ሰዋስው ☘☘☘☘
前往频道在 Telegram
በሰዋስወ ብርሀን ቅዱስ ዻውሎስ ገዳም እና ለተለያዩ ቤተክርስቲያን ለክብረ በአላት ማውጫ ። በተጨማሪም-ዋዜማ ሥርዓተ ማኅሌት - መዝሙራት ስንክሳር - የየእለቱን ምስባክ ቅኔያት ጥያቄዎች እንዲሁም የወቅታዊ ነገር መወያያ በተጨማሪም @eotcww ብለው ይቀላቀሉን ለወዳጅ ዘመድዎ share#Share#Share# ያድርጉ።
显示更多1 161
订阅者
无数据24 小时
无数据7 天
无数据30 天
帖子存档
1 161
ምንጭ፦ ገድለ አቡነ ኤዎስጣቴዎስ።
+ + +
❤ "ሰላም ዕብል መክራቲሁ ዐቢየ። ለበጸሎተ ሚካኤል አቡየ። ኀበ ኅብረ ከይሲ ዘሜጠ ዘዓሣ ራእየ። ወካዕበ ከይሴ ዓሣ ረሰየ። በሕራረ ዐፅሙ ፈወሰ ድውየ"። ሊቁ አርከ ሥሉስ (አርኬ) የሐምሌ 20።
❤ በየቀኑ ይህን ቴሌግራም ላይ ማግት ከፈለጉ ከታች ያለውን ሊኩን ይጫኑት።
https://t.me/Eotcw
1 161
እንደሚገደሉ ነገራቸው፡፡ አባታችንም "ወርቅህና ብርህ ጥሪትህም ሁሉ ከአንተ ጋራ ለጥፋት ይሁንህ"" ብለው መለሱለት፡፡ ከልጆቹም ጋር አባታችንን በግዳጅ ወደ ንጉሡ ዘንድ ሲወስዷቸው የንጉሡን ምግብ እንዳይቀምሱ ተማምለው አንደኛው መነኵሴ የገንዘባቸው የገዙትን ጎመን ተሸክሞ አብሯቸው ሄደ፡፡ ንጉሡም ባየው ጊዜ በጽኑ ጅራፍ እያስገረፈው እያለ ሕይወቱ በዚያው አለፈች፡፡ ከዚህም በኋላ ንጉሡ በግዞት ወደ አረማውያን መኖሪያ እየነዱ እንዲወስዷቸው አዘዘ፡፡
❤ ወደ ግሎ ማክዳ ምድር እንዳደረሱት በዚያ ያሉ ቅዱሳን በደስታ ተቀበሉት፡፡ ስማቸውም ማርቆ፣ ክርስቶስ አምነ፣ አባ ሲኖዳና ማማስ ናቸው፡፡ ማማስም ለአባታችን ለጸሎት የሚሆነውን የድንጋይ ዋሻ አሳየው፡፡ አባታችንም "ይህች ዋሻ ለዘላለም ማረፊያዬ ናት" ብሎ ውስጧን በድንጋይ ይወቅር ጀመር፡፡ በውስጧም አገልገሎቱን ፈጸመ፡፡ ወደ ቅዱሳኑ ወደ እነ አባ ማርቆስ፣ ክርስቶስ አምነ እና ሲኖዳ መጥተው የመቃብር ጉድጓድ እንዲቆፍሩ መልአክት ላከባቸው፡፡ በቀዳሚት ሰንበት ዕለትም ደቀ መዝሙሩ ዕንባቆም በአገኘውና "ነገ አባትህን ወደ መቃብር ትጥለዋለህ" አለው፡፡
❤ በማግሥቱም እሁድ ቀን ደቀ መዛሙርቱን ሁሉ ሲመክራቸው ዋለ፡፡ በመጨረሻም አንዱን ደቀ መዝሙሩን ብቻ አስከትሎ ወደ ዋሻዋ ግቶ በ4ቱም ማዕዘን ባረካት፡፡ ከዚህም በኋላ ሐምሌ 21 ቀን እጁንና እግሩን ዘርግቶ ነፍሱን በፈጣሪው እጅ አስረከበ፡፡ ነቢዩ ‹"የጻድቅ ሰው ሞቱ በእግዚአብሔር ፊት ክቡር ነው" እንዳለ ያለ ምንም ጻዕር ዐረፈ፡፡ መዝ 115፥6፡፡
❤ ደቀ መዛሙርቱም በመጡ ጊዜ ዐርፎ አገኙት፡፡ እነርሱም መሬት ላይ ወድቀው "አባት እንደሌላቸው እን ሙት ልጆች ለማን ትተወናለህ፣ በስውር የሠራነው ኃጢአትስ ማን ይነግረናል…." እያሉ ጽኑ ልቅሶን አለቀሱ፡፡ አስቀደሞም እርሱ ደቀ መዛሙርቱ በስውር የሚሠሩትን ሥራ ሁሉ እርሱ በግልጽ እያየ "አንተ ይህን ሠርተሃልና ንስሓ ግባ" እያለ ይመክራቸው ነበርና፡፡ ልቅሶአቸውንም ከፈጸሙ በኋላ ራሱ በጠረባት የድንጋይ ዋሻ ውስጥ ቀበሩት፡፡ የሀገሪቱም ሰዎች ክፉዎች ናቸውና ከጊዜም በኋላ ደቀ መዛመርቱ የአባታችች ዐፅሙን አፍልሰው ወደ ሌላ ቦታ አስቀመጡት፡፡ እስከ ኢትዮጵያ ጳጳስ አባ ያዕቆብ መምጣት ድረስ ደብቀው አኖሩት፡፡ አባ ያዕቆብም የአባታችንን ዐፅም ያመጡለት ዘንድ አዘዘቸው፡፡ ከጊዜም በኋላ ዐፅሙን ወደ ጋስጫ አፍልሰውታል፡፡ ይኸውም ጋስጫ ከሊቁ አባታችን ከአባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ ገዳም ሥር የሚገኝ ነው፡፡ ዋሻ ቤተ መቅደሱም በግሩም አሠራር የተሠራ ነው፡፡እግዚአብሔር አምላክ ከአባታችን ከአቡነ በጸሎተ ሚካኤል ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን። በጸሎታቸውም ይማረን!። ምንጭ፦ መዝገበ ቅዱሳን።
❤ ቅዱስ ላእከ ማርያም፦ ይህም ቅዱስ ደግ የሆነና በጎ ምግባር ያለው ምፅዋት መስጠትንም የሚወድ አነው። የዚህ ቅዱስም የእናቱ ስም ሮማነ ወርቅ ነው እርሷም መካነ ሥላሴን የሠራች የኢትዮጵያ ንጉሥ የናዖድ ልጁ ናት አባቱም የንጉሠ ገይኝ ልጅ ነው።ይህም ቅዱስ ከተወለደ በኋላ በክርስቲያን ወገኖችና በንጉሥ ልብነ ድንግል ላይ መከራና ስደት ሆነ። የዚህን ንጉሥ ዜና ግን በነገሥታት ታሪክ ተጽፎ ስለሚገኝ ትተንዋል።
❤ ንጉሥ ልብነ ድንግልም ከአረፈ በኋላ ገላውዴዎስ ነገሠ። እስላሞችም በእርሱ ላይ ተነሡ ከቀኖችም በአንዱ ሲዋጋ ድል ለእርሱ ሆነ በኋላ ግን ድሉ ለእስላሞች ሆነ የዚች ዓለም ሥርዓቷ እንዲህ ተለዋዋጭ ነውና ያን ጊዜም ይህን ጻድቅ ላእከ ማርያምን ይዘው አሚም ወደሚባለው አለቃቸው አደረሱት እርሱም በክብር አኖረው። በሃይማኖታቸውም እንዳልተባበራቸው አየው የተማረኩትንና የተገደሉትን በሚያያቸው ጊዜ ያለቅስ ነበርና። ስለዚህ እንዲሰልቡት አዘዘ። ይህንንም የጃንደራባነት ዕድል ሁሉ የሚያገኘው አይደለም ለተሰጠችው እንጂ። ክብር ይግባውና ጌታችን እንዳለ ከእናታቸው ሆድ ጀምሮ ሕፅዋን የሆኑ አሉ፣ በጦርነት ጊዜ ሰዎች ሕፅዋን ያደረጓቸውም አሉ፣ ስለ መንግሥተ ሰማያትም ራሳቸውን ሕፅዋን ያደረጉ አሉ ይህን ሊፈጽም የሚሻ ይፈጽም።
❤ ከዚህ በኋላም ወደ ቱርክ ወሰዱት በመንገድም ብዙ መከራ አገኘው በግመል ላይ ዘቅዝቀው የሚሰቅሉበት ጊዜ ነበረ፣ በውኃ ጥማትና በፀሐይ ቃጠሎ የሚያሠቃዩበት ጊዜ ነበረ በጌታችንም ፈቃድ ከየመን አገር ደረሰ። የእስላሞች ንጉሥም ወደርሱ እንዲአቀርቡት አዘዘ ከዚህም በኋላ በእግዚአብሔር ፈቃድ በየገጹ ሊናገሩት በማይቻል በታላቅ ተአምር ወደ ኢትዮጵያ ሀገር ተመለሰ።
❤ ከዚህም በኋላ ቤተ ክርስቲያን ሠራ በድኆችና በችግረኞች ላይ ቸርነትን አደረገ። ብዙ ትሩፋትንም አደረገ የጻድቃንና የሰማዕታትንም መታሰቢያቸውን ያደርጋል። ይልቁንም አምላክን የወለደች የቅድስት ድንግል እመቤታችን ማርያም የበዓሏን መታሰቢያ በየወሩ ያደርግ ነበር። ዕረፍቱም በደረሰ ጊዜ ይኸውም የጥበብ ሁሉ ፍጻሜ ሞት ነው ወንዶችና ሴቶች አገልጋዮችን ነፃ አውጥቶ አባቶቹ ወደ ሔዱበት ዓለም ሔደ። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱስ ላዕከ ማርያም ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን። ምንጭ፦ የሐምሌ 21 ስንክሳር።
+ + +
❤ ከፋሌ ባሕር አቡነ ኤዎስጣቴዎስ ልደት፦ ...
