ch
Feedback
ሰዋስው ☘☘☘☘

ሰዋስው ☘☘☘☘

前往频道在 Telegram

በሰዋስወ ብርሀን ቅዱስ ዻውሎስ ገዳም እና ለተለያዩ ቤተክርስቲያን ለክብረ በአላት ማውጫ ። በተጨማሪም-ዋዜማ ሥርዓተ ማኅሌት - መዝሙራት ስንክሳር - የየእለቱን ምስባክ ቅኔያት ጥያቄዎች እንዲሁም የወቅታዊ ነገር መወያያ በተጨማሪም @eotcww ብለው ይቀላቀሉን ለወዳጅ ዘመድዎ share#Share#Share# ያድርጉ።

显示更多
1 161
订阅者
无数据24 小时
无数据7 天
无数据30 天
帖子存档
ኖራቸዋለሁ" አለው። "በስምህ የታነጹትም አብያተ ቤተ ክርስቲያናት መላእክቶቼን እንዲጠብቋቸው አደርጋቸዋለሁ" ቡዙ ቃል ኪዳንም ሰጠው። በመለኮታዊ አፉ አፉን ሳመውና ከእርሱ ዘንድ ወደ ሰማያት በክብ ዐረገ። ❤ ከዚህም በኋላ እልዋሪቆን ወደ ምትባል ታላቅ አገር እስከሚደርስ በብዙ አገሮች ውስጥ ተመላለሰ በዚያም የብርሃን እናት እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ተገልጻለት አረጋጋችው ረዳችውም በመጋቢት ሃያ ዘጠኝ እንደጻፍነው የአገሩን ሰዎች እንዲያጠምቃቸውና እንዲያስተምራቸው አዘዘችው። ❤ ከዚህም በኋላ ወደ ሮሜ ከተማ ገብቶ በውስጧ ሰበከ በስብከቱም ብዙዎች ሰዎች አምነው የክርስትናን ጥምቀትን አጠመቃቸው። በመጻፍትነት የታወቁ ዐሥራ አራት መልክቶችን ጻፈ የመጀመሪያ መልክቱም ለሮሜ የተጻፈችው ናት። ❤ መልካም ሩጫውን ከፈጸመ በኋላ ንጉሥ ኔሮን ይዞ ጽኑ ሥቃይ አሰቃየው። ራሱንም በሠይፍ እንዲቆርጡት ለሠያፊ ሰጠው ከሠያፊውም ጋር አልፎ ሲሆድ ከንጉሥ ኔሮን ዘመዶች ወገን የሆች አንዲት ብቴና አገኘችው እርሷም ክብር ይግባውና በጌታችን ያመነች ነበረች ስለእርሱ አለቀሰች። እርሱ ግን "መጎናጸፍያሽ ስጭኝ እኔም ዛሬ እመልስልሻለሁ" አላት። እርሷም መጎናጸፍያዋን ሰጠችውና ራስ ወደሚቆርጡበት ቦታ ሔደ። ለሠያፊው ራሱ በዘነገበለለት ጊዜ በመጎናጸፍያዋ ፍቱን ሸፈነ ሠያፊው የቅዱስ ጳዌሎስ ራስ ሐምሌ 5 ቀን ቆርጦ በዚያች ብላቴና መጎናጸፍያ እንደተሸፈነ ጣለው። ❤ ሠያፊው ጳውሎስን እንደገደለው ለንጉሥ ሊነግረው በተመለሰ ጊዜ ያቺ ብላቴና አገኘችው "ያ ቅዱስ ጳውሎስ ወደ አለ" አለችው። ራስ በሚቆርጥበት ቦታ ወድቋል ራሱም በመጎናጸፍያሽ ተሸፍኗል" አላት። እርሷም እንዲህ ብላ መለሰችለት "ዋሽተሃል እነሆ ጴጥሮስና ጳውሎስ በእኔ ዘንድ አልፈው ሔዱ እነርሱም የመንግሥት ልስን ለብሰዋል በራሳቸውም ላይ በእንቊ የተጌጡ አይንን የሚበዘብዙ አክሊላትን አድርገዋል። መጎናጸፍያየም ሰጡኝ። እርሷም እነኋት ተመልከታት" ብላ ለዛያ ሠያፊ አሳየችው። ከእርሱ ጋር ለነበሩትም አሳየቻቸው። አይተውም አደነቁ ስለዚህም ክብር ይግባውና በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ አመኑ። ❤ ለዚህም ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ተአምራቶች ቁጥር የሌላቸው እጅግ የበዙ ናቸው። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛን በቅዱስ ጳውሎስ በጸሎት ይማረን በረከቱም ከርእሰ ሊቃ ጳጳሳት ከአባ መርቆሬዎና ከአባ ማትያስ ከሁሉ ሊቃነ ጳጳሳት እና የቅድስት የሐዋርያት ቤተ ክርስቲያ ልጆች ጋር ይኑር ለዘለላሙ አሜን። ምንጭ፦ የሐምሌ 5 ሰንክሳር። + + + ❤ "ሰላም ለራጉኤል ወለሳቁኤል፤ ለአፍኒን ወለራሙኤል እለ የዐውዱ መንበሮ ለልዑል"። ትርጉም፦ የልዑል ዙፋኑን ለሚዞሩ ለራጉኤልና ለሳቁኤል፤ ለአፍኒንና ለራሙኤል ሰላምታ ይገባል፡፡ + + + ❤ "ስማቸውም እስጢፋኖስ፣ ጳውሎስ፣ ጢሞቴዎስ፣ ሲላስ፣ በርናባስ፣ ቲቶ፣ ፊልሞና፣ ቀሌምንጦስ፣ ዘኬዎስ፣ ቆርነሌዎስ፣ ቴዎፍሎስ፣ ኤውዴዎስ፣ አግናቴዎስ፣ አንያኖስ፣ ማልዮስ፣ ኤሌኖስ፣ አርስጢስ፣ አስተራትዮስ፣ አርስጦስ፣ ጋይዮስ፣ አድማጥስ፣ ሉኪዮስ፣ ደዮናስዮስ፣ መርአንዮስ፣ አርክቦንስ፣ አንሴሞስ፣ ከርስጊስ፣ አኪላስ፣ ንክቲስ፣ ቅርስጳስ፣ ክርስትፎሮስ፣ ፊልጶስ፣ ጰርኮሮን፣ ኒቃሮና፣ ጢሞና፣ ጰርሜና፣ ኒቃላዎስ፣ ማርቆስ፣ ሉቃስ፣ ዮሴፍ፣ ኒቆዲሞስ፣ የጌታ ወንድም ያዕቆብ፣ ብርኮሮስ፣ ሮፎስ፣ እለእስክንድሮስ፣ ስልዋኖስ፣ ስስቴኖስ፣ ኢዮስጦስ፣ አክይቁ፣ አፍሮዲጡ፣ አንሞስ፣ ገማልኤል፣ እንድራኒቆስ፣ አናንያ፣ ጵርስቅላ፣ አቂላ፣ ኤጴንጦስ፣ አንድኒቆስ፣ ዩልያል፣ ጰልያጦስ፣ መርመራዖስ፣ ኬፋ፣ ኡርባኖስ፣ ሰጠክን፣ ኤጤሌን፣ አክምንጦስ፣ ሄሮድያኖስ፣ ጥርፌና ጠሪፎስ፣ አስሪጦስ፣ ሉቅዮስና ሶሲጴጥሮስ በመባል ለሚጠሩ ንጉሥ በፊቱ በአህጉሩ ኹሉ ለላካቸው ለሰባ ሁለቱ አርድእት ሰላምታ ይገባል"። ሊቁ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ በተአምኆ ቅዱሳን ላይ። + + + ❤ "ሰላም ለከ ጴጥሮስ ተልሚድ። ዘኢያቅበጽከ ተስፋ ነገረ ኑፋቄ ወካህድ፡፡ እንዘ ትረውጽ ጥቡዕ ለመልእክተ ክርስቶስ ወልደ። አመ ለሊከ ወሬዛ ቀነትከ በእድ። ወአመ ልህቀ አቅነተከ ባዕድ"። ሊቁ አርከ ሥሉስ (አርኬ) የሐምሌ3። + + + ❤ የዕለቱ የማኅሌት ምስባክ፦ "ውስተ ኵሉ ምድር ወፅአ ነገሮሙ። ወእስከ አጽናፈ ዓለም በጽሐ ነቢቦሙ። ወውስተ ፀሓይ ሤመ ጽላሎቶ"። መዝ 18፥4-5። የሚነበበው ወንጌል ዮሐ 15፥1-17። + + + ❤ የዕለቱ ምስባክ፦ "ወበኀቤየሰ ፈድፋደ ክቡራን አዕርክቲከ እግዚኦ። ወፈድፋደ ፀንዑ እምቀደምቶሙ። እኌልቆሙ እምኆፃ ይበዝኁ"። መዝ138፥17-18። የሚነበበው ወንጌል ዮሐ21፥15-20። የሚቀደሰው ቅዳሴ የሐዋርያት ቅዳሴ ነው። መልካም የቅዱሳን የጴጥሮሰና የጳውሎስ የዕረፍት በዓል ለሁላችንም፡ይሁንልን https://t.me/Eotcw

ት ላይ ብትረግጥ አንተን ይጎዳሃል" አለው። እየተንቀጠቀጠም አደነቀ "አቤቱ ምን እንዳደርግ ትሻለህ" አለው ጌታም "ተነሥና ወደ ከተማ ግባ ልታደርግ የሚገባህን ከዚያ ይነግሩሃል" አለው። ከርሱ ጋራ ቁመው የነበሩ ሰዎችም ንግግሩን ይሰሙ ነበር ነገር ግን የሚያዩት አልነበረም። ❤ ሳውልም ከምድር ተነሣ ዐይኖቹንም ተገልጠው ሳሉ አያይም ነበር እየመሩም ወደ ደማስቆ አስገቡት በዚያም ሳያይ ሳይበላና ሳይጠጣ ሦስት ቀን ሰነበተ። በዚያም በደማስቆ ከደቀ መዛሙርት ወገን ሐናንያ የሚባል አንድ ሰው ነበረ ጌታም በራዕይ ተገለጠለትና ሐናንያ ብሎ ጠራው እርሱም "አቤቱ ጌታዬ እነሆኝ" አለ። ጌታም "ተነሥና ቀጥተኛ ወደምትባለው መንገድ ሒድ በይሁዳ ቤትም ጠርሴስ ከሚባል አገር የመጣ ሳውል የሚባል ሰው ፈልግ እርሱ አሁን ይጸልያልና" አለው። ❤ ሐናንያ ግን መልሶ እንዲህ አለ "አቤቱ ስለዚያ ሰው በኢየሩሳሌም በቅዱሳኖችህ ላይ የሚደርገውን ክፉ ነገር ሁሉ ከብዙ ሰዎች ሰምቻለሁ ወደዚህም