ሰዋስው ☘☘☘☘
前往频道在 Telegram
በሰዋስወ ብርሀን ቅዱስ ዻውሎስ ገዳም እና ለተለያዩ ቤተክርስቲያን ለክብረ በአላት ማውጫ ። በተጨማሪም-ዋዜማ ሥርዓተ ማኅሌት - መዝሙራት ስንክሳር - የየእለቱን ምስባክ ቅኔያት ጥያቄዎች እንዲሁም የወቅታዊ ነገር መወያያ በተጨማሪም @eotcww ብለው ይቀላቀሉን ለወዳጅ ዘመድዎ share#Share#Share# ያድርጉ።
显示更多1 161
订阅者
无数据24 小时
无数据7 天
无数据30 天
帖子存档
1 161
🔔በዓለ ዕርገት ዘክርስቶስ🔔
ክፍል አራት
ዲ/ን የአብስራ
✝የክርስቶስ ዕርገት በትምህርተ ሐዋርያት
"ጌታ ኢየሱስም ከእነርሱ ጋር ከተነጋገረ በኋላ ወደ ሰማይ ዐረገ በእግዚአብሔርም ቀኝ ተቀመጠ"
ማር ፲፮፥፲፱
"እስከ ቢታንያ አወጣቸው እጆቹንም አንሥቶ ባረካቸው ሲባርካቸውም ከእነርሱ ተለየ ወደ ሰማይም ዐረገ እነርሱም ሰገዱለትና በብዙ ደስታ ወደ ኢየሩሳሌም ተመለሱ ዘወትርም እግዚአብሔርን እያመሰገኑና እየባረኩ በመቅደስ ኖሩ"
ሉቃ ፳፬፥፶
“ይህንም ከተናገረ በኋላ እነርሱ እያዩት ከፍ ከፍ አለ ደመናም ከዐይናቸው ሰውራ ተቀበለችው እርሱም ሲሄድ ወደ ሰማይ ትኩር ብለው ሲመለከቱ ሳሉ እነሆ ነጫጭ ልብስ ለብሰው ሁለት ሰዎች /መላእክት/ በአጠገባቸው ቆሙ ደግሞም የገሊላ ሰዎች ሆይ ወደ ሰማይ እየተመለከታችሁ ስለምን ቆማችኋል ይህ ከእናንተ ወደ ሰማይ የወጣው ኢየሱስ ወደ ሰማይ ሲሄድ እንዳያችሁት ዳግመኛ ይመጣል አሏቸው"
ሐዋ፩፥፱-፲፪
ሐዋርያት የክርስቶስን ዕርገት ከመላእክት ጋር ሆነው እንደተመለከቱ ደስታውን እንደተካፈሉ ቅዱስ ሉቃስ ጽፎልናል፡፡ በትንሣኤው ነጭ ልብስ ለብሰው የታዩ መላእክት የደስታ ዘመን ነው ሲሉ በዕርገቱም ነጭ ልብስ ለብሰው የዕርገቱን የምሥራች ለሐዋርያት አብስረዋል፡፡ ጌታችን በዚህ ዓለም ሲመላለስ ሲያስተምር የቅዱሳን መላእክት ምስክርነት አልተለየም
በልደቱ
"ለዓለም ሁሉ የሚሆን መድኀኒት ተወልዶላችኋል ታላቅ የምሥራችን እንነግራችኋለን"ሲሉ ለእረኞች አብስረዋል፡፡
ሉቃ ፪፥፲-፲፭
ክርስቶስ አርባ መአልትና አርባ ሌሊት ጾሞ ዲያብሎስን ድል በነሳ ጊዜ "መላእክትም ያገለግሉት ዘንድ መጡ"
ማቴ ፬፥፲፩
በትንሣኤውም
"እናንተስ አትፍሩ የተሰቀለውን ክርስቶስ እንድትሹ አውቃለሁ ተነሥቶአል ከዚህ የለም"
ማቴ፳፰፥፬-፲፬
ብለው ለሴቶች የትንሣኤውን የምሥራች ነግረዋል፡፡
በመስቀሉ ስርም ደሙን በብርሃን መነሳንስ ሲቀበሉ ለከ ኃይል እያሉ ሲሰግዱ ችሎታውን ቸርነቱን ሲያደንቁ ብሎ የቤተ መቅደስ መጋረጃ በሰይፋቸው ለሁለት ሲከፍሉ ታይተዋል፡፡ማቴ ፳፯፥፶፩
ዛሬም በዕለተ ዕርገት በዕለተ ልደት ያመሰገኑት ምሥጋና እያመሰገኑ የምሥራች ለሰው ልጆች ሲነግሩ እርገቱን ከዳግም ምጽአቱ ጋር አስተባብረው ሰብከዋል፡፡
ብርሃነ ዓለም ቅዱስ ጳውሎስም ስለ ዕርገቱ መስክሯል "በሥጋ የተገለጠ
መንፈስ የጸደቀ ለመላእክት የታየ
በአሕዛብ የተሰበከ በዓለም የታመነ
በክብር ያረገ"
፩ጢሞ ፫፥፲፮
ልደትን እንደ ዘር ዕርገትን እንደ መከር አድርጎ ገልጾልናል ወርኃ ዘር የመከር ጊዜ ነው፡፡ ገበሬ በጎተራ ያለውን እህል እያወጣ ሲዘራ ከላይ ዝናም ከታች ጭቃውን ታግሶ ነው፡፡ በመከር ጊዜ ያን የዘራውን ምርት በጥፍ ሲያገኝ ደስ ይለዋል መከራውን ይረሳዋል፡፡
ምነው በጨመርኩበት ይላል፡፡
የክርሰቶስም ልደቱ ስለኛ መከራን ለመቀበል ነውና፥ በሥጋ የተገለጠ ብሎ ትሕትናውን አሳየ፡፡ ዕርገቱን ግን በክብር ያረገ ብሎታል፡፡
ምክንያቱም የሰውነትን ሥራ ፈጽሟልና ድል ነስቶአልና ይህን በሥጋ ዕርገቱን ስናስብ ለምን ዕለቱን ተነሥቶ እለቱን አላረገም ለምንስ እስከ አርባ ቀን በምድር ላይ ቆየ? የሚሉ ጥያቄዎች ይነሳሉ፡፡ እስከ አርባ ቀን በምድር ላይ የቆየው ትንሣኤው በግልጽ እንዲረዳ ደቀ መዛሙርቱንም መጽሐፈ ኪዳንን ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን ያስተምር ዘንድ ነው፡፡
ሌላው አራት ባሕርየ ሥጋና አምስተኛ ባሕርየ ነፍስ ላለው የሰው ልጅ እንደ ካሰ ለማጠየቅ ነው፡፡