የሁለታቸው የክርስቶስ ሞዓና የሚስቱ ሥነ ሕይወት ልብ ሥለ ሕፃን አንድ ሆነ ከጥቂት ቀን በኋላም የክርስቶስ ሞዓ ሚስት ሥነ ሕይወት በጥቅምት ዐሥራ ሰባት ቀን ፀነሰች ከፀነሰች ቀን ጀምሮም ፊቷ በመንፈስ ቅዱስ ጸጋ የበራ ሆነ የወይን ጠጅንም እንደጠጣ በልቧ የምትደሰት ሆነች "ይህም በሆዴ ውስጥ ያለው ምንድን ነው" አለች። ሥነ ሕይወት ፈጽማ እየጸለየችና እየማለደች ተቀመጠች "ሕፃኑን ከፀነሰኩት ጀምሮ ሕሊናዬ (ሐሳቤ) እንደ ፋና ይበራል" እያለች።
❤ ከዚህም በኋላ በዘጠኝ ወር ከአምስት ቀን ሐምሌ ሃያ አንድ ቀን የኢትዮጵያ ንጉሥ ይኩኖ አምላክ በነገሠ በዘጠነኛው ዓመት የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤል እንዳበሰራት ሥነ ሕይወት ያማረ ልጅን ወለደች ሕፃኑም በተወለደ በሦስት ቀን የእናቱን ጡት እየጠባ ዐይኖቹን ወደ ሰማይ አቅንቶ እግዚአብሔርን ፈጽሞ አመሰገነው እናቱም ምስጋናውን ሰምታ አደነቀች ስለዚህም ሥራ እንዲህ አለች "ከሰው ጋራ ሳይነጋገር ወይም ፈጽሞ ከሚያመሰግን ከአንድ ሰው ጋር ሳይነጋገር ምስጋና የሚያቀርብ ከቀደሙትም ቢሆን ከኋለኞችም ቢሆን አልሰማሁም ከእናቱ ጋር ሳይነጋገር እግዚአብሔርን የሚያመሰግነውና የሚያነጋገረው እንደዚህ ያለ ሕፃን ከሁሉ ዓለም እና ከኢትዮጵያ ሀገር በየት ተገኘ?"።
❤ የሕፃኑ እናቱም ልጇን እንዲህ አለችው "የዓይኖቼ ብርሃን ልጄ ሆይ እንደዚህ ያሉትን ምስጋናዎች ማን አስተማረህ?" ያም ሕፃን ፈጽሞ የተናገራትንና የመለሰላት ነገር የለም ዳግመኛም በዚህች ሌሊት በእናቱ ዕቅፍ ተኝቶ ሳለ የጸሎት ሰዓት በደረሰ ጊዜ እግዚአብሔርን አመሰገነው እናቱ ግን ተኝታ ነበር ከልጁም የምስጋና ድመሰፅ የተነሣ ነቃች እንደ ላሜህ ልጅ እንደ ኖህ በተወለደ በሦስተኛው ቀን የሚያመሰግን ልጅን ስለ ሰጣትም እግዚአብሔርን አመሰገነችው።
❤ ይህም ሕፃን የመረጠው እግዚአብሔር በቅዱሳኑ ዘንድ በእውነት የተመሰገነ ነው ሕፃኑንም አርባ ቀን ከሞላው በኋላ ክርስትና አስነሡት ስሙንም ማዕቀ እግዚእ ብለው ሰየሙት መንፈስ ቅዱስም በዚህ ሕፃን ላይ አደረ የአባቱንና የእናቱንም ስም መጥራት ሳያውቅ ምስጋናውን ይናገር ዘንድ አንደበቱንም ፈታ በዳዊት አፍ "ከሕፃናትና ጡትን ከሚጠቡ አንደበት ምስጋናን አዘጋጀ" የሚል እንደ ተጻፈ...።
1 161
ም በ7 ገራፊዎች በታላቅ ጅራፍ አስገረፋቸው፡፡ ደማቸውም እንደ ውኃ ምድር ላይ ፈሰሰ፡፡ ከደማቸውም እሳት ወጣና እስከ ሦስት ቀን ድረስ ወደላይ እየነደደ ቆየ፡፡ በዚህም ንጉሡ እጅግ ደንግጦ ብዙ ውኃ ከወንዝ እየቀዱ እሳቱን እንዲያጠፉ አዘዘ፡፡ የበዛ ውኃም ባፈሰሱበት ጊዜ የእሳቱ መጠን ይበልጥ ይጨምር ነበር፡፡ ዳግመኛም ብዙ ጨምረው ውኃ እየቀዱ ቢያፈሱበትም ማጥፋት እንዳልተቻላቸው ባየ ጊዜ ንጉሡ የወንዙን ውኃ በቦይ መልሰው እንዲያመጡ አዘዘ፡፡ ንግሥቲቱ ዛንመንገሣም ንጉሥ ዐምደ ጽዮንን "የእግዚአብሔርን ቁጣ አታስተውልምን" ብላ ተናገረችው፡፡ ወዲያውም ነጭ የዝንብ መንጋ መጥቶ የንጉሡን ፈረሶችና በቅሎዎች ነከሳቸውና ሞቱ፡፡ ንጉሡም ፈርቶ በሌሊት ሸሽቶ ወጣ፡፡ ቅዱሳኑንም አንድ መውጫና መግቢያ ብቻ ባላት ደራ ወደምትባል ታላቅ ተራራ ቦታ አውጥተዋቸው እንዲያስሯቸው አደረገ፡፡
❤ በዚያም የሚኖሩት አሕዛብ ስለሆኑ ክርስቶስንም አያውቁም፣ ነፍሰ ገዳዮችም ነበሩ፡፡ ንጉሡም አቡነ በጸሎተ ሚካኤልንና ልጆቹን ይገድሏቸው ዘንድ ወደ እነርሱ መልእክት ይልክ ነበር፡፡ ነገር ግን አባታችን ወንጌልን ሰበከላቸውና አሳምኖ የክርስቶስ ተከታዮች አደረጋቸው፡፡ እነርሱም ወደ ንጉሡ ሄደው ክርስቲያን እንደሆኑ ነገሩት፡፡
❤ የአባታችን የተአምሩ ዜና በሀገሩ ሁሉ በተነገረ ጊዜ ንጉሡ ቅዱሳንን አሳደው ስሙ ዝዋይ ወደሚባል ታላቅ ባሕር ውስጥ ያገቧቸው ዘንድ አዘዘ፡፡ አባታችንና ልጆቹንም አረማዊያን ወዳሉበት ደሴት አስገቧቸው፡፡ ከብዙ ጊዜም በኋላ ከግዞት መልሰው በማውጣት በሴዋ አውራጃ እንዲያስተምሩ ፈቀደላቸው፡፡ ንጉሡም ናርእት የሚባሉ ሰዎችን በጦር ይወጋቸው ዘንድ ተነሣ፡፡ እነዚህም ሰዎች አስቀድመው በአቡነ በጸሎተ ሚካኤል ስብከት በጌታችን ያመኑ ክርስቲያኖች ሆነዋል፡፡ ንጉሡም ድጋሚ አባታችንን አሠራቸውና ማስፈራራት ጀመረ፡፡ አቡነ በጸሎተ ሚካኤል ግን የንጉሡን ማስፈራራት በመናቅ ተናገሩት፡፡ እንዲህም አሉት፡- "በጦር ብታስወጋኝ ሕዝቅኤልን አስበዋለሁ፤ አንበሶች እንዲበሉኝ ብታዝ ዳንኤልን አስበዋለሁ፤ ወደ እሳት ውስጥ ብትጥለኝ አናንያን አዛርያንና ሚሳኤልን አስባቸዋለሁ፤ በእንጨት መቁረጫ መጋዝ እንዲቆርጡኝ ብታዝ ኢሳይያስን አስበዋለሁ፤ በድንጋይ እንዲወግሩኝ ብታዝ ኤርሚያስን አስበዋለሁ፤ በሰይፍ አንገቴንም እንቆርጡኝ ብታዝ በወንደሙ ፊሊጶስ ሚስት ምክንያት የገደለው የዘካርያስ ልጅ ዮሐንስ መጥምቅን አስበዋለሁ፤ ልዩ ልዩ መከራዎችን ብታጸናብኝም መከራ የተቀበሉትን ሐዋርያትንና ሰማዕታትን አስባቸዋለሁ" ብለው ለንጉሡ መለሱለት፡፡
❤ ንጉሡም ከዚህ በኋላ አባታችንን "ይቅር ይበሉኝ" አላቸው፡፡ በአባታችን ምክር ብዙ የንጉሡ መኳንንቶችም ክፉ ሥራቸውን በመተው በንስሓ ተመለሱ፡፡ ንጉሡም አንዲት ሚስቱን ለጭፍራው አሳልፎ ሰጥቶት ነበርና እርሷም አባታችንን ስታገኛቸው ንስሓ ገባች፡፡ ንጉሡም ይህቺ የተዋት ሚስቱ ንስሓ እንደገባች ሲሰማ "ዛሬ ሌሊት ከእርሷ ጋር ተኝቼ ንስሓዋን አስተዋታልሁና ይዛችሁ አምጡልኝ" ብሎ ጭፍሮቹን ላከ፡፡ አባታችንም ሴቲቱን በንስሓዋ ወደዋት ነበርና አሁን ንጉሡ በእርሷ ላይ ሊያደር ያሰበውን ልጆቹ ነገሩት፡፡ አባታችንም ይህን ሲሰማ የቀረበውን ማዕድ ሳይቀምሱ አስነስቶ ሁሉም እንዲጸልዩ አዘዘና እርሱም ቆሞ መጸለይ ጀመረ፡፡ በዚያችም ሌሊት ወዲያው ንጉሡ ድንገት በጠና ታመመ፡፡ ያንጊዜም ንጉሡ "ይህ ድንገኛ ሕመም የመጣብኝ አቡነ በበጸሎተ ሚካኤል ጸሎት ነው" ብሎ ያችን ሴት ካመጡበት ቦታ እንዲመልሷት አዘዘ፡፡
