925
订阅者
无数据24 小时
无数据7 天
+930 天
帖子存档
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ለ2018 በጀት ዓመት 43 ቢሊየን 252ሚሊየን 509ሺ 909 ብር አጸደቀ
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ለ2018 በጀት ዓመት 43 ቢሊየን 252 ሚሊየን 509ሺ 909 ብር አጸደቀ
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 6ኛ ዙር 4ኛ ዓመት የስራ ዘመን 4ኛ መደበኛ ጉባኤ በሁለተኛ ቀን ውሎው የክልሉን መንግስት የ2018 በጀት ተወያይቶ አጽድቋል።
በክልሉ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የፕላን፣ መሠረተ ልማትና የመንግስት ሀብት ቁጥጥር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ ታመነ ገብሬ ለምክር ቤቱ የ2018 በጀት ዓመት ረቂቅ የበጀት አዋጅ አቅርበዋል።
በጀቱ ለክልል ማዕከል መስሪያ ቤቶች መደበኛ እና የካፒታል ወጪ፣ለዞኖችና ለልዩ ወረዳዎች ጥቅል በጀት፣ለክልላዊ ፕሮግራሞች፣ለዘላቂ የልማት ግቦች ማስፈጸሚያ፣ለክልሉ መጠባበቂያ መሆኑን ነው አቶ ታመነ በረቂቅ አዋጁ የጠቆሙት።
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ፋይናንስ ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ዘይቱና ኢብራሂም የ2018 በጀት አስመልክቶ ለምክርቤቱ በዝርዝር አቅርበዋል።
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ለ2018 የቀረበውን በጀት በሙሉ ድምጽ አጽድቋል።
ሐምሌ 16/2017 ዓ.ም
በጉራጌ ዞን ገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ የወጣቶችን ሁለንተናዊ ተሳትፎና ተጠቃሚነታቸውን ማረጋገጥ እንደሚገባ ተገለፀ።
፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨
ይህ የተገለፀው የወረዳው የስራ እድል ፈጠራ እና ኢንተርፕራይዝ ልማት ምክር ቤት የ2017 ዓ.ም አፈጻጸም እና የ2018 ዓ.ም እቅድ አስመልክቶ የንቅናቄ መድረክ ዛሬ ባካሄደበት ወቅት ነው።
በዚህ ወቅትም የፅህፈት ቤቱ ኃላፊ አቶ ጅላሉ ወራቄ የ2017 ዓ.ም አፈፃፀም እና የ2018 ዓ.ም ዝርዝር ዕቅድ ያቀረቡ ሲሆን በ2017 የስራ ዘመን 6 ሺህ 50 ወጣቶችን ለመለየት ታቅዶ 5 ሺህ 954 ወጣቶች መለየታቸዉን ገልፀዋል።
ከስራ ስምሪት አንፃር ለ5 ሺህ 625 ወጣቶች የስራ ዕድል ለመፍጠር ታቅዶ ለ5 ሺህ 734 ዜጎች የስራ ዕድል በመፍጠር አፈፃፀሙን መቶ በመቶ ማሳካት ስለመቻሉ ያነሱት ኃላፊዉ በቋሚ ለ2 ሺህ 890 ወንድ ለ1 ሺህ 635 ሴት በድምሩ ለ4 ሺህ 525 ስራ ፈላጊዎች ስራ ለመፍጠር ታቅዶ ለ2 ሺህ 987 ወንድ እና ለ1005 ሴት በድምሩ ለ3 ሺህ 992 ወጣቶች ቋሚ የስራ ዕድል ስለመፈጠሩ ያወሱት አቶ ጅላሉ በጊዜያዊ ለ707 ወንድ እና ለ3 መቶ 93 ሴት በጠቅላላው ለ1 ሺህ 100 ዜጎች ስራ ለመፍጠር በማቀድ ለ1 ሺህ 408 ወንድ እና ለ 334 ሴት በድምሩ ለ1 ሺህ 742 ወጣቶች ጊዜያዊ ስራ ዕድል ተፈጥሯል ብለዋል።
