ch
Feedback
ሰዋስው ☘☘☘☘

ሰዋስው ☘☘☘☘

前往频道在 Telegram

በሰዋስወ ብርሀን ቅዱስ ዻውሎስ ገዳም እና ለተለያዩ ቤተክርስቲያን ለክብረ በአላት ማውጫ ። በተጨማሪም-ዋዜማ ሥርዓተ ማኅሌት - መዝሙራት ስንክሳር - የየእለቱን ምስባክ ቅኔያት ጥያቄዎች እንዲሁም የወቅታዊ ነገር መወያያ በተጨማሪም @eotcww ብለው ይቀላቀሉን ለወዳጅ ዘመድዎ share#Share#Share# ያድርጉ።

显示更多
1 161
订阅者
无数据24 小时
无数据7 天
无数据30 天
帖子存档
❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤ + + + ❤ "ሰላም ለጳውሊ በውሳጤ ገዳም ዘተጸምደ። እንዘ ኢይሬኢ እምሰብእ መነሃ አሐደ። ፃመወ ብዙኀ ወተጋደለ ፈድፋደ። ድኅረ ሞቱሂ ከመ በሕይወቱ ለመደ። ለእግዚአብሔር ተረክበ ከዊኖ ስጉደ"። ትርጉም፦ ከሰው ወገን ማንንም ማን አንድ ሳያይ በገዳም ውስጥ የተጠመደ ለኾነ ለጳውሊ ሰላምታ ይገባል፤ በብዙ ወገን ደክሞ በብዙ ወገንም ተጋደለ፤ ከሞቱም በኋላ በሕይወቱ እንደለመደው ለእግዚአብሔር የሰገደ ኾኖ ተገኘ። ሊቁ አርከ ሥሉስ (አርኬ) የየካቲት 2። @eotcw

ከዚህም በኋላ አባ ሉክያኖስ ዐረፈ። ❤ የኬልቄዶንን ጉባኤ በሰበሰበ በከሀዲው መርቅያኖስም ዘመን ወደ አገሮችም ሁሉ መልእክተኞችን ላከ ከእርሳቸውም ጋር አንዱን ክርስቶስን ወደ ሁለት ባሕርይ የምትከፍል የረከሰች የሃይማኖቱ ደብዳቤ አለች። ከንጉሥ መልእክተኞች ሦስቱ ወደ ደብረ ዝጋግ በደረሱ ጊዜ ያንን ደብዳቤ ለአባ ለንጊኖስ ሰጡት በዚህ "ጽሑፍ እንድታምኑ በውስጡም እንድትፈርሙ ንጉሥ መርቅያኖስ አዝዞአል" አሉት። አባ ለንጊኖስም "ከቅዱሳን አባቶቼ ጋር ሳልማከር እኔ ምንም ምን መሥራት አልችልም እንድንማከርም እናንተም ከእኔ ጋር ኑ" አላቸውና የቅዱሳን በድኖች ወደ አሉበት ዋሻ ውስጥ አስገባቸውና "የከበራችሁ አባቶቼ ሆይ እናንተ ዐርፈን ተኝተናል አትበሉ እነሆ አንዱን ክርስቶስን ሁለት ባሕርይ የሚያደርግ በውስጡ የተጻፈበትን ይህን ደብዳቤ አምጥተዋልና በቃሉ አምን ዘንድ በውስጡም እፈርም ዘንድ ታዙኛላችሁን ወይም አታዙኝም የምሠራውንም ካልነገራችሁኝ ሕያው እግዚአብሔር ዐፅማቻችሁን ከዚህ ቦታ አወጣለሁ" አላቸው። ❤ ያን ጊዜ ሰዎች ሁሉም እየሰሙ ከአስከሬናቸው "የአባቶቻችንን የሐዋርያትንና የሦስት መቶ ዐሥራ ስምንቱን የቀናች ሃይማኖትን አትተው ይህንንም የረከሰ ደብዳቤ አትከተል ከአስከሬናችን ቦታ አርቀው እንጂ" የሚል ቃል ወጣ የንጉሥ መልክተኞችም ይህን ነገር ሰምተው እጅግ አደነቁ በላያቸውም ታላቅ ፍርሀት አደረባቸው ወደ ንጉሡም አልተመለሱም ራሳቸውን ተላጭተው መነኰሱ እንጂ እስከ ዐረፉም ድረስ ብዙ ዘመን እየተጋደሉ ኖሩ። የከበረ አባ ለንጊዮስ ያማረ ተጋድሎውን ጨርሶ እግዚአብሔርንም አገልግሎ የካቲት 2 ቀን በሰላም ዐረፈ የሕይወት አክሊልንም ተቀበለ። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በአባ ለጊዮኖስ በጸሎቱ ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን። ምንጭ፦ የካቲት 2 ስንክሳር። + + + ❤ የዕለቱ የማኅሌት ምስባክ፦ "ለስሒት መኑ ይሌብዋ። እምኅቡዓትየ አንጽሐኒ። ወእምነኪር መሐኮ ለገብርከ። መዝ 18፥12። የሚበበው ወንጌል ማቴ 5፥32-33። + + + ❤ የዕለቱ የቅዳሴ ምስባክ፦ "አንተ አጽናዕካ ለባሕር በኃይልከ። ወአንተ ሰበርከ ርእሰ ከይሲ በውስተ ማይ። ወአንተ ቀጥቀጥከ ለአርእስቲሁ ለከይሲ"። መዝ 73፥13-14። የሚነበቡት መልዕክታት ኤፊ 6፥10-19፣ ይሁ 1፥17-ፍ.ም እና የሐዋ ሥራ 28፥1-7። የሚነበበው ወንጌል ማር 16፥14-ፍ.ም። የሚቀደሰው ወንጌል የቅዱስ ዮሐንስ ወልደ ነጎድጓድ ነው። መልካም የአቡነ ጳውሊ የዕረፍት በዓል። ለሁላችንም ይሁንልን። ❤ በየቀኑ ይህን ቴሌግራም ላይ ማግት ከፈለጉ ከታች ያለውን ሊኩን ይጫኑት። @eotcw