❤ ወደ አባታችንም በሔድ "አባቴ ሆይ! ይቅር በለኝ፣ ይህ ሕመም ያገኘኝ በአንተ የተማጸነችውንና ንስሐ የገባችውን ሴት በኃጢአት ላረክሳት ስላሰብኩ ነው፤ አሁንም ልጅቷን ወደነበረችበት መልሻታሁና አባቴ ሆይ ከዚህ በሽታዬ ከዳንኩ በሕግህ እኖራለሁ" ብሎ መልእክተኛ ላከ፡፡ አባታችንም የቤተ መንግሥቱን ካህናተ ደብራዎች ወቀሳቸው፡፡ "ከእናንተ በቀር ይህን ንጉሥ የሚያስተው የለም ያለ ሥራው እያሞገሳችሁ በኃጢአት ላይ ኃጢአት እንዲሠራ የምታድርጉ እናንተ ናችሁ" ብለው በተናገሯቸው ጊዜ ደብተራዎቹም "እኛም በሕግህ እንኖራለን ይቅር በለን፣ ጉሡንም ይቅር ብለህ ከመጣበት ደዌው ፈውሰው" ብለው ለመኗቸው፡፡ አቡነ በጸሎተ ሚካኤልም "ንጉሡ ከኃጢአቱ ተመልሶ ንስሓ እንደማይገባ እኔ ዐውቃለሁ፡፡ ነገር ግን ሞቱ በእኔ ቃል ምክንያት እንዳይሆን እግዚአብሔር ከበሽታው ይፈውሰው" አሏቸው፡፡ ካህናቱም "ከደዌው በሚድን ነገር እንወስድለት ዘንድ የእግርህን ትቢያ ስጠን" አሏቸው፡፡ አባታችንም "የእግሬን ትቢያ አልሰጣችሁም ነገር ግን ሂዱ ከደዌው ሁሉ ተፈውሶ ታገኙታላችሁ" አሏቸው፡፡ ካህናቱም ወደ ቤተ መንግሥት በሄዱ ጊዜ ንጉሡን ከደዌው ፍጹም ተፈውሶ አገኙት፡፡
❤ አንዲት ድንግል መነኵሲት ከክብር ያሳነሳት ርጉም የሆነ አንድን መነኩሴ አገኙትና አባታችን መክረው ገሥረው ንስሓ ግባ አሉት፡፡ ነገር ግን እርሱ በወቅቱ እሺ ብሎ ንስሓ ሳይገባ ቀረ እንዲያውም በአባታችን ላይ ክፉ ያስበ ጀመር፡፡
❤ እንዲሁም ክህነት ሳይኖረው በውሸት ካህን ነኝ እያለ ሲቀድስ የነበረን አንድን ዲያቆን አባታችን አግኝተው "የክርስቶስን ሥጋ ቅዱሳን መላእክትስ እንኳን መንካት የማይቻላቸውን አንተ በውሸት ለመንካት እንዴት ደፈርክ…." ብለው በመምከር ንስሓ እንዲገባ አዘዙት፡፡ ነገር እነዚህ ሁለት ክፉ ሰዎች ንስሓ ከመግባት ይልቅ በአባታችን ላይ ክፋትን ያስቡ ጀመር፡፡ ወደ ንጉሡም ዘንድ ሄደው "በጸሎተ ሚካኤል የሚባለው መነኩሴ "ፈርዖንና ሠራዊቱን በባሕር ያሰጠመው እንደዚሁ ሁሉ ይህንንም ንጉሥ ያስጥመው" እያለ ይረግምሃል" ብለው አወሩለት፡፡
❤ ንጉሡም ተቆጥቶ አባታችንን ከነልጆቻቸው አስረው ያመጧቸው ዘንድ አዘዘ፡፡ አስረው አምጥተውም በንጉሡ ፊት ኦቆሟቸው፡፡ ንጉሠም አባታችንን "ለምን ትረግመኛለህ" ሲላቸው እሳቸውም "ጠላትህን ውደድ ያለንን የአምላክ ሕግ እንከተላለን እንጂ አንተንስ የረገመህ የለም፤ ጳውሎስም በምንኵስና ሥርዓት ሰይጣንንም እንኳ አትርገሙ ብሏል፡፡ ሰይጣንን እንኳ መርገም የሚከለክል ከሆነ ንጉሥን እንዴት ይረግሙታል" አሉት፡፡ ንጉሡም የከሰሱትን ሁለቱን ሰዎች አምጥቶ ለአባታችን አሳቸው፡፡ እሳቸውም የእያንዳንዳቸውን ክፉ ሥራ ለንጉሡ ነገሩት፡፡ ንጉሡም ይርታ ጠይቆ አባታችንን በሰላም አሰናበታቸው፡፡
❤ ከዚህ በኋላ ጠላት ዲያብሎስ በቅዱሳን ላይ ክፉ ሥራ ይሠራ ዘንድ በንጉሡ ልብ ክፉ ሀሳብን አስነሣ፡፡ ንጉሡም "እኔ በምገዛው አገር ሁሉ ያሉ ቅዱሳንን አምጧቸው" ብሎ በሕዘቡ ሁሉ ትእዛዝ አስተላለፈ፡፡ ቅዱሳንንም ሁሉ ሰብስበው አመጧቸው፡፡ አቡነ ዘአማኑኤል ከልጆቹና ከአባታችን ከአቡነ በጸሎተ ሚካኤል ጋር ደረሰ፡፡ ንጉሡም በቁርባንና በጸሎት ከእኔ ጋር ተባበሩ (አንድ ሁኑ) የምትፈልጉትን ሁሉ አሟላላችኋለሁ፣ ከእኔ ጋር መተባበርን እምቡ ካላችሁ ግን ወደ እርሱ እሰዳችሁ ዘንድ ሊቀ ጳጳሱ አዘዋልና ወደ ግብጽ በረኃብና በጥም ትሄዳላችሁ በመንገድም ሰውን የሚገድሉ ሽፍቶች አሉ" አላቸው፡፡ የአቡነ ዘአማኑኤል ደቀ መዛሙርት ግን "እኛ ከአንተ ጋር እንተባበራለን፣ ያዘዝከንን ሁሉ እንፈጽማለን" ብለውት የሚሹትን ሁሉ ሰጥቷቸው በሰላም አሰናበታቸው፡፡
❤ መምህራቸው አቡነ ዘአማኑኤል ግን ይህን አልፈልግም ብሎ ብቻውን ተሰደደ፡፡ ንጉሡም ወደ አቡነ በጸሎተ ሚካኤል መኳንንቱን በመላክ ከእርሱ ጋር እንዲተባበሩ ወርቅና ብሩን ላሞችንና ጥሪቶችን ሁሉ እንደሚሰጣቸው ካልሆነ ግን ወደ ኢሩሳሌም መንገድ እንደሚልካቸውና በመንገድም በሽፍቶች
1 161
ባ ገብረ ናዝራዊ ገዳምበሄድም ከጻዲቁ ጋር ተነጋገረ፡፡ ከሰንበት በቀር እህል ባለመቅመስ 40 ቀንና 40 ሌሊት በመጾም ሱባኤ በያዘ ጊዜ እግዚአብሔር የተለያዩ ምሥጢራትን ይገልጥለታል፡፡ በሄኖክ መጽሐፍ ላይ ተጽፎ ያለው የሰማይ ምሥጢር ሁሉ ተገለጠለት፡፡ የፀሐይ፣ የጨረቃ፣ የብርሃናት አፈጣጠራቸው፣ የንፋስ መስኮቶቸን ሁሉ በግልጥ ባየ ጊዜ ነቢዩ ሄኖክን "ሄኖክ ሆይ የራእይህ ምሥጢር እንደዚህ ብሩህ ነውን? የምሥጢርህ መሰወር እንዲህ ግልጥ ነውን?" ይለዋል፡፡ ዳግመኛም የነቢያት የትንቢታቸው ራእይ ይገለጥለት ዘንድ 40 ቀንና 40 ሌሊት በመጾም ሱባኤ በያዘ ጊዜ የመጻሕፍቶቻቸው ምሥጢር ይገለጥለታል፡፡
❤ ከዚህም በኋላ አቡነ በጸሎተ ሚካኤል በመማለጃ (በጉቦ) ክህነት በሚሰጥ ጳጳስ ምክንያት በሐዋርያት ግዝት ዓለም ሁሉ በግዝት እንደሚኖር ተመለከተ፡፡ ወደ ጳጳሱ አባ ዮሐንስ ዘንድ ሄደና አገኘው፡፡ ጳጳሱም "ልጄ በጸሎተ ሚካኤል ደህና ነህን?" አለው፡፡ አባታችንም "ደህና ነኝ" ባለው ጊዜ ጳጳሱ "ስለምን መጣህ?" አለው፡፡ አቡነ በጸሎተ ሚካኤልም ሰው ሁሉ ከአጠገባቸው እንዲርቅ ካደረገ በኋላ ጳጳሱን እንዲህ አለው፡- "ቅዱሳን ሐዋርያት በሲኖዶሳቸው መጽሐፍ "በመማለጃ ክህነትን የተቀበለና የሰጠ የተለየ የተወገዘ ነው" ያሉትን አልሰማህምን?" አለው፡፡ ዳግመኛም "እጄን በጫንኩበት መንፈስ ቅዱስ ይወርድ ዘንድ ተናገሩ ብሎ በሐዋርያት እግር ሥር ወርቁን አምጥቶ ባፈሰሰው ጊዜ ሲሞን መሠርይን ጴጥሮስ እንዳወገዘው አልሰማህምን? ጴጥሮስም "ወርቅህና ብርህ ለጥፋት ይሁንህ፣ የእግዚአብሔር ጸጋ በወርቅ የምትገዛ ይመስልሃልን?" አለው፡፡ በመራራ መርዝ ተመርዘህ አይሃለሁና"፡፡ ሐዋ 8፡19፡፡ "አባቴ ሆይ የውኃ ምንጭ የፈሰሰ የደፈረሰ እንደሆነ የምፈሰውም ውኃ ሁሉ ይደፈርሳል፡፡ ምንጩ ንጹሕ ከሆነ ግን የውኃው ፈሳሽም ሁሉ የጠራ ይሆናል፡፡ አንተ በሐዋርያት ውግዘት ብትገባ ሁሉም የተወገዘ ይሆናል" አለው፡፡ ጳጳሱም ተቆጥቶ "አንተ ከእኔ ተማር እንጂ ለእኔ መምህር ልትሆነኝ ትፈልጋለህ?" በማለት ተናገረው፡፡ በወንጌል ላይ "እናንተ ግብዞች ጸሐፍትና ፈሪሳውያን መንግሥተ ሰማያትን በሰው ፊት ስለምዘጉ ወዮላችሁ፣ እናንተ አትገቡም የሚገቡትንም ትከለክሏቸዋላችሁ" ያለው የእግዚአብሔር ቃል በእርሱ ላይ ደረሰ፡፡ ማቴ 23፡14፡፡
❤ ከዚህም በኋላ አቡነ በጸሎተ ሚካኤል ወደ ካህናተ ደብተራ በመሄድ ከንጉሡ ጋር ያገናኙት ዘንድ ጠየቃቸው፡፡ የቤተ መንግሥት ካህናትም ለንጉሡ ነግረውለት አስጉት፡፡ አባታችንም ንጉሡን "መንግሥትህ በግዝት ጨለመች፣ ሐዋርያት ጥምቀትም ቢሆን ወይም ክህነት በመማለጃ (በጉቦ) የሚሰጥንና የሚቀበልን አስቀድመው ሐዋርያት አውግዘዋል" አለው፡፡ ዳግመኛም "እነሆ ይህ ጳጳስ የሐዋርያትን ትእዛዝ ተላልፎ በጉቦ ክህነት ይሰጣል፣ ጳጳሱም በሐዋርያት ግዝት ከገባ በእጁ የተጠመቁና የተሾሙት ሁሉ የተወገዙ ይሆናሉ፣ እንደዚሁ ዓለሙ ሁሉ በውግዘት ውስጥ ይኖራል" አለው፡፡
❤ ንጉሡም ሦስቱ አንድ ላይ ሆነው እንዲመጋገሩ ቀጠሮ ሰጠውና በሌላ ቀን ሦስቱም ተገናኙ፡፡ ጳጳሱም ለንጉሡ "ይህ በጸሎተ ሚካኤል እኔን ከሹመቴ አንተን ከመንግሥትህ ሊሽረን ይፈልጋል ስለዚህ ልጄ የምነግርህን ስማኝ አስረህ ወደ ትግራይ ይወስዱት ዘንድ እዘዝ" አለው፡፡ ንጉሡም የጳጳሱት ክፉ የሀሰት ምክር በመስማት "ይሁን አንተ እንዳልከው ይሁን" በማለት አቡነ በጸሎተ ሚካኤልን በጽኑ ማሠሪያ አስረው በግዞት ወደ ሳርድ ይወስዱት ዘንድ አዘዘ፡፡ ጭፍሮቹም እንደታዘዙት አደረጉና አባታችን በዚያ በግዞት ሁለት ዓመት ታስሮ ቆየ፡፡ ከዚያም ወደ ጽራይ ምድር ወሰዱትና ቆራር በተባለ ቦታ ለተሾመው ሰው "እንደ ንጉሡ ትእዛዝ ይህንን መነኩሴ እሰረው" ብለው ሰጡት፡፡ የሀገሩ ሰዎችም አቡነ በጸሎተ ሚካኤልን እጅግ ወደዱትና ወደ ጽራር ሀገር ገዥ ሄደው እንዲፈታው ለምነው ከእስራቱ አስፈቱት፡፡ በሀገራቸውም ወንጌልን አስተምሮ ብዙ ተአምራት እያደረገላቸው ከቆየ በኋላ ወደ ልጁ ሳሙኤል ለመሄድ ተነሣ፡፡ ሲሄድም አቡነ ገብረ ናዝራዊ ጋር ደረሰና አብረው ሳሙኤል ጋር ደረሱ፡፡
❤ አቡነ በጸሎተ ሚካኤል በቅዳሴ ጊዜ ጌታችን በሕፃን ልጅ አምሳለ በመንበሩ ተቀምጦ ስለሚያየው ሁልጊዜ ሲቀድስ ያለቅሳል፡፡ አንድ ቀን አባታችንን ሲቀድስና ሕፃኑን በመንበሩ ላይ ሲሠዋው ወንድሞቹና ልጆቹ አይተውት በድንጋጤና በፍርሃት ሆነው አልቅሰዋል፡፡ የሕፃኑንም ሥጋ በፈተተው ጊዜ የአባታችን እጁ በለመለመ ሥጋ ይመላል፡፡ ቅዳሴውም ከተፈጸመ በኋላ ሁሉም መጥተው ሥጋወደሙን በፍርሃት ይቀበላሉ፡፡ ከእነርሱም ውስጥ አስቀድመው ስለ ሥጋወደሙ መለወጥ ጥርጣሬ የነበራቸው ሰዎች ስለነበሩ የእነርሱን ጥርጣሬ ዐውቆ አባታችን ቅዳሴውን ከፈጸመ በኋላ "ኅብስቱ የክርስቶስ ሥጋ ወይኑም ደሙ መሆን ይችላልን እያላችሁ በልባችሁ ስታስቡ አይቻለሁና ይኸው ዛሬ በግልጽ እንዳያችሁት አማናዊ ሆኖ ይለወጣልና ተጠራጣሪ አትሁኑ" ባላቸው ጊዜ እግሩ ሥር ወድቀው "አንተ ብፁዕ ነህ የተሸከመችህም ማኅፀን ብፅዕት ናት… " ብለው ይቅር እንዲላቸው ለመኑት፡፡
❤ አባታችንም ወንጌልን አስተማራቸው፡፡ መነኰሳት ልጆቹ ሩቅ ቦታ እየሄዱ ውኃ በመቅዳት ቢቸገሩ ውኃን አፍልቆላቸዋል፡፡ ከዚህም በኋላ ሰዎቹ አንድ ነገር ልንነግርህ እንወዳለን አሉት፡፡ አቡነ በጸሎተ ሚካኤልም ንገሩኝ ባላቸው ጊዜ የአባቱን ሚስት ስላገባው ንጉሥ ነገሩትና ሄዶ እንዲያስተምረው እንዲገሠጸው ለመኑት፡፡ አባታችንም "በጽኑ ማሰሪያ ታስሬ በእስር ስለነበርሁ አልሰማሁም" ካላቸው በኋላ ሄዶ ቢሰማው እንደሚመክረው ባይሰማውና ባይመለስ ግን እንደሚያወግዘው ነገራቸው፡፡ አባታችንም ልጆቹን አስከትሎ ወደ ንጉሡ ዘንድ ሄደ፡፡ አቡነ በጸሎተ ሚካኤል "ንጉሡ የአባቱን ሚስት በማግባቱ ሄደን ስንገሥጸው መከራ ቢያጸናብን ከሰማዕትነት ይቆጠርልናል" ብሎ ሲነግራቸው ከሰማይ መንፈስ ቅዱስ ወርዶ በሁሉም በላያቸው ላይ ሲወርድ አባታችን በግልጽ ተመለከተ፡፡ በረኃብ በጥም ሆነው ከተጓዙ በኋላ ትግራይ ሰወን ከምትባል ሀገር ደረሱ ንጉሡ ከዚያ ነበረና፡፡ ንጉሡም ቅዱሳኑ መክረው ሊመልሱት ካልሆነም ሊያወግዙት መምጣታቸውን በሰማ ጊዜ ጭፍሮቹን ልኮ ቅዱሳኑን ወደ እርሱ እንዲያመጧቸው አዘዘ፡፡
❤ ለማስፈራራትም ብዙ ጦረኛ ጭፍሮችንና የታሰሩ አስፈሪ አንበሶችን በፊቱ አቆመ፡፡ ቅዱሳኑንም "ስለምን ወደዚህ ከተማ መጥታችኋል?" አላቸው፡፡ አቡነ በጸሎተ ሚካኤልም "እውነትን ስለማጽናት ከአንተ ጋር ለመነጋገር መጥተናል" አሉት፡፡ ንጉሡም እሺ ንገሩን በላቸው ጊዜ አባታችን የእግዚአብሔርን ትእዛዝ ስለጠበቁ ደጋግ ነገሥታት ከመጽሐፍ ቅዱስ በመጥቀስ ንጉሡን አስተማሩት፡፡ ትእዛዙንም ያልጠበቁትን አመፀኞችን እንደቀጣቸው ነገሩት፡፡ በመጨረሻም "የአባትህን ሚስት ሀፍረተ ሥጋ አትግለጥ፣ የአባትህ ሀፍረተ ሥጋ ነውና" የሚለውን ኦሪት ዘሌ 18፥6 በመጥቀስ አስተማሩት፡፡ ዳግመኛም "ከአባቱ ሚስት ጋር የተኛ የአባቱን ሀፍረት ገልጧልና መሞትን ይሙት ሁለቱም በደለኞች ናቸውና" የሚለውን የሙሴን ሕግና ሌላም ከሐዲስ ኪዳን እየጠቀሱ አስተማሩት፡፡
❤ አባታችን ካስተማሩት በኋላም "የክርስቲያን ሚስቱ አንድ ብቻ ናት አንተ ግን ብዙ ሚስት አግብተህ የአባትህንም ሚስት አግብተሃልና ሕግ ተላልፈሃል" አሉት፡፡ ንጉሡም ተምሮ ከመመለስ ይልቅ በታላቅ ቁጣ ሆኖ ቅዱሳኑን ይደበድቧቸው አዘዘ፡፡ ሲደብድቧቸውም ታላቅ ጩኸት ተነሣ፡፡ ለየብቻ አስረው ካሳደሯቸው በኋላ ንጉሡ ለየብቻ ወደ እርሱ እያስመጣ አናገራቸው፡፡ እያንዳንዳቸውን
1 161
❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤
❤ ሐምሌ ፳፩ (21) ቀን።
❤ እንኳን ለኢትዮጵያውያን ጻድቃን ለአባታች ለአቡነ በጸሎተ ሚካኤል ለዕረፍት በዓል፣ ደግ ለሆነ በጎ ምግባር ላለው ምፅዋት መስጠትም ለሚወድ መግስቱን ትቶ ለመነነው ለቅድስት ለሮማነ ወርቅ ልጅ ለንጉሥ ላእከ ማርያም ለዕረፍት በዓል፣ ለአባታች ለከፋሌ ባሕር ለአቡነ ኤዎስጣቴዎስ ለልደት በዓል በሰላም አደረሰን።
+ + +
