ch
Feedback
ሰዋስው ☘☘☘☘

ሰዋስው ☘☘☘☘

前往频道在 Telegram

በሰዋስወ ብርሀን ቅዱስ ዻውሎስ ገዳም እና ለተለያዩ ቤተክርስቲያን ለክብረ በአላት ማውጫ ። በተጨማሪም-ዋዜማ ሥርዓተ ማኅሌት - መዝሙራት ስንክሳር - የየእለቱን ምስባክ ቅኔያት ጥያቄዎች እንዲሁም የወቅታዊ ነገር መወያያ በተጨማሪም @eotcww ብለው ይቀላቀሉን ለወዳጅ ዘመድዎ share#Share#Share# ያድርጉ።

显示更多
1 161
订阅者
无数据24 小时
无数据7 天
无数据30 天
帖子存档
ሰው መሆን ከአምላክ የተሰጠን ትልቅ ፀጋ ነው ይህን ጸጋ ካልተጠቀም ነው ግን መጥፊያችን ነው እንጠንቀቅ የተሰጠንን ፀጋ በአግባብ እንጠቀመው እኝ የተሰጠን እንጂ የኝ የሆነ የለም ነፍሳችንም ሆነ ስጋችን የእግዚአብሄር ነው በአደራ የተሰጠንን ነፍስ አናቆሽሽ ምክንያቱም የሰጠን ይቀጣናል

+ + + ❤ አባ ቴዎድሮስ፦ የእስክድርያ ሊቀ ጳጳሳት ቁጥሩም እርሱም ለአባቶች ሊቃነ ጳጳሳት አርባ አምስተኛ ነው። ይህ አባት መርዩጥ በሚባል አገር በአንድ ገዳም ውስጥ መነኰሰ የዚያም ገዳም ስም ጠንቡራ ነው። ለአንድ ፍጹም ጻድቅ የሆነ ሽማግሌ ሰው ደቀ መዝሙሩ ሆነ። እርሱም ልጁ ቴዎድሮስ በእስክድርያ አገር ላይ ሊቀ ጵጵስና እንደሚሾም በመንፈስ ቅዱስ አይቶ ይህንን ለመነኰሳቱ ነገራቸው። ❤ ይህም አባት ቴዎድሮስ በገድል የተጠመደ ሆነ መልኩም የሚያምር ነው በሰውነቱም ላይ ከውስጥ ማቅ በመልበስ በላዩ የብረት ልብስ መንቈር ይለብስ ነበር በቅንነቱና በትሕትናው ፍጹም ሆነ። በመንፈስ ቅዱስ ፈቃድ ተመርጦ በእስክንድርያ አገር ላይ ሊቀ ጵጵስና ተሾመ የክርስቶስንም መንጋዎች በበጎ አጠባበቅ ጠበቀ ሁልጊዜ መጻሕፍትን በማንበብ ያስተምራቸው ነበር ይልቁንም በሰንበትና በበዓላት ቀን። የሹመቱም ዘመን ጸጥታና ሰላም ነበር ቤተ ክርስቲያንም በሰላም ኖረች በወንጌላዊው ማርቆስ ወንበር ላይ ዐሥራ አንድ ዓመት ተኩል ከኖረ በኋላ፡ በሰላም ዐረፈ። ምንጭ፦ የየካቲት 7 ስንክሳር። + + + ❤ "ሰላም እብል ለገዳማዊ ብሑት። ዘኢርእዮ እምሰብእ መጠነ ሰብዓ ዓመት። ከመ አዘዞ አሐዱ እምላእክት። ድኅረ ወሀባ፡ ኑዛዜ ለነፍሰ ዕብሎይ ኃጥእት። ዘአዕረፈ ዮም በሠሉስ ዕለት"። ሊቀ አርከ ሥሉስ (አርኬ) የየካቲት 7። + + + ❤ የዕለቱ ምስባክ፦ "ወኢትትኃጐሉ እምፍኖተ ጽድቅ። ሶበ ነደት ፍጡነ መዓቱ። ብፁዓን ኵሎሙ እለ ተወከሉ ቦቱ"። መዝ 2፥12። የሚነበቡት መልዕክታት ሮሜ 2፥1-17፣ ያዕ 5፥1-10፣ የሐዋ ሥራ 2፥37-ፍ.ም የሚነበበው ወንጌል ማቴ 12፥38-43። መልካም የጾም ጊዜና በዓል ለሁላችን ይሁንልን። ❤ በየቀኑ ይህን ቴሌግራም ላይ ማግት ከፈለጉ ከታች ያለውን ሊኩን ይጫኑት። @eotcw

❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አሜን"። ❤ ❤ የካቲት ፯ (7) ቀን። ❤ እንኳን ለእስክንድርያ አገር አርባ ሦስተኛ ሊቀ ጳጳስ በአገሩ የነገሡ የተለያዩ አሕዛብ ነገሥታት በጽኑ ሥቃይ ላሠቃዩት ለከበረ አባት ለአባ እለስክድሮስና ለአርባ አምስተኛ ሊቀ ጳጳስ ለከበረ አባት ቴዎድሮስ ለዕረፍታቸው በዓል፣ የሰውን ፊት ሳያይ በበረሀ ለሰባ ዓመት ለኖረ አባ ዕብሎይን ላረጋጋ ለገዳማዊው አባት ለአባ አብዱልማስ ለዕረፍቱ መታሰቢያ በዓል በሰላም አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰቡ፦ ከከበሩ ከአብራቅያ፣ ከአባዲር፣ ከአባርያኖስና ከዕረፍታቸው መታሰቢያ እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን። + + + ❤ የእስክንድርያ ሀገር ሊቀ ጳጳሳት አባ እለእስክንድሮስ፦ እርሱም ለአባቶች ሊቃነ ጳጳሳት አርባ ሦስተኛ ነው። ይህም አባት "ታሮን" በሚባል ገዳም መነኰሰ ትርጓሜውም "የአባቶች ገዳም" ማለት ነው በጌታችንም ፈቃድ በእስክንድርያ አገር ላይ ሊቀ ጵጵስና ተሾመ እርሱ የተማረ አዋቂ ጻድቅ ሰው ነበረና። ❤ በሹመቱ ወራትም ብዙ መከራ ደረሰበት የግብጽ ንጉሥ ልጁን ሹሞ በመንግሥቱ ላይ አሠለጠነው እርሱም በአስቄጥስ በረሀ ያለውን የመነኰሳቱን ገዳማት አፈረሳቸው። ከክፋቱና ከክህደቱ ብዛት የተነሣ ከምስር በስተሰሜን ወዳለች ገዳም ገብቶ በዚያ አምላክን የወለደች የእመቤታችንን የቅድስት ድንግል ማርያምን ሥዕሏን አየና "ይች ምንድን ናት" አለ እርሷም በሽልማት ሁሉ የተሸለመችና ያጌጠች ናት በልብሶቿም ላይ ያማረ የሐር ልብስ ነበረ ሰዎችም "የክርስቶስ እናት የሆነች የእመቤታችን የድንግል ማርያም ሥዕል ናት" አሉት እርሱም ተሳድቦ የረከሰ ምራቁን በፊቷ ላይ ተፍቶ "ደኅና ከሆንኩ ክርስቲያኖችን ፈጽሜ አጠፋቸዋለሁ" አለ ዳግመኛም በክብር ባለቤት በጌታችን ክርስቶስ ላይ የስድብ ቃልን ተናገረ። ❤ ሌሊትም በሆነ ጊዜ የሚያስፈራና የሚያስደነግጥ ታላቅ ራእይን አየ በነጋም ጊዜ ለአባቱ እንዲህ ብሎ ነገረው "ዛሬ በዚች ሌሊት ታላቅ መከራና ብዙ ቅጣት ደረሰብኝ ታላቅ ዙፋንንም አየሁ በላዩ የተቀመጠበት ሰው እጅግ የሚያስፈራ የሚያስደነግጥ ነው ፊቱም ከፀሐይ ይበራል የብዙ ብዙ የሆኑ ሠራዊት የጦር መሣሪያ ይዘው በዙሪያው ቁመው ነበር እኔና አንተም እሥረኞች ሁነን በኋላው ቁመን ነበር እኔም "በዙፋን ላይ የተቀመጠው ማነው?" ብዬ ጠየቅሁ "ትላንት አንተ የዘበትክበት የክርስቲያን ንጉሥ ክርስቶስ ይህ ነው" አሉኝ ከዚህም በኋላ የጦር መሣሪያ ከተሸከሙት አንዱ ወደ እኔ መጥቶ ጐኔን በጦር ወጋኝ ጦሩንም ከጐኔ ውስጥ አላወጣውም"። ❤ አባቱም ሰምቶ ደነገጠ እጅግም አዘነ ያ ልጁም ወዲያውኑ ታመመ አንደበቱም ተዘግቶ በክፉ አሟሟት ሞተ። ዳግመኛም ከአርባ ቀን በኋላ አባቱ ሞተ። በርሱም ፈንታ ሌላ ንጉሥ ተሾመ እርሱም ክርስቲያኖችን እጅግ አሠቃያቸው ይህንንም አባት ሊቀ ጳጳሳት እለእስክንድሮስን አብዝቶ አሠቃየው ከሕዝቡ ሦስት ሺህ የወርቅ ዲናር ለምኖ እስከ ሰጠው ድረስ ጌታችንም ይህን ንጉሥ ፈጥኖ አጠፋው። ❤ ከዚህም በኋላ አሁንም ሌላ ንጉሥ ተሾመ እርሱም ሊቀ ጳጳሳቱን ይዞ እንደ ቀድሞው ሦስት ሺህ የወርቅ ዲናር እንዲሰጠው ፈለገ እርሱም ከወገኖቼ እስከምለምን ታገሠኝ ብሎ ማለደው ንጉሡም ቀጠሮ ሰጠውና ይለምን ዘንድ ወደ ላይኛው ግብጽ ወጣ። በተራራ ላይ አንድ ገዳማዊ ሰው ነበር ከእርሱም ጋር ሁለት ደቀ መዛሙርት አሉ በተራራውም በአንድ ቦታ እንዲቆፍሩና እንዲጠርጉ አዘዛቸው ወርቅን የተመላ አምስት ማሰሮ አገኙ አንዱን ሸሽገው አራቱን ወደ ገዳማዊ መምህራቸው አመጡ እርሱም ይረዳበት ዘንድ እንዲስጡት ወደ ሊቀ ጳጳሳቱ ላካቸው። እነርሱ ግን እነዚያን የወርቅ ማሰሮዎች ይዘው ተመልሰው ወደ ዓለም ገቡ የምንኵስና ልብሳቸውንም ጥለው ሚስት አገቡ በዚያም ወርቅ ወንዶችና ሴቶች ባሮችን እንስሳትንም ገዙ። ❤ የዚያችም አገር አስተዳዳሪ ያዛቸው ገንዘብንም ከወዴት እንዳገኙ በመግረፍ መረመራቸው እነርሱም አምስት የወርቅ ማሰሮዎችን እንዳገኙ አመኑ መኰንኑም ለንጉሥ የጭፍራ አለቃ አሳልፎ ሰጣቸው እርሱም ወደ ንጉሥ አቀረባቸውና አምስት የወርቅ ማሰሮ እንዳገኙ አስረዳው ንጉሡም ጭፍሮቹን ልኮ የሊቀ ጳጳሳቱን ቤት በረበረ የአብያተ ክርስቲያናት ከሆነ ከንዋየ ቅድሳት ያገኘውን ሁሉ ወሰደ ሊቀ ጳጳሳቱንም አሠረውና ወርቅን የተመሉ አራቱን ማሰሮዎች ደግሞም ሦስቱን ሽህ የወርቅ ዲናር አምጣልኝ አለው እርሱም ከዚህ ከኃላፊው ዓለም ገንዘብ ምንም ምን የለኝም አለው ወደ ሕዝቡ ልኮ ሦስቱን ሽህ የወርቅ ዲናር አምጥተውለት እስከ ሰጠው ድረስ አልተወውም ይህንንም ክፉ ንጉሥ ጌታችን አጠፉው። ❤ ከዚህም በኋላ ከእርሱ የከፋ ሌላ ንጉሥ ተሾመ እርሱም የሐሰተኛውንና የርኵሱን ነቢይ ስም በከበረ መስቀል ፈንታ በእጆቻቸው ውስጥ እንዲአትሙ የክርስቲያንን ወገኖች አስገደዳቸው። ይችም ምልክት የመለኮትን ነገር የሚናገር ወንጌላዊ ዮሐንስ የተናገራት ትንቢት ናት ይህም ክፋ ንጉሥ ወደ ሀገሮች ሁሉ ይህን እንዲአደርጉ አዘዛቸው ሊቀ ጳጳሳቱንም እንዲሁ ያደርግ ዘንድ አዘዘው። ሊቀ ጳጳሳትም ይተወው ዘንድ ብዙ ለመነው አልተቀበለውም ዳግመኛም እስከ ሦስት ቀን ይታገሠው ዘንድ ለመነው። ❤ ከዚህም በኋላ ደግሞ እንዳይጥለውና ወደዚህ ወደረከሰ ሥራ እንዳያስገባው ወደ እግዚአብሔር ፈጽሞ ማለደ ጌታችንም ልመናውን ተቀብሎ በጥቂት ደዌ ጐበኘው ወደ ቤቱ እስክንድርያ ይሔድ ዘንድ እንዲአዝዝለት ንጉሡን ለመነው። ንጉሡም ከለከለው ሰለ እጅ ኀትመት ምክንያት ለመፍጠር ሰለ መሰለው የእግዚአብሔርም መልአክ ተገለጠለትና ነገ ታርፋለህ አለው እርሱም አርድእቱን እግዚአብሔር ነገ ስለሚጐበኘኝ አርፋለሁና መርከብን አዘጋጁ አላቸው። አንዳለውም በማግሥቱ አረፈ ሥጋውንም በመርከብ ተሸክመው ወስደው ከአባቶች ሊቃነ ጳጳሳት ሥጋ ጋር ቀበሩት። በዚህም አባት አለእስክንድሮስ ዘመን በግብጽ አገር ለሚኖሩ መለካውያን ስሙ አንስጣስዮስ የሚባል ሊቀ ጳጳሳት ነበራቸው ያዕቆባውያን ምእመናንን ይወዳቸዋል ስለዚህም ወገኖቹ መለካውያን ተጣሉት። እርሱም ነፍሱን ያድን ዘንድ አስቦ ወደዚህ አባት አለእስክንድሮስ መጥቶ ከሥልጣኑ በታች በመሆን የሚታዘዝ ሆነ እለእስክንድሮስም አንስጣስዮስን በእርሱ ፈንታ የሊቀ ጵጵስናውን ሥልጣን ይዞ መንጋውን ይመራ ዘንድ እርሱ ግን ከመነኰሳት እንዳንዱ ሁኖ በገዳም ይኖር ዘንድ እንዲተወው ለመነው። ❤ አባ አንስጣስዮስም አልወደደም እንዲህም አለ "ይህን የምሻ ከሆነ አኔ እስከ ዛሬ ሊቀ ጳጳሳት አልነበርኩምን ላንተ ደቀ መዝሙርህ ሁኜ ላገለግልህ ወደድኩ እንጂ" አለ። በመካከላቸው ከተደረገው ከብዙ ልመና ከብዙ ምልልስም በኋላ ኤጲስቆጶስ ይሆን ዘንድ አንስጣስዮስ ፈቀደ በአንዲትም ሀገር ላይ ኤጲስቆጶስነትን ሾመው። መንጋውንም እንደሚገባ በጎ አጠባበቅን ጠበቀ፡፡ አባት እለእስክንድሮስም በወንጌላዊ ማርቆስ ወንበር የኖረው ሃያ አራት ዓመት ከስድስት ወር ነው እግዚአብሔርንም አገለገለው። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በአባ እለእስክንድሮስ ጸሎት ይማረን በረከቱ ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን።

