ch
Feedback
ሰዋስው ☘☘☘☘

ሰዋስው ☘☘☘☘

前往频道在 Telegram

በሰዋስወ ብርሀን ቅዱስ ዻውሎስ ገዳም እና ለተለያዩ ቤተክርስቲያን ለክብረ በአላት ማውጫ ። በተጨማሪም-ዋዜማ ሥርዓተ ማኅሌት - መዝሙራት ስንክሳር - የየእለቱን ምስባክ ቅኔያት ጥያቄዎች እንዲሁም የወቅታዊ ነገር መወያያ በተጨማሪም @eotcww ብለው ይቀላቀሉን ለወዳጅ ዘመድዎ share#Share#Share# ያድርጉ።

显示更多
1 161
订阅者
无数据24 小时
无数据7 天
无数据30 天
帖子存档
❤ "በስመ አብ ወወልደ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤ + + + ❤ "ቀሱታተ ይፅአን በአንበሳ ዕብነኒ። በርእሰ ሰይጣን ተቃራኒ አብሖ ለአሮን ሶርያዊ ኃይለ ፍቅርኪ ሰፋኒ። ጽጌ ደብረ ምጥማቅ ማርያም ተአምርኪ ኖኀኒ። ዘይገኒ ለዕበይኪ ኵሎ ይገኒ። ወአጋንንተ ከመ ገብር ይቀኒ"። ትርጉም፦ ኹሉ የሚቻለው የልጅሽ ኃይል እንስራዎችን በአንበሳ ድንጋይንም ጠላት በኾነ ሰይጣን ራስ ላይ ይጭን ዘንድ ሶርያዊ አሮንን አሠለጠነው፤ የደብረ ምጥማቅ አበባ ተአምርሽ በዝቶ ተትረፈረፈልኝ፤ ለክብርሽ ታላቅነት የሚገዛ ኹሉን ያስገዛለታል፤ አጋንንትንም እንደ አገልጋይ ይገዛል። ሊቆቹ አባ ጽጌ ድንግልና አባ ገብረ ማርያም በማኅሌተ ጽጌ። https://t.me/Eotcw

❤ "በስመ አብ ወወልደ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤ ❤ እንኳን ለትንሣኤ ስድስተኛ ሳምንት እግዚአብሔር አምላክ በሰላም አደረሰን። + + + ❤ የዚህ ሳምንት መዝሙር፦ ሃሌ ሉያ በ፫ "ፋሲካ ዛቲ ዕለት ቅድስት ይእቲ፤ አዝ፣ ዛቲ ዕለት ንትፈሣሕ ባቲ፤ አዝ፣ ንትፈሣሕ ባቲ ወንትሐሠይ ባቲ፤ ዛቲ ዕለት ናኅይ ወዕረፍት፤ አዝ፣ ሰማይ ወምድር ይትፌሥሑ ባቲ፤ አዝ፣ ፋሲካ ፋሲካ ተዝካረ ትንሣኤሁ ለመድኀኒነ። ትርጉም፦ ይህቺ ዕለት የተለየች የደስታ ቀን ናት፤ በዚች ዕለት እንደሰትባት፤ ፈጽመን ሐሤት እናድርግባት፤ ይህቺ ዕለት የዕረፍትና የእፎይታ ዕለት ናትና፤ ሰማይና ምድር ይደሰቱባታል፤ ይህቺውም የመድኀኒታችን የትንሣኤው መታሰቢያ ፋሲካ ናት። ሊቁ ቅዱስ ያሬድ በድጓው ላይ + + + ❤ የዕለቱ ምስባክ፦ "እስመ ሰበረ ኆኃተ ብርት። ወቀጥቀጠ መናሥግተ ዘሐፂን። ወተወክፎሙ እምፍኖተ ጌጋዮሙ"። 106፥16-17 ወይም መዝ 77፥29-30። የሚነበቡት መልዕክታት ፥14-ፍ.ም ወይም ሮሜ 4 6፥1-15፣ ጴጥ 4፥4-12 ወይም ራዕ 20፥1-ፍ.ም 1ኛ እና የሐዋ ሥራ 3፥15-22 ወይም 10፥39-44። የሚቀደሰው ቅዳሴ የቅዱስ ዲዮስቆሮስ ቅዳሴ ነው። መልካም የእመቤታችን በደብረ ምጥማቅ የተገለጠችበት በዓልና የበዓለ ሃምሳ ጊዜ ለሁላችንም ይሁንልን። https://t.me/Eotcw

+ + + ❤ "ሰላም ለአሮን ዕጓላተ ርግብ ዘአሥረረ። ድኅረ ተበስሉ በእሳት ከመ ይኩኑ ድራረ። ኢያንጥሙ ፍኖቱ ወኢያድክሞሙ ወትረ። ማየ ታሕቲት ኀበ ሐነፀ ማኅደረ። በማዕተበ እዱ ስሒቦ አዕረገ ደብረ። ትርጉም፦ እራትን እንዲኾኑ በእሳት ከተበሰሉ በኋላ የርግብ ልጆችን እንዲበርሩ ላደረገ ለአሮን ሰላምታ ይገባል፤ ጎዳናው አስቸግሮ ዘወትር እንዳያዳክማቸው በታች ያለ ውሃን ወዳነጸው በኣቱ በእጁ ማማተብ ስቦ ወደ ተራራ አወጣ። ሊቁ አርከ ሥሉስ (አርኬ) የግንቦት 21። ❤ በየቀኑ ይህን ቴሌግራም ላይ ማግት ከፈለጉ ከታች ያለውን ሊኩን ይጫኑት። https://t.me/Eotcw