አርባን ለአምስት ቢያካፍሉት ስምንት ስምንት ይደርሳቸዋል፡፡ ይህም ስምተኛው ሺህ ሲፈጽም የዚህ ዓለም ምግብና እንደሚጠናቀቅና፥ ክርስቶስ አራት ባሕርያተ ሥጋ አምስት ባሕርየ ነፍስ ላለው የሰው ልጅ እንደየ ሥራው ለመክፈል መምጣቱን ያስረዳናል፡፡
ከዚህ የሐዋርያት ትምህርት ተነሥተው ሊቃውንት አባቶቻችን ስለ ጌታችን ዕርገት አምልተው አስፍተው አጉልተው ጽፈዋል፡፡ ሠለስቱ ምዕትም /318ቱ ሊቃውንት/ "ታመመ ሞተ ተቀበረ በሦስተኛውም ቀን ከሙታን ተለይቶ ተነሣ፡፡ በምስጋና ወደ ሰማይ ዐረገ በአባቱም ቀኝ ተቀመጠ መንግሠቱም ፍጻሜ የለውም"
ጸሎተ ሃይማኖት፡፡
"በእርሱ ዕርገት በእርሱ የሚያምኑ ሰዎች ዕርገት ታወቀ"
ስንክሳር ግንቦት ፰
"የንጹሐን ጻድቃን ዕርገት ያስረዳ ዘንድ ዐረገ"በትንሣኤው ትንሣኤያችን እንደገለጸልን በዕርገቱም ዕርገታችንን አጸደቀልን ከዚህም የተነሣ ቅዱስ ጳውሎስ እንዲህ በማለት የሰው ልጆች ዕርገት ገልጾ አስተምሮአል፡፡
"እኛ ሕያዋን ሆንን ጌታ እስኪመጣ ድረስ የምንቀር ያንቀላፉትን አንቀድማቸውም ጌታ ራሱ በትእዛዝ በመላእክት አለቃ ድምጽ በእግዚአብሔር መለከት ከሰማይ ይወርዳልና በክርስቶስም የሞቱ አስቀድመው ይነሣሉ ከዚያም በኋላ እኛ ሕያዋን ጌታን በአየር ለመቀበል ከእርሱ ጋር በደመና እንነጠቃለን እንዲሁም ሁል ጊዜ ከጌታ ጋር እንሆናልን ስለዚህ እርስ በእርሳችሁ በዚህ ቃል ተጽናኑ"
፩ኛ ተሰ ፬፥፲፭-፲፰
በማለት የክርስቶስ ዕርገት ለምዕመናን ዕርገት መሠረት መሆኑን ገልጾልናል፡፡
✝ቅዱሳን ዐረጉ መባላቸውም ከእርሱ ስለሆነ እነኤልያስ ዐረጉ እነ ሄኖክ ከሞት አመለጡ ብለን ብንናገር በእርሱ ኃይል ስለሆነ ቅዱስ ዮሐንስ
"ከእርሱ በቀር ከሰማይ የወረደ ወደ ሰማይ የወጣ የለም"ብሎ ሰው መሆኑን አምላክነቱን ነገረን፡፡ በእርግጥም ቅዱሳን ዐረጉ ብንል ድንግል ማርያም ዐረገች ብንል ምዕመናን ያርጋሉ ብንልም ሰዎች ናቸው እንጂ የአምላክነት የፈጣሪነት ባህርይ የላቸውም፡፡ የክብር ባለቤት ጌታችን ግን ከሰማይ የወረደ በአምልኮነት በየማነ አብ በዘበነ ኪሩብ ለመቀመጥ ያረገ ነው፡፡
የቅዱሳን የዕርገት መሠረትም እርሱ ነው፡፡
በክብር ያረገው የአምላካችን ቸርነቱ አይለየን!አሜን!!!
ቃለሕይወት ያሰማልን
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
~ተፈጸመ~
ግንቦት 24/2014 የተጻፈ
1 161
🔔በዓለ ዕርገት ዘክርስቶስ🔔
ክፍል ሦስት
ዲ/ን የአብስራ
✝የክርስቶስ ዕርገት በትንቢተ ነቢያት
"ሰማዮችን ዝቅ ዝቅ አደረገ ወረደም ጨለማ /ዲያብሎስ/ ከእግሩ በታች ነበር በኪሩቤል ላይ ተቀምጦ በረረ በነፍሳትም ክንፍ በረረ"
መዝ፲፯፥፱
“አምላክ በእልልታ እግዚአብሔር በመለከት ድምጽ ዐረገ”
መዝ ፵፮፥፭
"ወደላይ ዐረግህ፥ ምርኮን ማረክህ ፥ስጦታንም ለሰዎች ሰጠህ"
መዝ ፷፯፥፲፰
“በምሥራቅ በኩል ወደ ሰማየ ሰማያት ለወጣ ለእግዚአብሔር ዘምሩ
መዝ ፷፯፥፴፫
“በሌሊት ራእይ አየሁ እነሆም የሰው ልጅ የሚመስል ከሰማይ ደመናት ጋር መጣ በዘመናት ወደ ሸመገለው ደረሰ /ወደ አብ/ ወደፊቱም አቀረቡት፡፡
ወገኖችና አሕዛብ በልዩ ልዩ ቋንቋም የሚናገሩ ሁሉ ይገዙለት ዘንድ ሥልጣን ተሰጠው ግዛቱም የማያልፍ የዘለዓለም ግዛት ነው፡፡ መንግሥቱም የማይጠፋ ነው”
ዳን ፯፥፲፫
ከዚህ ላይ ዳንኤል ስለጌታችን ዕርገት የተናገረው ዮሐንስ ከተናገረው ጋር ምንም ልዩነት የለውም፡፡
ግዛት ሥልጣን የዘለዓለም መንግሥት ተሰጠው በማለት ጌትነቱን አምላክነቱን አጉልቶ ዮሐንስ ከእርሱ በቀር ወደ ሰማይ የወጣ የለም ያለውን ቀደም ሲል በመንፈስ ረድኤት ጸንቶ በመንፈስ ቅዱስ ተቃኝቶ ተናግሮታል ቅዱስ ዳዊት እግዚአብሔር እያለ አምላክነቱን ገልጾታል ዐረገ ያለው ኢየሱስ ክርስቶስ እግዚአብሔር መሆኑን አጽንዖት ሰጥቶ ነግሮናል ዳዊት እግዚአብሔር ብሎ የገለጸውን ዳንኤልና ዮሐንስ እንደአንድ ልብ መካሪ እንደ አንድ ቃል ተናጋሪ ሆነው የሰው ልጅ በማለት ገልጸውታል፡፡ ፍጹም ሰው ሆኖአልና፡፡ ክርስቶስ ራሱም "የሰውን ልጅ ማን ይሉታል"ማቴ ፲፮፥፲፭ በማለት ከጠየቀ በኋላ እነ ዳንኤል የተናሩት ስለ እርሱ መሆኑን አረጋግጧል፡፡
✝የክርስቶስ ዕርገት በትምህርተ ሐዋርያት
ክፍል አራት ይቀጥላል....
