣ ብዙ ብዙ ነገር ያሳለፈህን የእርሱን የፈጣሪህን ውለታ እንዳትረሳ። በሁለት እግር ቆሞ መሔድ ትልቅ ፀጋ ነው፣ በራስ ፍላጎት ወደ ብዙ አቅጣጫ መንቀሳቀስ ስጦታ ነው፣ ሌላው ቢቀር ለማማረርና የጎደለውን ነገር ለመጠየቅ እንኳን መመረጥ ያስፈልጋል። የትናንት ከባድ አስጨናቂ ጊዜ እስኪያልፍ ረጅም ነበር ሲያልፍ ግን ምንም ነው። ለሰውም ይሁን ለሰዎች ውለታቢስ አትሁን፣ አምላክህንም የምትፈልገውን ለመጠየቅ አትፈር። ከላይ ከላይ ሳይሆን  የውስጥህን አውጥተህ ፈጣሪህን ጠይቅ። ሀሳብ ይዘህ አትተኛ፣ ራስህን እያስጨነክም ህይወትህን ለመግፋት አትሞክር። ልብህ አይደንግጥ፣ ውስጥህም አይረበሽ። ህይወት ብለህ የምትኖረውን ኑሮ በአምላክህ ፍቃድና በራስህ መንገድ ለመኖር ራስህን አሳምን። መልካም አዳር ቤተሰብ🥱 🙋‍♂ 🥳ALL IN ONE🥰 🏆WENDE TUTORIAL  ይለያል 🥇❤️ @WENDETUTORIAL @WENDETUTORIAL

Selam temariwoch YOUTUBE lay videowochun sitiketatelu VPN eyaberachu lemayet mokiru legna sitilu bicha sayihon videowoch hulunim enditagegnu ena private yehonutinim old new video lemagignet VPN eyaberachu tetekemu

19 እንኳን ለ ቅዱስ ገብርኤል አመታዊ ክብረ በዓል በሰላም አደረሳችሁ። @WENDETUTORIAL
19 እንኳን ለ ቅዱስ ገብርኤል አመታዊ ክብረ በዓል በሰላም አደረሳችሁ። @WENDETUTORIAL

#WENDETUTORIAL Grade 12 Students who wants to learn in Private tutorial join this group👉🏻👉🏻 https://t.me/+J5l4PkenG2g0ODZk please students who didn't want private class don't join the group.

LuCky gems የሰራቹትን በየሳምንቱ Withdraw ማረግ ትችላላችሁ ትኩረት ሰታቹ ከሰራቹት እስከ 200$ ድረስ በቀላሉ ትሰራላቹ በዚ ሰዐት ትክክለኛ ቶሎ  ከፋይ airdrop  ነው። ቴሌግራም ላይ ገንዘብ አጊቶ ማያቅ በሙሉ መስራት በቀላሉ መስራት ይችላል አዲስ ባሻሻሉት ህግ 1$ ብሰሩም ማውጣት ትችላላችሁ። እውነት ያልሆነ ነገር በፍፁም ለናንተ አናቀርብም 🤝🤝 ለመጀመር 👇👇 https://t.me/lucky_gems_official_bot/app?startapp=2E5gtWMbAaP9aed7a5N1bQTGeD2s2KBXxS7pdAvgF6dQvEP

Selam temariwoch YOUTUBE lay videowochun sitiketatelu VPN eyaberachu lemayet mokiru legna sitilu bicha sayihon videowoch hulunim enditagegnu ena private yehonutinim old new video lemagignet VPN eyaberachu tetekemu

🔥Grade 12 HISTORY Chapter 7 Part 1 AFRICA SINCE 1960'S; THE ROAD TO INDEPENDENCY AND AFRICAN POLITICS AFTER INDEPENDENCE🔥⚡️ 👆🏻👆🏻The video is posted on Our Channel on Youtube and go to the channel by using the above link, enjoy it.👏🏼👏🏼 🏆WENDE TUTORIAL ይለያል❤️ @WENDETUTORIAL