❤ "በስመ አብ ወወልደ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤ ❤ ግንቦት ፳፩ (21) ቀን። ❤ እንኳን ለከበሩ በአንድ ገዳም ስልሳ ሰባት ዓመት ለተጋደሉ አባት ገሃነመ እሳት በማሰብ በዝሙትም ላለመውደቅ ብለው ሰውነታቸውን የሚነድ እሳት ውስጥ በመጨመር ዘማዊቷን ሴት ለንስሓ ላበቋት ለአባ መርትያኖስና አንበሶች ውሃ ይዱላቸው ለነበረ፤ ሊፈታተናቸው የመጣውን ሰይጣን በዓታቸው ውስጥ አስገብተው በላዩ ዋሻውን ደፍነው ታላቅ የቋጥኝ ደንጊያም ለዘጉበት ለአባ አሮን ሶርያዊ ለዕረፍታቸው በዓል መታሰቢያ በሰላም አደረሰን። በተጨማሪ በዚህ ከሚታሰቡት፦ ከነቢዩ አሞጽ፣ ከመርዶላ፣ ከመታሰቢያ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን። + + + ❤ አባ መርትያኖስ፦ ይህም አባት በልጅነቱ ከአንድ ቅዱስ የሆነ አረጋዊ አባት ዘንድ መንኵሶ ታላቅ ገድልን ተጋደለ። ከዚህም በኋላ ሐመረ ኖኅ ወደምትባል በቂሣርያ ወደአለች ገዳም ሔደ በዚያም እጅግ በጣም የበዛ ገድልን ተጋደለ። በጸሎት በጾም በስግደትም በሌሊትና በመዓልት በመትጋት እየተጋደለ ስልሳ ሰባት ዓመት በኖረ ጊዜ የገድሉና ትሩፋቱ ወሬ በቦታው ሁሉ ተሰማ። ❤ እንሆ አንዲት በክፉ ሥራዋና በዝሙቷ የታወቀች ኃጢአተኛ አመንዝራ ሴት ሰማች። ጽድቁንና ቅድስናውን በመናገር የሚያመሰግኑትን እንዲህ አለቻቸው "እናንተ ታመሰግኑታላችሁ እርሱ የሚኖረው በዱር ነው የሴት ገጽ ከቶ አያይም እኔን ቢያይ ድንግልናውን አጥፍቼ ቅድስናውን በአረከስኩት ትኅርምቱንም ባፈረስኩት ነበር"። እነርሱ ግን ጥንክርናውን ስለ ሚያውቁ ተከራከሩዋት። ስለዚህም በመካከላቸው ክርክር ሆነ "ሒጄ ከእኔ ጋራ በኃጢአት ብጥለው ምን ትሰጡኛላችሁ" አለቻቸውና ገንዘብ ሊሰጡአት ተስማሙ። ❤ ያን ጊዜም ተነሥታ ጌጦቿን ልብሶቿንና ሽቱዎቿን ያዘች መልኳም እጅግ ውብ ነበረች ፊቷንም ተከናንባ ጨርቅ ለብሳ ወደ በዓቱ ሔደች። ልብሷንና ጌጦቿንም ለብቻቸው በከረጢት አሥራ ያዘች። ከበዓቱም ቅርብ በሆነ ቦታ ተሠውራ እስከ ሚመሽ ቆይታ የበዓቱን ደጃፍ አንኳኳች። "አራዊት እንዲበሉኝ በውጭ አትተወኝ እኔ መጻተኛ ነኝና መንገድንም ተሳስቼ ወደዚህ ደረስኩ" አለችው። እርሱም በልቡ አሰበ "በውጭ ብተዋት አራዊት ይበሏታል ባስገባትም ስለርስዋ ጦር በኔ ላይ ይነሣብኛል" አለ። ❤ ከዚህም በኋላ ከፈተላት በዚያች በዓት ውስጥ ትቷት ወደ ሌላ ቦታ ፈቀቅ አለ። እርሷ ግን ልብሶቿን ለብሳ ጌጦቿንም ተሸልማ ሽቱዎቿን ተቀብታ ወደርሱ ገባች ከርሷ ጋራም እንዲተኛ ፈልጋ "ከዚህ ማንም የሚያየን የለም" አለችው። ቅዱሱም የሰይጣን ማጥመጃው እንደሆነች አውቆ "ጥቂት ታገሺኝ መንገድን እስታይ እግዚአብሔርን የማንፈራው ከሆነ እንደእኛ ያሉ ሰዎችን ላንፈራቸው ይገባናል" አላት። ይህንንም ብሎ ከእርሷ ዘንድ ወጣ ታላቅ እሳትም አንድዶ እግሩን ከውስጡ ጨምረ ነፍሱንም "የሲዖልን እሳት የምትችዪ ከሆንሽ ኃጢአትን ሥሪያ" አላት። በዘገየ ጊዜ ወደርሱ ሔደች በእሳት ውስጥም እግሩን ሲያቃጥል አይታው እጅግ ደነገጠች። ከእሳትም ውስጥ ጐትታ አወጣችው ልቧም ወደ ንስሓ ተመለሰ። ልብሷንና ጌጦቿን ከላይዋ አውጥታ ጣለች ከእግሩ በታች ሰግደች ስለነፍሷ ድኅነትም እንዲረዳት ለመነችው። እርሱም ይህ ዓለም ፍላጎቱ ሁሉ ኀላፊ እንደ ሆነ ያስተምራትና ይመክራት ልብ ያስደርጋትም ጀመር እርሷም በጨከነ ልብ ንስሓ ገባች። ❤ ከዚህም በኋላ "በአንድነት መኖር አግባብ አይደለም" ብሎ ወደ ደናግል ገዳም ወሰዳት ትጠብቃትም ዘንድ እመ ምኔቷን አደራ አላት። በቀረው ዕድሜዋም በገድል ተጠምዳ እግዚአብሔርን አገለገለችው ወደ በጎ ሽምግልናም ደረሰች የመፈወስ ሀብትም አድሮባት ብዙዎች በሽተኞችን አዳነች። ❤ የከበረ አባ መርትያኖስ ግን ሌላ ሴት እንዳያመጣበት