LEARN TECH ||ethiopia ®
前往频道在 Telegram
We are dedicated to provide tech tips and other tech related information. #join and #share
显示更多1 495
订阅者
无数据24 小时
-107 天
-5530 天
帖子存档
Repost from የድሮ መፅሐፎች በPDF
የሎጥ መንገድ
ድርሰት - በተክሉ ጥላሁን
ዘውግ - ልብወለድ
የህትመት ዘመን - 2000 ዓ.ም
የገፅ ብዛት - 299
አዘጋጅ - ፍቅርተ 🥰
ይ🀄️ላ🀄️ሉ 👉 @OLDBOOKSPDF
ምርጥ 20 የአልበርት አንስታይን አባባሎች።
1. ‹‹ ሠላምን በጉልበት ማስጠበቅ አይቻልም፡፡ ሠላምን ማስጠበቅ የሚቻለው በመግባባት ብቻ ነው፡፡ ››
2. ‹‹ ስህተት ሠርቶ የማያውቅ ሠው ምንም ነገር ሞክሮ አያውቅም ማለት ነው፡፡ ››
3. ‹‹ ሁሉም ሠው ብሩህ ጭንቅላት አለው፡፡ ነገር ግን አሣን ዛፍ መዝለል አይችልም ብለህ ችሎታውን ካጣጣልከው በህይወትህ ሙሉ አሣ ደደብ እንደሆነ ታስባለህ፡፡ ››
4. ‹‹ ዓይነ ሕሊና ከዕውቀት የላቀ አስፈላጊ ነው፡፡ ››
5. ‹‹ ትምህርት አዕምሯችን የበለጠ እንዲያስብ እንጂ ጥሬ ሃቆችን ለመለማመድ አይደለም፡፡ ››
6. ‹‹ ሙከራህን እስከምታቆም ድረስ በህይወት አትሸነፍም፡፡
››
7. ‹‹ አንድን ነገር በቀላል ቋንቋ መግለፅ ካልቻልክ ነገሩን አልተረዳኸውም ማለት ነው፡፡ ››
8. ‹‹ እብደት ማለት አንድን ነገር በተመሳሳይ ዘዴ ደግሞ ደጋግሞ በመስራት የተለየ ውጤት መጠበቅ ነው፡፡ ››
9. ‹‹ ደስተኛ ሕይወት ለመኖር ከፈለግክ አንተነትህን ከሠዎች ወይም ከነገሮች ጋር ከማወዳደር ይልቅ ከግብህ ወይም ከዓላማህ ጋር ራስህን እሠር፡፡ ››
10. ‹‹ ስኬታማ ለመሆን ከፈለግክ የስኬት ፍላጎትህ እወድቃለሁ ብለህ ከምትፈራው ፍርሃትህ በእጅጉ የበለጠ መሆን አለበት፡፡ ››
11. ‹‹ መቀራረብ በፍቅር ለመውደቅ ዋስትና አይሆንም፡፡ ››
12. ‹‹ ዋጋ ያለህ ሠው ለመሆን ሞክር እንጂ ስኬታማ ብቻ ለመሆን አትሞክር፡፡ ››
13. ‹‹ ምክንያታዊነት ከአንድ ቦታ አንስቶ ወደሌላ ቦታ ሊወስድህ ይችላል፡፡ ዓይነ ሕሊና ግን የትም ይወስድሃል፡፡ ››
14. ‹‹ ጎበዝ ሠው ችግሮችን ይፈታል፡፡ ብልህ ሠው ግን ችግሮቹ መልሠው እንዳይፈጠሩ ያስወግዳቸዋል፡፡ ››
15. ‹‹ ተፈጥሮን በጥልቀት ተመልከት፡፡ ያን ጊዜ ሁሉንም ነገሮች በተሻለ ትረዳለህ፡፡ ››
16. ‹‹ ሴቶች ብዙ ጊዜ የሚጨነቁበት ወንዶች ጨርሠው በረሷቸው ነገሮች ላይ ነው፡ ወንዶችም ብዙ ጊዜ የሚጨነቁበት ጉዳይ ሴቶቹ በማያስታውሷቸው ነገሮች ላይ ነው፡፡ ››
17. ‹‹ ቅዱሱን ጉጉትህን አትጣለው፡፡ ››
18. ‹‹ የአመለካከት ድክመት እየቆየ ሲሄድ የባህሪ ድክመት ይሆናል፡፡ ››
19. ‹‹ ሞትን መፍራት ማለት ተገቢ ባልሆኑ ፍርሃቶች መንቦቅቦቅ ነው፡፡ ምንም ስጋት የሌለበት ሠው ቢኖር የሞተ ሠው ብቻ ነው፡፡ ››
20. ‹‹ ፍፁም የማይመስለውን የሚሞክሩ የማይቻለውን የሚችሉ ናቸው፡፡ ››
የትኛውን አባባል ወደዳቹለት እስኪ ሐሳባቹን አካፍሉን🙏🙏
©Philosophy my interest
@Abyssinianwisdom @Abyssinianwisdom @Abyssinianwisdom @Abyssinianwisdom
#ላሟ’ን_ግደላት !!
(አስተማሪ ታሪክ)
============
👉“ከነፃነቱ በላይ ምቾቱን የሚያስቀድም ሕዝብ ትንሽ ቆይቶ ምቾቱንም ፤ ነፃነቱንም ያጣል። W. Somerset Maugham................
አንድ ቤተሰብ በአንድ ትንሽ መሬት ላይ ራቅ ባለ መንደር ወጣ ብሎ ይኖራል። ቤተሰቡ አንድ ላም አላቸው። ህይዎታቸውን የሚመሩት ከላሟ በሚያገኙት ወተት ነው። ላሟ ትንሽ ወተት ሲኖራት ትንሽ ይበላሉ፤ ብዙ ወተት ሲኖራት ብዙ ይበላሉ፡፡ የእናት፣ የአባትና የልጆች ህይወት በላሟ ወተት ላይ የተመሰረተ ነው።
በአንድ የበልግ ቀን አንድ ብቸኛ መንገደኛ በመንደሩ ቆሟል፤ ተርቧል። ቤተሰቡ ወተታቸውን አጋሩት፡፡ መንገደኛው አመስጋኝ ስለሆነ ውለታውን ለመመለስ እና ቤተሰቡን ለመርዳት ፈለገ ፡፡ ቤተሰቡን እንዴት መርዳት እንዳለበት ግን አያውቅም ነበረ፡፡ በዚህ ጊዜ በመንደሩ ውስጥ አንድ አስተዋይ ሰው እንዳለ ይሰማና ወደ እኚህ አስተዋይ ሰው ቤት ይሄዳል።
“ተርቤ ነበር እና ይህ ቤተሰብ ወተት መገበኝ። ይህን ቤተሰብ መርዳት እፈልጋለሁ ፤ እንዴት መርዳት እችላለሁ? ” ብሎ አስተዋዩን ሰው ጠየቃቸው
እኝህ ብልህ ሰውም “ላሟን ግደላት !” ብለው መለሱለት ።
“ላሟን ግደላት ? ይህ እንዴት ሊረዳቸው ይችላል?” መንገደኛው መልሶ ጠየቀ
ሕይወታቸውን የተንጠለጠለው በዚያች ላም ነው ፤ “ላሟን ግደላት” በማለት አስተዋዩ ሰው ደግመው መለሱለት።
መንገደኛው ይህን ግራ የሚያጋባ ምክር ለመቀበል ፈርቶ ነበር ፤ ነገር ግን የአስተዋዩን ሰው ምክር ተፈጻሚ አደረገና ሄዶ ላሟን ገደለ።
ከአንድ አመት በኋላ መንገደኛው በድጋሚ በመንደሩ አለፈ። አዳዲስ ሱቆችንና የደመቀ ገበያ አስተዋለ። ለገበያ ለመጡ መንገደኞች አልጋ እና ምግብ የሚያቀርብ አዲስ ሆቴል ተመለከተ።
መንገደኛው ወደ ሆቴሉ ገባ። ከቡና ቤቱ ጀርባም የላምዋን ቤተሰብ የበኩር ልጅ አገኘው። ልጁም በፈገግታ እና በደስታ ቆሞ ነበር። መንገደኛውም ሰላምታ ሰጠውና “ ምን ተፈጠረ !?” ሲል ጠየቀው።
ልጁም “ላማችንን አጣን። ወተት አልነበረም። በዚህ ጊዜ ወጥተን የምንበላውን ለማግኘት የሆነ ነገር ማድረግ ነበረብን። ከዛም ትንሽዬ ገበያ ጀመርን ፣ አደገልን። ይህንን ሆቴልም አቋቋምነው፣ ይህም እያደገ ነው። የላማችን ወተት ከሌለ አዳዲስ ነገሮችን መሞከር ነበረብን።
😂በዚህ ጊዜ መንገደኛው አስተዋዩ ሰው የነገሩትን ምክር ጉልበት በዝምታ ተውጦ ማንሰላሰል ጀመረ ፣ "ላሟን ግደላት"
“ከነፃነቱ በላይ ምቾቱን የሚያስቀድም ሕዝብ ትንሽ ቆይቶ ምቾቱንም ፤ ነፃነቱንም ያጣል።
👉ላም’ህ ምንድን ነው? ፤ ላምህን ላይ ላም’ህን ግደል !
