ch
Feedback
የገ/ጉ/ወ/ወ/የመ/ኮ/ጉ/ጽ/ቤት

የገ/ጉ/ወ/ወ/የመ/ኮ/ጉ/ጽ/ቤት

前往频道在 Telegram
917
订阅者
-124 小时
+27 天
+930 天
帖子存档
ህዳር 26/2018 ዓ.ም የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ የ2017 ዓ.ም ማህበረሰብ አቀፍ ጤና መድህን እቅድ አፈፃፀም እና የ2018 በጀት ዓመት የማዕጤመ ንቅናቄ መድረክ በዛሬው እለት ተካሄዷል። ፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨ በመድረኩ የ2017 በጀት አመት እቅድ አፈፃፀም እና የ2018 በጀት አመት መነሻ እቅድ የወረዳው ጤና ፅ/ቤት የማዕጤማ አስተባባሪ የሆኑት አቶ ሰኢድ ገላን እና የጽ/ቤቱ ኃላፊ አቶ ኢብራሂም አብራር አዲሱን ማርበርግ በሽታ አስመልክቶ ለገንዛቤ የሚሆን ሰነድ አቅርበዋል። ‎በቀረበው ሰነድ መነሻ የመድረኩ ተሳታፊዎች በ2017 በጀት አመት የነበሩ ጥሩ አፈፃፀሞችና ፣ ጉድለቶች እንዲሁም በቀጣይ አቅጣጫዎች ዙሪያ ሰፊ ውይይት ተደርጓል። የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሚፍታ ሁሴን በንቅናቄ መድረኩ ላይ ተገኝተው መንግስት የህብረተሰቡን ጤና ለማሻሻል ከከባለሀብቶችና ከረጂ ድርጀቶች በማስተባበር የተለያዩ የህክምና መገልገያ መሳሪያዎች እንዲሁም መድኃኒት ማግኘታቸውን ገልፀው በሁሉም የጤና ተቋማት የመድኃኒት እጥረት ለመቅረፍ ካላቸው በጀት በተጨማሪ መንግስት የበጀት ድጎማ እያደረገ እንደሚገኝ አስታውቀዋል። የማህበረሰብ አቀፍ ጤና መድህን ለማህበረሰቡ ቀልጣፋና አሰተማማኝ ጤና አገልግሎት ተደራሸ እንዲሆን ከማድረግ አኳያ በጤናው ዘርፍ እየተመዘገበ ያለው ለውጥ ከፍተኛ አስተዋጽኦ መኖሩን ተናግረዋል። አቶ ሚፍታ አክለውም ህብረተሰቡ በገንዘቡ ልክ ሳይሆን በጤናው ልክ መታከም እንዲችል በመደጋገፍ የጤና መድህን አባል እንዲሆን ማድረግ እንደሚያስፈል ጠቅሠው ማህበረሰብ ዐቀፍ ጤና መድህን አገልግሎት ስራ ከታቀደለት ጊዜ ቀድሞ ለመጨረስ ሁሉንም አደረጃጀቶችን በመጠቀም የህዝባችንን የጤና አገልግሎት ለማሳደግ በትኩረት እንደሚሰራ አስተውቀዋል። የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ጤና ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ኢብራሂም አብራር የ2017 በጀት ዓመት አፈጻጸም ተገምግሞ እንደ ጠንካራ ጎን የተለዩትን መልካም ተሞክሮችን በ2018 ዓ.ም አጠናክሮ በመቀጠል ማህበረሰቡ በዘርፉ አገልግሎት በቂ ግንዛቤ እንዲኖረዉ ለማድረግ፣ አመራሮችና የጤና ባለሙያዎች ግንዛቤዎችን በመስጠትና አዳዲስ አባላትን በማፍራት ማህበረሰቡ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ለማስቻል ትኩረት ተሰጥቶ መሰራት እንዳለበት ተጠቁመዋል። የህብረተሰባችንን የመዐጤመ አባልነት ባደገ ቁጥር የጤና ተቋማት አገልግሎት አሰጣጥ ከማደጉም