ሰዋስው ☘☘☘☘
前往频道在 Telegram
በሰዋስወ ብርሀን ቅዱስ ዻውሎስ ገዳም እና ለተለያዩ ቤተክርስቲያን ለክብረ በአላት ማውጫ ። በተጨማሪም-ዋዜማ ሥርዓተ ማኅሌት - መዝሙራት ስንክሳር - የየእለቱን ምስባክ ቅኔያት ጥያቄዎች እንዲሁም የወቅታዊ ነገር መወያያ በተጨማሪም @eotcww ብለው ይቀላቀሉን ለወዳጅ ዘመድዎ share#Share#Share# ያድርጉ።
显示更多1 161
订阅者
无数据24 小时
无数据7 天
无数据30 天
帖子存档
1 161
#ዘየሀይድ አይነ
ዘየሀይድ አይነ/2/ ልብሰ ክብር ለቢሶ ዳዊት/2/
ቅድመ ታቦተ ህግ ኃለየ ቅድመ ታቦተ ህግ/2/
#ትርጉም:
ንጉስ ዳዊት ዓይንን የሚንፀባረቅ የክብር ልብስ ለብሶ ከሕግ ታቦት ፊት አመሰገነ
ለመቀላቀል_ሰማያዊውን_ይጫኑ
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
★ https://t.me/Eotcw
1 161
#ጽላት ዘሙሴ
ጽላት ዘሙሴ ዕፀ ጳጦስ ዘሲና
ጸናጽል ዘውስተ ልብሱ ለአሮን ካህን
ለመቀላቀል_ሰማያዊውን_ይጫኑ
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
★ https://t.me/Eotcw
1 161
ሶበ ተዘከርናሃ ለጽዮን
ሶበ ተዘከርናሃ ለጽዮን
ሶበ ተዘከርናሃ ለፅዮን
ውስተ አፍላገ ባቢሎን
ህየ ነበርነ ወበከይነ
እንዚራቲነ ሰቀልነ ውስተ ጒዓቲሃ
ባሰብናት ጊዜ ጽዮንን
ባሰብናት ጊዜ ጽዮንን
በባቢሎን ወንዞች አጠገብ
ተቀምጠን አለቀስን
መሰንቆዋችንን ሰቀልን በዛፎቿ ላይ
====#አዝማች====
ፅኑ መከራን ተቀበልን ተጨነቅን በፈተና
የደዌ ሞት በላያችን እንደዝናብ ወርዶዋልና
አህዛብም ዘበቱብን እንዲ ብለው በየተራ
ዘምሩለት ላምላካቹ ቢያድናቹ ከመከራ
እግዚአብሔር ፅዮንን በመንግስቱ መርጧታል እና
ማደሪያው ትሆነው ዘንድ ወዷታል እና
ፅዮን ሆይ እናታችን ቅድስት ድንግል ማርያም
ፅዮን ሆይ እናታችን ቅድስት ቤተ ክርስቲያን
አንቺን ብንረሳ ቀኛችን ትርሳን
=====#አዝማች ====
የማረኩን በጦራቸውበኃይላቸው የተመኩ
በጽዮን ደጅ ያለፍርሃት የጽዮንን ክብሯን ነኩ
ይህን ያየ ከላይ ሆኖ በደመና ተሸፍኖ
ባቢሎንን አሻገረ የማረኩንን በትኖ
እግዚአብሔር ፅዮንን በመንግስቱ መርጧታል እና
ማደሪያው ትሆነው ዘንድ ወዷታል እና
ፅዮን ሆይ እናታችን ቅድስት ድንግል ማርያም
ፅዮን ሆይ እናታችን ቅድስት ቤተ ክርስቲያን
አንቺን ብንረሳ ቀኛችን ትርሳን
====#አዝማች#===
ስጋችንን ሊገንዘን የሞት ጥላ ቢያጠላም
እናልፋለን ሁሉን ባንቺ
የአምላክ እናት ድንግል ማርያም
ቅድስት ሆይ ከባረክሽን
እንድናለን ከደወዌያችን
ለስጋና ለነብሳችን መድኃኒት ነሽ እናታችን
እግዚአብሔር ፅዮንን በመንግስቱ መርጧታል እና
ማደሪያው ትሆነው ዘንድ ወዷታል እና
ፅዮን ሆይ እናታችን ቅድስት ድንግል ማርያም
ፅዮን ሆይ እናታችን ቅድስት ቤተ ክርስቲያን
አንቺን ብንረሳ ቀኛችን ትርሳን
የመጋቤ ምሥጢር ሰሎሞን ተስፋዬ
💚 https://t.me/Eotcw
1 161
“መልካም ያደረጉ ብዙ ሴቶች አሉ አንቺ ግን ከሁሉ ትበልጫለሽ፡፡” ምሳ. 31፡29
ክርስቶስን ያከበሩ፤ መንገዱን የተከተሉ ብዙ ሴቶች አሉ፤ እውነትን የመሰከሩ፤ ስለ ቃሉ የኖሩ ብዙ ሴቶች አሉ፤ መስዋዕትነትን የከፈሉ በሰማዕትነት ያለፉ ብዙ ሴቶች አሉ፤ ታላላቅ የምድር ነገስታትን፤ ታላላቅ ነቢያትን የወለዱ ብዙ ሴቶች አሉ፤ ከነዚህ ሁሉ ግን አንቺ ትበልጫለሽ፡፡