@abyssinianwisdom @abyssinianwisdom
When going through a tough time; remind yourself that: It won't last forever. You'll overcome it. You'll become a better person. You will live a better life. Your story will inspire others.
ከባድ ጊዜ ውስጥ ስታልፍ፤ ለዘላለም እንደማይቆይ ለራስህ አስታውስ። ታሸንፈዋለህ። የተሻልክ ሰው ትሆናለህ፡፡ የተሻለ ህይወት ትኖራለህ። ታሪክህ ሌሎችን ያነሳሳል።
For more : Abyssinianwisdom
📚ብዙን ጊዜ ብዕርዎ ስለራዕይ ብዙ ያወሳል።ራዕይ ምንድን ነው?
«ራዕይ ብቻ ነው ሰውን ከእንስሳ የሚለየው። ዛሬ በጨለማ ተውጠህ ነገ ግን ፀሀይ ይወጣል ብለህ መተለም ያለብህ የሩቅ ተስፋ ነው ራዕይ።ዛሬ በሞት ታጥረህ ነገ ግን ትንሳኤ ይኖራል ብለህ ማየት ያለብህ የሩቅ ዕይታ ነው ራዕይ።ወይም ደሞ ዙሪያህን በሀጥያት ተዘፍቀህ ሳለህ በውስጥህ ግን በሰው ልጅ ቅንነት፤ በእግዚአብሔርና በኢትዮጵያ ህያውነትና ዘላለማዊነት ማመን መቻል ነው ራዕይ።»
📰 ጦቢያ መጽሔት(1990)
✍ ሎሬት ባለቅኔ ፀጋዬ ገብረመድህን
For more :@Abyssinianwisdom
ለመላው ሙስሊም የቻናላችን ቤተሰቦች እንኳን ለ1 ሺህ 444ኛው የዒድ አልፈጥር በዓል አደረሳችሁ።
ዒድ-ሙባረክ
@Abyssinianwisdom @Abyssinianwisdom @Abyssinianwisdom
#ከምርጥ_መጽሐፍቶች
“ማንም ሰው በመስጠት ደሀ አይሆንም፡፡”
"ያም ሆነ ይህ ሰዎች ከስር መሰረታቸው መልካሞች ናቸው፡፡ "
#ከአና_ፍራንክ መጽሐፍ የተወሰደ
“አንዳንድ ሰዎች የሰዎችን ከባድ ችግር መቅረፍ ቢችሉም በእነሱ ጥቂት ችግር ይወድቃሉ፡፡”
"በህይወትህ ትልቁ ጠላትህ ውስጥህ ያለው መጥፎ ሀሳብ ነው ስለዚህ መጀመሪያ እሱን ታግለህ አሸንፍ ከዛ ሌላው ቀላል ነው!"
