ch
Feedback
M.O.R. Medium Tax Payers No 1 Branch Office

M.O.R. Medium Tax Payers No 1 Branch Office

前往频道在 Telegram

This is official Telegram Channel of M.o.R Medium Tax payers No 1 Branch office Join the channel

显示更多

📈 Telegram 频道 M.O.R. Medium Tax Payers No 1 Branch Office 的分析概览

频道 M.O.R. Medium Tax Payers No 1 Branch Office (@mormto1) 阿姆哈拉语 语言赛道中的 是活跃参与者。目前社区聚集了 18 147 名订阅者,在 经济与金融 类别中位列第 6 709,并在 埃塞俄比亚 地区排名第 1 922 位。

📊 受众指标与增长动态

自 невідомо 创建以来,项目保持高速增长,吸引了 18 147 名订阅者。

根据 01 十月, 2026 的最新数据,频道保持稳定运转。过去 30 天订阅人数变化为 78,过去 24 小时变化为 2,整体触达仍然可观。

  • 认证状态: 未认证
  • 互动率 (ER): 平均受众互动率为 32.61%。内容发布后 24 小时内通常能获得 16.29% 的反应,占订阅者总量。
  • 帖子覆盖: 每篇帖子平均可获得 5 919 次浏览,首日通常累积 2 957 次浏览。
  • 互动与反馈: 受众积极参与,单帖平均反应数为 0。

📝 描述与内容策略

作者将该频道定位为表达主观观点的平台:
“This is official Telegram Channel of M.o.R Medium Tax payers No 1 Branch office Join the channel”

凭借高频更新(最新数据采集于 02 十月, 2026),频道始终保持新鲜度与高覆盖。分析显示受众积极互动,使其成为 经济与金融 类别中的关键影响点。

18 147
订阅者
+224 小时
+57 天
+7830 天
帖子存档
ደረሰኝ_የመጣላቸው_ግብር_ከፋዮች_ዝርዝር_20_01_19.xlsx0.15 KB

ምዕራፍ ሁለት የምጁላር ስልጠና ተጠናቀቀ፡፡ መስከረም 21/2019 ዓ.ም በገቢዎች ሚኒስቴር በመካከለኛ ቁጥር-1 ግብር ከፋዮች ቅ/ጽ/ቤት ግብር ከፋዮችን በተከታታይነት በመሰረታዊ የታክስ ህጎችና አሠ
+3
ምዕራፍ ሁለት የምጁላር ስልጠና ተጠናቀቀ፡፡ መስከረም 21/2019 ዓ.ም በገቢዎች ሚኒስቴር በመካከለኛ ቁጥር-1 ግብር ከፋዮች ቅ/ጽ/ቤት ግብር ከፋዮችን በተከታታይነት በመሰረታዊ የታክስ ህጎችና አሠራሮች እንዲሁም አዋጆች ላይ ያላቸውን ግንዛቤ ለማሳደግ በማሰብ ለ26ኛ ዙር የምጁላር ስልጠና ተከታታዮች ሲሰጥ የቆየው ምዕራፍ ሁለት የሞጁላር ስልጠና በዛሬው ዕለት ተጠናቋል፡፡ ሥልጠናው ምዕራፍ ሁለት ቀጥተኛ ባልሆኑ ታክሶች በአዲሱ የተጨማሪ እሴት ታክስ አዋጅ ቁጥር 1341/2016፣ ኤክሳይዝ ታክስ፣ የቴምብር ቀረጥ እና በሱር ታክስ አስተዳደር ሥርዓት ዙሪያ በቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ የታክስ ከፋዮች መረጃ አቅርቦት ባለሙያ በሆኑት አቶ ዘዳግም ሲሳይ አማካኝነት ተሰጥቷል፡፡