❤ አቡነ በጸሎተ ሚካኤል፦ ይኸውም ከካህናት ወገን የሆነው አባቱ ማርቆስ ሲሆን እናቱ እግዚእ ክብራ ትባላለች፡፡ እግዚእ ክብራም ወደ ወላጆቿ በሄደች ጊዜ "ከመኳንንቶቹ ለአንዱ እናጋባታለን" ብለው ወደ ባሏ ተመልሳ እንዳትሄድ ከለከሏት፡፡ ማርቆስም ስለዚህ ነገር አዝኖ ወደ ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን ሄዶ ሚስቱን እንደከለከሉት ለአንድ መነኵሴ ነገረው፡፡ መነኵሴውም ሄዶ ቢጠይቃቸው ወላጆቿ ድጋሚ ለመነኵሴውም ከለከሉት፡፡ ማርቆስም እየተመላለሰ መነኵሴውን ቢያስቸግረው ይዞት ሄደ ነገር ግን ወላጆቿ ጥላቻቸውን አበዙባቸው፡፡ መነኵሴውም "ማርቆስንና ሚስቱን ለአንድ ቀን ብቻ ሁለቱን አንድ ላይ ላናግራቸው" በማለት ይዟቸው አደረ፡፡ እርሱም በማደሪያው እንዲያድሩ ከነገራቸው በኋላ "በዚህች ሌሊት ሩካቤ ሥጋ ሳትፈጽሙ እንዳታድሩ" አላቸው፡፡ ሁለቱም በመነኵሴው ቤት አድረው ሳለ ሌሊት መልአኩ ቅዱስ ሚካኤል ለማርቆስ ተገለጠለትና "ሚስትህ ወንድ ልጅ ትወልዳለች፣ በወለደችም ጊዜ ስሙን በጸሎተ ሚካኤል ትለዋለህ፣ ለቤተ ክርስቲያንም ዐምድ ይሆናል" አለው፡፡ ማርቆስም ከእንቅልፉ በነቃ ጊዜ ከሚስቱ ጋር ተገናኘና አቡነ በጸሎተ ሚካኤል ተፀነሱ፡፡
❤ እግዚእ ክብራ ከፀነሰች በኋላ ፊቷ እንደፀሐይ የሚያበራ ሆነ፡፡ የታመሙ ሰዎችም ሆዷን በነኩት ጊዜ ይፈወሱ ነበር፡፡ በወለደችም ጊዜ በቤቷ ውስጥ ቀስተ ደመና ተተክሎ ታየ ሲሆን አስቀድሞ መልአኩ ስሙን እንዳወጣለት "በጸሎተ ሚካኤል" አሉት፡፡ አባቱም ካህን ነውና ምግባር ሃይማኖትን ጠንቅቆ እያስተማረ አሳደገው፡፡ በጸሎተ ሚካኤል ገና ሕፃን ሳለ መዝሙረ ዳዊትን፣ የነቢያት ጸሎትን በማዘውተር በጾም በጸሎት ሲጋደል ወላጆቹ "ይህ ሕፃን ልጃችን በረሃብ ይሞትብናል" በማለት በግድ እየገረፉ እንዲመገብ ያስገድዱት ነበር፡፡ በግድ አፉን ይዘው ምግብ ከጨመሩበር በኋላ "ይኸው ጾምህን ፈታህ" ሲሉት እርሱ ግን በሕፃን አንደበቱ "እኔ በፈቃዴ በአፌ ውስጥ ብጨምረው ጾሜን በሻርኩት ነበር፣ እናንተ በአፌ ውስጥ በግድ ከጨመራችሁት ግን ጾሜ አይሻርም" እያላቸው እስከ ማታ ይጾም ነበር፡፡
❤ ከዚህም በኋላ አባቱ ወደ ጳጳስ ዘንድ ወስዶ ዲቁና እንዲሾም አደረገው፡፡ ባደገም ጊዜ አባቱ ማርቆስ ሚስት ያጋባው ዘንድ ባሰበ ጊዜ አቡነ በጸሎተ ሚካኤል ሸሽቶ ወደ ገዳም ገባ፡፡ አበ ምኔቱም ከእርሱ ጋር አስቀምጦ የምንኩስናን ቀንበር ያሸክመው ዘንድ ብዙ ፈተነው፡፡ ወላጆቹም መጥተው አስገድደው ከገዳሙ ሊያወጡት ሲሉ እምቢ ቢላቸው እናቱ ዘመዷ ወደሆነው ንጉሡ ውድም ረአድ በመሄድ ስለ ልጇ ነገረችው፡፡ ንጉሡም ከወታደሮቹ ውስጥ በአለንጋ ይዞ የሚገርፍ ወታደር ላከላት፡፡ የተላከው ወታደርም በጸሎተ ሚካኤልን እየገረፈ በማስገደድ ከገዳም አውጥቶ ለወላጆቹ ሰጠው፡፡
❤ በጸሎተ ሚካኤልም በወላጆቹ ቤት ሳለ ወላጆቹን "እመነኵስ ዘንድ እስካልተዋችሁኝ ድረስ የቤታችሁን ምግብ አልበላም" ብሎ ማለ፡፡ አባቱም "ምግብ ካልበላህ" በማለት ጽኑ ድብደባ እየደበደበው ሦስት ቀንና ሦስት ሌሊት ቆየ፡፡ በጸሎተ ሚካኤልም ሦስቱንም ቀን እቤት ሳይገባ የቀን ፀሐይ ሐሩሩ የሌሊት ውርጭ ቅዝቃዜ እየተፈራረቀበት እቤትም ሳይገባ በደጅ ሆኖ በጾም በጸሎት ቆየ፡፡ በዚህም በአባቱ እጅ ሰማዕትነትን ተቀበለ፡፡ ጌታንም "ለምድር ሰላምን ያመጣሁ አይምሰላችሁ ሰይፍን ነው እንጂ፡፡ የመጣሁትስ ሰውን ከአባቱ ልጅንም ከእናቷ ልለይ ነው" ያለው ቃል በአባታችን ላይ ተፈጸመ፡፡ ማቴ 10፡34፡፡ አባቱ ማርቆስም ሥጋው እስኪያልቅ ድረስ በግርፋት ብዛት የልጁን ሀሳብ ለማስለወጥ ቢሞክርም እንዳልተሳካለት ሲያውቅ መልሶ ወደ ገዳሙ እንዲወስዱት አገልጋዮቹን ላካቸው፡፡
❤ አበ ምኔቱም መምህር ሆኖ ያገለግል ዘንድ እንዲማር ሲነግረው "እኔ መነኵሴ መሆን እንጂ መምህር መሆን አልፈልግም" በማለቱ ሳይስማሙ ቀሩና ወደ ሌላ ገዳም ወሰዱት፡፡ በዚያም እንዲሁ ሆነ፡፡ መልሰውም ወደ አባቱ ቤት ባመጡት ጊዜ ወላጆቹም ልጃቸው የምንኵስናን ሀሳቡን ይተወው ዘንድ ከአንድ ሴት ጋር ተማክረው በዝሙት እንድትጥለው ተነጋገሩ፡፡ ሴቷም ወደ በጸሎተ ሚካኤል ቀርባ በዝሙት ልትጥለው ብዙ ሞከረች፡፡ እርሱም ዐውቆ "ከእኔ ጋር አብረሽ መተኛት ደስ ካሰኘሽ እሺ ከእስራቴ ፍቺኝና እንተኛለን" አላት፡፡ ይህንንም ያላት ከታሰረበት እንድትፈታውና እንዲያመልጥ ነው፣ እርሷ የእውነት መስሏት ደስ አላትና ሄዳ ለወላጆቹ አብሯት እንዲተኛ መስማማቱን ነገረቻቸው፡፡ ነገር ግን በዚያች ሌሊት በጸሎተ ሚካኤል ማንም ሳያየው ተነሥቶ ከእናት አባቱ ቤት ወጥቶ ሄደ፡፡
❤ ከዚህም በኋላ የእግዚአብሔር መንፈስ ወደ ደብረ ጎል አደረሰው፣ ይኸውም ቀሲስ አኖርዮስ በብቸኝነት ሸሽቶ የሚጋደልባት ደብረ ጽሙና ናት፡፡ በጸሎተ ሚካኤልም በዚያ ከመነኰሰ በኋላ ጽኑውን የተጋድሎ ሕይወት መኖር ጀመረ፡፡ በጾም በጸሎት ሆኖ ቀን የጉልበት ሥራ ይሠራል ሌሊት ቆሞ ሲጸልይ ያድራል፡፡ 90 ሸክም የወይራ ፍልጥ እየፈለጠ ለቤተ ክርስቲያኑና ለአበ ምኔቱ ያመጣ ነበር፡፡ እንጨቱንም ሲቆርጥና ሲፈልጥ የብረት መቆፈሪያ ብቻ ይጠቀም ነበር እንጂ ስለታም የሆኑ ምሳርና መጥረቢያ አይጠቀምም ነበር፡፡ ምክንያቱም የወጣትነት ኃይሉና ሥጋው በእጅጉ ይደክም ዘንድ ነው፡፡ እንዲህም ሲሠራ ጾም፣ ጸሎት፣ ሥግደቱን አያስታጉልም ነበር፡፡ እስከ 4 ቀንም የሚጾምበት ጊዜ አለ፡፡ በጸሎተ ሚካኤል በእንደዚህ ያለ ጽኑ ተጋድግሎ 13 ዓመት በድቁና ሲያገለግል ኖረ፡፡ ከዚህም በኋላ ሥጋውን ማድከም ቢሳነው ከእኩለ ቀን ጀምሮ ፀሐይ ስታቃጥል አለቱ ሲግል ጠብቆ ሄዶ አለቱ ላይ ይተኛል፣ ከግለቱም የተነሣ የሥጋው ቆዳ እስኪበስል ድረስ በአለቱ ላይ ይተኛል፡፡
❤ በጸሎተ ሚካኤልም ከዚህ በኋላ ቅስና ተሾመ፡፡ ወደ ዋሻም ገብቶ በዓቱን አጸና፡፡ ከምግባር ትሩፋቱ የተነሣ ሌሎች ቅዱሳን ሁሉ አቡነ በጸሎተ ሚካኤልን እንደ መልአክ ያዩት ነበር፡፡ እርሱም ከሰው ጋር ላለመገናት ብሎ በቁመቱ ልክ ጉድጓድ ቆፍሮ መጻሕፍቱን ብቻ ይዞ ከዚያ ገባ፡፡ ቅዱሳንም መጥተው "አንተንም ሌሎችንም የምትጠቅመው ከዚህ ጉድጓድ ውስጥ ወተህ ብታስተምር ነው…" እያሉ በብዙ ልመና ከጉድጓዱ አወጡት፡፡ ከዚህም በኋላ የተሰወረውን ሁሉ በግልጥ የሚያይ ሆነ፡፡ ብዙ አስደናቂ ተአምራትን እያደረገ ወንጌልን ያስተምራል፡፡ ወደ በዓቱም እየገባ በቀን 8ሺህ ስግደትን ይሰግዳል፡፡ ከስግደቱም ብዛት የተነሣ ምድሪቱ ጎድጉዳ እስከ ጉልበቱ ትውጠው ነበር፤ ከሰገደበትም ቦታ ወዙ መሬትን ጭቃ እስኪያደርጋት ድረስ እንደ ውኃ ይፈስ ነበር፡፡
