ch
Feedback

不要被骗子欺骗!Telemetrio 会找到并标记这些频道 👉 如果想查看标记,请订阅

Hebrew 🇮🇱 עברית

Hebrew 🇮🇱 עברית

前往频道在 Telegram

የዕብራይስጥ ቋንቋን ይማሩ למדו איתנו את השפה עברית study hebrew with us

显示更多
3 350
订阅者
-724 小时
-277 天
-2730 天
帖子存档
ሻባት ሻሎም שַׁבָּת שָׁלוֹם SHABATH SHALOM @Hebrewethio @Hebrewethio
ሻባት ሻሎም שַׁבָּת שָׁלוֹם SHABATH SHALOM @Hebrewethio @Hebrewethio

ይህ በኢየሩሳሌም ኪድሮን ሸለቆ አካባቢ የሚገኝው የእየሱስ ክርስቶስ እናት የቅድስት ድንግል ማርያም የመቃብር ስፍራ የሚገኝበት ሲሆን ቦታው ላይም ከጥንት ጊዜ ጀምሮ ቤተ-ክርስቲያን ተሰርቶበት አለም
+1
ይህ በኢየሩሳሌም ኪድሮን ሸለቆ አካባቢ የሚገኝው የእየሱስ ክርስቶስ እናት የቅድስት ድንግል ማርያም የመቃብር ስፍራ የሚገኝበት ሲሆን ቦታው ላይም ከጥንት ጊዜ ጀምሮ ቤተ-ክርስቲያን ተሰርቶበት አለም ላይ የሚገኙ ክርስቲያኖች እየመጡ የሚጎበኙት ቅዱስ ስፍራ ነው፡፡ እስራኤል 🤍💙🇮🇱 @Hebrewethio @Hebrewethio

እስራኤል እጅግ ጥንታዊ የሆኑ ቅርሶችን፣ ትውፊቶችንና ታሪኮችን በውስጧ የያዘች አገር መሆኗ የሚታወቅ ቢሆንም ዘመኑን የዋጁ ውብና ማራኪ ዘመናዊ ህንጻዎች የሚገኙባት መሆኗንም ልናስታውሳችሁ ወደድን።
እስራኤል እጅግ ጥንታዊ የሆኑ ቅርሶችን፣ ትውፊቶችንና ታሪኮችን በውስጧ የያዘች አገር መሆኗ የሚታወቅ ቢሆንም ዘመኑን የዋጁ ውብና ማራኪ ዘመናዊ ህንጻዎች የሚገኙባት መሆኗንም ልናስታውሳችሁ ወደድን። ሰላም ለእስራኤል 🇮🇱 ሰላም ለኢትዮጵያ 🇪🇹 ሻባት ሻሎም🙏 @Hebrewethio @Hebrewethio

ሻባት ሻሎም שַׁבָּת שָׁלוֹם SHABATH SHALOM @Hebrewethio @Hebrewethio
ሻባት ሻሎም שַׁבָּת שָׁלוֹם SHABATH SHALOM @Hebrewethio @Hebrewethio