''ለሰዉ የከበደዉ የወደቀን ማንሳት እንጅ የቆመን በርታ ማለት አይደለም፡፡''
#ከውብ መጽሐፍ የተወሰደ
“ሞት ሆይ ....ና እስቲ እቀፈኝ ፤ ድብን አድርገህ እቀፈኝ ወደ ሰማየ ሰማያት እንምጠቅ።”
#ከየጭን_ቁስል መጽሐፍ የተወሰደ
“ቀን ጎድሎብህ ሁሉንም ብታጣ፣ሁሉም ቢከዳህ፣ ሁሉን ነገር እንደ ነበረ መመለስ የሚያስችልህ አንድ ነገር ብቻ አለ፣ በራስ ልቦና ዉስጥ የምትፈጥረዉ የአይበገሬነት እልህ።”
#ከያልታበሱ_እንባዎች" መጽሐፍ የተወሰደ
@Abyssinianwisdom @Abyssinianwisdom @Abyssinianwisdom
Repost from የድሮ መፅሐፎች በPDF
በአለም የታወቁ አጫጭር ልቦለዶች
ድርሰት - በተለያዩ ዕውቅ ደራሲያን
ትርጉም - አምሳሉ አክሊሉ
ይዘት - ልብወለድ ( አጫጭር )
የመጀመሪያ ዕትም - 1981 ዓ.ም
የገፅ ብዛት - 211
ይ🀄️ላ🀄️ሉ 👉 @OLDBOOKSPDF
በዓሉ ግርማ እድር የለውም ፣ እቁብ የለውም ፣ ማኅበረ የለውም። ስለ ነገ አይጨነቅም። “ መስከረም በዓሉ ግርማ ” የነገረችኝም ይህንኑ ነው ፣ 'በዓሉ አሁንን ነው የሚኖረው። እሱ ብቻ ሳይሆን መሪ ወንድ ገፀባሕርያቱ የአሁን ሰው ናቸው። ኦሮማይ ውስጥ የምናነበው ፀጋዬ ኃይለማርያም የሚናገረው ነገር በዓሉን የሚገልጸው ሆኖ አግኝቼዋለሁ።
✍ እንዳለጌታ ከበደ
📍ስለ ሕይወት እቅድ የለኝም ከመኖር ሌላ:: የሕይወት ግቡ እራሱ መኖር ነው::
ይህችም ውድ የሆነች ትንሽ ቁራሽ ሕይወት እንደአብርሃም ቤት የለኝ፣ እንደሙሴም መቃብሬ ሳይታወቅ መኖር፣ መጻፍ ፣ ሕይወትን በተስፋ ወደፊት እየኖርኩና ወደኋላም እያስተዋልኩ ስለ ኑሮ ቀርቶ ስለምጽፈው ልብወለድም ቢሆን እቅድ አላወጣም።
📖ደራሲው
📍« ስለሞት አስቤ አላውቅም። የሙያዬ ባህርይ ፣ ያለምንም ሥጋትና ጭንቀት በማያቋርጥ አሁን ሁኔታ ውስጥ የመኖር ልማድ አሳድሮብኛል። ስለ ወደፊቱ ለምን ይታሰባል ?” ትኩስ ዜና ፣ ትኩስ ሕይወት ! ሞት ለእኔ ምኔም አልነበረም ፣ ሆንም አያውቅም። ትኩስ ዜና ከማጣት ፣ አበቦችን ካለማየትና የቆንጆ ሴት እጅን ለመንካት ካለመቻል የበለጠ ስቃይና መለየት ምን ይኖራል ?” ሞት ትርጉም ሰጥቶኝ አያውቅም . . . እውን ነገር አሁን ብቻ ነው። አሁን አለሁ ፣ ደህና ነኝ ፣ እተነፍሳለሁ ፣ ውብ ኮከቦች እቆጥራለሁ ፣ ይበቃል።
📖 ኦሮማይ
✍በዓሉ ግርማ
ውብ ቀን❤️
@Abyssinianwisdom @Abyssinianwisdom @Abyssinianwisdom
☯እውነተኛ ሠላም
💟ንጉሱ በትክክል ሠላምን ሊወክል የሚችል ስዕል መሳል ለቻለ አርቲስት(የስዕል ሙያተኛ) ወሳኝ የሆነ ሽልማት ለመስጠት ተዘጋጅቶ አሳወጀ፡፡ ብዙ የስዕል ሙያተኞችም ሙከራ አደረጉ፡፡ ነግር ግን ንጉሱ የቀረቡትን ስዕሎች ሲመለከት ሁለት ስዕሎችን ብቻ ወደደ፡፡ ንጉሱ ቀልቡ ካረፈባቸው ሁለት ስዕሎች አንዱን መምረጥ የተዘጋጀውን ሽልማት መስጠት ነበረበት፡፡