❤ ከመነኰሰበት ጊዜ ጀምሮ ተቀምጦ በእጁ ላይ አረፍ ይላል እንጂ በጎኑ ተኝቶ አያውቅም፡፡ ጌታችንም ተገልጦለት ማደሪያው ከጴጥሮስና ከጳውሎስ ጋር መሆኑን ነግሮታል፡፡ አባታችን ወደተለያዩ ገዳማት በመሄድ የቅዱሳንን በረከት ተቀበለ፡፡ ወደ ደብረ ዳሞ በመሄድ ከአቡነ አረጋዊ ጋር ተነጋገረ፣ ወደ አባ መጣዕ ቤት በመሄድ ከአባ ሊባኖስ ጋር ተነጋገረ፣ ወደ አ
1 161
❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤
❤ ሐምሌ ፳፩ (21) ቀን።
❤ እንኳን ለእመቤታችን ለቅድስት ድንግል ማርያም ለወራዊ በዓሏ፣ ለሊቀ መላእክት ለቅዱስ ዑራኤል መታሰቢያ በዓል፣ ጸጋ ጥበብ ማስተዋልና ዕውቀትን ለተሰጠው ለጃንደረባው ለቅዱስ ሱስንዮስ ለዕረፍት በዒልና አስተዋይ ለሆነ ለተመሰገነ ለአወ ክረስቶስ ለዕረፍት በሰላም አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰበው፦ ጌታችን በመስቀል ላይ ጎኑን በተወጋ ጊዜ ከነበረው ከመኰንኑ ዮራኖስ ከመታሰቢያው ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።
+ + +
❤ ቅዱስ ሱስንዮስ፦ ይህም ቅዱስ ጸጋ ጥበብ ማስተዋልና ዕውቀት የተሰጠው። ጃንደረባው ቅዱስ ከንጉሥ ቴዎዶስዮስ መኳንንቶች ውስጥ ነበር እርሱም ለሰው ሁሉ ርኅራኄ የሚያደርግ በሽተኞችንም የሚጐበኛቸውና የሚያረጋጋቸው ነበር። በችግርና በመከራ ስለሚኖሩትም ይረዳቸው ዘንድ ወደ ጌታ ይጸልይ ነበር።
❤ ስለ ከሀዲው ንስጥሮስ በኤፌሶን የኤጲስቆጶሳት ጉባኤ በተደረገ ጊዜ የጉባኤው ርእሰ መንበር የእስክንድርያው ሊቀ ጳጳሳት ቅዱስ ቄርሎስም በመጣ ጊዜ ይህ ቅዱስ ሱስንዮስ ኤጲስቆጶሳቱንና ቅዱስ ቄርሎስን ያገለግላቸው ነበር። በዚያን ጊዜም በአስጨናቂ ደዌ ተይዞ ታመመ በደዌውም ውስጥ ሳለ ቃል ከሰማይ ወደ ታላቅ ሠርግ እንደሚጠራው ራእይን አየ።
❤ ለቅዱስ ቄርሎስም ነገረው አባት ቄርሎስም "ያድንህ ዘንድ ስለ አንተ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን እለምነው ዘንድ ትፈቅዳለህን" አለው እርሱም "ገንዘቤን ለድኆች እስከምሰጥ አዎ አባቴ እሻለሁ" ብሎ መለሰ። ቅዱስ ቄርሎስም ጸለየለትና ከደዌው ዳነ።ተነሥቶም ገንዘቡን ሁሉ ለድኆችና ለችግረኞች ሰጠ። ከዚህም በኋላ ተመልሶ ተኛና በሰላም ሐምሌ 21 ቀን ዐረፈ። ቅዱስ ቄርሎስም በላዩ ጸሎት አድርሶ ገንዞ ቀበረው በአረፈባት በዚች ዕለትም መታሰቢያውን እንዲአደርጉለት አዘዘ። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱስ ሱስንዮስ በጸሎቱ ይመረን በረከቱም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን።
+ + +
❤ ቅዱስ አወ ክርስቶስና ሚስቱ፦ ይህም ቅዱስ አስተዋይ የሆነ የተመሰገነ ነወ። ሚስት በአገባ ጊዜም በጾምና በጸሎት እያገለገሉ በድንግልና በአንድነት ኖሩ በሌሊትም ማቅ ለብሰው እየብቻቸው ይተኙ ነበር በቀንም እርሱ በጎችን እየጠበቀ በዱር ይውል ነበር እርሷም ለእንግዳ ምግብ እያዘጋጀች ትውል ነበር።
❤ ከስምሪቱም በገባ ጊዜ የእንግዶችን እግር ያጥብ ነበር። እርሷም ማዕድን በማዘጋጀት ታገለግል ነበር። ፍጹማን መነኰሳትም ሥራቸው እንዴት እንደሆነ ይገልጥላቸው ዘንድ ወደ እግዚአብሔር በጠየቁ ጊዜ ገድላችሁ በአወ ክርስቶስና በሚስቱ ተጋድሎ መጠን አልደረሰም የሚል ቃል ከሰማይ ወደ እነርሱ መጣ።
❤ እነዚያ መነኰሳትም ሒደው ሥራቸውን መረመሩ በጭንቅ በግዳጅም ሥራቸውን ገለጡላቸው እያደነቁም ተመለሱ በእንዲህ ያለ ሥራም ኑረው በሰላም አረፉ። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳን ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን። ምንጭ፦ የሐምሌ 21 ስንክሳር።
+ + +
❤ "ሰላም ለኪ ተረሳዪተ ክብር በዑጻፌ። ወቀናቲተ ንጹሕ አምሳለ መክፌ። እምባሕረ ጊጋይ ስፉሕ እንተ አልቦቱ ጸናፌ። ማርያም አንበሌኪ ኀጣእኩ ኃዳፌ። ሶበ ተመየጥኩ ለፌ ወለፌ"። ሊቁ አርከ ሥሉስ (አርኬ) የሐምሌ 21።
+ + +
❤ የዕለቱ የማኅሌት ምስባክ፦"ወትቀውም ንግሥት በየማንከ። በአልባሰ ወርቅ ዑጽፍት ወኊብርት። ስምዒ ወለትየ ወርእዪ ወአጽምዒ ዕዝነኪ"። መዝ44፥9-10። የሚነበበው ወንጌል ሉቃ 1፥39-57።
+ + +
❤ የዕለቱ የቅዳሴ ምስባክ፦ "ብፁዕ ዘይሌቡ ላዕለ ነዳይ ወምስኪን። እምዕለተ እኪት ያድኅኖ እግዚአብሔር። እግዚአብሔር የዐቅቦ ወያሐይዎ ወያበድዖ ዲበ ምድር"። መዝ 40፥1-2። የሚነበበው ወንጌል ማቴ 19፥1-16 ወይም ሉቃ 1፥39-57። የሚቀደሰው ቅዳሴ የማርያም ቅዳሴ ነው። መልካም በዓል ለሁላችንም ይሁንልን።
❤ በየቀኑ ይህን ቴሌግራም ላይ ማግት ከፈለጉ ከታች ያለውን ሊኩን ይጫኑት።
https://t.me/Eotcw
1 161
ይም ለቤተክርስቲያንህ መባን መጻሕፍትንም ለሚሰጥ እኔ ኃጢአቱን ሁሉ እደመስስለታለሁ። ገድልህንም የሚጽፈውን፣ ወይም የሚያነበውን፣ የሚሰማውን፣ ወይም የሚገዛውን እኔ ስሙን በሕይወት መጽሐፍ እጽፋለሁ"።
❤ ከዚህም በኋላ ብዙዎች ከንጉሥ ሠራዊትና ከሕዝቡ ተሰብስበው በንጉሡ ላይ እንዲህ ብለው ጮኹበት "አንተ ከሀዲ እግዚአብሔር ያጥፋህ ከጠላቶቻችን ያዳነንን ኃያልና ጽኑዕ የሆነውን የከበረ ቴዎድሮስን ታሠቃየዋለህና" ይህንንም ብለው በክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ታመኑ ያን ጊዜም ንጉሥ ተቆጥቶ ሁሉንም አስገደላቸው ሰማዕትም ሆኑ የሰማዕትነት አክሊልንም ተቀበሉ።
❤ ከዚህም በኋላ ንጉሡ አዘዘ የብረት ዐልጋም አምጥተው ቅዱሱን በላዩ አስተኙት ከበታቹም እሳትን አነደዱ ቅዱስ ቴዎድሮስም እንዲህ ብሎ ጸለየ "አቤቱ ፈጣሪዬ ሠለስቱ ደቂቅን ከእሳት ምድጃ እንደ አዳንካቸው አድነኝ ። ወዲያውኑም ያ እሳት ጠፋ እንደ ንጋት ጊዜ ቊርም ሆነ። ከሰማይም እንዲህ የሚል ቃል መጣ "ክብር ይግባውና ከጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ኃይል የተሰጠህ ሆይ ጽና በርታ" ያን ጊዜም ቅዱሱ ተነሥቶ በንጉሡ ፊት ቆመ እንዲህም አለው ክብር ይግባውና ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ አድኖኛልና አንተ ከሀዲ እፈር" አለው። የንጉሡም የጭፍራ አለቃ ይህን በአየ ጊዜ "ክቡር ቴዎድሮስ ከሚያመልከው ክብር ይግባውና ከጌታ ከኢየሱስ ክርስቶስ በቀር ሌላ አምላክ የለም" ብሎ ጮኸ ርሱንም ራሱን አስቆረጠውና በሰማዕትነት ሞተ።
