ch
Feedback
ስልክ መግዣና መሸጫ

ስልክ መግዣና መሸጫ

前往频道在 Telegram

ማንኛውም መሸጥ የምትፈልጉትን ስልክ እንገዛለን በ #0909255008 ወይም #0912739699 ላይ ያናግሩኝ @Abd_phone

显示更多

📈 Telegram 频道 ስልክ መግዣና መሸጫ 的分析概览

频道 ስልክ መግዣና መሸጫ (@jijiphone) 阿姆哈拉语 语言赛道中的 是活跃参与者。目前社区聚集了 51 738 名订阅者,在 技术与应用 类别中位列第 2 569,并在 埃塞俄比亚 地区排名第 614

📊 受众指标与增长动态

невідомо 创建以来,项目保持高速增长,吸引了 51 738 名订阅者。

根据 08 七月, 2026 的最新数据,频道保持稳定运转。过去 30 天订阅人数变化为 -1 595,过去 24 小时变化为 -68,整体触达仍然可观。

  • 认证状态: 未认证
  • 互动率 (ER): 平均受众互动率为 0.52%。内容发布后 24 小时内通常能获得 0.18% 的反应,占订阅者总量。
  • 帖子覆盖: 每篇帖子平均可获得 270 次浏览,首日通常累积 92 次浏览。
  • 互动与反馈: 受众积极参与,单帖平均反应数为 1

📝 描述与内容策略

作者将该频道定位为表达主观观点的平台:
ማንኛውም መሸጥ የምትፈልጉትን ስልክ እንገዛለን በ #0909255008 ወይም #0912739699 ላይ ያናግሩኝ @Abd_phone

凭借高频更新(最新数据采集于 09 七月, 2026),频道始终保持新鲜度与高覆盖。分析显示受众积极互动,使其成为 技术与应用 类别中的关键影响点。

51 738
订阅者
-6824 小时
-3197
-1 59530
帖子存档
🎁〰〰〰እዉነተኛ ታሪክ〰〰〰🎁   የታሪኩ ርዕስ 😢 #ፍቅር_እንዲህ_ነዉ_ወይ       🌀 #Part 2⃣ ✍ ፀሀፊ #አሚር_ሰይድ ............የደሀ ልጅ ፍቅር.............       10 ክፍል ፈተና ተፈተን ውጤቱ ሲመጣ ወደ ቀጣዩ ክፍል ማለፍ አልቻልኩም ምንም ማድረግ አይቻልም አላህ አላለውም፡፡ ቀጥታ ወደ ስራ እና ወደ ቂርአቴ አተኮርኩኝ፡፡ ጥሩ ጓደኞች ስላሉኝ በልጅነቴ ዲኔን እንዳዉቅ ሁኛለሁ ነብዩ ሙሀመድ ሰ.ዐ.ወ አልኢልሙ ፊሲገር ከነቅሺ አለል ሀጀር አልኢልሙ ፊልከቢር ከነቅሺ አለል ማእ ..እዉቀትን በልጅነት መማር በዲጋንይ ላይ እንደመቅረፅ ነዉ ካደጉ ትልቅ ከሆኑ መማር ደግሞ ዉሀ ላይ እንደመፃፍ ነዉ ብለዋል፡፡ ትልቅ ሁናችሁ ከመማር ተስፋ ሙቁረጥ ሳይሆን በልጅነት የተማሩት ግን ሁሌም አእምሮ ላይ ይቀራል ለማለት ነዉ፡፡  በልጅነቴ እስከ አስር እስከምማር እና ከአስር ስወድቅም የነበሩኝ ጓደኞች እንስገድ ቂርአት እንቅራ እነሀፍዝ የሚሉ ስለነበሩ ለኔ ሒወት መስመር መያዝ የጓደኞቼ ተፅእኖ ለኔ ጠቃሚ ነበር፡፡  ነቢዩ ሶ ዐ ወ እንዲህ ብለዋል ጥሩ ጓደኞች እንደ "ሚስክ" ነጋዴ ነው ባትገዛው እንኳን ከጥሩ ሽታው ትታወዳለህ መጥፎ ጓደኛ ደግሞ ልክ እንደ ወናፍ ነፊ ነው ከወናፍ ነፊ ጎን ከሆንክ እሳቱን ሲቀጣጠል ፍንጣሪው እየተረጨ ያቃጥልሃል       ጥሩ ጓደኛ በመልካም ባህሪው ሲማርክህ መጥፎ ጓደኛ ባህሪው ያስቀይመሃል ለስህተት ይጋብዘሃል ማለት ነው        ማትሪክ ውጤት ሲበላሽብኝ ብዙ ኢስላማዊ ህይወት ካሳለፍኩበት ምርጥ ጓደጮች ካፈራሁበት ብዙ ላይፍ ካሳለፍኩበት ለብዙ ዘመናት አዳሪ ሆኜ ቂርዐት ቀርቻለሁ፡፡ ከአዳሪ መርከዘል ፉርቃን ወጥቼ ወደ ዱኒያ አለም ብር የማገኝበት ሀሳብ መፈለግ ጀመርኩኝ ..... እናም ቀጣዩ ምእራፍ ወደ ሆነው የስራ አለም መግባት ግድ ሊለኝ ነው ለምን ቤተሰቦቼ በእድሜ የገፉ ለመጦር የደረሱ ናቸዉ ሲበዛ የድሃ ልጅ ነኝ፡፡     ግድ ቤተሰቦቼን ስራ እየሰራሁ የቤት አስቤዛ እንኳ ማሟላት አለብኝ፡፡    በፊት ተማሪ በነበርኩበት ጊዜ ከትምህርት ቤት እና ቂራአት መልስ ብየዳ( በረታ ብረት)  እየሰራሁ በሳምንት 20 ብር ይሰጡኛል ለእናቴ ሰጣታለሁ ይህን በማድረጌ ደስተኛ ሆነን ነበር የምንኖረዉ እናቴም ትመርቀኛለች      ሌሎቹ ወንድምና እህቶቸ አግብተው ህይወትን ይገፋሉ ፡፡ግን እነሱም እናት እና አባቴን የሚያግዙበት አቅም የላቸዉም ነበር፡፡ ዉጭ ሀገር ያለችዉ እህቴ አንዳንዴ ቢያንስ ከአራት ወር እየቆየች ብር ስትልክ ነዉ አንደንድ ነገሮች የምናሟላዉ፡፡     አባቴ በሰፈር ታዋቂ ጥሩ ሰዉ የሰዉ ሀቅ የማይነካ ታማኝ ነዉ.....በዚህም የተነሳ ሀብታም ጓደኞች ነበሩት....እናም የተወሰኑ የአባቴ ጓደኞች ለአባቴ ባጃጅ ገዝተው እየሰራህ ክፈል እዳህን ስትጨርስ ትጠቀልላለህ የሚል ሃሳብ አመጡ ......አባቴም እሽ ብሎ ተስማማ ለኔ ስራ ተፈጠረልኝ ቶሎ ብየ የባጃጅ መንጃ ፍቃድ አወጣሁኝ  የአባቴ ጓደኞችም በቃላቸዉም መሰረት ባጃጅ ገዝተዉ ሰጡን እዳችንን እኛም ልንከፍል ተነጋግረን ከዛ እዳዉን ስንጨርስ የቤተሰብ መተዳደሪያ ለማድረግ ተስማማን፡፡....     