924
订阅者
无数据24 小时
+57 天
+930 天
帖子存档
ታላቁ የኢትዮጽያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ተጠናቆ ለምረቃ መብቃቱ እንዳስደሰታቸው በጉራጌ ዞን የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ የመሃል አምባ ከተማ ነዋሪዎች ገለፁ።
፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨
እንደ ነዋሪዎቹ ገለፃ ከሆነ ታላቁ የኢትዮጽያ ህዳሴ ግድብ የሁሉም ኢትዮጵያዊ ህዝቦች አሻራ በመሆኑና ዛሬ ለምርቃት መብቃቱ ዳግማዊ አድዋ ነው ሲሉ አስተያየታቸውን ሠጥተዋል።
ግድቡ የትውልድ ቅብብሎሽን ያሳየ ነው ያሉት ነዋሪዎቹ እኛ ኢትዮጵያውያን በአንድነት ከቆምን የማናሳካው ጉዳይ የለም ብለዋል።
አክለውም ታላቁ የኢትዮጽያ ህዳሴ ግድብ በቆራጥ መሪዎቿ ጥረት የውስጥ እና የውጭ ጫናዎችን ተቋቁሞ ለፍሬ መብቃቱ እጅግ በጣም አስደሳች እንደሆነም ገልጸዋል።
ህዳሴ ግድቡ መመረቅ መቻሉ ለሌሎች አጎራባች ሀገራት ተሞክሮ ሲሆን ሃገራችን በቀጣይ ጊዜያት ለምታከናውናቸው ታላላቅ ፕሮጀክቶች በህብረተሰቡ ዘንድ መነቃቃት መፍጠር ያስቻለ መሆኑንም ያነጋገርናቸው አስተያየት ሰጪዎች ጠቁመዋል።
ዘገባው የገ/ጉ/ወ/ወ/የመ/ኮ/ጉ/ጽ/ቤት ነው።
የርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው(ዶ/ር) መልዕክት
የማንሰራራት ቀን፣
ዘላቂ ልማት ፣ ለሀገራዊ ማንሰራራት!
ኢትዮጵያ በሁሉም መስኮች የጀመረችዉ የማንሰራራት ዘመን ጉዞ ተጠናክሮ ይቀጥላል። ፀጋዎቻችን በማልማት ፣ የብዝሃ ዘርፍ ኢኮኖሚ ልማት ግንባታን በማጠናከር ፣ ለሀብት ፈጠራና ለኢኮኖሚ ብልጽግና እንተጋለን።
የኢትዮጵያ የማንሰራራት ዘመን ምልክትና መገለጫ የሆነዉ ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ለሚመረቅበት፣ ታላቁ የብስራት ቀን እንኳን አደረሳችሁ! አደረሰን !
የታላቁን የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ምረቃ ስነ ስርዓት ስናከናዉን፣ በግድቡ የግንባታ ሂደት የታየዉን ታላቅ የአንድነትና የብሔራዊ ዐርበኝነት ተጋድሎ እያስታወስን፣ እያወደስን፣ በሂደቱ ካጋጠሙ ዉስጣዊና ዉጫዊ ፈተናዎች ደግሞ እየተማርን፣ ራሳችንን እያጠናከርን እንዲሁም ተጨማሪ የቤት ሥራዎችንና ስኬቶችን እያሰላሰልንና ራሳችንን ለአዳዲስ ትግልና እመርታዊ ለዉጥ እያዘጋጀን ነዉ።
የትዉልዶች ቁጭትና ጥያቄ የነበረዉ ዓባይን በማልማት ብሔራዊ ጥቅማችንን የማስከበር አጃንዳ በህብረት፣በይቻላል የዐርበኝነት ወኔና ፅናት እዉን ሆኖ ፣ እነሆ የኢትዮጵያን የማንሰራራት ዘመን አብሳሪ ደማቅ ዐሻራ ለማኖር በቅተናል ።
እንኳን ደስ አላችሁ! እንኳን ደስ አለን !