ፈርቶ በባሕር መካከል ወዳለች ደሴት ገብቶ በዚያ የሚኖር ሆነ። አንድ ባለ ታንኳም የእጅ ሥራውን እየሸጠ ምግብ ያመጣለት ነበር። ከብዙ ዘመናትም በኋላ መርከብ ተሰብራ ሰጠመች አንዲት ሴትም በመርከብ ስባሪ ተጣብቃ አባ መርትያኖስ ወደ አለበት ደሴት የባሕሩ ማዕበል አደረሳት በአያትም ጊዜ ደነገጠ አደነቀም። ከእርሷ ጋራ በአንድነት ስለ መኖሩም አዘነ የእግዚአብሔርንም ቃል አስተምሮ የምንኵስና ልብስ አለበሳት ምግቧንም አዘጋጀላትና "ለእኛ በአንድነት መኖር አግባብ አይደለም" አላት። ያንንም ደሴት ትቶላት ወደ ባሕሩ ተወርውሮ ገባ አንበሪም ተሸክሞ ወደ የብስ አወጣው። መቶ ስምንት አገሮችንም እስቲአዳርስ በአገሮች በአሉ ገዳማት ሁሉ ከዚያች ቀን ጀምሮ የሚዞር ሆነ በአንድ ቦታ እንዳይቀመጥ አስቦ ነው። ❤ ከዚህ ኋላም የዕረፍቱ ጊዜ እንደ ቀረበ አውቆ በበዓት ውስጥ ራሱን እሥረኛ አደረገ። ኤጲስቆሱንም ጠርቶ ከመጀመሪያ እስከ መጨረሻ ገድሉን ሁሉ ነገረው ኤጲስቆሱም ከጸጋው ገናናነት የተነሣ አደነቀ። ከዚህም አስቀድሞ የእግዚአብሔር መልአክ ለኤጲስቆጶሱ ስለ አባ መርትያኖስ ሥጋ እንዲአስብ ነግሮት ነበር። ከዚህም በኋላ ነፍሱን በእግዚአብሔር እጅ ግንቦት21 ቀን ሰጠ ኤጲስቆጶሱም በታላቅ ክብር ገንዞ ቀበረው። ❤ ያቺ ሴት ግን እስከ ዕረፍቷ ቀን ባለ መርከብ የሚጐበኛት ሆነ በዐረፈችም ጊዜ ሥጋዋ እንደ በረዶ ነጥቶ አገኛት ሥጋዋንም ወደ አገሩ ተሸክሞ ወስዶ ቀበራት። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳን በአባ መርትያኖስ እና ለቅድስና ባበቃቸው ቅዱሳን ሴቶች ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን። + + + ❤ "ሰላም ለአባ አሮን ሶርያዊ ዘአሰረ ሰይጣን ወአጾሮ እብነ፤ በንጹሕ ዘተክህነ"። ትርጉም፦ በንጹሕ ያገለገለ ሰይጣንን አስሮ ደንጊያን ያሸከመ ለኾነ ለሶርያዊው ለአባ አሮን ሰላምታ ይገባል። ሊቁ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ በተአምኆ ቅዱሳን ላይ። + + + ❤ አባ አሮን ሶርያዊ፦ ለዚህ ቅዱስም የመፈወስና ድንቆች ተአምራትን ማድረግ ሀብት ተሰጥቶታል። ይኸውም እግዶች መነኰሳት ወደ ርሱ በመጡ ጊዜ የርግብ ግልገሎችን አብስሎ አቀረበላቸው። ሥጋ አንበላም ባሉት ጊዜ በላያቸው አማትቦ ርግቦቹን አድኖ እንዲበሩ አደረጋቸው። ደግሞ በተራራ ላይ ገዳም ሠራ ውኃው ከተራራው በታች የራቀ ነበረ በጸለየና በእጁ ባማተበ ጊዜ ስቦ ከተራራው ላይ አወጣው። ❤ በአንዲት ቀንም ሰይጣን በክፋቱ ሊአስጠፋው ወደርሱ መጣ እርሱ ግን በላዩ በአደረ መንፈስ ቅዱስ ተንኰሉን አውቆ "ና ወደ በዓት ግባ" አለው። በገባ ጊዜም በላዩ ዋሻውን ደፈነው ታላቅ የቋጥኝ ደንጊያም ጫነበት ሰይጣንም አፈረ። ደግሞም ሁለተኛ የአካ አገረ ገዥ በሞተ ጊዜ በጸሎቱ አስነሣው። ደግሞ ውኃ የሚቀዳባቸውን አራት እንስራዎችን በአንበሳ እየጫነ በመውሰድ ዐሥር ዓመት ያህል ኖረ። ከዚህም በኋላም ግንቦት21 ቀን ወደ ዘላለም ሕይወት ሔደ። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በከበረች በአባ አሮን ሶርያዊ ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን። ምንጭ፦ የግንቦት21 ስንክሳር።