ግን ሹፍርና ለኔ የሚመጥን ሒወት አይደለም ነበር የህይወቴ ምስቅልቅል የሚጀምረው ሹፌር ከሆንኩበት ቀን ጀምሮ ነዉ፡፡፡      ሀርቡ እስከ 40.000 ህዝብ የሚኖርባት ትንሽ ከተማ ነች መኪና የሚሽከረከርበት አስፓልት መንገድ አንድ ብቻ ነው ጠዋት ተማሪው ወደ ትምህርት ሰራተኛው ወደስራ ሲሄድ ማታም ሲመለስ በዚያው መንገድ ነው እኔም የባጃጅ  ስራየን ጀምሪያለሁ፡፡     ግን  እያሽከረከርኩኝ ጠዋት እና ማታ በጎን የሚሄዱትን ተማሪወች መመልከት ጀመርኩ፡፡ አንገቴን ብደፋም ብሸሽም የሴቱ ብዛት ጭራሽ የቀራሁት ኪታብ ሊከለክለኝ አልቻልኩም፡፡ ወሎ መቼም በቁንጂና አይታማም ፡፡ ወሎ ከተባለ ሁሉም የቆንጆ ሀገር እና የኢስላም ሀይማኖት ተከታይ ያለበት ለዛዉም ለዲናቸዉ ጠንካራ የሆኑ ያሉበት ነዉ፡፡ ኢትዮጲያ ህዝብ ስልጡን የሚሆነዉ ወሎየ አስተሳሰብ ሲያስብ ነዉ ለምን ..የት ነህ ዘርህ ብሔርህ የማይባልበት ወሎ ላይ ነዉ...ወሎ ስትሄድ መታወቂያም ባትይዝ ሰዉ ሁነህ ብቻ ተገኝ .    ..ታዳ የወሎየዎች ዋና መዲና ደሴ ከተማ ስትሆን በዙሪያ ሀርቡን ከሚሴን ወልደያን ባቲን ራያን አፋርን ሳይንትን አረብዙ ሀገር አቅፋ በፍቅር ይዛለች፡፡    ሀርቡም አንዱ የወሎ ክፍል ስትሆን ትምህርት ቤት ሲገቡ እና ሲወጡ የሚያምሩ እንስቶች  አጃኢብ ያስብላል፡፡ እኔም ይሄ ወጣትነት እያስቸገረኝ ...በመመልከት ፍዝዝ እልና መልሼ አላህዋ ማረኝ እያልኩ አንገቴን እሰብራለሁ፡፡ ........በጊዜ ብዛት ባጃጄን አየነዳሁ የሆነች ልጅ ላይ አይኔ አረፈ ቆንጅየ ነች አንዴ ከትምህርት ስተወጣ  አይነ ለአይን ተገጣጠምን..... እኔም ደንግጬ ባላየ አለፍኩኝ፡፡ ከመሸ መንጋቱ አይቀርም ጨለማ ለብርሀን ቦታዋን ለቀቀች.. እኔም በጠዋት ተነስቼ ባጃጅ ይዤ መስራት ተያይዠዋለሁ፡፡    ትናንት አይን ለአይን የተያየነዉ ያቺነዉ ልጅ ትናንት ያየሇት ቦታ ጧት ደግሜ አየኋት....ከዛ ቀን ጀምሮ ቀን በቀን በመተያየት ብቻ የተወሰኑ ቀናቶች አለፉ ግን ደፍሬ በሙሉ አይኔ ማየት አልቻልኩም ፊለፊት አይን ለአይን ስንገጣጠም አንገቴን አቀረቅራለሁ ፡፡     ግን ይቺ  ልጅ ጋር ቀን በቀን ታየኛለች እኔም አያታለሁ የመተያየት ሱስ ያዘን...መቼም ሴት ልጅ አይደለች ሻፈድ ትልልኛለች..አይታኝ አንገቷን ትደፋ እና መልሳ ቀጥ ብላ ስታየኝ እንደመደንገጥ ትልና በጥርሷ ሳቅ ስትለኝ ...እኔም በደስታ እየነዳሁም ቢሆን ትዝ ትለኛለች ...ትምህርት ስትገባ እና ስትወጣ እሷን መከታተል እሷም ለእኔ ፈገግ ማለት ያስደስታታል፡፡       ማታ ተኝቸ ስለሷ ማሰብ ጀመርኩ ..ብቻየን አስባለሁ ለምን አልተዋወቃትም??? አልኩኝ ...እንደገና እንዴ እኔ ሴት ልተዋወቅ ኦሆሆሆሆ  ድፍረቱ እና  ልምዱ ከየት መጥቶ..... የሰፈር ሴቶች የጎረቤት ልጆች የአጎቴ የአክስቴ ልጆችን በመፍራት  ሰላም የማልል ልጅ እንዴት ብየ ነዉ ልጅቷን እንተዋወቅ ብየ በድፍረት የምጠይቃት ?? አላህ ይቅር ይበለኝ ብየ ብቻየን ሀሳብ ሳወርድ እንቅልፍ  ከዚህ ለብቻ ክርክር ገላገለኝ...እንቅልፍ ይዞኝ ሄደ ....ግን በእሷ መጨከን አቅቶኛል ምን እንደማደርግ  አላውቅም፡፡     ነጋና ስራየን ቀጠልኩ አስታውሳለሁ ትምህርት ከጧት ነበረች 6፡30 ተለቀቁ ስትሄድም ስትመጣም ጓደኞቿ ጋር ናት ግን ጓደኞቿ ጋር ብትሆንም እኔ ጋር በሩቁ እንግባባለን ልባችን ሁለታችንም መቀራረብን ይፈልጋል..... ከርቀት ትታየኛለች እኔም አያታለሁ  ምን ላድርግ ??? እያልኩ ብቻየን ሁኜ ባጃጄ ዉስጥ ሁኜ ተወዛገብኩኝ፡፡ አንዳንዴ የምወስነዉ ግራ ሲገባህ ከጎንህ ለጊዜዉ የምታማክረዉ ልብህን ነዉ .....ጥያቄዉን ወደ ልቤ ወሰድኩት .....,ልቤም ከድሬ ለምን ትፈራለህ ወንድ ልጅ ነህ ደፈር በል  ጥቀሳት እና ይለይልህ መቼ ድረስ በአይን ተያይታችሁ .... የልጅቷን ሁኔታ ተመልከታት ሲለኝ ይሰማኛል ድምፅም ባያወጣም....... ከዛም ልጅቷን ጠቀስኳት..... #part 3⃣ @Sweet_Fikir @Sweet_Fikir

