ch
Feedback
ሰዋስው ☘☘☘☘

ሰዋስው ☘☘☘☘

前往频道在 Telegram

በሰዋስወ ብርሀን ቅዱስ ዻውሎስ ገዳም እና ለተለያዩ ቤተክርስቲያን ለክብረ በአላት ማውጫ ። በተጨማሪም-ዋዜማ ሥርዓተ ማኅሌት - መዝሙራት ስንክሳር - የየእለቱን ምስባክ ቅኔያት ጥያቄዎች እንዲሁም የወቅታዊ ነገር መወያያ በተጨማሪም @eotcww ብለው ይቀላቀሉን ለወዳጅ ዘመድዎ share#Share#Share# ያድርጉ።

显示更多
1 161
订阅者
无数据24 小时
无数据7 天
无数据30 天
帖子存档
❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤ ❤ ጥቅምት ፱ (9) ቀን። ❤ እንኳን ለኢትዮጵያዊው ጻድቅ እግዚአብሔር አምላክ በአንድነቱና በሦስትነቱ ለተገለጠላቸው በስብከታቸው "የሐዋርያት አምሳል" ለተባሉት ለአባችን አቡነ መዝገበ ሥላሴ ለዕረፍታቸው በዓል በሰላም አደረሰን። + + + ❤ አቡነ መዝገበ ሥላሴ፡- በታሪካዊነቱና በያዛቸው ድንቅ ድንቅ ቅርሶች ከሚታወቀውና ኢትዮጵያዊውን ሀሳበ ዘመን በመቀመር ከሚታወቀው ከእውነተኛው የብህትውና ቦታ ከደብረ ገሪዛን ቅድስት ማርያም ጉንዳጉንዶ ገዳም የተገኙ ታላቅ አባት ናቸው፡፡ እነ አቡነ አበከረዙንን ጨምሮ የባሕረ ሐሳብ ፍልስፍናና የሥነ ጽሑፍ ማዕከል ከሆነው ከዚህ ገዳም የወጡ ገድል ተጽፎላቸው፣ ታቦት በስማቸው የተቀረጸላቸው ከ17 በላይ ታላላቅ ቅዱሳን አሉ፡፡ ❤ አቡነ መዝገበ ሥላሴም ከእነዚህ የበቁ ቅዱሳን ውስጥ አንዱ ናቸው፡፡ አባታቸው ሀብተ ጽዮን እናታቸው ማርያም ሞገሳ ሲባሉ እነርሱም በእግዚአብሔር ፊት ቅኖች ነበሩ፡፡ ማርያም ሞገሳ ዕለት ዕለት አምሃ (ስጦታ) እየያዘች ወደ ቤተ ክርስቲያን እየሄደች ስትጸልይ በአንደኛው ዕለት የታዘዘ መልአክ መጥቶ "በእግዚአብሔር ፊት ሞገስ ያገኘና የተባረከ ልጅ ትወልጃለሽ" ብሎ አበሰራት፡፡እርሷም "ከማኅፀኔ እንደፀሐይ የሚያበራ ልጅ ሲወጣ አየሁ" አለች፡፡ በዚህም መሠረት አቡነ መዝገበ ሥላሴ በምሥራቃዊ ትግራይ ዞን በገላውዴዎስ ዘመነ መንግሥት በ1532 ዓ.ም ተወለዱ፡፡ በ40ኛ ቀናቸውም ሲጠመቁ ሰጊድለአብ ተባሉ፡፡ ❤ ሰጊድለአብ ከዕለታት በአንደኛው ቀን የእግዚአብሔር መልአክ ከእናታቸው እቅፍ ውስጥ ነጥቆ ወስዶ ደብረ ከስዋ (ደብረ ገሪዛን) ጒንዳጒንዶ ቅድስት ማርያም ገዳም አደረሳቸው፡፡ ወደ ቅድስተ ቅዱሳኑም ካስገባቸው በኋላ በውስጥ የነበሩትን ንዋያት ሁሉ እያሳየ "አንተ ሕፃን ሆይ! ዕወቅ ይህ የምታየው ሁሉ የአንተ ነው፣ ትጠብቀውም ዘንድ እግዚአብሔር ሰጥቶሃል፡፡ ደግሞም የክርስቶስን በጎች ትጠብቅ ዘንድ ተሰጥቶሃልና ፈጽሞ ደስ ይበልህ" አላቸውና ፈጥኖ ወደ እናታቸው