https://t.me/Eotcw
1 161
❤ "በስመ አብ ወወልደ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤
❤ ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ እምነታችን እጅግ አስደሳች ዜና።
❤ ብፁዕ አቡነ አብርሃም የባሕርዳር እና አካባቢው ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት ዋና ሥራ አስኪያጅ በመሆን ተመረጡ።
❤ የየኒዮርክ እና አካባቢው ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ የሆኑት ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ (ዶ/ር) የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ በመሆን ተመርጠዋል፡፡
❤ (በመ/ር አቤል አሰፋ ፣ግንቦት ፳፬ ቀን ፳፻፲፬ ዓም)
❤ ቅዱስ ሲኖዶስ በግንቦት 2014 ዓ.ም ርክበ ካህናት እያከናወነ በሚገኘው ጉባኤ ብፁዕ አቡነ አብርሃምን የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት ዋና ሥራ አስኪያጅ ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስን የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ በማድረግ መምረጡን ብፁዕ አቡነ ዮሴፍ የሲዳማ ጌዴኦ አማሮና ቡርጂ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ለኢኦአተቤ ቴቪ( EOTC TV) ገልጸዋል
በዛሬው ዕለት ግንቦት ፳፬ ቀን ፳፻፲፬ ዓም በተካሄደው ምርጫ አርባ አምስት ሊቃነ ጳጳሳት የተገኙ ሲሆን ለመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት ዋና ሥራ አስኪያጅነት ከተወዳደሩት።
1. ብፁዕ አቡነ አብርሃም 26 ድምጽ በማግኘት ሲመረጡ
2. ብፁዕ አቡነ ቀሌምንጦንስ 12
3. ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ 7
ድምጽ አግኝተዋል፡፡
❤ ለቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ በእጩነት ከቀረቡት መካከል
1. ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ 20 ድምጽ በማግኘት ሲመረጡ
2. ብፁዕ አቡነ ሩፋኤል 17
3. ብፁዕ አቡነ ኤልያስ 8
❤ ደምጽ ማግኘታቸውን ብፁዕ አቡነ ዮሴፍ ለኢኦአተቤ ቴቪ( EOTC TV) ገልጸዋል
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የመገናኛ በብዙኃን ሥርጭት አገልግሎት ድርጅት በኃላፊነት ለአገልግሎት ለተመረጡ አባቶች መልካም የአገልግሎት ዘመን ይመኛል፡፡
https://t.me/Eotcw
1 161
በጌታችንና በአምላካችን በመድኃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ
#በዓለ_ዕርገት በቅዳሴ ጊዜ
#ምንባባት
ሮሜ ም፲፥ቁ፩-ፍጻ
፩ጵጥ ም፫፥፲፭-ፍጻ
ግብ ሐዋ ም፩፥፩-፲፪
#ምስባክ
መዝ ፵፮፥፭
ዐርገ እግዚአብሔር በይባቤ
ወእግዚእነ በቃለ ቀርን
ዘምሩ ለአምላክነ ዘምሩ
#ትርጉም
አምላክ በእልልታ፥ እግዚአብሔር በመለከት ድምፅ ዐረገ።
ዘምሩ፥ ለአምላካችን ዘምሩ፤ ዘምሩ፥ ለንጉሣችን ዘምሩ።
#ወንጌል
የሉቃስ ወንጌል ም ፳፬÷፵፭-ፍጻ
#ቅዳሴ
ቅዳሴ ዲዮስቆሮስ
1 161
🔔በዓለ ዕርገት ዘክርስቶስ🔔
ክፍል ሁለት
ዲ/ን የአብስራ
✝ለምን ዐረገ?
ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ ቀደመ ክቡሩ ማረጉ… በሙሴ የሕግ መጽሐፍት በነቢያትም የትንቢት መጽሐፍ እንዲሁም በመዝሙረ ዳዊት የተነገረው ትንቢት አለና ይህ ይፈጸም ዘንድ ነው፡፡
መዝሙረኛው ልበ አምላክ ቅዱስ ዳዊት ስለጌታችን ዕርገት እንዲህ በማለት ጽፏል፡፡
መዝ፵፯፥፭
"…. አምላክ በእልልታ በእግዚአብሔር በመለከት ድምፅ ዐረገ"
መዝ፷፯፥፲፰
"ወደ ላይ ዐረግህ ፣ምርኮን ማረክ ፣ስጦታን ለሰዎች ሰጠህ"
መዝ፲፮፥፲
"በኪሩቤል ላይ ተቀምጦ በረረ፣ በነፋስም ክንፍ በረረ…."
በማለት በትንቢት መነጽር ተመልክቶ የዘመን ግድግዳ ሳያግደው የተናገረው ኃይለ ቃል ነው፡፡
✝ዕርገቱን ለምን በተነሳ በ40ኛው ቀን አደረገ?
💧አዳም በ40 ቀን አግኝቶ ያጣትን ልጅነት እንደተመለሰለት ለማጠየቅ
💧ጌታ በረቀቀ ጥበቡ ተሸብሮ የነበረውን የሐዋርያትን ልቡና እያረጋጋና እያጽናና መቆየቱን መርጦ ነው፡፡
💧ለአይሁድ ምክንየት ለማሳጣት ነው ዕርገቱን ከትንሳኤው አስከትሎ ወዲያው ቢያደርገው ዕርገቱ ምትሐት ናት እንዳይሉ በእርግጥ በሞቱ ሞት ድል አድረጎ የተነሣው ወልደ እግዚአብሔር መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እርሱ መሆኑን እንዲረዱ እንዲገነዘቡ የጥርጣሬ መንፈስ በአዕምሯቸው እንዳይሰርጽ ነው፡፡
💧ላላመኑት ለእስራኤላውያን (ለአይሁድ) የንስሐ ጊዜ ሲሰጣቸው ነው ብዙዎች በክርስቶስ የባሕርይ አምላክነት አምነው የተመለሱ አሉና፡፡
✝በዓለ ዕርገት መቼ ነው?