በእውነተኛ ታሪክ ላይ የተመሰረተ #ፍቅር_እንዲህ_ነዉ_ወይ አዲስ የፍቅር ታሪክ በየቀኑ የሚቀርብ መሳጭ ፣ ልብ አንጠልጣይ ታሪክ ክፍል 2 ዛሬ ምሽት 3:30 ላይ ይጠብቁን። @Sweet_Fikir @Sw
በእውነተኛ ታሪክ ላይ የተመሰረተ #ፍቅር_እንዲህ_ነዉ_ወይ አዲስ የፍቅር ታሪክ በየቀኑ የሚቀርብ መሳጭ ፣ ልብ አንጠልጣይ ታሪክ ክፍል 2 ዛሬ ምሽት 3:30 ላይ ይጠብቁን። @Sweet_Fikir @Sweet_Fikir

ልብ አንጠልጣይ #በኢስላማዊ አደብ የተዋዛ የፍቅር ታሪኮችን እንደጉድ የሚያገኙበት ብቸኛው ቻናል join አድርገው ይቀላቀሉ!
ልብ አንጠልጣይ #በኢስላማዊ አደብ የተዋዛ የፍቅር ታሪኮችን እንደጉድ የሚያገኙበት ብቸኛው ቻናል join አድርገው ይቀላቀሉ!

🚫::::::::ድንግል/ቢክራ አላገኘዉባትም::::::🚫 ሰውየው ልጅ አገረድ አግብቶ ድንግል ሁና ካላገኛት ምን ማድረግ ነው ያለበት ? ይሄ ብዙ ምክኒያቶች ይኖሩታል ድንግሏ ምናልባት.........Read more ሀቂቃ  ውሸት አይደለም ገብታቹ አንብቡት