❤ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን። ❤ ❤ እንኳን ከሰባቱ አጿማት አንዱ ለሆነ ለነነዌ ጾም እግዚአብሔር አምላክ በሰላም አደረሰን። ቀን ከየካቲት 7 እስከ የካቲት 9 2014 ዓ.ም። + + + ❤ የዕለቱ አቡን፦ ሃሌ ሉያ "አድኅነነ እግዚኦ አምላክነ ዘአድኀንካ ለነነዌ ሀገር በትንብልና ሣህልከ"። ትርጉም፦ አቤቱ ጌታችንና አምላካችን ሀገረ ነነዌን (ከጥፋት) ያዳንካት እኛንም (ከጥፋት) አድነን። + + + ❤ የዕለቱ አርያም፦ "ሰብአ ነነዌ ጸዊሞሙ ተማኅሊሎሙ ድኅኑ እሞቶሙ"። ትርጉም፦ የነነዌ ሰዎች ጾመውና ምሕላ ይዘው ከሞት ዳኑ። ሊቁ ቅዱስ ያሬድ በጾመ ድጓው ላይ። ❤ ጾሙ ለአገራችና ኢትዮጵያና ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ እምነቻችን ሰላም፣ ፍቅርና አንድነት የሚያመጣ ያድርግል። መልካም ጾም ለሁላችንም ይሁንልን። @eotcw

❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤ + + + ❤ "ሰላም ለማርያም እንተ ቀብዐቶ ለእግዚእነ ዕፍረተ፤ በአንብዓ ዘረከበት ሥርየተ፤ ዘአርኀወት ለኃጥኣን ዘንሥሓ ፍኖተ"። ትርጉም፦ ለኃጥኣን የንሥሓ ጐዳናን የከፈተች በዕንባዋ ይቅርታን ያገኘች፤ ጌታችንን ሽቱን የቀባችው ለኾነች ለማርያም ሰላምታ ይገባል። ሊቁ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ በተአምኆ ቅዱሳን ላይ። @eotcw

+ + + ❤ አባ አቡሊዲስ፦ ይህም የከበረ በእውቀቱም ፍጹም የሆነ ሰው ነው ከአባት አውክዮስም በኋላ ለሮሜ አገር ሊቀ ጳጳሳት ይሆን ዘንድ መንፈስ ቅዱስ መረጠው ይህም የእስክንድር ሊቀ ጳጳሳት አባ ከላድያኑ በተሾመባት በመጀመሪያ ዓመት ነው ሕዝቡንም ከአረማውያን ጠባይ የሚጠብቃቸው የምያስተምራቸውና በክብር ባለቤት በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሃይማኖት የሚያጸናቸው ሆነ። ❤ በከሀዲውም ንጉሥ በከላድያኖስ ዘንድ ዜናው ተሰማ ይህንንም የከበረ አቡሊዲስን ይዞ በብዙ ግርፋትና ድብደባ አሠቃየው ማሠቃየቱንም በሰለቸው ጊዜ በእግሮቹ ውስጥ ታላቅ ድንጊያ አሥሮ ከጥልቅ ባሕር የካቲት አምስት ቀን አሰጠመው። ማግሥትም ሲሆን የካቲት ስድስት በዛሬዋ ቀን የዚህ አባት ሥጋው በውኃ ላይ ተንሳፎ ተገኘ ደንጊያውም በእግሮቹ ውስጥ እንደታሠረ ነበር አንድ ምእመን ሰው ወስዶ በርሱ ዘንድ አኖረው በከበሩ ልብሶችም ገንዞ ሠወረው ወሬውም በሮሜ አገሮች ሁሉ ተሰማ ንጉሡም ሊአቃጥለው ፈልጎት ነበር ግን አላገኘውም ያ ሰው ሠውሮታልና። ❤ ይህም የከበረ አባት ስለ ቀናች ሃይማኖት ብዙ ድርሳናትን ደርሶል ከእርሳቸውም ስለ አካላዊ ቃል ሰው መሆንና ከኃጢአት በቀር በሥራው ሁሉ አንድ ባሕርይ ስለ መሆኑ የደረሰው አለ። ዳግመኛም እግዚአብሔር የሚወደውን ስለ መሥራት የደረሳቸው ተግሣጻትና ትምህርቶች አሉ ስለ ቤተ ክርስቲያንም ሕግ ሠላሳ ስምንት መመሪያዎችን ሠርቷል እሊህም በሁሉ አብያተ ክርስቲያን ይገኛሉ። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በአባ አቡሊዲስ ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን። ምንጭ፦ የየካቲት6 ስንክሳር። + + + ❤ "ሰላም እብል ዕርገተ ሥጋሁ እምባሕር። እንዘ ዕብን ክቡድ ውስተ እገሪሁ እሡር። አቡሊዲስ ሊቅ ዘበትውልዱ ማእምር። ያምጽእ ሊተ በረከተ እምነ ገሪዛን ደብር። ከመ ንዋየ ክቡር ወብዕል ያመጽእ ሐመር"። ሊቁ አርከ ሥሉስ (አርኬ) የየካቲት 6። + + + ❤ የዕለቱ ምስባክ፦ "እግዚአብሔር ስቡህ በምክረ ቅዱሳን። ዐቢይ ወግሩም ዲበ ኲሎሙ እለ ዐውዱ። እግዚኦ አምላክ ኃያላን መኑ ከማከ"። መዝ85፥7-8። የሚነበበው ዮሐ10፥30-ፍ.ም። የሚቀደሰው ቅዳሴ ቅዳሴ ዲዮስቆሮስ። መልካም የማርያም እንተ ዕፍረት የዕረፍት በዓል። ለሁላችንም ይሁንልን። ❤ በየቀኑ ይህን ቴሌግራም ላይ ማግት ከፈለጉ ከታች ያለውን ሊኩን ይጫኑት። @eotcw

❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤ ❤ የካቲት ፮ (6) ቀን። ❤ እንኳን ጌታችንን ሽቱ ለቀባችው ለማርያም እንተ ዕፍረት ለዕለፍቷ መታሰቢያ በዓል፣ ለዓለሙ ሁሉ መምህር ለሆነ ለሮሜ አገር ሊቀ ጳጳሳት ለከበረ አባት ለአባ አቡሊዲስ ሥጋው ከባሕር ለወጣበት በዓልና ለከበሩ ቅዱሳን አቡቂርና ዮሐንስ ለሦስቱ ደናግላን ለቅዱሳት ቴዎድራ፣ ቴዎፍና፣ ቴዎዶክስያና ለእናታቸው ለቅድስት አትናስያ ሰማዕትነት ለተቀበሉበት ለዕረፍታቸው በዓል በሰላም አደረሰን። ከእነዚህ ቅዱሳን እግዚአብሔር ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን። + + + ❤ የዚህ ሳምንት መዝመር፦ ሃሌ ሉያ ፮ ተበሃሉ ጻድቃን በበይናቲሆሙ እንዘ ይብሉ ቦኑ ዘርኢክምዎ ለልዑል ኢሳይያስኒ ይቤ ርኢክዎ ለልዑል ርኢክዎ ለልዑል ርእየ ወስዕነ ጠይቆቶ ሙሴኒ ይቤ ዘርእዮ በዐምደ ደመና ርኢክዎ ለልዑል ርእየ ወስዕነ ጠይቆቶ ማርያምኒ ትቤ እንተ ፆረቶ በከርሣ ርኢክዎ ለልዑል ርእየት ወክህለት ጠይቆቶ ዮሐንስኒ ይቤ ዘአጥመቆ በዮርዳኖስ ርኢክዎ ለልዑል ርኢክዎ ለልዑል ርእየ ወስዕነ ጠይቆቶ አኃውየ በትፍሥሕት ንግበር በዓለነ እስመ አስተርእየ ዘኢያስተርኢ ክርስቶስ ፀሐይ ጽድቅ አስተርአየ። ትርጉም፦ ጻድቃን እርስ በእርሳቸው እንዲህ ተባባሉ፣ በውኑ ያያችሁትን ልዑሉን ኢሳይያስ አየሁት አለ መጠየቅ ግን ተሳነው በአምደ ደመና ያየው ሙሴም ልዑሉን አየሁት አለ፤ እርሱም መጠየቅ ተሳነው በማህፀኗ የተሸከመችው ማርያም ልዑሉን አየሁት አለች፣ አየች መሸከም ቻለች፣ በዮርዳኖስ ያጠመቀው ዮሐንስም ልዑሉን አየሁት አለ መጠየቅ ተሳነው፣ ወንድሞቼ በዓላችንን በደስታ እናክብር የማይታየው የእውነት ፀሓይ ክርስቶስ ተገልጧልና። ሊቁ ቅዱስ ያሬድ በድጓው ላይ። + + + ❤ ማርያም እንተ ዕፍረት፦ ይችም ቅድስት አስቀድማ ኑሮዋን በዝሙት ያሳለፈች ኃጢኣተኛ ነበረች። እርሷም ጐልማሶችን ወደርሷ ትማርካቸው ዘንድ በየራሱ በሆነ ሽልማትና ጌጥ ትሸለም ነበር። በአንዲትም ዕለት እንደ ልማድዋ ተሸልማ አጊጣ ሽቱም ተቀብታ ፊቷን በመስታዋት ተመለከተች የጉንጯ ቅላትና ደም ግባቷ፡የዓይኗም ወገግታና ጥራት ማማሩን አይታ እያደነቀች አንድ ሰዓት ያህል ቆየች ከዚህም በኋላ በጎ ኀሳብ በላይዋ መጣ ሞትንና የዚህን ዓለም ማለፍ አሰበች። የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስም ኃጢኣተኞችን እንደ ሚቀበልና ኃጢአትንም እንደሚያአስተሰርይ ሰምታ በዝሙት የሰበሰበችውን ሦስት መቶ ወቄት ወርቅ አላት ያን ይዛ ኼዳለች። ❤ ዲያብሎስም ታመልጠኛለች ይኽነን ጊዜ ላስታት ብሎ ቀድሞ ከምታውቀው አንዱን መስሎ፡በመልከ፡መልካም ወጣት አምሳል ከመንገድ ላይ ቆይቷት "ወዴት ትኼጃለሽ" አላት፤ ዝም አለችው፤ "አንቺ ባትነግሪኝ እኔ እነግርሽ የለም፤ እንግዳ ወንድ መጥቶብሽ ለርሱ የምትቀቢው ሽቶ ልትገዢ ትኼጃለሽ" አላት፤ "አዎን" አለችው፤ ይኽም አይደለም "ፍቅሩ ያላለቀበት ወንድ መጥቶብሽ ለርሱ የምትቀቢው ሽቱ ልትገዢ ትኼጃለሽ" አላት፤ "አዎን" አለችው። ይኽም አይደለም "በጥቂት ገንዘብ ብዙ ገንዘብ የሚሸጥ ነጋዴ መጥቶብሽ ለርሱ የምትቀቢው ሽቱ ልትገዢ ትኼጃለሽ" አላት፤ "አዎን" አለችው። ኹሉንም "አዎን አዎን ትያለሽ ማናቸው ነው ትክክል" አላት፤ ርሷም ተገልጾላት "እንግዳ ወንድ መጥቶብሽ አልከኝ፤ ከዚኽ ዓለም ልዩ የሚኾን ጌታ መጥቷል፤ ፍቅሩ ያላለቀበት ወንድ መጥቶብሽ ላልከኝ የሰው ፍቅር አገብሮት ሊሞት መጥቷል፤ በጥቂት ገንዘብ ብዙ ገንዘብ የሚሸጥ ነጋዴ መጥቶብሽ ላልከኝ "አዎን በጥቂት ትሩፋት ብዙ ክብር የሚሰጥ ኢየሱስ ክርስቶስ መጥቷልና ለርሱ የምቀባው ሽቱ ልገዛ እኼዳለኊ"ብላ ስሙን ብትጠራበት እንደ ትቢያ በኖ እንደ ጢስ ተንኖ ጠፍቶላታል፤ ከዚኽ በኋላ ሃድኖክ የሚባል ባለጸጋ ነጋዴ አለ፤ ኼዳ "ለነገሥታት የሚገባ ሽቱ አምጣ" ብላ ሦስት መቶ ወቄት ወርቅ ሰጠችው፤ በአገራቸው "ሐሰት የለምና ይኽን ያኽልስ የሚያወጣ የለለኝም" አላት፤ ርሱ የማያውቀው እናቱ የምታውቀው ዳዊት ሰሎሞን ተቀብተውለት የተረፈ ነበርና ከእንዲኽ ያለ ቦታ አለና ሽጥላት ብላው ሽጦላት አምጥታ ቀብታዋለች፤ ይኽም ብቻም አይደለም ጌታ ከእናቱ ጋር ግብጽ በተሰደደበት ጊዜ ሰሎሜም ፈያታዊ ዘየማንም ይዘውት ሳለ ከልብሱ ላይ ወዛ ቢያጥቡት ሰፈፈ ይኽም በዕቃ አኑረውት ነበርና ያም ተጨምሮበታል፤ በቢታንያ በለምጻሙ በስምዖን ቤት ሳለ ዋጋው እጅግ የበዛውን ይኽነን ሽቱ የመላው የአልባስጥሮስ ብልቃጥ ይዛ ወደ ርሱ ቀርባ በማዕድም ተቀምጦ ሳለ በራሱ ላይ አፍስሳዋለች፤ ጌታችንም ለደቀ መዛሙርቱ "ይኽነን ሽቱ በሰውነቴ ላይ አፍስሳ ለመቃብሬ አደረገች፤ እውነት እላችኋለኊ ይኽ ወንጌል በዓለም ኹሉ በማናቸውም ስፍራ በሚሰበክበት ርሷ ያደረገችው ደግሞ ለርሷ መታሰቢያ እንዲኾን ይነገራል" ብሏታልና። ምንጭ፦ የየካቲት6 ስንክሳርና መጽሐፈ ተአምኆ ቅዱሳን ንባብና ትርጓሜው መጋቢ ሐዲስ ሮዳስ ከጻፈው። + + + ❤ ቅዱስ ዮሐንስ፣ ቅዱስ አቡቂር፣ ቅድስት ሦስቱ ደናግልም ልጆቿና እናታቸው ቅድስት አትናስያና፡- የእሊህም ስማቸው ቴዎድራ ትርጓሜው "የእግዚአብሔር ስጦታ" ነው ሁለተኛወ ቴዎፍና ትርጓሜውም "የእግዚአብሔር ሃይማኖት" ሦስተኛይቱም ቴዎዶክስያ ትርጓሜውም "የእግዚአብሔር ምስጋና" የእናታቸውም የአትናስያ ትርጓሜው "ሕይወት የሆነ" ነው፡፡ ይህም የከበረ ቅዱስ አቡቂር ከታናሽነቱ ጀምሮ በገድል ተጠምዶ የሚኖር መነኰስ ነው፡፡ የከበረ ቅዱስ ዮሐንስ ግን በንጉሥ ሠራዊት ውስጥ ወታደር ነበር፡፡ የእነርሱም አገራቸው እስክንድርያ ሲሆን የሚኖሩት ግን አንጾኪያ ነው፡፡በንጉሥ ዲዮቅልጥያኖስም ፊት ቁመው ከእሊህ ደናግል ከእናታቸው ከአትናስያም ጋር በክብር ባለቤት በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ታመኑ። እርሱም ከወዴት እንደሆኑ ጠየቀ ከእስክንድርያ አገር እንደሆኑ በተረዳ ጊዜ ወደዚያ ይወስዷቸው ዘንድ አዘዘ፡፡ ❤ ወደ እስክንድርያ በደረሱ ጊዜ ዳግመኛ በመኰንኑ ፊት ቁመው በክብር ባለቤት በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ታመኑ መኰንኑም ጽኑዕ ሥቃይን አሠቃያቸው ማሠቃየትንም በደከመው ጊዜ ራሶቻቸውን በሰይፍ እንዲቆርጡ አዘዘ፡፡ አትናስያም ደናግል ልጆቿን በከበረ ስሙ ምስክር ሁነው ከሞቱ ለሰማያዊው ሙሽራ ለክርስቶስ እነርሱም ሙሽሮቹ እንደሚሆኑ በማስረዳት ታጽናናቸው ታስታግሣቸው ነበር፡፡ እንዲሁም ቅዱስ አቡቂር በከበረች ሐዋርያዊት በቅድስት ቴክላ ላይ የደረሰውን መከራና ያገኘችውን ክብር ይገልጥላቸውና ያጽናናቸው ነበር፡፡ ወታደሮችም ባለ ሰይፍ በማከታተል አንዲቱን ከአንዲቱ በኋላ የሚያቀርቡ ሆኑ ከዚህም እናታቸውን የከበሩ፣ ቅዱስ አቡቂርንና ቅዱስ ዮሐንስን ቆረጡ። መኰንኑም ሥጋቸውን ለአራዊትና ለአዕዋፍ ይጥሉ ዘንድ አዘዘ፡፡ ምእመናንም ሥጋቸውን በሥውር ወሰዱ በክብር ገነዙአቸው የመከራው ዘመን እስቲያልፍ በሣጥን አድርገው ሠወሩአቸው፡፡ ከዚህም በኋላ ቤተ ክርስቲያን ተሠርቶላቸው ቅዱስ ሥጋቸውን በውስጧ አኖሩ፡፡ ከእርሳቸውም ታላላቅ ድንቆች ተአምራቶች ተገለጠ። በረከታቸው ከእኛ ጋራ ትኑር ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን ለዘላለሙ አሜን።

