452
订阅者
无数据24 小时
无数据7 天
无数据30 天
吸引订阅者
十二月 '24
十二月 '24
+11
在0个频道中
十一月 '24
+26
在0个频道中
Get PRO
十月 '24
+12
在0个频道中
Get PRO
九月 '240
在0个频道中
Get PRO
八月 '240
在0个频道中
Get PRO
七月 '240
在0个频道中
Get PRO
六月 '240
在0个频道中
Get PRO
五月 '240
在0个频道中
Get PRO
四月 '240
在0个频道中
Get PRO
三月 '240
在0个频道中
Get PRO
二月 '240
在0个频道中
Get PRO
一月 '24
+2
在0个频道中
Get PRO
十二月 '23
+9
在0个频道中
Get PRO
十一月 '23
+12
在1个频道中
Get PRO
十月 '23
+2
在0个频道中
Get PRO
九月 '23
+16
在0个频道中
Get PRO
八月 '23
+12
在0个频道中
Get PRO
七月 '23
+1
在0个频道中
Get PRO
六月 '23
+11
在0个频道中
Get PRO
五月 '23
+30
在0个频道中
Get PRO
四月 '23
+53
在0个频道中
Get PRO
三月 '23
+106
在0个频道中
Get PRO
二月 '23
+22
在0个频道中
Get PRO
一月 '23
+65
在0个频道中
Get PRO
十二月 '22
+92
在0个频道中
Get PRO
十一月 '22
+54
在0个频道中
Get PRO
十月 '22
+110
在0个频道中
Get PRO
九月 '22
+203
在0个频道中
| 日期 | 订阅者增长 | 提及 | 频道 | |
| 21 十二月 | 0 | |||
| 20 十二月 | 0 | |||
| 19 十二月 | +1 | |||
| 18 十二月 | +1 | |||
| 17 十二月 | 0 | |||
| 16 十二月 | 0 | |||
| 15 十二月 | 0 | |||
| 14 十二月 | +1 | |||
| 13 十二月 | 0 | |||
| 12 十二月 | 0 | |||
| 11 十二月 | +2 | |||
| 10 十二月 | 0 | |||
| 09 十二月 | 0 | |||
| 08 十二月 | 0 | |||
| 07 十二月 | +2 | |||
| 06 十二月 | +1 | |||
| 05 十二月 | 0 | |||
| 04 十二月 | +2 | |||
| 03 十二月 | 0 | |||
| 02 十二月 | +1 | |||
| 01 十二月 | 0 |
频道帖子
------የመጥረቢያ ወግ-----
አምላክ ቀጥቃጩ
ብረት አቅላጩ
ጨፍጭፎ ሰራን
በ ስለት ኳለን።
በእንጨት እጀታ አቅም ለገሰን።
አለመታደል
እኔን እጫካ እንዲሆን ሜዳ
ጓዴን ልኳንዳ
ላከን።
ህይወት እንዲ ናት አብሮ ተፈጥሮ አንዱ ሰማይ አንዱ ምድር።ብቻ ግን እስቲ በርቱ!!
| 2 | ቄሱ በለሊት ቅዳሴ ሊገቡ ይጣደፋሉ። ጨልሟል።በጭለማው ውስጥ የሚታየው የቄሱ ትልቅ ጥምጣም እና ነጭ ኩታ ነው።ወደ ቤተክርስቲያኑ ሊደርሱ ጥቂት ርቀት ሲቀራቸው....አንተ!ቁም! የሚል ከ ትእዛዝነቱ ይልቅ ንቀቱ ያየለ ድምፅ ሰሙ።ከማንም እንዲህ አይነት ለጠብ የተጋበዘ ትእዛዝ ሰምተው ስለማያውቁ ትእዛዙ ለእርሳቸው መሆኑ አጠራጠራቸው።ሆኖም በዛ ደረቅ ለሊት ከሳቸው ውጭ ማንም እንደሌለ እርግጥ በመሆኑ ግራ ተጋብተው ቆሙ።ወዲያው መሳሪያ ሲቀባበል ተሰማ።ቄሱ በጥንቃቄ እጃቸውን ወደ ደረት ኪሳቸው ሰደዱ።"አርፈህ ቁም!"ድምፁ አሁንም አንባረቀ። ባለድምፁ ሰው ተጠጋቸው ወጣት ነው።"ምነው ልጄ አባትህ አልሆ..."አላስጨረሳቸውም። ዝምበል።አላቸው።አንቱታውን የነፈጋቸው ሰው ለሌላም እንደማይመለስ ስላሰቡ አሁንም እጃቸውን ወደ ደረት ኪሳቸው ሰደዱ።"አርፈህ ቁም ብዬሀለው"አስጠነቃቀቸው።ያቀባበለውን መሣሪያ አስጠግቶ በአፈ ሙዙ ጎረበጣቸው።እጃቸውን በድጋሚ ወደ ደረት ኪሳቸው ሰደዱ እና እኔን ባታከብር ቆቤን አታከብርም ልጄ ሲሉት ዝጋ ለቆብ ለቆብማ ሚስማርም ቆብ አለው አለ እና የ ጠብመንጃውን ምላጭ ሳበው። ቄሱ አቃስተው ወደቁ።ቆባቸው እዚ እሳቸው እዛዛ።ለምን ተኮስክበት አለ አንድ አዲስ ድምፅ።አታየውም እንዴ ከኪሱ አውጥቶ እኮ ሊቀድመን ነበር ብሎ የቄሱን ደረት ኪስ ውስጥ ያለውን እጃቸውን ስቦ አወጣው።እጃቸው የእንጨት መስቀል አጥብቆ እንደያዘ ነበር.....