ጥንተ ዕርገቱ ግንቦት ስምንት ሐሙስ ቀን በ34 ዓ.ም በዘመነ ማርቆስ ነው፡፡
የዕረገት በዓል አከባበር እስከ አራተኛው መቶ ዓመት ድረስ እንደ ዛሬው ሐሙስን ሳይጠብቅ በጥንተ ዕርገቱ ግንቦት ስምንት ቀን ብቻ ይከበር ነበር፡፡
በአራተኛው ምዕተ ዓመት ወዲህ ግን ትንሣኤ በዋለ በአርባኛው ቀን ብቻ እንዲከበር ቅዱስ ዲሜጥሮስ በባሕረ ሐሳብ ቀመሩ ስሌት መሠረት ይከናወን ዘንድ በቀኖና ቤተክርስቲያን ተወስኖ በሥራ ላይ ውሎ ይገኛል፡፡
💧የይሁዳ ምትክ መምረጥ
ፊት አውራሪ ሆኖ ጌታን ለመስቀል ሞት አሳልፎ የሰጠው ይሁዳ ቁጥሩ ከ12 ሐዋርያት ነበር ይህን ማዕረግ አርክሶ አጉድፎ በመገኘቱ ከሐዋርያ አንድነት ሕብርት ሊገለል በቅቷል የሰው ልጅ እኩይ ተግባርን በፈጸመ ቁጥር ጸጸት በውስጡ ያድር ዘንድ የገዛ ሕሊናው ወጥሮ ይይዘዋል፡፡ ይህ የሕሊና ፍርድ ይሁዳንም ስላስጨነቀው "ንጹህ ደም አፈሰስኩ ጻድቅ ሰው አስገደልኩ አወይ አላበጀሁም" በማለት ጌታን ለማስያዝ የተቀበለውን 30 ብር ከዕቃ ቤት አፍስሶ ገመድ ይዞ ዛፍ ላይ በማሰር ለመታነቅ ሙከራ ቢያደርግም ዛፏ በሰው አንደበት "እንደወንድምህ ጴጥሮስ ንስሐ ግባ" እያለች ዘንበል ብትልም ራሱን አላዘጋጀም ነበርና ለሦስተኛ ጊዜ ለመታነቅ ሲሞክር ከመሬት ደባልቃዋለች በዚህ ክፉኛ ተጎድቷል ምድርም ላይ
ወድቆ ሳለ ነጋድያን ሲያልፉ አይተውት ለዘመዶቹ "…ያክፉ ዘመዳችሁ ከዚያ ወድቆላችኋል" ብለው ስለነገሯቸው ዘመዶቹ አንስተው ወሰዱት ለአርባ ቀን ያህል ሆዱ አባብጦ ተኝቶ ነበርና ጌታ ሲያርግ "…ያሰቀልከው ዐረገልህ" ብለው ቢነግሩት ለማየት ሲወጣ የክፍሉ መወጣጫ አደናቅፎት ቢወድቅ የሳንቃው መወርወርያ ጎኑን ቢወጋው ያበጠው ሆዱ ፈንድቶ ሞቷል፡፡
ለማየት ሲወጣ መልአኩ የእሳት ሰይፍ ቢያሳየው ተደናግጦ ወደ መኝታው ሲመለስ የአልጋው ሸንኮር ሆዱን ወግቶት ነዋየ ውስጡ ፈሶ ለህልፈት በቅቷል በዚህም የጌታን ትንሣኤ እንዳላየ ሁሉ ዕርገቱን ለማየት ሳይታደል
ስቀድሞ በዳዊት አፍ እንደተናገረው መኖሪያው ምድረ በዳ ትሁን የሚኖርባት አይኑር ደግሞም ሹመቱ ሌላ ይውሰዳት ተብሎ እንደተጻፈ ጌታን በ30 ብር ለሞት አሳልፎ በሰጠው ከሐዋርያት አንድነት በሞት በተለየው በይሁዳ ምትክ ክፍተቱን የሚሞላ ሐዋርያዊ ተልዕኮውን ሊወጣ የሚችል መምረጥ እንዳለባቸው ቅዱስ ጴጥሮስ ለ120 ቤተሰብ በማሳወቅ ሁለት ፍጹማን ዮሴፍና ማትያስ ለምርጫ ቀረቡ፡፡ በመቀጠል " የሁለቱን ልብ የምታውቅ አንተ ጌታ ሆይ ይሁዳ ያቃለላትን ይህችን የሐዋርያት ማኅበር /አንድነት/ ይቀላቀል ዘንድ ከሁለቱ አንዱን ሹመው" በማለት ወደ እግዚአብሔር ከጸለዩ በኋላ ዕጣ ቢጣጣሉ ለማትያስ በመውጣቱ ከ11ዱ ሐዋርያት ጋር 12ኛ ሆኖ ተቆጠረ፡፡
ሐዋርያት ማን ብቁ እንደሆነ የሚያውቁ ሆነው ሳለ በዕጣ ለምን አደረጉት?
💧ለትህትና
💧በሰው ሰውኛ ሥርዓት ከእከሌ ይልቅ ለእከሌ አድልተው መረጡ ብለው እንዳይሰናከሉባቸው ለቢፅ ሐሳውያን ምክንያት እንዳንሆንባቸው ሲሉ
💧ሥርዓት ሊሰሩ ሊያስተምሩ ፈቅደው በመንፈሳዊ አገልግሎት እኩል የሆኑትን አገልጋዮች በዕጣ በመለየት ምረጡ ሲሉ በዕጣ መረጡ
✝የክርስቶስ ዕርገት በትንቢተ ነቢያት
ክፍል ሦስት ይቀጥላል....
https://t.me/Eotcw
1 161
በስመአብ ወወልድ ወመንፈስቅዱስ
አሐዱ አምላክ አሜን
🔔በዓለ ዕርገት ዘክርስቶስ🔔
ክፍል አንድ
ዲ/ን የአብስራ
እንኳን ለአምላካችን ለመድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዓለ ዕርገት አደረሳችሁ
"አምላካችን በዕልልታ እግዚአብሔር በመለከት ድምጽ ዐረገ፥ ዘምሩ ለአምላካችን ዘምሩ"
መዝ፵፥፮፭
"ወደላይ ዐረግህ፥ ምርኮን ማረክህ፥ ስጦታንም ለሰዎች ሰጠህ"
መዝ፷፯፥፲፰
"በምሥራቅ በኩል ወደ ሰማየ ሰማያት ለወጣ ለእግዚአብሔር ዘምሩ"
መዝ፷፯፥፴፫
“ጌታ ኢየሱስም ከእነርሱ ጋር ከተነጋገረ በኋላ ወደ ሰማይ አረገ በእግዚአብሔርም ቀኝ ተቀመጠ”
ማር ፲፮፥፲፱
“እስከ ቢታንያ አወጣቸው እጆቹንም አንሥቶ ባረካቸው ሲባርካቸውም ከእነርሱ ተለየ ወደ ሰማይም ዐረገ እነርሱም ሰገዱለትና በብዙ ደስታ ወደ ኢየሩሳሌም ተመለሱ ዘወትርም እግዚአብሔርን እያመሰገኑና እየባረኩ በመቅደስ ኖሩ”
ሉቃ፳፬፥፶
ከዘጠኙ የጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ዓበይት በዓላት አንዱ ዕርገት ነው፡፡
በዓለ ዕርገት ከትንሣኤ በዓል በኋላ በ40ኛው ቀን ስለሚውል ሐሙስን አይለቅም፡፡
ዕርገት ማለት ዐርገ አረገ ወጣ ከሚለው የግእዝ ግሥ የወጣ ቃል ሲሆን ትርጉሙም ወደ ላይ መውጣት ከምድር ከፍ ከፍ ማለት... እስከ ሰማየ ሰማያት መምጠቅ ማለት ነው፡፡
የጌታ ዕርገት እንደ ኤልያስ እንደ ሔኖክ እንደሌሎቹም ቅዱሳን ያይደለ በገዛ ሥልጣኑ የሆነ ነው ሌሎቹ አጋዥ አስነሽ ይሻሉና ነው፡፡
ስለጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ዕርገት ቅዱስ ዳዊት "አምላክ በዕልልታ እግዚአብሔር በመለከት ድምጽ ዐረገ ዘምሩ ለአምላካችን ዘምሩ"መዝ፵፮፥፭ በማለት በትንቢት መነጽርነት ተመልክቶ በመንፈስ ዘምሯል።
ይህም ትንቢት ይፈጸም ዘንድ ከሙታን ተለይቶ በተነሳ በአርባኛው ቀን ደቀ መዛሙርቱን ወደ ቢታንያ ይዟቸው ሄዷል።ሉቃ፳፬፥፶
ወደ ሰማይ ከማረጉ በፊት ለደቀ መዛሙርቱ በተለያየ ቦታ ተገልጾ ታይቷቸዋል። ትምሕርትም አስተምሯቸዋል።
"ኢየሱስ የመረጣቸውን ሐዋርያትን በመንፈስ ቅዱስ ካዘዛቸው በኋላ እስከ ዐረገበት ቀን ድረስ ያደርገውና ያስተምረው ዘንድ ዐርባ ቀን እየታያቸው ስለ እግዚአብሔርም መንግስት ነገር እየነገራቸው በብዙ ማስረጃ ከሕማማቱ በኋላ ህያው ሆኖ ለእነርሱ ራሱን አሳያቸው"ሐዋ፩፥፫
በነዚህ ቀናት ውስጥ ጌታችን ሥርዓትን አስተምሯቸዋል። ቤተ ክርስቲያንም ይህን ትምሕርት ኪዳን ብላ ትጠራዋለች።
ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከሙታን ተለይቶ ከተነሳ በኋላ ለሐዋርያት የነገራቸው መጽሐፈ ኪዳን ይባላል፡፡ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከትንሣኤው በኋላ አርባ ቀናት በምድር ቆይታ ባደረገበት ወቅት በግልጽ ተገልጦ ስለ እግዚአብሔር መንግሥትና መጽሐፈ ኪዳንን አስተምሯቸዋል፡፡
ጉባኤ ዘርግቶ ያስተማራቸው ለሦስት ጊዜ ብቻ ነው፡፡ በተናጠል ግን ለአንዱም ለሁለቱም እየተገለጠ ያስተምራቸው ነበር። ዮሐ፳፩፥፲፬
እነሱም፦
፩. ሞትን ድል አድርጎ ሙስና መቃብርን አጥፍቶ መግነዝ ፍቱልኝ መቃብር ክፈቱልኝ ሳይል በተነሳበት በትንሣኤ ዕለት
፪. ምሳ ባበላቸው /በአግብኦተ ግብር/ ዕለት
፫. በጥብርያዶስ ባሕር ዳርቻ ናቸው፡፡
በዚህ በዕርገቱ ዕለት ቅዱስ ጴጥሮስ ታላቁን ሹመት የመንግሥተ ሰማያትን መክፈቻን ቁልፍ ተሰጥቶታል ፍቁረ እግዚእ ቅዱስ ዮሐንስ ደግሞ ሞትን ሳይቀምስ እስከ እለተ ምፅአት እንደሚቆይ ተገልጿል። ዮሐ፳፩፥፲፭-፳፫
✝እንዴት ዐረገ?
ሐዋርያትን ከባረካቸው በኋላ ከቅድስት ድንግል ማርያም በነሳው ሥጋ በማነስ፣ በመርቀቅ፣ በመጥፋት ሳይሆን በመራቅ ሐዋርያት በዓይናቸው እየተመለከቱት በጥቂት በጥቂት ምድርን ለቆ ከፍ ከፍ እያለ በፍጹም ምሥጋና ፈጽሞ ወደ አልተለየው ወደ ባሕርይ አባቱ ዐርጓል፡፡
በሥጋና በነፍስ፣ በአጥንትና በደም፣ በጅማት፣ በጸጉርና በፂም እንዳለ በጥንተ አኗኗሩ በአብ ቀኝ ተቀመጠ በሰማይ በምድር ያሉትን ረቂቁም ግዙፉም ሁሉ ተገዙለት፡፡እርሱም መላእክትና ሥልጣናት ኃይላትም ከተገዙለት በኋላ ወደ ሰማይ ሄዶ በእግዚአብሔር ቀኝ አለ።
፩ኛጴጥ ፫፥፳፪
ክርስቶስ የሰውን አካል የሰውን ባህርይ ገንዘቡ አድርጎ በአጭር ቁመት በጠባብ ደረት ተወስኖ ሲገለጥ ሰውም የአምላክን ገንዘብ ገንዘብ አድርጎ በእግዚአብሔር አብ ቀኝ በዘባነ ኪሩቤል የመላእክትንም ምሥጋና ለመቀበል በቃ፡፡
✝ለምን ዐረገ?
ክፍል ሁለት ይቀጥላል....
https://t.me/Eotcw
1 161
❤ "በስመ አብ ወወልደ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤
+ + +
❤ "ሰላም ለዕርገቱ መድምም እንዘ ያንበለብል ጸዳሉ ግሩም"። ትርጉም፦ አስፈሪ ብርሃኑ እያንበለበለ (ቦግ ቦግ እያለ) ለተደረገ ድንቅ ዕርገቱ ሰላምታ ይገባል። ሊቁ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ በተአምኆ ቅዱሳን ላይ።
+ + +
❤ "ሰላም ለዕርገትከ ዘኢይትረከ መጠኑ። ወለንብረትከ ሰላም ለአቡከ ውስተ የማኑ። ኢየሱስ ክርስቶስ እለ ኪያከ ተአመኑ። ቅዱሳነ ዘእምኀቤከ ወንጹሐነ ይኩነ ጰራቅሊጦስሃ መንፈሰከ ፈኑ"። ትርጉም፦ ጌታዬ ኢየሱስ ለማይመረመር ዕርገትህ ሰላምታ ይገባል በአባትህ ቀኝ ለመቀመጥህም ክቡር ይገባል። ፈጣሪዬ ሆይ በአንተ ለሚያምኑና ለሚተማመኑ ሁሉ የተቀደሱና ንጹሐን ይሆኑ ዘንድ እንደ በረዶ የሚያነፃ እንደ ውሀ የሚያጠራ ካንተ ዘንድ የሚገኝ መንፈስህን ላክላቸው። መልክአ ኢየሱስ።
https://t.me/Eotcw
1 161
አገር ነኝ። ከልጅነቴ ጀምሮ ለምድራዊ ሟች ለሆነ ንጉሥ ሳገለግል ኖርኩ እንግዲህስ ሕያው ለሆነ ሰማያዊ ንጉሥ አገለግላለሁ" ብሎ መለሰለት።