ቅድስት ድንግል ሆይ አንቺ እኮ፡- ሰማይ ዙፋኑ ምድር መረገጫው የሆነ፤ ድንቅ መካር ኃያል አምላክ የሰላም አለቃ፤ ሁሉ በእርሱ የሆነ ከሆነውም አንዳችም እንኳን ያለርሱ ያልሆነ፤ ዓለምን ሁሉ ከሞት ወደ ሕይወት የመለሰ፤ መንበሩን የሚሸከሙ ኪሩቤልና ሱራፌል የሚንቀጠቀጡለት፤ የሁሉ ፈጣሪ፤ የሁሉ አምላክ እናት ነሽ፡፡
በፊትም አሁንም ወደፊትም ካንቺ በቀር ፈጣሪዋን ልጄ ብላ የምትጠራ ሴት አልነበረችም፤ የለችም፤ አትኖርምም ክርስቶስም እናቴ ብሎ የሚጠራት ብቸኛዋ ሴት አንቺ ነሽ በእውነት ከሁሉ ትበልጫለሽ፡፡
እናት ስትሆኝ ድንግል፤ ድንግል ስትሆኝ እናት በእውነት ከሁሉ ትበልጫለሽ፡፡ ትውልድ ሁሉ ብጽዕት ብሎ የሚጠራሽ ብቸኛዋ ሴት በእውነት ከሁሉ ትበልጫለሽ፡፡
እግዚአብሔር መርጦና ጠብቆ ያስቀረሽ ዘር በእውነት ከሁሉ ትበልጫለሽ፡፡ ለዓለም ሁሉ ድህነት ምልክት የሆንሽ በእውነት ከሁሉ ትበልጫለሽ፡፡
እናቴ ሆይ እንግዲህ እኔ ምን ልናገር? ሺህ ቃላትን ብደረድር ያንቺን ክብር ልገልፀውስ እንደምን እችላለው? አዎ አሁንም እላለሁ “መልካም ያደረጉ ብዙ ሴቶች አሉ አንቺ ግን ከሁሉ ትበልጫለሽ፡፡” ምሳ. 31፡29
የቅድስት ድንግል ማርያም በረከቷ በሁላችን ላይ ይደር፤ ምልጃ ቃል ኪዳኗ ይጠብቀን፡፡ አሜን!!!
Join @EOTCW
1 161
እንኳን አደረሳችሁ! ህዳር 21 አክሱም ጽዮን ማርያም
ኅዳር ጽዮን በአክሱም አክሱም ማርያም ጽዮን በኢትዮጵያ ውስጥ ለሚገኙት አብያተ ክርስቲያናት ሁሉ መሠረታቸው ስትሆን ከተማዋም የኢትዮጵያ ሥልጣኔ መነሻ ናት፡፡ አክሱም በሕገ ልቡና የጸናች፣ ሕገ ኦሪትን የፈጸመች፣ በሕገ ወንጌል ያመነች ናት፡፡
ህዳር 21 ቀን የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም ዓመታዊ በዓል ነው ብለን በተለየ መልኩ የምናከብርበት ምክንያት፦
➤ታቦተ ጽዮን በምርኮ በሄደችበት በሀገረ ፍልስጤም ዳጎን የተባለ የአህዛብን ጣኦት አድቅቃ በድል የተመለሰችበትን ዕለት በማሰብ። ታቦተ ጽዮን ንጉሥ ሰሎሞን ወደ ሠራላት ቤተመቅደስ በክብር የገባችበትን ዕለት በማሰብ፤
➤የቀደሙ ነብያት ስለእመቤታችን በተለያየ አምሳል ያዩበት ለምሳሌ፦ ነብዩ ዕዝራ በሃገር መንፈሳዊት፣ ሕዝቅኤል በተዘጋች ቤተመቅደስ፣ ዘካርያስ በተቅዋመ ወርቅ ወዘተ ያዩበትን ዕለት በማሰብ፤
➤ቀዳማዊ ምኒሊክ ከዐሥራ ሁለቱ ነገድ እስራኤል የበኩር ልጅ ጋር ሊቀ ካህናቱን አዛሪያስንና ታቦተ ጽዮንን ይዞ አክሱም የደረሰበትን ዕለት ለማሰብ፤
➤በአብርሃ ወአፅብሃ ዘመነ መንግስት ክርስትና የኢትዮጵያ ብሔራዊ ሃይማኖት ሆኖ አዋጅ የታወጀበትን በማሠብ፤
➤አብርሃ ወአጽብሃ በወርቅና በዕንቁ ያሠሩት ባለ አሥራ ሁለት ክፍል ቤተ መቅደስ ለመጀመሪያ ጊዜ ቅዳሴ ቤቱ የተከበረበት ዕለት በመሆኑ፤
➤በዘጠነኛው መቶ ክፍለ ዘመን ዮዲት ጉዲት አብያተ ክርስቲያንን ስታቃጥል ታቦተ ጽዮንን ይዘው ወደ ዝዋይ ሀይቅ ከተሰደዱ በኋላ ዘመነ ሰላም ሲጀመር አክሱም በነበሩ ካህናት አስታዋሽነት ከዝዋይ ወደ አክሱም የገባችበት ዕለት በመሆኑም በርእሰ አድባራት ወገዳማት አክሱም ጽዮን ከፍ ባለ መንፈሳዊ በዓል እናከብራለን።
ከእመቤታችን ረድኤትና በረከት ይክፈለን አሜን!