❤ ቅዱስ ቴዎድሮስንም ብዙ ከአሠቃየውና ማሠቃየቱ ከሰለቸው በኋላ ራሱን በሰይፍ እንዲቆርጡ ሥጋውንም እንዲአቃጥሉ አዘዘ። በጌታችንም ፈቃድ ከእናቱ ደጅ ወስደው እራሱን ቆረጡ ከእርሱም ደም፣ ወተትም ፈሰሰ ታላቅ እሳትም አንድደው ሥጋውን በውስጡ ጨመሩ እሳቱም ከቶ አልነካውም። እናቱም ለወታደሮች ብዙ ወርቅ ሰጥታ ሥጋውን ወሰደች በአማሩ ልብሶችም ገነዘችው እስከ መከራው ፍጻሜም በቤቷ ውስጥ አኖረችው።
❤ ከዚያ በኋላም አብያተ ክርስቲያናት ተሠሩለት ስብጥ በሚባል በአባቱ አገርም በተሠራች ገዳም ሥጋውን አኖሩ ከሥጋውም ድንቆችና ተአምራቶች ተደረጉ ታላቅ ፈውስም ሆነ። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በበሰማዕቱ ቅዱስ ቴዎድሮስ በጸሎቱ ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን። ምንጭ፦ የሐምሌ ስንክሳር።
+ + +
❤ "ሰላም ሰላም ለቴዎድሮስ ማር። ሊቀ ሠራዊት ክቡር። በረድኤተ አምላክ ባሕቲቱ እምሕዝበ በርበር። መስተጽዕናነ አፍራስ አኅለቀ ለእለሂ ዘእግር። እስከ ኢያትረፈ ነፋጼ ለዝክር"። ሊቁ አርከ ሥሉስ (አርኬ) የሐምሌ 20።
+ + +
❤ የዕለቱ ምስባክ፦ "ሕገ ለእግዚአብሔር ንጹሕ ወይመይጣ ለነፍስ። ስምዑ ለእግዚአብሔር እሙን ወያጠብብ ሕፃናተ። ኵነኔሁ ለእግዚአብሔር ርቱዕ ወያስተፌሥሕ ልበ"። መዝ18፥7-8። የሚነበበው ወንጌል ዮሐ6፥35-48። የሚቀደሰው ቅዳሴ የማርያም ቅዳሴ ነው። መልካም በዓል ለሁላችንም ይሁንልን።
❤ በየቀኑ ይህን ቴሌግራም ላይ ማግት ከፈለጉ ከታች ያለውን ሊኩን ይጫኑት።
https://t.me/Eotcw
1 161
❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤
❤ ሐምሌ ፳ (20) ቀን።
❤ እንኳን ለእናታችን ለእመቤታችን ለቅድስት ድንግል ማርያም ከተወለደች በኋላ በሰማንያ ቀን ከርግብ ገላግልቶች ጋር ወደ መቅደስ ለተወሰደችበት ቀን መታሰቢያ በዓልና ለታላቁና ለክቡር ለሆነ ለሠራዊት አለቃ ለሰማዕቱ ለቅዱስ ቴዎድሮስ ለዕረፍት በዓለ በሰላም አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰቡ፦ ከታአኪጦስ፣ ከእስክንድርያው ሊቀ ጳጳሳት ከቅዱስ ጢሞቴዎስ ከሙሴ፣ ከኢየሉጣ ከመታሰቢያቸውና ከሕፃኑ ከቅዱስ ቂርቆስ ጋር በሰማዕትነት ከአረፉ ከአራት መቶ አራት ሰማዕታት ከመታሰቢያቸው እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።
+ + +
❤ የሠራዊት አለቃ ሰማዕቱ ቅዱስ ቴዎድሮስ፦ የዚህ ቅዱስ አባት ስሙ ዮሐንስ ይባል ነበር። እርሱም ከላይኛው ግብጽ ሰጥብ ከምትባል መንደር ነበር። ወደ አንጾኪያ ከተማም ከሠራዊቱ ጋራ ወሰዱትና በዚያ ኖረ ከዚያች ከተማ መኳንንቶችም ያንዱን ልጅ አገባ እርሷም ጣዖትን ታመልክ ነበር። ባሏ ዮሐንስ የሚያመልከውን ግን አታውቅም ነበር።
❤ ከዚህም በኋላ ይህን ቅዱስ ቴዎድሮስን በወለዱት ጊዜ እናቱ ወደ ጣዖቷ አቅርባ አምልኮትዋን ልታስተምረው ፈለገች አባቱ ግን አስተወው ስለዚህም ተቆጥታ ባሏ ዮሐንስን አባረረችው ሕፃኑ ቴዎድሮስም በእናቱ ዘንድ ቀረ። አባቱ ዮሐንስም ልጁ ቴዎድሮስን ወደ እውነተኛ መንገድ ይመራው ዘንድ ወደ እግዚአብሔር ይጸልይና ይማልድ ነበር። ሕፃኑ ቴዎድሮስም በአደገ ጊዜ ጥበብን ተማረ ጌታችንም ልቡን ብሩህ አደረገለት ስሙ አውላኪስ ወደሚባል ኤጲስቆጶስም ሒዶ የክርስትና ጥምቀትን ተጠመቀ። እናቱም ታላቅ ኅዘንን አዘነች።
❤ ከዚህም በኋላ ስለ አባቱ በሕይወት እንዳለ ወይም እንደሌለ ጠየቀ ከአገልጋዮቹም አንዱ የአባቱን ሥራ በሥውር ነገረው። ቅዱስ ቴዎድሮስም ጐለመሰ እጅግም ብርቱ ሆነ ንጉሡም የሠራዊት አለቃ አድርጎ ሾመው። የፋርስ ሰዎችንም ሊወጋቸው በወጣ ጊዜ ይህ ቅዱስ ቴዎድሮስ በረታ የፋርስ ንጉሥንም ልጅ ይዞ ማረከው ከእርሱም ጋር ምሥራቃዊው ቴዎድሮስ ነበር የፋርስንም ሠራዊት አሳደዱአቸው።
❤ ከጥቂት ወራቶች በኋላም የፋርስና የበርበር ስዎች በሮማውያን ላይ ተነሡ። ብዙ ከተሞችንም አጠፉ ዲዮቅልጥያኖስም በሰማ ጊዜ እጅግ ፈራ ቴዎድሮስንም ጠርቶ "ምን እናድርግ ሠራዊትህን ሁሉ የጦር መሣሪያህንም ሁሉ ይዘህ ወደ ሰልፍ ውጣ" አለው። ቅዱስ ቴዎድሮስም እንዲህ ብሎ መለሰለት "አንተ የጦር መሣሪያህን ወስደህ ለአሽከሮችህ ስጣቸው እኔ ክብር ይግባውና በፈጣሪዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ርዳታ እተማመናለሁና የጦር መሣሪያ አልሻም እኔም ብቻዬን ወደ ጦርነቱ እሔዳለሁ ከወታደሮችም አንድ እንኳ ከእኔ ጋራ አልወስድም። በእጄ ውስጥ ያለ ይህ ጦር የተቀመጥኩበትም ፈረስ ይበቃኛል ከእኔ ጋራ የሚወጣ ፈጣሪዬ እርሱ ይረዳኛልና"። ንጉሡም "እነሆ ጠላቶቻችን ወደእኛ ቀርበዋልና የወደድከውን አድርግ" አለው።
❤ በማግሥቱም ቅዱስ ቴዎድሮስ ወደ ሰልፍ ወጣ ንጉሡም "የበርበርን ሰዎች ትወጋቸው ዘንድ ምን ኃይል አለህ እነርሱ ብዙ ወገኖች ናቸውና" አለው። ቅዱሱም ለንጉሡ እንዲህ ብሎ መለሰለት "አንተ ከሠራዊትህ ጋራ በዚህ ቁም እኔም ወደ እነርሱ ብቻዬን እሔዳለሁ በነርሱም ላይ ደሚደርሰውን ታያለህ። እኔ በእግዚአብሔር ኃይል እንደማጠፋቸው አውቃለሁና። ከእነርሱም አንዱ እንኳ ወደቤቱ አይመለስም"። ንጉሡም አደነቀ ከእርሱ ጋር ያሉትም አደነቁ።
❤ ከዚህም በኋላ ቅዱስ ቴዎድሮስ ወደ ጦርነቱ ብቻውን ሔደ ንጉሡንም ከእርሱ ሩቅ በሆነ ቦታ ተወው። ወደ በርበር ሰዎችም ደርሶ "ትዋጋላችሁን ወይስ በሰላም ወደ አገራችሁ ትመለሳላችሁ" አላቸው። እነርሱም "ከአንተ በቀር ለሰልፍ የመጣ አናይምና ከማን ጋር እንዋጋለን" አሉት እርሱም "ማንም ከእኔ ጋር እንዲመጣ አልሻም። እኔ ብቻዬን በፈጣሪዬ ኃይል አጠፋችኋለሁ" አላቸው። "ምናልባት ውሻ ልታባርር መጥተህ ይሆናል ከፈቀድህ ግን ወደ አንተ ይመጣ ዘንድ ከእኛ ውስጥ አንዱን ምረጥና ሁለታችሁ ተጋጠሙ" አሉት።