❤ ሉክያኖስ መኰንንም "ብዙ ገንዘብ ሰጥቼህ ከጭፍሮቹ ሁሉ በላይ እጅግ ከፍ ከፍ አድረግህ ዘንድ ለአማልክት ለአጵሎንና ለአርዳሚስ ለመሠዋት ተዘጋጅ" አለው። ቅዱስም እንዲህ ብሎ መለሰለት "ልብ የሌለህ ደንቆሮ ሆይ እምነቱን በሰው ላይ ላደረገ ሰው ወዮለት ግን እምነቱ በእግዚአብሔር ላይ የሆነ የተመሰገነ ነው የሚል በቅዱሳት መጻሕፍት ተጽፏል። እኔም ለረከሱ አማልክት አልሠዋም አለኝታዬ እግዚአብሔር ስለሆነ ለእርሱ ብቻ እሠዋለሁ"። ያን ጊዜም መኰንኑ ተቆጥቶ እንዲገርፉትና እሾህ ባላቸው በብረት ዘንጎችም እንዲደበድቡት ደሙ እንደ ውኃ እስቲፈስ ድረስ እንዲአሠቃዩት አዘዘ። ጌታችንም በመልአኩ እጅ አጽንቶ አዳነው ጤነኛም ሆነ። ሕዝቡም ይህን ድንቅ ተአምር በአዩ ጊዜ በክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አምነው በሰማዕትነት ዐረፉ። ቊጥራቸውም ሠላሳ ሺህ አምስት መቶ ነው። መኰንኑም መሠቃየቱ በሰለቸው ጊዜ ራሱን በሰይፍ እንዲቆርጡ አዘዘ።
❤ እንሆ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ተገልጸለትና እንዲህ አለው "ብፁዕ ኄሮዳ ሆይ ሰላም ለአንተ ይሁን አትፍራ እኔ ፈጣሪህ ክርስቶስ ነኝ እንሆ መቀመጫህን ከቅዱሳን ጋራ በሰማያት አዘጋጅቼልሃለሁ። በእውነት እነግርሃለሁ በመታሰቢያህ ቀን መከራ ድካምህን አስቦ መሥዋዕት፣ ለሚያቀርብ ለድኃ ምጽዋትን ለሚሰጥ በእንስሶቹ ውስጥ ርባታ ይሆናል። በቤቱም የተባረከ ልጅ አይታጣም። ሰይጣንም በእርሱ ላይ በሥራውም ሁሉ ሊበረታበት አይችልም። የገድልህን መጽሐፍና ስምህን የሚጽፈውንም እኔ በሕይወት መጽሐፍ ስሙን እጽፋለሁ የዕዳ ደብዳቤውን እደመስሳለሁ። ደግሞ በችግር በመከራ ውስጥ ስምህን ጠርቶ የሚለምነኝን ከመከራው ሁሉ እኔ አድነዋለሁ። መታሰቢያህንም ለሚያደርግ ሁሉ በደሉን ሁሉ እተውለታለሁ ሰላሜም ከአንተ ጋራ ይሁን" ይህንንም ብሎ መድኃኒታችን ከእርሱ ዘንድ ዐረገ።
❤ የከበረ አባ ኄሮዳም ፍጹም ደስታን ተደሰተ። ተጋድሎውንም በሚፈጽምበት ጊዜ በዚያ ወደ አሉት ሕዝቡ ተመልሶ "ከውስጣችሁ እግዚአብሔርን የሚፈራ ሰው ያለ ከሆነ ሥጋዬ በጎ በረከትን እስከሚያደርግለት ድረስ ሥጋዬን ወስዶ በእርሱ ዘንድ ያኑረው" አላቸው። ያን ጊዜም አንገቱን ዘረጋላቸው በሰይፍም ቆረጡት የምስክርነቱ አክሊልንም በግንቦት ወር በሃያ አምስት ቀን ተቀበለ።
❤ ከሦስት ወር በኋላም ዘመዶቹ መጡ ሥጋውንም ወሰዱ ተሸክመውም ወደ አገሩ ስብስጣ አድርሰው በአነፁለት ቦታ አኖሩት ከሥጋውም ታላላቅ የሆኑ ድንቆች ተአምራት ተገለጡ ለድውያን ፈውስ ተገኘ። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በአባ ኄሮዳ ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋራ ለዘላለሙ አሜን። ምንጭ፦ የግንቦት 25 ስንክሳር።
+ + +
❤ "ሰላም ለኄሮዳ እግዚአብሔር ዘሐወጾ። ከመ የሀቦ ኪዳነ በኢሐስዎ ወዐምፆ። ለዝ መዋዒ ትግርምት መኰንን ኢያደንገፆ። በብልሐ ቅትራት አመ ገቦሁ ደጐፆ። በአእዳወ ኀፂን ካዕበ እንዘ ይጸፍዕ ገጾ። ሊቀ አርከ ሥሉስ (አርኬ) የግንቦት 25።
❤ በየቀኑ ይህን ቴሌግራም ላይ ማግት ከፈለጉ ከታች ያለውን ሊኩን ይጫኑት።
https://t.me/Eotcw
1 161
❤ "በስመ አብ ወወልደ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤
❤ ግንቦት ፳፭ (25) ቀን።
❤ እንኳን የክብር ባለቤት ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የዮሴፍን በትሮች በአረንጓዴ ቦታ ላይ ተክሎ ወዲያውኑ ዛፎች ላደረገበት ዓመታዊ በዓል (ይህ በዓል ከእመቤታችን ከ33 በዓላት አንዱ ነው) ና ለእመቤታችን ለቅድስት ድንግል ማርያም ለአክስት ልጅ ለብፅዕት ቅድስት ሰሎሜ ለዕረፍት በዓል መታሰቢያ፣ ስብስጣ ከሚባል ለሆነ በዕረፍቱ ጊዜ ጌታችን ተገልጦ ብዙ ቃል ኪዳንን ለሰጠው ለአባ ኄሮዳና ከእንዴናው አገር አገር ለሆነ ለከበረ በቀን መቶ እንዲሁ በሌሊትም መቶ ጸሎታትን ይጸልይ ለነበረ ቅዱስ ኮጦሎስ ሰማዕትነት ለተቀበሉበት ለዕረፍታቸው በዓል በሰላም አደረሰን። በተጨማሪ በዚህ ቀን ከሚታሰቡት፦ ከአባ ኄሮዳ ማኅበረ ሰማዕታት ከሠላሳ ሺህ አምስት መቶ ሰዎች፣ ከከበሩ ቅዱሳን በላኖስ፣ ከእሎንትራን፣ ከራምኔሳ፣ከመቶ ኃምሳ ሰማዕታት፣ ከቈስጠንጢኖስና ከእናቱና ከሔላም ከመታሰብያቸው እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።
+ + +
❤ "ምዕረ በዘባንኪ ወምዕረ በገቦኪ፡፡ ማርያም ብዙኃ በሐዚለ ሕፃን ደከምኪ። ሶበኒ የሐውር በእግሩ ከመ ትጹሪዮ ይበኪ አልቦ እንበለ ሰሎሜ ዘያስተባርየኪ ለኪ፡፡ ወዮሴፍ አረጋዊ ዘይጸውር ስንቀኪ"። ትርጉም፦ ማርያም! አንድ ጊዜ በጀርባሽ፣ አንድ ጊዜ በጎንሽ ልጅን በማዘል በእጅጉ ደከምሽ በእግሩ በሚሄድበት ጊዜም ትሸከሚው ዘንድ ያለቅሳል ስንቅሽን ከሚሸከም ከሽማግሌው ዮሴፍና ከሰሎሜ በቀር አንችን የሚያስተጋግዝሽ የለም። በሰቆቃወ ድንግል ላይ።