የእስራኤል ቡድን ዛሬ ማታ ከአየርላንድ ጋር በሚያደርገው ሁለተኛ ጨዋታ «7.10» የሚል ጽሁፍ ያለበት ጥቁር የክንድ ማሰሪያ ያሰራል የእስራኤል ብሔራዊ የእግር ኳስ ቡድን ዛሬ ማታ ከአየርላንድ ጋር
የእስራኤል ቡድን ዛሬ ማታ ከአየርላንድ ጋር በሚያደርገው ሁለተኛ ጨዋታ «7.10» የሚል ጽሁፍ ያለበት ጥቁር የክንድ ማሰሪያ ያሰራል የእስራኤል ብሔራዊ የእግር ኳስ ቡድን ዛሬ ማታ ከአየርላንድ ጋር በሚያደርገው ጨዋታ «7.10» (ጥቅምት 7) የሚል ቀን የተጻፈበት ጥቁር የክንድ ማሰሪያ እንደሚያስር የእስራኤል እግር ኳስ ማህበር (IFA) በሰጠው መግለጫ አስታውቋል። ይህ እርምጃ ባለፈው መስከረም 27 በሁለቱ ቡድኖች መካከል በተደረገው ጨዋታ የአየርላንድ ቡድን ላሳየው ባህሪ የተሰጠ ምላሽ ነው። የአየርላንድ ቡድን በጋዛ «በግፍ ለጠፉ ሕይወቶች በሙሉ» መታሰቢያ በሚል ጥቁር የክንድ ማሰሪያ ያሰረ ሲሆን፣ ከእስራኤላውያኑ ጋር ለመጨባበጥ ፈቃደኛ ሳይሆኑ ቀርቶ የእስራኤል ብሔራዊ መዝሙር በሚዘመርበት ወቅት ተጨዋቾች አንገታቸውን ደፍተው ነበር፤ ይህም በእስራኤል ዘንድ ከፍተኛ ቁጣን አስነስቷል። የእስራኤል ቡድን አዛዥ (captain) ማኖር ሶሎሞን (Manor Solomon) ከጨዋታው በኋላ እንደተናገረው፣ አንዳንዶቹ የአየርላንድ ተጫዋቾች በጨዋታው ወቅት ለእስራኤላውያን ተቃዋሚዎቻቸው ደስ የማይሉ ነገሮችን ተናግረዋል። «ስለ አየርላንድ ተጫዋቾች መናገር አልፈልግም። ስለ እነሱ የማስበውን ብናገር ለጥቂት ጨዋታዎች ልታገድ እችላለሁ… በእርግጥ ይጠሉናል። እኛም አንወዳቸውም።» በኤክስ (X) ገጹ ላይ የእስራኤል እግር ኳስ ማህበር እንዲህ ብሏል፦ «ዩኤፍኤ (UEFA) የእስራኤል ብሔራዊ ቡድን ዛሬ ማታ በሚያደርገው ጨዋታ በጥቅምት 7 ጭፍጨፋ ለተገደሉት ሰዎች መታሰቢያ ጥቁር የክንድ ማሰሪያ እንዲያሰር ያቀረበውን ጥያቄ ፈቅዷል። መታሰቢያቸው ለበረከት ይሁን።» @Hebrewethio @Hebrewethio

ሻባት ሻሎም שַׁבָּת שָׁלוֹם SHABATH SHALOM @Hebrewethio @Hebrewethio
ሻባት ሻሎም שַׁבָּת שָׁלוֹם SHABATH SHALOM @Hebrewethio @Hebrewethio

ይህን ጀግና አውሮፕላን አብራሪ ልናመሰግነው ወደድን። ይህ ህንዳዊ ፓይለት ካፒቴን ስሚት ማቻር ይባላል። ካፒቴኑ ፍላይ ዱባይ የበርራ ቁጥር 1073 የተሰኝውን አውሮፕላን እያበረረ ባለበት ወቅት የአብ
ይህን ጀግና አውሮፕላን አብራሪ ልናመሰግነው ወደድን። ይህ ህንዳዊ ፓይለት ካፒቴን ስሚት ማቻር ይባላል። ካፒቴኑ ፍላይ ዱባይ የበርራ ቁጥር 1073 የተሰኝውን አውሮፕላን እያበረረ ባለበት ወቅት የአብራሪዎች ክፍል ውስጥ በሙያ አጋሩ በስለት ተወጋ። ምንም እንኳን ካፒቴኑ ከባድ ጉዳት የደረሰበት ቢሆንም የአውሮፕላኑን የአብራሪዎች ክፍል በር መክፈት በመቻሉ እስራኤላዊያን ተሳፋሪዎችና የተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች የአውሮፕላን ሠራተኞች ጣልቃ በመግባት ሁሉንም ተሳፋሪዎች እንዲታደጉ አስችሏል። ህንዳዊያን፣ እስራኤላዊያን እና ኤሜራቶች በጋራ እና በትብብር የሰሩት አስደናቂ ጀግንነት የ174 ሰዎችን ሕይወት ታድጓል። ለካፒቴን ማቻር ልባዊ ምስጋናን እያቀረብን ከጉዳቱ እንዲያገግም እንመኛለን! 🇮🇳🇮🇱🇦🇪 Via፦ Israel in Ethiopia