በበጀት ዓመቱ 5 ሚሊዮን 790 ሺህ 450 ብር ለማስቆጠብ ታቅዶ 6 ሚሊዮን 703 ሺህ 755 ብር በማስቆጠብ አፈፃፀሙን ከመቶ ፐርሰንት በላይ ማሳካት ተችሏል ያሉት ኃላፊው በበጀት ዓመቱ 9 ሚሊዮን 945 ሺህ 938 ብር ብድር ገንዘብ ለማሰራጨት ታቅዶ ወደ ስራ መገባቱን ጠቅሰው 7 ሚሊዮን 224 ሺህ 10 ብር በማሰራጨት አፈፃፀሙን 72 በመቶ ማሳካት ተችሏልም ብለዋል።
በተያያዘም 7 ሚሊዮን 32 ሺህ 484 ብር ለማስመለስ በማቀድ 7 ሚሊዮን 408 ሺህ 981 ብር የተመለሰ ሲሆን አፈፃፀሙም ከበጀት ዓመቱ ዕቅድ አንፃር ከመቶ ፐርሰንት በላይ ነው ብለዋል።
አክለውም በቀጣዩ የ2018 ዓ.ም የስራ ዘመን በገጠር ስራ ዕድል ፈጠራ መስክ ለ3 ሺህ 413 ዜጎች እና በከተማ መስክ ለ1 ሺህ 911 ወጣቶች የስራ ዕድል ለመፍጠር አቅዶ እየተሠራ ስለመሆኑ ከቀረበው እቅድ ለመረዳት ተችሏል።
የቀረበውን ሪፖርት መነሻ በማድረግ ጥልቀት ያለው ውይይትና ምክክር በማድረግ የጋራ መግባባት ላይ ተደርሶ የተለያዩ የቀጣይ አቅጣጫዎች ተቀምጧል።
የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሚፍታ ሁሴን ተሳታፊዎች ላነሷቸዉ ሃሳብና አስተያየቶች ምላሽና ማብራሪያ በሰጡበት ወቅት ወጣቶችን ሙሉ በሙሉ አሟጦ ወደ ስራ በማስገባት ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ተሳትፎና ተጠቃሚነታቸውን ማረጋገጥ እንደሚገባ አስታውቀው በመስኩ የተስተዋሉ ጉድለቶችን ወስዶ መቅረፍና ለውጤታማነት በአፅንኦት መስራት እንደሚያስፈልግ አሳስበዋል።
የወረዳው የስራ እድል ፈጠራና ኢንተርፕራይዝና ልማት ፅህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ጅላሉ ወራቄ በበኩላቸው ከመድረክ የተነሱ ግብዓቶች የቀጣይ የትኩረት አቅጣጫ ተደርጎ እንደሚሰራ ገልፀዋል። አክለውም ተቋሙ የወጣቶችን ሁለንተናዊ ተሳትፎና ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የሚደረገውን ጥረት በየደረጃው የሚገኙ አካላት በተገቢው በማገዝ የሚጠበቅባቸውን ሃላፍትና ሊወጡ እንደሚገባ አስገንዝበዋል።
ዘገባው የገ/ጉ/ወ/ወ/የመ/ኮ/ጉ/ፅ/ቤት ነው።
ሐምሌ 16/2017 ዓ.ም
የበጎ ፍቃድ አገልግሎት የመረዳዳትና የመደጋገፍ ባህልን የሚያጠናክር በመሆኑ የዘውትር ተግባራችን ሊሆን እንደሚገባ በጉራጌ ዞን ገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ወጣቶችና ስፖርት ጽ/ቤት ገለጸ።
፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨
በጉራጌ ዞን ገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ የ2017 በጀት አመት የበጋ ወራት የበጎ ፍቃድ አገልግሎት ማጠቃለያ እና የክረምት ወራት የበጎ ፍቃድ አገልግሎት ማብሰሪያ የንቅናቄ መድረክ" በጎነት ለኢትዮጵያ ከፍታ " በሚል መሪ ቃል በዛሬው እለት ተካሄዷል።
የወረዳው ወጣቶችና ስፖርት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሸምሱ ኢብራሂም መድረኩን አስመልክተው እንኳን ደህና መጣች መልዕክ ባስተላለፉበት ወቅት እንዳሉት ፓርቲያችን ሰው ተኮር በመሆኑ ባለፉት አመታት በበጋና በክረምት ወራት እንደሀገር በበጎ ፍቃድ አገልግሎት ትኩረት ሰጥቶ በርካታ ስራዎች ተሰርቷል ብለዋል።