ምን ለማለት ፈልጌ ነው የሀይማኖት አባት አትግደሉ!!!
@dawitview
@addemiinilik
ዳዊት ጌታቸው | 107 |
| 3 | ዠንበሬ ያልኩሽ
ለ ውድቅት ነፍሴ
ተስፋዬ ሆነሽ
ለእውር አይኔ
ጮራ ፈንጥቀሽ
አይደለም እቴ!!!
አንቺን ተግቼ ዠንበር ማለቴ
እግዜር ሲያሳየኝ
መጥለቅሽ ገብቶኝ
ነው!!!!
ዠንበር=በድሮው የአነጋገር ዘይቤ ጀንበርን ይወክላል
@addemiinilik | 109 |
| 4 | የእለት እንጀራ ጉርሷ ቢጨንቃት
ሄደች ተራምዳኝ ወደ ሚበጃት
ምን ለይ ልትዘራው
በምን እንዲፀድቅ
ከ እኔ ከ አፈሩ ወደደች መራቅ?????
@dawitview
ዳዊት ጌታቸው
@addemiinilik | 128 |
| 5 | ------------ብሩክ ጣት---------
ከ ጠጉሬ ለይ ገለባ አንስታ
ብትን ጠጉሬን ብትሰበስበው
ሸራፋ ልቤን በጎነት ሞላው።
ሳትነካኝ በፊት ሳትደባብሰኝ
ሳይደርስ ያንጀቴ
ይሻክር ነበር የጥጥ ጃኬቴ።
በጎ ትንፋሿን እፍ ብትለኝ
እንኳንስ ዜማ ጥሩንባ ሳበኝ
---__----___-----እሮሮ ጣመኝ።
ሳታየኝ በፊት ካይኗ ሳልገባ
ጨረቃም ፉንጋ ፀሀይም ሽባ
ነበሩ ለኔ!!
---@dawitview--
ዳዊት ጌታቸው
---@addemiinilik-- | 130 |
| 6 | ውድ አንባቢ ሆይ እስራኤልን እንደ boyfriend ፓለስታይንን እንደ girlfriend እንግሊዝ እና ፈረንሳይ የ ፍቅረኛሞቹን መጣላት እንደ እድል ተጠቅመው ፓለስታይንን ለማስረገዝ ለማስረገዝ ባይሆንም የ ልጥጢቱን ፓለስታይን ሀብት ለመውረስ እንደተዘጋጁ አጉል አሳቢ ነን ባይ እና ሲከፋሽ አለን ባዮች ወንድ የgirlfriend best friend እንደሆኑ አስቡ።
እንግዲህ እኚ ጥንዶች ሁሌ እንደሚደባደቡ ባል እና ሚስት አርጋችሁ አስቧቸው።ጥላቸው አደባባይ የዋለ።ስድድባቸውን ሰፈር ሰምቶ የሳቀባቸው አይነት።
part1 | 125 |
| 7 | ብሩክ ይሁን የተባለ ባለንጀራዬ የዛሬ 3 አመት ጥር 1 ቀን "ምፅአተ እስራኤል"የሚል መጥሀፍ በ ስጦታ ሸጠልኝ😂። የሆነው ሆኖ ከ 3 አመት በሗላ እስራኤል የቀለጠ ጦርነት ውስጥ ገባች።ተዛሬ ነገ ይረግባል ሲባል እስራኤል protien powder እንደጠጣ ጀማሪ ስፖርተኛ ተደባድባ(ደብድባ)ሊወጣላት አልቻለም።ምናልባት የዚህ ሁሉ እሰጥአገባ ምክንያት እዚ መጥሀፍ ለይ ካለ ብዬ መፈለግ ጀመርኩ።መጥሀፉን exodus በሚል ርእስ leon yoris ፅፎት እንደነበር ተርጓሚው ማሞ ውድነህ ያትታል።ዋናው ታሪክ ሳይጀምር በፊት እንደ መቅድም የተቀመጠውን ፅሁፍ ብነግራችሁ ብዙ ነገር ታውቁበታላችሁ እኔም እንደ ቀልድ ጀምሬው ቀልቤን ስለያዘው ነው።ግና ፖለታካ እና ዳቦ በደረቁ ደስ ስለማይሉ ይህንን politics በ አርቲስቲክ ብሩሽ ነካክቼ አቀርበዋለው ትንሽ ብቻ ታገሱኝ ወገን!!! | 113 |
| 8 | -----እሰይ ነጋ/ለምን ነጋ?----_
መሽቷል አትሂድ ያለችኝ ግዜ
በፈጣሪ አመንኩ
"እዚ ጋር ተኛ እኔ እጠጋለው"!
