ch
Feedback
ሰዋስው ☘☘☘☘

ሰዋስው ☘☘☘☘

前往频道在 Telegram

በሰዋስወ ብርሀን ቅዱስ ዻውሎስ ገዳም እና ለተለያዩ ቤተክርስቲያን ለክብረ በአላት ማውጫ ። በተጨማሪም-ዋዜማ ሥርዓተ ማኅሌት - መዝሙራት ስንክሳር - የየእለቱን ምስባክ ቅኔያት ጥያቄዎች እንዲሁም የወቅታዊ ነገር መወያያ በተጨማሪም @eotcww ብለው ይቀላቀሉን ለወዳጅ ዘመድዎ share#Share#Share# ያድርጉ።

显示更多
1 161
订阅者
无数据24 小时
无数据7 天
无数据30 天
帖子存档
❤ "በስመ አብ ወወልደ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤ ❤ መስከረም ፬ (4) ቀን። ❤ እንኳን ከግብጽ ለኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ተሾመው ለመጡ በመላው ዓለም እና በኢትዮጵያ ከ 10 ሺህ በላይ የዋሻ እና ሕንጻ ቤተ ክርስቲያንን ላነጹ ለብጹዓዊ አቡነ ሙሴ ዘድባ ለዕረፍት በዓል በሰላም አደረሰን። + + + ❤ ብጹዕ አቡነ ሙሴ ዘድባ፦ በአባታቸው የእቤታችን ጠባቂ የአረጋዊ ቅዱስ ዮሴፍ የልጅ ልጅ ሲሆኑ፤ በእናቸው በኩል ድንግል ማርያም ከልጇ ጋር በቃና ዘገሊላ ሰርግ የተገኘችበት የዶኪማስ የልጅ ልጅ ናቸው። የአባታቸው ስም ቅዱስ ዮስጦስ ሲባል፤ የእናታቸው ስም ቅድስት ጵስርስቅላ (ሶልያና ማርያም) ይባላል። ❤ በሊቀ መላእክት በቅዱስ ገብርኤል አብሳሪነት ታኅሣሥ 8 ቀን ተወለዱ። በዚህች ቀን ከእናታቸው እቅፍ በመውረድ "ለአብ ለወልድ ለመንፈስ ቅዱስ ምስጋና ይሁን፤ ከጨለማ ወደ ብርርሃን ላወጣኸኝ" ብለው ፈጣርያቸውን አመስግነዋል። በ40 ኛው ቀን የጌታ ሐዋርያት ቅዱሳን ጴጥሮስ፣ ያዕቆብ፣ ፊሊጶስና እንድርያስ ሆነው ጥር18 ክርስትናን አቡነ ሙሴን አነሱዎቸው። ❤ በ3 ዓመታቸው ወላጆቻቸው ለቤተ ክርስቲያን ሰጧቸው። ቅዱስ ፋኑኤልና ቅዱስ ዮናኤል ሕብስት ሰማያዊ እያመጡ ይመግቧቸው ነበር። ከዚህ በኋላ መምህራቸው ዝክረ ጻድቅ ብሉያትንና ሐዲሳትን አስተማራቸው። በወንጌላዊው በቅዱስ ማርቆስ እጅ ዲቁና ተሾሙ። እመቤታችን ማርያምም ለብፁዓዊ ሙሴ ልፋፈ ጽድቅ፣ ሰኔ ጎልጎታን፣ ባርቶስና ራዕየ ማርያምን ሰታቸዋለች። ወገባቸውን ከጠጉር በተሰራ መታጠቂያ ይታጠቁ ነበር። አቡነ ዘበሰማያትም በጀመሩ ጊዜ ሰባቱ ሰማያት ተከፍተውላቸው ከአጋዕዝተ ዓለም ሥላሴ ጀምሮ ሁሉንም ቅዱሳን በግልጥ ያያሉ። ሲሰግዱ እንባቸው ደረታቸውና እግራቸውን እያራሰ በመሬት ይፈሳል። በዓለም ብዙ የዋሻ ቤተ ክርስቲን አንጸዋል። ❤ የሕንፃ ሥራ ከመደመራቸው በፊት 40 ቀን ይጾማሉ። ሁለቱ መላእክት ቅዱስ ፍርክኤልና ቅዱስ ፍናኤል እየረዷቸው መቅደስን ያንጻሉ። የዋሻ ቤተ መቅደስ ሥራ ጎን ለጎን መስቀልና ሌሎች ንዋየ ቅዱሳት ይሠራሉ። የሚሠሯቸው መቅደሶች ከፊሉ የሚታዩ ምዕመናን የሚገለገሉባቸው ሲሆን የቀሩት የማይታዩ ስውራን የሚገለገሉበት ነው። አቡነ ሙሴ ጵጵስና የተሾሙት በ 12ቱ ሐዋርያት በአንድነት ነው። ዘመናቸውን ሁሉ ከ24ቱ ካህናተ ሰማይ ጋር በመሆን የአብ የወልድ የመንፈስ ቅዱስን መንበር አጥነዋል። በድንግልናቸው በንጽሕናቸው የከበሩ 12 ክንፍ የተጎናጸፉ ናቸው። ጥቂቶች ለማየት የታደሉትን ብሔረ ብፁዓን ሄደው አይተዋል። ❤ አቡነ ሙሴ በግብፅና በእስራኤል መካከል ሲካር በሚባል ቦታ ካገለገሉ በኋላ ጣዖታትን ለማሳፈር ወደ መቄዶንያ ሄደው ጣዖት አምላኪውን ንጉሥ ገሰጹት። ንጉሥ ተቆጥቶ አጥንታቸው እስኪሰበር ድረስ በብረት አስደብድቦ በብረት አልጋ ላይ አስተኝቶ እሳት አነደደባቸው። ቅዱስ ሚካኤልና ቅዱስ ገብርኤል ግን ዳሰው ፈወሷቸው። በማግስቱ ወደ ፍርድ አደባባይ ቢወስዷቸው ምንም እንዳልሆኑ ንጉሡ በማየቱ በንዴት ሰውነታቸውን በሰይፍ አስቆራረጠ። ከሰውነታቸው ደም፣ ውሃ፣ ወተትና መዓር ወጣ። ጌታችንም አድኗቸው "በስምህ የተማፀነውን መልካም ነገር አደርግታለሁ" ብሎ ቃል ኪዳን ገባላቸው። ❤ በግብጽ አንስጣስዮስ ቴዎዶስዮስ ተብለው ሢነግሡ መላእክት የአባቱ የዳዊት መንግሥት ቅባት ቀቧቸው፤ የመንግሥት ልብስ አለበሷቸው፤ የመንግሥት ሥርዓት ሁሉ ሰጧቸው። የጣዖታትን ቤት አፍርሱ "ቤተ ክርስቲያንን ሥሩ" በማለት ኅዳር 12 ቀን አዋጅ ነጋሪን ላኩ። ጌታችን በግብፅ ተሶዶ ሳለ ለአረጋዊ ቅዱስ ዮሴፍ የተናገረው ትንቢት ተፈፀመ "ከልጅህ የሚወለድ በግብፅ ያሉትን ጣዖቶች አፍርሶ ሃይማኖትን ያጸናል" ብሎ ነበር። እዲሁም ቅድስት አርሴማ ሳትወለድ በስሟ የተሰየመውን ታቦት በግብፅ ያገኙና ያከበሩ ናቸው (ገድለ አርሴማ 7ኛ ተአምር)። ❤ በግብፅ ደብረ ምጥማቅ ማርያም በመጀመሪያ ሰርተው የቀደሱት አቡነ ሙሴ ናቸው። በተጨማሪ ብዙ የሕንጻ ቤተ ክርስቲያንና የዋሻ ቤተ ክርስቲያን አንጸዋል። እንደ ቅዱሳን ብዙ ድንቅ ተአምር አድርገዋል። ለምሳሌ አውሬ ገድሏቸው ተጠራቅሞ የነበረ አፅም ላይ ጸልየው አራት ሺህ የሞቱ ሰዎችን ከሞት አስነስዋል። 40 ዓመት በንግሥና ከቆዩ በኋላ ከብዙ ተከታዮቻቸው ጋር ወደ አስቄጥስ ገዳም ለምነና ስጓዙ በበረሃው ተርበው ለወደቁት ወደ እግዚአብሔር ሲጸልዩ መና ወርዶላቸው መግበዋል አስቄጥስ ገዳም ሲደርሶ አቡነ መቃርስ ነበሩ የተቀበሏቸው፡፡ ❤ በአስቄጥስ በአቡነ እንጦንስ ስም የመጀመሪያውን ቤተ ክርስቲያን ሠርተው ከፈፀሙ በኋላ አቡነ እንጦንስንና አቡነ መቃርስ በምንኵስና ልብስ፣ በመላእክት አስኬማ፣ በቅንዓት፣ በቀሚስና በቆብዕ ላይ ለ40 ቀን ጸልየው ጥር 22 ቀንተክለ ማርያም ብለው ሰይመው አመነኰሷቸው። በዚያውም አቡነ መቃርስ ከበታቻቸው ሾሙ። በአስቄጥስ ብዙ ተከታዮቻቸውን አመንኵሰው ቀድሞ ወደ፡ሠሯቸው ቤተ መቅደሶች ይልኳቸው ነበር። የቀሩት ደግሞ በኋላ ወደ ኢትዮጵያ ሲመጡ አብረዋቸው መጥተዋል። ❤ የኢትዮጵያ የመጀመርያው ጳጳስ አቡነ ሰላማ በማረፋቸው ነገሥታት አብርሃ ወአጽብሃ ጳጳስ እንዲልኩላቸው ከእጅ መንሻ ጋር ወደ ግብፅ ላኩ። አቡነ አትናቴዎስ ፈቃደ እግዚአብሔር ጠይቀው አቡነ ሙሴ ከአስቄጥስ ገዳም ለኢትዮጵያውያን አባት እዲሆኑ አቡነ ሚናስ ብለው ሾሙ። ከሦስት ሺህ ልጆቻቸው ጋር ሆነው ብዙ ቅርስ ይዘው አባታችን ወደ ኢትዮጵያ ሲመጡ ሕዝቡ በደስታ ተቀበሏቸው። ብዙ መጽሐፍትን ከአረብኛ ወደ ግእዝ ቋንቋ ተርጉመው ጽፈዋል። ይጽፉበት የነበረው ብዕር አድሮ በማግስቱ ለምልሞ አብቦ ይገኛል። ቀለም ይበጠብጡበት የነበረው የቀንድ ዋንጫም ከመሬት ተጣብቆ ያገኙት ነበር። በእጃቸው ሲያላቅቁት ከመሬት ጠበል ይፈልቃል፣ በጠበሉም ህሙማንን ፈውሰውበታል። ❤ በኢትዮጵያ 5መቶ የዋሻ ቤተ ክስቲያን ያነጹ ሲሆን በአጠቃላይ በመላው ዓለም ከ10 ሺህ በላይ ቤተ ክርስቲያ ሰርተዋል፣ አንጸዋል (መለከት መጽሔት 2007 ዓ.ም)። በእንቁና በእብነ በረድ ከሠራቸው ቤተ ክርስቲያኖች መካከል በአራራት ደብር (ከምድር ጥፋት በኋላ የኖኅ መርከብ መጀመርያ ያረፈችበት) በጻድቁ ኖኅ ስም፣ አብርሃም ሥላሴን በድንኳኑ ባስተናገደበት ስፍራ በቅድስት ሥላሴ ስም፣ በሕንድ (በሐዋርያው ቅዱስ ቶማስ መቃብር ቦታ) በቅዱስ ቶማስ ስም፣ በአርማንያና በፋርስ (በሰማዕቱ ቅዱስ ጊዮርጊስ ስጋውን ባሳረፉበት ቦታ) በቅዱስ ጊዮርጊስ ስም። ❤ በኢትዮጵያ በአቡነ ሙሴ ከታነጹት ቤተ ክርስቲያ ውስጥ የተወሰኑት፦ 1.የድባ መቅደሰ ማርያም አቡነ ሙሴ አንድነት ገዳም (ባለ ሰባት መቅደስ ፎቅ)፣ የረፍታቸው ቦታ፣ በትረ ሙሴያቸውና የእጅ መስቀላቸው ያለበት (ሰሜን ወሎ ዳውንት) 2.አእማድ ቅድስት ሥላሴ ገዳም (መቄት) እንደ አቡነ አሮን መንክራዊ ጣራው ክፍት ሆኖ ዝናብ የማይገባው፣ ❤ በመጨረሻ ብጹዕ አቡነ ሙሴ በቤተ ሚናስ ቤተመቅደስ የድባ መቅደሰ ማርያም አቡነ ሙሴ ገዳም መሰከረም 4 በዕለተ እሁድ ዐረፋ። ወርሃዊ በዓላቸው ወር በገባ በ4 ነው። በተለይ ጋብቻን የሚቀድሱ፣ ክህነት የሚባርኩ፣ መናንያንን የሚያጸኑ አረጋዊን አባት ናቸው። ከአባታችን ከብፁዕ አቡነ ሙሴ እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትንና በረከትን ያሳትፈን በጸሎታቸውም ይማረን!። ምንጭ፦ የድባ መቅደሰ ማርያም አቡነ ሙሴ አንድነት ያሳተመው መጽሔት ላይ የተወሰደ። ❤ በየቀኑ ይህን ቴሌግራም ላይ ማግት ከፈለጉ ከታች ያለውን ሊኩን ይጫኑ