በላይ የግብዓት አቅርቦትም በዚያው ልክ የሚያድግ በመሆኑ በትኩረት ሊተገበር ይገባል ሲሉ አቶ ኢብራሂም አክለው ገልጸዋል። የማዕጤመ ሀብት አሰባሰብ በተመጠለት ጊዜ መጠናቀቅ እንዳለበት፣የባለሙያ የስነምግባር ችግሮች መኖሩ፣አገልግሎት አሰጣጥ ጉደለቶች መስተካከል እንደሚያስፈልግ የገለጹ ሲሆን የጤና ተቋማት የመድኃኒት እና የቁሳቁስ ችግር ለመቅረፍ እየተደረገ ያለው ጥረት ሚበረታታ መሆኑ ከመድረኩ የተነሱ ሀሳቦች ናቸው። በእለቱ የወረዳው አመራሮች፣ቀበሌ ሊቀመንበሮችና ስራስኪያጆች፣ ከየቀበሌው የተወጣጡ የጤና ፅ/ቤት ባለያሙዎች እና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል። በመጨረሻም በ2017 በጀት አመት በማዕጤመ የተሻለ አፈጻጸም ላስመዘገቡ ቀበሌዎች የእውቅና ሠርተፍኬት ተበርክቷላቸዋል።

ህዳር 26/2018 ዓ.ም ያለፉት ሁለት ዓመታት ጉዞ አድካሚ ቢሆንም በርካታ ያጋጠሙ ችግሮችን ማስተካከል በመቻሉ ክልሉ በትክክለኛ አቅጣጫ ላይ መሆኑን ተገንዝበናል :- ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር) ፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር)20ኛውን የኢትዮጵያ የብሔር፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን በዓል በማስመልከት ከመገናኛ ብዙሀን ጋር ቆይታ አድርገዋል የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር )እንደገለጹት ከሌሎች የሀገሪቱ ህዝቦች ጋር ያለንን መስተጋብር ወደ ላቀ ደረጃ በማድረስ በወዳጅነት፣ በወንድማማችነትና በእህታማማችነት ላይ የተመሰረተ ስራ ለመስራት ጽኑ ፍላጎት አለን ብለዋል። በክልሉ በተለያዩ አካባቢዎች የሚከበሩ የመስቀል እና የዘመን መለወጫ በዓላት ብራንድ አድርጎ ማውጣት ይቻላል ሲሉም ርዕሰ መስተዳድሩ አስረድተዋል። በክልሉ በኢንዱስትሪ፣በቱሪዝም እንዲሁም ለኤክስፖርት የሚሆኑ የእርሻ ምርቶችን በማስፋፋት ብራንድ ማድረግ የሚያስችል ስርዓት መዘርጋት ተገቢ ስለመሆኑም አመላክተዋል። በእነዚህ እና በመሳሰሉት ነጥቦች ላይ ጠንክረን በመስራት የክልሉ መገለጫ የሚሆኑ ጉዳዮች ላይ ብራንድ እንዲኖረን እንሰራለን ብለዋል። ባለፉት ሁለት ዓመታት ያጋጠሙ ተግዳሮቶች በርካታ ናቸው ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ መጀመሪያ ችግሮችን በደንብ መለየት እና መረዳት፣ለችግሮች መፍትሄ ለማበጀት ደረጃቸውን ጭምር መለየት ላይ ትኩረት አድርገናል ሲሉም ጠቁመዋል። ካጋጠሙን ተግዳሮቶች ውስጥ የሰላም እጦት፣የደመወዝ ፣የማዳበሪያ፣ የጥሬ ገንዘብ እዳ እና ሌሎች በርካታ ችግሮችን መጥቀስ ይቻላል ብለዋል። ሰራተኛው እና አመራሩ ለረጅም ጊዜ ስራ ላይ ባለመኖሩ በተቀዛቀዘ ስሜት ላይ ነበር ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ በሌላ በኩል ከአፈር ማዳበሪያ ጋር የተያያዘ ስርዓት አልበኝነትም ተስተውሎ እንደነበር ጠቅሰዋል። የእነዚህን ችግሮች ደረጃ በመለየት እንዴት እንፍታቸው፣መቼ እልባት እንስጣቸው በሚል እሳቤ አቅደን ወደ ተግባር ገብተናል በማለት አብራርተዋል። አሁን ካለው ነባራዊ ሁኔታ አንጻር አብዛኛዎቹን ችግሮች በጊዜ ሂደት መፍታት ተችሏል ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ አልፎ አልፎ የሚመላለሱ ችግሮች ሊኖሩ ስለሚችሉ እያስተካከልን እንሄዳለን ብለዋል። ባለፉት ሁለት ዓመታት ሁሉም አመራር ርብርብ ያደረገበት ስራ የሰላም ማስከበር ተጠቃሽ ስለመሆኑ የገለጹት ርዕሰ መስተዳድሩ በተደጋጋሚ ስለ ዘላቂ ሰላም ስናነሳ ሰላም ወዳዱ ህብረተሰብ ከመንግስት ጋር በቅንጅት እየሰራ ይገኛል ብለዋል። ነገር ግን በክልላችን በተለያየ ጊዜ ችግር ለመፍጠር የሚፈልጉ አካላት ይሄ ጉዳይ በጥብቅ ዲሲፕሊን እየተመራ መሆኑን ሲገነዘቡ ይከፋቸዋል ሲሉም ጠቁመዋል። በዘርፉ የሚደረገውን ጥረት ለመቀልበስ በፕሮፓጋንዳ ስራ ላይ መጠመዳቸውንም ጠቅሰዋል። በሰላም ጉዳይ ላፍታም ሳንዘናጋ ዛሬም፣ነገም ለሚቀጥሉት ቀናት ወራትና ዓመታት ስለ ሰላም እንሰራለን ብለዋል። ሌላው ትኩረት አድርገን የሰራንበት ጉዳይ ግብርና ነው ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ በክልሉ ቅድመ በልግና ጸደይን ጨምረን በቂ የምርት እድገት እንዲኖር በትኩረት እየተሰራ ስለመሆኑም በአብነት ጠቅሰዋል። ከዚህ ቀደም በክልሉ በጣም አነስተኛ መጠን ያለው ገቢ ሲሰበሰብ እንደነበር ያስታወሱት ርዕሰ መስተዳድሩ አሁን ከዛሬ ሁለትና ሶስት ዓመታት ሲሰበሰብ ከነበረው ገቢ በእጥፍ አሳድገናል ብለዋል። አንድ ከተማ አሊያም ክልል እራሱን ማሳደግ የሚፈልግ ከሆነ የገቢ እና የንግድ ስርዓቱን ፈትሾ ማስተካከል አለበት ሲሉም ርዕሰ መስተዳድሩ አመላክተዋል። በትምህርት፣በጤና በኢንቬስትመንት ፣በወጣቶች የስራ እድል ፈጠራ እንዲሁም በመሰረተ ልማት ዘርፍ እንደ ውሃ፣መንገድ፣መብራት ቴሌኮም እና መሰል የልማት መስኮችን ማሟላት የክልሉ መንግስት የእለት ተዕለት ስራ ስለመሆኑም ርዕሰ መስተዳድሩ አጽንኦት ሰጥተዋል። በክልሉ ህገወጥነትን መከላከል ሌላው አብይ የትኩረት መስክ መሆኑን የገለጹት ርዕሰ መስተዳድሩ ህገወጥነትን ስንከላከል ደግሞ የኑሮ ውድነትን መቀነስ ያስችላል ብለዋል። የመጣንበት መንገድ አድካሚ ቢሆንም በርካታ ጉዳዮችን ለማሻሻል ሞክረናል ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩእነዚህ በቂ ባለመሆናቸው ተጨማሪ ስራ መስራት ያስፈልጋል። በክልሉ የቤተሰብ ብልጽግናን ለማሳካት በልዩ ትኩረት እየተሰራ ነው ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ በግብርናው መስክ ጠንክሮ በመስራት ከእለት ፍጆታ ባለፈ ገበያውን ማረጋጋት የሚያስችል አቅም መፍጠር ያስፈልጋል ሲሉም ርዕሰ መስተዳድሩ አብራርተዋል። የመደመር ፍልስፍና እና