❤ "በስመ አብ ወወልደ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤ ❤ ግንቦት ፳፩ (21) ቀን። ❤ እንኳን አምላክ ለወለደች ለእናታች ለእመቤታችን ለቅድስት ድንግል ማርያም በደብረ ምጥማቅ በስሟ በተሰራች ቤተ ክርስትያን ጉልላት ላይ በብርሃን መርከብ ተቀምጣ ፊቷ በግልጥ ለአምስት ተካታታይ ቀን ለታየችበት ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሰን።? + + + ❤ የዕለቱ እግ.ነግ ዓራራይ ዜማ፦ "ትበርህ እምፀሐይ ወትትሌአል እምአድባር እንተ በአማን ድንግል ሰአሊ ለነ ወልድኪ ይምሐረነ ወመዋርስቲሁ ይረስየነ"። ትርጉም፦ ከፀሐይ ይልቅ ትበራለች ከተራራም ከፍ ከፍ ትላለች ስለዚህ በእውነት ድንግል ለምኝልን ልጅሽ ይቅር እንዲለን ወረሾቹም እንዲያደርገን። ሊቁ ቅዱስ ያሬድ በድጓው። + + + ❤ በዚች ዕለት አምላክን የወለደች እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በደብረ ምጥማቅ በስሟ በተሠራች ቤተ ክርስቲያን ጉልላት ላይ በብርሃን መርከብ ተቀምጣ ፊቷ በግልጥ ስመታየቱ የክርስቲያ ወገኖች ሁሉም በታላቅ በዓልን ያደርጋሉ። ❤ እርሷም በልጅዋ የመለኮት ብርሃን የተጐናጸፈች ናት በዙሪያዋም የመላእክት ሠራዊት የመላእክት አለቆችም በየማዕርጋቸው ክንፋቸውን ዘርግተው ይቆሙ ነበር ይጋርዷታልም። ሱራፌልም ማዕጠንታቸውን ይዘው ለንግሥናዋ ገናናነት ይሰግዳሉ ስግደታቸውም እንዲህ እያሉ ያመሰግኗታል "አብ በሰማይ ሁኖ ተመለከተ እንደ አንቺ ያለ አላገኘም አንድ ልጁንም ልኮ ከአንቺ ሰው ሆነ"። ❤ ሁለተኛም ሰማዕታትም በየማረጋቸው ረቂቃን በሆኑ ፈረሶቻቸው ተቀምጠው እየመጡ መጀመሪያ ቅዱስ ጊዮርጊስ ከአምባላይ ፈረሱ ወርዶ ይሰግድላታል እንዲሁም ባልጀሮቹ ሰማዕታት መጥተው ይሰግዱላታል። ከእርሱ በኋላ የሚመጣው በዱሪ ፈረስ የሚቀመጠው ይህ ቅዱስ መርቆሬዎስ ነው። ከዚህም በኋላ ሰማዕታት ሁሉ በመከታተል መጥተው ይሰግዱላታል ምስጋና ያቀርብላታል። ❤ ሁለተኛም ደግሞ የጻድቃን አንድነታቸው መጥተው በፊቷ ሰግደው ይመላለሳሉ። ኄሮድስ የገደላቸው ሕፃናትም መጥተው ይሰግዱላታል በፊቷም እየዘለሉ አንዱ በአንዱ ላይ እየዘለለ በመታቃቀፍም ይጫወታሉ የተሰበሰብትም በአዩ ጊዜ ደስታ ይመላቸዋል በሰማይም ያሉ ይመስላቸው ነበር። ❤ እናትና አባቱም የሞቱበት ቢኖር ወይም ከዘመዶቹ ወይም ባልጀራው "ቅድስት ድንግል እመቤቴ ሆይ ዕገሌን አሳዪኝ ብሎ በሚለምናት ጊዜ ቀድሞ በነበረበት መልኩ ያን ጊዜ ታመጣዋለች። ደግሞ መሀረባቸውን ወደላይ ይወረውሩላታል የወደደችውንም በእጅዋ ተቀብላ መልሳ ትጥልላቸዋለች ለበረከትም በየጥቂቱ ይካፈሉታል። ❤ እንዲህም አምስት ቀን ሁሉ ክርስቲያንም እስላሞችም አረማውያንም ያይዋታል። ወደ ቤታቸውም ለመሔድ ሲሹ በፊቷ ሰግደው ይሰናበቷታል እርሷም ትባርካቸውና ይመለሳሉ። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም አምላክ በወለደች በእመቤታችን በቅድስት ድንግል ማርያም አማላጅነት ይማረን በረከቷም ከእኛ ጋራ ይኑር ለዘላለሙ አሜን። ምንጭ፦ የግንቦት 21 ስንክሳር። + + + ❤ የበዓሉ የማኅሌት ምስባክ፦ "ወለገጽኪ ይትመሐለሉ ኵሎሙ አሕዛብ ብዑላነ ምድር። ኵሉ ክብራ ለወለተ ንጉሠ ሐሴቦን። በዘአዝፋረ ወርቅ ዑፅፍት ወኊብርት"። መዝ 44፥12-13። የሚነበበው ወንጌል ሉቃ 1፥39-57። + + + ❤ የበዓሉ የቅዳሴ ምስባክ፦ "ሰወረከኒ በዕለተ ቀትል መልዕልተ ርእስየ። ኢትመጥወኒ እግዚኦ እምፍትወትየ ለኃጥአን። ተማከሩ ላዕሌየ ኢትኅድገኒ ከመ ኢይዘኀሩ"። መዝ 139፥7-8 ወይም መዝ 140፥4-5። የሚነበቡት መልዕክታት 1ኛ ቆሮ 7፥9-ፍ.ም፣ ራእ.ዮሐ 12፥1-5 እና የሐዋ ሥራ 7፥44-51። የሚነበበው ወንጌል ማቴ 18፥6-12። የሚቀደሰው ቅዳሴ የእመቤታች የማርያም ቅዳሴ ነው፡፡ መልካም የደብረ ምጥማቅ በዓል ለሁላችንም ይሁንልን። ❤ በየቀኑ ይህን ቴሌግራም ላይ ማግት ከፈለጉ ከታች ያለውን ሊኩን ይጫኑት። https://t.me/Eotcw