ገደ ወዲያውም ዐረፈ አባ ሳሙኤልም ቀበረው ገድሉንም ጻፈ። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በአባ ሙሴ ጸሎት ይማረን ለዘላለሙ አሜን። ምንጭ፦ የመስከረም 2 ስንክሳር። + + + ❤ "ሰላም ለሙሴ ዘረሰየ እምዓለም ተፈልጦ። ቈጽለ ሆሣዕና አራዘ ወፍሬ ዘይቶን ሥብጦ። በብዙኅ መከራ አምድኅረ ሰይጣን አስፈጦ። እግዚአብሔር መሐሪ መንገደ ገዳም ሜጦ። ኀበ ሥጋሁ የዓርፍ ወነፍሶ ይትሜጦ። ሊቁ አርከ ሥሉስ (አርኬ) የመስከረም 3። + + + ❤ የዕለቱ ምስባክ፦ "እስመ አድኀንካ ለነፍስየ እሞት። ወለአዕይንትየኒ እምአንብዕ። ወለእገርየኒ እምዳኅዕ"። መዝ 55፥13-14። የሚነበቡት መልዕክታት 2ኛ ተሰ 3፥13-ፍ.ም፣ 2ኛ ዮሐ 1፥8-ፍ.ም እና የሐዋ ሥራ 20፥28-31። የሚነበበው ወንጌል 18፥18-23። የሚቀደሰው ቅዳሴ የቅዱስ ዲዮስቆሮስ ቅዳሴ ነው። መልካም የአባ አንበስ የዕረፍት በዓል ለሁላችንም ይሁንልን። ❤ በየቀኑ ይህን ቴሌግራም ላይ ማግት ከፈለጉ ከታች ያለውን ሊኩን ይጫኑት። https://t.me/Eotcw