ከካህናቱ አለቃ አስፈቅዶ የመጣ ስምህን የሚጠሩትን ሁሉ ሊአሥር ነው"። ጌታችንም "ተነሥና ሒድ በአሕዛብና በነገሥታት በእስራኤልም ልጆች ፊት ስሜን ይሸከም ዘንድ ለእኔ የተመረጠ ዕቃ አድርጌዋለሁና። እኔም ስለ ስሜ መከራ ይቀበል ዘንድ እንዳለው አሳየዋለሁ"። ❤ ያን ጊዜም ሐናንያ ሔደ ወደ ቤትም ገባ "ወንድሜ ሳውል በመንገድ ስትመጣ የታየህ ጌታችን ኢየሱስ ታይ ዘንድ የመንፈስ ቅዱስም ጸጋ ይሞላብህ ዘንድ ወደ አንተ ልኮኛል" አለው። ያን ጊዜም የሸረሪት ድር የመሰለ ከዐይኖቹም ተገለጡ። ወዲያውም አየ ተነሥቶም ተጠመቀ እህልም በልቶ በረታ። ከደቀ መዛሙርትም ጋር በደማስቆ ጥቂት ቀን ሰነበተ። በዚያው ጊዜ የእግዚአብሔር ልጅ ነው ብሎ ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ ሰበከ አስተማረም። የሰሙትም ሁሉ አደነቁ እንዲህም አሉ "በኢየሩሳሌም ይህም ስም የሚጠሩትን ሁሉ ያሳድድ የነበረ ይህ አልነበረምን ወደዚህስ የመጣው እያሠረ ወደ ሊቀ ካህናቱ ሊወስዳቸው አይደለምን"። ❤ አጽናኝ መንፈስ ቅዱስም አደረበት እውነተኛንም ሃይማኖት ግልጽ አድርጎ አስተማረ። ለኦሪት ሕግ የሚቀና እንደ ነበረ እንዲሁ ክብር ይግባውና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለሠራት ሕግ ወንጌል ዕጽፍ ድርብ ቅንዓትን የሚቀና ሆነ። ከዚህም በኋላ በአገሮች ሁሉ ዞሮ ሰበከ በጌታችንም ስም ሰበከ። ድንቆችንና ተአምራትንም አደረገ። ቁጥር የሌላቸው ብዙዎች አሕዛብንም አሳመናቸው ነገር ግን ብዙ ጊዜ በመገረፍ በመደብደብና በመታሠር ብዙ መከራ ደረሰበት መከራውንም ሁሉ ታግሶ በሁሉ ቦታ አስተማረ። ❤ በሐዋርያት ሥራ መጽሐፍ እንደተጻፈ የእግዚአብሔርን ሥራ ሲሠሩ ሲጾሙና ሲጸልዩ መንፈስ ቅዱስ "እኔ እነርሱን ለመረጥሁለት ሥራ ሳውልና በርናባስ ለዩልኝ" አላቸው። ከዚህም በኋላ ጾመውና ጸልየው እጃቸውንም በራሳቸው ላይ ጭነው ሾሙአቸው ከመንፈስ ቅዱስም ተሹመው ወደ ሴሌውቅያ ወረዱ። ❤ በደሴቱም ሁሉ ሲዘዋወሩ ጳፋ ወደ ምትባል አገር ደረሱ። በዚያም ሐሰተኛ ነቢይ የሆነ ስሙ በርያሱስ የሚባል አንድ ሥራየኛ አይሁዳዊ ሰው አገኙ እርሱም ሰርግዮስ ጳውሎስ ከሚባል ብልህ ሰው ከሆነ አገረ ገዥ ዘንድ የነበረ ነው። የእግዚአብሔርን ቃል ሊሰማ ወዶ በርናባስንና ሳውልን ጠራቸው። የስሙ ትርጓሜ እንዲህ ነበርና ኤልማስ የሚሉት ያ ሥራየኛ ሰው ይከራከራቸው ነበር ገዥውንም ማመንን ሊከለክለው ወዶ ነበር። ❤ ጳውሎስ በተባለው ሳውል ላይም መንፈስ ቅዱስ መላበት። አተኵሮም ተመለከተው "ኃጢአትንና ክፋትን ሁሉ የተመላህ የሰይጣን ልጅ የጽድቅ ሁሉ ጠላት ሆይ የቀናውን የእግዚአብሔርን መንገድ እያመጣመምኽ ተው ብትባል እምቢ አልኽ እነሆ አሁን የእግዚአብሔር እጅ በአንተ ላይ ተቃጥታለች ትታወራለህ እስከ እድሜ ልክህም ፀሐይን አታይም" አለው። ወዲያውኑም ታወረ ጨለማም ዋጠው የሚመራውንም ፈለገ አገረ ገዥውም የሆነውን አይቶ ደነገጠ በጌታችንም አመነ። ❤ ከዚህ በኋላ ሒደው ወደ ሊቆኦንያ ከዚያም ወደ ልስጥራንና ደርቤን ከተማ ወደ አውራጃውም ሁሉ ገብተው አስተማሩ። በልስጥራን ከተማም ከእናቱ ማኅፀን ጀምሮ እግሩ ልምሾ የሆነ አንድ ሰው ነበረ ተቀምጦ ይኖር ነበረ እንጂ ልምሾ ከሆነ ጀምሮ ቁሞ አልሔደም። ቅዱስ ጳውሎስንም ሲያስተምር አደመጠው ጳውሎስ ተመልክቶ ሃይማኖት እንዳለው እንደሚድንም ተረዳ። ድምፁንም ከፍ አድርጎ "በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ተነሥና ቀጥ ብለህ ቁም እልሀለሁ" አለው ወዲያውኑ ተነሥቶ ሔደ። አሕዛብም ቅዱስ ጳውሎስ ያደረውን አይተው በጌታች አመኑ...። ❤ ከዚህም በኋላ ከሐዋርያ ፊሊጶስ ጋር ወደ ሁለት አገሮች በአንድነት ሔዱ ከዚያም በጌታችን ስም ሰበኩ የአገሩም አለቆች ያዟቸው እጆቻቸውንና እግሮቻቸው አሰሯቸው በአንገቶቻቸውም የብረት ሰንሰለቶችን አስገቡ እራሳቸውንም የሸፋን የብር ቆብን ሰሉላቸው ዳግመኛም በእጅና በሐል እጅ በጣቶችም ምሳሌ ሰሩ በእጆቻቸውና በክንዶቻቸው እያንዳንዱን የብረት እጅ ጨመሩ። ከብረቶችም ጋር ቸነከሯቸው። ❤ ሁለተኛም እስከ አንገት የሚደርስ በትከሻ አምሳል ሰሩ በፊትና በኋላም ቸነከሯቸው ደግሞም መላ አካላቸውን የሚከብና ከአካላቸው ምንም እንዳይታይ የሚሸፍን የብረት ሰሌዳ ሰሩ ከወገቦቻቸው ጋራ ቸነከሯቸው ችንካሮችም ተረከዛቸውን ነድለው ወደ ጭኖቻቸው እስከሚደርሱና እስከሚያቆስሏቸው ድረስ የብረት ጫማ ሰርተው እግሮቻቸውን ቸነከሩ። ደግሞ በመሸፈኛ አምሳል የብረት ሰናፊል ሠሩ ቀማሚዎችም መጡ አንድ መክሊት የሚመዝን እርሳስንም አመጡ ታላቅ የብረት ጋንንም ሰባት ልጥር የሰሊጥ ቅባት አመጡ። ስቡንና አደሮ ማሩን የእሳቱን ኃይል አብዝቶ የሚያነደውን ቅመሙን ከሙጫውና ከድኙ ጋር ቀላቀሉት ከዋርካና ከቁልቋል ከቅንጭብም ደም ሰባት ልጥር አንድ ወይን ሐረግንና ቅባት ያለቸውን እንጨቶች ሁሉ አመጡ። ❤ በጋን ውስጥ ያበሰሉትንና ያሟሙትን ልዩ ልዩ ቅመምን አምጥተው ከሥጋቸው እስሚጣበቅ በቅዱሳን ሐዋርያት ሥጋ ላይ ባሉት ሠሌዳዎች ውስጥ ጨመሩት። ከእግራቸው እስከ ራሳቸው ከፍ ከፍ እስከሚል ድረስ በእሳት ያቀለጡትን ያንን እርሳስ ጨመሩት። ርዝመቱ ዐሥራ አምስት ክንድ በሆነ ወፍራም የጥድ ምሰሶ ላይም አቆማቸውና ከበታቻቸው ፍሬ በሌለው በወይን ሐረግና በተልባ እሳቱን አቀጣጥለው አነደዱ። የእሳቱም ነበልባልም ከሥጋቸው በላይ ከፍ ከፍ አለ ሐዋርያትን ግን ወደ እግዚአብሔር ይጸልዩ ነበር። ❤ ከመኳንቱም በአንዱ ልብ ርኅራኄ አሳደረና እንዲፈቷቸው አዝዞ ፈቷቸው። በፈቷቸውና ሠሌዳው ከሥጋቸው ላይ ባስወገዱ ጊዜ ቆዳቸው ተገፈፈና ከብረቱ ሠሌዳዎች ጋር ወጣ። ብዙ ደምም ከሥጋቸው ፈሰሰ። ❤ ሰይጣንም በከተማው ሰዎች ልብ አደረና ሐዋርያትን ወደ እሳት ውስጥ መለሷቸው ያን ጊዜ ጌታች ወርዶ የእሳቱ ነበልባል አጠፋው። ዝናብን የተሞላች ብርሕት ደመና መጥታ ቅዱሳን ሐዋርያት ከበበቻቸው በዚያም አገር አንድ ጊዜ በደንጊያ በመወገር አንድ ጊዜም በፍላጻ በመንደፍ ብዙ ተሰቃዩ። ❤ ከዚህም በኋላ ሙታንን በአነሱ ጊዜ የከተማው ሰዎች ሁሉ አመኑ አጠመቋቸው። ቤተ ክርስቲያንንም ሠሩላቸው ካህናትንም ሾሙላቸው በቀናች ሃይማኖት እስኪጸኑ አስተማሯቸው። ከዚያም ወጥተው ጌታችን ወደ አዘዛቸው ወደ ሌላ አገር ሔዱ። ❤ ክብር ይግባውና ጌታች ኢየሱስ ክርስቶስ ለቅዱስ ጳውሎስ ተገለጠለትና "የመረጥኩህ ጳውሎስ ሆይ ስላም ላንተ ይሁን። መታሰቢያህን የሚደርገውን፣ በስምህ ቤተ ክርስቲያን የሚሰራውንና የሚጸልየውን፣ ስለትንና መባንም የሚሰጠውን፣ በመታሰቢያህም ቀን ለድኆች የሚመጸውተውን ሁሉ ከአንተ ጋር በመንግሥተ ሰማያት አ