እሳቤ ከተለያዩ ችግሮች ወጥተን ወደ አንድ እንምጣ፣ወደ ኋላ ከሚጎትተን አጀንዳ በመውጣት በጋራ ጉዳዮቻችን ላይ በማተኮር መስራት ተገቢ ስለመሆኑም አመላክተዋል። የጋራ አጀንዳችን ከሆኑ ጉዳዮች ውስጥ ልማት፣ዘላቂ ሰላም እንዲሁም የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ስራዎች ተጠቃሽ ናቸው ብለዋል። የሁለት ዓመታት ጉዞችንን ስንፈትሽ ክልሉ በትክክለኛ አቅጣጫ ላይ መሆኑን ተገንዝበናል በማለት ነበር ርዕሰ መስተዳድሩ የገለጹት። ለኢትዮጵያ ከፍታ ከግብርና መር ኢኮኖሚ በተጓዳኝ ማዕድን፣ቱሪዝምን፣ዲጂታል ኢትዮጵያን እውን ማድረግ እንዲሁም በኢንዱስትሪ ዘርፉ ላይ ትኩረት ማድረግ ይገባል ብለዋል።

ህዳር 25/2018 ዓ.ም ጥራት ያለውና ቀልጣፍ የጤና አገልግሎትን በብቃት ለህብረተሰቡ ተደራሽ ማድረግ ጤናው የተጠበቀ ማህበረሰብ በመፍጠር ረገድ የሚያበረክተው አስተዋጽኦ የጎላ መሆኑን የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሚፍታ ሁሴን ገለጹ። ፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨ በጉራጌ ዞን ገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ የአበዘት ጤና ጣቢያ የ2018 ዓ/ም የ1ኛ ሩብ አመት ዕቅድ አፈፃፀም የቦርድ አባላት በተገኙበት በዛሬው ዕለት ተገምግሟል። የቦርድ አባላት በአበዘት ጤና ጣቢያ በመዞዞር በአገልግሎት አሰጣጡ ዙሪያ፣ለእናቶች ማረፊያ የሚሆን በመኸር የለማ የገብስ ሠብል ምርት አሰባሰብ እንዲሁም በኢትዮጵያ መድሀኒት ድርጅት ድጋፍ የተደረጉ የህክምና መገልገያ ቁሳቁሶችን የመስክ ምልከታ አድርገዋል። የአበዘት ጤና ጣቢያ ኃላፊ ወ/ሮ ላምሮት ያሪሞ የ2018 ዓ.ም የ1ኛ ሩብ አመት አፈፃፀም ሪፖርት ቀርቦ በቀረበው ሪፖርት መነሻ በማድረግ የቦርድ አባላት ሰፊ ውይይት አካሂደዋል። የቦርድ ውይይቱን የመሩት የወረዳው ዋና አስተዳዳሪና የጤና ጣቢያው የቦርድ ሰብሳቢ አቶ ሚፍታ ሁሴን በዚህ ወቅት የህብረተሰቡን ጤና አገልግሎት ተደራሽነትና ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ እየተከናወኑ ያሉ የጤና ስራዎችን በቅንጅት መሠረት እንደሚያስፈልግ ገልጸዋል። አቶ ሚፍታ አክለውም ከአገልግሎት ጥራት ጋር በተያያዘ የሚስተዋሉ ችግሮችን በመቅረፍ ከህብረተሰቡ የሚነሱ ችግሮችን በልዩ ትኩረት መቅረፍ እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡ የባለሙያዎች የአገልግሎት አሰጣጥ ጉድለቶችና የስነ ምግባር ችግሮች፣ብልሹ አሠራሮች ማስተካከል እንደሚገባ ጠቅሠው በ1ኛ ሩብ ዓመቱ ክፍተቶችን ማረም እንደሚያስገልግ የቦርድ አባላት በአስተያየታቸው አስታውቀዋል።