❤ "በስመ አብ ወወልደ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤ ❤ መስከረም ፫ (3) ቀን። ❤ እንኳን ለገዳመ ሲሐቱ ለአባ ሙሴ ለዕረፍት በዓል፣ የከበረ አባት ሊቀ ጳጳሳት አባ ዲዮናስዮስ ከተሾመ በሁለተኛው ዓመት በእስክንድርያ ከተማ ነፍስ ከሥጋዋ ጋር ትሞታለች በዕለተ ትንሣኤም ከሥጋዋ ጋር አብራ ትነሣለች ስለሚሉ ክፉዎች የኤጲስቆጶሳት የአንድነት ጉባዔ ለተደረገበት ቀን በሰላም አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰቡ፦ ከሰማዕት ከአባ ዲዮስቆሮስ፣ ሰማዕት ከሆነ ከሊቀ ጳጳሳት አባ ዲዮናስዮስ፣ ከዲያቆን በትንከል፣ ከብዙዎች የፋርስ ሰማዕታት ከዕረፍታቸው መታሰቢያ እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን። + + + ❤ በዚች ቀን የከበረ አባት ሊቀ ጳጳሳት አባ ዲዮናስዮስ ከተሾመ በሁለተኛው ዓመት በእስክንድርያ ከተማ የኤጲስቆጶሳት የአንድነት ጉባዔ ተደረገ። ❤ ይህም ጉባዔ የሆነው ነፍስ ከሥጋዋ ጋር ትሞታለች በዕለተ ትንሣኤም ከሥጋዋ ጋር አብራ ትነሣለች ስለሚሉ ክፉዎች በዐረቢያ አገር ስለ ተነሡ ሰዎች ነው። እነርሱም ለከፋችና ብልሹ ለሆነች ሃይማኖታቸው የፈጠራ ድርሰትን ደርሰው በእስክንድርያ ከተማ ወደሚኖሩ ሰዎች ላኩ። ❤ አባታችን ሊቀ ጳጳሳት አባ ዲዮስናስዮስም ይህን ነገር በሰማ ጊዜ እጅግ አዘነ ከዚህ ከክፉ ሥራም እንዲመለሱ አስተማራቸው ገሠጻቸውም እነርሱ ግን አልሰሙትም አልተመለሱም። ስለዚህም በእነርሱ ላይ ይህን ጉባዔ ሰብሰቦ ተከራከራቸው ስሕተታቸውንም ገልጾ አስረዳቸው እነርሱ ግን ሰይጣን አሳውሮአቸዋልና ተጸጽተው አልተመለሱም ይህም ጉባኤ ረግሞ ከቤተ ክርስቲያን አንድነት ለይቶ አሳደዳቸው። ❤ ይህም አባት ዲዮናስዮስ ስለርሳቸው ድርሳናትን ደረሰ በውስጣቸውም እንዲህ የሚል "በዚህ በቸርነቱ ስጦታ ውስጥ የእግዚአብሔር ፍቅር የጎላ የተረዳ ሆነ ነፍስ ረቂቅ ስለሆነች እንደ መላእክት በሕይወት እንድትኖር እንጂ እንዳትሞት እንዳትጠፋ ማድረጉ ነው። ❤ ከሥጋዋም በምትወጣ ጊዜ ስለ በጎ ሥራዋ እንደሚገባት መጠን ወደ ሕይወት ቦታዋ ይወስዷታል ወይም እንደ ሥራዋ ክፉነት ወደ ሥቃይ ይወስዷታል። በትንሣኤ ቀንም ንቃሕ መዋቲ ተብሎ ዓዋጅ ሲነገር በፈጣሪያቸው ትእዛዝ የሙታን በድኖች ሲነሡ ነፍሳት እንዲህ ይሆናሉ እያንዳንዲቱ ነፍስ ከሥጋዋ ተዋሕዳ አብራ ትነሣለች"። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳን አባቶቻችን ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ትድረሰን ለዘላለሙ አሜን። + + + ❤ የገዳመ ሲሐት አባ ሙሴ፦ ይህም ቅዱስ ከመነኰሰ ጀምሮ ዓለምን ትቶ ከበረሀ ገብቶ በጾም በጸሎት በመጠመድ ተጋደለ። እግዚአብሔር ዘይቶንና የተምር አትክልት ያለባትን የአትክልት ቦታ በማየት ልቡን ብሩህ እስከ አደረገለት ድረስ በወሩ መባቻም ከዘንባባ ዕንጨትና ከዘይቶን የወደቀውን ፍሬ ወስዶ ይበላል። ምግቡም ታናሽ ወፍ በሚመገበው መጠን ልክ ነው ልብሱም ከዘንባባ ቅጠል የተሠራ ሰሌን ነው። ስለዚህ ለሚያስጨንቅ ለክረምት ቅዝቃዜና ለበጋ ቃጠሎ የተጋለጠ ከዚህም ጋር በጾምና በጸሎት የተጠመደ ነው ። ❤ ነገር ግን መጻሕፍትን የሚያውቅ አይደለም የዱር አራዊትም በየወገናቸው ወደርሱ ይመጡ ነበር እርሱም ያረጋጋቸዋል። የጸሎት ጊዜም ሲደርስ በእጁ ሲጠቅሳቸው ይሔዳሉ። ድርቅ የሆነ እንደሆነም ሊያነጋግሩት እንደሚሹ ሁነው መጥተው በፊቱ ይቆማሉ እርሱም የሚሹትን በመንፈስ ቅዱስ አውቆ በጸሎቱ ዝናብን ያወርድላቸዋል። እንዲሁም እያደረገ ከእርሳቸው ጋር አርባ አምስት ዓመት ኖረ ። ❤ ሰይጣንም ቀናበት ዘመኑ በአለፈና እጅግ በአረጀ ሽማግሌ አምሳል በጥቂት በጥቂት ሲያዘግም ከበዓቱ ውስጥ ሁኖ አየው ለዚህ ቅዱስ አባ ሙሴም ገዳማዊ መናኒ መስሎት ወደርሱ ሒዶ አምጥቶ ወደ በዓቱ አስገባው አራዊት ግን በሽማግሌ የተመሰለውን ሰይጣን በአዩት ጊዜ ከእርሱ ሸሹ። ❤ ከዚህ በኋላ አባ ሙሴን አገሩንና ሃይማኖቱን ጠየቀው እርሱም ሁሉን ነገረው ደግሞ አባ ሙሴ ኑሮው እንዴት እንደሆነ ሽማግሌውን ጠየቀው ። በሽማግሌ የተመለሰ ሰይጣንም እንዲህ ብሎ መለሰለት "እኔ በዓለም ኃጢአት በመሥራት ብዙ ዘመናት ኖርኩ አንዲት ሴት ልጅንም ወለድኩ ። ከዚያም የዓለምን ኃላፊነትና ጠፊነት አሰብኩ ከዓለምም ወጥቼ በበረሀ ውስጥ አርባ ዓመት ኖርኩ። ልጄን ያገባት እንደሌለ በአሰብኩ ጊዜ በዚህ ነገር ምክንያት ወዳንተ መጣሁ ከአንተ በቀር የሚያገባት የለምና በሞትኩም ጊዜ የምትቀብረኝ አንተ ነህ ብዙ ስፍራዎችና የአታክልት ቦታዎችም ስላሉኝ ሁሉንም እንተ ትወርሳለህ"። ❤ አባ ሙሴም ሰምቶ ደነገጠ "እኔ መነኲሴ ስሆን ይህን እንዴት አደርጋለሁ" አለ የተመረጡ ጻድቃን ሲሆኑ ሚስቶች የነበሩአቸው አብርሃምን ሙሴን ዳዊትን ከብሉያት መጻሕፍት ምስክር ማስረጃ አድርጎ አመጣለት በዚህም ወደ ተንኰሉ ልቡን አዘነበለው። በውስጡ ያጌጠች ሴት ልጅ ያለችበትን የተሸለመ አዳራሽ አሳየውና ከዚያም በኋላ እንደሞተ ሆነ አባ ሙሴም አይቶ በለዩ አለቀሰ ገንዞም ቀበረው። ❤ ልጅቷ ወዳለችበት ለመግባት በፈለገ ጊዜ ጥቅል ነፋስ ነፍሶ የኋሊት ጣለው ከዚህ በኋላ ልቡ ሲመለስለት አዳራሹንም ልጅቷንም የአትክልት ቦታዎችንም አጣ ፈጽሞ እያደነቀ ወደ ማደሪያው ተመለሰ ከዕንጨቱም ፍሬ ምግቡን ሊመገብ ፈለገ በአፉም ውስጥ መራራ ሆነበት በረኃብም ስለ ተጨነቀ ወደ ዱር ወጥቶ ሔደ። ❤ ከዚህም በኋላ በአህያው ላይ ተቀምጦ ወደ እስክንድርያ በሚሔድ በሽማግሌ ነጋዴ አምሳል ሰይጣን ተገናኝው መብልና መጠጥም ይዞ ነበር አባ ሙሴንም ከርሱ ጋር ወሰደው ወዳንድ አገርም አድርሶ በዚያ ተወው ። ❤ ዳግመኛም በገዳማዊት በመናኒነት በምትኖር አምሳል ሰይጣን ታየው እርሷም ውኃ የምትቀዳ መስላ ነው ሥራውን ጠየቀችው ሰይጣን እንደ ፈተነው ሁሉን ነገራት በልቧም ሳቀችበት ወደ ቤቷም ወስዳው አብልታ አጠጥታ ከዚያ በኋላ የጋብቻን ነገር አሳሰበችው ብዙ ገንዘብም እንዳላት እርሷም የሟች ንጉሥ እንደሆነት ነገረችው። ልቡም እንደአዘነበለ አይታ "እኔ አይሁዳዊት ነኝ እኛም ብዙዎች ነን" ሃይማኖቱንም እስከካደ ድረስ በብዙ ተንኰል ተስፍ አስደረገችው ። ❤ ዳግመኛም እንዲህ አለችው "ና ወደ በረሀ እንውጣና ያኖርኩትን ገንዘብ እንውሰድ" ብላ ውኃ ወደሌለበት በረሀ ወሰደችው ከተራራ በላይም ወጥታ ተለወጠችበት እንዲህም አለችው "እኔ ብዙዎችን ያሳትኩ ሰይጣን አንተነንም ከገዳምህ አስመጣሁህ ሃይማኖትህንም አስካድኩህ እነሆ በዚህ በረሀም ሙተህ ነፍስህ ወደገሃነም ትወርዳለች" ይህንንም ብሎ ሰይጣን ከርሱ ተሠወረ። በተመለሰም ጊዜ በቀኝም በግራም መንገድ አጣ የሚጠጣውም ውኃን አላገኘም ምድር ጠበበችው በምድር ላይም ወድቆ በፊቱ ውስጥም አፈርን በተነ ነፍሱም ከሥጋው ለመለየት እስከደረሰች ደረስ ተንከባለለ ጭኸ መሐሪና ይቅር ባይ ሰውን የሚወድ እግዚአብሔር ራራለት ያጽናናው ዘንድ መልአኩን ላከለት እርሱም "ኃጢአትህ ተሠረየልህ እስከ ሰባት ቀንም ታርፍለህ የእግዚአብሔር አገልጋይ ሳሙኤልም ይቀብርሃል" ብሎ አጽናናው ሰላምታም ሰጥቶት ዐረገ ። ❤ ያን ጊዜም ሳሙኤል መጣ ንጉሥ ኢጋቦም በበረሃ ውስጥ ወደአነፃት ቤተ ክርስታያን ወሰደው እርሷም ገዳማውያን የሚሰበሰቡባት ተሰውራ የምትትኖር ናት ወደርሷም በደረሱ ጊዜ ቅዱሳን ተሰብስበው መሥዋዕትን ሲያሳርጉ አገኙና በአንድነት ሥጋውንና ደሙን ተቀበሉ ሰንብትም ከሆን በኋላ ከቅዱሳን መቃብር በረከትን ሊቀበሉ ከአባ ሳሙኤል ጋራ አብረው ሔዱ ከዚያም ደርሶ አባ ሙሴ ሰ