የሚመለሱ አሕዛብን ስለመቀበል እንደሆነ አስተዋለ። ለወንድሞቹ ሐዋርያትም አሕዛብ የእግዚአብሔር ቃል እንደተቀበሉ የመቶ አለቃ ቆርኔሎስንም ከወገኖቹ ጋር እንዳጠመቀው ነገራቸው። ❤ ከዚህም በኋላ ቅዱስ ጴጥሮስ ከቅዱ ዮሐንስ ጋር ጌታችን እንደአዘዛቸው ወደ አንጾኪያ ከተማ ገቡ የአገሪቱንም ሁኔታ ይጠይቅ ዘንድ ቅዱስ ጴጥሮስ ቅዱስ ዮሐንስን ላከው ሰዎችንም አግኝቶ ክፉ ነገርን ተናገሩት። ሊገድሉትም ፈለጉ እያለቀሰም ተመለሰ ሰውነቱም ተበሳጨች ጴጥሮስንም አለው "አባቴ ሆይ የእሊህ ጎስቋሎች ክፍታቸው እንዲህ ከሆነ ወደ ነገሥታቱና ወደ መኳንንቱ ገብተን በጌታችን ስም በሰበክን ጊዜ ምን እንሆ ይሆን እንዴትስ ሃይማኖትን እናስተምራለን"። ቅዱስ ጴጥሮስም "ወዳጄ ሆይ የሃያውን ቀን መንገድ በአንዲት ሌሊት ያመጣን እርሱ ሥራችንን መልካም ያደርግልናል አትፍራ አትዘን" አለው። ❤ ከዚህም በኋላ ወደ ከተማ መካከል ክብር ይግባውና በጌታችን ስም ሰበኩ የከተማውም ሰዎችና የጣዖታቱ አገልጋዮችም በእነርሱ ላይ ተሰበሰቡ ታላቅ ድብደባንም ደበደቧቸው አጎሳቋሏቸውም ግማሽ የእራስ ጠጉራቸውን ላጭተው ተዘባበቱባቸው አሥረውም በግንብ ውስጥ ጣሏቸው። ❤ ከዚህም በኋላ ተነሥተው ይረዳቸው ዘንድ ወደ እግዚአብሔር ጸለዩ ወደያውን ክብር ይግባውና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ኪሩቤልና ሱራፊል እያጀቡት ተገለጠላቸውና እንዲህ አላቸው "የመረጥኳችሁ ጴጥሮስና ዮሐንስ ሆይ በዘመኑ ሁሉ እኔ ከእናንተ ጋር እኖራለሁና አትፍሩ አትዘኑም"። ለመዘባባቻም በራሷችሁ መኳካከል ስለላጩአችሁ አታድንቁ ይህም መመኪያና ክብርን የክህነት ሥርአትና ምልክትንም ይሆናችኋል ካህን የሚሆን ሁሉ ያለዝህ ምክንያት ሥጋዬንና ደሜን ማቀበል አልችልም። ይህ መልእክት እያለው የሚሞት ካህምን ኃጢያቱም ይሰረይለታል" ይህን ካላቸው በኋላ ከእርሳቸው ዘንድ በክብር ዐረገ። ❤ ከዚህም በኋላ ቅዱስ ጳውሎስ ወጥቶ ቅዱስ ዮሐንስን ተገናኘው "የዚህ አገር ሰዎች ያደረጉብህ ምንድን ነው" አለው እርሱም "ስለ እኔ አታድንቅ የሐዋርያትን አለቃ በእኔ ላይ ባደረጉት አምሳል አድርገውበታልና" አለው። ቅዱስ ጳውሎስ አጽናናቸው እንዲህ አላቸው "እኔ በጌታችን ፍቃድ ወደ ከተማው ውስጥ ገብቼ እናንተንም አስገባቸዋለሁ"። ❤ ከዚህም በኋላ ቅዱስ ጳውሎስ ሒዶ ምክንያትን ፈጠረ ጣዖታቸውንም እንደሚያመልክ መስሎ ሐዋርያትን እንዲያቀርቡለትና ስለ ሥራቸውም እንዲይቃቸው የከተማውን መኳንን አነጋገራቸው። መኳንንቱም ወደ ቅዱስ ጳውሎስ እንዲያቀርቧቸው አዘዙ በቀረቡም ጊዜ ቅዱስ ጳውሎስ ስለሥራቸው ጠየቃቸው። እነርሱም "ድንቆችንና ተአምራቶችን የሚያደርግ ለክርስቶስ ወደ መዛሙርቶቹ እንደሆኑ ነገሩት። ዳግመኛም "እናንተ እንደርሱ ማድረግ ትችላላችሁ" አለቸው እነርሱም "አዋ በእርሱ ስም ሁሉን ሥራ መሥራት እንችላለን" አሉት። ❤ ከዚህም በኋላ ከእናቱ ማኅፀን እውር ሁኖ የተወለደውን አይኑን አበሩ። የንጉሡንም ልጅ ከሞተ በሦስት ወሩ ሥጋውን ከተባላሸ በኋላ ከመቃብር አሥነሱት። ንጉሡና የከተማ ሠዎች ሁሉ ክብር ይግባውና በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ አመኑ ጴጥሮስም ምድሩን ረግጦ ውሃን አፈለቀ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም አጠመቋቸው በቀናች ሃይማኖትም እንዲጸኑ አደረጓቸው። ❤ ከዚህም በኋላ በሎዶቅያ ያሉ ምእመናን የቂሳሮስ ባሕር ከወሰኑ አልፎ ቡዙ ሰዎችን ከአትክልት ቦታዎቻቸውና ከከቡቶቻቸው እንዳሰጠማቸው ወደ ቅዱስ ጴጥሮስ ላኩ ጴጥሮስም ተወዳጅ ቅዱስ ዮሐንስን ወደ እነርሱ ላከ ዮሐንስም ወደ እነርሱም ሲጓዝ በጎዳና በግ አገኘ በጉንም እንዲህ ብሎ ላከው "ወደ ቂሳሮስም ወንዝ ሒደ የክርስቶስ ደቀ መዝሙር ወደ አንተ ልኮኛል ወደ ቀድሞው ወሰንህ ተመልሰህ ትገባ ዘንድ አንተ በእግዚአብሔር ቃል የታሰርክ ነህ ብሎሀል በለው"። ያን ጊዜ በጉ ሒዶ እንደአዘዘው አደረገ ወንዙም ሸሽቶ ወደ ቦታው ተመለሰ ቁጥር የሌላቸው ቡዙዎች የከተማ ሰዎችም ይህን አይተው በጌታ አመኑ። ❤ ከዚህም በኋላ ቅዱስ ጴጥሮስ አልፎ ወደ ሮሜ ከተማ ገባ በዚያም ሥራ መሠሪው ሲሞን ተቃወመው እርሱንም ከአየር አውርዶ ጥሎ አጠፍው ይህንንም ድንቅ ሥራ አይተው ብዙዎች ሕዝቦች አመኑ። የከተማው ገዢ የአክሮጶስ ቊባቶችም የቅዱስ ጴጥሮስን ትምህርት ተቀበሉ ሌሎችም የከበሩ ቡዙዎች ሴቶች ትምህርቱን በመቀበል ከባሎቻቸው እርቀው ንጽሕናቸውን ጠበቁ። ስለዚህም ነገር ቅዱስ ጴጥሮስ ሊገድሉት የሮሜ መኳንንት ተማከሩ። የአልታብዮስ ሚስትም እንዳይገሉት ከሮሜ ከተማ ወጥቶ እንዲሆድ ወደ ቅዱ ጴጥሮስ ላከች ምእመናን ወንድሞችም ውጣ አሉት እርሱም ቃላቸውን ተቀበለ ትጥቁንም ለውጦ ከከተማ ወጣ። በሚወጣበትም ጊዜ መስቀል ተሸክሞ ወደ ከተማ ሲገባ ጌታችንን አገኘውና "አቤቱ ጌታዬ ወዲት ትሆዳለህ" አለው ጌታዬም "ልሰቀል ወደ ሮሜ ከተማ እህሔዳለሁ" ብሎ መለሰለት። ቅዱስ ጴጥሮስ "አቤቱ ዳግመኛ ትሰቀላለህን?" አለው። ❤ ያን ጊዜም "ጎልማሳ ሳለህ ወገብህ በገዛ እጅህ ታጥቀህ ወደ ወደድከው ትሔዳለህ በሸመገልክ ጊዜ ግን እጅህን ታነሳና ሌላ ያስታጥቅሃል ወደ ማትወደው ይወስድሃል" ያለውን የጌታችንን ቃል አሰበ አስተዋለውም። ያን ጊዜም ወደ ከተማው ተመልሶ ክብር ይግባውና ከጌታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ የሆነውን ለወንድሞች ነገራቸው እነርሱም እጅ አዘኑ። ❤ ንጉሥ ኔሮንም ቅዱስ ጴጥሮስን እንዲሰቅሉት አዘዘ ሊሰቅሉት በያዙት ጊዜ ወታደሮችን እንዲህ ብሎ ለመናቸው "የክብር ንጉሥ ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ ላይ ሁኖ ስለተሰቀለ እኔ ቊልቊል ልሰቀል ይገባኛል"። ወዲያውንም እንደነገራቸውም ሰቀሉት። ተሰቅሎም ሳለ ለምእመናን የሕይወትን ቃል አስተማራቸው በቀናች ሃይማኖትም እንዲጸኑ አዘዛቸው ከዚህም በኋላ ሐምሌ 5 ቀን ነፍሱን በእግዚአብሔር እጅ ሰጠ። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በአባታች በሐዋርያው ቅዱስ ጴጥሮስ ጸሎት ይማረ በረከቱም ከእኛ ጋራ ይኑር ለዘለላለሙ አሜን። + + + ❤ "ሰላም ለጳውሎስ ልሳነ ዕፍረት ሐዋርያሆሙ ለአሕዛብ ፈልፈለ ጥበብ"። ትርጉም፦የጥበብ ምንጭ (ፈሳሽ) የአሕዛብ ሐዋርያቸው ለአንደበተ ሽቱው ለጳውሎስ ሰላምታ ይገባል። ሊቁ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ በተአምኆ ቅዱሳን ላይ። + + + ❤ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ፦ ይህም ቅዱስ በተለያዩ ስሞች ይጠራ ይኸውም ልሳነ ዕረፍት፣ የክርስቶስ አንደበት፤ የዕውቀት አዘቅት፤ የቤተ ክርስቲያን መብራት፤ እንደ ስሙም ትርጓሜ መሪ አመስጋኝ ወደብ ጸጥታ ነው። ❤ ይህም ጳውሎስ አስቀድሞ በክርስቶስ ያመኑትን የሚያሳድድ ነበር፤ እርሱም ከብንያም ወገን የፈሳሪሳዊ ልጅ ነው። ወላጆቹም ሳውል ብለው ስም አወጡለት ትርጓሜውም ስጦታ ማለት ነው። ቁመቱ ቀጥ ያለ መልኩ ያማረ ፊቱ ብሩህ ቅላቱ እንደ ሮማን ቅርፍት ደበብ ያለ ዐይኑም የተኳለ የሚመስል አፍንጫው ቀጥ ያለ ሸንጎበታም ጉንጩ እንደ ጽጌ ረዳ ነበር። ❤ እርሱም ሕገ ኦሪትን አዋቂ ነበረ። ለሕጉም ቀናተኛ ሆኖ ምእመናን አሳዳጅ ነበረ። ወደ ሊቀ ካህናቱም ሔዶ መንገድ የሚያገኘው ሰው ቢኖር ወንዶችንና ሴቶችን እንደ ታሠሩ ወደ ኢየሩሳሌም ይመልሳቸው ዘንድ ለደማስቆ ከተማና ለምኵራቦች የፈቃድ ደብዳቤ ለመነ። ሲሔድም ወደ ደማስቆ ከተማ አቅራቢያ በደረሰ ጊዜ ድንገት ከሰማ መብረቅ ብልጭ አለበት በምድር ላይም ወደቀ ወዲያውም "ሳውል ሳውል ለምን" ታሳድደኛለህ የሚለውን ቃል ሰማ። ❤ ሳውልም "አቤቱ አንተ ማነህ" አለው "አንተ የምሳድደኝ የናዝሬቱ ኢየሱስ ነኝ በሾለው ብረ

❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን" ❤ ❤ ሐምሌ ፭ (5) ቀን። ❤ እንኳን ለብርሃናተ ዓለም ለቅዱሳን ጴጥሮስ ወጳውሎስ በጫካኙ ንጉሥ በኔሮን ቄሳር እጅ ሰማትነት ለተቀበሉበት ለዕረፍታቸው መታሰቢያ ዓመታዊ በዓል፣ ለመላእክት አለቃ ለቅዱስ ሳቁኤል ለበዓሉ መታሰቢያ፣ ለሰባ ሁለቱ አርድእት ለመታሰቢያቸው በዓላቸው፣ ለአባታችን ለአቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ዓመታዊ የመታሰቢያ በዓላቸውና ለሐዋርያት (ለሰኔ) ፆም ፍቺ በሰላም አደረሰን። በተጨማሪ፡በዚች ከሚታሰቡ፦ በጋዛ ሰማዕት ከሆነ ከይስሐቅና ከደብረ ዓሣ ጻድቃንም ከመታሰቢያቸው ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን። + + + ❤ የዕለቱ አንገርጋሪ ግእዝ ዜማ፦ "ይቤሎ ጴጥሮስ ለጳውሎስ ጥባዕኬ እኁየ ጳውሎስ ኢትናፍቅ እምዝ ዳግመ ኢንመውት ዳግመ ወእምዝ ዳግመ ኢንመውት"። ትርጉም፦ ቅዱስ ጴጥሮስ ቅዱስ ጳውሎስን ወንድሜ ጳውሎስ ጨክን፤ አትጠራጠር ከዚኽ በኋላ ዳግመኛ አንሞትም አለው። ሊቁ ቅዱስ ያሬድ። + + + ❤ የሐዋርያት አለቃ ቅዱስ ጴጥሮስ፦ ይህም ጴጥሮስ ከቤተ ሳይዳ የነበረ ዓሣ አጥማጅም ነበረ ጌታችንም ከተጠመቀባት ዕለት ማግስት አግኝቶ መረጠው ከእርሱ አስቀድሞም ወንድሙ እንድርያስን አግኝቶ መረጠው። መድኀኒታችንንም እስከ መከራው ጊዜ ሲያገለግለው ኖሩ ፍጹም ሃይማኖት ለጌታውም ቅንዓትና ፍቅር ነበረው። ስለዚህም በሐዋርያት ሁሉ ላይ አለቃ አድርጎ ሾመው። ❤ ጌታችን ም ሰዎች ማን እንደሆነ ማንም እንደሚሉት ስለ ራሱ በጠየቃቸው ጊዜ ሌሎች "ኤርምያስ ይሉሃል ወይም ኤልያስ ወይም ከነቢያት አንዱ ነው ይሉሃል" አሉት። ቅዱስ ጴጥሮስ ግን "የሕያው እግዚአብሔር ልጅ ክርስቶስ አንተ ነህ" አለ። ጌታችንም "የሃይማኖት አለት የቤተ ክርስቲያንም መሠረት ነህ" ብሎ ብፅዕና ሰጠው "የመንግሥተ ሰማያትንም መክፈቻ ቁልፍ ሰጥቼሃለሁ" አለው። ❤ አጽናኝ የሆነ የመንፈስ ቅዱስንም ጸጋ ከተበቀለ በኋላ ተናገሪዎች ከሆኑ በዚህ ዓለም ተኲላዎች መካከል ገባ በውስጣቸውም ክብር ይግባውና በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ሰበከ ቊጥር የሌላቸው ብዙዎች አሕዛብንም መልሶ የዋሆች ምእመናን አደረጋቸው። ጌታችንም የማይቈጠሩ ታላላቅ ድንቆችና ተአምራቶችን በእጆቹ አደረገ ጥቅም ያላቸው ሦስት መልእክቶችንም ጽፎ ለምእመናን ላከቸው። ለማርቆስም ወንጌሉን ተርጒሞ አጽፎታል። ❤ ከዚህም በኋላ ወደ ሮሜ ከተማ ገባ የከተማው መኳንንት ወደሚሰበሰቡበት ወደታላቁ የጨዋታ ቦታም ሔዶ በታላቅ ድምፅ እንዲህ ብሎ ተናገረ "የሚራሩ ብፁዓን ናቸው ለርሳቸውም ይራሩላቸዋልና" የዚህንም ተከታታይ ቃሎች ተናገረ። በዚያም ከዚያ የነበሩ አራት የደንጊያ ምሰሶዎችም በሚያስፈራ ድምፅ "አሜን" አሉ የተሰበሰቡትም ይህን ቃል በሰሙ ጊዜ ደነገጡ። ከሰባ ዓመት ጀምሮ ሰይጣን ያደረበት አንድ ሰው ነበረ ከእነዚያ ድንጋዮች ቃልን ስለ ሰማ ያን ጊዜ ጋኔኑ ጣለው ከእርሱም ወጥቶ ሔደ። መኳንንቱም ፈርተዋልና ስለዚህ ነገር እያደነቁ ወደ ቤታቸው ገቡ። ❤ ከከተማ መኳንንቶችም ቀውስጦስ የሚባል አንዱ ወደ ቤቱ በገባ ጊዜ ስሟ አክሮስያ የምትባል ሚስቱ ዓለምን ስለ መተው ለድኆችም ስመራራትና የመሳሰለውን ቃል ቅዱስ ጴጥሮስ እንዴት እንዳስተማረ ነገራት። እርሷም በሰማች ጊዜ በልቧ ነቃታ "ይህ ገገር መልካምና ድንቅ ነው" አለች። ቅዱስ ጴጥሮስ ያስተማረውንም ሁሉ ያደርጉ ዘንድ በአንድነት ተስማሙ ሁሉ ያደርጉ ዘንድ በአንድነት ተስማሙ ከዚህም በኋላ ገንዘባቸውን ሁሉ ለድኆች ሰጡ ከዕለት ራት በቀር ምንም አላስቀሩም። ❤ ከጥቂት ቀኖችም በኋላ ንጉሡ ስለ መንግሥት ሥራ ከርሱ ጋራ ለመማከር በቶሎ እንዲደርስ ወደርሱ መልክትን ላከ። ቀውስጦስም ይህ በሰማ ጊዜ ገንዘብ ስላልነበረው ፈርቶ ደነገጠ ተጨነቀም። ምክንያትም አመካኝቶ ይሰወር ዘንድ ከሚስቱ ጋራ ተማከረ። እርሷ ግን "ምክንያት አታድር ነገር ግን ወደ ንጉሥ ሒድ የቅዱስ ጴጥሮስ አምላክን ጎዳናህን ያቅናልህ" አለች። እርሱም ነገሯን ተቀብሎ ወደ ንጉሡ ሔደ በመንገድም ከእግዚአብሔር የታዘዘ ብዙ በረከትን አገኘ ወደ ንጉሡም ደረሰ ንጉም በደስታና በክብር ተቀበለው። ❤ ከሦስት ዓመት በኋላም ወደ ቤቱ በተመለሰ ጊዜ ሁለቱ ልጆቹ የተመረዘ ውሃ ጠጥተው እነሆ ሞተው ነበር ሚስቱም ለእርሱ መንገርን ፈራች ብዙ ምሳሌዎችን ከመሰለችለት በኋላ ነገረችው። በሰማ ጊዜ እጅግ አዝኖ አለቀሰ። ሚስቱም እንዲህ አለችው "ጌታዬ ሆይ ልባችን የሚጽናናበትን እርሱ ያደርግልናል የቅዱስ ጴጥሮስ ፈጣሪ እግዚአብሔርን እንለምነው"። ሊጸልዩም በጀመሩ ጊዜ ቀወስጦስና አክሮስያ "የደቀ መዝሙሬ የጴጥሮስ ቃል ስለሰማችሁና ስለተቀበላችሁት ስለዚህ ልጆቻችሁን በሕይወታቸው እሰጣቸዋለሁ" የሚል ቃልን ከሰማይ ሰሙ ያን ጊዜም ልጆቻቸው ድነው ተነሱ ቀውስጦስና ሚስቱም ደስ አላቸው የተመሰገነ እግዚአብሔርንም አመሰገኑት። ❤ እሊህም ከሞት የተነሱ ልጆች ለቅዱስ ጴጥሮስ ቀደ መዝሙሮቹ ሆኑ የአንዱ ስሙ ቀሌምንጦስ ነው እርሱም ቅዱስ ጴጥሮስ ያየውንና ጌታች በሥጋ ወደ ሰማይ በሚያርግ ጊዜ የገለጠለትን ምስጢር ሁሉ የነገረው ነው ሰዎች ሊያዪአቸው የማይገባቸውን መጻሕፍትን አስረከበው። ይህንም