እቅፍ መለሳቸው፡፡ ዕድሜአቸውም ለትምህርት ሲደርስ ወደ ጒንዳጒንዶ ተመልሰው የሁሉንም መጻሕፍትን ምሥጢር ጠንቅቀው ተማሩ፡፡ በገዳሙም የምንኵስናን ሥራ እየሠሩ በተጋድሎ ኖሩ፡፡ ክብርት እመቤታችንም ተገልጻላቸው "ልጄ በተፈቀደልህ ተጋድሎ አሰልጥኖሃልና ጨክን፣ በርታ እኔም ከአንተ አልለይም" አለቻው፡፡ ❤ ከመነኰሱም በኋላ ስማቸው "አቡነ መዝገበ ሥላሴ" ተባሉ፡፡ አቡነ መዝገበ ሥላሴ ስብከተ ወንጌልን በመላ ሀገራችን በማስፋፋት ብዙ የደከሙ ታላቅ አባት ናቸው፡፡ በዚህም ምክንያት "የሐዋርያት አምሳል" ተብለዋል፡፡ የገዳሙ አበምኔት ሲያርፉ መነኰሳቱ በፈቃደ እግዚአብሔር አቡነ መዝገበ ሥላሴን ይዘው በግድ አበምኔትነት ሾሟቸው፡፡ እሳቸውም ከተሾሙ በኋላ በመላ ሀገራችን ተዘዋውረው ወንጌልን ሰብከዋል፡፡ ብዙ ድውያንን ፈውሰዋል፣ ሙታንን አንሥተዋል፡፡ በዓታቸውንም በማጽናት በጸሎት ተወስነው የዐይኖቻቸው ቅንድቦች እስኪላጡ ድረስ ጉንጮቻቸውም እስኪቀሉ ድረስ በጸሎት ይተጉ ነበር፡፡ 40 ቀንና 40 ሌሊትም ይጾማሉ፡፡ ስግደታቸውም በቀንና በሌሊት ያለ እረፍት እንደመንኰራኵር ፈጣን ሆነ፡፡ ወዛቸውና ዕንባቸው አንድ ላይ ተቀላቅሎ እንደጅረት እስኪፈስ ድረስ በጭንቅ ተጋድሎ እንደኖሩ ገድላቸው ይናገራል፡፡ ❤ እመቤታችንም ብዙ ጊዜ እየተገለጠችላቸው ከህመማቸው እየፈወሰች ታበረታቸው ነበር፡፡ ከዕለታትም በአንደኛው ቀን አቡነ መዝገበ ሥላሴ ራእይ ተመለከቱ፡፡ እነሆም ውበታቸው የሚያስገርም፣ መልካቸውም የሚያስደንቅ፣ የምስጋና ነፀብራቅ የከበባቸው፣ የራሳቸው ፀጉር ነጭ የሆነ ሦስት ወፎችን ተመለከቱ፡፡ አባታችንም አንድ ጊዜ ሦስት ሌላ ጊዜ ደግሞ አንድ ሲሆኑ ተመልክተው ፈጽሞ አደነቁ፡፡ እንዲህ እያደነቁ ሳለ እግዚአብሔር በቃሉ ጠርቶ ካነጋገራቸው በኋላ ብዙ ምሥጢራትን ነገራቸው፡፡ ለመረጣቸው ቅዱሳን እንዲህ መገለጥ ለእግዚአብሔር ልማዱ ነውና ለአባታችን ለአዳም፣ ለሄኖክ፣ ለኖኅ፣ለአብርሃም በልዩ ልዩ ህብር ተገልጧል፡፡ኦ.ዘፍ 3፡10፣ 5፡24፣ 6፡13፣ 18፡1፡፡ ለሕዝቅኤልም በኮበር ወንዝ፣ ለዳንኤል በሱሳ ግንብ፣ ለኢሳይያስ ሱራፌል እያመሰገኑት ተገልጦላቸዋል፡፡ ሕዝ 1፡1፣ ዳን 8፡1-3፣ ኢሳ 6፡1-3፡፡ ❤ አቡነ መዝገበ ሥላሴ በዘመን ደረጃ በኋለኛው ዘመን የተነሡ አባት ይሁኑ እንጂ በሰጡት ሐዋርያዊ አገልግሎትና ገንዘብ ባደረጉት የተጋድሎ ጽናት የከበሩ ቅዱሳን ሐዋርያትን መስለዋቸዋል፡፡ የታዘዘ መልአክ ወደ መንግሥተ ሰማያት ነጥቆ ወስዶ ማደሪያቸውን አሳይቷቸው መልሶ ወደ ምድር ካመጣቸው በኋላ የዕረፍታቸው ጊዜ እንደደረሰ ነገራቸው፡፡ "በሰኔ ወር ታርፋለህ" ቢላቸው "በሰኔማ ልጆቼ ተዝካሬን