❤ ያን ጊዜ ቅዱስ ቴዎድሮስ ከፈረሱ ላይ ወረደና ፊቱን ወደ ምሥራቅ መልሶ እንዲህ እያለ ጸለየ "ጣዖታትን እስከ አጠፋቸውና የባቢሎንን ከተማ ዘንዶ እስከ ገደለው ድረስ ነቢዩ ዳንኤልን ያጸናኸው ጌታዬ አምላኬ ሆይ እንዲሁም ዛሬ ከእኔ ጋራ ሁን በረድኤትህም አጽናኝ አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ሆይ ምስጋና ይገባሀል ለዘላለሙ አሜን"።
❤ ጸሎቱንም በፈጸመ ጊዜ ጦሩን አንሥቶ በላዩ በመስቀል ምልክት አማተበ በፈረሱ ላይም ተቀምጦ በበርበር ሰዎች ላይ እንዲህ እያለ ጮኸ "እንዋጋ ዘንድ ወደኔ ኑ ክብር ይግባውና ለእግዚአብሔር ኢየሱስ ክርስቶስ እኔ ባሪያው ነኝ" እንዲህም እያለ በመካከላቸው ገብቶ የበርበርን ሰዎች አጠፋቸው ከእነርሱም ፈረሰኛንም ሆነ እግረኛን ምንም አላስቀረም የመኳንንቶቻቸውንም ቸብቸቦ ቆርጦ ወደ ንጉሡ አቀረበ። ንጉሡም ተቀበለው ሠራዊቱም ሁሉ ሰገዱለት። የአንጾኪያም ከተማ ሰዎች ሁሉም ወጥተው የበርበርን አገር ማረኩ።
❤ አውኪስጦስ በሚባል አገርም ሰዎች የሚያመልኩት ታላቅ ዘንዶ ነበረ ይበላቸውም ዘንድ በየዕለቱ ሁለት ሁለት ሰዎችን ይሰጡት ነበር ሁለት ልጆችም ያሏት አንዲት ክርስቲያናዊት መበለት ነበረች። እንዲበላቸውም ልጆችዋን ወሰደው ለዘንዶው አቀረቧቸው።
❤ በዚያን ጊዜም ቅዱስ ቴዎድሮስ ወደዚያ አገር ደረሰ ያች መበለትም በፊቱ ቆመች ልጆቿን ወስደው እንዲበላቸው ለዘንዶው እንዳቀረቧቸው በእርሷ ላይ የሆነውን ሁሉ አልቅሳ ነገረችው። ክርስቲያን እንደሆነችም ባወቀ ጊዜ በልቡ ይችን ሴት በድለዋታል እግዚአብሔርም ይበቀልላታል" አለ። ወዲያውኑም ከፈረሱ ወረደና ፊቱን ወደ ምሥራቅ መልሶ ጸለየ። ከዚህም በኋላ ወደ ዘንዶው ቀረበ የከተማው ሰዎችም ሁሉ ወደርሱ ይመለከቱ ነበር። በጦሩም ወግቶ ያንን ዘንዶ ገደለው። ርዝመቱም ሃያ አራት ክንድ ሆነ የመበለቷንም ልጆች አዳናቸው።
❤ ከዚህም በኋላ አባቱን ይፈልገው ዘንድ ወደ ላይኛው ግብጽ ሔደ አባቱንም አገኘው አባቱም ልጁ እንደሆነ በምልክቶቹ አወቀው ቅዱሱም አባቱ እስከ አረፈ ድረስ በዚያ ኖረ። ከዚህም በኋላ ወደ አንጾኪያ ከተማ ተመለሰ ንጉሥ ዲዮቅልጥያኖስንም ክብር ይግባውና ክርስቶስን እንደካደና ጣዖትን እንደአመለከ ክርስቲያኖችንም ሲአሠቃያቸው አገኘው።
❤ ከዚህም አስቀድሞ የከተማው ሰዎች የሚያመልኩትን ዘንዶ እርሱ እንደ ገደለው የአውኪስጦስ አገር ሰዎች ወደ ንጉሥ ከሰውት ነበርና ስለዚህ ንጉሥ ልኮ አስቀረበው። ቅዱስ ቴዎድሮስም ወደ ንጉሡ በቀረበ ጊዜ ንጉሡን እንዲህ ብሎ ዘለፈው "አንተ የክፉ ሥራ ሁሉ መገኛ የሆንክ ሰማይንና ምድርን የፈጠረ የክብር ባለቤትን ትተህ የረከሱ ጣዖታትን ያመለክ የኃጢአት ልጅ ሆይ ወዮልህ እግዚአብሔርም ፈጥኖ መንግሥትህን ያጠፋታል"።
❤ በዚያን ጊዜም ንጉሡ ተቆጥቶ ከመሬት ላይ ጥለው ይገርፉት ዘንድ ወታደሮችን አዘዛቸው። ይህንንም አደረጉበት ደሙም እንደ ውኃ ፈሰሰ። እጆቹንና እግሮቹንም ከግንድ ጋር ቸነከሩት። በሥቃይም ውስጥ ሳለ ከእግዚአብሔር የታዘዘ የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤል ወደርሱ ወረደ እንዲህም አለው "ጽና እነሆ የገድልህ ፍጻሜ ቀርቦአል ሥጋህ በውስጡ በሚኖርበትም ቦታ ድንቆችና ተአምራቶች ይገለጣሉ" እነሆ ክብር ይግባውና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እንዲህ ብሎ ቃል ኪዳን ሰጠህ "መታሰቢያህን ለሚያደርግ ሁሉ፣ ወይም በስምህ የተራበ ለሚያጠግብ፣ የተጠማውን ለሚያጠጣ፣ ወ
1 161
" ጌታ ሆይ እርሻውን አቃጥለህ ሰብሉን ብትባርክ ምን ይጠቅማል ? ዛፉንስ ቆርጠህ ቅርንጫፉን ብትባርክ ምን ይረባል ? እናቴ እርሻ ናት እኔ ሰብል ነኝ ፡፡ እናቴ ዛፍ ናት እኔ ቅርንጫፍ ነኝ ፡፡ እባክህን እናቴ ብትክድ እኔ ባምን ምን ይጠቅማል? ጌታ ሆይ የእናቴን ልብ በሃይማኖት አጽናልኝ "
(ሕጻኑ ቅዱስ ቂርቆስ ስለ እናቱ ቅድስት ኢየሉጣ የጸለየው ድንቅ ጸሎት)
እንኳን ለሕጻኑ ቅዱስ ቂርቆስ እና ለእናቱ ቅድስት ኢየሉጣ በዓል በሰላም አደረሳቹ
1 161
ሊቀመላዕክት ገብርኤል
ሊቀመላዕክት ገብርኤል ዘአብሰራ ለድንግል
#ሀያል_ሀያል*4 #ሰዳዴ_ሳጥናኤል*2 ሀያል መልዐከ ሀይል
ለመቀላቀል_ሰማያዊውን_ይጫኑ
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
https://t.me/Eotcw
1 161
#ገብርኤል_ኃያል
ገብርኤል ኃያል መልአከ ሰላም መልአከ ብሥራት
የምታወጣ የእግዚአብሔርን ሕዝብ ከሚነድ እሳት
ፍቅርህ ተስሏል በልባችን
ፊትህ ቆመናል ባርከን ብለን
#አዝ...
የጽናታቸው ዝናው ሲሰማ
ከዛ ባቢሎን ከሞት ከተማ
ህፃናት ሳሉ በራ እምነታቸው
ቆመህ ተገኘህ መሐከላቸው
#አዝ...
ውኃው ሲዘል ቢያስደነገጥም
በጋኖቹ ውስጥ ቢነዋወጥም
ፀንተው ዘመሩ ልጅና እናቱ
አንተ ስትደርስ ከዚያ ከእሳቱ
#አዝ...
ቂርቆስም ፀና ሞተን ሳይፈራ
አንተ ስላለህ ከነርሱ ጋራ
አትፍሪ አላት ስለምን ትፍራ
አምነው ድል ነሱት ያንን ተራራ
#አዝ...
እኔም አምናለሁ አድነኝ ብዬ
ፈጥነህ አማልደኝ ከቸር ጌታዬ
ክፉውን ዘመን የማልፍበት
ፅናቱን ስጠኝ ድል ልንሳበት
ለመቀላቀል_ሰማያዊውን_ይጫኑ
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
https://t.me/Eotcw
1 161
#የራማው ልዑል
የራማው ልዑል ገብርኤል (2)
ተመላለስ መሐላችን ስምህን ጠርተን ንአ ስንል (2)
ብርሃን ልብሱ እሳታዊ መልአክ
አንተ አማልደን ከመሃሪው አምላክ (2)
#አዝ….
የምስራች ነጋሪ ድንቅ ልደት አብሳሪ
የጽድቅ ፋና የምህረት ጎዳና (2)
#አዝ….
ላመኑብህ ለተማጸኑብህ
ፈጥኖ ደራሽ አለኝታቸው ነህ (2)
#አዝ….
የአናንያ የአዛርያ የሚሳኤል ጠባቂያቸው
ከእሳት ነበልባል ያዳንካቸው (2)
#አዝ….
ምሰሶ አምባችን መጠጊያችን
ቅዱስ ገብርኤል ጠባቂያችን (2)
#አዝ….
ዕለት ዕለት የምንማልድህ
ልጀችህን ይምራን መንፈስህ /2
ለመቀላቀል_ሰማያዊውን_ይጫኑ
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
https://t.me/Eotcw