ለመቁረብ አሰብኩ።
"በረደኝ እኮ ትንሽ ተጠጋ!"
ጧፍ አስገባለው ስወርድ ከ አልጋ!!
ብዬ አምኜ አምሮ ምሽቴ
ተምኔው ነጋ ሳይደርስ ያንጀቴ?!
አሁን ሳስበው🤔
እግዜር ሲሰራው...
ምሽቱ አጥሮ ቀኑ ረጅም ነው!!!
እክደው ዘንዳ ምክንያት አገኘው!!!
ካድኩት!!
ለምን አጠረ???
@addemiinilik
@dawitview
ዳዊት ጌታቸው | 136 |
| 9 | አብዛኞቹ መምህራን በአንድ ማሽን የተሰሩ ይመስል በተደጋጋሚ የሚናገሯቸው ሀረጎች ተመሳሳይ ናቸው።ለምሳሌ:- ምሳህን ረስተሀል፣mind is absent body present፣መማር ማይፈልግ ይውጣ(ላያስወጡን ነገር ሆዳችንን ሲያጮሁት እኮ ነው)፣እንዲሁም የመጨረሻው እና እኔ የደረሰብኝ "ለኛም ቀልዱን ንገረን እና አብረን እንሳቅ"የሚለው የ አስተማሪ ዘለፋ ነው።
ነገሩ እንዲህ ነው የምማርበት ክፍል ውስጥ ተቀምጫለው። መምህሬ በከፍተኛ ምስጠት እጃቸውን ለማስረዳት በሚመች መልኩ ቅርፁን እየቀያየሩ ያስረዳሉ። አልሰማዋቸውም!!!! በራሴ ሀሳብ ስዋከብ ቆይቼ ለካ ሳላስበው አለቅጥ ፊቴ በፈገግታ ተሞልቷል። መምህሬ የዚን ግዜ ነው እንግዲህ በተረባቸው ያነቁኝ።ያስፈገገኝን ጉዳይ አጫወትሁዋቸው መምህሬም ሳቁ ተማሪዎቹም ገለፈጠሉኝ ተ ሶስት ቀን በሗላ ግን ተ ትምህርት ቤት ተባረርከሁ።ለካ መምህሌ ሳቁብኝ እንጂ አልሳቁልኝም...ለማንኛውም ያሳቀኝ(ያስባረረኝ ሀሳቤ)ይህ ነው።ተየት መጣ ሳልለው የቴዲ አፍሮ ጎዣም ኑራ ማሬን በአእምሮዬ መዝፈን ለይ ነበርኩ ከዛ አንድ ስንኝ አእምሮዬን ኮረኮረው እሱም "ሳዋህድ ተኖርኩት ቅኔን ተደብተሬ
ተሽሎኝ ተገኘ ባለ አንዲሩ ገብሬ" ይህችን ቃል የሚናገረው አፍቃሪው በዛብህ ነው። በዛብህ በዚህ ሰአት ስር የሰደደ የ ሴት
አልባነት (singleness)ስሜት ተጠቅቶ ነበር።ሰብለንም ለመጠየቅ ድፍረቱ ተገዛ ቁምጣው አጠረው። ሳሰላስለው(interpret)ሳደርገው በዛብህ በንዴት በግኖ መሬቱን በሽመሉ እየተመተመ ገብሬስ አንዲሩን ነፋ እንግዲህ እኔ ምኔን ልን....