Join @EOTCW
1 161
✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨
በእለቱ በቅዳሴ ሰዓት የሚነበብ ወንጌል
✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨
ማቴ. 21:42-ፍ፡ም፡ - "ወይቤሎሙ ኢየሱስ አልቦሁ" "ኢየሱስ፡እንዲህ፡አላቸው፦ግንበኛዎች፡የናቁት፡ድንጋይ፡ርሱ፡የማእዘን፡ራስ፡ሆነ፤ይህም፡ከጌታ፡ዘንድ፡ሆነ፥ለዐይኖቻችንም፡ድንቅ፡ነው፡የሚለውን፡ከቶ፡በመጽሐፍ፡አላነበባችሁምን? ስለዚህ፥እላችኋለሁ፥የእግዚአብሔር፡መንግሥት፡ከእናንተ፡ትወሰዳለች፥ፍሬዋንም፡ለሚያደርግ፡ሕዝብ፡ትሰጣለች። በዚህም፡ድንጋይ፡ላይ፡የሚወድቅ፡ይቀጠቀጣል፤ድንጋዩ፡ግን፡የሚወድቅበትን፡ሁሉ፡ይፈጨዋል። የካህናት፡አለቃዎችና፡ፈሪሳውያንም፡ምሳሌዎቹን፡ሰምተው፡ስለ፡እነርሱ፡እንደ፡ተናገረ፡አስተዋሉ፤ ሊይዙትም፡ሲፈልጉት፡ሳሉ፡ሕዝቡ፡እንደ፡ነቢይ፡ስላዩት፡ፈሯቸው።"
✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨
1 161
ህዳር 21/ቀን በቅዳሴ ጊዜ
#ምንባባት
፪ቆሮ ፯፥፲፪-ፍጻሜ
፩ጴጥ ፪፥፭-፲፩
ሐዋ፯፥፵፬-፶፱
#ምስባክ
መዝ፻፴፩፥፲፫
እስመ ኀርያ እግዚአብሔር ለጽዮን
ወአብደራ ከመ ትኩኖ ማኅደሮ
ዛቲ ይእቲ ምዕራፍየ ለዓለም
#ትርጉም
እግዚአብሔር ጽዮንን መርጦአታልና፥
ማደሪያውም ትሆነው ዘንድ ወድዶአታልና፥
እንዲህ ብሎ፦ይህች ለዘላለም ማረፊያዬ ናት፤
#ወንጌል
ማቴ፳፩፥፵፪-ፍጻሜ
#ቅዳሴ
ዘእግዝእትነ(የእመቤታችን ቅዳሴ)
https://t.me/Eotcw
1 161
✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨
በእለቱ በነግህ የሚነበብ ወንጌል
✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨
ማቴ. 23:1-ፍ፡ም፡ "ወእምዝ ነገሮሙ ኢየሱስ" - " በዚያን፡ጊዜ፡ኢየሱስ፡ለሕዝቡና፡ለደቀ፡መዛሙርቱ፡እንዲህ፡ብሎ፡ነገራቸው፦ ጻፊዎችና፡ፈሪሳውያን፡በሙሴ፡ወንበር፡ተቀምጠዋል። ስለዚህ፥ ያዘዟችኹን፡ሁሉ፡አድርጉ፥ጠብቁትም፤ነገር፡ግን፥እየተናገሩ፡አያደርጉትምና፥እንደ፡ሥራቸው፡
