1 357
订阅者
-424 小时
-137 天
-8830 天
帖子存档
1 357
በሰሙነ ሕማማት ዕለተ ዓርብ የስቅለቱ መታሰቢያ ነው፡፡ ምእመናን በሰሙነ ሕማማት የሠሩትን ኃጢአት ይናዘዛሉ፡፡ ካህናቱም በወይራ ቅጠል ትከሻቸወን እየጠበጠቡ ቀን ከሰገዱት በተጨማሪ ሌላ ስግደት ያዟቸዋል፡፡ ጥብጠባው የተግሣጽ ምሳሌ ነው፡፡
••
ጥብጣብ የሚደረግለት ሰው በሕማማቱ ወቅት የፈጸመው በደል ወይንም ኃጢአት ካለ ይህንኑ በመናገር የስግደቱ ቍጥር ከፍ እንዲል ይደረጋል፡፡ ይህ በስቅለት ቀን የሚፈጸም ሥርዓት ሲሆን፣ ጠብጣቤ ማለት ቸብ ቸብ ማድረግ ማለት ነው፡፡ ሕዝበ ክርስቲያኑ በዕለተ ስቅለት ሲሰግድ ፣ ሲጸልይ ፣ መጻሕፍትን ሲያነብ ከዋለ በኋላ ሰርሆተ ሕዝብ / የሕዝብ መሰነባበቻ / ከመሆኑ በፊት በወይራ ቅጠል የእያንዳንዱ ምእመን ጀርባ ቸብ ቸብ መደረጉ ፣ የጌታን ግርፋት ያስታውሳል፡፡
现已上线!2025 年 Telegram 研究 — 年度关键洞察 