🎁〰〰〰እዉነተኛ ታሪክ〰〰〰🎁   የታሪኩ ርዕስ 😢 #ፍቅር_እንዲህ_ነዉ_ወይ???       🌀 #Part 1⃣ ✍ ፀሀፊ #አሚር_ሰይድ      ፍቅር ....ፍቅር ማለት ምን ማለት ነዉ ??? ማንኛችንም ስለፍቅር ስንጠየቅ መልሳችን ሀሳባችንን መግለፅ አንችልም ...ፍቅርን ብዙ ጊዜ ተጠያቂዉ ፍቅርን ግለፅ ሲባል ሊገልፀዉ የማይችል ግዑዝ ነገር ነዉ፡፡ አንድ ሰዉ አፈቅርሻለሁ ወይም አፈቅርሀለሁ የሚባለዉን ድምፅ ከሌላ ሰዉ ሲሰማ ከበፊቱ ካለበት አንድ ደስታ ይጨምራል ...ግን አፈቅርሻለሁ ያለዉ ሰዉ...ፍቅር ምንድን ነዉ ብለህ ስጠይቀዉ እንጃ ስለፍቅር መግለፅ አልችልም ሲሉ ይደመጣሉ፡፡ ለመናገር ቀላል የሆነ ለመግለፅ ግን የከበደ ፍቅር ትርጉሙ ምንድን ነዉ ??? ትርጉም አልባ መልስ ያስተናግዳል፡፡      ስለፍቅር እናንተ ምን አመለካከት አላችሁ???ፍቅር ማለት ዛሬ ተዋወቁ ነገ ተዋደዱ ከዛ ተጣሉ ..ከዛም አለቀሰ አለቀሰች ታረቁ ..ከዛስ............ይቀጥላል ሆነ ነገሩ፡፡ ፍቅርን በአፍህ መግለፅ ካልቻልክ መግለፅ ያልቻልከዉ ሶስት ፊደላት አሉ እነሱም ፍ...ቅ.....ር አይነቱ ይለያይ እንጂ በማንኛዉም ሰዉ ዉስጥ ያለ ነገር ነዉ ...ነገር ግን የፍቅር አይነቶች የተለያዩ ናቸዉ ፍቅርን በሰዉ ልጅ ብቻ ማመሳሰል አይቻልም፡፡    ግን .ፍቅር ማለት ምን ማለት ነዉ??? እኔም ትርጉሙ ይጠፋኛል ፡፡ከፍቅር ሁሉ ከባድ ግን የወደዱትን ሰዉ ለራስ እንደማይሆን ለእሱ መስዋአትነት ከፍለን የሌላ እንደመሆን የሚያሳዝን የለም፡፡ ወንድ ልጅ ፍቅሩ ከላይ ነዉ የሚሉ ወገኖች አሉ ..የወንድ ልጅ ፍቅር ግን እስከ ጥግ እንደሚሄድ እና ወንድ ልጅ ባህሪዉ ሴትን የማያምንበት ምክንያት መጀመሪያ በሴት ልጅ ፈተና ተለክፎ ሁኖ ሊሆን ይችላል  .......     ግን ይሄ ትርጉሙን በአፋችን መግለፅ የማንችለዉ ፍቅር የሚለዉ አንድ መልስ አለዉ መልሱም....የመጀመሪያዉ ፍቅርን ካመጣዉ ..ፍቅር የሚባልን በሰዉ ልጅ ላይ ካስቀመጠዉ ..ከፈጣሪህ ከአላህ ፍቅር ስጀምር...ምንም ፍቅር የሚባል ቢመጣብህ ከፈጣሪህ ፍቅር በላይ እንደማይሆን 100% እርግጠኛ ሁን(ኚ)      ታሪኬን ከስሜ ልጀመር ከድር መሀመድ አህመድ ይባላል የተወለድኩት ደቡብ ወሎ ሀርቡ ከተማ ነዉ፡፡ ቀጠን ብየ በባህሪም በመልክም ሸጋ የሆንኩ ልጅ ነኝ ... የቤተሰቦቼ አኗኗር በጣም ድሆች ስንሆን ግን በቀዷ እና ቀድር የምናምን በአለን ተብቃቅተን የምናድርD ነን፡፡ የምንኖረው መንግስት በሰጠን በቀበሌ ቤት ነው፡፡ አባቴ ስራ አይሰራም .... እናቴም ብትሆን እድሜዋ ከ 60-70 ይደርሳል፡፡ታላቅም ታናሽም ወንድሞች አሉኝ፡፡   ሀርቡ ከተማ ለደሴ ደግሞ የ 20 ብር ትራንስፖርት ሲሆን ርቀቱ 40 ኪ.ሜ ገደማ ነው ወደ ኋላ ስንመላስ የሀፊዞች የጀግኖች ሀገር ከሚሴ ታዋስነናለች ርቀቱ 30 ኪ.ሜ ሲሆን ለአዲስ አበባ ደግሞ 345 ኪ.ሜ ርቀት ላይ ትገኛለች፡፡      ሀርቡ የአየሯ ፀባይ ወይና ደጋ ነው ለአኗኗር በጣም ይመቻል ..በተጨማሪም ሀርቡ የሸንኮራ አገዳ''ወደ አዲስ አበባ ወደ  አፋር ትልካለች፣የቦርከናን ወንዝ በአግባቡ መጠቀም ቢያቅታትም የአትክልት ና የፍራፍሬ ከተማ ናት። ''ሀርቡ ሌላ አንድ የተፈጥሮ ሀብት አለት።በከሀርቡ ከተማ  በግምት 8,ኪሜ ርቀት ላይ የሚገኝ ፍልዉሀ አላት ፍሉሀውን የውጭ ሀገር ዜጎች ሳይቀር እየመጡ ህመማቸውን''ይፈወሱበታል፡፡     እድሚየ ሲደርስ እንደማንኛዉም ተማሪ የተማርኩ ሲሆን፡፡ የትምህርት ቤት ህይወቴ ብዙም ትኩረት የለኝም ነበር  :: .ከ1 እስከ 8 ሀርቡ አጠቃላይ አንደኛ ደረጃ ሲሆን 9 እና 10 ደግሞ ሀርቡ አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ነዉ፡፡    የአላህ ፈቃድ ሁኖ ወደ ዲን አለም የገባሁት በልጅነቴ ነበር..