አታድርጉ። ከባድና፡አስቸጋሪ፡ሸክም፡ተብትበው፡በሰው፡ትከሻ፡ይጭናሉ፥እነርሱ፡ግን፡በጣታቸው፡ስንኳ፡ሊነኩት፡አይወዱም። ለሰውም፡እንዲታዩ፡ሥራቸውን፡ዅሉ፡ያደርጋሉ፤ስለዚህ፥ዐሸን፡ክታባቸውን፡ያሰፋሉ፥ዘርፉንም፡ያስረዝማሉ፥ በምሳም፡የከበሬታ፡ስፍራ፥በምኵራብም፡የከበሬታ፡ወንበር፥ በገበያም፡ሰላምታና፦መምህር፡ሆይ፡መምህር፡ሆይ፡ተብለው፡እንዲጠሩ፡ይወዳሉ። እናንተ፡ግን፦ መምህር፡ተብላችሁ፡አትጠሩ፤ መምህራችሁ፡አንድ፡ስለ፡ሆነ፡እናንተም፡ሁላችሁ፡
ወንድማማች፡ናችሁ። አባታችሁ፡አንዱ፡እርሱም፡የሰማዩ፡ነውና፥በምድር፡ላይ፡ማንንም፦አባት፡ብላችሁ፡አትጥሩ። ሊቃችሁ፡አንድ፡እርሱም፡ክርስቶስ፡ነውና፦ ሊቃውንት፡ተብላችኹ፡አትጠሩ። ከእናንተም፡የሚበልጠው፡አገልጋያችኹ፡ይሆናል። ራሱን፡ከፍ፡የሚያደርግ፡ሁሉ፡ይዋረዳል፥ራሱንም፡የሚያዋርድ፡ሁሉ፡ከፍ፡ይላል። እናንተ፡ግብዞች፡ጻፊዎችና፡ፈሪሳውያን፥መንግሥተ፡ሰማያትን፡በሰው፡ፊት፡ስለምትዘጉ፥ወዮላችሁ፡እናንተ፡አትገቡም፡የሚገቡትንም፡እንዳይገቡ፡ትከለክላላችሁ። እናንተ፡ግብዞች፡ጻፊዎችና፡ፈሪሳውያን፥በጸሎት፡ርዝመት፡እያመካኛችሁ፡የመበለቶችን፡ቤት፡ስለምትበሉ፥ወዮላችሁ፤ ስለዚህ፥የባሰ፡ፍርድ፡ትቀበላላችሁ። እናንተ፡ግብዞች፡ጻፊዎችና፡ፈሪሳውያን፥አንድ፡ሰው፡ልታሳምኑ፡በባሕርና፡በደረቅ፡ስለምትዞሩ፥በኾነም፡
ጊዜ፡ከእናንተ፡ይልቅ፡ሁለት፡ዕጥፍ፡የባሰ፡የገሃነም፡ልጅ፡ስለምታደርጉት፥ወዮላችሁ። እናንተ፦ማንም፡በቤተ፡መቅደስ፡የሚምል፡ምንም፡የለበትም፤ማንም፡በቤተ፡መቅደስ፡ወርቅ፡የሚምል፡ግን፡በመሐላው፡ይያዛል፡የምትሉ፥ዕውሮች፡መሪዎች፥ወዮላችሁ። እናንተ፡ደንቈሮዎችና፡ዕውሮች፥ማናቸው፡ይበልጣል፧ወርቁ፡ነውን፧ወይስ፡ወርቁን፡የቀደሰው፡ቤተ፡መቅደስ፧ ደግማችሁም፦ማንም፡ በመሠዊያው፡የሚምል፡ምንም፡የለበትም፤ማንም፡በላዩ፡ባለው፡መባ፡የሚምል፡ግን፡በመሐላው፡ይያዛል፡ትላላችሁ። እናንተ፡ደንቈሮዎችና፡ዕውሮች፥ማናቸው፡ይበልጣል፧መባው፡ነውን፧ወይስ፡መባውን፡የሚቀድሰው፡ መሠዊያው፧
20፤እንግዲህ፡በመሠዊያው፡የሚምለው፡በርሱና፡በርሱ፡ላይ፡ባለው፡ሁሉ፡ይምላል፤ በቤተ፡መቅደስም፡የሚምለው፡በርሱና፡በርሱ፡በሚኖረው፡ይምላል፤ በሰማይም፡የሚምለው፡በእግዚአብሔር፡ዙፋንና፡በእርሱ፡ላይ፡በተቀመጠው፡ይምላል።
እናንተ፡ግብዞች፡ጻፊዎችና፡ፈሪሳውያን፥ ከአዝሙድና፡ከእንስላል፡ከከሙንም፡ዓሥራት፡ስለምታወጡ፥ፍርድንና፡ምሕረትን፡ታማኝነትንም፥በሕግ፡ያለውን፡ዋና፡ነገር፡
ስለምትተዉ፥ወዮላችኹ፤ሌላውን፡ሳትተዉ፡ይህን፡ልታደርጉ፡ይገባችኹ፡ነበር። እናንተ፡ዕውሮች፡መሪዎች፥ትንኝን፡የምታጠሩ፡ግመልንም፡የምትውጡ። እናንተ፡ግብዞች፡ጻፊዎችና፡ፈሪሳውያን፥በውስጡ፡ቅሚያና፡ሥሥት፡ሞልቶ፡ሳለ፡የጽዋውንና፡የወጭቱን፡.ውጭ፡ስለምታጠሩ፥ወዮላችሁ። አንተ፡ዕውር፡ፈሪሳዊ፥ውጭው፡ደግሞ፡ጥሩ፡እንዲሆን፡አስቀድመህ፡የጽዋውንና፡የወጭቱን፡ውስጡን፡