☮አንደኛው ስዕል ፀጥ ያለ ባሕርን የሚወክል ስዕል ነው፡፡ አሳሳሉም ባሕሩ በዙሪያው ያሉትን የተራራ ማማዎች እንደ መስታውት አንጸባርቆ ለተመልካች ቅርብ ያደርጋል፡፡ አናቱ ላይም በነጭ ደመና ተሸፍኖ ሰማዩ አርብቦበታል፡፡
☯ይህን ስዕል የተመለከተ ማናቸውም ሰው እውነተኛ የሠላም ምልክት አድርጎ ሊወስደው የሚችል የአሳሳልጥበብ ያረፈበት ነው፡፡
ሌላኛው ስዕል እንዲሁ የተራራ ስዕል ሲሆን በተራራው ላይ የሚታየው የተራቆተና ያገጠጠ አለት በላዩ ላይም ቁጣ የሚነበብብት ሰማይ የዝባብ እንባውን ሊያንጠባጥ በብልጭታ ጥፊ እየተመታ ይታያል፡፡ በተራራው ጎንም የሚያጓራ ፏፏቴ ይታይበታል፡፡ ስዕሉን ላየ ጨርሶ የሠላም ስሜት የማይፈጥር ስዕል ነበር፡፡ ነገር ግን ንጉሱ ተጠግተው በአንክሮ ሲመለከቱት በፏፏቴው መውረጃ ጀርባ በተሰነጠቀው አለት ላይ ትንሽየ ቁጥቋጦ በቁጥቋጦው ላይ ደግሞ ወፏ ጎጆዋን ቀልሳ ተመለከቱ፡፡ በዛ በተናወጠው የፏፏቴ ድምጽ መሃል ወፏ በፍጹም ሠላም ተቀምጣለች፡፡
የትኛው ስዕል የአሸናፊነት ሽልማቱን የሚወስድ ይመስላችኋል? ንጉሱ የመረጡት ስዕል ሁለተኛው ስዕል ነበር፡፡
☯ ለምን እንደመረጡት ንጉሱ ሲያብራሩ “ሠላም ማለት ምንም አይነት ድምጽ በማይሰማበት፣ ሁከትና ጫጫታ በሌለበት ስፍራ መሆን ማለት አይደለም፡፡ ሠላም ማለት ያለነው በግር ግር መሃል ቢሆንም ፀጥ ያለ ልብ ሲኖረን ሠላም አለን ማለት ነው፡፡ እሱ ነው እውነተኛና ፍፁም ሠለም፡፡” አሉ፡፡ መጽሐፉም የሠላም መጓደልን ሲያጠይቅ አፋቸው ዝም ብሏል በልባቸው ግን ብርቱ ሰልፍ አለባቸው እንዳለው፡፡ ውስጣችን ሠላም ሲያጣ በሆነ ባልሆነው መበሳጨት እንጀምራለን፡፡ እንዲሁም ደግሞ በተቃራኒው ያለው እውነት ነው፡፡
Source: Wisdom pearls “The Real Meaning of Peace”
✍ምስጋናው ግሸን
☮☯☮☯☮☯☮☯☮☯
❤️❤️❤️
@Abyssinianwisdom @Abyssinianwisdom @Abyssinianwisdom
የቱ ነው ሰው ማለት
በውስጡ እያደባ በአፉ የሚጫወት
እኔን ግራ ገባኝ የቱ ነው ሰው ማለት?
ወይስ እያበላህ ዞር ብሉ የሚያማህ
ዛሬ የኔ ነው ስትል ነገ የሚከዳህ
ጓደኛ ስትለው የሚሆንህ ጠላት
እስቲ እንነጋገር የቱ ነው ሰው ማለት?
እኔ አንዳንድ ጊዜ ጓደኛዬ እልና
የሆዴን በሙሉ ዘክዝኬ እነግርና
መፍትሔ ስጠብቅ ለነገርኩት ሚስጥር
ሲወራ እሰማለሁ ጉዳዬ ከመንደር።
እኔም ጓደኛዬን ምነው እባክህ ብለው
ችግሬን አዳምጠህ መፍትሔ ሳትሰጠው
ምን በደልኩህና ለአገር ነዛኽው?