❤ "በስመ አብ ወወልደ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤ + + + ❤ "ሰላም ለካሌብ ወለሣህል ኄራን መዋዕያን ነገሥት፤ እለ ሃይማኖቶሙ ምሉዕ ከመ ደመና ክረምት፤ ለመንገለ እግዚአብሔር እለ አርአዩ ቅንአተ፤ እለ ዓቀቡ በንጽሕ መንግሥተ፤ ዘተወፈዩ ጽድቀ ወቅድሳተ ወሃይማኖተ በመንፈስ ቅዱስ እለ አፍረዩ፤ ለእግዚአብሔር ርእሶሙ እለ አቅነዩ"። ትርጉም፦ ለእግዚአብሔር ራሳቸውን ያስገዙ፤ በመንፈስ ቅዱስ ፍሬን ያፈሩ፤ እውነትን፣ ክብርንና ሃይማኖትን የተቀበሉ፤ መንግሥትን በንጽሕና የጠበቁ፤ የእግዚአብሔር ወደሚኾን አምልኮት ቅንአትን ያሳዩ፤ ሃይማኖታቸው እንደ ክረምት ደመና ምሉእ የኾኑ ቸሮችና ድል ነሾች ለኾኑ ነገሥታት ለሣህልና ለቅዱስ ካሌብ ሰላምታ ይገባል። ሊቁ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ በተአምኆ ቅዱሳን ላይ https://t.me/Eotcw

❤ "በስመ አብ ወወልደ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤ ❤ ግንቦት ፳ (20) ቀን። ❤ እንኳን ለሀገረ ቶና ለከበረ ልታስተው የመጣችውን ሴት በማስተማር ለቅድስና ላበቃ ለአባ አሞንዮስ ለዕረፍት በዓል መታሰቢያ በሰላም አደረሰን። በተጨማሪ በዚህ ቀን ከሚታሰብት፦ አባ አሞንዮስ ለቅድስና ካበቃት ከቅድስት ሳድዥ ከመታሰቢያዋ፣ ከቅዱስ አሞኒ ረድእ አባ ዳርማ ከዕረፍት፣ ከአባ ኄሮዳና ከአባ ዘካርያስ ጋር በሰማዕትነት ከዐረፉበት ከመታሰቢያቸው እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን። + + + ❤ አባ አሞንዮስ፦ ይህም ቅዱስ ጐልማሳ ሁኖ ሳለ አባ እንጦንዮስ ወደ ምንኵስና ሲጠራው ራእይን አየ። በነቃም ጊዜ ተነሥቶ ወዲያውኑ ወደ አባ ኤስድሮስ ሔደ ከእርሱም አስኬማን ለብሶ እያገለገለውም በእርሱ ዘንድ ኖረ። ❤ ከዚህ በኋላ ወደ ደብረ ቶና ተመልሶ ለራሱ በዓትን ሠራ በታላቅ ገድልም ተጠምዶ በቀንና በሌሊትም ተጋደለ። ሰይጣንም በእርሱ ላይ ቀንቶ በሴት መነኵሲት አምሳል ወደርሱ መጣ የበዓቱን ደጃፍ በአንኳኳ ጊዜ ከፈተለትና ገባ "ቅዱሱም ተነሥተን እንጸልይ" አለው ያን ጊዜ ተንኰሉን ገለጠ መልኩም እንደ እሳት ላቦት ሆነ ቅዱሱንም "እኔ ታላቅ ጦርነት አመጣብሃለሁ" አለው። ❤ ከዚህም በኋላ መልኳ ውብ ወደ ሆነ ወደ አንዲት ወጣት ሴት ሰይጣን ሒዶ አነሣሣት። ቅዱስ አሞንዮስን እርሷ ጋራ በኃጢአት ልትጥለው ቀጭን ልብሶችን ለብሳ ወደ ርሱ በምሽት ጊዜ ደረሰች። እንዲህም እያለች ደጃፉን አንኳኳች "እኔ መጻተኛ ሴት ነኝ መንገድንም ስቼ በምሽት ጊዜ ከዚህ ደረስኩ አራዊትም እንዳይበሉኝ በውጭ አትተወኝ እግዚአብሔርም ስለ እኔ ደም እንዳይመራመርህ" አለችው። በከፈተላትም ጊዜ የሰይጣን ማጥመጃው እንደ ሆነች የላካትም እርሱ እንደሆነ አወቀ በአምላካውያት መጻሕፍት ቃልም ገሠጻት ለኃጥአን ስለ ተዘጋጀ የሲዖል እሳትም አስገነዘባት ሁለተኛም ለጻድቃን ስለ ተዘጋጀ ፍጹም ተድላ ደስታ ነገራት። ያን ጊዜም የሚላትን ታስተውለው ዘንድ እግዚአብሔር ልቧን ከፈተላት። መልካሙንም ልብስ ከላይዋ አውጥታ ጣለች ከእግሮቹ በታችም ሰግደች ነፍሷንም ያድን ዘንድ በማልቀስ ለመነችው። የጠጉር ልብስም አለበሳት ራስዋንም ተላጭታ በገድል ሁሉ በብዙ ትሩፋትም ተጠመደች በቀንም በሌሊትም ዐሥራ ሁለት ጊዜ የምትጸልይ ሁናለችና በየሁለትና በየሦስት ቀንም