+ + +
❤ የእመቤታች የአክስት ልጅ ቅድስት ሰሎሜ፦ተተተ እርሷም የማጣት ልጅ የሌዊ ልጅ የሚልኪ ልጅ የካህኑ አሮን ልጅ ናት። ለማጣት ሦስት ሴቶች ልጆች አሉት የታላቂቱ ስማ ቅድስት ማርያም ነው የሁለተኛዪቱ ስም ቅድስት ሶፍያ የሦስተኛዪቱ ስም ቅድስት ሐና ነው ይቺም ቅድስት ማርያም ቅድስት ሰሎሜን ወለደቻት ቅድስት ሶፍያም ቅድስት ኤልሳቤጥን ወለደቻት ቅድስት ሐናም ቅድስት ድንግል ማርያምን ወለጀቻት።
❤ እመቤታችንም ድንግል ስትሆን የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በወለደችው ጊዜ ይቺ ቅድስት ሰሎሜ የእመቤታችንን አወላለድ እንደ ሴቶች ሁሉ አወላለድ መስሏት ተጠራጠረች ከዚህም በኋላ የድንግል እመቤታችንን ገላዋን ዳሠሠቻት ያን ጊዜ እጇ ተቃጠለ ሕፃኑን በዳሠሠችው ጊዜ ደግሞ ዳነች። በዚህም በኅቱም ድንግልና አምላክን እንደወለደችው አወቀች።
❤ ከተረገመ ኄሮድስ ፊት እመቤታችን በሸሸች ጊዜ ከቅዱስ ዮሴፍ ጋራ በመሆን አብራ በመሰደድ የእመቤታችንን ድካሟን ተካፍላ አገለገለቻት ከስደት እስከ ተመለሱ ድረስ ሕፃኑን ታዝለዋለች የምታጥብበት ጊዜ አለ። መድኃኒታችን ሰው በሆነበት ወራት ሁሉ አልተለየችም በመከራውም ቀን ከእመቤታችን ጋራ ከከበሩ ሁሉ ሴቶች በትምህርቱ ወራት ከተከተሉት ጋራ እያለቀሰች ነበር። በተነሣባት ዕለት ወደ መቃብር ገሥግሣ ከሐዋርያት ቀድማ ያየች ናት።
❤ በኃምሳኛው ቀን መንፈስ ቅዱስ በወረደ ጊዜ ከባልንጆሮቿ የከበሩ ሴቶች ጋራ ሰማያዊ ሀብትን ተቀብላ በክብር ባለቤት መድኃኒታችን ስም ሰበከች ብዙዎችንም አሳመነች። ከአይሁድም ብዙ ስድብና ሽሙጥ አገኛት ከዚያም ግንቦት25 ቀን ዐረፈች። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በቅድስት ሰሎሜ በጸሎቷ ይማረን በረከቷም ከሁላችን ጋራ ይሁን ለዘላለሙ አሜን።
+ + +
❤ ቅዱስ ኮጦሎስ፦ የዚህም ቅዱስ እናትና አባቱ እግዚአብሔር የሚፈሩ ናቸው አባቱም የእንዴናው ገዥ መኰንን ነው ልጅ አልነበረውም ይህን ቅዱስ ልጅ እስከ ሰጠው ድረስ ጌታችንን አዘውትሮ ይለምነው ነበር የቤተ ክርስቲያንንም መጻሕፍት አስተማረው። ከታናሽነቱ ጀምሮ ንጹሕ ሆነ ለራሱም ሥርዓት በመሥራት በቀን መቶ እንዲሁ በሌሊትም መቶ ጸሎታትን ይጸልያል። ጥቂት በአደገ ጊዜም ወላጆቹ ሊአጋቡት ፈለጉ እርሱ ግን አልፈቀደም። ነገር ግን ከእርሱ በኋላ የተወለደች ሴት ልጅ ነበረቻቸውና እርሷን ከአርያኖስ ጋራ አጋቧት። አባቱም ከሞተ በኋላ ለስደተኞች የእንግዳ መቀበልን ጀመረ።
❤ ከዚህም በኋላ የጥበብ መጽሐፍን ተምሮ ሐኪም ሆነ። በሽተኞቹ ሁሉ ወደ ርሱ ይመጣሉ እርሱም ያለዋጋ ይፈውሳቸዋል። ዲዮቅልጥያኖስም በካደ ጊዜ አርያኖስ ስለ ሹመቱ ከንጉሡ ጋራ ተስማምቶ ሰማዕታትን የሚያሠቃያቸው ሆነ። ይህም ቅዱስ ሰማዕት ለመሆን ይተጋ ነበር ወደ ፍርድ አደባባይም ሒዶ አርያኖስን ንጉሡንም አለቆቹን ሁሉ ረገማቸው ጣዖታቱንም ሰደበ። አርያኖስ ስለ እኅቱ በእርሱ ክፋ ሊአደርግበት አልቻለውም ወደ እኅቱ ላከው እንጂ። እርሷም ከመታሠር አዳነችው።
❤ ከአርያኖስም በኋላ ሌላ መኰንን ተሾመ የዚህ የቅዱስ ኮጦሎስን ዜና ነገሩት። ጭፍራ ልኮ ወደርሱ አስመጣውና በርሱ ላይ በመቆጣት "ለአማልክት ካላጠንክ ይህ ካልሆነ ጽኑ ሥቃይ አሠቃይሃለሁ" አለው። ቅዱሱም "እኔ ለረከሱ አማልክት ዕጣን አላቀርብም ለክብር ባለቤት ለሕያው እግዚአብሔር ልጅ ለጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ንጹሕ መሥዋትን አቀርባለሁ እንጂ" ብሎ መለሰለት። በዚያን ጊዜም መኰንኑ ተቆጥቶ በየአይነቱ በሆነ ሥቃይ እንዲአሠቃዩት አዘዘ። የእግዚአብሔር መልአክም ወደ ርሱ መጥቶ ይፈውሰው ያጽናናውና ያረጋጋው ነበር።
❤ ጌታችንም በእጆቹ ታላቅ የሆነ ድንቆች ተአምራትን አደረገ። ማሠቃየቱ በሰለቸው ጊዜ በሰይፍ ራሱን ይቆርጡ ዘንድ አዘዘ። የሰማዕትነትንም አክሊል ግንቦት25 ቀን ተቀበለ ቤተሰቦቹም ገንዘው በመልካም ቦታ አኖሩት። ከሥጋውም እጅግ ብዙ ድንቆች ተአምራት የሚታዩ ሆነ። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱስ ኮጦሎስ ጸሎት ይማረን ለዘላለሙ አሜን።
+ + +
❤ አባ ኄሮዳ፦ ይህም አባት ስብስጣ ከሚባል አገር የሆነ ነው። ከከሀዲ ዲዮቅልጥያኖስ በክርስቲያን ወገኖች ላይ የስደት ወራት በሆነ ጊዜ ይህ ቅዱስ አባ ኄሮዳ ከሕፃንነቱ ጀምሮ እግዚአብሔርን ይፈራ ነበር።