❤ ከዚህም በኋላ አባ እንጦኒ አባ ጳውሊን "አባቴ ሆይ ይህ አስኬማ በምድር ላይ ይበዛ እንደሆነ ወይም አለመብዛቱን ትነግረኝ ዘንድ እሻለሁ" አለው። የከበረ ጳውሊም ወደ ሰማይ ተመለከተና ፈገግ አለ። ከዚህም በኋላ አዘነ ጩኾም አለቀሰ አባ እንጦንዮስም "ፈገግ ስትል በአየውህ ጊዜ ደስ አለኝ በአዘንክም ጊዜ አዘንኩ" አለው። የከበረ ጳውሊም እንዲህ ብሎ መለሰለት "እሊህ ተራሮችና በረሐዎች እግዚአብሔር ከሁሉ አገሮች መርጦ ለሚሰበስባቸው ንጹሐን ርግቦች ማደሪያዎች ይሆናሉ"። ❤ "ዳግመኛም ይህ ስም ያልፋል ስማቸውም መነኰሳት ይባላሉ እነርሱም ብዙ ዘመናት ደስ ይላቸዋል እግዚአብሔርም ከቁጣው ቀን አስቀድሞ ከዚያ ያፈልሳቸዋል። ከእነርሱም በኋላ ሰምተው ለመምህሮቻቸው የማይታዘዙ ትውልድ ይነሣሉ ስለ ነፍሳቸውም ድኅነት በቀንና በሌሊት የማይተጉና የማይጸልዩ ናቸው። ያን ጊዜ እግዚአብሔር ተቆጥቶ ይፈርዳል የማያስተውሉ ሕግ የሌላቸው አረማውያንም ተነሥተው ገዳማቱንና አድባራቱን ያጠፋሉ ብዙ ዘመናትም ምድረ በዳ ይሆናሉ የቅዱሳን መታሰቢያቸው አይጠፋም እግዚአብሔርም በሌሎች ሰዎች ልቡና ይቅርታውን ያሳድርባቸዋል እነርሱም ወደ ገዳማቱና ወደ አድባራቱ በመሔድ በውስጣቸው ዳግመኛ ይኖራሉ ሰይጣንም ወደ ገዳማት ሔዶ በመካከላቸው ጸብን ይዘራል እነርሱም የእግዚአብሔርን ፍቅር ገንዘብ በማድረግ ጨክነው አልታገሡባትምና ምንኵስናቸውን አስኬማቸውን ትተው ወደ ዓለም ይወርዳሉ "በትዕግሥታችሁ ነፍሳችሁን ገንዘብ ታደርጓታላችሁ" የሚለውን ጽሑፍ አላስተዋሉምና"። ❤ እንጦንዮስም "የከበርክ አባቴ ጳውሊ ሆይ ፊትህን አይ ዘንድ የታደልኩባት ሰዓት የተባረከች ናት" አለ። የከበረ አባ ጳውሊም "አሁን ወደ ማደሪያህ ሒድ ቈስጠንጢኖስ ለሊቀ ጳጳሳት አትናቴዎስ የሰጠውን ልብስ እርሱም አንተን ያለበሳትን ያቺን ከአንተ ጋር ይዘሃት ና ሥጋዬን በርሷ ትገንዝ ዘንድ" ብሎ ተናገረው የተሠወረውን በማወቁ እጅግ አደነቀ የተነበየለትንም ትንቢት ሁሉ አመነ። ዳግመኛም እንዲህ አለው "በሰው ሁሉ ላይ እንደተሠራ ከዓለም የምወጣበት ጊዜዬ ቀርቧልና ፈጥነህ ሒድና ተመለስ እርሱም ከአባ ጳውሊ ዘንድ ወጥቶ ወደ በዓቱ እስኪደርስ የሁለት ቀን ጎዳና ተጓዘ ያቺንም ልብስ ይዞ ተመለሰ በመንገድም እየተጓዘ ሳለ በአየር ውስጥ አባ ቡላን የመላእክትንም ማኅበር አየ "ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን" ይሉ ነበር። ❤ ሁለተኛም "እግዚአብሔር ኢየሱስ ክርስቶስ የመረጠህ ሰላምታ ፍቅር አንድነት ይገባሃል የእግዚአብሔር ሰው አንተ ጳውሊ የተመሰገንክ ነህ እንግዲህስ በሰማያዊ መንግሥት ከመላእክት ጋር ደስ ይበልህ የጨለማውን ዓለም ትተህ የብርሃን ሀገርን አግኝተሃልና ወደ ዘላለማዊ ተድላ ደስታ ይወስዱሃልና የእግዚአብሔር ማደሪያ የሆንክ አንተ ገዳማዊ ጳውሎስ በትውልድህ የከበርክና የተመሰገንክ ነህ" እንዲህ እያሉ ተሠወሩ። ❤ የከበረ እንጦኒም "ይህች ወደ ሰማይ የሚያሳርጓት የአባቴ የጳውሊ ነፍስ ናት" አለ ወደ በዓቱም በገባ ጊዜ እንደ ሰገደ ሁኖ እጆቹም በመስቀል ምልክት ተዘርግተው አገኘው አንሥቶም ሸፈነው "አባቴ ሆይ በሰማያዊ ማደሪያህ ሁነህ አስበኝ" ብሎ በላዩ አለቀሰ። ❤ ከዚህም በኋላ ተነሥቶ በዚያች ልብስ ሥጋውን ገነዘና በላዩ የቤተ ክርስቲያንን የጸሎት ሥርዓት ፈጸመ አደረሰም ከዚህም ቀጥሎ ከእርሱ ጋር የተማከርኩት ነገር የለም ምን ላድርግ ብሎ አሰበ በዚያንም ጊዜ አንበሶች መጡ እጅ ነሡትም ቀድሞ እንደሚያውቁትም ዘንበል ብለው የእግሩን ትቢያ ላሱ መቃብሩን በየት ቦታ እንቆፍርለት እንደሚሉ አመለከቱት እርሱም ምልክታቸውን አውቆ በቁመቱ ልክ ለክቶ ሰጣቸው አንዱ በራስጌ አንዱ በግርጌ ሁነው ቆፈሩ በአደረሱም ጊዜ "በቃችሁ" ብሎ አመለከታቸው እሊህ አንበሶችም ወጥተው ሰገዱለት። እርሱም ባረካቸውና ወደ ቦታቸው ሔዱ የከበረ እንጦኒ ወደ መቃብር አስገብቶ ዘጋው። ከሰኔል ቅጠልም የተሠራች ዐጽፉን ወሰደ የአባቱን ገንዘብ እንደሚወርስ ልጅ ነውና ወደ እስክንድርያም ሔደ፡፡ ወደ ሊቀ ጳጳሳት አትናቴዎስም ገብቶ ከከበረ አባ ጳውሊ የሆነውን ሁሉ ነገረውና ያቺን ከሰኔል የተሠራች ዐጽፍ ሰጠው። ❤ ሊቀ ጳጳሳት አትናቴዎስም የከበረ ጳውሊን ዜና በሰማ ጊዜ ፈጽሞ ደስ አለው ያቺንም ዐጽፍ ተቀብሎ በእርሱ ዘንድ አኖራት በየዓመቱም በከበረ በልደት በዓል በጥምቀትም በዓል በመድኃኒታችን ክርስቶስ ትንሣኤ በዓልም ሦስት ጊዜ ይለብሳት ነበር። ❤ ጌታችንም የቅዱስ ጳውሊን የልብሱን ክብር ሊገልጥ ወደደ በዚያችም ወቅት አንድ ወጣት ልጅ ሞተ አባ አትናቴዎስም ያቺን ልብስ በሞተው ላይ አኖራት ወዲያውኑ ተነሣ ይህንንም ያየ ኤጲስቆጶስ አባ ኤስድሮስ ምስክር ሆነ ይችም ተአምር በአገሮች ሁሉ ተሰማች። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በከበረ በአባ ጳውሊ ጸሎት ይማረን በረከቱ ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን። + + + ❤ ሐዋርያው ቅዱስ ቶማስ ያደረገው ተአምር፦ ጌታችን ወደ አዘዘው ሊአስተምር በወጣ ጊዜ ከመንገድ ጥቂት ፈቀቅ አለ ድንገትም የሞተ ጐልማሳ አየ መልኩ እጅግ የሚያምር ነበር ሐዋርያውም "አቤቱ ይህን ጥፋት አይ ዘንድ ወደዚህ አመጣኸኝን ነገር ግን ፈቃድህ ይሁን" አለ። ❤ ከዚህም በኋላ ስለሞተው ሰው ጸለየ ያን ጊዜ ታላቅ ከይሲ ከደንጊያዎች ውስጥ ወጥቶ በጅራቱ ምድሩን እየደበደበ መጣ "የክርስቶስ ሐዋርያ ሆይ እኔ ካንተ ጋር ምን አለኝ ሥራዬን ልትዘልፍ መጣህን" ብሎ በታላቅ ድምጽ ጮኸ ሐዋርያውም "አዎን ሥራህን ተናገር" አለው። ከሲውም እንዲህ አለ "በዚህ ቦታ አንጻር መልከ መልካም ሴት ነበረች እኔ የምወዳት ናት ይህም ጐልማሳ ሲሰማት አየሁት በሰንበት ቀንም ከርሷ ጋር አደረ ስለዚህም ነክሼ በመርዝ ገደልኩት" ሐዋርያውም "መርዝህን ከሱ ትወስድ ዘንድ በጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ስም አዝዤሃለሁ" አለው። ሒዶም ከዚህ ከሞተው መርዙን መጠጠና ወሰደ ወዲያውኑ ተነፍቶ አበጠ ተሠንጥቆም ሞተ የሞተውም ሰው ድኖ ተነሣ። ስለዚች ምልክትም ብዙዎች በክብር ባለቤት ጌታችን አመኑ እርሱም ሃይማኖትን አስተምሮ የክርስትና ጥምቀትን አጠመቃቸው። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በሐዋርያው በአባታችን በቅዱስ ቶማስ ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን። + + + ❤ የደብረ ዝጋግ ገዳም አበ ምኔት አባ ለንጊኖስ፦ ይህም ቅዱስ ከኪልቅያ አገር ነው በዚያም መነኰሰ መምህሩም ክርስቶስን የሚወድ ሰው ከሚሰጠውም ክብር የሚሸሽ ነበር። በዚያንም ጊዜ የገዳማቸው አበ ምኔት ዐረፈ ይህንንም ስሙ ሉክያኖስ የተባለ አረጋዊ መምህሩን አበ ምኔትነት ሊሾሙት መነኰሳቱ ወደዱ እርሱም ደቀ መዝሙሩን ለንጊኖስን ይዞ በጭልታ ከኪልቅያ ወጥቶ ወደ ሶርያ አገር ሔደ በአንዲት ቤተ ክርስቲያንም ግቢ በአንድነት ተቀመጡ በእጆቻቸውም ብዙዎች ድንቆች ተአምራቶችን ያደርግ ዘንድ ከንቱ ውዳሴና ክብር ሆነባቸው። ❤ አባ ለንጊኖስም በመምህሩ ምክር ወጥቶ ወደ ግብጽ አገር ሔደ ወደ ደብረ ዝጋግ ገዳምም በገባ ጊዜ በደስታ ተቀበሉትና ከእርሳቸው ጋራ ኖረ ከዚያም በኋላ አበ ምኔቱ ዐረፈ ተጋድሎውን ትሩፋቱንና ደግነቱን ስለ አወቁ በደብረ ዝጋግ ገዳም ላይ አባ ለንጊኖስን አበ ምኔት አድርገው ሾሙት። ከጥቂትም ወራት በኋላ መምህሩ አባ ሉክያኖስ መጣ የመርከቦችን ጣሪያዎች እየሠራ በእጆቻቸውም ከሚሠሩት እየተመገቡ በአንድ ልብ በመሆንም በአንድነት ኖሩ እግዚአብሔርም በእጆቻቸው ብዙዎች የሆነ ድንቆች ተአምራቶችን አደረገ

❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤ ❤ የካቲት ፪ (2) ቀን። ❤ እንኳን ለመላእክት ወገን ለሆነ ለገዳማውያን ባሕታውያን (መናንያን) ሁሉ አለቃ ለሆነ ለከበረ ለታላቁ አባት ለአባ ጳውሊ ለዕረፍት በዓል፣ ለከበረ ለሐዋርያው ቅዱስ ቶማስ አንድ ከይስ ነድፎ የገደለው ሰው ተምራትን በማድረግ ከሞት ላስነሳበትና ከይሲውን በመግደል ብዙዎችን አስተምሮ ላጠመቀበትና ከእስክንድርያ ውጭ ለደብረ ዝጋግ ገዳም አበ ምኔት የቅዱሳን ዐፅም ቃል በቃል በማጋገር የሃይማኖት ነገር ለተረዳ ለከበረ አባት ለአባ ለንጊኖስ ለዕረፍት በዓል በሰላም አደረሰን። ከእነዚህ ቅዱሳን እግዚአብሔር ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን። + + + ❤ "ሰላም ለአባቱ ጳውሊ ዘንጉሥ ወዓሊ፤ ገዳማዊ ዘበአማን ኅሩይ፤ ርእሶሙ ለፈላስያን እለ በገዳም"። ትርጉም፦ በበረሓ ላሉ ባሕታውያን (መናንያን) አለቃቸው፤ በእውነት የተመረጠ ገዳማዊ፤ የንጉሥ ሎሌ ለኾነ ለአባ ጳውሊ ሰላምታ ይገባል። ሊቁ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ በተአምኆ ቅዱሳን ላይ። + + + ❤ ርዕሰ ገዳማውያን ባሕታውያን(መናንያን) አቡነ ጳውሊ፦ ይህም ቅዱስ ከእስክንድርያ አገር ጴጥሮስ የሚባል ወንድም አለው አባታቸውም የገንዘቡ ብዛት ሊቈጠር የማይቻል እጅግ ባለጸጋ ነበር በዐረፈም ጊዜ የኀዘናቸው ቀን ሲፈጸም ርስቱንና ገንዘቡን ሊካፈሉ ጀመሩ ጴጥሮስም ታላቁን ክፍል ወደራሱ በመውሰድ የሚያንሰውን ለጳውሊ የሚሰጠው ሆነ። ስለዚህም ጳውሊ አዘነና "ከአባቴ ርስት በትክክል ለምን አትሰጠኝም?" አለው እርሱም "አንተ ወጣት ስለሆንክ ታባክነዋለህ እስከ ምታድግ እኔ እጠብቅልሃለሁ" ብሎ መለሰለት። ❤ ስለዚህም ጳውሊ ተቆጣና እርስ በርሳቸው ተጣሉ ይፈርድላቸውም ዘንድ ወደ ዳኛ ሔዱ እነርሱም ወደ ዳኛ ሲሔዱ ሰዎች ተሸክመውት ወደ ሚቀብሩበት ሲወስዱት ብዙዎችም የተከተሉትን የሞተ ሰውን አገኙ ጳውሊም ከተከተሉት አንዱን ሰው "ዛሬ የሞተው ማን?" ነው ብሎ ጠየቀው። ያም ሰው እንዲህ ብሎ መለሰለት "ልጄ ሆይ ዕወቅ አስተውል ይህ የሞተ ሰው በወርቅ በብር እጅግ ባለጸጋ የሆነ ሁል ጊዜ ደስ የሚለው ነበር አሁንም እነሆ ይህን ሁሉ ትቶ ራቁቱን ወደ መቃብር ወደማይመለስበት መንገድ ይሔዳል በኃጢአት ማዕበል ውስጥ እያለ ሙቷልና። አሁንም ልጄ ሆይ ስለ ነፍሳችን ድኅነት ልንታገል ይገባናል እኛ መቼ እንደምንሞት አናውቅምና ነገር ግን በዚህ ዓለም ውስጥ ገንዘብ ኑሮት ሥልጣንም ኑሮት ሳለ ይህን ሁሉ የተወ የተመሰገነ ነው እርሱ የቅዱሳን ሀገር በሆነች በኢየሩሳሌም ሰማያዊት ታላቅ ክብርን ይቀበላልና"። ❤ የከበረ ጳውሊም ይህን ነገር በሰማ ጊዜ ከልቡ አዘነ እንዲህም አለ "የዚህ የኃላፊው ዓለም ገንዘብ ምኔ ነው ምን ይጠቅመኛል ከጥቂት ቀኖች በኋላ ትቼው ራቁቴን የምሔድ አይደለሁምን" አለ። ከዚህም በኋላ ወደ ወንድሙ ተመልሶ "ወንድሜ ሆይ ወደ ቤታችን እንመለስ ከእንግዲህ ስለ ገንዘብ ምንም ምን ከአንተ ጋር አልነጋገርም" አለው። ❤ ከዚህም በኋላ ከወንድሙ ሸሽቶ ከሀገሩ ወጣ ከመቃብር ቤት ውስጥም ሦስት ቀንና ሦስት ሌሊት መንገዱን ይመራው ዘንድ ወደ እግዚአብሔር እየጸለየና እየማለደ ኖረ። ወንድሙ ጴጥሮስም በሀገር ውስጥ እየዞረ ሲፈልገው ሰነበተ ግን አላገኘውም ታላቅ ኃዘንንም አዘነ። የተመሰገነ ጳውሊ ግን ሦስት ቀኖች ያህል በዚያች መቃብር ቤት ሲኖር መብልና መጠጥን አላሰበም ፍርሀትና ድንጋፄም አልደረሰበትም አምላካዊ ኃይል ትጠብቀው ነበርና። ❤ በአራተኛዪቱም ዕለት እግዚአብሔር ወደርሱ መልአኩን ላከ ከዚያም ነጥቆ ወሰደው በምሥራቅ በኵል በምትገኝ በረሀ ውስጥ አኖረው በዚያም የውኃ ምንጭ አለ መልአኩም ሰላምታ ሰጥቶት ወደ ሰማይ ዐረገ የከበረ ጳውሊም አራዊት የሚኖሩበትን ጒድጓዶች አግኝቶ ወደ አንዲቱ ፍርኩታ ገባ ልብሱንም ሰኔል ሠርቶ ለበሰ። እንዲህም ብሎ ጸለየ "የሕያው የእግዚአብሔር ልጅ ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ ርኀራኄ ከሌለው ጠላት እጅ ጠብቀኝ አድነኝም ተጋድሎዬን እስከምፈጽም ተጸናኝ ዘንድ ቸርነትህ ወደእኔ ትምጣ የትውልድ ሁሉ ንጉሥ ሆይ ኃይል ጌትነት ክብር ገንዘብህ ነውና ለዘላለሙ"። ❤ በዚያችም ዋሻ ውስጥ ሰማንያ ዓመት ኖረ ከሰውም ከቶ ማንንም አላየም ልብሱም ከሰኔል ቅጠል የተሠራ ነው እግዚአብሔር ወደ ማታ ሁል ጊዜ ወደርሱ ቁራን ይልክለታል ከርሱም ጋራ ግማሽ እንጀራ አለ ያንን ለከበረው ጳውሊ ይሰጠዋል። ❤ የክብር ባለቤት እግዚአብሔርም ቅድስናውንና ጽድቁን ይገልጥ ዘንድ በወደደ ጊዜ መልአኩን ወደ ታለቅ አባት ወደ እንጦንዮስ ላከ ይህም እንጦንዮስ በበረሀ ውስጥ መኖርን የጀመረ እርሱ እንደሆነ በልቡ ያስብ ነበር መልአኩም እንዲህ አለው "እንጦንዮስ ሆይ ከአንተ የሁለት ቀን ጎዳና ርቆ በበረሀ ውስጥ ሰው አለ የዓለም ሰዎች ከሚረግጥባቸው የእግሩ ጫማዎች እንደ አንዲቱ ሊሆኑ የማይገባቸው ስለ ርሱም ጸሎት ዓለም ተጠብቆ የሚኖር ምድርም ፍሬዋን የምትሰጥ ጠል በምድር ላይ የሚወርድ በምድር በሚኖሩ ኃጢአተኞች ሁሉ ላይ ፀሐይ የሚወጣ የሰውም ፍጥረት በእግዚአብሔር እጅ ውስጥ ተጠብቆ የሚኖር"። ❤ አባ እንጦንዮስም ይህን ቃል በሰማ ጊዜ ተነሥቶ ወደ በረሀው መካከል ተጓዘ እግዚአብሔርም ከእርሱ ጋር ሁኖ ጎዳናውንም እንደሚጠርግለት አምኖ ሲጓዝ የሰውና የአራዊትን ፍለጋ አገኘ ያንንም ፍለጋ ተከትሎ ከቅዱስ ጳውሊ በዓት ደረሰ በሩንም አንኳኳ የከበረ አባ ጳውሊ ግን ከሰይጣን ሥራ እንደሆነ አስቦ ታላቅ ደንጊያ ወስዶ ከመዝጊያው ጀርባ አኖረ አባ እንጦንዮስም "ይሰጠኝ ዘንድ ፈለግሁ አገኝ ዘንድ ለመንኩ ይከፈትልኝም ዘንድ ቡሩን አንኳኳሁ" ብሎ አሰምቶ ተናገረ። በዚያንም ጊዜ ከፈተለትና ገባ እርስ በርሳቸውም በመንፈሳዊ ሰላምታ አጅ ተነሣሥተው በአንድነትም ጸልየው ተቀመጡ። ❤ አባ እንጦንዮስም "አባቴ ሆይ ስምህ ማነው?" አለው አባ ጳውሊም "አንተ ስሜን ካላወቅህ እስከዚች ቦታ ለምን ተጓዝክ" ብሎ መለሰለት በዚያችም ሰዓት እግዚአብሔር የእንጦንዮስን ልቡን ገለጠለትና "ገዳማዊ ጳውሎስን አየው ዘንድ ስለተገባኝ እኔ ብፁዕ ነኝ" አለ ከዚህም በኋላ እርስ በእርሳቸው የእግዚአብሔርን ልዕልናውን ቸርነቱን ይነጋገሩ ጀመር በመሸም ጊዜ ቍራ መጥቶ አንዲት ሙሉ እንጀራ ጣለለት አባ ጳውሊም አባ እንጦኒን "አንተ የእግዚአብሔር አገልጋይ እንደሆንክ አሁን አወቅሁ እስከ ዛሬ ሰማንያ ዓመት በዚህ በረሀ ስኖር እግዚአብሔር ሁልጊዜ የሚልክልኝ ግማሽ እንጀራ ነበር እነሆ አሁን ምግብህን ላከልህ" አለው። ❤ ከዚህም በኋላ ተነሥተው የማዕድ ጸሎት ጸለዩ በልተውም እግዚአብሔርን አመሰገኑት መላ ሌሊቱንም ሲጸልዩ አደሩ። ነግቶ ፀሐይ በወጣ ጊዜም እርስ በርሳቸው ሰላምታ ተሰጣጡ አባ እንጦኒም "አባቴ ሆይ በዚህ ሁሉ ዘመን ሥጋውንና ደሙን ከወዴት ትቀበላለህ?" አለው የከበረ ጳውሊም "እግዚአብሔር መልአኩን ይልክልኛል በቀዳሚት ሰንበትና በእሑድ ሰንበት በየሳምንቱ ከሥጋውና ከደሙ ያቀብለኛል በዘመኑም ሁሉ እንዲህ ያደርግልኛል" ብሎ መለሰለት።

✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝ ጉባኤ ቃና ዘወልደሐና ዘዲ/ን የአብስራ ጌታሁን እምገፀሐና ማሰነ ምክነተሜልኮል ዶርሆ እስመ ርእየ በትረ በእዳ እምነልቡ ነቂሆ ትርጉም እና ሰም፦ የሜልኮል ምክነት ዶሮ ከሐና ፊት ጠፋ ከልቡ ነቅቶ በእጇ ዱላን አይቷልና ከፊቷ ጠፋ ወርቅ፦ የሜልኮል ምክነት በዶሮ ተመስሎ የመጣ ሲሆን ከሐና ፊት ጠፋ የተባለውም ሐና ምክነቷ ጠፍቶ ወልዳለች ማለት ሲሆን ከሐና እጅም በትር(ዱላን) አየ የተባለው እመቤታችንን ሲሆን እመቤታችን ስትወልድ ምክነቷ እንደጠፋ በዚህ ቅኔ በሰምና ወርቅ ተጠቅሎ ቀርቧል ሙያ፦ እም...አገባብ ፍቺው ከ ሙያው መነሻ ገፅ..........የመነሻ ባለቤት ሐና........የገፅ ዘርፍ ማሰነ........ማሰሪያ ይስባል እንጂ አይሳብም ምክነት ዶሮ ምሳሌ ዶሮ ሰም ምክነት ወርቅ ተመስሎ የቅኔ ባለቤት ሜልኮል.......የምክነት ዘርፍ እስመ .......አገባብ ፍቺው ና ሙያው አስረጅ አስረጅነቱ ለማሰነ ርእየ.......እንዳያስር እስመ ይጠብቀዋል በትር.......የርእየ ተሳቢ በ.........አገባብ ፍቺው በቁም ቀሪ ሙያው ማድረጊያ እድ..........የማድረጊያ ባለቤት እም...........አገባብ ፍቺው ከ ሙያው መነሻ ልብ.......የመነሻ ባለቤት ነቂሆ ..........ቦዝ አንቀፅ ይስባል እንጂ አያስርም @Eotcw