❤ "በስመ አብ ወወልደ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤ ❤ መስከረም ፫ (3) ቀን። ❤ እንኳን ለኢትዮጵያዊው ጻድቅ ታላቁ የሥውራ ቅዱሳን መኖርያ የሆነው ገዳም ደብረ ሐዘሎው ለመሰረቱ፤ አንበሳ እንደ ፈረስ ያገለግላቸው ለነበሩ ለታላቁ አባት ለአቡነ አንበስ ለዕረፍት በዓል በሰላም አደረሰን። + + + ❤ አባ አንበስ፦ እኚህ አባት ከቅድስናቸው የተነሣ ከቦታ ቦታ የሚንቀሳቀሱት በአንበሳ ላይ ተጭኖ ነው፡፡ ተአምራትን በማድረግና ወንጌልን በማስተማር በጾም ጸሎት አብዝቶ የደከመ ሲሆን ስለ ሀገራችን ኢትዮጵያ ሌት ተቀን በጸሎት ይተጉ የነበረ ታላቅ አባት ናቸው፡፡ አቡነ አንበስ ትውልዳቸው ትግራይ አድዋ በእንጭጮ ወረዳ ነው፡፡ በስማቸው ትግራይ አድዋ "እንጭጮ አቡነ አንበስ ገዳም" እና በትግራይ ሽሬ ሁለት ትላልቅ ገዳማት አሏቸው፡፡ ቅዱስ ያሬድ በድርሰቱ ደጋግሞ የጠቀሳቸው ሲሆን የያሬድንም የድርሰቱን የአቋቋም ሥርዓት ያመጡት አቡነ አንበስ ናቸው፡፡ ❤ አቡነ አንበስ በአቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ እና በአቡነ ሳሙኤል ዘዋልድባ ጊዜ የነበሩ ሲሆን እሳቸውንም አንበሶች ያገለግሏቸው ነበር፡፡ ጻድቁ አቡነ አንበስ ከአቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ጋር የተገናኘ ትልቅ ታሪክ አላቸው፡፡ የላዕላይ ግብጹ አባ ብንያም፣ በአቡነ ሳሙኤል ዘዋልድባ እና የሐዘሎው አቡነ አንበስ እነዚህ 3ቱ ቅዱሳን ከየአሉበት በአንበሳቸው ተጭነው ምድረ ከብድ አቡዬ ዘንድ እንደደረሱ የአቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ አንበሶች የ3ቱንም ቅዱሳን አንበሶች ዋጡዋቸው፣ አቡዬም በዚህ አዝነው ከበዓታቸው ወጥተው አንበሶቻቸውን "ትፉ" ብለው የበሉአቸውን አንበሶቻቸውን አስተፍተዋቸው ለ3ቱም ቅዱሳን የተበሉባቸውን አንበሶቻቸውን መልሰውላቸዋል፡፡ ❤ ይኸውም የሆነው እኝዲህ ነው፡- አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ በዝቋላ 7ቱ ሊቃነ መላእክት እየረዷቸው 70 ሺህ እልፍ አጋንንትን በእሳት ሰይፍ ፈጅተው ካጠፏቸው በኋላ ወደ ምድረ ከብድ ተመለሱ፡፡ ከዚህም በኋላ መንፈስ ቅዱስ የጠራቸው ሦስቱ ቅዱሳን አቡነ ሳሙኤል ዘዋልድባ አቡነ አንበስ ዘሐዘሎ እና የላዕላይ ግብጹ አቡነ ብንያም በአንበሶቻቸው ሆነው ወደ ጻድቁ አባት አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ዘንድ ምድረ ከብድ ገዳም መጡ፡፡ አባታችን ግን ስለተሰወራቸው እስከ 7 ቀን ድረስ በምህላ ሰነበቱ፡፡ የአቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ አንበሶችም መጥተው የ3ቱን ቅዱሳን አንበሶች በልተውባቸው ተሰወሩ፡፡ 3ቱም ቅዱሳን ፈጽመው ደነገጡ፡፡ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስም የቅዱሳኑን ሀዘንና ድንጋጤ ተመልክተው በታላቅና በሚያስፈራ ግርማ ሆነው ስልሳ ነብሮችንና ስልሳ አንበሶችን አስከትለው ተገለጡላቸው፡፡ ቅዱሳኑም ከአቡነ ገብረ መንፈስቅዱስ ግርማ የተነሣ ስለደነገጡ እንዳይፈሩም አረጋጉአቸው፡፡ ❤ ከዚህም በኃላ አባታችን "በምን ምክንያት ወደዚህ ገዳም ወደ እኔ መጣችሁ?" አሏቸው፡፡ ሦስቱ ቅዱሳን እንዲህ አሉ፡- "ጸሎትህ ቅድስት እንደሆነች ባወቅን ጊዜ ወደ አንተ መጣን፤ አንተ በሁሉ ርእሰ ባሕታውያን ነህና የእግዚአብሔርን ሥራ ትነግረን ዘንድ መጣን፤ ባላገኘንህም ጊዜ እስከ 7ቀን አለቀስን" አሉት፡፡ ❤ ዳግመኛም "አንበሶችህ መጥተው አንበሶቻችንን ደማቸውን ጠጡ ቆዳቸውንም በጥፍራቸው በጣጠሱ" ብለው ነገሯቸው፡፡ አባታችንም ይህንን ሲሰሙ አንበሶቻቸውን "እስከ ዕለቴ ሞቴ ድረስ በእግሬ ከረገጥኩት ትቢያ በቀር ምንም እንዳትበሉ ታዛችሁ የለምን? እግዚአብሔር ያላዘዛችሁትን ለምን በላችሁ? በሉ አሁንም የበላችሁትን ትፉ" አላቸው፡፡ እነዚያም አንበሶች አፋቸውን ከፍተው አንዳች ሳያስቀሩ አጥንታቸውን ሥጋቸውን በሙሉ ተፉአቸው፡፡ ጻዲቁ አባታችንም ወደ ምሥራቅ ተመልሰው እግዚአብሔርን ከለመኑ በኋላ በአንበሶቹ ሥጋ ላይ ባረኩና "በኢየሱስ ክርስቶስ ኃይል ተነሡ" አሏቸው፡፡ አንበሶቹም እንደ ዐይን ፈጥነው ተነሥተው እንደ ቀድሞው ሆኑ፡፡ ከአባታችን ከአቡነ አንበስ እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን። በጸሎታቸውም ይማረን!። ምንጭ፦ ከገድላት አንደበት። + + + ❤ "ሰላም ለአባ አንበስ በፍኖተ ፃሞ ወሥራሕ። ዘይጼዓን ዘልፈ ዲበ አንበሳ መፍርህ። ለዘይጻድቅ ብእሲ እስከ ይገብእ ፍትሕ። ኢያጠፍኦ ማይ ወርደተ ዝናም ብዙኅ። ለዓሠረ ደሙ ቀይሕ ዘሀሎ በኰኵሕ"። ሊቁ አርከ ሥሉስ (አርኬ) የመስከረም 2። ❤ በየቀኑ ይህን ቴሌግራም ላይ ማግት ከፈለጉ ከታች ያለውን ሊኩን ይጫኑት። https://t.me/Eotcw

🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿 ሥርዓተ ማኅሌት ዘመስከረም ምትረተ ርእሱ ለቅዱስ ዮሐንስ "መስከረም ፪" 🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼 ስምዓኒ እግዚኦ ጸሎትየ ሃሌ ሉያ፤ ሃሌ ሉያ ወይብጻሕ ቅድሜከ ገዓርየ ሃሌ ሉያ፤ ሃሌ ሉያ ወኢትሚጥ ገጸከ እምኔየ፤ በዕለተ ምንዳቤየ አጽምእ ዕዝነከ ኀቤየ ሃሌ ሉያ፤ ሃሌ ሉያ አመ ዕለተ እጼውአከ ፍጡነ ስምዓኒ ሃሌ ሉያ፤ ሃሌ ሉያ ለዓለም ወለዓለመ ዓለም፤ ሃሌ ሉያ ዘውእቱ ብሂል፤ ንወድሶ ለዘሃሎ እግዚአብሔር ልዑል፤ ስቡሕ ወውዱስ ዘሣረረ ኲሎ ዓለመ፤ በአሐቲ ቃል። @EOTCWW ነግሥ ሰላም ለአብ ገባሬ ኲሉ ዓለም፤ ለወልድ ሰላም ወለመንፈስ ቅዱስ ሰላም፤ ለማርያም ሰላም ወለመላእክት ሰላም፤ ሰላም ለነቢያት ወለሐዋርያት ሰላም፤ ለሰማዕታት ሰላም ወለጻድቃን ሰላም። @EOTCWW @EOTCWW ዚቅ ዛቲ ይእቲ ትንቢቶሙ ለነቢያት፤ ስብከቶሙ ለሐዋርያት፤ እሞሙ ለሰማዕት ወእኅቶሙ ለመላእክት። @EOTCWW ዓዲ ዚቅ (ሌላ) ዛቲ ይእቲ እኅተ ትጉሃን መላእክት፤ ወለተ ኄራን ነቢያት፤ እሞሙ ለሐዋርያት፤ ሞገሶሙ ለጻድቃን ወሰማዕት። @EOTCWW ዘጣዕሙ ሰላም ለዝክረ ስምኪ ዘመንክር ጣዕሙ፤ ለወልድኪ አምሳለ ደሙ፤ መሠረተ ሕይወት ማርያም ወጥንተ መድኃኒት ዘእምቀዲሙ፤ ኪያኪ ሠናይተ ዘፈጠረ ለቤዛ ዓለሙ፤ እግዚአብሔር ይትባረክ ወይትአኮት ስሙ። @EOTCWW ዚቅ ንትፈሣሕ ኲልነ በዝክረ ስምኪ ጥዑም፤ ወበደመ ዮሐንስ መዓድም፤ ቅድስት ማርያም ቤዛዊተ ኲሉ ዓለም። @EOTCWW መልክአ ዮሐንስ ሰላም ለሥእርተ ርእስከ እንተ ደለዎ እኳቴ፤ ወለርእስከ ሰላም ዘተመትረ ከመ ናቡቴ፤ ርእሰ ዓውደ ዓመት ዮሐንስ ወላዴ መጥቅዕ ወአበቅቴ፤ መብልዕ ዜና ፍቅርከ ወነገረ ጽድቅከ ስቴ፤ ያስተፌሥሕ መላእክተ ወሰብአ መዋቴ። @EOTCWW ዚቅ አመ ይገብር ሄሮድስ በዓለ ዘዕለተ ልደቱ፤ መጽአት ወለተ ሄሮድያዳ ወዘፈነት ሎቱ፤ አሥመረቶ ወትቤሎ ሀበኒ በፃህል ርእሰ ዮሐንስ ወንጌላዊ። @EOTCWW ወረብ አመ ይገብር ሄሮድስ በዓለ ዘዕለተ ልደቱ መጽአት ወለታ ለሄሮድያዳ/፪/ አሥመረቶ ወትቤሎ ሀበኒ በጻሕል ርእሰ ዮሐንስ ወንጌላዊ/፪/ @EOTCWW መልክአ ዮሐንስ ሰላም ለጒርኤከ ወለክሣድከ ዓዲ፤ እምዓጸደ ሞት በሊህ ዘኢያጎነዲ፤ እመ ይሄሉ ሕያወ ዮሐንስ አስካለ ጋዲ፤ ጊዜ ቀሠመከ ንጉሠ ዓመፃ ረዋዲ፤ እምበከየ እፎ አቡከ ወላዲ። @EOTCWW ዚቅ ዘሕማማተ እግዚኡ መዋቅሕተ ፆረ፤ ወርእሶ አምተረ ዓቢያተ ተናገረ፤ አስተምህር ለነ ዮሐንስ ዘአጥመቀ ቃለ። @EOTCWW @EOTCWW አመላለስ ዘሕማማተ እግዚኡ መዋቅሕተ ፆረ/፪/ ወርእሶ አምተረ ዓቢያተ ተናገረ/፪/ @EOTCWW @EOTCWW ወረብ ዘሕማማተ እግዚኡ መዋቅሕተ ፆረ ወርእሶ አምተረ/፪/ ዓቢያተ ተናገረ አስተምሕር ለነ ዮሐንስ ዘአጥመቀ ቃለ/፪/ @EOTCWW @EOTCWW መልክአ ዮሐንስ ሰላም ለመከየድከ በአስተሐምሞ ወጻሕቅ፤ ወለአጻብዒከ ሰላም ዘአእዋመ ሥጋ አዕጹቅ፤ ለመንግሥተ ሰማይ ዮሐንስ በእንተ ኪዳንከ ጽድቅ፤ ነዳያን ይወርስዋ እንበለ ብሩር ወወርቅ፤ በሕፍነ ማይ ወክልኤ ጸሪቅ። @EOTCWW ዚቅ ግፉዓን ይትመሐፀንዋ፤ ለመንግሥተ ሰማያት፤ አንተ ውእቱ ዮሐንስ ምስለ ኲሎሙ ሰማዕት። @EOTCWW ወረብ ግፉዓን ይትመሐፀንዋ ለመንግሥተ ሰማያት/፪/ አንተ ውእቱ ዮሐንስ ምስለ ኲሎሙ ሰማዕት/፪/ @EOTCWW @EOTCWW ዓርኬ ተዘኪረከ ምትረተ ርእሱ ለዮሐንስ ግዩር፤ በቅናተ ዓዲም ዘዔለ ወበሠቀ ጸጒር፤ ማዕበለ ጌጋይየ አቅም እግዚአብሔር፤ በከመ አቀምከ ተከዜ ዮርዳኖስ ባሕር፤ እስከ ካህናት ዐደዉ በእግር። @EOTCWW ዚቅ መጽአት ወለተ ሄሮድያዳ ወዘፈነት ሎቱ፤ አሥመረቶ ወትቤሎ፤ ሀበኒ በፃህል ርእሰ ዮሐንስ ወንጌላዊ። @EOTCWW አመላለስ መጽአት ወለተ ሄሮድያዳ ወዘፈነት ሎቱ/፪/ አሥመረቶ ወትቤሎ/፪/ @EOTCWW ወረብ መጽአት ወለተ ሄሮድያዳ ወዘፈነት ሎቱ/፪/ ሀበኒ በፃሕል ርእሰ ዮሐንስ ወንጌላዊ ወንጌላዊ ክቡር (መጥምቅ)/፪/ @EOTCWW @EOTCWW ምልጣን እምሄሶ ለሄሮድስ ይብላዕ መሐላሁ፤ እምያምትር ርእሶ ለዮሐንስ፤ ዓቢይ ነቢይ ሰባኬ ጥምቀት ለንሥሐ ከመ ይእመኑ ሕዝብ በብርሃኑ። @EOTCWW ወረብ እምኄሶ ለሄሮድስ ይብላዕ መሐላሁ ይብላዕ መሐላሁ እምያምትር ርእሶ ለዮሐንስ/፪/ ዓቢይ ነቢይ ዓቢይ ነቢይ ሰባኬ ጥምቀት/፪/ @EOTCWW ወረብ እምኄሶ ለሄሮድስ ይብላዕ መሐላሁ እምያምትር ርእሶ ለዮሐንስ/፪/ ዓቢይ ነቢይ ሰባኬ ጥምቀት ለንሥሐ ሰባኬ ጥምቀት/፪/ @EOTCWW እስመ ለአለም፦ አመ ይገብር ሄሮድስ በዓለ ዘዕለተ ልደቱ መጽአት ወለተ ሄሮድያዳ ወዘፈነት ሎቱ፤ማ፦ አስመረቶ ወትቤሎ፤ሀበኒ በፃህል ርእሰ ዮሐንስ ወንጌላዊ @EOTCW @EOTCW እስመ ለዓለምና ዓዲ(ሌላ) መጽአት ወለተ ሄሮድያዳ፤ ኀበ ንጉስ ወትቤሎ ሀበኒ በፃህል ርእሰ ዮሐንስ ወንጌላዊ፤ማ፦ ወውእቱኒ ወሀባ፤ ወይእቲኒ ወሰደት ለእማ 🌼 መልካም አዲስ ዓመት 🌼 https://t.me/Eotcw # Join & share

እምሄሶ ለሄሮድስ.m4a19.09 MB

❤ "በስመ አብ ወወልደ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤ ❤ መስከረም ፪ (2) ቀን። ❤ እንኳን ለታላቁ ነብይ፣ ሰማዕት፣ ሐዋርያ፣ ካህን ለመጥምቀ መለኮት ለቅዱስ ዮሐንስ ሕግ አፍራሽ በሆነ በንጉስ ሄሮድስ እጅ አንገቱን በመሰየፍ ሰማዕትነት ለተቀበለበት ለዕረፍቱ በዓል በሰላም አደረሰን። በዚች ቀን በጨማሪ ከሚታሰቡ፦ በግብጽ ውስጥ ታዕዳ ከሚባል አገር በሰማዕትነት ከዐረፈ ከቅዱስ ዳስያ፣ ከሰማዕት ዲዲሞስና ቅድስት መሪና ከመታሰቢያቸው እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን። + + + ❤ የዕለቱ አንገርጋሪ ግእዝ ዜማ፦ ሃሌ ሉያ "እምኄሶ ለሄሮድስ ይብላዕ መሐላሁ እምያምትር ርዕሶ ለዮሐንስ ዐቢይ ነቢይ ሰባኬ ጥምቀት ለንስሐ ከመ ይመኑ ህዝብ በብርሃኑ"። ትርጉም፦ ሕዝቡ በብርሃን ኢየሱስ ክርስቶስ ያምኑ ዘንድ የንስሐን ጥምቀት የሚያስተምር የታላቅ ነቢይ የከበረች እራሱን ከሚያስቆርጥ ሄሮድስ መሐላውን ቢሽር ቢያፈርስ ቢክድ ይሻለው ነበር። + + + ❤ የዚህ ሳምንት መዝሙር፦ ሃሉ ሉያ በ፭ "ዮሐንስ አኅድዐ እምካልዓኒሁ አንሐ ወክሐ እንዘ ይብል እምላዕሉ ወረደ ቃለ አብ ወተሐውከ ማየ ዮርዳኖስ እምግርማ ወመለኮት ወደንገጹ ኵሉ ኃይለ ሰማያት ወምድር ከማሁ ኮነ በቢታንያ በተቤ ራባ በማዕዶተ ዮርዳኖስ ወሶበ ርእዩ ዮሐንስ ለኢየሱስ ከልሐ ወይቤ ነዋ በግዑ ለእግዚአብሔር ይቤሎ ኢየሱስ ለዮሐንስ አጥምቀኒ በማይ ከመ ይትቀደስ ማይ በማዕተበ ሰማይ አጥመቆ ዮሐንስ ለኢየሱስ በፈለ ዮርዳኖስ እምድኅረ አጥመቀ ለሊሁ ተጠምቀ ምህሮሙ ሐህዝብ ወይቤሎሙ አክብሩ ሰንበተ ተገበሩ ጽድቀ። ትርጉም፦ የአብ ቃል ከላይ ወረደ የአብ ቃል ከላይ ወረደ እያለ ዮሐንስ ከሌሎቹ ይልቅ አሰምቶ ተናገረ የዮርዳኖስ ውኃ ከመለኮት ግርማ የተነሣ ታወከ የሰማይና የምድር ኃይል ሁሉ ደነገጡ በቢታንያና በቤተ ራባ ዮርዳኖስ ማዶ እንዲሁ ሆነ ዮሐንስ ኢየሱስን ባየው ጊዜ እነሆ የእግዚአብሔር በግ እያለ ጮኸ ኢየሱስ ዮሐንስን በሰማይ ውኃ ይቀደስ ዘንድ በውኃ አጥምቀኝ አለው። ሊቁ ቅዱስ ያሬድ በድጓው ላይ። + + + ❤ የታላቁ ነብይ፣ ሰማዕት፣ ሐዋርያ፣ ካህን፣ የመጥምቀ መለኮት የቅዱስ ዮሐንስ ሰማዕትነት፦ ይህም እንዲህ ነው ፊሊጶስ ሚስት በሄሮድያዳ ምክንያት ነቢዩ ቅዱስ ዮሐንስ በገሠጸው ጊዜ ፊሊጶስ ወንድሙ ስለሆነ ቅዱስ ዮሐንስም የወንድህን ሚስት ልታገባ አይገባህም ይለው ነበርና። ❤ ቅዱስ ዮሐንስም ሄሮድስን የወንድሙን የፊልጶስን ሚስት ሄሮድያዳን ስለማግባቱና ሌላም ያደርገው ስለነበረ ክፉ ሥራ ሁሉ ይገሥጸው ነበር። ደግሞም በተግሣጽ ላይ ተግሣጽን ጨመረ። ስለዚህም ቅዱስ ዮሐንስን ተቀየመውና በግዞት ቤት አኖረው። ❤ ሄሮድስም ቅዱስ ዮሐንስን ይፈራው ነበር ጻድቅ ቅዱስ ሰው እንደሆነ ያውቅ ነበርና ብዙ ይጠባበቀውም ነበር። ሄሮድስ የተወለደባትን ቀን በዓል የሚያከብርባት ዕለት ነበረች መኳንንቱን አለቆቹን መሣፍንቱን ሹሞቹን በገሊላ አገር ያሉትን ታላላቅ ሰዎች ግብር አገባ። ❤ የሄሮድያዳ ልጅም ወደ አዳራሹ ገብታ ዘፈነች ሄሮድስንም ደስ አሰኘችው ከእርሱ ጋር በማዕድ የነበሩትንም ንጉሡም ያቺን ብላቴና "የምትሺውን ለምኚኝ እሰጥሻለሁ" አላት። እስከ መንግሥቱ እኩሌታ ድረስም ቢሆን የለመነችውን ሊሰጣት ማለላት። ወጥታም እናቷን "ምን ልለምነው" አለቻት እናቷም "የመጥምቁ ዮሐንስን ራስ" አለቻት። ❤ ያን ጊዜም እየሮጠች ወደ ንጉሡ ገብታ "የመጥምቁ ዮሐንስን ራስ በውጭት አሁን እንድትሰጠኝ እሻለሁ" ብላ ለመነችው። ንጉሡም ስለ መሐላው አብረውት ስለ ነበሩትም ሰዎች አዘነ እምቢ ሊላት ግን አልወደደም። ❤ ያን ጊዜም ባለወጎችን ላከ በእሥር ቤትም ሳለ የቅዱስ ዮሐንስን ራስ ቆረጡ ራሱንም በወጭት አምጥተው ለዚያች ብላቴና ሰጡአት እርሷም ወስዳ ለእናቷ ሰጠች። ❤ በዚያችም ቀን የቅዱስ ዮሐንስ ራስ ከሄሮድያዳ ከእጆቿ ላይ ወደ አየር ስለ በረች ታላቅ ድንጋፄ ሆነ። "ደግሞም ሄሮድስ ሆይ የወንድምህን ሚስት ልታገባ አይገባህም" እያለች በመጮኸ ዘልፋዋለችና። ❤ ደቀ መዛሙርቱም በሰሙ ጊዜ መጥተው በድኑን ወስደው ቀበሩት። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በከበረ በአጥማቂው ቅዱስ ዮሐንስ ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን። + + + ❤ ቅዱስ ዳስያ፦ ይህም ቅዱስ በግብጽ ውስጥ ታዕዳ ከሚባል አገር ነው። ቅዱስንም የእንዴናው አገረ ገዥ አርያኖስ አሠቃየው ጽኑ ሥቃይንም ከአሠቃየው በኋላ ራሱን በሰይፍ እንዲቆርጡ አዘዘ በመንግሥተ ሰማያትም የሰማዕትነት አክሊልን ተቀበለ። የቅዱስ ዳስያ በረከቱም ከእኛ ጋራ ለዘላለሙ ትኑር አሜን። ምንጭ፦ የመስከረም 2 ስንክሳር። + + + ❤ "ሰላም ለዮሐንስ ግፋዕ ወቅቱል ንጹሕ ወቅዱስ ወስቡሕ ላእክ ወነቢይ ወሰማዕት ድንግል ካህን ጸያሒ ወሰባኪ መጥምቀ እግዚኡ"። ትርጉም፦ ጌታውን ያጠመቀና ሰባኪ፤ መንገድ ጠራጊ፣ ካህን ድንግል ሰማዕት፣ ነቢይና አገልጋይ፤ ምስጉን ቅዱስና ንጹሕ፤ ተገፍቶ የተገደለ ለኾነ ለቅዱስ ዮሐንስ ሰላምታ ይገባል። ሊቁ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ በተአምኆ ቅዱሳን ላይ። + + + ❤ የዕለቱ የማኅሌት ምስባክ፦ "ወይርአዩ አሕዛብ በቅድመ አዕይንቲነ። በቀለ ደሞሙ ለአግብርቲከ ዘተክዕወ። ይባዕ ቅድሜከ ገዐሮሙ ለሙቁሓን"። መዝ 78፥10-11 ወይም 138፥9። የሚነበበው ወንጌል ማርቆስ 6፥14-30 ወይም ማቴ 14፥1-13። + + + ❤ የዕለቱ የቅዳሴ ምስባክ፦ "ሣህል ወርትዕ ተራከባ። ጽድቅ ወሰላም ተሰዐማ። ርትዕሰ እምድር ሠረፀት"። መዝ 84፥10-11። የሚነበበው ወንጌል ዮሐ 1፥15-38። የሚነበቡት መልዕክታት 1ቆሮ 11፥17-ፍ.ም፣ ያቆ 2፥1-14 እና የሐዋ ሥራ 18፥24-ፍ.ም። የሚቀደሰው ቅዳሴ የቅዱስ አትናቴዎስ ወይም የቅዱስ ዮሐንስ ወልደ ነጎድጓድ ቅዳሴ ነው። መልካም የመጥምቀ መለኮት የቅዱስ ዮሐንስ የዕረፍት በዓልና የመጀመሪያ 2014 ዓ.ም ዕለተ ሰንበት ለሁላችንም ይሁንልን። ❤ በየቀኑ ይህን ቴሌግራም ላይ ማግት ከፈለጉ ከታች ያለውን ሊኩን ይጫኑት። https://t.me/Eotcw