❤ በአንዲት ሌሊትም በአልጋው ተኝቶ ሳለ እርሱም ስለ እግዚአብሔር ፈቃድ በማሰብ "በኃላፊው ዓለም ውስጥ መኖር ምን ይጠቅማኛል። በከበረ ወንጌል የተናገረውን የጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ቃል ይህን ዓለም ያልካደ ሊያገለግለኝ አይችልም ያለውን ሰምቻለሁና አሁንም ተነሥቼ ሒጄ በክብር ባለቤት ክርስቶስ ስም ደሜን አፈሳለሁ" አለ። ይህንንም በልቡ ሲያስብ እንሆ የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤል ወደርሱ መጥቶ "የከበርክና የተመሰገንህ ኄሮዳ ሆይ ሰላም ለአንተ ይሁን አትፍራ እግዚአብሔር የክብር ዙፋን አዘጋጅቶልሃልና እኔም የመላእክት አለቃ ሚካኤል ነኝ። እኔም ወደ ፍርድ አደባባይ ከአንተ ጋራ እሔዳለሁ በከበረ ሥጋህም ላይ ምንም የሚበረታብህ የለም" ብሎት ሰላምታም ሰጥቶት ወደ ሰማይ ዐረገ።
❤ ከዚህም በኋላ ብፁዕ አባ ኄሮዳ ወደ ምዕራባዊ አገር ወጣ። ፊቱንም ወደ ምሥራቅ መልሶ እንዲህ ብሎ ጸለየ "ልዩ ሦስት አንድ አምላክ ሆይ ጌትነት በረከት ክብር ገንዘብህ የሆነ ለአንተም ለብቻህ ስግደትና አምልኮት የሚገባህ የተሳልኩትን እስከምፈጽም ታጽናኝ ዘንድ እለምንሃለሁ"። ይህንንም ብሎ ወደ ፍርድ ሸንጎ ሔዶ "እኔ ክርስቲያን ነኝ" ብሎ በግልጥ ጮኸ። መኰንኑም "ክርስቲያንስ ሁነሃል አገርህ ወዴት ነው? አንተ ማነህ? ስምህስ ማነው? ወገንህስ ምንድነው? አለው። የከበረ ኄሮዳም "በብህንሳ አውራጃ ስብስጣ ከሚባል
1 161
❤ "በስመ አብ ወወልደ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን።❤
❤ እንኳን ለክብር ባለቤት ለጌታችን ለአምላካችን ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ ለብርሃነ ዕርገቱ በዓል በሰላም አደረሰን።
+ + +
❤ የዕለቱ አንገርጋሪ ግእዝ ዜማ፦ "ዮም ፍሥሐ ኮነ በእንተ ዕርገቱ ለክርስቶስ እምድኅረ ተንሥአ እሙታን በዓርብአ ዕለት በይባቤ ወበቃለ ቀርን አማን መንክር ስብሐተ ዕርገቱ"። ትርጉም፦ ዛሬ በኢየሱስ ክርስቶስ ዕርገት ደስታ ሆነ ከሙታን ከተነሳ በኋላ በአርባ ቀን በእልልታ በመለከት ድምጽ ዐረገ በእውነት ድንቅ ነው የዕርገቱ ምስጋና። ሊቁ ቅዱስ ያሬድ በድጓው ላይ።
+ + +
❤ የጌታችን የአምላካችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ዕርገት፦ እርሱም በረቀቀ ጥበቡ በመከራው በሞቱና በመነሣቱ ሥራውን ከፈጸመ በኋላ አርባው ቀን ሲፈጸም በነፋሳት ክንፍ ላይ ሁኖ ዐረገ። ያን ጊዜ በኪሩቤል ላይ ተቀምጦ ወጣ በነፋሳትም ክንፎች ላይ ሁኖ ወጣ ያለው የዳዊት ትንቢት ተፈጸመ።
❤ በዚህም ዕርገቱ የሚያምኑበት በልዕልና ወደሚኖሩበት የሚዐርጉ መሆናቸው ተረዳ ተረጋገጠ ራስ በአለበት ሕዋሳት ሊኖሩ ይገባልና። አዳም አስቀድሞ በምድራዊ ርስቶች በሲኦልም እንደኖረ መኖርንም እንደቀደመ እንዲሁ ዳግማዊ አዳም ጌታ በመንግሥተ ሰማያት ርስት መኖርን ቀደመ።
❤ የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስም ዕርገቱን ከትንሣኤው አከታትሎ ወዲያውኑ አላደረገም መናፍቃን ዕርገቱ ምትሐት ናት ብለው እንዳያስቡ። ጌታችንም በረቀቀ ጥበቡ የደቀ መዛሙርቱን ተሽብሮ የነበረ ልቡናቸውን እያጽናና መነሣቱንም እያስረዳቸው ከትንሣኤው በኋላ አርባ ቀን ኖረ።
❤ በጌታችንም ዕርገት የቅዱስ ዳንኤል ትንቢት ተፈጸመ እንዲህ የሚል "ሌሊት በራእይ አየሁ እንሆ ታላቅ እንደ ሰው ልጅ የሆነ መጣ ዘመናትን ወደሚያስረጃቸው ደረሰ ከፊቱም አቀረቡት። የዘላለም አገዛዝ፣ ጌትነት፣ መንግሥት፣ የዘላለም ሥልጣን ተሰጠው ሕዝቡና አሕዛቡ ሁሉ መንደር መንድረው የሚኖሩትና ነገዱም ነገሥታቱም ሁሉ ይገዙለታል አገዛዙም የዘላለም አገዛዝ ነው መንግሥቱም የሚያልፍ የማይጠፋ ነዋሪ ነው"። ለእርሱም ምስጋና ይሁን ከቸር አባቱ ሕይወት ከሆነ መንፈስ ቅዱስም ጋር ለዘላለሙ አሜን። ምንጭ፦ የግንቦት8 ስንክሳር።
+ + +
❤ የዕለቱ የማኅሌት ምስባክ፦ "ዘምሩ ለእግዚአብሔር ዘዐርገ ውስተ ሰማይ። ሰማይ ዘመንገለ ጽባሕ። ናሁ ይሁብ ቃሎ ቃለ ኃይል"። መዝ67፥32-33። የሚነበበው ወንጌል ሉቃ24፥45-ፍ.ም።
+ + +
❤ የዕለቱ የቅዳሴ ምስባክ፦ "ዐርገ እግዚአብሔር በይባቤ። ወእግዚእነ በቃለ ቀርን። ዘምሩ ለአምላክነ ዘምሩ"። መዝ 46፥5-6። የሚነበቡት መልዕክታት ዕብ 1፥1-ፍ.ም፣ 1ኛ ጴጥ 3፥18-ፍ.ም እና የሐዋ ሥራ 1፥1-12። የሚነበበው ወንጌል ማር16፥14-ፍ.ም። የሚቀደሰው ቅዳሴ የቅዱስ ዲዮስቆሮስ ነው። መልካም የብርሃነ ዕርገቱ በዓል ለሁላችንም ይሁንልን።
https://t.me/Eotcw