ቅኔ_ምርሒት_||_ግእዝ_ጉባኤ_ቃና_Qine_Zema_||_Geez_Gubae_Qana256k.mp32.32 MB

+ + + ❤ አባ ጴጥሮስ የተባለ አባ ብሶይ፦ እርሱም ከላይኛው ግብጽ አክሚም ከሚባል ከተማ ነው። በጐልማሳነቱም ጊዜ የክፉ ሥራዎችን የሚሠራ ሁኖ ነበር በመብላትና በመጠጣትም ይደሰት ነበር። እግዚአብሔርም የነፍሱን ድኅነት ሽፍ ጽኑ ደዌ አምጣበትና ለመሞት ተቃረበ። ነፍሱንም በተመሥጦ አውጥተው የሥቃይ ቦታዎችንም ጥልቅ የሆነች ጒድጓድንም አሳዩት። በዚያም ብሩህ ልብስ የለበሱ ሰዎች አሉ በእጆቻቸውም የሰው በድን ነበር አራት ክፍል አድርገው ለያዩትና "የሰውን ገንዘብ የሚሰርቀውን ሁሉ እንዲህ ያድርጉበታል" አሉት። ይህንንም ነገር በሰማ ጊዜ ጮኸ ከልቡም አዝኖ አለቀሰ ከዚህም በኋላ ነፍሱ ተመለሰች ዐይኖቹንም ወደ ሰማይ አቅንቶ "ጌታዬና ፈጣሪዬ ከዚህ ደዌ ከአዳንከኝ እኔ ስለ ኃጢአቴ ንስሐ በመግባት በፍጹም ልቡናዬ አመልክሃለሁ ከእንግዲህም ከቶ ለዘላለሙ የሴት ፊት አላይም" አለ። ❤ በዚያንም ጊዜ ከደዌው አዳነውና ተነሥቶ ብንዋይ ወደሚባል ገዳም ሔደ መንኰሳቱም ከፈተኑት በኋላ የምንኵስናን ልብስ አለበሱት በግብጽ አገር ሁሉ እስከሚሰማ ታላቅ ተጋድሎን በጾም፣ በጸሎት፣ በመስገድም ተጋደለ። ከሁሉ በላይም ከፍ ከፍ አለ ለመነኰሳትም ትምርት የሚሆኑ የሚጠቅሙ ድርሳናትንና ተግሣጻትን ደረሰ አንድ ጊዜም እንጀራ ሳይቀምስ ውኃ ሳይጠጣ አንድ ወር ጾመ እንዲህም እየተጋደለ ሠላሳ ስምንት ዓመት ያህል ኖረ። ❤ መላዋንም ሌሊት በጸሎትና በስግደት በመትጋት ቁሞ ያድራል ሰዎች የሚሠሩት ሁሉ ጻድቅም ቢሆን ኃጢአተኛም ቢሆን በፊቱ ግልጥ ሆነ ከዚህም በኋላ ጥቂት ታመመና የካቲት 5 ቀን በሰላም ዐረፈ። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በአባ ብሶይ ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን። + + + ❤ አባ አክርጵስ፦ ይህም አባት የእስክንድር አገር ሊቀ ጳጳሳት ዐሥረኛ ነው። እግዚአብሔርን የሚፈራ ንጹሕ ቅዱስ ነው። በእስክንድርያ አገርም ቄስ ሁኖ የሚያገለግል ነበር ከእርሱ በፊት የነበረ ሊቀ ጳጳሳት አባ ከላድያኖስ በዐረፈ ጊዜ የእስክንድር አገር ሕዝቡና ኤጲስቆጶሳት መረጡት በወንጌላዊ ቅዱስ ማርቆስ ወንበር ላይ ጵጵስና ሾሙት። ❤ ከዚህም በኋላ እንደ ሐዋርያት መልካም ጒዞን ተጓዘ የእግዚአብሔርን ሃይማኖት ሕይወት የሆነ ሕጉንም እያስተማረ ቅዱሳት መጻሕፍትንም እያነበበላቸውና እያስተማራቸው መንጋዎቹን ይጠብቃቸው ነበር ሁል ጊዜም ይመለከታቸዋል አንድ የብር አላድን ወይም አንድ የወርቅ ዲናርን ጥሪት አላኖረም ከዕለት ምግቡ ከቁርና ከሐሩር ሥጋውን ከሚሸፍንበት ልብስ በቀር ምንም አላከማቸም። ❤ በዚህ ተጋድሎ ዐሥራ ሁለት ዓመት ኑሮ ጌታችንንም አገልግሎ የካቲት5 በሰላም ዐረፈ። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በአባ አክርጵዮስ በጸሎቱ ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን። ምንጭ፦ የየካቲት 5 ስንክሳር። + + + ❤ "ሰላም ለብሶይ ጴጥሮስሃ ዘተሰምየ። ኵነኔ ሰራቂ በሕልሙ ሶበ ነጸረ ወርእየ። ኀዲጎ ዘትካት ምግባሮ እኩይየ። እንዘ ይፈዲ ብፅዓቶ በከመ ውእቱ ጸለየ። በመዋዕለ ጾሙ ኢጥዕመ ኅብስተ ወማየ"። ሊቁ አርከ ሥሉስ (አርኬ) የየካቲት5። + + + ❤ የዕለቱ ምስባክ፦ "ብፁዓን እለ ተኀድገ ሎሙ ኃጢአቶሙ። ወእለ ኢሐሰበ ሎሙ ኵሎ ጌጋዮሙ። ብፁዕ ብእሲ ዘኢኈለቈ ሎቱ እግዚአብሔር ኃጢአቶ"። መዝ 31፥1-2። የሚነበቡት መልዕክታት ሮሜ 14፥12-16 ፣ ይሁ 5፥15-ፍ.ም እና የሐዋ ሥራ 1፥20-ፍ.ም። የሚነበበው ወንጌል ማቴ 9፥10-14። የሚቀደሰው ቅዳሴ የቅዱስ ባስልዮስ ቅዳሴ ነው። መልካም የአቡነ አሞኒ የልደታቸው በዓልና የልጃቸው የአቡነ ዮሐኒ የመታሰቢያቸው በዓል። ለሁላችንም ይሁንልን። ❤ በየቀኑ ይህን ቴሌግራም ላይ ማግት ከፈለጉ ከታች ያለውን ሊኩን ይጫኑት። @Eotcw

❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አሜን"። ❤ ❤ የካቲት ፭ (5) ቀን። ❤ እንኳን አስቀድሞ ራሱን በኃጢአት አስገዝቶ ለነበረ ለጽኑዕ ተጋዳይ ለአባ ዕብሎይ ለዕረፍት በዓል፣ ለተጋዳይ ለሆነ አባት ጴጥሮስ ለተባለው አስቀድሞ በድሎት ብቻ ይኖር ለነበረውና በኋላም ነፍሱ ተነጥቃ ሲኦልን አይቶ ከተመለሰ በኋላ በታላቅ መንፈሳዊ ተጋድሎ ሠላሳ ስምንት ዓመት ለኖረው ለአባ ብሶይ ለዕረፍት በዓል፣ መነሳንሱ የወርቅ፡ ለሆነ፡ ለጻድቅ አባ ኖብ ለዕረፍት በዓልና ለእስክድርያ አገር ዐሥረኛ ሊቀ ጳጳሳት ለከበረ አባት ለአባ አክርጵዮስ ለዕረፍት በዓል በሰላም አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰቡ፦ በአስቄጥስ ገዳም በሰማዕትነት ከሞቱ ከአባ ዘጠኝ መነኰሳት፣ ከሮሜ ሊቀ ጳጳሳት ከአባ አቡሊዲስ፣ ከቡላ፣ ከአሞኒ ከዕብሎይ እናት ከአበያ ከመታሰቢያቸው እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን። + + + ❤ አባ ዕብሎይ፦ ይህይ የበጎች አርቢ ራሱን ለሰይጣን በማስገዛት ከኃጢአት ሥራ ምንም የቀረው የለም ያመነዝራል፣ ይሰርቃል፣ ይቀማል፣ ይድላል በዚህም የሰይጣንን ሥራ እየፈጸመ አርባ ዓመት ያህል ኖረ። በአንዲትም ዕለት ከቀኑ እኩሌታ ከበጎቹ ጋር በዱር ውስጥ ሳለ እነሆ የመውለጃዋ ጊዜ የደረሰ ያረገዘች ሴትን አየ ሰይጣንም በልቡ ክፉ ሐሳብን ጨመረ እንዲህም አለ "የተረፈችኝ ኃጢአት አንዲት አለች እርሷም ያረገዘች ሴት ሆዷን ሠንጥቄ በእናቱ ሆድ ሕፃኑ የማተኛበትን አይ ዘንድ ነው"። ያን ጊዜ ተወርውሮ ሔዶ በራስዋ ጠጒር ይዞ ከምድር ላይ ጣላት ሾተልም አንሥቶ ሆዷን ሠነጠቀ ሕፃኑንም በማሕፀኗ ውስጥ እንዴት ሁኖ እንደተኛ አየው እርሷም በጻዕር ተጨንቃ አስቀድማ ሞተች ሕፃኑ ግን በጻዕር እየተሠቃየ ብዙ ቆይቶ ሞተ። ❤ አባ ዕብሎይ (በግ አርቢው የሠራውን ይህን ታላቅ ኃጢአት ተመልክቶ ደነገጠ እጅግም አዘነ መራራ ልቅሶንም። በማልቀስ "ታላቅ ኃጢአትን ሠርቻለሁና ወዮልኝ" አለ። በጎቹ እንደተበተኑ ትቷቸው በእጁ የያዛትን መጠበቂያ በትሩን ብቻ ይዞ አስቄጥስ ገዳም እስከሚደርስ እያለቀሰ ተጓዘ፡፡ ወደ አረጋውያን መነኰሳት አልገባም ይልቁንም ዐሥር ምዕራፍ ያህል ርቆ ከበረሃው ውስጥ ገባ፡፡ ከዱር አራዊት ጋር በጫካ ያድራል እንጂ በቤት ውስጥም አያድርም ነበር፡፡ከአራዊት ጋር የሚኗር ሆነ እንጂ ከዕፅዋትም ፍሬ በየጥቂቱ ይመገብ ነበር። ከዕንባ እየጮኸ አላቋረጠም፡ "አቤቱ በደልኩ ክፉ ሥራንም ሠራሁ ይቅር በለኝ እኔ ኃጢአተኛ የሆንኩ ክፉ ባሪያ ነኝና አንተም ቸር አምላክ ይቅር ባይ አባት ነህና የማይበድል ባሪያ የማይምር ጌታ የለምና አቤቱ ይቅር በለኝ…" እያለ፡፡ እንዲህም እየተደለ አርባ ዓመት ኖረ፡፡ ከሌሊት ቁርና ከቀን ፀሐይ ሐሩርና የተነሣ ሥጋው ደርቆ ጠቆረ፡፡ከዚህም በኋላ እንዲህ የሚል ቃል ሰማ "ስለ ሴቲቱ ደም ጌታ ይቅር ብሎሃልና ጽና በርታ"፡፡ ይህንንም ያለው እንዳይታክትና ዳግመኛ ወደ በኃጢአት ውስጥ እንዳይወድቅ ነው፡፡ ይህንም በሰማ ጊዜ ከሦስት ቀን ብቻ በቀር ያቺን ዓመት እስከሚፈጽም መሪር ልቅሶ እያለቀሰ ተጋድሎውን ጨመረ የእግዚአብሔር መልአክ ከእርሱ ዐሥራ አምስት ምዕራፍ ያህል ርቆ ለሚገኝ ከቶ ሰውን ሳያይ በዚያች በርሀ ለሰባ ዓመት ዘግተው የኖረውን አንድ ገዳማዊ "አንተ ካለህበት ቦታ ወደ ውጭ ሂድና አንድ ሽማግሌ ታገኛለህ፣ ኃጢአቱን ካመነልህ አጽናናው፣ ኃጢአትህ ሁሉ ስለ ሕፃኑም መገደል ተሠርዮልሃል በለው" በማለት አዘዘው። ❤ በዚያም ጊዜ ያ ገዳማዊ ሒዶ አገኘው እርስበርሳቸው ሰላምታ ተሰጣጡ። እርሱ ዕብሎይ ግን ያለማቋረጥ ያለቅስ ነበር ገዳማዊውም "የሠራኸውን ንገረኝ በምን ምክንያት ወደዚህ ወጣህ" አለው።