ትጾማለች። ❤ ሰይጣንም በአፈረ ጊዜ በመነኵሴ ተመስሎ በየአንዳንዱ ገዳም ሁሉ በመግባት እያለቀሰና እያዘነ እንዲህ አላቸው "በአባ አሞንዮስ ቤት ሴት አለችና እርሱ ታላቅ ገድል በኋላ የአንዲትን ሴት ፍቅር ወዶአልና እርሷም በእርሱ ዘንድ በበዓቱ ውስጥ ትኖራለች እነህ መነኰሳትን አሳፈራቸው እስኬማውንም አጐሳቈለ"። ❤ የመላእክት አምሳል የሆነ ጻድቅ አባ ዕብሎ ያን ጊዜ ተነሣ አባ ዮሴፍንና አባ ቦሂንም ከእሱ ጋራ ወሰዳቸው። ወደ ቅዱስ አሞንዮስ ገዳም ደብረ ቶና ደረሱ ደጃፋንም በአንኳኩ ጊዜ ያቺ ሴት ወደ እርሳቸው ወጣች እርስ በርሳቸውም "ያ መነኵሴ የነገረን እውነት ነው ተባባሉ። የከበረ አሞንዮስም ሳድዥ ብሎ ስም አውጥቶላታል ይህም የዋሂት ማለት ነው። ገብተውም ጸሎት አድርገው የእግዚአብሔርንም ገናናነት እየተነጋገሩ እስከ ምሽት ተቀመጡ። አባ አሞንዮስም "አምበሻ እየጋገረችልን ነውና ተነሡ ሳድዥን እንያት" አላቸው። በገቡም ጊዜ በሚነድ የእሳት ምድጃ ውስጥ ቁማ እጆቿም ወደ ሰማይ ተዘርግተው ስትጸልይ አገኙዋት። አይተውም ስለዚህ ድንቅ ሥራ እጅግ አደነቁ የተመሰገነ እግዚአብሔርም አመሰገኑ። ❤ ከዚህ በኋላም አቅርባላቸው በሉ። በዚያችም ሌሊት መልአክ ስለ አባ አሞንዮስና ስለ ሳድዥ ገድላቸውን ለአባ ዕብሎ ነገረው "ወደዚህም ዛሬ ያደረሳችሁ እግዚአብሔር ነው የሳድዥን ዕረፍት እንድታዩ" አላቸው። ሦስት ሰዓትም በሆነ ጊዜ የሚያስጨንቅ የሆድ ዝማ ታመመች በእግዚአብሔር ፊት አንዲት ስግደትን ሰገደችና በዚያም ነፍሷን ሰጠች መልካም አገናነዝም ገንዘው ቀበሩዋት። ❤ አባ አሞንዮስም ትሩፋቷን ሊነግራቸው ጀመረ እርሷ በእርሱ ዘንድ ዐሥራ ስምንት ዓመት ስትኖር ከቶ ፊቷን እንዳላያት ምግባቸውም አምባሻና ጨው እንደሆነ። ከጥቂ ቀን በኋላም አባ አሞንዮስ ግንቦት 20 ቀን ዐረፈ። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳን በአባ አሞንዮስና በቅድስት ሳድዥ ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋራ ለዘላለም ትኑር አሜን። ምንጭ፦ የግንቦት 20 ስንክሳር። + + + ❤ "ሰላም ሰላም ለረዳኢተ አሞንዮስ ሳድዥ። ዝ ብሂል የዋሂተ ግዕዝ። በሑረታቲሃ አዳም ወበምግባራ ሐዋዝ። ኢውዕየት ቀዊማ ከመ ዘመጥልል ውኂዝ። ማዕከለ ውዑይ ወርሱን ማሕበዝ"። ሊቁ አርከ ሥሉስ (አርኬ) የግንቦት 20። + + + ❤ የዕለቱ የማኅሌት ምስባክ፦ "ነፍስነሰ ትሴፈዎ ለእግዚአብሔር። እስመ ረዳኢነ ወምስካይነ ውእቱ። እስመ ቦቱ ይትፌሣሕ ልብነ"። መዝ 32፥20-21። የሚነበበው ወንጌል ማር 15፥33-42። + + + ❤ የዕለቱ የቅዳሴ ምስባክ፦ "ዝርዎሙ ለአሕዛብ እለ ይፈቅዱ ቀትለ። ይምጽኡ ተናብልት እምግብፅ። ኢትዮጵያ ታበጽሕ እደዊሃ ኀበ እግዚአብሔር"። መዝ 67፥30-31 ወይም መዝ 74፥2-3፡፡ የሚነበቡት መልዕክታት ሮሜ 13፥1-11፣ 1ኛ ጼጥ 2፥11-20 እና የሐዋ ሥራ 13፥44-ፍ.ም። የሚነበበው ወንጌል ማቴ16፥24-28። የሚቀደሰው ቅዳሴ የቅዱስ ባስልዮስ ወይም የቅዱስ ዲዮስቆሮስ ቅዳሴ ነው። መልካም የጻድቁ ንጉሥ ዐፄ ቅዱስ ካሌብ የዕረፍት በዓልና የበዓለ ሃምሳ ጊዜ። ለሁላችንም ይሁንልን። ❤ በየቀኑ ይህን ቴሌግራም ላይ ማግት ከፈለጉ ከታች ያለውን ሊኩን ይጫኑት። https://t.me/Eotcw

በዛሬው እለት የጎንደር አቡን ቤት ደብረ ምህረት ቅዱስ ገብርኤል የቅኔ ምስክር ጉባኤ ቤት ፳፭ የቅኔ ደቀመዛሙርትን በቅኔ መምህርነት መርቋል እግዚአብሔር አምላክ የአገልግሎት ዘመናቸውን ይባርክላቸው