ብዬ ብጠይቀው ብሎ መለሰልኝ ለአንድ ሰው ብቻ ነው።
ሚስጥር ከሁለት ሰው ካለፈ ጨዋታው
ነገር መባከኑን እንደምን አጣኽው?
መፍትሔ ሳይሰጥህሚስጥር የሚያወጣው
የጓደኝነት እምነት መለኪያ ምንድነው?
ለጥያቄዬ መልስ ሃሣብ እፈልጋለሁ።
እናንተም ንገሩኝ ሰው ማለት የቱነው ሰው ያለሰው መኖር እንደማይችል አውቀህ ሰው ሆይ ለጓደኛህ ታማኝ ሁን እባክህ።
#ህልምና ስኬት ከሚለው የገጣሚ ሙሉመቤት ገብረዮሐንስ የግጥም መጽሐፍ ላይ የተወሰደ...
@Abyssinianwisdom @Abyssinianwisdom @Abyssinianwisdom
የትችት ጠንቅ!
አንድ ጊዜ ታዋቂው ሳይንቲስተት አልበርት አይንስታይን (Albert Einstein) በክፍል ውስጥ ባለው ሰሌዳ ላይ የሚከተሉትን ስሌቶች እየጻፈ ለተማሪዎቹ እያሳየ ነበር፡-
(9 X 1 = 9) . . . (9 X 2 = 18) . . . (9 X 3 = 27) . . . (9 X 4 = 36) . . . (9 X 5 = 45) . . . (9 X 6 = 54) . . . (9 X 7 = 63) . . . (9 X 8 = 72) . . . (9 X 9 = 81) . . . (9 X 10 = 91)
ከእነዚህ የሂሳብ የድምር ስሌቶች ሁሉም ትክክል ሆነው ሳለ ለመጨረሻው የሰጠው መልስ 90 መሆን ሲገባው 91 በመሆኑ እንደተሳሳተ የተመለከቱ ተማሪዎቹ በጣም ሳቁበት፡፡ “ይህንን የመሰለ ሊቅ እንዴት ይሳሳታል” ነበር የሳቁ መነሻ፡፡
እሱም ሳቃቸውን እስከሚጨርሱ ጠበቀና፣ “የመጀመሪያዎቹን ዘጠኙን ጥያቄዎች በትክክል መመለሴን በማንሳት ማንም ተማሪ አላደነቀኝም፡፡ ነገር ግን አንዷን ስለተሳሳትኩኝ ብቻ ሁላችሁም ሳቃችሁብኝ፡፡ ይህ ማለት ምንም እንኳ በአብዛኛው ነገር ስኬታማ ብትሆኑም ሕብረተሰቡ አንዷንና አናሳዋን ስህተት የማጉላትና የማሾፍ ዝንባሌ አለው፡፡
ለማስተላለፍ የፈለገው መልእክት፡- “አናሳ አመለካከት ያላቸው ሰዎች ትችት ትልቁን ሕልማችሁን ከመከተል አይከልክላችሁ”፡፡
ቀና በሉ! አልሙ! ተንቀሳቀሱ! ስሩ! ስትሳሳቱ እንደገና ሞክሩ! በሰዎች ትችት አትታሰሩ!
#Dr_Eyob
@Abyssinianwisdom @Abyssinianwisdom @Abyssinianwisdom
#ትንሳኤ
እንኳን አደረሳችሁ !