ቀሌምጦስን ሊቀ ከጵጵስና ወንድሙንም ዲቁና ሾማቸው። ❤ ከዚህም በኋላ ዳግመኛ ቅዱስ ጴጥሮስ አምላክን የወለደች የንጽሕት ድንግል እመቤታችን ማርያም ክብራን በምሳሌ አየ። በቀስት አምሳል ደመናን አይቷልና በላዪዋም የብርሃን ድንኳን ነበር በድንኳን ውስጥም አምላክን የወለደች ቅድስት ድንግል ማርያም ተቀምጣለች። በእጆቻቸው ውስጥ የነበልባል ጦሮችና ሰይፈችን ያያዙ መላክትና የመላእክት አለቆች በዙሪያዋ ነበር። እንዲህም እያሉ ያመሰግኗት ነበር። "ከእርሷ የደኅንነት ፍሬ የተገኘ የሰመረች የወይን ተክል አንቺ ነሽ ማኅፀንስሽም የእግዚአብሔር በግ የተሸከመ ንጽሕት አዳራሽ አንቺ ነሽ"። ❤ ሁለተኛም እንዲህ ይሏት ነበር " የብርሃን እናቱ ሆይ የምሕረት መገኛ ሆይ ደስ ይበልሽ የአማልክት አምላክ የፍጥረት ሁሉ ጌታ የሆነ የመድኅን ዙፋን ሆይ ደስ ይበልሽ ክብርና ምስጋናን የተመላሽ የፍጥረት ሁሉ እመቤት ደስ ይበልሽ"። መላእክት ምስጋናዋንና ሰላምታዋን ባደረሱ ጊዜ ክብር ይግባውና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለእርስዋ ተገልጦ ከእርሷ በቀር ማንም ሊያውቀው የማይቻል ነገርን ነገራት ወዲያውኑም ምድር ተናገወች ሊነገር የማይቻል ምሥጢራትንም ገለጠላት። ❤ ከዚህም በኋላ መድኀኒታችን ለአገሩ ሁሉ ቅዱስ ወንጌልን ይሰብክ ዘንድ ቅዱስ ጴሮስን አዘዘው ቅዱስ ጴጥሮስም መጥቶ ሔደ ኢዮጴም ወደምትባል የባሕር ዳርቻና ልድያ ወደምትባል አገር ደረሰ። በአንዲት ዕለትም በኢዮጴ ሳለ ብርሕት ደመና ዞረችው። እነሆም ሰፊ መጋረጃ ወደርሱ ወረደች በውስጧም የእንስሳት የምድረ በዳ አውሬዎችና የሰማይ አዕዋፍ አምሳል ነበር። "ጴጥሮስ ሆይ ተነሥና አርደህ ብላ" የሚል ቃልም ከሰማይ ጠራው። ቅዱስ ጴጥሮስም "አቤቱ አይገባኝም እርኲስ ነገር አልበላም ወደ አፌም ከቶ አልገባም" አለ። ያም ቃል ዳግመኛ ጠራውና እግዚአብሔር ንጹሕ ያደረገው አንተ ርኲስ ነው አትበል" አለው ያም ቃል ሦስት ጊዜ መላልሶ እንዲህ ነገረው። በየንግግሩም ወደ እሪያዎች፣ ወደ አራዊትና ወደ አእዎፍ ሥዕሎች ጣት ያመለክተው ነበር። ❤ ከዚህም በኋላ ያቺ መጋረጃ ወደ ሰማይ ተመለሰች። ቅዱስ ጴጥሮስም ስለ አየው ራእይ አደነቀ ይህም ራእይ ወደ ፈጣሪያቸው እግዚአብሔር

❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን" ❤ ❤ ሐምሌ ፬ (4) ቀን። ❤ እንኳን ለዐሥራ ሁለቱ ደቂቅ ነቢያት ለመታሰቢያ በዓላቸውና ከእነርሱ አንዱ ለሆነው ለሴዴቅያስ ልጅ ለጎዶልያ ልጅ ለኩሲ ልጅ ለነቢዩ ቅዱስ ሶፎንያስ ለዕረፍቱ መታሰቢያ በዓል በሰላም አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰቡ፦ ከቅዱሳን አቡቂርና ዮሐንስ ከሥጋቸው ፍልሰት ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን። + + + ❤ ነቢዩ ቅዱስ ሶፎንያስ፦ እርሱም በይሁዳ ንጉሥ በኢዮስያስ ዘመን ትንቢት ተናገረ። እንዲህም አለ "እግዚአብሔር ከዚህ ዓለም ፈጽመው ይጠፋሉ አለ ከብቶችም ሰዎችም ያልቃሉ። የባሕር አሳዎች በሰማይ የሚበሩ አእዋፍም ያልቃሉ"። ❤ ዳግመኛም ስለሞአብ እንዲህ አለ "ስለዚህ ሞአብ እንደ ሰዶም ትሆናለች የሞአብ ልጆች እንደ ገሞራ ልጆች ይሆናሉ ደማስቆም እንደ እህል ታልቃለች"። እርሱም እንደ ተነበየው እነዚያ አገሮች በናቡከደነፆር ምርኮ ይጠፋሉና። ❤ ዳግመኛም ስለ ፋርስ ስለ ነነዌ ትንቢት ተናገረ እንዲህም አለ "የፋርስን ሰዎች አጠፋቸዋለሁ ነነዌም ፍርስራሽና ውኃ እንደሌለባት ምድረ አደርጋታለሁ መንጋዎችም በመካከሏ ይሠማሩባታል"። ይቺ ከተማ በመቄዶናዊው እስክንድር እጅ ጠፍታለች። ❤ ዳግመኛ ስለ ክርስቶስ መምጣት እንዲህ ተናገረ "ያን ጊዜም ሁሉ የእግዚአብሔር ስም ይጠራ ዘንድ በአንድ ሕግም ይገዙልኛ ዘንድ የአሕዛብን ሁሉ አንደበት ወደ ሕግ እመልሳለሁ"። ደግሞም እንዲህ አለ "ከኢትዮጵያ ወንዞች ማዶ መሥዋቴን ያመጡልኛል"። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በነቢዩ ቅዱስ ሶፎንያስ በጸሎቱ ይማረን በረከቱ ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላዓለሙ አሜን። + + + ❤ ዳግመኛም በዚች ቀን ስለ ክርስቶስ ትንቢታቸውን እንደ ፈሳሽ ውኃ ያጎረፉ የዐሥራ ሁለቱ ደቂቀ ነቢያት መታሰቢያቸው ነው። በረከታቸው ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላዓለሙ አሜን። + + + ❤ የቅዱሳን አቡቂርና ዮሐንስ የሥጋ ፍልሰት፦ ይህም እንዲህ ነው እሊህ ቅዱሳን የካቲት ስድስት ቀን ሰማዕት ሆኑው በሞቱ ጊዜ ምዕመናን ሥጋቸውን ተሸክመው ወስደው በእስክንድርያ በስተሰሜን ባለች በቅዱስ ማርቆስ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ በሥውር አኖሩዋቸው እስከ ሊቀ ጳጳሳት አባ ቄርሎስ ዘመንም በዚያ ኖሩ። ❤ እግዚአብሔር መልአክም ለቅዱስ ቄርሎስ ተገለጸለት ወደ ወንጌላዊ ቅዱስ ማርቆስ ቤተ ክርስቲያንም ሔዶ የቅዱሳን የአቡቂርና የዮሐንስን ሥጋቸውን አውጥቶ እንዲሸከም አዘዘው። እርሱም ተነሥቶ ሔደ ከእርሱም ጋራ ቡዙ ሕዝቦች ነበሩ በደረሱም ጊዜ ጸለዩ ምድሩንም ሲቆፍሩ ሥጋቸው በውስጡ ያለበት ቦታ ተገለጠላቸው በባሕር ዳርቻ ወደ አለች ወደ ሌላዪቱም ወደ ቅዱስ ማርቆስ ቤተ ክርስቲያን በታላቅ ክብር የቅዱሳኑን ሥጋ ተሸክመው አድርሰው በዚያ አኖሩ። በዚያም ቤተ ክርስቲያን ሠሩላቸው በዚች ቀን ታላቅ በዓል አደረጉ ከሥጋዎቻቸው ድንቆች ተአምራት ተገለጡ። ❤ አረማውያንም ተሰበሰቡ ይህን ድንቅ ተአምር በአዩ ጊዜ ጣዖቶቻቸው ትተው ክርስቲያን ሆኑ። በዚያችም ጣዖት ቤት አሸዋ በላይዋ ተከመረባት ታላቅ ኮረብታም ሆነ። የቅዱሳንም ሥጋቸው ታአምራትንና ለበሽተኞች ታላቅ ፈውስን ያደርናጋል። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳን አቡቂርና በዮሐንስ በጸሎታቸው ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን። ምንጭ፦ የሐምሌ 4 ስንክሳር። + + + ❤ "ሰላም ለከ ሶፎንያስ ክቡር። ዘተነበይከ በእንተ ይሁዳ ኅልቀተ ኃጥአን እምድር። እንዘ ትብል ከመዝ እንበለ ሠናይ ምግባር። ኢያድኅን ወኢይትቤዘው ብሩር። አመ ምጽአተ እግዚእ ዕለተ ፍዳ ዘድምፃ መሪር"። ሊቁ አርከ ሥሉስ (አርኬ) የሐምሌ 4። + + + ❤ የዕለቱ ምስባክ፦ "ዘያበቊል ሣዕረ ለእንስሳ። ወሐመልማል ለቅኔ እጓለ እምሕያው። ከመ ያውፅእ እክል እምድር"። መዝ 103፥14 ወይም መዝ64፥10። የሚነበበው ወንጌል ማቴ 24፥36-ፍ.ም ወይም ማቴ13፥1-31። የሚቀደሰው ቅዳሴ የቅዱስ ኤጲፋንዮስ ወይም ቅዳሴ ለእግዚእነ ቅዳሴ ነው። መልካም የዐሥራ ሁሉቱ ደቂቀ ነቢያት በዓል፣ የነቢዩ የቅዱስ ሶፎንያስ የዕረፍት በዓልና የጾም ጊዜ ለሁላችንም ይሁንልን። https://t.me/Eotcw