እንኳን ለብርሃነ መስቀሉ በሰላም አደረሳችሁ። መልካም በዓል ይሁንላችሁ። @Hebrewethio @Hebrewethio
እንኳን ለብርሃነ መስቀሉ በሰላም አደረሳችሁ። መልካም በዓል ይሁንላችሁ። @Hebrewethio @Hebrewethio

ሻባት ሻሎም שַׁבָּת שָׁלוֹם SHABATH SHALOM @Hebrewethio @Hebrewethio
ሻባት ሻሎም שַׁבָּת שָׁלוֹם SHABATH SHALOM @Hebrewethio @Hebrewethio

ኔታንያሁ በተመድ፦ «እኛ እናሸንፋለን፤ ከዚህ ውጪ ሌላ አማራጭ የለንም» #Ethiopia  | የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቢንያም ኔታንያሁ፣ እየጨመረ በመጣው ዓለም አቀፍ ጫና ውስጥ ሆነው የእስራኤልን አቋም ለዓለም ለማስረዳት በተባበሩት መንግሥታት (ተመድ) ጠቅላላ ጉባኤ ላይ ንግግር አደረጉ። ኔታንያሁ ወደ መድረኩ ሲወጡ የበርካታ ሀገራት ልዑካን አዳራሹን ለቀው የወጡ ሲሆን፣ ሌሎች ደግሞ በጭብጨባ ተቀብለዋቸዋል። ከእስራኤል ልዑካን ቡድንም «አም ይስራኤል ኻይ» የሚል፣ «የእስራኤል ሕዝብ በሕይወት ይኖራል» የሚል መፈክር ተሰምቷል። ኔታንያሁ ንግግራቸውን ሲጀምሩም አዳራሹን ለቀው ለወጡት ልዑካን «ሌሎች የሞራል ፈሪዎች ካሉ እባካችሁ አሁኑኑ ውጡ» ሲሉ ተናግረዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከ14 ዓመታት በፊት በተመድ የኢራንን የኑክሌር ፕሮግራም ለማስጠንቀቅ የቦምብ ምስል በማሳየት ቀይ መስመር ማስመራታቸውን አስታውሰዋል። «የኢራን አምባገነን መንግሥት አቶሚክ ቦምብ እንዳታደራጅ ለመከላከል ቃል ገብቼ ነበር፤ ያደረግኩትም በትክክል እሱን ነው» ብለዋል። የኢራንን የኑክሌር ፕሮግራም ማፍረስ «በጣም ከባድ» ቢሆንም፣ እንደ ጠቅላይ ሚኒስትር ካሳለፏቸው ውሳኔዎች ሁሉ ቀላሉ ውሳኔ እንደነበር ገልጸዋል። ኔታንያሁ እስራኤል ራሷን በመከላከል አዳራሹን ለቀው የወጡትን ሀገራት ጭምር እንደታደገች ገልጸው፣ የእነዚህ ሀገራት መሪዎች በግል እንደሚያመሰግኗቸው ተናግረዋል። ይህንንም «ዓለም አቀፍ ግብዝነት» ሲሉ ገልጸውታል። ለሶሪያው ፕሬዝዳንት አህመድ አል-ሻራዕ ምላሽ ሲሰጡም፣ አይሁዶች በጎላን ኮረብታዎች ላይ ከሙሴ ዘመን ጀምሮ ይኖሩ እንደነበር ጠቅሰው፣ ይህንንም በመጽሐፍ ቅዱስ ማረጋገጥ እንደሚቻል ተናግረዋል። እስራኤል ከአጠቃላይ የአረብ ምድር 0.3 በመቶ ብቻ የምትሸፍን ትንሽ ሀገር መሆኗን የጠቀሱት ኔታንያሁ፣ እስራኤልን «ቅኝ ገዥ» በማለት የሚቀርብባትን ክስ አጣጥለዋል። «ቅኝ ገዥነትን ፈጥረው ዓለምን በሙሉ የገዙት የእንግሊዝ እና የፈረንሳይ ሰዎች እኛን ይከሰናሉ» ብለዋል። በ1967 ዓ.ም. በተካሄደው ጦርነት ወቅት ወንድማቸውን ዮኒ ኔታንያሁን ለመጎብኘት ወደ ጦር ግንባር በሄዱበት ወቅት ወንድማቸው «እኛ እናሸንፋለን፤ ከዚህ ውጪ ሌላ አማራጭ የለንም» እንዳላቸው አስታውሰዋል። ይህ አባባል ዛሬም ለእስራኤል የሚሰራ መሆኑን የገለጹት ኔታንያሁ፣ ኦክቶበር 7 ቀን 2023 የእስራኤል ታሪክ «ጨለማው ቀን» እንደነበር ገልጸዋል። «ጠላቶቻችን እስራኤል ትወድቃለች ብለው አስበው ነበር፤ አልወደቅንም። ይልቁንም ተነስተን እንደ አንበሳ ተዋጋን» ብለዋል። እስራኤል ከአሜሪካ ጋር በመተባበር በበርካታ ግንባሮች መዋጋቷን የጠቀሱት ኔታንያሁ፣ በኢራን ላይ የተወሰዱ የጦር እርምጃዎችን፣ እንዲሁም ሐማስና ሂዝቦላህ ላይ የተወሰዱ ወታደራዊ እርምጃዎችን ጠቅሰዋል። በንግግራቸው ወቅት ፔጀር ከኪሳቸው በማውጣትም የሂዝቦላህ አባላት በ2024 በተካሄደው የፔጀር ፍንዳታ ጥቃት የተጎዱበትን ክስተት አስታውሰዋል። በይሁዳና ሰማሪያ የሚፈጸሙ የሽብር ጥቃቶች በዓለም አቀፍ ሚዲያ በቂ ሽፋን እንደማያገኙ የተናገሩት ኔታንያሁ፣ ዓለም አቀፍ ሚዲያዎች በአንዳንድ የሰፋሪዎች ጥቃት ላይ ከፍተኛ ትኩረት ሲሰጡ በሰላማዊ ሰዎች ላይ የሚፈጸሙ በሺዎች የሚቆጠሩ ጥቃቶችን ችላ እንደሚሉ ከሰዋል። «እኛ የሕግ ሀገር ነን፤ ሺን ቤትንም በእነሱ ላይ አሰማርተናል» ያሉት ኔታንያሁ፣ ይህንን የሚዲያ አቀራረብ «ትልቅ ማዛባት» ብለው ንግግራቸውን ደምድመዋል።