በዛሬው እለት የጎንደር አቡን ቤት ደብረ ምህረት ቅዱስ ገብርኤል የቅኔ ምስክር ጉባኤ ቤት ፳፭ የቅኔ ደቀመዛሙርትን በቅኔ መምህርነት መርቋል እግዚአብሔር አምላክ የአገልግሎት ዘመናቸውን ይባርክላቸው ዘንድ አርድዕተ ጉባኤ ይመኛል ፡፡ አምላከ ሊቃውንት ተጠያቂ ሊቅ አያሳጣን

🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀 ሥርዓተ ማኅሌት ዘግንቦት ማርያም (ደብረ ምጥማቅ) 🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼☘ የማንኛውም ወርኃ በዓልና ክብረ በዓል ሥርዓተ ማኅሌት መጀመሪያ "ሥርዓተ ነግሥ" ስምዓኒ እግዚኦ ጸሎትየ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ ወይብጻሕ ቅድሜከ ገዓርየ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ ወኢትሚጥ ገፀከ እምኔየ፡ በዕለተ ምንዳቤየ አጽምእ ዕዝነከ ኃቤየ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ አመ ዕለተ እጼውአከ ፍጡነ ስምዓኒ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ ለዓለም ወለዓለመ ዓለም፡ ሃሌ ሉያ ዘውእቱ ብሂል፡ ንወድሶ ለዘሃሎ እግዚአብሔር ልዑል፡ ስቡሕ ወውዱስ ዘሣረረ ኲሎ ዓለመ፡ በአሐቲ ቃል። @EOTCW @EOTCW መልክዐ ሥላሴ ሰላም ለኲልያቲክሙ እለ ዕሩያን በአካል: ዓለመክሙ ሥላሴ አመ ሐወጸ በሣሕል: እምኔክሙ አሐዱ እግዚአብሔር ቃል: ተፈጸመ ተስፋ አበው በማርያም ድንግል: ወበቀራንዮ ተተክለ መድኃኒት መስቀል። @EOTCW @EOTCW ዚቅ ወሀለወት አሐቲ ድንግል ብርህት ከመ ፀሐይ: እንተ ታስተርኢ እምአርዕስተ አድባር: ወትትመረጎዝ በትእምርተ መስቀል። @EOTCW @EOTCW ነግሥ ሰላም ለልሣንከ መዝሙረ ቅዳሴ ዘነበልባል: ወለድምፀ ቃልከ ሐዋዝ ቀርነ መንግሥቱ ለቃል: ሞገሰ ክብሩ ሚካኤል ለተላፊኖስ ባዕል: አልቦ ዘይትማሰለከ በልማደ ምሕረት ወሣሕል: እንበለ ባሕቲታ እኅትከ ማርያም_ድንግል። @EOTCW ዚቅ መላእክት በልሳነ እሳት ይሴብሑኪ: መላእክት በአክናፈ ብርሃን ይኬልሉኪ: ማርያም እምነ ወእሙ ለእግዚእነ: መላእክት በቀለመ ወርቅ ይጽሕፉ ውዳሴኪ: እስከ ዳግም ምጽአቱ ለበኲርኪ። @EOTCW @EOTCW ዘጣዕሙ ሰላም ለዝክረ ስምኪ ዘመንክር ጣዕሙ: ለወልድኪ አምሳለ ደሙ: መሠረተ ህይወት ማርያም ወጥንተ መድኃኒት ዘእምቀዲሙ: ኪያኪ ሠናይተ ዘፈጠረ ለቤዛ ዓለሙ: እግዚአብሔር ይትባረክ ወይትአኮት ስሙ። @EOTCW @EOTCW ዚቅ እግዚአብሔር ውእቱ ብርሃንኪ ለዓለም: ወመሠረትኪ ለትውልደ ትውልድ: ኢየኀልቅ ብዝኃ ሰላምኪ: ወነገሥት ይትቀነዩ ለኪ: ያመጽኡ አምኃኪ እምርኁቅ ብሔር። @EOTCW @EOTCW መልክአ ማርያም ሰላም ሰላም ለዝክረ ስምኪ ሐዋዝ: እምነ ከልበኔ ወቊስጥ ወእምነ ሰንበልት ምዑዝ: ማርያም ድንግል ለባሲተ ዓቢይ ትዕዛዝ: ይስቅየኒ ለለጽባሑ ወይነ ፍቅርኪ አዚዝ: ከመ ይሰቅዮ ውኂዝ ለሠናይ አርዝ። @EOTCW @EOTCW ዚቅ በአልባሰ ወርቅ ዑጽፍት ወኁብርት: እኅትየ መርዓት ርግብየ ሠናይት: ርቱዕ አፍቅሮትኪ እምወይን: መዓዛ ዕፍረትኪ እምኲሉ አፈው: እትፌሣሕ ወእትኃሠይ ብኪ: ናፍቅር አጥባትኪ እምወይን: ኲለንታኪ ሠናይት እንተ እምኀቤየ: አልብኪ ነውር ወኢምንትኒ ላዕሌኪ: ፃዒ እምሊባኖስ እኅትየ መርዓት። @EOTCW @EOTCW ወረብ "በአልባሰ ወርቅ"/፪/ ዑጽፍት ወኁብርት/፪/ እኅትየ መርዓት ርግብየ ሠናይት እኅትየ/፪/ @EOTCW @EOTCW መልክዐ ማርያም ሰላም ለገጽኪ ዘጥቀ ይልሂ: እምሥነ ከዋክብት ወወርኅ ወእምሥነ ፀሐይ መብርሒ: ማርያም ድንግል ፍንዋትየ ሠርሂ: በመዓልት ወበሌሊት ኢይርከበኒ ጸናሂ: መሥገርተ አበሳ ዘይጠፍር ወግብ ይድሂ። @EOTCW @EOTCW ዚቅ ከበበ ገፃ ከመ ወርኅ: ወአዕይንቲሃ ከመ ኮከበ ጽባሕ: ወቆማ ከመ በቀልት ለማርያም ድንግል: ወላህያ ከመ ጽጌረዳ: ከመ ፍህም ቀይሕ ከናፍሪሃ: እስመ ወለደት ለነ መና ኅቡዓ: ዘውእቱ ህብስተ ህይወት: መፍትሔ ሕማማት። @EOTCW @EOTCW ወረብ ከበበ ገፃ ከመ ወርኅ ወአዕይንቲሃ ከመ ኮከበ ጽባሕ/፪/ ወቆማ ከመ በቀልት ለማርያም ድንግል/፪/ @EOTCW @EOTCW መልክዐ ማርያም ሰላም ለጒርኤኪ ሠናይ እምወይን: በከመ ይቤ ሰሎሞን: ማርያም_ድንግል ለባሲተ ዓቢይ ብርሃን: ክድንኒ ገርዜነ ጸጋ ኢያዕጽበኒ ዕርቃን: ዘኢአነምዎ ጠቢባን በኪን። @EOTCW ዚቅ በከመ ይቤ ሰሎሞን በእንተ ማርያም: ንዑ ንትፈጋዕ ወኢይኅልፈነ ጽጌ ደመና መስቀል ዘዮም አብርሃ በስነ ማርያም: ጴጥሮስኒ ሰመያ እመ ብርሃን: ጳውሎስኒ ይቤላ ደብተራ ግዕዛን: አጽገዩ ሕዝበ ወመሐይምናን: በቤተ መርዓ ተመልዑ ክርስቲያን። @EOTCW @eotcW ወረብ በከመ ይቤ "ሰሎሞን"/፪/ በእንተ ማርያም/፪/ ንዑ ንትፈጋዕ ወኢይኅልፈነ "ጽጌ"/፪/ ደመና አብርሃ በስነ ማርያም/፪/ @EOTCW @EOTCW መልክዐ ማርያም ሰላም ለመልክዕኪ ዘተሠርገወ አሚረ: ዘያበርህ ወትረ: ፍቅርትየ አንቲ እንተ ታበድሪ ፍቅረ: አርእይኒ ገፀ ዚአኪ ማርያም ምዕረ: ዘኢይሰምዖ ካልዕ እንግርኪ ነገረ። @EOTCW @EOTCW ዚቅ ትበርህ እምኮከበ ጽባሕ: ወታስተርኢ እምአርእስተ አድባር: አዳም ወሠናይት ጽዕዱት: ወብርህት ከመ ፀሐይ። @EOTCW @EOTCW ወረብ ትበርህ እምኮከበ ጽባሕ ወታስተርኢ እምአርዕስተ አድባር/፪/ አዳም ወሠናይት ጽዕዱት ወብርህት ከመ ፀሐይ ብርህት/፪/ @EOTCW @EOTCW መልክዐ ማርያም በዝንቱ ቃለ ማኅሌት ወበዝንቱ ይባቤ: ለዘይስዕለኪ ብእሲ ጊዜ ረከቦ ምንዳቤ: ብጽሒ ፍጡነ ትሰጠዊዮ ዘይቤ: ማርያም ዕንቊየ ክርስቲሎቤ ወምዕዝተ ምግባር እምከርቤ: ዘጸገየ ማሕጸንኪ አፈወ ነባቤ። @EOTCW @EOTCW ዚቅ ኢይትአጸው አናቅጽኪ: ክቡራት ዕንቊ መሠረትኪ ሠናይት ሰላማዊት እንተ ናፈቅራ በጽድቅ: መዓዛ አፉሃ ከመ ኮል። @EOTCW @EOTCW ወረብ ኢይትአጸው አናቅጽኪ ክቡራት ዕንቊ መሠረትኪ/፪/ ሠናይት ሰላማዊት "እንተ ናፈቅራ"/፪/ በጽድቅ/፪/ @EOTCW @EOTCW ማኅሌተ ጽጌ ኦ ሰላመ ሰጣዊት እንተ ትሔውጺ እምርኁቅ: ወትትረአዪ ለኲሉ በደብረ ምጥማቅ: ተፈሥሒ ድንግል ዘገዳመ ጽጌ ማዕነቅ: እስመ ተሰምዓ በምድርነ ቃለ ተአምርኪ ጽድቅ: ለአድኅኖ ኃጥዕ ዘይበቊዕ እምብሩር ወወርቅ። @EOTCW @EOTCW ዚቅ እንተ ታስተርኢ እምአርእስተ አድባር ርኁቅ: ጻድቃን ኪያሃ አብደሩ እምወርቅ: ሀገረ ክርስቶስ ሐዳስ ንድቅ: ወበውስቴታ የሐጽር ጽድቅ። @EOTCW @EOTCW ምልጣን ዓይ ይእቲ ዛቲ እንተ ታስተርኢ እምርኁቅ ከመ ማኅቶት: ብርህት ከመ ፀሐይ: ሙሴኒ ርእያ ሀገር ቅድስት: ዕዝራኒ ተናገራ: ዳዊት ዘመራ። @EOTCW @EOTCW አመላለስ ዕዝራኒ ተናገራ/፪/ ተናገራ ዳዊት ዘመራ ተናገራ ዘመራ ዳዊት/፪/ @EOTCW @EOTCW እስመ ለዓለም ዘሰንበት የማነ ብርሃን ኀደረ ኃበ ማርያም ድንግል፤ ጥዕምት በቃላ ወሠናይት ምግባራ ፤ እሞሙ ለሰማዕት፤ ወእኅቶሙ ለመላእክት ፤ ማ፦ እንተ ተሰምየት ሰንበተ ክርስቲያን ተስፋ ቅቡፃን፤ መድኃኒት ኮነት ለኩሎ ዓለም 🇪🇹👇👇👇👇👇👇🇪🇹 👉@EOTCW👈 👉@EOTCW👈 👉@EOTCW👈 🇪🇹👆👆👆👆👆👆🇪🇹 @ https://t.me/Eotcw # Join & share #