❤ ሌሎችም ከአገረ ፍዩም የጎልማሳውን ሥጋ ሰርቀው ወደ ፍዩም አገር ሲአደርሱት የእግዚአብሔር መልአክ ነጥቆ ወደ አባቱ ሥጋ መለሰው መነኰሳቱም ብዙ ጊዜ ፈተኑት የወጣቱን ሥጋ ከአባቱ ሥጋ የሚለዩት ሁነው ነበር። በጥዋትም በአንድነት ያገኙአቸዋል ከመነኰሳቱም አንዱ እንዲህ የሚለውን እስኪያይና እስከሚሰማ ድረስ። "ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛ በሕይወተ ሥጋ ሳለን እርስበርሳችን አልተለያየንም በጌታችን ክርስቶስም ዘንድ አልተለያየንም እናንተ እርስ በርሳችን ለምን ትለያዩናላችሁ" ከዚያችም ቀን ወዲህ የለያቸው የለም። ❤ አረማውያንም የአስቄጥስን ገዳም በአጠፉ ጊዜ ስለ ቅዱሳን ሰማዕታት ሥጋ መነኰሳቱ ፈሩ ከቦታቸውም አፍልሰው ወስደው በከበረ አባ መቃርስ ቤተ ክርስቲያን ጎን አኖሩዋቸው የመቃብር ቦታም ሠሩላቸው በላዩም ሊቀ ጳጳሳት ታውዳስዮስ ዘመን በስማቸው ቤተ ክርስቲያን ሠሩላቸው። ሊቀ ጳጳሳት አባ ብንያሚንም ወደ አስቄጥስ ገዳም በመጣ ጊዜ የካቲት አምስት ቀን እንዲከበር በዓልን ሠራላቸው ይኸውም ሥጋቸው የተገለጠበት ነው ቤተ ክርስቲያናቸውም እስከ ዛሬ አለች በቅብጢ ቋንቋ ብህም ብሲት በመባል የታወቀች ናት ይህም አርባ ዘጠኝ ማለት ነው። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በከበሩ ሰማዕታት ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን። ምንጭ፦ የጥር 26 ስንክሳር። + + + ❤ "ሰላም ለክሙ ሱቱፋነ ፃማ ወሕማም። አርብዓ ወተሰዓቱ አእሩገ ገዳም። ምስለ ላእከ ንጉሥ ወወልዱ ዘተከልክሙ ዮም። ለአንስጣስያ ቅድስት ዓዲ ሰላም። ጽንዐ ወራዙት ዘሞዐት በድካም"። ሊቁ አርከ ሥሉስ (አርኬ)የጥር26። + + + ❤ የዕለቱ ምስባክ፦ "እበውእ ቤተከ ምስለ መባእየ። ወእሁብ ብጽዓትየ ዘነበብኩ በአፉየ። ዘእቤ በከናፍርየ አመ ምንዳቤየ"። መዝ 65፥13-14። የሚነበቡት መልዕክታት 2ኛ ቆሮ 2፥1-8፣ 1ኛ ጴጥ 5፥9-ፍ.ም እና የሐዋ ሥራ 16፥14-16። የሚነበበው ወንጌል ሉቃ 11፥1-19። የሚቀደሰው ቅዳሴ የቅዱስ ዲዮስቆሮስ ቅዳሴ ነው። መልካም በዓል የቅድስት ለሁላችንም ይሁንልን። ❤ በየቀኑ ይህን ቴሌግራም ላይ ማግት ከፈለጉ ከታች ያለውን ሊኩን ይጫኑት። @Eotcw

❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አሜን"። ❤ ❤ ጥር ፳፮ (26) ቀን። ❤ እንኳን ከቁስጥንጥንያ ቤተ መንግሥት ታላላቆች ለአንዱ ልጅ ለሆነች በዋሻ ውስጥ ለብቻዋ ወንድ መስላ በመኖር ለ28ዓመታት በታላቅ ተጋድሎ ለተጋደለች ለታላቋ ጻድቅ ለቅድስት አንስጣስያ ለዕረፍት በዓልና ለጻድቅ አርቃዴዎስ ልጅ በሆነ በጻድቁ ቴዎዶስዮስ ዘመነ መንግስት አርባ ዘጠኝ ለሆኑ ለከበሩ አረጋውያን መነኰሳት ከንጉሥ መልክተኛ ከልጁም ጋር ሰማዕትነት ለተቀበሉበት ለዕረፍታቸው በዓላቸው። በተጨማሪ በዚችን ከሚታሰቡ፦ ከከበሩ መጥረያስ፣ ከስርስንዮስ ሰማዕትና ከመፍቀሬ ነዳያን ከዮሴፍ ከመታሰቢያቸው ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን። + + + ❤ ቅድስት አንስጣስያ፦ ይቺም ቅድስት ከቊስጥንጥንያ ቤተ መንግሥት ታላላቆች የአንዱ ልጅ ናት። እርሷም በላይዋ በደም ግባቷ እጅግ ያማረች ናት ንጉሥ ብስጥያኖስም ሊአገባት ፈለገ እርሷ ግን ይህን በልቧ አልወደደችም የንጉሡም ሚስቱ በሕይወት ነበረች ንጉሡ እንደሚሻትም ለንግሥት ሚስቱ አስረዳቻት በዚያንም ጊዜ ንግሥቲቱ ወደ ግብጽ በመርከብ አሳፍራ በሥውር ሸኘቻት ከእስክንድርያም ከተማ ውጭ ገዳም አሠራችላት በዚያም ኖረች ያም ገዳም በስሟ ተጠራ። ❤ የከበረች አንስጣስያም በግብጽ አገር እንዳለች ንጉሥ በአወቀ ጊዜ ፈልገው ወደርሱ ያመጡአት ዘንድ መልክተኞችን ላከ ይህንንም ነገር ተረድታ ተነሣች የወንዶችንም ልብስ ለብሳ መስፍንን መሰለች ወደ አስቆጥስ ገዳም ሔዳ ወደ አበ ምኔቱ ወደ አባ ዳንኤል ገባች ምሥጢርዋን ሁሉ ገለጠችለት። እርሱም ወስዶ በዋሻ ውስጥ ለብቻዋ አኖራት እርሷም ሴት እንደሆነች ማንም አላወቀም በየሳምንቱም በእንስራ ውኃ ቀድቶ ከዚያ ዋሻ ደጃፍ እንዲያኖር አንዱን ደግ አረጋዊ አባ ዳንኤል አዘዘው ያም ሽማግሌ አያውቅም ይችም ቅድስት አንስጣስያ በጸሎት በጾምና በመስገድ በመትጋትም እየተጋደለች ሃያ ስምንት ዓመት ኖረች። ውኃ ሲቀዳላት የነበረ ያ ሽማግሌ በዐረፈ ጊዜ አባ ዳንኤልም ያ ሽማግሌ ሲሠራ እንደ ነበር ይሠራ ዘንድ ረዳቱን አዘዘው ቅድስት አንስጣስያም ሀሳቧን በገል ላይ እየጻፈች በበዓቷ ደጃፍ ታኖረው ነበር ረድኡም ወደ መምህሩ ወደ አባ ዳንኤል ይወስደዋል። የምትጽፈውንም ምን እንደሆነ አያውቅም። ❤ በአንዲት ዕለትም የጻፈችበትን ገል አመጣ አባ ዳንኤልም በአነበባት ጊዜ አለቀሰ ረድኡንም "ልጄ ሆይ ተነሥ የዚያን ቅዱስ ሰው ሥጋ ሒደን እንቅበር እርሱ ከዚህ ዓለም ይለያልና" አለው። በሔዱም ጊዜ ወደ በዓቷ ገብተው ከእርሷ ተባረኩ እርሷም አባ ዳንኤልን "አባቴ ሆይ ስለ እግዚአብሔር ብለህ በላዬ ካለው በቀር በምንም ልብስ እንዳትገንዘኝ" አለችው ከዚህም በኋላ የከበረች አንስጣስያ ተነሥታ ጸለየች "እኔ በእግዚአብሔር ዘንድ አደራ አስጠበቅኋችሁ" አለችና በምድር ላይ ተቀምጣ ዐረፈች በላይዋም አለቀሱ ሊቀብሩዋትም አስበው ረድኡ ይገንዛት ዘንድ ሲቀርብ እንደ በለስ ቅጠሎች ደርቀው ጡቶቿን ተመለከተ። ከተጋድሎ ብዛትም የተነሣ እንዲህ ሁኗልና አባ ዳንኤልም አይቶ በማድነቅ ዝም አለ። ❤ ከቀበርዋትም በኋላ ወደ በዓታቸው ተመለሱ ረድኡም ወደ አባ ዳንኤል ቀርቦ ሰገደለትና እንዲህ ሲል ለመነው "ስለ እግዚአብሔር ብለህ የዚችን ቅድስት ዜናዋን ንገረኝ ሴት እንደሆነች አይቻለሁ"። አባ ዳንኤልም የገድሏን ዜና ሊነግረው ጀመረ እንዲህም አለው "እርሷ ከቊስጥንጥንያ አገር ከመንግሥት ታላላቅ ወገኖች ውስጥ የሆነች ስትሆን ሰውነቷን ለክርስቶስ ሰጥታ የዚህን የኃላፊውን ዓለም ክብር ሁሉ ተወች። ሰይጣንን ተዋጋችበት ከዚህ ከታላቅ ተጋድሎዋ ለእኛ ለወንዶች መመከሪያ ሊሆነን ይገባል ከእርሷም የሴቶችን ደካማነት አርቃ የኃይለኞች ወንዶችን ብርታት ገንዘብ እስከማድረግ ደርሳ እግዚአብሔርን አገልግለችው" አለው። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በቅድስት አንስጣስያ በጸሎቷ ይማረን በረከቷም ከእኛ ጋር ይኑር ለዘላለሙ አሜን። + + + ❤ በጻድቁ ንጉሥ በቴዎዶስዮስ ዘመን የከበሩ አርባ ዘጠኝ አረጋውያን መነኰሳትና ከንጉሥ መልክተኞች ከልጁም ጋር ሰማዕት መሆጋቸው፦ የሰማዕትነታቸው ምክንያት ቴዎዶስዮስ ልጅ አልነበረውም በአስቄጥስ ገዳም ወደ ሚኖሩ አረጋውያን መነኰሳት ልጅን ይሰጠው ዘንድ ወደ እግዚአብሔር እንዲማልዱለት እየለመናቸው መልእክትን ላከ ከውስጣቸውም ስሙ ቢስዱራ የሚባል አንድ ታላቅ አረጋዊ ስለ እርሱም ወደ ንጉሥ እንዲህ ብሎ ጻፈ "ከአንተ በኋላ ከሚነሡ መናፍቃን ጋር አንድ እንዳይሆን ልጅን ይሰጥህ ዘንድ እግዚአብሔር አልወደደም"። መልእክቱን በአነበበ ጊዜ ንጉሥ ደስ ብሎት እግዚአብሔርን አመሰገነው ሃሳቡንም አሳረፈ። ❤ ዳግመኛም ግብዞች ሰዎች ሌላ ሚስት አግብቶ ከእርሱ በኋላ በዙፋኑ የሚቀመጥ ልጅን ይወልድ ዘንድ መከሩት እርሱም "የትሩፋታቸው ዜና በዓለም ዳርቻ ሁሉ ደርሷልና በአስቄጥስ ገዳም ከሚኖሩ ቅዱሳን አረጋውያን ትእዛዝ በቀር ምን ምንም አላደርግም" ብሎ መለሰላቸው። ስለዚህም አረጋውያንን ይጠይቅ ዘንድ ንጉሥ መልክተኛውን ዳግመኛ ላከ ለንጉሡም መልእክተኛ ልጅ ነበረው ልጁም በረከታቸውን ይቀበል ዘንድ ከእርሱ ጋራ ወደ አረጋውያን እንዲወስደው አባቱን ለመነው መልክእተኛው ከልጁ ወደ አረጋውያን በደረሰ ጊዜ የንጉሥ ደብዳቤ ሰጣቸው እርሱንም አነበቧት ያን ጊዜ ግን አባ ቢስዱራ ስለሞተ አልተገኘም አረጋውያንም የንጉሡን መልእክተኛ የአባ ቢስዱራ ሥጋ ወዳለበት ወሰዱትና አደረሱት ሥጋውንም "አባታችን ሆይ እነሆ የንጉሥ መልክት ወደ እኛ ደረሰ እኛም የምንመልስለትን አናውቅም" አሉት። በዚያንም ጊዜ አረጋዊ አባ ቢስዱራ ተነሥቶ "እግዚአብሔር ልጅን ሊሰጥህ አልፈቀድም አላልኩህምን አለ በሉት ለንጉሥ አሁንም ከዓላውያን ጋር አንድ ሁኖ እንዳይረክስ ሌሎች ሴቶችንም ቢአገባ ልጅን አይሰጠውም" ይህንንም ተናግሮ ተመልሶ ተኛ። ❤ አረጋውያንም ይህን ቃል በክርታስ ጽፈው ለንጉሥ መልእክተኛ ስጡት እርሱም ወደ አገሩ ሊመለስ በተነሣ ጊዜ እነሆ የበርበር አረማውያን ደረሱ አባ ዮሐንስ የሚባል አረጋዊም ቁሞ ወገኖቹን እንዲህ አላቸው "እነሆ የበርበር ሰዎች ይገድሉን ዘንድ መጡ ምስክርነት የሚሻ ከእኔ ጋር ይቁም የሚፈራ ግን ወደ ግንብ ሒዶ ይሠወር" አለ። የሸሹም አሉ ከአባ ዮሐንስም ጋር የቀሩ አርባ ዘጠኝ አረጋውያን መነኰሳት የንጉሥ መልእክተኛም ልጅ ከጎዳና ጒዞ ላይ ዘወር ሲል በአረጋውያን ሰማዕታት ራሶች አክሊላትን ሲያኖሩ መላእክትን አያቸው የዚያም ጎልማሳ ስሙ ድያስ ነው አባቱንም "እነሆ በአረጋውያን ራሶች ላይ አክሊላትን ሲያኖሩ ረቂቃን መላእክትን አያለሁ አሁንም እንደርሳቸው አክሊልን ለመበቀል እኔ እሔዳለሁ" አለው አባቱም "ልጄ ሆይ እኔም ከአንተ ጋር እሔዳለሁ" አለው። በዚያችም ጊዜ አረጋውያን መነኰሳት ለአረማውያን ተገለጡላቸው አረማውያንም ገደሏቸው የምስክርነት አክሊልንም ተቀበሉ። ❤ አረማውያንም ከሔዱ በኋላ መነኰሳቱ ከተሠወሩበት ግምብ ወርደው የሰማዕታትን ሥጋቸውን ሰበሰቡ ገንዘውም በበዓት ውስጥ አኖሩዋቸውም በእርሳቸውም ዘንድ ሌሊቱን ሁሉ የሚጸልዩና የሚዘምሩ ከእርሳቸውም የሚባረኩ ሆኑ የአባ ዮሐንስንም ሥጋ ሰዎች ሰርቀው ባታኑን ወደሚባል አገር ወሰዱት ከእርሳቸውም ዘንድ ጥቂት ቀኖች ኖረ ከዚህም በኋላ ቅዱሳን ወደቦታው መለሱት።

❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አሜን"። ❤ ❤ ጥር ፳፭ (25) ቀን። ❤ እንኳን ለታላቁ ሰማዕት ለሮም ንጉሥ ልጅ ለከበረ ለሰማዕቱ ለቅዱስ ስብስትያኖስ ምስክርነቱ ለፈጸመበት ለዕረፍቱ በዓልና አስቀድሞ ቀራጭ ለነበነ ራሱን ለሸጠው በገድል ለተጸመደ ለኖረ ለከበረ ቅዱስ ጴጥሮስ ለዕረፍቱ በዓል በሰላም አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰበው፦ ከሰማዕት ቅዱስ አስኪላ ከመታሰቢያው እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን። + + + ❤ ሰማዕቱ ቅዱስ ስብስትያኖስ፦ ይህም የቅዱስ የሮሜ ንጉሥ ልጅ ነው። እርሱንም ወላጆቹ በተግሣጽና እግዚአብሔርን በመፍራት የአሳደጉት ነው። አባቱም ከሞቱ በኋላ ዲዮቅልጥያኖስና መክስምያኖስ ነገሡ ይህንንም ቅዱስ አገረ ገዥነት ሾሙት እንደ አባቱም እጅግ አከበሩት። እርሱሜ በጥበብና በማስተዋል ይጓዝ ነበር በሽተኞችን ሁሉ የዕውራንንም ዐይኖች በጸሎቱ ከፈተ። ❤ ከዚህም በኋላ የክብር ባለቤት ክርስቶስን ዲዮቅልጥያኖስ በካደው ጊዜ ለጣዖት ይሰግድ ዘንድ ስብስትያኖስን ግድ አለው ባልሰማውም ጊዜ ከደረቀ ግንድ ጋር አሠረው ቊጥር በሌላቸው ፍላጻዎች ይነድፉት ዘንድ አዘዘ እንደሞተም ጠርጥረው ትተውት ሔዱ ምእመናንም በሌሊት ሲመጡ በሕይወት አገኙት ፈትተውም ወደ ደሴት መካከል ወስደው በዚያ አኖሩት። ❤ ዲዮቅልጥያኖስም ሰምቶ ወደርሱ አስቀረበውና በብረት ዘንጎች ይደበድቡት ዘንድ አዘዘ እየደበደቡትም ብዙ ቀኖች ኖሩ ከዚህም በኋላ ነፍሱን አሳለፈ። ለቅድስት ውሉድስና በሕልም ተገልጦ ሥጋው ያለበትን ነገራት እርሷም ሒዳ ወደ ቅዱስ ጴጥሮስና ጳውሎስ መቃብር ወስዳ ቀበረችው። ጌታችንም መታሰቢያውን ለሚያደርግና ስሙን ለሚጠራ የቸነፈር ሕመም እንዳይቀርበው ቃል ኪዳንን ሰጠው። + + + ❤ የከበረ ቅዱስ ጴጥሮስ፦ ይህም ቅዱስ አስቀድሞ ቀራጭ ነበረ እርሱም ልቡ የደነደነ ርኅራኄ የሌለው ነው በዚህም ክፉ ስም ጨካኝ ርኅራኄ የሌለው ብለው ይጠሩታል። ከዚህም በኋላ የኃጢአተኞች ሞት የማይሻ ጌታችን ከእርሱ ምጽዋት የሚለምነውን ድኃ ላከለትና ለመነው በዚያንም ጊዜ አገልጋዩ እንጀራ ተሸክሞ ደረሰ አገልጋዩ ከተሸከመው ከራሱ ላይ አንድ እንጀራ ለዚያ ድኃ ጣለለት ይህንንም ያደረገ ስለ ርኅራኄ አይደለም ከአጠገቡ እንዲሔድለትና ከቶ ወደርሱ እንዳይመለስ ነው ምስኪኑም ተቀብሎ ወደ ማደሪያው ሔደ። ❤ በዚያችም ሌሊት ተኝቶ ሳለ በሕልሙ እንዲህ አየ ብዙዎች ሊተሳሰቡት ይሻሉ በእጆቻቸውም ሚዛኖች ተይዘዋል ብዙዎችም መልካቸው እጅግ የከፉ ጥቋቊሮች ኃጢአቱ ሁሉ ከእርሳቸው ጋር አለ በግራ በኩል ባለው ሚዛን ውስጥ አኖሩት ደግሞ ልብሳቸቻው ነጫጭ የሆኑ ከብርሃናውያን መላእክት መልካቸው ያማረ ብዙዎች ነበሩ እነርሱም ቁመው በማዘን "ምንም ያገኘነው ነገር የለም በቀኝ ባለው ሚዛን ውስጥ ምን አናኖራለሁ" ይሉ ነበር በዚያንም ጊዜ ከእርሳቸው አንዱ መልአክ ጴጥሮስ ለድኃው የጣላትን ያችን እንጀራ አምጥቶ "ከዚች እንጀራ በቀር ሌላ ከበጎ ሥራ ምንም አላገኘሁለትም" አለ ባልንጀሮቹ መላእክትም "በእነዚህ ሁሉ ኃጢአቶቹ አንጻር ይቺ ምን ትጠቅማለች" ብለው መለሱ በዚያንም ጊዜ እየፈራና እየደነገጠ ከእቅልፋ ነቅቶ ከተኛበት ተነሣ። ❤ ከዚያችም ዕለት ወዲህ ስለቀደመች ክፉ ሥራው ተጸጸተ እጅግም የሚራራ ሆነ ቤቱንና ጥሪቱን ሁሉ ሽጦ ለድኆችና ለምስኪኖች ሰጠ ራሱንም ሸጠ። ብዙዎችም ከበጎ ሥራዎች ይህን ስለ ሠራ እንደሚአመሰግኑትና እንደሚያደንቁት በአወቀ ጊዜ ከዚያ በመሸሽ ወደ አስቄጥስ ገዳም ገብቶ ከአባ መቃርስ ገዳም በዚያ መነኰሰ ፍጹም በሆነ ተጋድሎም ተጠምዶ እግዚአብሔርን አገልግሎ የዕረፍቱን ጊዜ አውቆ የከበሩ አረጋውያንን ጠርቶ ተሳለማቸውና በዚያን ጊዜ ጥር24 ቀን ዐረፈ። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በሰማዕቱ በቅዱስ ሰብስትያኖስና በአባ ጴጥሮስ በጸሎታቸ ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን። ምንጭ፦ የጥር25 ስንክሳር። + + + ❤ "ሰላም ለከ ስብስትያኖስ ሰማዕተ ዋሕድ ወልድ። ዘንዱፍ በአሕፃ ወእሡር በጒንድ። ተውላጠ ዝንቱ ፃማከ ወሕማምከ ፍድፉድ። መጽሐፈ ገድልከ በኀበ ሀሎ ዐፀድ። እግዚአብሔር አሕረመ ኢይባዕ ብድብድ"። ሊቁ አርከ ሥሉስ (አርኬ) የጥር 25። ❤ የዕለቱ የማኅሌት ምስባክ፦ "ተፈሣሕ በእግዚአብሔር ወይሁበከ ስእለተ ልብከ። ክሥት ለእግዚአብሔር ፍኖተከ። ተወከል ቦቱ ወውእቱ ይገብር ለከ"። መዝ 36፥4-5። የሚነበበው ወንጌል + + + ❤ የዕለቱ የቅዳሴ ምስባክ፦ "ዘረወ ወወሀበ ለነዳይ። ወጽድቁኒ ይነብር ለዓለም። ወይትሌዓል ቀርኑ በክብር"። መዝ 111፥9-10። የሚነበቡት መልዕክታት 2ኛ ቆሮ 9፥5-ፍ.ም፣ 1ኛ 3፥16-ፍ.ም እና የሐዋ ሥራ 4፥29-ፍ.ም። የሚነበበው ወንጌል ማር 10፥17-28። የሚቀደሰው ወንጌል የቅዱስ ዮሐንስ ወልደ ነጎድጓድ ነው። መልካም የአቡነ ሕፃን ሞዐ የልደት በዓልና የቅዱስ መርቆሬዎስ የተአምራት በዓል። ለሁላችንም ይሁንልን። ❤ በየቀኑ ይህን ቴሌግራም ላይ ማግት ከፈለጉ ከታች ያለውን ሊኩን ይጫኑት። @eotcw

❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አሜን"። ❤ ❤ ጥር ፳፭ (25) ቀን። ❤ እንኳን ለኢትዮጽያዊ ጻድቅ ለአቡነ ተክለ ሃይማኖት ለአጎት ልጅ ለታላቁ አባት ከበሬ ጋር ተጠምደው በማረስ ሰማዕትነት ለተቀበሉት ለአቡነ ሕፃን ሞዐ ለልደታቸው በዓልና ለታላቁ ሰማዕት ለቅዱስ መርቆሬዎስ በሥዕሉ ላይ አድሮ ቅዱሳን ለሆኑ ባስልዮስንና ጎርጎርዮስን በመርዳት ከሃዲውን ንጉሥ ዑልያኖስን ለገደለባት በዓል በሰላም አደረሰን። + + + ❤ "ሰላም ለጎርጎርዮስ ወለባስልዮስ ዘተናገሮሙ ሥዕሉ ለቅዱስ መርቆሬዎስ፤ ዘከመ ቀተሎ ለዑልያኖስ"። ትርጉም፦ ዑልያኖስን እንዴት እንደገደለው የቅዱስ መርቆሬዎስ ሥዕሉ የተናገራቸው ለኾነ ለጎርጎርዮስና ለባስልዮስ ሰላምታ ይገባል። ሊቁ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ በተአምኆ ቅዱሳን ላይ። + + + ❤ ሰማዕቱ ቅዱስ መርቆሬዎስ ያደረገው ተአምር፦ በቀጰዶቅያና በቂሳሪያ በተሾመ በኢጲስቆጶስ ቅዱስ ባስልዮስ ዘመን ዑልያኖስ በነገሠ ጊዜ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን ካደ። ከቅዱስ ባስልዮስ ተአምራት በአንዷ ውስጥ እንደተጻፈው ከሓዲ ዑልያኖስ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ የሚያምኑትን ከባድ ሥቃይ አደረሰባቸው። በቅዱስ ባስልዮስ ላይም ተቈጣ፤ አሰረውም። በክርስቲያኖች ላይ ከባድ ሥራ ባበዛባቸው ጊዜ ቅዱስ ባስልዮስ ስለ ከሐዲ ዑልያኖስ ወደ እግዚአብሔር ይጸልይ ይለምን ጀመረ። ወደ ቅዱስ መርቆሬዎስ ለመነ። ❤ እግዚአብሔር ጸሎቱን ሰማና ታላቁን ሰማዕት ቅዱስ መርቆሬዎስን ላከለት። በፈረስ ተጭኖ መጣና ከሓዲ ዑልያኖስን አንገቱን በጦር ወጋው። በፋርስ ምድር በውጊያ በክፉ አሟሟት ሞተ። ቅዱስ ባስልዮስ ይህን ራእይ በቅዱስ መርቆሬዎስ ሥዕል ላይ ባየ ጊዜ ፈጽሞ ደስ አለው። የታላቁ ሰማዕት የቅዱስ መርቆሬዎስ አካለ ሥጋ ያለበት ቦታ ተገልጦለት እየጸለየና እያደነቀ ገባ። ያን ጊዜ የቅዱስ መርቆሬዎስ ሰይፍና ጦር ከቅዱስ መርቆሬዎስ ሥዕል ሥር ያለበት ቦታ እስኪሞላ ድረስ ከእነርሱ ብዙ ደም እየፈሰሰ ወደ ቦታቸው ተመለሱ። ❤ ያን ጊዜ ቅዱስ ባስልዮስ ጮኸ። "የክርስቶስ ሰማዕት ሆይ፤ የእውነት ጠላት የሆነውን ዑልያኖስን ገደልከውን?" አለ። ቅዱስ መርቆሬዎስ በቅዱስ ባስልዮስ ፊት "አወን ገደልኩት" እያለ በሥዕሉ ላይ ራሱን ዘንበል አደረገ። ቅዱስ ባስልዮስ የእግዚአብሔርን ክብርና ምስጋና የኢየሱስ ክርስቶስ ሰማዕት የሆነውን የቅዱስ መርቆሬዎስን ብዙ ተአምርና ድንቅ ድንቅ ሥራ አደነቀ። የሰማዕቱ የቅዱስ መርቆሬዎስ ጸሎቱና በረቱ ከእኛ ጋር ለዘለዓለሙ ይሁን አሜን። ምንጭ፦ የቅዱስ መርቆሬዎስ ገድል ተአምር 2። + + + ❤ አቡነ ሕፃን ሞዐ፡- በአባታቸው አርከሌድስ እናታቸው ትቤ ጽዮን ይባላሉ፡፡ የተወለዱት ጥር25 ነው፡፡ አቡነ ሕፃን ሞዐ እና ከእነ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ጋር የሥጋ ዝምድና አላቸው፡፡ ይኸውም አባታቸው አርከሌድስና ጸጋ ዘአብ ወንድማማቾቸ ናቸው፡፡ አርከሌድስና ጸጋ ዘአብ ሌሎች ሌሎች አራት ወንድሞች አሏቸው፡፡ ❤ እነርሱም እንድርያስ፣ ዘርዐ አብርሃም፣ ቀሲስ ዮናስ እና ቀሲስ ዮሐንስ ናቸው፡፡ አርከሌድስ ሕፃን ሞዐን ይወልዳል፣ ጸጋ ዘአብ ተክለ ሃይማኖትን ይወልዳል፣ እንድርያስ ሳሙኤል ዘወገግን፣ዘርዐ አብርሃም ታላቁ አኖሬዎዮስን፣ ቀሲስ ዮናስ ገላውዲዮስንና የፈጠጋሩን ማትያስን፣ እና ቀሲስ ዮሐንስ ዜና ማርቆስን ይወልዳሉ፡፡ እነዚህ የከበሩ ቅዱሳን አባቶቻችን በእናታቸውም ወገን ቢሆን እንዲሁ በዝምድና የተቆራኙ ናቸው፡፡ አቡነ ሕፃን ሞዐ በሌላኛው ስማቸው ሕፃን ዘደብረ በግዕ ተብለውም ይጠራሉ፡፡ ይኸውም የደብረ በግዕን ገዳም የመሠረቱት እርሳቸው ስለሆኑ ነው፡፡ ❤ ከአራባ ሰባቱ የአገራችን ቀደምት ቅዱሳን ውስጥ አንዱ ናቸው፡፡ በመንዝና በተጉለት የሚገኙ ታላላቅ ገዳማትን አብዛኞቹን የመሠረቷቸው አቡነ ሕፃን ሞዐ ናቸው፡፡ ጻድቁ በክፉዎች ወሬና ሴራ ምክንያት ከበሬ ጋር ተጠምደው ሰማዕትነት የተቀበሉ አባት ናቸው፡፡ ከበሬ ጋር ሲታረሱ ውለው በእጅጉ ከደከማቸ በኋላ በኃይል የተነፈሱባት ምድሪቱ ዛሬም ድረስ ልክ እንደሰው የሚሞቅ ትንፋሽ ታወጣለች፡፡ ያም በጻድቁ እስትንፋስ አምሳል ከመሬት ውስጥ የሚወጣው እስትንፋስ ለአስም በሽታ መድኃኒት ሆኖ ብዙዎችን እየፈወ ነው፡፡ ገዳማቸው ከደብረ ብርሃን ከተማ በእግር የሁለት ሰዓት መንገድ ርቀት ይገኛል፡፡ ይኸውም ከወንይዬ ተክለ ሃይማኖት ገዳም አጠገብ ነው፡፡ ጻድቁ ጥር25 ቀን ልደታቸው፣ ጥቅምት25 ቃል ኪዳን የተቀበሉበት ዕለት ሲሆን ሐምሌ25 ደግሞ ዕረፍታቸው ነው፡፡ ምንጭ፦ ከገድላት አንደበት። ❤ በየቀኑ ይህን ቴሌግራም ላይ ማግት ከፈለጉ ከታች ያለውን ሊኩን ይጫኑት። @eotcw

Share 'ሥርዓተ_ማኅሌት_ዘበዓለ_አቡነ_ተክለሃይማኖት_ጥር_፳፬.pdf'

✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝ ጉባኤ ቃና ዘዲ/ን የአብስራ ጌታሁን ጊዮርጊስ ተደመ በደብረይድራስ ቀዊሞ ዘኢየአምሮ በለስ አምጣነ ፀውአ ስሞ ሰም፦ ጊዮርጊስ በይድራስ ተራራ ቁሞ ተደነቀ ተገረመ ምን አግኝቶ?? የማያውቀው በለስ (ቅጠል) ስሙን ጠርቶታልና ስለዚህ ተደነቀ ወርቅ፦ ጊዮርጊስን ቅጠል ስሙን ጠርቶታል የተባለው ለሰሙ ሲሆን ለወርቁ ደግሞ አካለ ጊዮርጊስን ፈጭተው በይድራስ ተራራ በበተኑት ጊዜ ቅጠሉ ላይ ሁሉ " ጊዮርጊስ ሰማዕቱ ለክርስቶስ" የሚል ፅሁፍ ተገኝቷልና ነው። ሙያ፦ ጊዮርጊስ......የቅኔ ባለቤት ተደመ.....ማሰሪያ ይስባል እንጂ አይሳብም በ.........አገባብ ፍቺው በቁም ቀሪ ሙያው ማድረጊያ ደብር......... የማድረጊያ ባለቤት ይድራስ ........የደብር ዘርፍ ቀዊሞ...........ቦዝ አንቀፅ ዘ..........አገባብ የ ሙያው ቅፅል ቅፅልነቱ ለበለስ ኢ...........አሉታ ሙያው አፍራሽ የአምር.........እንዳያስር ዘ ይጠብቀዋል በለስ ........የቅፅል ባለቤት አምጣነ .........አገባብ ፍቺው ና ሙያው አስረጅ አስረጅነቱ ለተደመ ፀውአ.......እንዳያስር አምጣነ ይጠብቀዋል ስሞ .........የፀውአ ተሳቢ

☘እንኳን ለ ቅዱስ ጊዮርጊስ ክብረ በአል በሰላም አደረሳችሁ☘
☘እንኳን ለ ቅዱስ ጊዮርጊስ ክብረ በአል በሰላም አደረሳችሁ☘