ch
Feedback
ሰዋስው ☘☘☘☘

ሰዋስው ☘☘☘☘

前往频道在 Telegram

በሰዋስወ ብርሀን ቅዱስ ዻውሎስ ገዳም እና ለተለያዩ ቤተክርስቲያን ለክብረ በአላት ማውጫ ። በተጨማሪም-ዋዜማ ሥርዓተ ማኅሌት - መዝሙራት ስንክሳር - የየእለቱን ምስባክ ቅኔያት ጥያቄዎች እንዲሁም የወቅታዊ ነገር መወያያ በተጨማሪም @eotcww ብለው ይቀላቀሉን ለወዳጅ ዘመድዎ share#Share#Share# ያድርጉ።

显示更多
1 161
订阅者
无数据24 小时
无数据7 天
无数据30 天
帖子存档
ጌልን አስፋፍው ሕግ ሠርተዋል፡፡ የከበሩ ቅዱሳን ነገሥት አብርሃ ወአጽብሓ በእንዲህ ዓይነት ግብር ጸንተው በመኖር እግዚአብሔርንም ሰውንም አገልግለው ለሀገራችንም ብርሃን አብርተውላት ነው ያለፉት፡፡ ❤ ታላቁ አብርሃ በ364 ዓ.ም ጥቅምት 4 ቀን እሑድ ዕለት ዐረፉ፡፡ ከ13 ዓመት በኋላ ታናሹ አጽብሓ በ379 ዓ.ም ጥቅምት 4 ቀን ዐረፉ፡፡ ልደታቸውም ሆነ ሞታቸው አንድ ቀን ነው የዕረፍታቸው ዓመቱ ይለያይ እንጂ፡፡ የተቀበሩበት ቦታም አንድ ነው፡፡ የንግሥና ስማቸው ኢዛናና ዛይዛና ይባላል፡፡ ከቅዱሳን ነገሥታት ከአብርሃ ወጽብሓ እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን በጸሎታቸው ይማረን። + + + ❤ አቡነ በርተሎሜዎስ፦ እኚህም ጻድቅ ከአቡነ ተክለ ሃይማኖት ልጆች ውስጥ አንዱ ሲሆኑ ያመነኰሷቸውና የሾሟቸውም እርሳቸው ናቸው፡፡ የቆባ፣ የጠጠርና የኮረም ኤጲስ ቆጶስ ሆነው ተሹመው በብዙ ድካም አገልግለዋል፡፡ ጻድቁ ደብረ ሊባኖስን የሚያጥኑበት ተራቸው በወርሃ ጳጉሜን ነበር፡፡ ❤ ወሎ ራያ ውስጥ ያለችውን ጥንታዊቷንና ባለታሪኳን ደብረ ዘመዳን የመሠረቷት እኚህ ታላቅ አባት ናቸው፡፡ ወንጌላዊው ቅዱስ ሉቃስ የሳላት የእመቤታችን ሥዕል ሁልጊዜ ሰዓታትና ማኅሌት በማይታጎልባት በዚህች ጥንታዊ ገዳም ውስጥ ትገኛለች፡፡ እጅግ በርካታ ቅርሶችም ይገኙባታል፡፡ በአካባቢዋም ዘብ ሆነው የሚጠብቋት በርካታ የዱር አራዊት ይገኛሉ፡፡ ጻድቁ በታላቅ መንፈሳዊ ተጋድሎ ኖረው ጥቅምት 4 ቀን በሰላም ዐርፈዋል፡፡ ከአባታችን ከአቡነ በርተሎሜዎስ እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን በጸሎታቸው ይማረን!። ምንጭ፦ መዝገበ ቅዱሳን ከሚለው መጽሐፍ የተወሰደ። + + + ❤ "ሰላም ለአብርሀ ወለአጽብሐ ዘነበሩ። በመንግሥታት አሐቲ እንዘ ይትፋቀሩ። ለእለ ትካት ሰብእ በትዛዘ ኦሪት ዘሖሩ። ተሰብከ በአፉሆሙ ወንጌለ ክርስቶስ ነገሩ። ወበንዋዮሙ ተሐንፀት ማኅደሩ"። ሊቁ አርከ ሥሉስ አርኬ የጥቅምት 4። ❤ በየቀኑ ይህን ቴሌግራም ላይ ማግት ከፈለጉ ከታች ያለውን ሊኩን ይጫኑት። https://t.me/Eotcw

❤ "በስመ አብ ወወልደ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤ ❤ ጥቅምት ፬ (4) ቀን። ❤ እንኳን ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሃይማኖት በኢትዮጵያ ብሔራዊ ሃይማኖት እንዲሆን ላደረጉ ለቅዱሳን ለወንድማማቾች ነገሥታት ያለፈረቃም በፍቅር አንድነት በአክሱም ተቀምጠው ለነገሡ (ለገዙ) ለአብርሀና አጽብሐ ለዕረፍታቸው መታሰቢያ በዓል፣ ለኢትዮጵያዊው ወሎ ራያ ውስጥ ያለችውን ጥንታዊቷንና ባለታሪኳን ቅዱስ ሉቃስ የሳላት የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም ስዕል የምትገኝበት ደብረ ዘመዳን ለመሠረቱ ለታላቁ አባት ለአቡነ በርተሎሜዎስ ለዕረፍታቸው በዓል በሰላም አደረሰን። + + + ❤ "ሰላም ለአብርሀ ወአጽብሐ እለ ነግሡ በፍትሕ ወወጽኡ በንጽሕ፤ እለ ኮኑ መሠረተ ክርስትና፤ ለብሔረ ኢትዮጵያ እለ ሐነጽዋ ለገበዝ፤ እለ በሃይማኖት እዙዝ"። ትርጉም፦ በሃይማኖት የታዘዘ ለኢትዮጵያ ሀገር ጠረፏን ያነጹ፤ ለክርስትና መሠረት የኾኑ፤ በፍትሕ ነግሠው በንጽሕና የወጡ ለአብርሀና አጽብሐ ሰላምታ ይገባል። + + + ❤ ቅዱሳን ወንድማማቾች ነገሥታት አብርሀ ወአጽብሐ፦ አባታቸው ታዜር እናታቸው ሶፍያ (አህየዋ) ይባላሉ፡፡ መንትዮች የሆኑት እነዚህ ቅዱሳን የተወለዱት ጌታችን በተወለደባት ዕለት በታኅሣሥ 29 ቀን 312 ዓ.ም ነው፡፡ በታላቁ አባት በአቡነ ሰላማ ከሣቴ ብርሃን እየተማሩ አድገው በእሳቸው እጅ በ330 ዓ.ም መጋቢት 29 ቀን ተጠመቁ፡፡ በእነርሱም ጊዜ አማናዊው ጥምቀትና ቊርባን መጣልን፡፡ በሀገራችን 154 አብያተ ክርስቲያናትን ያሠሩ ሲሆን 44ቱ ፍልፍል ናቸው፡፡ በተለይም ገርዓልታ ያለው ቀመር ዓርባዕቱ እንስሳ ፍልፍል ቤተ መቅደስ በሩ በራሱ ጊዜ ይከፈታል ይዘጋል እንጂ ሰው አይከፍተውም አይዘጋውም፡፡ ❤ አቡነ ሰላማ ከሣቴ ብርሃን በአክሱም ሲኖሩ ከሳምንቱ ቀናት ውስጥ ቅዳሜና እሑድ ብቻ የዛፍ ቅጠሎችን ከመመገብ በቀር ሌላ ምግብ ባለመመገብ በታላቅ ተጋድሎ ይኖሩ ነበር፤ አህልም አይቀምሱም፤ በየቀኑም አምስት ሺህ ስግደትን ይሰግዳሉ፡፡ በእርሳቸውም የተጋድሎ ዘመን ደጋግ የሆኑ ቅዱሳን ነገሥታት አብርሃና አጽብሓ ነገሡ፡፡ ❤ ነገሥታቱም ሆኑ የኢትዮጵያ ሕዝብ አቡነ ሰላማ ከሣቴ ብርሃንን እጅግ በጣም ይወዷቸው ነበር፡፡ አባታችንም በእንዲህ ዓይነት ተጋድሎ ሲኖሩ ከዕለታት በአንደኛው ቀን የብርሃን እናቱ ድንግል ወላዲተ አምላክ ለአቡነ ሰላማ ከሣቴ ብርሃን ተገልጣላቸው "ዲቁናና ቅስናን መቀበል ይገባሃል፣ ለጵጵስና ተዘጋጅ፣ እግዚአብሔር ይህችን ከፍ ያለችውን ማዕረግ ሰጥተሃልና የልጄ ወዳጅ ሆይ በጸሎትህና በልመናህ በስብከትህም የኢትዮጵያ ሰዎች ሁሉ ይድናሉ፣ በእጅህ ጥምቀትንና ሥጋ ወደሙን ይቀበላሉ!" አለችው፡፡ ጌታችንም እንዲሁ ተገልጦላቸው "ወደ ሊቀ ጳጳሳት ወደ አትናቴዎስ ሄደህ ከፍ ያችውን ማዕረግ ተቀብለህ የኢትዮጵያን ሰዎች አጥምቅልኝ፣ ነቢዩ ዳዊት ስለ እነርሱ "ኢትዮጵያ እጆቿን ወደ እግዚአብሔር ትዘረጋለች" ብሎ ተናግሯልና" አላቸው፡፡ ❤ ነገሥታቱ አብርሃንና አጽብሓ ነገረ ክርስቶስን እያሰቡ ስለ ጥምቀት ልጅነት ይጨነቁ ነበር፡፡ ከሊቀ ካህናቱም ጋር በዚህ ጉዳይ ሲጨዋወቱ ሊቀ ካህናቱ ስለ አቡነ ሰላማ ነገሯቸው፡፡ ነገሥታቱም አቡነ ሰላማን አስጠርተው ስለነገረ ክርስቶስ ምሥጢር እንዲያስረዷቸው ጠየቋቸው፡፡ አባታችንም "ነቢያት በመንፈስ ቅዱስ ተቃኝተው አካላዊ ቃል እግዚአብሔር ወልድ ይወለዳል ካሉበት ጀምሮ የልደቱን፣ የትምህርቱን የጥምቀቱን፣ የስቅለቱን፣ የሞቱን፣ የትንሣኤውንና የእርገቱን ነገር ሌላውንም ሁሉ ተንትነው አስተማሯቸው፡፡ ሐዋርያትም በጌታ ተሾመው ዓለምን ዞረው ማስተማራቸውን እንዲሁ ተረኩላቸው፡፡ ነገሥታቱም ይህንን በሰሙ ጊዜ እጅግ ደስ ብሏቸው ፍሬምናጦስን "ወንድማችን ሆይ! ይህን ሥርዓት በሀገራችን እንድታስፋፋ" አሏቸው፡፡ አባታችን ግን "ለዚህ የሚያበቃ ሥልጣን ያለው እንጂ ለእኔ አይቻለኝም" አሉ፡፡ ነገሥታቱም "ይህን የሚችል ማነው?" ብለው ቢጠይቋቸው "በእስክንድርያ ጳጳሳትን፣ ቀሳውስትንና ዲያቆናትን የሚሾም አባት አለ" አሏቸው፡፡ ከዚህም በኋላ ነገሥቱ ወደ እስክንድርያው ሊቀ ጳጳሳት ወደ ቅዱስ አትናቴዎስ ደብዳቤ በመጻፍ "አባታችንና መምህራችን ሆይ! የምንጠይቅህን እሺ በጀ በለን ይኸውም ወደ ጽድቅ ጉዳና የሚመራንን ጳጳስ ሹምልን" በማለት ብዙ ወርቅና ብር ገጸ በረከት አስይዘው ከብዙ ሊቃውንት ጋር ፍሬምናጦስን ወደ እስክንድርያ ላኳቸው፡፡ ❤ ከዚህም በኋላ አባታችን ከነገሥታቱ አብርሃና አጽብሓ ጋር ተማክረው ወደ እስክንድሪያ ሄደው በቅዱስ አትናቴዎስ እጅ በአገራችን ላይ ሊቀ ጳጳስ ሆነው ታኅሣሥ 18 ቀን ተሾሙ፡፡ ቅዱስ አትናቴዎስ ከሾሟቸውና ከመረቋቸው በኋላ ለአቡነ ሰላማና አብረውት ለነበሩ ሊቃውንት መጻሕፍተ ብሉያትን፣ መጻሕፍተ ሐዲሳትንና ሥርዐተ ቤተ ክርስቲያንን፣ ታቦተ ማርያምን፣ ታቦተ ሚካኤልንና ታቦተ ገብርኤልን አስይዘው ለነገሥታቱም ደብዳቤ ጽፈው ከብዙ ገጸበረከት ጋር በታላቅ ክብር ሸኟቸው፡፡ ❤ ቅዱሳን የሚሆኑ ሁለቱ ነገሥታትም አቡነ ሰላማ ከእስክንድርያ ተሾመው መምጣቸውን በሰሙ ጊዜ "የኢትዮጵያ ሰዎች ሁላችሁ እስከ 40 ቀን ተሰብሰቡ" ብለው አዋጅ አስነገሩ፡፡ አባታችንንም በደብረ ሲናም ሄደው አገኟቸውና ከዚያች ቀን ጀምሮ ሕዝቡም ሁሉ እስከ 40 ቀን ድረስ ተጠመቁ፡፡ በዚያችም ዕለት ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዚያች በደብረ ሲና አገር ላይ ወረደና ሕዝቡን ሁሉ ባረኮ ተመልሶ ሲያርግ ከአባ ሰላማ በቀር ያየው አልነበረም፡፡ ወደ አክሱምም ሄደው ቅዱሳን ነገሥታቱም የአድባራት ሁሉ የበላይ የምትሆን የቅድስት ጽዮንን ቤተ ክርስቲያን በወርቅና በዕንቊ ሠሯትና አባ ሰላማ ባርከው ቀደሷት፡፡ ታቦተ ጽዮንም ከድንኳን ወጥታ ማንም ካህን ሳይሸከማት አብርሃና አጽብሓ ወዳሠሩላት ቤተ መቅደስ ራሷ በመንፈስ ቅዱስ ገብታ ተገኘች፡፡ አባታችን በእመቤታችንም በዓለ ዕረፍት ጥር 21 ቀን በውስጧ ለመጀመሪያ ጊዜ ሲቀድሱ ቅዱስ ሚካኤልና ቅዱስ ገብርኤል በግራ በቀኝ እየተራዷቸው እርሳቸውም ከምድር ሦስት ክንድ ከፍ ብለው ሥርዓተ ቅዳሴውን ፈጽመው ለነገሥታቱና ለሕዝቡም ሁሉ አቆረቧቸው፡፡ የዚያን ዕለትም እጅግ ታላቅ በዓልን አደረጉ፡፡ ❤ እነዚህም ቅዱሳን ነገሥታት ትምህርተ ወንጌልን እየሰጡ በአክሱም ቤተ መንግሥታቸው ሳሉ ከዕለታት አንደኛው ቀን ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ መላእክቱን አስከትሎ መጥቶ በአክሱም "ማይ ኰኩሐ" በሚባል ተራራ ላይ ቁሞ አብርሃ ወአጽብሓን ጠርቶ "በዚህች ቦታ ላይ ቤተ መቅደሴን አንጹልኝ" አላቸው፡፡ እነርሱም "ቦታው ባህር ላይ ነው በየት እናንጽልህ?" አሉት፡፡ ጌታችንም በጥበቡ ከገነት ጥቂት አፈር አምጥቶ በባሕሩ ላይ ቢበትንበት