አባቴ ዲኔን እንድይዝ እንጂ ብዙም ለአካዳሚክ ትምህርት ትኩረት የለዉም ነበር.... ገና የሶስተኛ ክፍል ተማሪ ሁኜ ቁርዐን አክትሚያለሁ፡፡ ከዛም በየደረጃወ ኪታብ እየቀራሁ አደኩኝ፡፡ የፊቂህ ደርስም ቢሆን የሻፊኢን መዝሃብ ሰፊና ሹጃአ ባፈድል እያልኩኝ .... ሶርፍ ጀመሬ ነው የትውኩት .....     ቁርዐን ተፍሲርም  ጓደኛየ ጋር አብሬ ቀርቻለሁ፡፡ ሃዲስ እንቀራለን ኡሱሉ ሰላሳ ,,ኪታቡ ተውሂድ,, አርባ ሃዲስ ,,ቡልገል መራም ,,ሪያዱ ሷሊህ ,,ተጅሪድ ኢብነ ማጅህ እና ቡኻሪና ሙስሊም ቀርተናል .....ተርቢያ የሚያደርገን ደግሞ የመስጅዳችን ሙአዚን ጀማል ዩሱፍ ይባላል ጎልማሳ ወጣት ነው እሱ ቂርዐት የቀራው ገጠር ተቸግሮ እንደሆነና እኛ ከተማ እየኖርን ትምህርት እየተማርን በትርፍ ጊዜያችን ካልቀራን በአላህ ዘንድ እንደምንጠየቅ ይመክረናል ዳእዋ እንድናደርግ ይጎተጉተናል አረብኛ እንድንጽፍ የዳእዋ ኖት ራሳችን ከኪታብ አውጣተን እንድናዘጋጅ ያስተምረናል ያዘጋጀነውን ያርምልናል::      ወንበር ላይ ያስቀምጠንና ከፊታችን ድንጋይ ደርድሮ ድንጋዩ ሰው እንደሆነ አስቡት ከዚያ ዳእዋ ማድረግ ጀምሩ ይለናል ብቻ ዳኢወች ሆንን ለመጀመሪያ ጊዜ ዳዕዋ ለማድረግ መስጅድ ስቆም አስታውሳለሁ ከፈጂር ሶላት በኋላ ነበር እጥር ምጥን ያለ ከ 5 ደቂቃ አትበልጥም ግን የመጀመሪያየ ሆኖም እየፈራሁ ያደረኩት ዳእዋ ሰውን በእንባ አራጨው ስጨርስም ብዙወቹ ማሻአላህ እያሉ ግንባሬን ይስሙኝ ነበር .......ይህን ሳደርግ እድሜየ ገና 17 ነበር ታዲያ በዚህ ኡስታዝ ተርቢያ እየተደረግን ማን ይቻለን ለኢስላም ፍቅሩ አደረብን መስጊድ የማይመጡ ቁርአን ያልቀሩትን ማበረታታት ተያይዘንዋል፡፡ ቅዳሜና እሁድ በረፍት ጊዜያችን ሪህላ በየሰፈሩ ቤት እየቆረቆርን ዳእዋ እናደርጋለን      አስታውሰዋለሁ አሪፍ ጊዜ ነበር ትምህርት ቤት በእረፍት ሰአት ዳእዋ ፕሮግራም ይዘን ከጓደኛየ ኑረዲን ጋር እየተቀያየርን ዳእዋ እናደርጋለን ኑረዲን ከእኔ በእድሜ ከፍ ይላል ሰለምቴ ነው የድሮ ስሙ ኤፍሬም ይባላል፡፡ ሴት ወንዱ ሙስሊም ክርስቲያኑ የትምህርት ቤት መስገጃ ቦታ ተሰባስቦ ዳእዋችንን ይሰሙ ነበር ሱሪ የለበሱ ክርስቲያን ሴቶች ሳይቀሩ ይታደማሉ ዳእዋው ሲያስለቅስ አብረው ያለቅሳሉ ምን አይነት አሪፍ ጊዜ ነበር ታዲያ በዚያን ጊዜ ፍቅር የማይታሰብ ነው፡፡     አስታውሳለሁ ከትምህርት ቤት ስለቀቅ ከኛ ሰፈር በታች አዚዛ የምትባል ልጅ ልትተዋወቀኝ ፈልጋ አዚዛ እባላለሁ ስትለኝ ከክላስ የሮጥኩኝ ቤቴ ገባሁ፡፡ ላየኝ ሰዉ የመቶ ሜትር እሯጭ ወይም የማራቶን ተወዳዳሪ ነበር የምመስለዉ፡፡ መቅሰፍት የወረደብኝ እስኪመስለኝ ሴቶች አሰላሙ አለይኩም ቢሉኝ እንኳ ላብ በላብ ነበር የምሆነዉ፡፡ ሴት ጋር ወሬ ቀጥ ብሎ ማየት በጭራሽ አይታሰብም ፡፡ ቂራአትና ዳእዋ ትምህርት ብቻ ነበር እንቅስቃሴያችን    አልሃምዱሊላህ ይህ ሁሉ የአላህ ጸጋ ነው ኡስታዝ ጀማልንም ሳላመሰግነው አላልፍም አብሶ አንድ ጊዜ ረመዳን ወር ላይ በ 27 ኛው ለይል ታላላቅ ኡለሞች ሳይቀር ዳእዋ ለማድረግ ፈልገው ሲቋምጡ ዛሬ ተረኛው ከድር ነው ብሎ ሚንበሩ ላይ እጀን ይዞ ያስቀመጠኝን አልረሳውም፡፡ እንደዚህ አይነት የአኼራ ወንድም የትም አይገኝም ብዙ ነገር በህይወቴ አበርክቶልኛል    እሁድ ረፋድ ላይና ጅሙአ ከመግሪብ በኋላ መስጅድ ዳእዋ ፕሮግራም ይዞልኝ አደርግም ነበር ሁልጊዜ ለአላህ ብየ ስወደው እኖራለሁ፡፡ ከቂርአቴም ጎን ትምህርቴንም እየተማርኩ ነዉ 10 ኛ ክፍል ማትሪክ ተፈተን ውጤቱ ሲመጣ ግን .... #part ➋ይቀጥላል 👇👇👇 @Sweet_Fikir @Sweet_Fikir