በወረዳው በ2017 የበጋ ወራት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት በ14 ስራ መስኮች 11 ሺህ 105 ወጣቶችን በማሳተፍ 22 ሺህ 835 የህብረተሠብ ክፍሎችን ተጠቃሚ ማድረግ መቻሉን ጠቅሠው ከ6 ሚሊዮን ብር በላይ ተጨማሪ ሃብት መፍጠሩን አስታውቀዋል።
በዘንድሮ የክረምት ወራት የበጎ ፍቃድ አገልግሎት
በጎነት ለኢትዮጵያ ከፍታ " በሚል መሪ ቃል በ15 ስራ መስኮች 39 ሺህ 113 ወጣቶችን እንዲሳተፉ በማድረግ 77 ሺህ 143 የህብረተሠብ ክፍሎችን ለማስጠቀምና ከ44 ሚሊዮን ብር በላይ ተጨማሪ ሃብት ለመፍጠር ታቅዶ እንቅስቃሴ መጀመሩን ያወሱት አቶ ሸምሱ የበጎ ፍቃድ አገልግሎት
በሰላም ፣ በደም ልገሳ፣ በአካባቢ ፅዳት ዘመቻ፣
በአረንጓዴ አሻራ፣ለአቅመ ደካሞች ቤት መስራት እንዲሁም በትምህርት፣ በጤና በመንገድና በግብርና በአጠቃላይ በ15 ስራ መስኮች ወጣቶችን በማሰማራት በርካታ ተግባራትን ለማከናወን መታቀዱን አብራርተዋል።
በመድረኩ የ2017 የበጋ ወራት የበጎ ፍቃድ አገልግሎት ማጠቃለያ እና የክረምት ወራት የበጎ ፍቃድ አገልግሎት እቅድ ሪፖርት በጽ/ቤቱ ምክትልና ወጣቶች ዘርፍ ኃላፊ በአቶ ጀማል ናስር ቀርቦ ወይይት ከተሳታፊዎች ጋር በማድረግ የቀጣይ ትኩረት አቅጣጫዎች ተቀምጧል።
የንቅናቄ መድረኩን የመሩት የወረዳው ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሚፍታ ሁሴን እንደገለጹት በዘንድሮው የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት ወጣቶችን በንቃት በማሳተፍ በተለያዩ መስኮች ዘርፈብዙ ተግባራትን በማከናወን በርካታ አቅመ ደካሞችንና አረጋዊያንን ለመደገፍ ለመደገፍ መታቀዱን ተናግረዋል።
ወጣቱ መልካምነት ለራስ መሆኑን በመረዳት በወረዳ ውስጥ የሚከናወኑ የልማት ተግባራትን በበጎ ፈቃድ ከመደገፍ ባለፈ ለአቅመ ደካሞችና አረጋዊያን አለኝታ በመሆን የዘንድሮ ክረምት በጎ ስራን በቁርጠኝነት በመስራት ለወገን ያላቸውን አለኝታ እንዲያሳዩ አቶ ሚፍታ አክለው ገልጸዋል።
ለዚህ ተግባር ስኬት ሁሉም ባለድርሻ አካላት የበኩላቸውን ሚና እንዲወጡ መልዕክት አስተላልፈዋል።
የወረዳው ወጣቶችና ስፖርት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሸምሱ ኢብራሂም በበኩላቸው በጎ ተግባር የማጠናከር እንዲሁም በህብረተሰቡ ዘንድ ትልቅ ቅቡልነት እንዲኖር ማድረግ ወሳኝ መሆኑን ገልጸዋል።
በጎነት ለማህበረሰባችን እጅግ ወሳኝ መሆኑን በመገንዘብ ሁሉም ተግባር የሚመሩ ባለድርሻ አካላት በሁሉም ስራ መስኮች በቁርጠኝነት መሠራት እንደሚገባም አቶ ሸምሱ አስገንዝበዋል።
በመጨረሻም አቶ ሸምሱ ኢብራሂም የበጎ ፍቃድ አገልግሎት የመረዳዳትና የመደጋገፍ ባህልን የሚያጠናክር በመሆኑ የዘውትር ተግባራችን ሊሆን እንደሚገባ አሳስበዋል።
ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር) በተገኙበት በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የ2017 በጀት ዓመት የፓርቲና የመንግስት አፈጻጸሞች፣በ2018 በጀት ዓመት የዕቅድ አቅጣጫዎች ላይ ያተኮረ የአመራር መድረክ በሆሳዕና ከተማ እየተካሔደ ነው
፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨
"ከመስፈንጠር ከፍታ ወደ ላቀ እምርታ " ! በሚል መሪ ሀሳብ እየተካሔደ ባለው መድረክ በብልጽግና ፓርቲ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ ዲላሞ ኦቶሬ(ዶ/ር)፣የክልሉ ብሔረሰቦች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አቶ አቡቶ አኒቶ፣ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አንተነህ ፍቃዱ፣በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የክላስተር አስተባባሪዎች፣የክልል፣የዞን እና የልዩ ወረዳ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።
ሐምሌ 14/2017 ዓ.ም
የወልቂጤ ግብርና ምርምር ማዕከል በጉራጌ ዞን ገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ እያደረገ ያለውን ድጋፍ ተጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑን አስታወቀ።
፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨
ይህ የተገለፀው የግብርና ምርምር ማዕከሉ በጥላሞ ቀበሌ በኩታ ገጠም ለሚገኙ አርሶ አደሮች ከ38 ኩምታል በላይ የተሻሻለ የስንዴ ምርጥ ዘር በማቅረብ ዘር የመዝራት መርሃ-ግብር ዛሬ በተካሄደበት ወቅት ነው።
በዚህ ወቅትም የወረዳው ምክትል አስተዳዳሪና ግብርና ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ ከድር መርጋ በዘንድሮ መኸር እርሻ 14 ሺህ 909 ሄ/ር መሬት ለማልማት በማቀድ እየተሠራ እንደሚገኝ ገልጸው የወልቂጤ ግብርና ምርምር ማዕከል የአርሶ አደሩን ምርትና ምርታማነት ለማረጋገጥ እያከናወናቸው የሚገኙ መጠነ-ሠፊ ስራዎች አበረታች መሆናቸውን ያነሱት አቶ ከድር መርጋ አርሶ አደሩ ከዕቅድ ዝግጅት አንስቶ ምርት እስከ ማሰባሰብ ድረስ ያለው ሂደት ተጠናክሮ መቀጠል እንደሚገባው አስታውቀዋል።
የወልቂጤ ግብርና ምርምር ማዕከል ተመራማሪና ዳይሬክተር አቶ ቤተል ነክር የወልቄጤ ግብርና ምርምር ማዕከል ከተቋቋመ አጭር ጊዜ ቢሆንም በአንፃሩ በርካታ ሊታዩና ሊቆጠሩ የሚችሉ ተጨባጭ ስራዎች ማከናወኑን ገልፀዋል።
በወረዳው በግብርና ልማት መስክ እየተከናወነ ያለው እንቅስቃሴ የሚደነቅ ስለመሆኑ ያወሱት አቶ ቤተል ነክር በዘንድሮ ዓመት እንደ አጠቃላይ 100 ሄ/ር በወረዳ ደረጃ ደግሞ 30 ሄ/ር መሬት ለማልማት ግብ ተጥሎ እየተሰራ እንደሆነ በማንሳት ለዚህም ልማት የሚውል ከ38 ኩምታል ስንዴ ምርጥ ዘር ስለመቅረቡ በመግለፅ ግብርና ምርምር ማዕከሉ ከወረዳው መንግስት ጋር በቅንጅት እየሠራ ያለው ስራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታውቀዋል።