ውድ የክርስትና እምነት ተከታይ በሙሉ እንኳን ለትንሳኤ በዓል አደረሳችሁ ፤ አደረሰን።
በዓሉ የሰላም ፣ የደስታ ፣ የፍቅር ፣ የመተሳሰብ ይሆን ዘንድ እንመኛለን።
በዓሉን ስናከብር ፤ የተቸገሩ ወገኖቻንን አለንላችሁ በማለት ፣ የወደቁትን በማንሳት ፣ በሀዘን ላይ ያሉ ወገኖችን በማፅናናት፣ ከክፉ ድርጊትና ሀሳብ ርቀን ሊሆን ይገባል።
🎉መልካም በዓል።
5.ለነገ አትበል ዛሬን በሙላት ኑር
እያንዳንዱ ቀናቶች ለሰው ልጅ የሚሰጡት የራሳቸው ውበት ፣ ጥንካሬ ብሎም ድክመት ያለ ሲሆን ዛሬ ላይ የኖርነውን አሁን ነገ ላይ ፈፅሞ አናገኘውም ምክንያቱም ነገ ሌላ ቀን ነውና። ዛሬ የማይደገም ውድ ጊዜ መሆኑን ተረድተን ዛሬን በትምህርትም ሆነ በስራ ህይወታችን ብሎም ባለን ግንኙነት ልንኖረው በሚገባ ልክ ልንኖር ይገባናል። ዛሬን ልንሮጥ በሚገባን ልክ እንሩጥ መራመድ ባለብን ልክ እንራመድ መሥራት ባለብን ልክ እንሥራ ምክንያቱም በነገ ውስጥ ዛሬ ላይ መሮጥ መራመድ ብሎም መሥራት በምንችለው ልክ ላንሮጥ ላንራመድ ብሎም ላንሰራ እንችላለንና።
ይቀጥላል.........
@Abyssinianwisdom @Abyssinianwisdom @Abyssinianwisdom
ደብዳቤው
በአንድ ጦርነት ላይ ከከሞተ ወጣት የደረት ኪስ ውስጥ የተገኘው ደብዳቤ እንዲህ ይነበባል
«የኔ ወዳጅ «እንደገና እኩለ ሌሊት መጣ። እናም ከሚፈሰው ዕንባዬ በስተቀር መፅናኛ የለኝም። ከአሰቃቂዎቹ የጦርነት መዳፎች መካከል ሾልከህ ወደ እኔ ስለመመለስህ ያለኝ ተስፋ እንዳይሟጠጥ አድርጎ የሚያፅናናኝም ምንም ነገር የለም፡፡ በሄድክ ጊዜ የተናገርካቸውን ቃላት ልረሳቸው አልችልም፡፡ እያንዳንዱ ሰው በአንድ ወቅት የሚመልሳቸው የዕንባ ብድሮች አሉት» ነበር ያልከው?
«ወዳጄ ሆይ! ምን እንደምል አላውቅም፡፡ ሆኖም በመለያየት የተጎዳችው፣ ግን ደግሞ ለስቃይ ደስታን እንዲሁም ለሀዘን ተድላን በሚሰጥ ፍቅር የተፅናናችው ነፍሴ ራሷን በብራና ውስጥ ተድላን አንቆረቆረችው፡፡ ፍቅር ልባችንን ሲያጣምረው እና ሁለቱ ልቦቻችን በሀያሉ እግዚኣብሄር እስትንፋስ የሚዋሃዱበትን ቀን ስንናፍቅ ጦርነት በአስፈሪ ጩኸቷ ተጣራች። አንተም መሪዎቹ በጣሉብህ ግዴታ ተገፋፍተህ ተከተልካት"
«ሴቶችን ጋለሞቶች፣ ህፃናትን ደግሞ የሙት ልጆች አድርጎ ፍቅረኞችን የነጣጠላው ይህ ግዴታ ምንድን ነው? ጦርነቶችን ቀስቅሶ ግዛቶችን በከንቱ ያጠፋው ይህ የሀገር ፍቅር ምንድን ነው? ደግሞስ ከአንዷ ህይወት ጋር ሲነፃፀር የበለጠ ተራ ሊሆን የሚችለው ምንድን ነው? በአታላይ ፖለቲከኞች ዘንድ ከምንም የማይቆጠሩትን ምስኪን መንደርተኞችን ለጨቋኞቻቸው ሃያልነት ሲሉ እንዲሞቱ የሚጋብዛቸው ግዴታ ምንድን ነው? ግዴታ በህዝቦች መካከል ያለውን ሰላም ካጠፋ እንዲሁም የሀገር ፍቅር የሰውን ህይወት መረጋጋት ከበጠበጠ የሀገር ፍቅር ምንድነው??