አጥራ። እናንተ፡ግብዞች፡ጻፊዎችና፡ፈሪሳውያን፥በውጭ፡አምረው፡የሚታዩ፡በውስጡ፡ግን፡የሙታን፡አጥንት፡ርኵሰትም፡ዅሉ፡የተሞሉ፡በኖራ፡የተለሰኑ፡መቃብሮችን፡ስለምትመስሉ፥ ወዮላችሁ። እንዲሁ፡እናንተ፡ደግሞ፡በውጭ፡ለሰው፡እንደ፡ጻድቃን፡ትታያላችሁ፥በውስጣችሁ፡ግን፡ግብዝነትና፡ዐመፀኝነት፡ሞልቶባችዃል። እናንተ፡ግብዞች፡ጻፊዎችና፡ፈሪሳውያን፥የነቢያትን፡መቃብር፡ስለምትሠሩ፡የጻድቃንንም፡መቃብር፡
ስለምታስጌጡና፦ በአባቶቻችን፡ዘመን፡ኖረን፡በሆነስ፥በነቢያት፡ደም፡ባልተባበርናቸውም፡ነበር፡ስለምትሉ፥ወዮላችሁ። እንግዲያስ፡የነቢያት፡ገዳዮች፡ልጆች፡እንደሆናችሁ፡በራሳችሁ፡ላይ፡ትመሰክራላችሁ። እናንተ፡ደግሞ፡የአባቶቻችሁን፡መስፈሪያ፡ሙሉ። እናንተ፡እባቦች፥የእፍኝት፡ልጆች፥ከገሃነም፡ፍርድ፡እንዴት፡ታመልጣላችሁ? ስለዚህ፥እንሆ፥ነቢያትንና፡ጥበበኛዎችን፡ጻፊዎችንም፡ወደ፡እናንተ፡እልካለሁ፤ከእነርሱም፡ትገድላላችሁ፡ትሰቅሉማላችሁ፥ከነእርሱም፡በምኵራባችሁ፡ትገርፋላችሁ፡ከከተማም፡ወደ፡ከተማ፡ታሳድዳላችሁ፤ ከጻድቁ፡ከአቤል፡ደም፡ጀምሮ፡በቤተ፡መቅደስና፡በመሠዊያው፡መካከል፡እስከገደላችሁት፡እስከበራክዩ፡ልጅ፡እስከዘካርያስ፡ደም፡ድረስ፡በምድር፡ላይ፡የፈሰሰው፡የጻድቅ፡ደም፡ዅሉ፡ይደርስባችሁ፡ዘንድ። እውነት፡እላችዃለሁ፥ይህ፡ሁሉ፡በዚህ፡ትውልድ፡ላይ፡ይደርሳል። ኢየሩሳሌም፡ኢየሩሳሌም፡ሆይ፥ነቢያትን፡የምትገድል፡ወደ፡እርሷ፡የተላኩትንም፡የምትወግር፥ዶሮ፡ጫጩቶቿን፡ከክንፎቿ፡በታች፡እንደምትሰበስብ፡ልጆችሽን፡እሰበስብ፡ዘንድ፡ስንት፡ጊዜ፡ወደድኹ!አልወደዳችሁምም። እንሆ፥ቤታችሁ፡የተፈታ፡ሆኖ፡ይቀርላችኋል። እላችኋለሁና፥በጌታ፡ስም፡የሚመጣ፡የተባረከ፡ነው፡እስክትሉ፡ድረስ፡ከእንግዲህ፡ወዲህ፡አታዩኝም። "
✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨
1 161
ህዳር ፳፩ ቀን
#ምስባክ_ዘነግህ
መዝ፵፯፥፲፪
ዕግትዋ ለጽዮን ወሕቀፍዋ
ወተናገሩ በውስተ ማኅፈዲሃ
ደዩ ልበክሙ ውስተ ኀይላ
#ትርጉም
ጽዮንን ክበቡአት፥
በዙሪያዋም ተመላለሱ፥
ግንቦችዋንም ቍጠሩ፤
በብርታትዋ ልባችሁን አኑሩ፤
https://t.me/Eotcw
1 161
እንኳን ለእናታችን ለጽዮን ማርያም ዓመታዊ በዓል አደረሳችሁ አደረሰን!