ሕብር ከደኖ። ወትስብእተ በኀፂን ዘእሳት አርሰኖ"። ትርጉም፦ የማኅበር አለቃ ኾኖ ቴዎፍሎስ ካሳደገው በኋላ የመጻሕፍትን ቃል የተከተለ ለኾነ ለቄርሎስ ሰላምታ ይገባል፤ የንስጥሮስን የክሕደት እምነት ለመቃወም መለኮትን ቀለም በሸፈነው ፀምር፤ ትስብእትንም እሳት ባጋለው በብረት መሰለው። ሊቁ አርከ ሥሉስ (አርኬ) የሐምሌ3። + + + ❤ ዕለቱ ምስባክ፦ "እነግሮሙ ስመከ ለአኃውየ። ወበማዕከለ ማኅበር እሴብሓከ። እለ ትፈርህዎ ለእግዚአብሔር ሰብሕዎ"። መዝ 21፥22-23። የሚነበበው ወንጌል ማቴ18፥15-21።የሚቀደሰው ቅዳሴ የቅዱስ ቄርሎስ ቅዳሴ ነው። መልካም የአቡነ ቄርሎስ የዕረፍት በዓልና የጾም ጊዜ ለሁላችንም ይሁንልን። https://t.me/Eotcw

❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን" ❤ ❤ ሐምሌ ፫ (3) ቀን። ❤ እንኳን ለእስክድርያ ሃያ አራተኛው ሊቀ ጳጳስ ከሃዲ (መናፍቅ) ንስጥሮስን በጉባኤ ኤፊሶን 431 ዓ.ም ተከራክሮ ለረታው ለዓምደ ሃይማኖት ለታላቁ አባት ለአቡነ ቄርሎስ ለዕረፍት መታሰቢያ በዓልና ከእርሱ በፊት ለነበረው ሊቀ ጳጳሳት ዮናክንዲኖስ ደቀ መዝሙሩ ለነበረው ለሮሜ ሊቀ ጳጳሳት ለቅዱስ አባት ለአባ ክልስቲያኖስ ለዕረፍት መታሰቢያ በዓል በሰላም አደረሰን። + + + ❤ "ሰላም ለቄርሎስ ወልደ አንበሳ ጽኑዕ፤ ነባቢ ምስጢረ ሥላሴ ቅድስት፤ ዘተናገረ ላዕለ መለኮት"። ትርጉም፦ በመለኮት ላይ የተናገረ፤ የቅድስት ሥላሴን ምስጢርን ተናጋሪ፤ ብርቱ (ጠንካራ) ለኾነ ለአንበሳው ልጅ ለቄርሎስ ሰላምታ ይገባል። ሊቁ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ በተአምኆ ቅዱሳን ላይ። + + + ❤ አባ ቄርሎስ፦ ይህም አባት ለእስክንድርያ (ለግብጽ) ለአባቶች ሊቃነ ጳጳሳት ሃያ አራተኛ ነው። ይህም ቅዱስ የእናቱ ወንድም በሆነው በአባ ቴዎፍሎስ ዘንድ አደገ፤ ጥቂት ከፍ ባለ ጊዜም ወደ አስቄጥስ ወደ መቃርስ ገዳም ላከው በዚያም አምላካውያን የሆኑ መጻሕፍትን ተማረ እግዚአብሔርም መጽሐፍትን አንድ ጊዜ አንብቦ እስከሚአጸናው ድረስ ዕውቀትንና ማስተዋልን ሰጠው። ❤ ከዚህም በኋላ ደግሞ ያስተምረው ዘንድ ለአባ ሰራብዮን ሰጠው ከእርሱም ዘንድ ያለውን ትምህርትን በፈጸመ ጊዜ ወደ ሊቀ ጳጳሳት ቴዎፍሎስ መለሰው። እርሱም እጅግ ደስ ተሰኘበት እግዚአብሔርንም አመሰገነው። ❤ ከዚህም በኋላ ሁል ጊዜ መጻሕፍትን እንዲያነብና ሕዝቡን እንዲያስተምር ለሊቀ ጵጵስና ሥራ ውስጥ ሾመው። ከትምህርቱም ጣዕም የተነሣ ዝም ይል ዘንድ ማንም አይወድም ነበር። ❤ አባ ቴዎፍሎስ በዐረፈ በኋላ በእስክንድርያ ከተማ ላይ ይህን አባ ቄርሎስነ ሊቀ ጵጵስና ሾሙት በዘመኑም በትምህርቱ ቤተ ክርስቲያን በራች። ይኸው አባት ቄርሎስ የቊስጥንጥንያ ሊቀ ጳጳሳት የነበረው ንስጥሮስ በካደ ጊዜ በንጉሥ ቴዎዶስዮስ ዘመን የሁለት መቶ ኤጲስቆጶሳት ጉባኤ ማኅበርን በኤፌሶን ከተማ ሰበሰበ። ይህ አባት ቄርሎስን መረጠው ሊቀ ጉባኤ አደረጉት ንስጥሮስንም ተከራከረው ስህተቱንም ገለጠለት ከስህተቱም ባልተመለሰ ጊዜ አውግዘው ከመንበረ ሲመት አሳደዱት። ❤ ይህም አባት ቄርሎስ አሥራ ሁለት አንቀጾችን ደረሰ። በውስጣቸውም የቀናች ሃይማኖትን ገለጠ። ከዚህም በኋላ ግን ብዙዎች ድንሳናትን ተግሳጻትንና መልእክቶችን ደረሰ። እሊህም በሁሉ ቦታ በመምእመናን እጆች ይገኛሉ። ❤ ይህም አባት ቄርሎስ እግዚአብሔር ቃል ከትሥብእቱ ጋራ ከተዋሐደ በኋላ በሥራ ሁሉ በምንም በምን የማይለያይ አንድ አካል አንድ ባሕሪይ እንደሆነ አስረዳ። ይህም አባት ቄርሎስ ሃይማኖታቸው ከቀና ከሦስት መቶ አሥራ ስምንት አባቶ ሃይማኖት ወጥተው ክርስቶስ ወደ ሁለት የሚከፍሉት መናፍቃንን ሁሉንም አውግዞ ለያቸው። ❤ ወንጌላዊው ቅዱስ ማርቆስ መንበር ላይ ሠላሳ ሁለት ዓመት ኖረ መልካም የሆነው ሥራውም ፈጽሞ ሐምሌ 3 ቀን በሰላም ዐረፈ። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በአባ ቄርሎስ ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላዓለሙ አሜን። + + + ❤ የሮሜ ሊቀ ጳጳሳት ቅዱስ አባት አባ ክልስቲያኖስ፦ ይህ አባ ዮናክንዲዮስ በሚያርፍበት ጊዜ በእርሱ ፈንታ አባ ክልስቲያኖስን ሊቀ ጵጵስና እንዲሾሙት አዘዘ እርሱንም አባ ክልስቲያኖስን "በሮሜ አገር ነጣቂ ተኩላዎች አሉና ልጄ ሆይ ተጠበቅ" ብሎ አዘዘ። ❤ ከዚህም በኋላ አባ ዮናክንዲዮስ በዐረፈ ጊዜ ይህን አባት ክልስቲያኖስን በእርሱ ፈንታ ሊቀ ጵጵስና ሾሙት። በዚያ ወራት ደግ ንጉሥ አኖርዮስ ነበር ከእርሱም በኋላ አመጸኛ ሉልያኖስ ነገሠ እርሱም ክርስቲያኖስን ከመንበሩ አሳድዶ መናፍቁን ንስጥሮስን ሊቀ ጵጵስና ሾመው። የከተማ ሰዎች ግን አባረሩት እንጂ አልተቀበሉትም በከሀዲው ንጉሥም ልብ በክርስቲያስ ላይ ቂም ነበረ ሊገድለውም ይሻ ነበር። እርሱ አባ ክልስቲያኖስ ግን በሮሜ ከተማ የሚገኙ ገዳማት በንዱ ገብቶ ኖረ እግዚአብሔርም ብዙ ድንቆችንና ተአምራቶችን በእጆቹ ያደርግ ነበር። ❤ ከዚህም በኋላ ከሀዲው ንጉሥ ወደ ጦርነት ሆደ የእግዚአብሔር መልአክ የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሩፋኤልን ለክልስቲያኖስ ተገለጠለት ወደ አንጾክያ ከተማ ወደ ሊቀ ጳጳሳት ድምትርያኖስ ይሔድ ዘንድ አዘዘው "በዚያም ኑር" አለው። "ንጉሡ ከጦርነት እንደተመለሰ ይገድልህ ዘንድ በልቡ አስባልና"። ከእንቅልፉም በነቃ ጊዜ ከዚያ ገዳም ወጣ ከእርሱም ጋራም ሁለት መነኰሳት ነበሩ ወደ አንጾኪያ ከተማ ወደርሶ ቅዱስ ድምትርያኖስ አገኘው ከአመጸኛው ንጉሥም የደረሰበትን ሁሉ ነገረው እርሱም በአንጾኪያ ከተማ የሚገኙ ገዳማት በአንዱ ገዳም አኖረው። ❤ ከዚህ በኋላ ቅዱሳን ሊቃ ጳጳሳት አግናጥዮስና ዮናክንዲዮስ በሌሊት ዕራይ ለንጉሡ ተገለጡለት ከእርሳቸውም ጋራ የነበረው አንዱ እጅግ የሚያስፈራና ግሩም ነበር። እርሱም ንጉሡን እንዲህ አለው "ሊቀ ጳጳሳቱን ክልስቲያኖስን አገሩን ለምን አስተውከው እነሆ እግዚአብሔር ነፍስህን ከአንተ ይወስዳል በጠላቶችህም እጅ ትሞታለህ"። ንጉሥም ጌታዬ "ምን ላድርግ" አለው እነዚያም ሁለትም አባቶች "በእግዚአብሔር ልጅ ሕማም በመቀበሉ ታምናለህን" ብለው መለሱለት "እኔ አምናለሁ" አላቸው "ዳግመኛም መልእክትን