ባሕሩ ደርቆ ሜዳ ሆነ፡፡ በዚህ ጊዜ ጌታችን "ቤተ መቅደሴን በዚህ ሥሩ" ብሏቸው ወደ ሰማይ ዐረገ፡፡ ጌታችንም በቆመባት ዓለት ላይ የእግሩ ጫማ ቅርጽ እስከ አሁን ሳይጠፋ በግልጽ ይታያል፡፡ ቦታውም ከዚያ ወዲህ "መከየደ እግዚእ" እየተባለ ይጠራል፡፡ ❤ አብርሃ ወአጽብሓ ከመንግሥት አስተዳደሩ ጋር ክርስትናንና ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያንን በመላ ኢትዮጵያ በማዳረስ እጅግ ከፍተኛ አስተዋፅዖ አድርገዋል፡፡ ካህናትንና ዲያቆናትን ይዘው በመላ ኢትዮጵያ ሐዋርያዊ ጉዞ በማድረግ ሕዝቡን ሁሉ እያስተማሩ፣ ሃይማኖትን እያጸኑ፣ ሥርዓተ ጥምቀትን እያስፋፉ ብዙ አብያተ ክርስቲያናትን አንጸዋል፡፡ በሀገራችን በአራቱም አቅጣጫ ወን

+9
🌱🌱ዚቅ ዜማ@EOTCW

❣❣❣❣❣❣❣❣❣ ሥርዓተ ማኅሌት ዘጥቅምት አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ 🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹 ስምዓኒ እግዚኦ ጸሎትየ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ ወይብጻሕ ቅድሜከ ገአርየ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ ወኢትሚጥ ገጸከ እምኔየ፡ በዕለተ ምንዳቤየ አጽምእ እዝነከ ኀቤየ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ አመ ዕለተ እጼውአከ ፍጡነ ስምዓኒ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ ለዓለም ወለዓለመ ዓለም፡ ሃሌ ሉያ ዘውእቱ ብሂል፡ ንወድሶ ለዘሃሎ እግዚአብሔር ልዑል፡ ስቡሕ ወውዱስ ዘሣረረ ኲሎ ዓለመ፡ በአሐቲ ቃል። @EOTCW ✨መልክአ ሥላሴ ሰላም ለሕፅንክሙ ምርፋቀ ጻድቃን አግብርቲሁ፤ ማያተ ኢያሱ ሥላሴ እለ ትውኅዙ እምሕሊናሁ፤ እንዘ በአፍአሁ አንትሙ ወአንትሙ በውሣጤሁ፤ ኢነጸረ ኀበ ሐይመት ከመ አብርሃም አቡሁ፤ ወመስኮተ ነቢይ ዳንኤል ኢፈቀደ ያርኁ። @EOTCW 🌱ዚቅ በአፍአኒ አንትሙ፣ ወበውሣጤኒ አንትሙ፤ በገዳምኒ አንትሙ፤ ብርሃኑ ለዓለም (ለኢያሱ) አንትሙ። @EOTCW ✨መልክአ ሚካኤል ሰላም ለሕፅንከ እንተ በዲቤሁ ሕቁፍ፤ ጸሎተ ቅዱሳን ውኩፍ፤ ሚካኤል ክቡር መስፍነ ትጉሃን አእላፍ፤ ለረዲኦትየ ከመ ዘይሠርር ዖፍ፤ እንዘ ትሠርር ነዓ በ፪ኤ አክናፍ። @EOTCW 🌱ዚቅ ከመ መዓዛ ቅዱሳን፤ ውስተ አብያተ ክርስቲያን፤ ይሰምዖሙ ጸሎቶሙ ለንጹሐን ከመ መዓዛ ቅዱሳን። @EOTCWW 🌱🌱ዘጣዕሙ ሰላም ለዝክረ ስምኪ ዘመንክር ጣዕሙ፤ ለወልድኪ አምሳለ ደሙ፤ መሠረተ ህይወት ማርያም ወጥንተ መድኃኒት ዘእምቀዲሙ፤ ኪያኪ ሠናይተ ዘፈጠረ ለቤዛ ዓለሙ፤ እግዚአብሔር ይትባረክ ወይትአኮት ስሙ። @EOTCW 🌱ዚቅ እስመ ርእየ ሕማማ ለዓመቱ፤ ወገብረ ኃይለ በመዝራዕቱ፤ መዝገቡ ለቃል ጽጌ እንተ ኢትትነገፍ መድኃኒተ ሕዝብ፤ መዓዛሆሙ ለቅዱሳን። @EOTCW ✨መልክአ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ሰላም ለዝክረ ስምከ ዘኆኅያቲሁ ቅሩጽ፤ ኀበ ዓምደ ብርሃን ጽዱል ወአኮ ዘዕፅ፤ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ኃያል ሠዋቄ ትንቱናን እምዳኅፅ፤ ለዝክረ ስምከ ሠናየ ዜና ወድምፅ፤ ትሴብሕ ኢትዮጵያ ወትዜምር ግብፅ። @EOTCW 🌱ዚቅ ኮከብ ብሩህ ዘሠረቀ እምአቅሌስያ፤ ቤተ ክርስቲያን ዘንሰምያ፤ ኮኖሙ አበ ለሰብአ ግብፅ ወኢትዮጵያ፤ አማን ገብረ መንፈስ ቅዱስ ሐዋርያ። @EOTCWW ❣❣ወረብ ኮከብ ብሩህ ዘሠረቀ እምአቅሌስያ ቤተ ክርስቲያን ዘንሰምያ/፪/ ኮኖሙ አበ ለሰብአ ግብፅ ወኢትዮጵያ አማን በአማን ሐዋርያ/፪ @EOTCWW ዓዲ (ወይም) 🌱ዚቅ ፃማ ቅዱሳን ዲቤሁ አዕረፈ፤ አፈዋተ ወንጌል ጸገየ ዘልፈ፤ አባ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ሃይማኖተ ተአጽፈ፤ ኀበ ዓምደ ወርቅ ስሙ ተጽሕፈ። @EOTCW ✨መልክአ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ሰላም ለጒርኤከ ኅሩመ መብልዕ ዘኮነ፤ ወእስከ ስቴ ማይ መነነ፤ ሶበ ረድኤተከ ርእዩ ወኪዳነከ እሙነ፤ ይቤሉከ ኲሉ ገብረ መንፈስ ቅዱስ አቡነ፤ በኪዳንከ አሥራተ ንሥአነ። @EOTCW @EOTCW ❣❣ወረብ አሥራተ ንሥአነ አሥራተ ንሥአነ/፪/ ገብረ መንፈስ ቅዱስ አሥራተ ንሥአነ/፪/ @EOTCW 🌱ዚቅ በመንግሥተ ሰማያት ይነግሥ ምስሌከ፤ ኃጥእ ዘገብረ ተዝካረከ፤ ወጸውዓ ስመከ እንዘ ይብል አምላከ ተካየድከ፤ በእንተዝ ንሥአነ ለሕዝብከ፤ ገብረ መንፈስ ቅዱስ አሥራተ በኪዳንከ። @EOTCWW @EOTCWW ✨መልክአ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ሰላም ለአዕጋሪከ እለ ኢሖራ በፍናዊሃ፤ ለዛቲ ዓለም ዘዕበድ ጥበባቲሃ፤ ለኢትዮጵያ ምድርነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ሐዋርያሃ፤ ውስተ ገፀ ኲሉ ደወላ ዜና ነገርከ በዝኃ፤ ወእስከ ጽንፋ ለምድር ነቢብከ በጽሐ። @EOTCW 🌱ዚቅ ዝንቱሰ ብእሲ መምህርነ፤ ዘተፈነወ ውስተ ምድርነ፤ ይክሥት ብርሃነ ይፈውስ ዱያነ፤ ሐዋርያ ዘኮነ ወተሰምዓ ዜናሁ፤ ውስተ ኲሉ ምድር። @EOTCW ❣❣ወረብ ዝንቱሰ ገብረ ሕይወት ተፈነወ ውስተ ምድርነ/፪/ ይክሥት ብርሃነ ይፈውስ ዱያነ ሐዋርያ ሐዋርያ ዘኮነ/፪/ @EOTCW @EOTCW ✨ሰቆቃወ ድንግል እስከ ማእዜኑ እግዝእትየ ማርያም ውስተ ምድረ ነኪር ትሔልዊ፤ሀገረኪ ናሁ ገሊላ እትዊ፤ለወልድኪ ሕፃን ዘስሙ ናዝራዊ፤ለክብረ ቅዱሳን በከመይቤ ኦዝያን ዜናዊ፤እምግብጽ ይጼውዖ አቡሁ ራማዊ። @EOTCW ❣❣ወረብ በከመይቤ"ኦዝያን"(፪) ለክብረ ቅዱሳን/2/ እምግብጽ ይጼውዖ ለወልድኪ አቡሁ ራማዊ አቡ/2/ @EOTCW 🌱ዚቅ ትንቢተ ኢሳይያስ ዘተብህለ እምግብፅ ጸዋዕክዎ ለወልድየ ለክብረ ቅዱሳን ጸዋዕክዎ @EOTCW @EOTCW ✨ማኅሌተ ጽጌ እምደቂቀ ሕዝብኪ አነ እንዘ ነዳይ ወአባሲ፤ በብዕለ ዚአኪ ድንግል እትሜካሕ ከመ ነጋሢ፤ወበጽድቅኪ እትፌሣሕ አርአያ ጻድቅ ብእሲ፤እስመ ብየ ተአምርኪ ጌጋየ ኃጥአን ደምሳሲ፤ወመዝገበ ብዕል ጽጌኪ ለኲሉ ዘይሴሲ @EOTCW 🌱ዚቅ ማርያምሰ ረከብኪ ሞገሰ በኀበ እግዚአብሔር፤ወአነሂ እትፌሣሕ በእንቲአኪ፤እስመ ረከብኩ እምዉስተ ደቂቅኪ እለ የሐዉር በትእዛዝየ፤አምኂ አምኂ፤አምኂ ደቂቀ እኅትኪ ኅሪት። @EOTCW @EOTCW ❄️ምልጣን ኮከብ ብሩህ ዘሠረቀ እምአቅሌስያ፤ ቤተ ክርስቲያን ዘንሰምያ፤ ኮኖሙ አበ ለሰብአ ግብፅ ወኢትዮጵያ፤ አማን ገብረ መንፈስ ቅዱስ ሐዋርያ። @EOTCW @EOTCW 🔹አመላለስ አማን በአማን/፬/ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ሐዋርያ/፬/ @EOTCW ☘ቅንዋት እስመ አንተ ትክል አንጽሖትየ እግዚኦ፤ወበቃልከ እለ ለምፅ አንጸሕከ፤ወበፅጌያት ምድር አሠርጎከ፤ወበመስቀልከ ለጻድቃን አብራህከ #ለወዳጆ_ያጋሩ https://t.me/Eotcw # Join & share #

ዘገብረ መንፈስ ቅዱስ ዋይዜማ @EOTCW

❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️ ስርአተ ዋዜማ ዘጥቅምት ገብረ መንፈስ ቅዱስ ❣❣❣❣❣❣❣❣❣❣❣ በ 1 - ሃሌ ሉያ እንተ አጽናዕኮሙ ለአድባር በኃይልከ፤ወቅኦታን እሙንቱ በኃይል፤ዝንቱሰ ብእሲ መምህርነ፤አባ፤ጸሊ በእንቲአነ @EOTCWW ❄️ምልጣን፦ ዝንቱሰ ብእሲ መምህርነ፤አባ ጸሊ በእንቲአነ፤አባ ጸሊ በእንቲአነ @EOTCWW @EOTCWW 🔹አመላለስ፦ አባ ጸሊ በእንቲአነ/2/ አባ ጸሊ ጸሊ በእንቲአነ/4/ @EOTCWW @EOTCWW 💎ለእግዚአብሔር ምድር በምላህ፦ አባ ጸሊ በእንቲአነ፤ ጸሎትከ ወትረ ይብጽሐነ፤ አባ ጸሊ በእንቲአነ። @EOTCWW @EOTCWW 💎እግዚአብሔር ነግሠ፦ ጼና አልባሢሁ አባ መባእ ጽዮን ስሂን ገነት ከመ ይርአይ ዘሜላት ዘወረደ ውስተ ገነት ከመ ይርአይ ስነ ፅጌያት @EOTCWW @EOTCWW ✴️ይትባረክ፦ ኪያከ መሠረት አንተ ብነ፤ አባ ጸሊ በእንቲአነ፤ እስመ ጸሎተ ጻድቅ ይሰምዕ እግዚአብሔር @EOTCWW @EOTCWW 🔸ሰላም፦ ድምፀ ወተሠብከ ውስተ አለም ዜና ምግባሩ ትሩፍ ለአረጋዊ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ኮከብ ገዳም ፤ድምፀ ወተሠብከ ውስተ አለም ፀጉያን እሙንቱ እምፅጌ ሮማን ወቀ ይሐን እምከላ ገዳም ፤ ድምፀ ወተሠብከ ውስተ አለም ደቂቁ ሔራን ልኡላን ክቡር ወስያ፤ድምፀ ወተሠብከ ውስተ አለም እንዘ የአርግ መስዋዕት ሰላም ድምፀ ወተሠብከ ውስተ አለም፤ድምፀ ወተሠብከ ውስተ አለም @EOTCWW @EOTCWW 🔹አመላለስ፦ ድምፀ ወተሠብከ ውስተ አለም/2/ ድምፀ ወተሠብከ ውስተ አለም/4/ https://t.me/Eotcw # Join & share

✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨ በእለቱ በቅዳሴ ሰዓት የሚነበብ ወንጌል ✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨ ሉቃ. 10፡38-ፍ፡ም፡ "ወእምዝ ሐዊሮሙ" - "ሲሄዱም፡ርሱ፡ወደ፡አንዲት፡መንደር፡ገባ፤ማርታ፡የተባለች፡አንዲት፡ሴትም፡በቤቷ፡ተቀበለችው። ለርሷም፡ማርያም፡የምትባል፡እኅት፡ነበረቻት፥ርሷም፡ደግሞ፡ቃሉን፡ልትሰማ፡በኢየሱስ፡እግር፡አጠገብ፡ ተቀምጣ፡ነበር። ማርታ፡ግን፡አገልግሎት፡ስለ፡በዛባት፡ባከነች፤ቀርባም፦ጌታ፡ሆይ፥እኔ፡እንድሠራ፡እኅቴ፡ብቻዬን፡ስትተወኝ፡አይገድህምን፧እንኪያስ፡እንድታግዘኝ፡ንገራት፡አለችው። ኢየሱስም፡መልሶ፦ማርታ፥ማርታ፥በብዙ፡ነገር፡ትጨነቂያለሽ፡ትታወኪማለሽ፥ የሚያስፈልገው፡ግን፡ጥቂት፡ወይም፡አንድ፡ነገር፡ነው፤ማርያምም፡መልካም፡ዕድልን፡መርጣለች፡ከርሷም፡አይወሰድባትም፡አላት።" ✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨

✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨ በእለቱ በነግህ የሚነበብ ወንጌል ✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨ ዮሐ. 15:1-12 "አነ ውእቱ ሐረገ ወይን" - "እውነተኛ፡የወይን፡ግንድ፡እኔ፡ነኝ፤ገበሬውም፡አባቴ፡ነው። ፍሬ፡የማያፈራውን፡በእኔ፡ያለውን፡ቅርንጫፍ፡ዅሉ፡ያስወግደዋል፤ፍሬ፡የሚያፈራውንም፡ዅሉ፡አብዝቶ፡እንዲያፈራ፡ያጠራዋል። እናንተ፡ስለነገርኋችሁ፡ቃል፡አሁን፡ንጹሓን፡ናችሁ፤ በእኔ፡ኑሩ፡እኔም፡በእናንተ።ቅርንጫፍ፡በወይኑ፡ግንድ፡ባይኖር፡ከራሱ፡ፍሬ፡ሊያፈራ፡እንዳይቻለው፥እንዲሁ፡እናንተ፡ደግሞ፡በእኔ፡ባትኖሩ፡አትችሉም። እኔ፡የወይን፡ግንድ፡ነኝ፡እናንተም፡ቅርንጫፎች፡ናችሁ።ያለእኔ፡ምንም፡ልታደርጉ፡አትችሉምና፡በእኔ፡የሚኖር፡እኔም፡በእርሱ፥እርሱ፡ብዙ፡ፍሬ፡ያፈራል።;በእኔ፡የማይኖር፡ቢሆን፡እንደ፡ቅርንጫፍ፡ወደ፡ውጭ፡ይጣላል፡ይደርቅማል፤እነርሱንም፡ሰብስበው፡ወደ፡ እሳት፡ይጥሏቸዋል፥ያቃጥሏቸውማል። በእኔ፡ብትኖሩ፡ቃሎቼም፡በእናንተ፡ቢኖሩ፡የምትወዱትን፡ሁሉ፡ለምኑ፡ይሆንላችሁማል። ብዙ፡ፍሬ፡ብታፈሩና፡ደቀ፡መዛሙርቴ፡ብትኾኑ፡በዚህ፡አባቴ፡ይከበራል። አብ፡እንደ፡ወደደኝ፡እኔ፡ደግሞወደድዃችኹ፤በፍቅሬ፡ኑሩ። እኔ፡የአባቴን፡ትእዛዝ፡እንደ፡ጠበቅኹ፡በፍቅሩም፡እንደምኖር፥ትእዛዜን፡ብትጠብቁ፡በፍቅሬ፡ትኖራላችኹ። ደስታዬም፡በእናንተ፡እንዲኾን፡ደስታችኹም፡እንዲፈጸም፡ይህን፡ነግሬያችዃለኹ። እኔ፡እንደ፡ወደድዃችኹ፡ርስ፡በርሳችኹ፡ትዋደዱ፡ዘንድ፡ትእዛዜ፡ይህች፡ናት።" ✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨

1.25 KB

3/2/2015 ዓ.ም (፫/፪/፳፻፲፭ ዓ.ም) 🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯 በእለቱ በነግህ የሚባል ምስባክ 🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯 ተከልከ ሥርዊሃ ወመልዐት ምድረ። ወከደነ አድባረ ጽላሎታ። ወአእፁቂሃኒ ከመ አርዘ ሊባኖስ። መዝ. 79፥9 🕯 ትርጉም ሥሮቿንም ተከልህ ምድርንም ሞላች። ጥላዋ ተራራዎችን ከደነ። ጫፎቿ እንደእግዚአብሔር ዝግባ ሆኑ። 🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯

❤ "በስመ አብ ወወልደ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤ ❤ ጥቅምት ፫ (3) ቀን። ❤ እንኳን ለእስክንድርያ ለአባቶች ሊቃነ ጳጳሳት ሃምሳ አንተኛ ለሆነ ሊቀ ጳጳሳት ለአባ ስምዖን ለዕረፍት በዓል፣ ለሐዲስ ለቅዱስ ጊዮርጊስ ለምስክርነቱ መታሰቢያ በዓልና ለታላቁ ቴዎዶስዮስ ልጅ ለሆነ ለንጉሥ አርቃድዮስ ለወለዳት ለቅድስት ታኦድራ ለመታሰቢያ በዓል በሰላም አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰቡ፦ ከኒኀዋ ከወገን ከነገዱ ከመቃርስና ታኦፊላ፣ ከአውመራና ከአርማንያ ሊቀ ጳጳሳት ከአባ ጎርጎርዮስ ከመታሰቢያቸው እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን። + + + ❤ የእስክንድርያ ሃምሣ አንደኛ ሊቃነ ጳጳሳት አባ ስምዖን፦ ይህም አባት ከእስክንድርያ ከታላላቆች ተወላጅ የሆነ ወላጆቹም ሃይማኖታቸው የቀና ነው እርሱም ከታናሽነቱ የሃይማኖት ወተትን ጠጥቶ አደገ ስለዚህም የቤተ ክርስቲያንን ትምህርት ተማረ። ❤ የምንኵስናንም ልብስ ሊለብስ በልቡ አስቦ ወደ አስቄጥስ ገዳም በመሔድ ከእርሱ አስቀድሞ ሊቀ ጳጳሳት በሆነ በአባ ያዕቆብ ገዳም መነኰሰ በየጊዜው በሚጨመር ተጋድሎም ሥጋውን እያደከመ አብዝቶ በመጋደል በእርሱ ዘንድ ኖረ። ዳግማዊ አባ ማርቆስም ሊቀ ጵጵስና በተሾመ ጊዜ ይህን አባ ስምዖንን ስለ በጎ ተጋድሎውና ስለ አገልግሎቱ ከአባ ያዕቆብ ዘንድ ወሰደው እያገለገለውም ከእርሱ ጋር ኖረ። አባ ማርቆስም በዐረፈ ጊዜ አባ ያዕቆብ ተሾመ ያን ጊዜም እያገለገለው ከአባ ያዕቆብ ጋር ኖረ። ❤ ከዚህም በኋላ አባ ያዕቆብ በዐረፈ ጊዜ ብዙዎች ካህናትና ኤጲስቆጶሳት የሀገር ታላላቆች ሁሉም ይህን አባት አባ ስምዖንን መረጡት። ትሩፋቱንና የአማረ ሥራውን በእነዚህ በሁለቱ ሊቃነ ጳጳሳት ዘንድ በነበረበት ጊዜ ስለተመለከቱ አምላካዊ ፍቅር አነሣሥቷቸዋልና በወንጌላዊ ማርቆስ መንበር ላይ ይዘው ሊቀ ጵጵስና ሾሙት። ❤ ከዚህም በኋላ በሹመቱ ጸንቶ መልካምን ጉዞ ተጓዘ እግዚአብሔርንም አገለገለው የሃይማኖትንም ሕግ በማስጠበቅ የክርስቶስን መንጋዎች ጠበቀ። በሹመቱ ወራትም ቤተ ክርስቲያን በጸጥታና በሰላም ኖረች። ❤ ከዚህም በኋላ እግሮቹን በጽኑዕ ደዌ ታመመ ፈጣሪ እግዚአብሔርንም ከዚህ ደዌ ያሳርፈው ዘንድ ለመነው። ክብር ይግባውና ጌታችንም ልመናውን ተቀብሎ በሰላም በፍቅር አንድነት አሳረፈው የሹመቱ ወራትም አምስት ወር ከዐሥራ አምስት ቀን ነው። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በአባ ስምዖን ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን። + + + ❤ "ሰላም እብል ለብፅዕት ታኦድራ። ወለተ አርቃድዮስ ንጉሥ ለማርያም ፍቁራ። ዘበቃላ ጥዕምት ወሠናይት በምግባራ። ኀበ ተዓየኑ ጉባኤ ቅዱሳን ማኅበራ። ዘክሮተነ ኢትፍልጥ እምዝክራ"። ሊቁ አርከ ሥሉስ አርኬ የጥቅምት 3። + + + ❤ የዕለቱ የማኅሌት ምስባክ፦ "ተከልከ ሥርዊሃ ወመልዕተ ምድረ። ወከደነ አድባር ጽላሎታ። ወአእፁቂሃኒ ከመ አርዘ ሊባኖስ"። መዝ 79፥9-10። የሚነበበው ወንጌል ዮሐ 15፥1-12። + + + ❤ የዕለቱ የቅዳሴ ምስባክ፦ "አዋልደ ንግሥት ለክብርከ። ወትቀውም ንግሥት በየማንከ። በአልባሰ ወርቅ ዑጽፍት ወኊብርት"። መዝ 44፥9። የሚነበቡት መልዕክታት ቲቶ 2፥1-9፣ 1ኛ ጴጥ 5፥2-5 እና የሐዋ ሥራ 16፥8-16። የሚነበበው ወንጌል ማቴ 20፥28-31። የሚነበበው ወንጌል ሉቃ 10፥38-ፍ.ም። የሚቀደሰው ቅዳሴ የሠለስቱ ምዕት ቅዳሴ ነው። መልካም የአባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ የጽንሰት በዓልና የጾም ጊዜ ለሁላችንም ይሁንልን። ❤ በየቀኑ ይህን ቴሌግራም ላይ ማግት ከፈለጉ ከታች ያለውን ሊኩን ይጫኑት። https://t.me/Eotcw