የእግዚአብሔር የክብሩ መገለጫ የኾነቺው የእግዚአብሔር ታቦት፤ በንጽሕና በቅድስና የተጌጠችው የእግዚአብሔር ወልድ እናት የኾነቺው የአማናዊት ታቦት የቅድስት ድንግል ማርያም ምሳሌ የኾነችው ጽዮን በደብተራ ኦሪት በቅድስተ ቅዱሳን ውስጥ ተቀምጣ የኖረች፤ የዮርዳኖስን ባሕር የከፈለች (ኢያ 3:14-17)፤ ቅጽረ ኢያሪኮን ያፈረሰች (ኢያ 6:1-21)፤ ዳጎን የተባለ የፍልስጤማውያንን ጣዖት ቆራርጣ ያጠፋች (1ኛ ሳሙ 5:1-5፤ 2ኛ ቆሮ 6:16)፤ በድፍረት ሊነካት የሞከረ ኦዛን የቀሠፈች (2ኛ ሳሙ 6:6)፤ በአቢዳራ ቤት ሦስት ወር ተቀምጣ ቤቱን በበረከት የመላች (2ኛ ሳሙ 6:11)፤ ከብዙ ዘመን በኋላ በታላቅ ክብር ወደ ሀገሯ ስትመለስ ነቢየ እግዚአብሔር ዳዊት በታላቅ መንፈሳዊ ደስታ በፊቷ የዘመረላት (2ኛ ሳሙ 6:14-23፤ 1ኛ ዜና 14:25-28)፤ የቅዳስ ዳዊት ልጁ ንጉሥ ሰሎሞንም ልዩና ውብ የኾነ በወርቅ የተጌጠ ቤተ መቅደስ ሠርቶ በክብር ያኖራት ናት። (1ኛ ነገ 8:11)
እናታችን ጽዮን በሀገራችንን በሁሉም ቦታ ያሉትን የዘመኑን ዳጎናውያንን ፈጽማ ታጥፋልን በእውነት!
በዲ/ን የአብስራ ጌታሁን
https://t.me/Eotcw
1 161
ኅዳር 21 ታቦተ ጽዮን (ጽላተ ኪዳን ወይም ታቦተ ሕጉ )
ጽዮንን ክበቧት፥ በዙሪያዋም ተመላለሱ፥ ግንቦቿንም ቅጠሩ፥ አዳራሿን ተመልከቱ፥ በብርታቷ የልባችሁን ተስፋ አኑሩ፡፡ /መዝ. 47፥12/
share እና like ያድርጉ
#ኅዳር_21_የታቦተ_ጽዮን_(#ጽላተ_ኪዳን_ወይም_ታቦተ_ሕጉ_) #ዓመታዊ_ክብረ_በዓል_የምናከብርበት_ምክንያት_፤
፩ኛ. በሊቀ ካህናት ኤሊ ዘመን በሕዝበ አስራኤል(በአፍኒን ፊንሐስ) ኀጢአት ምክንያት፤ ታቦተ ጽዮን በታሪኳ ለመጀመሪያ ጊዜ በአሕዛብ (ኢሎፍላውያን) እጅ ተማርካ፤ ዳጐን የተባለ የአሕዛብ ጣዖትን ቀጥቅጣ አድቅቃ ወደ እስራኤል የተመለሰችበት በመኾኑ፡፡ (1ሳሙ. ከ1-6)
፪ኛ. ታቦተ ጽዮን መፍቀሬ ጥበብ ቅዱስ ሰሎሞን ወዳሠራው ቤተ መቅደስ (በዓለም ላይ እስካሁን ያልታየ ድግስ ደግሶ) የገባችበት እለት በመኾኑ፡፡ / (1ኛ ነገ. 8፥2፣ 2ኛ ዜና. 5፥1፣ ስንክሳር ዘሐምሌ 23)
፫ኛ. በቀዳማዊ አፄ ምኒልክ (ዕብነ ሐኪም) አማካኝነት ከዐሥራ ሁለቱ ነገደ እስራኤል የበኲር ልጆች ጋር በ318ቱ ሌዋውያን ካህናት ፥ በሊቀ ካህናቱ አዛርያስ እየተመራች ታቦተ ጽዮን ወደ ኢትዮጵያ የገባችበት በመኾኑ፡፡ /ክብረ ነገሥት፣ መጽሐፈ ምሥጢር፣ መጻሕፍተ ሰሎሞን ወሲራክ አንድምታ መቅድም፣ …/
፬ኛ. ነቢያት ስለ እመቤታችን በተለያየ ኅብረ መልክእና አምሳል (ዕዝራ በቅድስት ሃገር መንፈሳዊት፣ ሕዝቅኤል በተዘጋች ቤተ መቅደስ፣ ዘካርያስ በተቅዋመ ወርቅ፣ ……) ያዩበት በመኾኑ፡፡ /ሕዝ. 44፥1፣ መጽ. ዕዝራ/
፭ኛ. በንጉሥ አፄ ባዜን (በ4 ዓ.ም. አካባቢ) አማናዊት ጽዮን ድንግል ማርያም ዋልድባን፣ ደብረ ዐባይን፣…… ሌሎችንም የኢትዮጵያ መካናት በስደት ከልጇ ጋር ባርካ አኵስም ጽዮን ላይ መጥታ የገባችበትና የባረከችበት፤ በወቅቱም አኵስምና አካባቢዋ በብርሃን ጎርፍ የተጥለቀለቁበት በመኾኑ፤ /ታሪከ ዋልድባ፣ ታሪከ አኵስም፣ ድርሳነ ዑራኤል፣ ....)