Cash Register Mashine Yemigezu.xlsx12.18 MB

በተሻሻለው የፌደራል ታክስ አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 1434/2018 ላይ የሚሰጠው ስልጠና ተጠናክሮ ቀጥሏል፡፡ መስከረም 20/2019 ዓ/ም በገቢዎች ሚኒስቴር በመካከለኛ ቁ-1 ግብር ከፋዮች ቅርንጫፍ
+4
በተሻሻለው የፌደራል ታክስ አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 1434/2018 ላይ የሚሰጠው ስልጠና ተጠናክሮ ቀጥሏል፡፡ መስከረም 20/2019 ዓ/ም በገቢዎች ሚኒስቴር በመካከለኛ ቁ-1 ግብር ከፋዮች ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በተሻሻለው የፌደራል ታክስ አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 1434/2018 ላይ ለግብር ከፋዮች የሚሰጠው የአንድ ጊዜ ስልጠና ተጠናክሮ ቀጥሏል፡፡ የቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ የታክስ ከፋዮች ትምህርትና መረጃ አቅርቦት የሥራ ሂደት አስተባባሪ የሆኑት አቶ ተግባሩ ታምሩ እንደገለፁት፣ ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ግብር ከፋዮች በመሰረታዊ የታክስ ህጎችና አሰራሮች ያላቸውን ግንዛቤ በማስፋት ግብርን በፍቃደኝነት የመክፈል ባህላቸውን እንዲያሳድጉ እንዲሁም ባለማወቅ እንዳይቀጡ ለማድረግ በማሰብ በተለያዩ የሥልጠና አማራጮች ማለትም በመደበኛው የስልጠና መርሃ ግብር በሞጁላር እንዲሁም ስልጠናውን በአካል መጥተው መዉሰድ ላልቻሉ ግብር ከፋዮች በርቀት የስልጠና መርሃ ግብር እና ድርጅታቸው ያለበት ቦታ ድረስ በአካል በመሄድ የታክስ ህግ ዕዉቀቶችን ለሁሉም ግብር ከፋዮች ተደራሽ በማድረግ ረገድ መጠነ ሰፊ ሥራ እየሰራ እንደሆነ ገልፀዋል፡፡ አቶ ተግባሩ በተሻሻለው የፌደራል ታክስ አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 1434/2018 ላይ ስልጠናውን ሰጥተው ከሠልጣኞች በተነሱ ጥያቄዎች እና ሀሳቦች ዙሪያ ምላሽ ሰጥተዋል፡፡ በሌላ በኩል በስልጠና መርሃግብሩ ላይ የቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ የተቋማዊ ስጋት ስራ አመራር ሥነ-ምግባር ቡድን አስተባባሪ የሆኑት አቶ አበራ አምሳሉ ተገኝተው በግብር ከፋዮች መብትና ግዴታ ዙሪያ እንዲሁም በሥነ-ምግባር ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ሰጥተዋል።

የፌዴራል_ታክስ_አስተዳደር_ማሻሻያ_አዋጅ_ቁጥር_1434_2018_1.pdf7.73 MB

በቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ የሚሰጠው የሞጁላር ስልጠና ተጠናክሮ ቀጥሏል፡፡ መስከረም 19/2019 ዓ/ም በገቢዎች ሚኒስቴር በመካከለኛ ቁጥር-1 ግብር ከፋዮች ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ግብር ከፋዮችን በመሰረታዊ የታክ
+4
በቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ የሚሰጠው የሞጁላር ስልጠና ተጠናክሮ ቀጥሏል፡፡ መስከረም 19/2019 ዓ/ም በገቢዎች ሚኒስቴር በመካከለኛ ቁጥር-1 ግብር ከፋዮች ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ግብር ከፋዮችን በመሰረታዊ የታክስ ህጎችና አሠራሮች እንዲሁም አዋጆች ላይ ያላቸውን ግንዛቤ ለማሳደግ ታስቦ ለ26ኛ ዙር የምጁላር ስልጠና ተከታታዮች በክፍል ሁለት የሚሰጠው ስልጠና በዛሬው ዕለትም ተጠናክሮ ቀጥሏል፡፡ ስልጠናው በክፍል ሁለት ቀጥተኛ ባልሆኑ ታክሶች በአዲሱ የተጨማሪ እሴት ታክስ አዋጅ 1341/2016 እና የተጨማሪ እሴት ታክስ ደንብ ቁጥር 570/2017 ላይ በቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ የታክስ ከፋዮች ትምህርትና መረጃ አቅርቦት ከፍተኛ ባለሙያ በሆኑት አቶ ዘሪሁን ዉበቱ አማካኝነት ተሰጥቷል::