ብሎ ሲከፋ በሀሳቤ አይቼው ስቄ ነው የተባረርኩት......
*አንዲር=ዋሽንት የመሰለ የሙዚቃ መሳሪያ*
@dawitview
@addemiinilik
ዳዊት ጌታቸው! | 160 |
| 10 | አብዛኞቹ መምህራን በአንድ ማሽን የተሰሩ ይመስል በተደጋጋሚ የሚናገሯቸው ሀረጎች ተመሳሳይ ናቸው።ለምሳሌ:- ምሳህን ረስተሀል፣mind is absent body present፣መማር ማይፈልግ ይውጣ(ላያስወጡን ነገር ሆዳችንን ሲያጮሁት እኮ ነው)፣እንዲሁም የመጨረሻው እና እኔ የደረሰብኝ "ለኛም ቀልዱን ንገረን እና አብረን እንሳቅ"የሚለው የ አስተማሪ ዘለፋ ነው።
ነገሩ እንዲህ ነው የምማርበት ክፍል ውስጥ ተቀምጫለው። መምህሬ በከፍተኛ ምስጠት እጃቸውን ለማስረዳት በሚመች መልኩ ቅርፁን እየቀያየሩ ያስረዳሉ። አልሰማዋቸውም!!!! በራሴ ሀሳብ ስዋከብ ቆይቼ ለካ ሳላስበው አለቅጥ ፊቴ በፈገግታ ተሞልቷል። መምህሬ የዚን ግዜ ነው እንግዲህ በተረባቸው ያነቁኝ።ያስፈገገኝን ጉዳይ አጫወትሁዋቸው መምህሬም ሳቁ ተማሪዎቹም ገለፈጠሉኝ ተ ሶስት ቀን በሗላ ግን ተ ትምህርት ቤት ተባረርከሁ።ለካ መምህሌ ሳቁብኝ እንጂ አልሳቁልኝም...ለማንኛውም ያሳቀኝ(ያስባረረኝ ሀሳቤ)ይህ ነው።ተየት መጣ ሳልለው የቴዲ አፍሮ ጎዣም ኑራ ማሬን በአእምሮዬ መዝፈን ለይ ነበርኩ ከዛ አንድ ስንኝ አእምሮዬን ኮረኮረው እሱም አፍቃሪው በዛብህ "ሳዋህድ ተኖርኩት ቅኔን ተደብተሬ
ተሽሎኝ ተገኘ ባለ አንዲሩ ገብሬ" የምትለዋ ግጥም ናት።በዛብህ የዚኔ ሴት አልባ(single)ነበር።ሰብለንም ለመጠየቅ ድፍረቱ ተገዛ ቁምጣው አጥሮት ነበር። ሳሰላስለው(interpret)ሳደርገው በዛብህ በንዴት በግኖ መሬቱን በሽመሉ እየተመተመ ገብሬስ አንዲሩን ነፋ እንግዲህ እኔ ምኔን ልን....
ብሎ ሲከፋ በሀሳቤ አይቼው ስቄ ነው የተባረርኩት......
*አንዲር=ዋሽንት የመሰለ የሙዚቃ መሳሪያ*
@dawitview
@addemiinilik
ዳዊት ጌታቸው! | 46 |
| 11 | አብዛኞቹ መምህራን በአንድ ማሽን የተሰሩ ይመስል በተደጋጋሚ የሚናገሯቸው ሀረጎች ተመሳሳይ ናቸው።ለምሳሌ:- ምሳህን ረስተሀል፣mind is absent body present፣መማር ማይፈልግ ይውጣ(ላያስወጡን ነገር ሆዳችንን ሲያጮሁት እኮ ነው)፣እንዲሁም የመጨረሻው እና እኔ የደረሰብኝ "ለኛም ቀልዱን ንገረን እና አብረን እንሳቅ"የሚለው የ አስተማሪ ዘለፋ ነው።
ነገሩ እንዲህ ነው የምማርበት ክፍል ውስጥ ተቀምጫለው። መምህሬ በከፍተኛ ምስጠት እጃቸውን ለማስረዳት በሚመች መልኩ ቅርፁን እየቀያየሩ ያስረዳሉ። አልሰማዋቸውም!!!! በራሴ ሀሳብ ስዋከብ ቆይቼ ለካ ሳላስበው አለቅጥ ፊቴ በፈገግታ ተሞልቷል። መምህሬ የዚን ግዜ ነው እንግዲህ በተረባቸው ያነቁኝ።ያስፈገገኝን ጉዳይ አጫወትሁዋቸው መምህሬም ሳቁ ተማሪዎቹም ገለፈጡልኝ ተ ሶስት ቀን በሗላ ግን ተ ትምህርት ቤት ተባረርከሁ።ለካ መምህሬ ሳቁብኝ እንጂ አልሳቁልኝም...ለማንኛውም ያሳቀኝ(ያስባረረኝ ሀሳቤ)ይህ ነው።ተየት መጣ ሳልለው የቴዲ አፍሮ ጎዣም ኑራ ማሬን በአእምሮዬ መዝፈን ለይ ነበርኩ ከዛ አንድ ስንኝ አእምሮዬን ኮረኮረው እሱም አፍቃሪው በዛብህ "ሳዋህድ ተኖርኩት ቅኔን ተደብተሬ
ተሽሎኝ ተገኘ ባለ አንዲሩ ገብሬ" የምትለዋ ግጥም ናት ሳሰላስለው(interpret)ሳደርገው በዛብህ በንዴት በግኖ መሬቱን በሽመሉ እየተመተመ ገብሬስ አንዲሩን ነፋ እንግዲህ እኔ ምኔን ልን....