፮ኛ. በ4ኛው መቶ ክፍለ ዘመን በቅዱሳን ጻድቃን ነገሥታት አብርሐ ወአጽብሐ አማካኝነት መሥዋዕተ ኦሪት ሲሰዋባት የቆየችው አኵሱም ጽዮን፤ ጽዮን ማርያም ተብላ ባለ 12 መቅደሶች ባሏት በወርቅና በዕንቊ ያሸበረቀች ቤ.ክ ሠርተው ቅዳሴ ቤቷ የተከበረበትና ክርስትና ብሔራዊ ሃይማኖት ሆኖ የታወጀበት፡፡
፯ኛ. በየጊዜው (በዮዲት ጉዲትና በግራኝ አማካኝነት ስትፈርስ) ወደ ዝዋይ፣ ወደ ጣና ቂርቆስ፣ …… ተሰድዳ ቆይታ፤ ተመልሳ (ከዮዲት በኋላ በአንበሳ ውድምና፤ ከግራኝ በኋላ በአፄ ፋሲል የታነጹት ሕንፃ ቤተ ክርስቲያን) ቅዳሴ ቤቷ የተከበረበት በመኾኑ፡፡
፰ኛ. ወደ አኵሱም ደብረ ጽዮን ማርያም በቦታው ርቀት ለመሳለም ላልቻሉ ክርስቲያኖች ዳግሚት ደብረ ጽዮን በዳግማዊ አፄ ምኒልክ አዲስ አለም ላይ የተሠራችበት በመኾኑ፡፡
፱ኛ. ሴቶችም ወንዶችም የሚያስቀድሱበትና ያለ ዐምድ ዕፁብ ድንቅ በኾነና በሃግያ ሶፍያ ቤ.ክ. አምሳል የተሠራው የጽዮን ቤተ ክርስቲያን (ኅዳር 21 ጾም በመኾኑ ቅዳሴ ቤቷ የተከበረው ግን ጥር 30 ቀን 1957 ዓ.ም ግርማዊ ንጉሠ ነገሥት ቀዳማዊ ዐፄ ኀይለ ሥላሴ፣ እቴጌ መነን፣ የታላቋ ብሪታንያ ንግሥት ግርማዊት ንግሥት ኤልሳቤጥና ልዑል ፊልፕ በተገኙበት ቢሆንም) ቅዳሴ ቤት የተከበረበት በመሆኑ፡፡
————
#ታቦተ_ጽዮንና #ጽዮን_ድንግል_ማርያም_፤
፠ ታቦተ ጽዮንን፤ ሌዋውያን ከበዋት ውዳሴ፥ ዝማሬ ያቀርቡላት እንደነበረው፤
✤ ዛሬም እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምን ካህናትና ምእመናን ከሩቅ እና ከቅርብ ተሰብስበው በማኅሌት፥ በዝማሬ፥ በቅዳሴና በውዳሴ ያከብሯታል፡፡
፠ ታቦተ ጽዮን በደብተራ ኦሪት በቅድስተ ቅዱሳን ውስጥ የኖረች ፥ የዮርዳኖስን ባሕር የከፈለች /ኢያሱ 3÷14-17/ ፥ ቅጽረ ኢያሪኮን ያፈረሰች /ኢያሱ 6÷1-21/ ፥ ዳጎን የተባለ የፍልስጤማውያንን ጣዖት የቈራረጠች /1ኛ ሳሙ. 5÷1-5/ ፥ በድፍረት ሊነካ የሞከረውን ኦዛን የቀሰፈች /1ኛ ሳሙ. 6÷6/ ፥ በአቢዳራ ቤት ሦስት ወር ተቀምጣ ቤቱን በበረከት የመላች /2ሳሙ 6÷12/ ፥ ዳዊት የዘመረላት /2ሳሙ 6÷14/ ፥ ጠቢቡ ሰሎሞን በቤተ መቅደስ በክብር ያኖራት /1ኛ ነገ፣ 8÷1/ ፥ የእግዚአብሔር የክብር መገለጫ ናት፡፡
✤ ጽዮን ቅድስት ድንግል ማርያምም ንጽሐ ጠባይዕ ሳያድፍባትና የቅድስና ባሕርይ ሳይጎድፍባት፤ (በማየት፣ በመስማት፣ በመዳሰሰ፣ በማሽተት አንዳችም እድፍ ጉድፍ ሳያገኛት)
በንጽሕናና (በኀልዮ፣ በነቢብ፣ በገቢር) በቅድስና ጸንታ በኀጢአት ሳትለወጥ ኖራለች፡፡ /ውዳሴ ማርያም፣ ሊቁ ቅዱስ ኤፍሬም፤ አንቀጸ ብርሃን፣ ሊቁ ቅዱስ ያሬድ/ እንዲሁም ‹‹ምክንያታዊ ነውር ኃጢአት የሌለብሽ የኀጢአት ሸታ ያልደረሰብሽ ንጽሕት በድንግልና ሥርጉት በቅድስና ክብርት በልዕልና አንቺ ነሽ» ብሏታል ጠቢቡ ሰሎሞን /መሓ. 4÷7/