አያይዘውም ተቋማቸው አስፈላጊውን ለእቅዱ መሳካት እያደረገ ያለው የግብዓት እና ሙያዊ ድጋፍ ተጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑን ጠቁመው አርሶ አደሩ የተጠናከረ ስራ ማከናወን እንደሚጠበቅበትም አስገንዝበዋል።
የገ/ጉ/ወ/ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሚፍታ ሁሴን በበኩላቸው ሃገራችን ልዩ ትኩረት ሠጥታ ከምትሠራባቸው መስኮች አንዱና ዋነኛው የግብርናው ክፍለ ኢኮኖሚ ሲሆን የስንዴ መስክ ደግሞ በዋናነት ተጠቃሽ ነው ብለዋል።
የወልቂጤ ግብርና ምርምር ማዕከል በወረዳችን እያከናወናቸው ያሉ ስራዎች ምርትና ምርታማነትን ከማሳደግም ባሻገር የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ ተጨባጭ ዉጤት እያስመዘገቡ ይገኛሉ ያሉት ዋና አስተዳዳሪው ተቋሙ እያደረገ ላለው ድጋፍና እገዛ በወረዳው ህዝብና መንግስት ስም የላቀ ምስጋናቸውን በመግለፅ መሠል እገዛዎች ተጠናክሮ መቀጠል እንደሚኖርባቸውም አሳስበዋል።
አንዳንድ አርሶ አደሮች በሠጡት አስተያየት ምርምር ማዕከሉ እያቀረበላቸው ባለው አቅርቦት ደስተኞች መሆናቸውን ጠቁመው ምርትና ምርታማነትን ለማረጋገጥ ከቅድመ-ዝግጅት ስራዎች ጀምሮ ምርት እስከሚሰበሰብበት ጊዜ ድረስ አፅንኦት ሠጥተው እንደሚሰሩ በመግለፅ የባለሙያዎች ድጋፍና ክትትል ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባዋልም ብለዋል።
ዘገባው የገ/ጉ/ወ/ወ/የመ/ኮ/ጉ/ፅ/ቤት ነው።
ሐምሌ 14/2017 ዓ.ም
የጉራጌ ዞን የብልፅግና ፓርቲ ጽ/ቤት በአጠቃላይ የፖለቲካና ንቅናቄ ስራዎች የአንደኝነት ደረጃን አገኘ‼
፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨
የጉራጌ ዞን የብልፅግና ፓርቲ ጽ/ቤት ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ከሚገኙ ዞኖችና ልዩ ወረዳዎች ከሁሉም የላቀ ውጤት በማስመዝገብ በአጠቃላይ የፖለቲካና የንቅናቄ ስራዎች አንደኛ ደረጃን መያዙ ተገለጸ።
ይህ ስኬት ዞኑ በ2017 ዓ.ም. ባከናወናቸው ዘርፈ ብዙ ስራዎች የተገኘ ሲሆን፣ እነዚህም ስራዎች የህዝብን አመኔታ ከማሳደግ ባለፈ የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት ያረጋገጡ መሆናቸውን ያመላክታል።
የጉራጌ ዞን የብልፅግና ፓርቲ ጽ/ቤት ባከናወናቸው ውጤታማ ስራዎች የክልሉ የብልፅግና ፓርቲ ጽ/ቤት ዋንጫ፣ ሰርተፍኬት፣ ኮምፒውተር እና ፕሪንተር ሽልማት አበርክቶለታል።
ይህ ሽልማት የዞኑን አመራሮችና አባላት የላቀ ጥረት የሚያሳይ ከመሆኑም በላይ በቀጣይ ለተሻለ ስራ መነቃቂያ እንደሚሆን ተገልጿል።
እንኳን ደስ አላቹ፣እንኳን ደስ አለን‼
መረጃው የጉራጌ ዞን ኮሚኒኬሽን ነው።
ኢትዮጵያ ተጨማሪ የወርቅ ሜዳልያ አገኘች
ኢትዮጵያ በአፍሪካ ከ18 እና ከ20 ዓመት በታች አትሌቲክስ ሻምፒዮና ሁለተኛውን የወርቅ ሜዳልያ አግኝታለች፡፡
በሴቶች የ800ሜ ከ18 ዓመት በታች የፍፃሜ ውድድር ኤልሳቤጥ አማረ በበላይነት በማጠናቀቅ ለኢትዮጵያ የወርቅ ሜዳልያ አስገኝታለች።
አትሌት ሕይወት አምባው በሴቶች ከ18 ዓመት በታች 5 ሺህ ሜትር ርምጃ ውድድር የመጀመሪያውን የወርቅ ሜዳልያ ማግኘቷ ይታወሳል።
FMC