ህዳር 23/2018 ዓ.ም የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ትራንስፖርትና መንገድ ልማት ጽ/ቤት የ2018 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ሩብ አመት ዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት ባለድርሻ አካላት በተገኙበት በዛሬው እለት መገምገሙን አስታወቀ። ፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨ የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ትራንስፖርት መንገድ ልማት ጽ/ቤት የ2018 በጀት አመት የ1ኛ ሩብ አመት ዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት የዜጎች ቻርተር እና የህዝብ ክንፍ አባላት በተገኙበት ውይይት በዛሬው እለት አካሄደ። በመድረኩ የ2018 በጀት ዓመት የ1ኛ ሩብ አመት እቅድ አፈጻጸም ሪፖርት በጽ/ቤቱ የልማት እቅድ ባለሙያ አቶ አንዋር መሃመድ አማካይነት ቀርቡ ሀሳብ አስተያየቶች ተነስተው ውይይት ተደርጓበታል። ውይይቱ ተሳታፊዎች የቀረበውን ሪፖርት መነሻ በማድረግ እንደተናገሩት ሰፊ የሆነ ተደራሽ የገጠር መንገድ እየተሠራ መሆኑ የሚበረታታ እንደሆነ፣ ፣የትራንስፖርት ክፍያ በተገቢው ቁጥጥር ከማድረግ አንጻር፣የተሽከርካሪ ፍጥነት በተለይ ባለ ሁለት እግር፣ ከተቋማት ጋር ጠንካራ ቅንጅታዊ አሰራሮች ሊኖሩ ይገባል የሚሉት ተሳታፊዎች ከነሷቸው ሃሳብና አስተያየቶች ይገኙበታል። የትራንስፖርትና መንገድ ልማት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አሸብር ረጋ ለተነሱ ሀሳብና አስተያየቶች ምላሽና ማብራሪያ በሠጡበት ወቅት እንዳሉት ከመድረኩ የተገኙ ግብዓቶች ተቋሙ ወስዶ እንደሚሠራ ገልጸዋል። አክለውም ህብረተሰቡ የተዘረጉ የመሠረተ ልማት አውታሮችን በባለቤትነት ወስዶ መጠበቅና መንከባከብ እንደሚጠበቅበት ጠቁመው የህብረተሠቡን የመንገድ ልማት ተደራሽነት ችግር ሙሉ በሙሉ ለመፍታት የተጀመረዉን ርብርብ በየደረጃው የሚገኙ አካላት ሊያግዙ እንደሚገባ አስገንዝበዋል። በመጨረሻም የትራንስፖርት ዘርፍ ላይ የሚተስዋሉ ችግሮችን ለመፍታት በዘንድሮ አመት በልዩ ትኩረት እንደሚሠራ ገልጸው ህብረተሠቡ ለተቋሙ መረጃ በመስጠት እንዲሁም የተገነቡ መነገዶችን በባለቤትነት እንዲጠብቅ አሳስበዋል። በመድረኩ ላይ የተቋማት የልማት እቅድ ባለሙያዎች ፣ የህዝብ ክንፍና የዜጎች ቻርተር አባላት፣ እና ሌሎች በላድርሻ አካላት ተሳትፈዋል።

ህዳር 24/2018 ዓ.ም ፍትሃዊና ቀልጣፋ የጤና አገልግሎት ለመስጠት ሁሉም ማህበረሠብ የማህበረሰብ አቀፍ ጤና መድህን ተጠቃሚ እንዲሆን በትኩረት ሊሰራበት እንደሚገባ የጉራጌ ዞን አስተዳደር አስታወቀ። ፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨ "እንደ አቅሜ አዋጣለሁ፣ እንደ ህመሜ እታከማለሁ" በሚል መሪ ቃል የተዘጋጀው የማህበረሰብ አቀፍ ጤና መድህን የ2017 አፈጻጸምና የ2018 የንቅናቄ መድረክ በጉራጌ ዞን ወልቂጤ ከተማ ተካሂዷል። የጉራጌ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ላጫ ጋሩማ እንዳሉት ማጤመ የህዝቡን የጤና ዋስትና ለማረጋገጥ እጅግ ወሳኝ መሆኑን በመግለፅ፣ ፍትሀዊና ቀልጣፋ የጤና አገልግሎት ለመስጠት ሁሉም ማህበረሰብ የማጤመ ተጠቃሚ እንዲሆን በትኩረት ሊሰራበት እንደሚገባ አሳስበዋል። በዘንድሮ አመት ከማጤመ ጋር ተያይዞ የሚተገበሩ ኢኒሼቲቮች መኖራቸው የገለጹት አቶ ላጫ፣ ህብረተሰቡ በአቅሙ ደረጃ በዝቅተኛ፣በመካከለኛና በከፍተኛ ደረጃ እየከፈለ እንዲሄድ በማድረግ የማጤመ ተጠቃሚ እንዲሆኑ በትኩረት ይሰራል ብለዋል። ማጤመን ከፋይዳ መታወቂያ ጋር አስተሳስሮ በመስራት የማጤመ ተጠቃሚ አባላቶች የፋይዳ መታወቂያ ተጠቃሚ መሆን ይጠበቅባቸዋልም ነው ያሉት። ዘርፉን ውጤታማ ለማድረግ አባላት በማፍራት፣ ያልተመለሱ ገንዘቦች እንዲመለሱ በማድረግ፣ ዞናል ቋት በመክፈት፣አምና የነበሩ ጉድለቶች በማረምና ጥንካሬዎችን በማስቀጠል ጤናው የተጠበቀ አምራች ዜጋ መፍጠር ይገባል ብለዋል። የወባ በሽታ ለመቀነስና የማርበርግ በሽታ ለመቆጣጠር የጤና ኤክስቴንሽን ተግባራት በአግባቡ መፈፀም እንደሚገባም አቶ ላጫ ተናግረዋል። የጉራጌ ዞን ዋና የመንግስት ተጠሪ አቶ አለማየሁ ገ/መስቀል እንደገለጹት ስራዎችን ህብረተሰቡ ተጠቃሚ በሚያደርጉ መልኩ በጥራትና በፍጥነት በመስራት አዳጊና ተጨባጭ ለውጥ ለማምጣት ይበልጥ መትጋት እንደሚገባ መክረዋል። በጤና ተቋማት ስነ-ምግባር በተላበሰ መልኩ ማህብረሰባችን ማገልገል ይጠበቃል ያሉት አቶ አለማየሁ የማጤመ ተጠቃሚ የህብረተሰብ ክፍሎች መረጃ ተጣርቶ እንዲያዝና የድሀ ድሀ የሆኑ አካላት ተጠቃሚ እንዲሆኑ ስገንዝበዋል። ጤና ተቋሟት በማጤመ ምክንያት የበጀት እጥረት እንዳይገጥማቸው ማህበረሰቡ በአቅራቢያውና በዞኑ ያሉ ሆስፒታሎችን በአግባቡ መጠቀም አለበት ብለዋል። የጉራጌ ዞን ጤና መምሪያ ኃላፊ አቶ አየለ ፈቀደ በበኩላቸው በዞኑ የማጤመ አፈጻጸምና የጤና አገልግሎት አሰጣጥ በየ ጊዜው እየተሻሻለ መጥቷል። ይሁን እንጂ ለህብረተሰቡ የሚፈለገው የጤና አገልግሎት ለመስጠት በቁርጠኝነት፣በቅንጅትና በኃላፊነት መስራት ያስፈልጋል። በጉራጌ ዞን ከ1ሚሊየን 127 ሺ በላይ የህብረተሰብ ክፍሎች የማጤመ ተጠቃሚ መሆናቸው አስታውቀው በዘንድሮ አመትም ከ3መቶ 31 ሚሊየን 3መቶ 84 ሺ 500 ብር እንደሚሰበሰብ ተናግረዋል። አቶ አየለ አክለውም የጤና ባለሙያዎችና ቤተሰቦቻቸው የማጤመ ተጠቃሚ የሚሆኑበት ስርአት በዘንድሮ ዓመት እንደሚጀመር ተናግረዋል። በኢትዮጵያ ጤና መድህን አገልግሎት የሆሳእና ክላስተር ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ምህረት አብ ዋምሾ እንደተናገሩት ጽ/ቤቱ በስሩ ያሉ መዋቅሮች በማጤመ ዘርፍ የሚሰሩ ተግባራት በመቆጣጠር ህብረተሰቡ የማጤመ ተጠቃሚ እንዲሆን ይሰራል። ከፌደራል የሚወርዱ የድጎማ በጀቶች ሳይቆራሩጡ በጊዜያቸው እንዲወርዱ በቀጣይ በትኩረት እንደሚሰራ የጠቆሙት አቶ ምህረት አብ ማህበረሰቡ ደግሞ በአካባቢው ባሉ ጤና ተቋሟት ቢገለገል ለስራው ይበልጥ አጋዥ እንደሚሆን አስገንዝበዋል። በውይይቱ የተገኙ አካላት እንዳሉት የማህበረሰቡን ፍትሀዊ የጤና አገልግሎት ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ዋነኛ አማራጭ የጤና መድህን አባል ማድረግ ነው ብለዋል። የጤና አገልግሎት አሰጣጥ ለማሳለጥ ጤና ተቋማት ልዩ ልዩ ግብአት ሊሟላላቸው እንደሚገባ ተናግረው ከክልልና ከፌደራል የሚወርዱ የበጀት ፈንዶች በአግባቡ እንዲወርዱ አንስተዋል። ማህበረሰቡ የማጤመ ተጠቃሚ በመደረጉ ጤናውን በአግባቡ እንዲጠብቅ አስችሎታል ያሉት ሀሳብ ሰጪዎቹ ይሁን እንጂ ለጤና ተቋማት የሚከፈለው ገንዘብ በወቅቱና በሚፈለገው አክል መክፈል፣የኦዲት ተደራሽነት ማስፋትና የግንዛቤ ስራዎች ማሳደግ ያስፈልጋል ብለዋል። በመጨረሻም በ2017 በማጤመ ዘርፍ የተሻለ አፈጻጸም ላመጡ ወረዳዎችና ከተማ አስተዳደሮች የእውቅና ሽልማት ተበርክቶላቸዋል።

ህዳር 23/2018 ዓ.ም የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ የኢንጌ ጤና ጣቢያ ስራ አመራር ቦርድ አባላት የ2018 በጀት ዓመት የ1ኛ ሩብ አመት እቅድ አፈጻጸም እና የቀጣይ ወቅጣጫዎች ዙሪያ በዛሬው አለት ውይይት ተካሄደ። ፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨ የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ የኢንጌ ጤና ጣቢያ ስራ አመራር ቦርድ አባላት የ2018 በጀት ዓመት የ1ኛ ሩብ አመት እቅድ አፈጻጸም እንዲሁም የጤና ጣቢያውን የአገልግሎት አሰጣጥ ሂደትን ቀልጣፋና ውጤታማ ለማድረግ ባሉ ጥንካሬዎችና ጉድለቶች ላይ ጥልቅ ውይይት በማድረግ የቀጣይ አቅጣጫዎች ተቀምጠዋል። የኢንጌ ጤና ጣቢያ ኃላፊ አቶ ደበበ ንጉሴ የ2018 ዓ.ም የ1ኛ ሩብ አመት አፈፃፀም ሪፖርት ቀርቦ በቀረበው ሪፖርት መነሻ በማድረግ የቦርድ አባላት ሰፊ ውይይት አካሂደዋል። በመድረኩ የቦርድ አባላት እንዳሉት የተገልጋይ ህብረተሰብን ፍላጎትን መሠረት ያደረገ የመድኃኒት አቅርቦት ፣የባለሙያዎች የአገልግሎት አሰጣጥ ጉድለቶችና የስነ ምግባር ችግሮች እና በሌሎች ጉዳዮች ሰፊ ውይይት ተደርጎ በጥንካሬ የተለዩ ጉዳዮችን አጠናክሮ በማስቀጠል በጉድለት የተለዩትን በቀጣይ የእቅድ አካል አድርጎ ማስተካከል እንደሚገባ እንዲሁም የቀጣይ አቅጣጫ ተቀምጧል። የቦርድ ውይይቱን የመሩት የወረዳው ዋና አስተዳዳሪና የጤና ጣቢያ የቦርድ ሰብሳቢ አቶ ሚፍታ ሁሴን በማጠቃለያ ወቅት እንዳሉት የጤና ጣቢያው አገለግሎት አሰጣጥ ዙሪያ ከተገልጋይ ህብረተሰብ የሚነሱ የመልካም አስተዳደር ችግሮችን በማረም ለህብረተሰቡ ተገቢ አገለግሎት መሠጠት እንደሚገባ ገልጸዋል። ጤና ጣቢያው ላይ ያሉ ጠንካራ ስራዎችን በተሻለ መልኩ ማስቀጠልና የአገልግሎት አሰጣጥ ውጤታማነትን በማጠናከር ጤናው የተጠበቀና አምራች ማህበረሰብ መፍጠር እንደሚገባ አቶ ሚፍታ አሳስበዋል።