ኢትዮጵያ ከሕዳሴ ግድብ ጋር የሚስተካከል የኒውክሌር ማበልጸጊያ በቅርቡ ትጀምራለች - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
ጳጉሜ 03/2017 ዓ.ም
አንድም ህጻን በትምህርት ቁሳቁስ እጦት ከትምህርት ገበታ እንዳይቀር በክረምት በጎ ፍቃድ አገልግሎት የትምህርት መማሪያ ቁሳቁስ በማሰባሰብ ለ30 የተቸገሩ ህፃናት 20 ደርዘን ደብተርና 2 ፓኬት እስክሪብቶ በዛሬው እለት ድጋፍ ማድረጉን
የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ወጣቶችና ስፖርት ጽ/ቤት ገለፀ።
፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨
"አንድም ህጻን በትምህርት ቁሳቁስ እጦት ከትምህርት ገበታ መቅረት የለበትም" በሚል መሪ ቃል በተለያዩ ምክንያቶች ለችግር የተጋለጡና የኢኮኖሚ ችግር የገጠማቸው የህብረተሰብ ክፍሎችን ለመደገፍ ደብተር፣ እስክሪብቶ፣ አልባሳት ሌሎች አይነት ድጋፎች ከተለያዩ መንግስታዊና መንግስታዊ ካልሆኑ ድርጀቶች፣ ከንግዱ ማህበረሰብ፣ ከበጎ አድራጊ ግለሰቦች፣ ከሌሎችም ሀብትና ድጋፍ የማሰባሰብ ስራ በዘንድሮ የክረመት በጎ ፍቃድ ሲሰራ መቆየቱን ጽ/ቤቱ አክሎ ገልጿል።
በዛሬው እለትም በወረዳው መሃል አምባ ከተማና በዙሪያው ለሚገኙ 30 ለሚሆኑ ለዘማች ቤተሰብ፣ ለተፈናቃይ እና ለአቅመ ደካሞች ተማሪዎች
20 ደብተርና 2 ፓኬት እስክሪብቶ ድጋፍ መደረጉን አስታውቀዋል።
በድጋፉ ወቅት የወረዳው ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሚፍታ ሁሴን ተማሪዎቹ በትምህርታቸው ጠንከረው እንዲማሩ መልዕክት አስተላልፈው መሠል እገዛዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ ገልጸዋል።
ይህንን በጎ ተግባር ከወረዳው ወጣቶችና ስፖርት ጽ/ቤት በተጨማሪ የሴቶችና ህጻናት እንዲሁም ሠራተኛና ማህበራዊ ጽ/ቤት መሳተፍቸውን ለማወቅ ተችሏል።
ጳጉሜ 3 የእምርታ ቀን " ሁለንተናዊ እምርታ ለኢትዮጵያ ከፍታ " በሚል መሪ ቃል በጉራጌ ዞን ገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ በፓናል ውይይትና በልዩ ልዩ መርሐግብሮች ተከበረ።
፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨
በጉራጌ ዞን ገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ጳጉሜ 3 "የእምርታ ቀን" ሁለንተናዊ እምርታ ለኢትዮጵያ ከፍታ " በሚል መሪ ቃል በደማቅ ሁኔታ በተለያዩ ኩነቶች ተከብሮ ውሏል።
በእለቱ ፓናል ውይይት፣አጫጭር የግብርናና መሠረተ ልማቶች የሚያሳይ ቪዲዮ እና ስፖርታዊ ውድድር ተካሄዷል።
የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አ/ረሂም ርዳ መክፈቻ ንግግር ያደረጉ ሲሆን በዚህ ዓመት ከጳጉሜ 1 _ 5 የሚከበሩ ስያሜዎችን አከባበራቸውን አስመልክቶ ማብራሪያ ሰጥተዋል።
ባለፉት የለውጥ ዓመታት በመንግስትና በህዝቡ የተቀናጀ ጥረት የተከናወኑ ስራዎችና ውጤቶች መገኘታቸው የሚያበረታታ ብለዋል።
በቀጣይ የበለጠ ስራ ለመስራትና የህዝቡን ጥያቄ ለመመለስ በዚህ ውይይት መግባባት ይኖርብናል ብለዋል።
የወረዳው ፕላንና ልማት ጽ/ቤት ተወካይ የውይይት መነሻ የሆነ ወረዳዊ እምርታዊ ውጤቶችንና የቀጣይ አቅጣጫ በዝርዝር አቅርበዋል።
የፓናል ውይይቱን የመሩት የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሚፍታ ሁሴን ጳጉሜ 3 "የእምርታ ቀን" ስናከብር ሀገራችን በሁሉም ዘርፍ ያስመዘገበችውን ስኬቶች በማጉላት ያልተጠናቀቁ ተግባራትን ከስኬት ለማድረስ የምንዘጋጅበት መሆኑን ገልጸዋል።
የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አ/ረሂም ርዳ በበኩላቸው እምርታ ለኢትዮጲያ ከፍታ ስናከብር ሀገራችንን በሁሉም ዘርፍ በኢኮኖሚ በማሳደግ ከተረጂነት ወጥተን እምርታን በማረጋገጥ አገራችንን ወደ ከፍታ ማድረስ አለብን ብለዋል።
ጷግሜ 03/2017 ዓ.ም
በጉራጌ ዞን ገደባኖ ጉታዘር ወለኔ በጠይባ ቀበሌ በጠረጴዛማ እርከን በወጣቶች የለማ የስንዴ ማሳ በምስል፦