ዛሬ ምሽት ይጀምራል👌
ዛሬ ምሽት ይጀምራል👌

እንደ ሌሎች Airdrop Listing date ምናምን አትጠብቁም እራሱ Telegram ነው ያመጣው.... Bot Verify የተደረገ ነው Telegram wallet Connect አድርጉ በTelegram star የተለያዩ ነገሮችን Telegram ላይ መግዛት ትችላላችሁ ምሳሌ (Telegram premium) ... https://t.me/major/start?startapp=1349220473 https://t.me/major/start?startapp=1349220473

እንደ ሌሎች Airdrop Listing date ምናምን አትጠብቁም እራሱ Telegram ነው ያመጣው.... Bot Verify የተደረገ ነው Telegram wallet Connect አድርጉ በTelegram star የተለያዩ ነገሮችን Telegram ላይ መግዛት ትችላላችሁ ምሳሌ (Telegram premium) ... https://t.me/major/start?startapp=1349220473 https://t.me/major/start?startapp=1349220473

እንደ ሌሎች Airdrop Listing date ምናምን አትጠብቁም 🎊🎊🎊 እራሱ Telegram ነው ያመጣው.... Bot Verify የተደረገ ነው Telegram wallet Connect አድርጉ  በTelegram star የተለያዩ ነገሮችን Telegram ላይ መግዛት ትችላላችሁ ምሳሌ ( Telegram premium) ... https://t.me/major/start?startapp=1753715732 https://t.me/major/start?startapp=1753715732

✅ አሁን online ላላችሁ ብቻ ጥያቄና መልስ ውድድር ልንጀምር ነው❗️ 1️⃣ ለወጣ 100 ብር ካርድ 2️⃣ ለወጣ 50 ብር ካርድ 3️⃣ ለወጣ 25 ብር ካርድ 👉 ዝግጁ ከሆናችሁ ጀምር የሚለውን ይጫኑ።👇

😋የጠበሳ ዘዴዎች ለወንድም ለሴትም 👌🤦‍♀ሴቶች ደፍረዉ የማይናገሩት ግን ከወንዶች🤷‍♂ የሚጠብቋቸዉ 7 ነገሮች❤️❤️ ⬜️⬜️OPEN⬜️⬜️
😋የጠበሳ ዘዴዎች ለወንድም ለሴትም 👌🤦‍♀ሴቶች ደፍረዉ የማይናገሩት ግን ከወንዶች🤷‍♂ የሚጠብቋቸዉ 7 ነገሮች❤️❤️            ⬜️⬜️OPEN⬜️⬜️

ቤቲንግ ይጫወታሉ መበላትስ ሰልችቶታል እንግዲህያዉንሱ በነፃ ያለምንም ክፍያ በቀን ከ 30-45 odd የሚለቀቅበት ቻናል ልጠቁማቹ ይጠቀሙበታል ይቀላቀሉ👇👇👇

🔞🔞🔞🔞ከ 18 አመት በታች ለሆናችሁ የተከለከለ ነው!🔞🔞🔞🔞
🔞🔞🔞🔞ከ 18 አመት በታች ለሆናችሁ የተከለከለ ነው!🔞🔞🔞🔞

❤ ️የተወለዱበትን ወር ቶሎ ይምረጡ እና በ Zodiac ሳይንስ ስለራስዎ በደንብ ይወቁ😍😍😍 የፍቅር ሁኔታዎንም ይጠቁማል 👏 100% ትክክል የሆነ
❤ ️የተወለዱበትን ወር ቶሎ ይምረጡ እና በ Zodiac ሳይንስ ስለራስዎ በደንብ ይወቁ😍😍😍 የፍቅር ሁኔታዎንም ይጠቁማል 👏 100% ትክክል የሆነ

🔴 ሰበር ዜና ዛሬ ትምህርት ሚኒሰትር ያወጣው አዲስ ያልተጠበቀ መግለጫ   ‼️ ሙሉ መግለጫውን ለማንበብ ከስር open ሚለውን ይጫኑ 👇👇

እድሜዎ ስንት ነው?
እድሜዎ ስንት ነው?

◇አክሽን ◇የጦርነት ◇የጫካ ◇የወንጀል እንዲሁም የፍቅር ፊልም ሚመችክ ከሆነ አሁኑኑ JOIN በለው ይሄ ቻናል ምርጥ ምርጥ ፊልሞችን በጥራትና በፍጥነት ያሳያል። Join 👇 https://t.me/ad
◇አክሽን ◇የጦርነት ◇የጫካ ◇የወንጀል  እንዲሁም የፍቅር ፊልም ሚመችክ ከሆነ አሁኑኑ JOIN  በለው  ይሄ ቻናል ምርጥ ምርጥ  ፊልሞችን በጥራትና በፍጥነት ያሳያል።  Join 👇 https://t.me/addlist/hsmi4bjCNuRhMTNk https://t.me/addlist/hsmi4bjCNuRhMTNk

ቤቲንግ ይጫወታሉ መበላትስ ሰልችቶታል እንግዲህያዉንሱ በነፃ ያለምንም ክፍያ በቀን ከ 30-45 odd የሚለቀቅበት ቻናል ልጠቁማቹ ይጠቀሙበታል ይቀላቀሉ👇👇👇

✅ አሁን online ላላችሁ ብቻ ጥያቄና መልስ ውድድር ልንጀምር ነው❗️ 1️⃣ ለወጣ 100 ብር ካርድ 2️⃣ ለወጣ 50 ብር ካርድ 3️⃣ ለወጣ 25 ብር ካርድ 👉 ዝግጁ ከሆናችሁ ጀምር የሚለውን ይጫኑ።👇

የተወለዱበትን ወር በመምረጥ ኮከቦን ይመልከቱ
የተወለዱበትን ወር በመምረጥ ኮከቦን ይመልከቱ