ብሎ ሲከፋ በሀሳቤ አይቼው ስቄ ነው የተባረርኩት......
*አንዲር=ዋሽንት የመሰለ የሙዚቃ መሳሪያ*
@dawitview
@addemiinilik
ዳዊት ጌታቸው! | 45 |
| 12 | ❤❤❤ | 208 |
| 13 | ---ponytail ይሻላል----
ጠጉርሽ ርዝመቱ
ተ ማቱሳላ እድሜ
ተ እናቴ አርጬሜ
ወዘና ቅባቱ
እንደ ባለጠጋ
ቅቤ የጠገበ
ተ ዳሌሽ ሲላጋ
እያሉ አሞገሱሽ።
በስተመጨረሻ በዛ እና መካሪ
ብለው አሳመኑሽ ሹሩባ ተሰሪ
አልከፋኝም እኔ ሲያምርብሽ እንደ ሰው
ግና ያ ሹሩባሽ ቅማልን ተመቸው!!!!
ፍቺው በቃ!
@addemiinilik
@dawitview
ዳዊት ጌታቸው | 219 |
| 14 | ዛሬ በ ዊልቼር የሚሄደው ጓደኛዬ ምን ቢል ጥሩ ነው.....ብንሄድ ይሻላል!!😂😂😂
@addemiinilik
@dawitview | 34 |
| 15 | @bewketuseyoum | 1 |
| 16 | -----አንድ አንድ ዜ ደሞ-----
ብርቱ የምላቸው
እድሜ እና ጤናቸው
ሲቀዛቀዝ ከርሞ
አልያም እንደ ችግኝ
ሳየው ተከርክሞ
ተመስገን እላለው አንድ አንድ ዜ ደሞ።
ሁዳዴን ገድፌ
መላእክት ነቅፌ
ቅዳሴ አቋርጬ
ሀይማኖት መርጬ
ደረቴን ነፍቼ ለ ሀጥያትአዛዡ
ሆኜ እያገለገልጉ ሳላይ ከ መዘዙ
ተጠብቄ ስኖር ቢገርመኝ ችሎታው
አንድ አንድ ዜ ደሞ ተመስገን እላለው።
አንድ አንድ ዜ ደሞ
ለጠሀይ መኪና
ለብርዱ ኮት ስጠኝ
ለዛውም ደንዳና
ራስጌው በጠጉር
የተቀመቀመ
ብዬ ፀልይ እና
ታልጋ ሳይነሱ
ደም እያፈሰሱ
ጠሀዩ ናፍቋቸው
ንፋሱ አምሯቸው
አንዲት እፍኝ ጤናን
ሲመኙ ባያቸው
ገባኝ መሰል ህይወት
ፀሎቴ የቅብጠት
እንደነበር!!!
አንድ አንድ ዜ እናመስግን ሁል ግዜ አናማረው!!!
@dawitview
@addemiinilik
ዳዊት ጌታቸው | 233 |
| 17 | ---ዛሬ---
ዛሬ ብላ!
ዛሬ ጀግን!
ዛሬ ጠጣ
ዛሬ ጀንጅን
ዛሬ ቁረብ
ዛሬ አመንዝር
ዛሬ ታመን
ዛሬ ቅጠር
ዛሬ ንደድ
ዛሬ ክሰም
ዛሬ ቀድስ
ዛሬ ስለም
ዛሬ ጠርጥር
ዛሬ ስጋ
ነገ ይሆናል የማይነጋ
.
.
ማን ያውቃል!!!
@dawitview
ዳዊት ጌታቸው
@addemiinilik | 233 |