🌻እንቋዕ፡አብጽሐክሙ፡አብጽሐነ፡እምዘመነ፡ማርቆስ፡ኀበ፡ዘመነ፡ሉቃስ፡በሰላም፡በፍቅር፡ወበጥዒና። ሠናይ፡በዓል፡ይኩን፡ለኲልክሙ።

🌼 🌼 🌼 🌼 🌼 🌼 🌼 🌼 🌼 🌼 "የምወዳችኹ ልጆቼ! አዲሱ ዓመት የደስታ የሰላምና የጤና እንዲኾንላችኁ ትሻላችሁን? እንኪያስ ገና ከጅምሩ በስካር፣ በዘፈን፣ በገቢረ ኃጢአት ለማሳለፍ አታቅዱ፡፡ የአዲሱ ዓመት የመጀመሪያውን ዕለት ብቻ ሳይኾን እያንዳንዱን ቀን በገቢረ ኃጢአት አትጀምሩት፡፡ እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝ ሥራ፣ ምግባር ትሩፋት በመሥራት አሐዱ በሉ እንጂ፡፡ ዕለታት ክፉዎች ወይም ጥሩዎች የሚኾኑት በተፈጥሮአቸው እንደዚያ ኾነው አይደለም፡፡ ዕለቱን ክፉ ወይም ደግ እንዲኾን የምናደርገው እኛው ነን፡፡ የአምናው ማክሰኞ ከዘንድሮ ማክሰኞ የተለየ አይደለም፡፡ የተለየ የሚያደርገው የእኛ ብርታት ወይም ስንፍና ብቻ ነው። የጽድቅን ሥራ የምንሠራበት ከኾነ አዲሱ ቀን ብቻ ሳይኾን አዲሱ ዓመት ለእኛ መልካም ነው፡፡ ኀጢአት የምንሠራበት ከኾነ ግን ቀኑ ብቻ ሳይኾን አዲሱ ዓመትም ክፉና መከራ የመላበት ይኾንብናል፡፡ አዲሱን ዓመት በበጐ ሥራ የምንጀምረው ከኾነ በዓመቱ በምናደርገው ማንኛውም ክንውን ላይ በጐ ተጽዕኖ ያሳድርብናል፡፡ በትግሃ ሌሊት፣ በቀዊም፣ በጾም በጸሎት እንድንበረታ ስንቅ ይኾነናል፡፡ በስካር፣ በዘፈን፣ በኀዘን የምንጀምረው ከኾነ ግን ዓመቱ ሙሉ እንዲኽ የተጐሳቈለ ዓመትን እናሳልፋለን፡፡ ሕይወታችንን በከንቱ እንገፋለን። ዲያብሎስም ይኽን ጥንቅቅ አድረጐ ስለሚያውቅ ዓመቱን በገቢረ ኀጢአት እንድንጀምረው እየቀሰቀሰ ነው፡፡ ፈቃዳችንን አጥፍቶ፣ ዓይነ ልቡናችንን አሳውሮ በዘፈን፣ በስካር፣ በዋይታ እንድንጀምረው በተለያየ መንገድ እየለፈፈ ነው፡፡...." 💥 💥 💥 💥 💥 💥 💥   ✍ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ 💥 💥 💥 💥 💥 💥 💥

✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨ በእለቱ በቅዳሴ ሰዓት የሚነበብ ወንጌል ✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨ ማቴ. 11:1-20፡ "ወኮነ እምዘሠለጠ" - "ኢየሱስም፡ዐሥራ፡ሁለቱን፡ደቀ፡መዛሙርቱን፡ማዘዝ፡በፈጸመ፡ጊዜ፡በከተማዎቻቸው፡ሊያስተምርና፡ ሊሰብክ፡ከዚያ፡ዐለፈ። ዮሐንስም፡በወህኒ፡ሳለ፡የክርስቶስን፡ሥራ፡ሰምቶ፡ከደቀ፡መዛሙርቱ፡ሁለት፡ላከና።የሚመጣው፡አንተ፡ነህን? ወይስ፡ሌላ፡እንጠብቅ፧አለው። ኢየሱስም፡መልሶ፡እንዲህ፡አላቸው፦ኼዳችሁ፡ያያችሁትን፡የሰማችሁትንም፡ለዮሐንስ፡አውሩለት፤ ዕውሮች፡ያያሉ፡ዐንካሳዎችም፡ይሄዳሉ፥ለምጻሞችም፡ይነጻሉ፡ደንቈሮዎችም፡ይሰማሉ፥ሙታንም፡ይነሣሉ፡ ለድሃዎችም፡ወንጌል፡ይሰበካል፤በእኔም፡የማይሰናከለው፡ሁሉ፡ብፁዕ፡ነው። እነዚያም፡ሲሄዱ፡ኢየሱስ፡ለሕዝቡ፡ስለ፡ዮሐንስ፡ሊናገር፡ጀመረ፥እንዲህም፡አለ፦ምን፡ልታዩ፡ወደ፡ምድረ፡በዳ፡ወጣችሁ? ነፋስ፡የሚወዘውዘውን፡ሸምበቆን፧ወይስ፡ምን፡ልታዩ፡ወጣችሁ? ቀጭን፡ልብስ፡የለበሰ፡ሰውን? እንሆ፥ቀጭን፡ልብስ፡የለበሱ፡በነገሥታት፡ቤት፡አሉ። ወይስ፡ምን፡ልታዩ፡ወጣችሁ? ነቢይን፧አዎን፡እላችኋለሁ፥ከነቢይም፡የሚበልጠውን። እንሆ፥መንገድህን፡በፊትህ፡የሚጠርግ፡መልክተኛዬን፡በፊትህ፡እልካለሁ፡ተብሎ፡የተጻፈለት፡ይህ፡ነውና። እውነት፡እላችኋለሁ፥ከሴቶች፡ከተወለዱት፡መካከል፡ከመጥምቁ፡ዮሐንስ፡የሚበልጥ፡ አልተነሣም፤በመንግሥተ፡ሰማያት፡ግን፡ከሁሉ፡የሚያንሰው፡ይበልጠዋል። ከመጥምቁም፡ከዮሐንስ፡ዘመን፡ጀምሮ፡እስከ፡ዛሬ፡ድረስ፡መንግሥተ፡ሰማያት፡ትገፋለች፥ግፈኛዎችም፡ይናጠቋታል። ነቢያት፡ሁሉና፡ሕጉ፡እስከ፡ዮሐንስ፡ድረስ፡ትንቢት፡ተናገሩ፤ ልትቀበሉትስ፡ብትወዱ፥ይመጣ፡ዘንድ፡ያለው፡ኤልያስ፡ይህ፡ነው። የሚሰማ፡ጆሮ፡ያለው፡ይስማ። ነገር፡ግን፥ይህን፡ትውልድ፡በምን፡እመስለዋለሁ? በገበያ፡የሚቀመጡትን፡ልጆች፡ይመስላሉ፥እነርሱም፡ባልንጀራዎቻቸውን፡እየጠሩ። እንቢልታ፡ነፋንላችሁ፥ዘፈንም፡አልዘፈናችሁም፤ሙሾ፡አወጣንላችሁ፥ዋይ፡ዋይም፡አላላችሁም፡ይሏቸዋል። ዮሐንስ፡ሳይበላና፡ሳይጠጣ፡መጣ፥እነርሱም፦ጋኔን፡አለበት፡አሉት። የሰው፡ልጅ፡እየበላና፡እየጠጣ፡መጣ፥እነርሱም፦እንሆ፥በላተኛና፡የወይን፡ጠጅ፡ጠጪ፥የቀራጮችና፡የኀጢአተኛዎች፡ወዳጅ፡ይሉታል።ጥበብም፡በልጆቿ፡ጸደቀች። በዚያን፡ጊዜ፡የሚበዙ፡ተኣምራት፡የተደረገባቸውን፡ከተማዎች፡ንስሓ፡ስላልገቡ፡ሊነቅፋቸው፡ጀመረ፡እንዲህም፡አለ።" ✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨

1.33 KB

ሰዋስው ☘☘☘☘ - Telegram 频道 @eotcw 的统计与分析