ይህ ቤተ ክርስቲያን በኢየሩሳሌም የሚገኝ ቤተ ክርስቲያን ሲሆን ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከተሰቀለ በኋላ የተቀበረበት፣ ከሞትም የተነሳበት ቦታ ላይ የተሰራ ቤተ ክርስቲያን ነው። @Hebrewethio
+1
ይህ ቤተ ክርስቲያን በኢየሩሳሌም የሚገኝ ቤተ ክርስቲያን ሲሆን ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከተሰቀለ በኋላ የተቀበረበት፣ ከሞትም የተነሳበት ቦታ ላይ የተሰራ ቤተ ክርስቲያን ነው። @Hebrewethio @Hebrewethio

የኢትዮጵያ ጎዳና በእስራኤል ቀደም ብሎ ''Abyssinian Street'' ወይም "Habashim Street'' ይባል ነበር። በ1968 የመንገዱ ስም ወደ ''Ethiopia Street'' ተቀየረ። ይህ
የኢትዮጵያ ጎዳና በእስራኤል ቀደም ብሎ ''Abyssinian Street'' ወይም "Habashim Street'' ይባል ነበር። በ1968 የመንገዱ ስም ወደ ''Ethiopia Street'' ተቀየረ። ይህ በኢየሩሳሌም የሚገኘው የኢትዮጵያ ጎዳና ''ቤተ እስራኤላውያን'' ኢትዮጵያውያንን ለማሰብ የተሰየመ መንገድ ነው። Ethiopia street in Jerusalem! @Hebrewethio @Hebrewethio