፠ ታቦተ ጽዮን በከበረ ወርቅ እንደተሸለመች
✤ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምም በንጽሐ ሥጋ፣ በንጽሐ ነፍስ እና በንጽሐ ልቡና የተሸለመች ያጌጠች ናት፡፡
፠ ታቦተ ጽዮን የቃለ እግዚአብሔር ማደሪያ እንደሆነች፤
✤ ጽዮን ቅድስት ድንግል ማርያምም ለአካላዊ ቃል ለእግዚአብሔር ወልድ ማደሪያ ኾናለች፡፡ «ድንግል ማርያም ሆይ ሰማይና ምድርን ለፈጠረ አምላክ ለእርሱ ማደሪያ ሆንሽ ዘጠኝ ወር ከአምስት ቀን በማኅፀንሸ ቻልሽው ተሸከምሽው ሰማይና ምድር የማይወስኑትን ለመወሰን የታመንሽ አንቺ ነሽ» /ውዳሴ ማርያም፣ ቅዱስ ኤፍሬም/
——-
**** በእመቤታችን በቅድስት ድንግል ማርያም እና በቃል ኪዳኑ ታቦት መካከል ጥልቅ የሆነ ምሥጢራዊ ትምህርት አለ፡፡ /ዘፀ. 25÷9-20/፡፡ ይህንንም በተመለከተ ሊቁ አባ ጽጌ ድንግል ምሥጢሩን ከምሥጢር አመሳጥሮ፤ እንደ ሸማ አንከባሎ፥ እንደ ወርቅ ከብልሎ እንዲህ አስቀምጥታል፤
«ታቦተ አምላከ እስራኤል ጽዮን ዘነገደት ምድረ ኢሎፍሊ፤
ወቀጥቀጠቶ ለዳጎን ነፍሳተ ብዙኃን ማህጎሊ፡፡
አመ ነገደት ቊስቋመ በኀይለ ወልዳ ከሃሊ፤
ወድቁ አማልክተ ግብፅ መናብርተ ሰይጣን ሐባሊ፤
ወተኀጉሉ ኲሎሙ ዘቦሙ አስጋሊ፡፡
ወደ ኢሎፍሊ ምድር ተማርካ የሔደች የእስራኤል አምላክ የቃል ኪዳኑ ታቦተ ጽዮን የብዙዎችን ነፍሳት ያጠፋ ዳጎንን ሰባበረችው፡፡ ድንግል ማርያምም ሁሉን ማድረግ ከሚችለው ከልጇ ጋር ግብፅ ወደሚባል ሀገር በሔደች ጊዜ የሐሰተኛ ሰይጣን ዙፋኖች የሆኑ የግብፅ ጣዖታት ፈረሱ ጠንቋይ አስጠንቋይ ያላቸው ሁሉ ዐፈሩ» /ኢሳ 19÷1፣ ሊቁ አባ ጽጌ ድንግል/
https://t.me/Eotcw
🌼🌼🌼🌼🌼🌼
#Share #like
1 161
❤ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤
+ + +
❤ የዕለቱ እግ ነግ ዓራራይ ዜማ፦ "ታቦተ ሕጉ ለእግዚአብሔር በካህናት ሕጽርት ወበመንፈስ ቅዱስ ክልልት ንጉሥኪ ጽዮን ኢትመዋዕ ለፀር ወኢየኃድጋ ለሀገር"። ትርጉም፦ የእግዚአብሔር ታቦት ሕግ በካህናት የታጠረች ናት ጽዮንን ንጉሥሽ በጠላት አይሸነፍም ሃገርንም አሳልፎ አይሰጥም። ሊቁ ቅዱስ ያሬድ በድጓው ላይ።
+ + +
❤ "ሰላም ለእምነ ጽዮን መርዐተ ሰማይ ሥርጉት በስብሐት ከመ ፀሓይ ብርህት ዘሙሴ ጽላት እንተ ውስቴታ ትእዛዛተ ዐሥሩ ቃላት እለ ጽሑፋት በአጻብዒሁ ለጸባኦት"። ትርጉም፦ እንደ ፀሓይ የምታበራ ለኾነች፤ በክብር ላጌጠች ለሰማይ ሙሽራ ለእናታችን ጽዮን ሰላምታ ይገባል ፤ በሰራዊት ጌታ ጣቶች የተጻፉ የዐሥሩ ቃላት ትእዛዛት በውስጦቿ ያሉ የሙሴ ጽላት ሰላምታ ላንቺ ይገባል። ሊቁ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ በተአምኆ ቅዱሳን ላይ።
https://t.me/Eotcw