ልከህ ልጃችን ክልስቲያኖስ ወደ መንበሩ መልሰው" አሉት። ❤ ከእንቅልፉም በነቃ ጊዜ መልክትን ጽፌ ወደ ድምትራያኖስ እንዲህ ብሎ ላከ "ስለ ሊቀ ጳጳሳት ክልስቲያኖስ በእኔ ላይ አትዘን ወደ መንበረ ሲመቱ ይመልሱት ዘንድ ሊቀ ጳጳሳት ክልስቲያኖስ ያለበትን በመላእክተኞቼ ታመላክታቸውና ታደርሳቸው ዘንድ እለምንሀለሁ"። መልአክተኞችም በሔዱ ጊዜ አገኙትና መለሱት ሕዝቡም በታላቅ ክብርና በብዙ ደስታ ተቀበሉት በዚያም ወራት ንጉሡ ከጦርነት በደና ተመለሰ ቤተ ክርስቲያንም በዕረፍትና በሰላም ኖረች። ❤ የንስጥሮስም ክህደቱ በተገለጠ ጊዜ በእርሱ ምንክያት አንድነት ያላቸው ማኅበር ተሰበሰቡ ይህ አባት ክልስቲያኖስ በደዌውና በእርጅናው ምክንያት ወደ ጉባኤው መምጣት አልተቻላቸውም ነገር ግን ንስጥሮስን ከሚያወግዝ ደብዳቤ ጋር ሁለት ቀሳውስትን ላከ። ❤ ክብር ይግባውና ጌታችንም ከዚህ ኃላፊ ዓለም ድካም ሊያሳርፈው በፈቀደ ጊዜ ዮናክንዲዮስና አትናስዮስ ተገለጡለት እንዲህም አሉት "ክብር ይግባውና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ ሕይወት ጠርተሀልና አንተ ወደ እኛ ስለምትመጣ አስጠንቅቃቸው" አሉት። ከእንቅልፉ ነቅቶ ወገኖቹን ጠራቸው እንዲህም አላቸው "ተኩላዎች ወደዚች ከተማ ይገቡ ዘንድ አላቸውና ተጠንቀቁ"። ❤ ይህንም ከተናገረ በኋላ ዳግመኛ እንዲህ አለ "እንነሳና እንሂድ እነሆ ቅዱሳን ይሹኛልና ሁለቱ ሌሎች ናቸው በዚችም ሰዓት በዚች ዓለም በአንድነት እንወጣለን እነርሱም የእስክንድርያ ሊቀ ጳጳሳት ቄርሎስና የፃን አገር ኤጲስቆጶስ ሉቅያስ ናቸው" ይህንንም ብሎ ሐምሌ 3 ቀን በሰላም ዐረፈ። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳን አባቶቻችን ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘለዓለሙ አሜን። ምንጭ፦ የሐምሌ 3 ሰንክሳር። + + + ❤ "ሰላም ለቄርሎስ ለቃለ መጻሕፍት ዘዴገኖ። ቴዎፍሎስ ድኅረ ሐፀኖ ሊቀ ማኅበር ከዊኖ፡፡ ሃይማኖተ ንስጡር ለተቃርኖ፡፡ መሰለ ፀምረ መለኮተ ዘጥምዐተ

ዜም ተወው። ሐዋርያው ቅዱስ ታዴዎስም "ጌታችን እንደአንተ ላለው ሀብታም ባለፀጋ ወደ መንግሥተ ሰማይ ከሚገባ ገመል በመርፎ ቀዳዳ ቢያልፍ ይቀላል" ብሎ በእውነት ተናገረ አለው። ጎልማሳ "ባለፀጋም ይህ ነገር ትክክል አይደለም እንዴት ሊሆን ይችላል" አለ። ❤ በዚያ ጊዜም በዚያ ጎዳና ሊያልፍ ባለ ገመል መጣ ሐዋርያው ቅዱስ ታዴዎስም ጠርቶ አስቆመውና መርፌ ከሚሸጥ ዘንድ መርፌን ፈለገ መርፌ የሚሸጠው ግን ሐዋርያው ሊረዳው ፈልጎ ቀዳዳው ሰፊ የሆነ መርፌ አመጣለት ሐዋርያው እግዚአብሔር ዋጋህን ይክፈልህ ነገር ግን በዚች አገር የእግዚአብሔር ክብር ይገለጥ ዘንድ ቀዳዳው ጠባብ የሆነ መርፌ አምጣል" አለው። ❤ ከዚህ በኋላ በላ መርፌው ቀዳዳው ጠባብ የሆነውነ መርፌ በአቀረበለት ጊዜ "ኃይልህ ግለጥ" ብሎ ወደ ጌታችን ጸለየ እጁንም ዘርግቶ በአለ ገመሉን ክብር ይግባውና በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስም አንተ ከገመልህ ጋር በመርፎ ቀዳዳ ውስጥ ግባና እለፍ" አለው ገብቶም አለፈ "ሕዝቡም የፈጣሪያች የክርስቶስ ኃይል ይረዱ ዘንድ ዳግመኛ ገብተህ እለፍ" አለው። ባለ ገመሉም በመርፎው ቀዳዳ ሦስት ጊዜ ከገመሉ ጋር አልፎ ሆደ። ❤ ሕዝቡም አይተው "ከቅዱሳን ሐዋርያት አምላክ ከህያው እግዚአብሔር ልጅ ከኢየሱስ ክርስቶስ በቀር ሌላ አምላክ የለም" እያሉ ጽምጻቸውን ከፍ አድርገው ተናገሩ። ያም ጎልማሳ ባለጸጋ መጥቶ ከሐዋርያው እግር በታች ወድቆ ሰገደና ኃጥያቴን ሁሉ ይቅ በለኝ ገንዘቤንም ሁሉ ወስደህ ለድኆችና ለምስኪኖች አከፍፍልልኝ" አለው። እንደ ለመነውም አደረገለት የሃይማኖትንም ሕግ አተምሮ የክርስትና ጥምቀትንም አጠመቀው ሥጋውንና ደሙ አቀበለው ሁሉንም በቀናች ሃይማኖት አጸናቸው። ❤ ከዚህ በኋላ ከዚያ ወጣ በሰላምም ሸኙት በቡዙ አገሮችም ውስጥ ገብቶ ሰበከ ከአይሁድና ከአረማውያን መከራ ደረሰበት ከዚህም በኋላ ሐምሌ 2 ቀን በሰላም ዐረፈ። ለእግዚአብሔር ይሁን እኛንም በሐዋርያው ቅዱስ ታዴዎስ ጸሎት ይማረን በረከቱ ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላዓለሙ አሜን። ምንጭ፦ የሐምሌ 1 ስንክሳር። + + + ❤ "ሰላም ለታዴዎስ ምንዳቤ ሕንቀት ዘተወክፈ። እንበይነ ጥሪቱ ወብዕሉ አመ ባዕለ ዘለፈ። ለትውልድ ደኀሪ እስከ ተአምሩ ተጽሕፈ። ሰቀለ ብእሲተ በነፋስ ዘትዜሙ ዘልፈ። ወበስቊረተ መርፍዕ ካዕበ ገመለ አኅለፈ"። ሊቁ አርከ ሥሉስ (አርኬ) የሐምሌ 2። + + + ❤ የዕለቱ የማኅሌት ምስባክ፦ "ውስተ ኵሉ ምድር ወፅአ ነገሮሙ። ወእስከ አጽናፈ ዓለም በጽሐ ነቢቦሙ። ወወስተ ፀሓይ ሤመ ጽላሎቶ"። መዝ 18፥4-5። የሚነበበው ወንጌል ማቴ 13፥24-33። + + + ❤ የዕለቱ የቅዳሴ ምስባክ፦ "ሐወጸካ ለምድር ወአርወይካ። ወአብዛኅኮ ለብዕላ። ፈለገ እግዚአብሔር ምሉዕ ማያት"። መዝ 64፥9። የሚነበበው ወንጌል ማቴ19፥16-30። የሚቀደሰው ቅዳሴ የቅዱሳን ሐዋርያት ቅዳሴ ነው። መልካም የሐዋርያው የቅዱስ ታዴዎስ የዕረፍት በዓልና የጾም ጊዜ ለሁላችንም ይሁንልን። ❤ በየቀኑ ይህን ቴሌግራም ላይ ማግት ከፈለጉ ከታች ያለውን ሊኩን ይጫኑት። https://t.me/Eotcw

❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን" ❤ ❤ ሐምሌ ፪ (2) ቀን። ❤ እንኳን ከዐሥራ ሁለቱ ሐዋርያት ለአንዱ ገመልን በመርፌ ቀዳዳ ላሳለፈ ለሐዋርያው ለቅዱስ ታዴዎስ ለዕረፍት በዓል መታሰቢያ በሰላም አደረሰን። + + + ❤ "ተዘከረኒ እግዚኦ በምሕረትከ በእንተ እሉ ሐዋርያቲከ፤ እለ ሰበኩ በስምከ ወዘርዑ መዝገበ ቃልከ ውስተ ኵሉ ምድር በዐቢይ ምንዳቤ፤ በረኀብ ወበጽምዕ በቊር ወበዕርቃን፤ በሐፍ ወበድካም በኵነኔ ወበመከራ እምኀበ ነገሥት ወመኳንንት። ቦ በእሳት ወቦ በኵናት ወቦ በመጥባሕት፤ ቦ በመንኰራኵር ወቦ በዕብን ወበበትር። ተዘከረኒ ወመሐረኒ በእንቲኣሆሙ፤ ወበእንተ ሥቃዮሙ ወምንዳቤሆሙ ወደሞሙ ወሥጥጥ መጽሐፈ ዕዳየ ለገብርከ አሜን"። ትርጉም፦ አቤቱ በስምኽ የሰበኩ፤ በታላቅ መከራ በረኀብና በጥም፤ በብርድና በመራቆት፤ በመውዛትና በመድከም፤ ከነገሥታትና ከመኳንንት ዘንድ ተፈርዶባቸው መከራን በመቀበል በምድር ኹሉ ውስጥ የቃልኽን መዝገብ ስለዘሩ ስለነዚኽ ደቀ መዛሙርትኽ ብለኽ በምሕረትኽ ዐስበኝ፤ በእሳት መከራ የተቀበሉ አሉ፤ በጦርም የተወጋ አለ፤ በሰይፍም የተቆረጠ አለ፤ በመንኰራኵርም የተፈጨ አለ፤ በድንጊያም የተወገረ፤ በበትርም የተቀጠቀጠ አለ፤ ስለነርሱ ብለኽ ማረኝ ዐስበኝም፤ ስለሥቃያቸው ስለመቸገራቸውና ስለደማቸው ብለኽ የእኔ የአገልጋይኽን ዕዳ መጽሐፌን ቅደድ፤ አሜን። ሊቁ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ በተአምኆ ቅዱሳን ላይ። + + + ❤ ሐዋርያው ቅዱስ ታዴዎስ፦ ይህንንም ሐዋርያ ከዐሥራ ሁለት ጋራ ጌታችን አስቀድሞ መረጠው አጽናኝ መንፈስ ቅዱስ በላቸው በወረደ ጊዜ ወደ አገሮች ወጥቶ የወንጌልን ትምህርት አስማረ ከአይሁድና ከአረማውያን ብዙዎቹን ወደ ፈጣሪያቸው እግዚአብሔር መልሶ የክርስትና ጥምቀትን አጠመቃቸው። ❤ አንድ ቀንም ወደ ሶርያ ከተማ ሲጓዝ ክብር ይግባውና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ መልአኩ በሚአምር ጎልማሳ አምሳል ለእርሱ ተገልጦ "ወዳጄ ታዴዎስ ቸር አለህን አትፍራ እኔ ከእንተ ጋራ እኖራለሁና" አለው። ሰላምታም ሰጥቶት ከእርሱ ዘንድ ዐረገ። ❤ ወደ ከተማውም በቀረበ ጊዜ ከእርሱ ጋራ አባት ጴጥሮስ ነበረ ማሳ የሚያርስ ሽማግሌ ሰውን አዩ ሐዋርያትም ሰላምታ ሰጡትና "ሽማግሌ ሆይ የምንበላው እንጀራ ስጠን" አሉት። እርሱም "ከዚህ የለም ግን አመጣላችኋለሁ እናንተም ከበሮቹ ዘንድ ተቀመጡ" አላቸው። እነርሱም " እንዳልክ ይሁን" አሉት። ❤ ያሽማግሌም ከሔደ በኋላ ሐዋርያ "ከበሮች ጋር ያለ ሥራ በከንቱ መቀመጥ ለኔ ኀፍረት ነው ያሽማግሌ ለእኛ በጎ ሊሠራ ሒዷልና" አለ። ይህንኔም ብሎ ተነሥቶ እርፋን ይዞ በበሮቹ ላይ ድምፅ አሰማና ያርስ ጀመረ በዚያም ከርሱ ጋራ የሥንዴ ዘር ነበርና ያን ጊዜ ዘሩንና ማሳውን ባርኮ የሐዋርያት አለቃ ቅዱስ ጴጥሮስ ክብር ይግባውና በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም በእርሻው ላይ ዘራ ሠላሳ ትልሞችኖም አረሰ። ❤ የተዘራው ዘርም ወዲያውኑ በቀለና አደገ እሸትም ሆነ ያ ሽማግሌም በተመለሰ ጊዜ ሐዋርያት ያደረጉትን ተመልክቶ ደነገጠ። ከእግራቸውም በታች ወድቆ ሰገደ "እናንተ ከሰማይ የወረዳችሁ አማልክት ናችሁን" አላቸው እነርሱም "እኛ የቸሩ አምላክ ባሮቹ ነን እንጂ አማልክት አይደለንም" አሉት ደግሞ እንዲህ አላቸው "ስለ አደረጋችሁልኝ በጎ ሥራ በምትሔዱባት ቦታ ሁሉ ልከተላችሁን"። "ይህን ልታደርግ አይገባም ነገር ግን በሮቹን ለጌታቸው ወስደህ መልስ ቤትህንም አዘጋጅልን የምንበላውንም ታዘጋጅልን ዘንድ ለሚስትህ ንገራት። እኛም ወዚች ከተማ ልንገባና እግዚአብሔር እስከ ጠራን ድረስ በውጧ ለመኖር እንሻለን" አሉት። ❤ ከዚህም በኋላ ያ ሰው ከዚያ እርሻ እሸት ቆርጦ ተሸከመ በሮቹንም እየነዳ ሔደ የከተማው ሰዎችም የተሸከመውን እሸት አይተው "አሁን የእርሻ ወቅት አይደለምን ይህን ከወዴት አገኘህ" አሉት ቃልንም አልመለሰላቸውም። በሮቹንም ለጌታቸው መለሰ ወደ ቤቱም ሔዶ ለሐዋርያት ቦታን አዘጋጀ ራትንም እንድታዘጋጅላቸው ለሚስቱ ነገራት። ❤ ወሬውም ወደ ከተማው መኳንንት ደረሰ "በክፉ አሟሟት እንዳትሞት ይህን እሸት ከወዴት እንዳገኘህ ንገረን" ብለው ወደርሱ ላኩ። ይህንም በሰማ ጊዜ "ከእኔ ጋራ ሕይወት ሳለ ሞትን አልፈራም" አለ ይህንንም ብሎ ከመጀመሪያው እስከ መጨረሻው ነገራቸው። "ሒደህ ወደእኛ አምጣቸው" አሉት እርሱም "ጥቂት ቆዩ እነርሱ ወደእኔ ቤት ይመጣሉ በመጡም ጊዜ በዐይኖቻቸችሁ ታይዋቸዋላችሁ" አላቸው። ❤ ሰይጣንም የከተማ መኳንንቱን ልቡና ለውጦ አከፋ "እኒህ አይሁድ ከሰቀሉት ከናዝሬቱ ኢየሱስ ዐሥራ ሁለት ወገኖች ውስጥ ከሆኑ ወዮልን እንድንገድላቸውም ተዘጋጁ" አሉ። እኩሌቶቹም "ልገድላቸው አንችልም አምላካቸው ኢየሱስ የሚሹትን ሁሉ እንደሚያደርግላቸው ሰምተናልና ነገር ግን አመንዝራ ሴት ወስደን በከተማ መግቢያ በር ራቁቷን እናስቀምጣት በአዩዋትም ጊዜ ወደ ኋላቸው ይመለሳሉ ወደ ከተማችንም አይገቡም" አሉ። ❤ እንዲሁም አደረጉ ሴትዮዋንም አራቁተው በከተማው መግቢያ በር ላይ አስቀመጧት። ሐዋርያው ቅዱስ ታዴዎስም በአያት ጊዜ "ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ ወደ ከተማው ገብተን በከበረ ስምህ እስክንሰብክ ድረስ በራሷ ጠጉር በአየር ላይ ይሰቅላት ዘንድ የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤልን ላክልን" አለ። በዚያን ጊዜም ተሰቀለች የከተማዋ ሰዎችም አዩዋት ያቺ ሴትም በከተማው መኳንንቶ "አቤቱ ፍረድልኝ እያለች ጮኸች" ነገር ግን የሐዋርያትን ቃል ወደ መቀበል አልተመለሱም ሰይጣን የሰዎችን ልብ አጽንቷልና። ❤ ከዚህም በኋላ ወዲያውኑ ተነሥተው ወደ እግዚአብሔር ጸለዩ ያንጊዜም የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤል ወረደና የከተማው ሰዎችን ልቡና የማረኩ መናፍስት ርኩሳንን አስወጥቶ ሰደዳቸው ሰዎቹም የሐዋርያትን ትምህርት ተቀበሉ። ክብር ይግባውና በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ አመኑ ያን ጊዜም ሐዋርያው ቅዱስ ታዴዎስ ያቺን በአየር ላይ የተሰቀለትውን ሴት አወረዳት። ❤ ከዚህም በኋላም ኤጲስቆጶሳትን ቀሳውስትንና ዲያቆናትን ሾመላቸው በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስም ስም አጠመቃቸው ያቺንም ተሰቅላ የነበረች ሴት ለቤተ ክርስቲያን የምትላላክ ዲያቆናዊት አደረጋት። ❤ በሐዋርያትም እጆች ብዙ ድንቅና ተአምር ተደረገ እውሮች አየ፣ ሀንካሶችም በትክክል ሔዱ፣ ዲዳዋች ተናገሩ፣ ደንቆሮዎች ሰሙ ለምጻሞች ነጹ፣ አጋንትም ከሰው እየወጡ ተሰደዱ የከተማው ሰዎችም ሁሉ በጌታችን ስኪያምኑ ሙታን ተነሱ። ❤ ሰይጣንም የከተማው ሰዎች ሁሉም በጌታችን እንዳመኑ በአየ ጊዜ ተቆጣ በአንድ ገንዘብ በሚወድ ጎልማሳ ባለጸጋ ልቡ አድሮ በሐዋርያው ቅዱስ ታዴዎስ ላይ አነሳሳው ወደእርሱም ሰገደለትና እንዲህ አለው "የእግዚአብሔር አገልጋይ ሆይ እኔ ብዙ ገንዘብ አለኝ እድን ዘንድ ምን ላድርግ" አለው። ሐዋርያውም ጎልማሳውን "ፈጣሪህ እግዚአብሔርን በፍጹም ልቡህ በፍጹም ኃይልህ ውደደው፣ አትግደል፣ አትስረቅ፣ አታመንዝር፣ በአንተ ሊያደርጉብህ የማትሻው በሌላው ላይ አታድርግ፣ ደግሞም ገንዘብህ ሸጠህ ለድኆችና ለምስኪኖች ስጥ በሰማያትም ለዘላለዓለም የሚኖር ድልብ ታገኛለህ" አለው። ይህንንም በሰማ ጊዜ ቊጣን ተመልቶ ሐዋርያው ቅዱስ ታዴዎስ ይገድለው ዘንድ አነቀው የእግዚአብሔርም ኃይል ከዚህ ሐዋርያ ጋር ባይኖር ኖሮ ከመታነቁ ጽናት የተነሳ አይኖቹ ተመዘው በወጡ ነበር። ❤ አባት ቅዱስ ጴጥሮስም "የክርስቶስን ሐዋርያ እንዴት ደፍረህ ታንቃለህ" አለው። ያን ጊ