🇮🇱 ኤላት ከተማን ምን ለየት ያደርጋታል ? በእስራኤል ደቡባዊ ጫፍ በቀይ ባህር አጠገብ የምትገኘው ኤላት  Etzion Gaber ወደብ በሚል የቀድሞ ስያሜዋ ትታወቃለች። ይኽ ወደብ የሳባ ንግስት ንጉሥ ሰለሞንን ለመጎብኘት ስትመጣ የተጓዘችበት እንደነበር የታሪክ መዛግብት ያስረዳሉ። በከተማዋ የሚገኘው የሳባ ንግስት ሆቴል አንዱ የቱሪስት ማረፊያ ነው። ኤላትን ዮርዳኖስና ግብፅ ያዋስኗታል። ከተማዋ የበርካታ የባህር ዳርቻዎች፣ ምግብ ቤቶችና የመዝናኛ ስፍራዎች ባለቤት መኾኗ የቱሪስት ማዕከል አድርጓታል። ሌላው ለየት የሚያደርጋት በከተማዋ በርካታ እቃዎች ከቀረጥ ነጻ ግብይት ማድረግ መቻሉ ነው። ሻሎም🤍💙🇮🇱 @Hebrewethio @Hebrewethio

በ1929 በጀርመን ፍራንክፈርት የተወለደች የአይሁድ ቤተሰብ ልጅ ስትኾን በሁለተኛ ዓለም ጦርነት ወቅት ናዚዎች በአይሁዳውያን ላይ ያደረጉትን ስደት ለመሸሽ ከቤተሰቧ ጋር በአምስተርዳም በምስጢራዊ መደ
በ1929 በጀርመን ፍራንክፈርት የተወለደች የአይሁድ ቤተሰብ ልጅ ስትኾን በሁለተኛ ዓለም ጦርነት ወቅት ናዚዎች በአይሁዳውያን ላይ ያደረጉትን ስደት ለመሸሽ ከቤተሰቧ ጋር በአምስተርዳም በምስጢራዊ መደበቂያ አሳልፋለች። የእለትተእለት ሕይወቷን፣ ፍርሃቷን፣ ስሜቷን፣ ሕልሟን እና ለወደፊት ያላትን ተስፋ በደብተሯ ላይ ጽፋለች። ማስታወሻ ደብተሯ በኋላ ላይ የአና ማስታወሻ ተብሎ ታትሟል። የአሁኗን ሃያል ሀገር እስራኤል ለማየት ባትታደልም፤ በዘመኗ እስራኤላውያን ያሳለፉትን መከራ ለዓለም ማሳየት ችላለች። አና ፍራንክ💙🤍 @Hebrewethio @Hebrewethio

ሾፋር (Shofar — ሾ-ፋር ተብሎ የሚነበብ) ከበግ ወይም ከሌሎች ንጹሐን (ኮሸር) እንስሳት ቀንድ (እንደ ኩዱ ወይም ፍየል፣ ነገር ግን በፍጹም ከላም ቀንድ የማይሰራ) የሚዘጋጅ ጥንታዊ የሙዚቃ መ
ሾፋር (Shofar — ሾ-ፋር ተብሎ የሚነበብ) ከበግ ወይም ከሌሎች ንጹሐን (ኮሸር) እንስሳት ቀንድ (እንደ ኩዱ ወይም ፍየል፣ ነገር ግን በፍጹም ከላም ቀንድ የማይሰራ) የሚዘጋጅ ጥንታዊ የሙዚቃ መሣሪያ ነው። በአይሁድ እምነት እና ባህል ውስጥ ጥልቅ ሃይማኖታዊ እና ታሪካዊ ቦታ ያለው ሲሆን፣ ዛሬም ድረስ በጥቅም ላይ ከሚውሉ በጣም ጥንታዊ የትንፋሽ የሙዚቃ መሣሪያዎች አንዱ ነው። ሾፋር በይበልጥ የሚነፋው በሮሽ ሀሻና (የአይሁድ አዲስ ዓመት) በዓል ወቅት እና በዮም ኪፑር (የስርየት ቀን) ማጠቃለያ ላይ ነው። የሾፋርታላቅ እና ሹል ድምፅ ሰሚዎችን ከነፍስ ድካም እና መንፈሳዊ እንቅልፍ ለማንቃት፣ ራሳቸውን እንዲመረምሩ፣ ንስሐ እንዲገቡ እና ለሚመጣው አዲስ ዓመት ታድሰው እንዲዘጋጁ ለማድረግ የታለመ ነው። በጥንት ዘመን ሾፋር የጦርነት መጀመርን ለማብሰር (እንደ የኢያሪኮ ጦርነት)፣ የኢዮቤልዩ ዓመታትን ለማወጅ፣ የአዲስ ጨረቃ መውጣትን ለማሳወቅ እና የነገሥታትን ዘውድ መጫን ለማብሰር ይነፋ ነበር። በይበልጥ የበግ ቀንድ ጥቅም ላይ የሚውለው መጽሐፍ ቅዱሳዊውን የይስሐቅ መሥዋዕትነት ታሪክ (ኦሪት ዘፍጥረት 22) ለማሰብ ሲሆን፣ በዚያም እሾህ ውስጥ የተያዘው በግ በይስሐቅ ምትክ መሥዋዕት ሆኖ ቀርቧል። @Hebrewethio @Hebrewethio

🌼🌼🌼 2019 ዓ.ም 🌻🌻🌻 ለመላው ቤተሰቦቻችን በሙሉ መልካም የአዲስ ዓመት በዓል ይሁንላችሁ። አዲሱ ዓመት የሰላም፣ የፍቅር፣ የበረከት ይሁንላችሁ።🌼🌼🌼 @Hebrewethio @Hebrewethio

አጋም ቤርጌር '' Agam Berger'' ሐማስ October 7 በፈፀመው ጥቃት ታግተው ከተወሰዱ እስራኤላውያን መካከል አንዷ ናት። ከታገተች በኋላ ሐማስ እና የእስራኤል መንግሥት ባደረጉት የእስረኛ
አጋም ቤርጌር '' Agam Berger'' ሐማስ October 7 በፈፀመው ጥቃት ታግተው ከተወሰዱ እስራኤላውያን መካከል አንዷ ናት። ከታገተች በኋላ ሐማስ እና የእስራኤል መንግሥት ባደረጉት የእስረኛ ልውውጥ January 30/2025 ተለቃ ወደ ቤተሰቧ መመለስ ችላለች። የሚገርመው ነገር ዛሬ በዚህ ሰዓት አጋም ቤርጌርን ካገቷት የሐማስ ወታደሮች ውስጥ በሕይወት የሚገኘው አንዱ ብቻ ነው። IDF '' የእስራኤል መከላከያ ሃይል'' የአጋም ቤርጌርን አጋቾች የገቡበት ገብቶ አንድ በአንድ አስወግዷቸዋል። ትላንት አንዲት ወጣት እሥራኤላዊ አግተው ሲፎክሩ የነበሩትን የሐማስ ወንበዴዎች ዛሬ እስራኤል ለቅማ ጨርሳቸዋለች። በበረሃዎቿ ውስጥ ቀብራቸዋለች። ራሳቸውን በጭንብል ቢሸፍኑም ማንነታቸው ከእስራኤል የስለላ ቡድን ሊደበቅ አልቻለም። እስራኤል 💙🤍 @Hebrewethio @Hebrewethio

ሐይፋ ባሐይ ጋርደን Haifa, Bahai Garden የእስራኤልን ምድር ውበት ተመልከቱ! @Hebrewethio @Hebrewethio
ሐይፋ ባሐይ ጋርደን Haifa, Bahai Garden የእስራኤልን ምድር ውበት ተመልከቱ! @Hebrewethio @Hebrewethio

ሰላም ቤተሰብ 🫡 שלום משפחה ✡ ዛሬ በዕብራይስጥ ቋንቋ ትምሕርታችን በብዛት የምንጠቀምባቸውን ሐረጋት እንማራለን። 1. טוֹב, תּוֹדָה Tov, toda Good, thank you ጥሩ : አመሰግናለሁ። 2. אֲנִי בְּסֵדֶר Ani bseder I'm fine ደህና ነኝ። 3. תּוֹדָה רַבָּה Toda raba Thank you very much በጣም አመሰግናለሁ። 4. מָה שִׁמְךָ? Ma shimkha? What's your name? (to male) ስምህ ማነው? 5. מָה שְׁמֵךְ? Ma shmech? What's your name? (to female) ስምሽ ማን ነው? 6. שְׁמִי ... Shmi … My name is … ስሜ... 7. יֵשׁ לִי שְׁאֵלָה Yesh li sh’ela I have a question ጥያቄ አለኝ ለተጨማሪ የዕብራይስጥ ቋንቋ ትምህርት አብራችሁን ቆዩ። ✡ @Hebrewethio @Hebrewethio