እርሱም ሁሉንም ነገረው ያረገዘችውንም ሴት ሆድዋን እንደሠነጠቀ ነገው ገዳማዊውም "ኃጢአትህ ሁሉ ተሠርዮልሃል፣ አባቴ ሆይ ደስ ይበልህ ነገ የእግዚአብሔር መልአክ ወደ አንተ መጥቶ የክርስቶስን ሥጋና ደም ያቀብልሃል" አለው፡፡ የቀዳሚት ሰንበት ዕለትም በነጋ ጊዜ ከቶ እንደርሱ ሁኖ የማያውቅ ጣፋጭ ሽታ ሸተተ ለአባ ዕብሎይ ገዳማዊውን "ከፍርሀት የተነሳ ነፍሴ ከሥጋዋ ልትለይ ደረሰች" አለው። ይህንንም ባለ ጊዜ በመነኰስ አምሳል መልአኩን አየው እርሱም ተቸገርኩ እግዚአብሔር አዳነኝ፡፡ ነፍሴ ሆይ ወደ ዕረፍትሽ ተመለሽ። እግዚአብሔር ረዳትሽ ነውና። ነፍሴን ከሞት አድኗታልና። ዐይኖቼንም ከእንባ እግሮቼንም በዳጥ ከመሰናከል። በሕያዋን አገር እግዚአብሔር አገለግለው ዘንድ" እያለ ይዘምር ነበር። የበጎች ጠባቂ የነበረው አባ ዕብሎይም ይህን ነገር በሰማ ጊዜ በምድር ላይ ወድቆ እንደ በድን ሆነ መልአኩም በሰው አምሳል እጁን ዘርግቶ አነሣው ልቡም ጸንቶ በመልአክ እጅ ከሰማይ የወረደለትን ሥጋውንና ደሙን ተቀበለ መልአኩም ወደ ሰማይ ዐረገ፡፡ ❤ አባ ዕብሎይም ቊርባኑን በተቀበለ ጊዜ ሰውነቱ ሁሉ እንደ በረድ ፀዓዳ እንደ ፋናም ብሩህ ሆኖ በዚያችም ዕለት ሁለቱም ደስ እያላቸው እግዚአብሔርን እያመሰገኑ እስከ ማታ ግን፡ የቀድሞ ጸሎቱን አላቋለጠም እንዲህም እያለ "እኔ ክፉ ባሪያ በየሰባቱ ሰባ ጊዜ በደልኩ ቸር ጌታ ይቅር በለኝ የማይበድል ባሪያ የማይምር ጌታ የለምና"። በዚያችም ዕለት እስከ ሌሊቱ እኩሌታ እግዚአብሔርን እያመሰገኑ አደሩ እርሷም እሑድ ናት። በዚያች ጊዜ ከፊተኛው የሚበልጥ የሽቱ መዓዛ ሸተተ ገዳማዊውም "ወንድሜ ዕብሎይ ና በውኃ ታጠብ ደስ ይበልህም በዚህች ሰዓት ከተቀበልከው መከራ ታርፋለህና" አለው፡፡በዚያንም ጊዜ ከእግዚአብሔር የታዘዘ መልአክ ለሁለቱም ቊርባኑን አቀበላቸው፡፡ አባ ዕብሎይም ዐረፈና መላእክት ነፍሱን ተሸክመው እስከ አርያም በረሩ፡፡ ❤ ያ ገዳማዊ "እኔ ሽማግሌም ነኝ ሥጋውን መሸከም አልችልም የምቆፍርበትም የሌለኝ ምን አደርጋለሁ" ብሎ የሚያስብ ሆነ በዚያንም ጊዜ ሁለት፡ አንበሶች መጥተው ለሥጋ ሰገዱ መቃብራቸውን ቆፍረው ሥጋውን እንደ ሰው ተሸክመው ወስደው፡ ቀበሩት፡፡ገዳማዊውንም እጅ ነሱት እርሱም ባረካቸውና በሰላም ሄዱ፡፡ ከዚህም በኋላ ያ ገዳማዊ "የሚቀብረኝ አገኝ ይሆን" ብሎ አሰበ ወደርሱም እንዲህ የሚል ቃል መጣ "አትዘን ሥጋህን እኔ አስቀብራለሁ ያለ ሦስት ቀንም አልቀረህም ወደአንተም ሦስት ሰዎች እልካለሁ የበግ ጠባቂው የአባ ዕብሎይን ገድል ንገራቸው እነርሱም ለሌሎች ይንገሩ ከእግዚአብሔርም ምሕረት ተስፋ እንዳይቆርጡ በኃጢአት ለወደቁ አለኝታ ይሆን ዘንድ። በማግስቱም ሦስት ሰዎች መጡ እርሱም የበግ ጠባቂውን የአባ ዕብሎይን ተጋድሎ ነገራቸው እነርሱም እጅግ አድንቀው ጻፉት ከገዳማዊው ዘንድ ሦስት ቀን ተቀመጡ ከዚያም በኋላ ገዳማዊው ተነሥቶ ጸለየ ነፍሱንም በእግዚአብሔር እጅ ሰጠ፡፡ እነዚያም ሁለቱ አንበሶች መጡ መቃብርንም ቆፍረው እንደ፡ሰው ወስደው ቀበሩትና እነዚያ ሦስት ሰዎች ጋር ተጓዙ ወደ፡ አስቄጥስ ወደ አባ መቃርስ ገዳም እስከሚአደርሷቸው መርተው ወሰዱአቸው ሰዎችም የሆነውን ሁሉ ለመነኰሳት ነገሩአቸው፡፡ እነርሱ እጅግ አደነቁ የበግ አርቢው የአባ ዕብሎይ ገድል ጻፉ ሁል ጊዜም እሑድ እሑድ የሚያነቡት ሆነ። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳን ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን። ምንጭ፦የየካቲት5፡ስንክሳር።

❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤ ❤ የካቲት ፭ (5) ቀን። ❤ እንኳን ለኢትዮጵያዊያኑ ጻድቃን ለአቡነ አሞኒ ለልደታቸው በዓልና ለልጃቸው ለአቡነ ዮሐኒም ለመታሰቢያቸው በዓላቸው በሰላም አደረሰን። + + + ❤ አቡነ አሞኒ፦ አባታችን የካቲት5 ቀን አክሱም ውስጥ ሲወለዱ ሰይጣናት የወላጆታቸውን ቤት ከበው በማየታቸው እንደተወለዱ በእጃቸው ቢያመለክቱ በአንድ ጊዜ 60ሰይጣናት ተሸንፈው እንጢስ በነው ጠፍተዋል። አሞኒ ማለት አሸናፊ ማለት ነው። አባ አሞኒ የራስ ፀጉራቸው ልብስ መጎናጸፊያ ሆኖቸው የኖሩ ታላቅና ቀደምት አባት ናቸው። በደመና ተጭነው ኢየሩሳሌም ደብረ ዘይት ድረስ በመሄድ ከአባ ዕብሎይ ጋር ተገናኝተው ብዙ ምሥጢርን፡ አውርተዋል። አባ ዮሐኒንያ ሳደጉት አስተምረው ያሳደጓቸው አባ አሞኒ ናቸው፡፡ የእናቱን ጡት ፈጽሞ ጠብቶ የማያውቀውን የመንፈስ ቅዱስ ልጃቸውን አባ ዮሐኒን እሳቸው እያጫወቱት የታዘዘ አሞራ በክንፎቹ እያለበሰው ቶራ (ሰሳ) እያጠባችው ነው ያደገው፡፡ ❤ አባ አሞኒ ልጃቸው አባ ዮሐኒ አድጎ 12ዓመት ሲሆነው ከዚህም በኋላ ዲቁና ሊያሾሙትና አክሱም ጽዮን ወስደው ሊያስባርኩት ቤተ ካህናት ከተባለው ቦታ ይዘውት ሲሄዱ ልዩ ስሙ ሲሂታ ከሚባለው ቦታ ሲደርሱ ከወገባቸው በላይ እራቁታቸውን የሆኑ እንስራ የተሸከሙ ዐሥር ሴቶች አገኙ፡፡ አባ ዮሐኒም አባታቸውን "አባቴ እነዚህ ደረታቸው ላይ ቀንድ ያላቸው ጽጉራቸው የረዘመ ምንድናቸው? እንደእኛ የሆኑ መስህታን የሚባሉት እነዚህ ናቸውን?" አሏቸው፡፡ አባ አሞኒም"አይደሉም፡ልጄ፡ዝም፡ብለህ፡ሂድ" አሏቸው፡፡በኋላ ግን ትዝ ሲላቸው "በዱር እንስሳት ያሳደኩት ልጄ ወንድና ሴት ለይቶ ሲያውቅ በዚያው ሊሳሳት አይደልምን?" ብለው በማሰብ ዲቁናና ክህነቱ ይቅርበት ብለው ተመልሰው ወደ በዓታቸው ይዘውት ገቡ፡፡ ከዚህም በኋላ አባ አበይዶ ወደ አባ አሞኒ መጣና እሳቸውን ከአባ ዮሐኒ ጋር እያገለገሏቸው ተቀመጡ፡፡ ዮሐኒ እየጻፈ አበይዶ የሚጻፍበትን ቆዳ እያዘጋጁ ሦስቱም በአንድነት በተጋድሎ መቀመጥ ጀመሩ፡፡ ❤ አባ ዮሐኒ ሃያ ዓመት አባ አሞኒ ደግሞ አርባ ዓመት በሆናቸው ጊዜ መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል ለአባ አሞኒ ተገለጠላቸውና "አሞኒ ሆይ ከእንግዲህስ እግዚአብሔር ወደኔ ና ብሎሃል" አላቸው። እሳቸውም ልጆቻቸውን አባ ዮሐኒንና አባ አበይዶን ጠርተው "በሉ እንግዲህ እኔ ወደ እግዚአብሔር መሄዴ ነውና ጸልዩልኝ" አሏቸው፡፡ ከማረፋቸውም በፊት አባ ዮሐኒን ለብቻቸው ጠርተው "አንተ አባ ዮሐኒ ካሁን በፊት ሲሂታ ላይ ያየሃቸው ሴቶች ናቸው፣ አዳምንም ከገነት ያስወጡ ናቸው፡፡ ወደፊትም እንደ እነርሱ ያለ የደረሰብህ እንደሆነ ካለህበት ገደል ተወርውረህ ውደቅመ በባሕር ውስጥ ጥለቅ" ብለው ነግረዋቸው ዕለት ኅዳር5 ቀን በሰላም ዐረፉና ወደ ጠራቸው እግዚአብሔር ሄዱ፡፡ ምንጭ፦ መዝገበ ቅዱሳን። ❤ በየቀኑ ይህን ቴሌግራም ላይ ማግት ከፈለጉ ከታች ያለውን ሊኩን ይጫኑት። @Eotcw

፬ኛ ወረብ አዕምሮ ቀደሙ-1644507115803.mp31.98 MB

፫ኛ ወረብ ነአምን-1644507076353.mp31.87 MB