«ተወው ወዳጄ ሆይ! ተወው! ዝም ብዬ ነው። ለቃላቶቼ ትኩረት አትስጥ! ጀግናና ለሀገርህ የምትታመን ሁን፡፡ ... በፍቅር ታውራ በስንብት እና ብቸኝነት ውስጥ የጠፋችውን ልጃገረድ ወሬም አትስማ፡፡በዚህኛው ህይውት ፍቅር ለእኔ ሲል በህይወት ካልመለሰህ እንግዲያውስ በእርግጠኝነት ፍቅር በመጪው ህይወት ያገናኘናል።ለዘለአለም ያንተው»
#ካህሊል_ጂብራን
@Abyssinianwisdom @Abyssinianwisdom @Abyssinianwisdom
አወይ የሷ ነገር አወይ የሷ ስቅለት፤
በደል ሳይገኝባት ምግባር ሳይጎልባት፤
ተገርፋ በጥፊ ተመታ ላታሳልፍበት፤
መስቀሏ ላይነሳ ደንድኖ ሲሳናት፤
ቀራንዮን ስትመኝ ልታርፍ በስቅላት፤
ከወዴት ትሄዳለች? ጵላጦስ ሄሮደስ ሳይሆንባት ተርት።
በር ያለበት ከሁሉ ቤተ መንግስት ሆኖ፤
ሄሮደስ ጵላጦስ በየበሩ ሞልቶ፤
እዝኛዉን ስትጨር ወደዝያኛው ተብሎ፣
ማለቂያ ያለው ዕለተ አርብ ጠፍቶ፤
ወዴት ትመጣለች ? ፍርድ ቤቱ በዝቶ።
አይዞሽ ትደሪሽያለሽ ታርፍያለሽ ተሰቅለሽ፤
ዳግም ላትቀምሽ የችንካሩን ጣእም ትቀምሽያለሽ ወደሽ፤
ቀራኒዮን በእምባ ጎልጎታን በዋይታ ትደርሽያለሽ መተሽ፤
ምጥሽ የከበደሽ ኢትዮጵያ እናቴ ይዞ የሚመጣ ያን ትንሳኤሽ ፤
ስቅለትሽ ይቅረብሽ እላለሁኝ እኔ።
@Abyssinianwisdom @Abyssinianwisdom @Abyssinianwisdom
Repost from የድሮ መፅሐፎች በPDF
ፍቅር እስከ መቃብር
ደራሲ - ክቡር ዶ.ር ሀዲስ አለማየሁ
ዘውግ - ልብ ወለድ
የህትመት ዘመን - 1957
የገፅ ብዛት - 556
የሀገራችን ስነ ፅሁፍ Masterpiece የሆነውን ታላቅ ልብወለድ ፍቅር እስከመቃብርን እነሆ
ይ🀄️ላ🀄️ሉ @OLDBOOKSPDF
ጥበብ 🇪🇹ዘአቢሲንያ🇪🇹
📚 @abyssinianwisdom 📚
በ1993 በኢኮኖሚክስ የኖቤል ሽልማት አሸናፊው አሜሪካዊው ኢኮኖሚስት ዳግላስ ስሜን እንዲህ ይላል።
<<ሀገር እያደገች ነው ወይስ አይደለም የሚለውን ለማወቅ ከፈለጋችሁ ኢንደስትሪዎቿንና ፋብሪካዎቿን አትመልከቱ።እነዚህ በቀላሉ ሊገዙ ወይም ሊሰረቁ ወይም ሊገለበጡ ይችላሉ። ይልቁኑ የአገሪቱን የወደፊት ሁኔታ ለመተንበይ ወደ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ሂዱ። እዚያ ልጆችን እንዴት እንደሚያስተምሩ ተመልከቱ።ልጆቻችሁን ጠያቂ ፣ፈጣሪ ፣ታጋሽ፣ ዲሲፕሊን፣ አደጋን መቀበል፣ መነጋገር እና መስተጋብራዊ እንዲሆኑ እየረዷቸው ከሆነ እና የጋራ ተሳትፎ እና የቡድን ትብብር መንፈስ ካላቸው በርግጥም ሀገሪቱ ዘላቂና ሰፊ ደረጃ ላይ ለመድረስ ጥቂት እርምጃዎች እንደሚቀሯት እርግጠኛ መሆን ትችላላችሁ>>
@abyssinianwisdom @abyssinianwisdom @abyssinianwisdom