ደረሰኝ_የመጣላቸው_ግብር_ከፋዮች_ዝርዝር.xlsx0.16 KB

+3
module 4 new vat (2).pptx4.54 KB

በድርጅቶች የሚፈጸሙ ወንጀሎች መስከረም 18/2019 ዓ.ም (የገቢዎች ሚኒስቴር) በተሻሻለው የፌዴራል ታክስ አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 1434/2018 መሰረት የታክስ ህግን በመተላለፍ በድርጅቶች የሚፈጸ
በድርጅቶች የሚፈጸሙ ወንጀሎች መስከረም 18/2019 ዓ.ም (የገቢዎች ሚኒስቴር) በተሻሻለው የፌዴራል ታክስ አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 1434/2018 መሰረት የታክስ ህግን በመተላለፍ በድርጅቶች የሚፈጸሙ ወንጀሎችን በተመለከተ የሚከተለውን ይላል፡- የታክስ ህግን በመተላለፍ ወንጀል የፈጸመው ድርጅት ወይም የሕግ ሰውነት የተሰጠው በግለሰብ ባለቤትነት ሥራ ያለ የንግድ ሥራ በሚሆንበት ጊዜ ወንጀሉ በተፈጸመበት ወቅት የድርጅቱ ስራ አስኪያጅ፤ የፋይናንስ ኃላፊ ወይም በተመሳሳይ የኃላፊነት ቦታ ላይ ያለ ሰው ከታች የተዘረዘሩትን ማስረዳት ካልቻለ ወንጀሉን እንደፈጸመ ይቆጠራል። ስራ አስኪያጁ፤ የፋይናንስ ኃላፊው ወይም በተመሳስይ የኃላፊነት ቦታ ላይ ያለው ሰው የሚከተሉትን ያስረዳ እንደሆነ በወንጀሉ ተጠያቂ አይሆንም፦ 👉 ወንጀሉ የተፈጸመው ከርሱ እውቅና ውጪ መሆኑን፤ 👉 ወንጀሉ እንዳይፈጸም ያልፈቀደ፣ ያላዘዘ ወይንም ያልተባበረ መሆኑን፤ ወይም 👉 የዚህ አይነቱ ወንጀል እንዳይፈጸም መከላከል የሚያስችል ውስጥ ቁጥጥር ስርአት የዘረጋ መሆኑን፤

ለኢትዮጵያ ፖስታ አገልግሎት ድርጅት አመራርና ሠራተኞች ሲሰጥ የነበረው የሞጁላር ስልጠና ተጠናቀቀ፡፡ መስከረም 16/2019 ዓ/ም በገቢዎች ሚኒስቴር የመካከለኛ ቁጥር-1 ግብር ከፋዮች ቅርንጫፍ ጽ/ቤ
+1
ለኢትዮጵያ ፖስታ አገልግሎት ድርጅት አመራርና ሠራተኞች ሲሰጥ የነበረው የሞጁላር ስልጠና ተጠናቀቀ፡፡ መስከረም 16/2019 ዓ/ም በገቢዎች ሚኒስቴር የመካከለኛ ቁጥር-1 ግብር ከፋዮች ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የታክስ ከፋዮች ትምህርትና መረጃ አቅርቦት የስራ ሂደት አመራር እና ባለሙያዎች አማካኝነት ለኢትዮጵያ ፖስታ አገልግሎት ድርጅት አመራርና ሠራተኞች ከመስከረም 11/2019 ጀምሮ ሲሰጥ የነበረው የሞጁላር ስልጠና ተጠናቋል። ስልጠናው በክፍል አንድ ከመቀጠር የሚገኝ ገቢ እና የወጪ መጋራት፣ ከቤት ኪራይ እና ከንግድ ስራ ከሚገኝ ገቢ፣ ከተከፋይ ሂሳቦች ላይ ታክስ ቀንሶ ማስቀረት፣ በክፍል ሁለት ቀጥተኛ ባልሆኑ ታክሶች በአዲሱ የተጨማሪ እሴት ታክስ አዋጅ ቁጥር 1341/2016፣ ኤክሳይዝ ታክስ፣ የቴምብር ቀረጥ እና በሱር ታክስ አስተዳደር ሥርዓት እንዲሁም በክፍል ሶስት ታክስ ባልሆኑ ገቢዎች የታክስ ከፋይ ምዝገባ፣ ስረዛ እና ክሊራንስ አሰጣጥ፣ የታክስ ማስታወቂያዎች እና ቅጾች፣ ታክስንና ሌሎች ክፍያዎችን ስለመሰብሰብና ማስከፈል እንዲሁም የታክስ አስተዳደራዊ እና የወንጀል ቅጣቶች እና ተያያዥ ርዕሰ ጉዳዮች ዙሪያ ተሰጥቷል፡፡ በመጨረሻም የኢትዮጵያ ፖስታ አገልግሎት ድርጅት የሥልጠና ክፍል ኃላፊ የሆኑት ዶ/ር እንዳልካቸው አበበ ተገኝተው ከስልጠናው በርካታ የታክስ ህግ እውቀቶችንና አሰራሮችን እንዳገኙ ስልጠናውን ለሰጡ የመካከለኛ ቁጥር-1 ግብር ከፋዮች ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የታክስ ከፋዮች ትምህርትና መረጃ አቅርቦት የስራ ሂደት አመራርና ባለሙያዎች ምስጋናቸውን አቅርበዋል።