ማድረግ አይችሉም" አሉት፡፡ መልአኩም መልሶ "ዕረፍትህ በሐምሌ ይሁን" ቢላቸው ጻድቁ አሁንም "አይሆንም" ብለው ተከራከሩ፡፡ በነሐሴም እንደዚያው ሆነ፡፡ መልአኩም መስከረምን አሳልፎ በጥቅምት እንደሚያርፉ ነግሯቸው ዐረገ፡፡ ❤ ከዚህም በኋላ ለስም አጠራሩ ምስጋና ይግባውና ጌታችን ቅድስት እናቱን፣ መላእክትን፣ ቅዱሳን ጻድቃን ሰማዕታትን ሁሉ አስከትሎ መጥቶ "አንተ የዓሥራ አንደኛው ሰዓት ቅጥረኛ ወዳጄ ሆይ! (ከቅዱሳን ሁሉ በኋላ የተነሣህ-ማቴ 20፡1-5) የምስራች እነግርህ ዘንድ የድካምህም ዋጋ እሰጥህ ዘንድ መጥቻለሁ፡፡ እነሆ ከጠዋት ጀምሮ ከደከሙት ጋር አንድ አድርጌሃለሁ፡፡ ከአንተም ጋር ቃልኪዳን ገብቻለሁ፣ ስምህን በእምነት የጠራ፣ መታሰቢያህን ያደረገ፣ በጸሎትህም የታመነ እስከ ሰማንያ ሺህ ስድስት መቶ (80,600) ነፍሳት ዓሥራት ይሁኑህ…" በማለት ቃልኪዳን ከገባላቸው በኋላ ወደ ሰማያት ዐረገ፡፡ በዚያን ጊዜም አቡነ መዝገበ ሥላሴ ፊታቸው እንደፀሐይ አበራና ጥቅምት 9 ቀን ከሌሊቱ በ6 ሰዓት እንደመልካም እንቅልፍ ዐረፉ፡፡ መላ ዘመናቸው 115 ሲሆን የደብረ ገሪዛን ጒንዳጒንዶ ቅድስት ማርያም ገዳም አበምኔት ሆነው ከመሾማቸው በፊት 62 ዓመት፣ ከተሾሙበት ጊዜ እስከ ዕለተ ዕረፍታቸው ድረስ 53 ዓመት ነው፡፡ መካነ መቃብራቸው እዚያው የደብረ ገሪዛን ጉንዳጉንዶ ቅድስት ማርያም ገዳም ይገኛል፡፡ ❤ በጉንዳጉንዶና አዲግራት በሚገኘው ገዳማቸው ውስጥ በስማቸው የፈለቁ ብዙ ፈዋሽ ጠበሎች አሉ፡፡ አዲግራት የሚገኘው ገዳማቸው ውስጥ ያለው ጠበል የትኛውንም በሽታ በአስቸኳይ ፈውስ በመስጠት ይታወቃል፡፡ ተጠማቂው ሰው የማይድንም ከሆነ ቶሎ ይሞታል እንጂ ከ7 ቀን በላይ አይቆይም፡፡ ጻድቁ ብዙ የተጋደሉበት ይህ ገዳም በግራኝ አህመድ ዘመን 44 ጽላቶች ተሰውረውበታል፡፡ዮዲት ጉዲትም ልታገኘው ያልቻለችው ታላቅ ገዳም ነው፡፡ በአንድ ወቅት ከሃዲያን አሕዛብ ጦረኞች ወደ ገዳሙ ሲወጡ በተአምራት ወደ ፅድ ዛፍነት ተለውጠዋል፡፡ ፅዶቹ አሁንም ድረስ በገዳሙ ክልል ውስጥ የሚገኙ ሲሆን ፅዶቹን በእሳት አቃጥለው ከሰል ቢያደርጓቸው ደም ሆነው ይፈሳሉ እንጂ ፈጽሞ ከሰል መሆን አይችሉም። ከአቡነ መዝገበ ሥላሴ እግዚአብሔር አምላክ ረድኤት በረከታቸው ያሳትፈን፣ በጸሎታቸው ይማረን!። ምንጭ፦ መዝገበ ቅዱሳን ከሚለው መጽሐፍ የተወሰደ። ❤ በየቀኑ ይህን ቴሌግራም ላይ ማግት ከፈለጉ ከታች ያለውን ሊኩን ይጫኑት። https://t.me/Eotcw

❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤ ❤ ጥቅምት ፱ (9) ቀን። ❤ እንኳን ለኢትዮያዊው ጻድቅ በኤርትራ አገር በሐማሴን አውራጃ ከአስመራ ከተማ በስተምሥራቅ 25ኪ.ሜ ርቀት የሚገኝ አስደናቂ ገዳም ዘደብረ ቢዘን ለመሰረቱት እንደ ሐዋርያው ቅዱስ ጴጥሮስ በጥላቸው ድውያንን ይፈውሱ ለነበሩት ለአንዳዴ ባሕር ለአባታችን ለአቡነ ፊልጶስ ለልደታቸው በዓል በሰላም አደረሰን። + + + ❤ አቡነ ፊልጶስ ዘደብረ ቢዘን፦ እንደ ነቢዩ ኤርምያስ በእናታቸው ማኅፀን ሳሉ የተመረጡና እንደተወለዱ ነው ሰማንያ አንዱን የብሉይ መጻሕፍትን አጠናቀው ያወቁት ናቸው፡፡ በ12 ዓመታቸውም ለመመንኰስና ገዳም ለመግባት ወስነው ወላጅ እናታቸውን "አሰናብቺኝ" በማለት ጠይቀዋል፡፡ ቅድስት እናታቸውም መርቀው ሸኟቸውና ትግራይ ውስጥ ወደሚገኘውና ደብረ ጸራቢ ወደሚባለው ገዳም ገቡ፡፡ አስተዳዳሪ አቡነ በኪሞስም የምንኵስና ቀንበሩና ሸክሙ እጅግ ከባድ መሆኑን በመንገር ወደ እናታቸው እንዲመለሱ ቢመክሯቸውም አቡነ ፊልጶስ ግን ለምንኵስና የታጩ ሙሽራ መሆናቸውን ነገሯቸው፡፡ ከብዙ ፈተናም በኋላ አመነኰሷቸው፡፡ ❤ በገዳሙም እንጨት እየለቀሙና እየፈለጡ፣ ውኃ እየቀዱ፣ የክርስቶስን ሕማሙን ሞቱን እያሰቡ በጾምና ጸሎት ሲጋደሉ ከኖሩ በኋላ ጌታችን ተገልጦላቸው ወደ ሽሬ እንዲሄዱ ነገራቸውና ሽሬ አደያቦ ወደሚባለው ስፍራ ሄዱ፡፡ ብዙ አስደናቂ ተአምራት እያደረጉ ወንጌልን በሀገሩ ዞረው ሰበኩ፡፡ እንደ ሐዋርያው ቅዱስ ጴጥሮስ በጥላቸው ድውያንን ይፈውሱ ነበር፡፡ ከዚህ በኋላ ወደ ደብረ ቢዘን እንዲሄዱ ተነግሯቸው የእርሳቸውን በረከት ለመቀበል ከመጡ 16 ደጋግ መነኰሳት ጋር ወደ ደብረ ቢዘን ሄዱ፡፡ ይኸውም በኤርትራ ክፍለ ሀገር በሐማሴን አውራጃ ከአሥመራ ከተማ በስተምሥራቅ 25 ኪ.ሜ ርቀት ላይ የሚገኘው አስደናቂው ገዳም ነው፡፡ ❤ ጻድቁ የሐይቅ እስጢፋኖስን ባሕር በተአምራት ያቃጠሉት አባት ናቸው፡፡ በንጉሡ በዐፄ ዳዊት ዘመን ሰንበትን አንድ ብቻ ናት እያሉ በአንደኛዋ ሰንበት ሥራ ሲሠሩ ጻድቁ አቡነ ፊልጶስ ይህን ሰምተው አንዲት ሰንበት የሚሉትን ሁሉ ተቃወሟቸው፡፡ ከግብፅ የመጡት ጳጳስም ቀደም ብሎ ከአባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ አሁንም ከአቡነ ፊልጶስ ጋር ንጉሡ ዐፄ ዳዊት አከራክረዋቸው ጳጳሱም በክርክሩ ተረቱ፡፡ ክፉዎችም በአቡነ ፊሊጶስ ላይ በክፋት ተነሱባቸው፡፡ በአቁማዳ ጠቅልለው ሐይቅ ባሕር ውስጥ ጣሏቸው፡፡ በዚህም ጊዜ እሳቸው የተጣሉበት ባሕር በእሳት ተቃጥሎ ጽድቃቸውን መስክሮላቸዋል፡፡ ❤ ዛሬም ድረስ በሐይቅ እስጢፋኖስ ባሕር ዳርቻ ላይ የተቃጠለው ድንጋይ ምልክቱ በግልጽ ይታያል፡፡ በወቅቱ የንጉሡ ሚስት በዋናተኛ አስፈልጋ ከሐይቁ ውስጥ አስወጣቻቸው፡፡ እግራቸውንም አጥባቸው ስትጨርስ የእግራቸውን እጣቢ ጠጣችው፡፡ ወዲያውም "ከማኅፀንሽ ፍሬ ታላቅ ጻድቅ ልጅ ይወጣል" ብለው ትንቢት ነገሯት፡፡ በትንቢታቸውም መሠረት ታላቁ ጻድቅ ንጉሥ ዐፄ ዘርዐ ያዕቆብ ተወልዱ፡፡ በወቅቱ በተፈጠረው አለመግባባትና ክፉዎችም በባሕር ውስጥ ስለጣሏቸው ንጉሡ ዐፄ ዳዊትም አቡነ ፊልጶስን ከልብ ይቅርታ ጠይቀው ወዲያው ታርቀዋል፡፡ በዘመናቸውም ርኃብ ስለነተሳ ጻድቁን ከገዳማቸው አስጠርተው "ምን ባደርግ ይሻለኛል?" ብለው አማክረዋቸዋል፡፡ አቡነ ፊልጶስም "የጌታችንን መስቀል ያስመጡ" ብለው መከሯቸው፡፡ ❤ ንጉሡ ዐፄ ዳዊትም በአቡን ፊልጶስ ምክር መሰረት ከኢየሩሳሌም፣ ከቍስጥንጥንያና ከእስክንድርያ መንግሥታት ጋር ተጻጽፈው ዐሥሩን ታላላቅ ቅዱሳን ይዘው ሄደው መስቀሉን መስከረም 10 ቀን አምጥተውታል፡፡ ቅዱስ መስቀሉን ያመጡት ዓሥሩ ቅዱሳንም የደብረ ቢዘኑ አቡነ ፊልጶስ ፣ የጣና ደሴቱ አቡነ ኂሩተ አምላክ፣ የጣና ደሴቱ አቡነ እንድርያስ፣ አቡነ በትረ ማርያም፣ አቡነ ዮሐንስ፣ አቡነ ታዴዎስ፣ አቡነ ያፍቅረነ እግዚእ፣ አቡነ ዘካርያስ፣ አቡነ ያሳይና አቡነ ቶማስ ናቸው፡፡ አቡነ ፊሊጶስ ዘደብረ ቢዘን በታላቅ ተጋድሎ ኖረው ከጌታችን ዘንድ ታላቅ ቃልኪዳን ከተቀበሉ በኋላ ነሐሴ 5 ቀን በታላቅ ክብር ዐርፈዋል። ከአባታችን አቡነ ፊሊጶስ እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን በጸሎታቸው ይማረን!። ምንጭ፦ መዝገበ ቅዱስ ከሚለው መጽሐፍ። ❤ በየቀኑ ይህን ቴሌግራም ላይ ማግት ከፈለጉ ከታች ያለውን ሊኩን ይጫኑት። https://t.me/Eotcw

❤ "በስመ አብ ወወልደ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤ ❤ ጥቅምት ፰ (8) ቀን። ❤ እንኳን ለሽማግሌው አባት ለአባ መጥራ ሰማዕትነት ለተቀበለበት ለዕረፍት በዓል፣ ከርእርሱ ጋር ብዙዎችን በሰማዕትነት ለዐረፋበት በዓልና ተርታ ነገርንም እንዳይናገር ደንጊያ በአፉ ጎርሶ ለኖረ ለባሕታዊ ለአባ አጋቶን ለመታሰቢያው በዓል በሰላም አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰቡ፦ ከቅዱስ ባኮስና ከቅድስት በላግያ በሰማዕትነት ከዐረፋ፣ ከአባ ሖር ከመታሰቢያውና ሰማዕትነት ከሆኑ ከልጆቹና ከሶስና ይምሕው በሚባል አገር ከመታሰቢያቸው ከሆነ እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን። + + + ❤ ሽማግሌው አባት አባ መጥራ ብዙዎች ሰዎች በሰማዕትነት፦ ይህም ቅዱስ ከእስክንድርያ አገር አማኒ ክርስቲያን ነው። ከሀዲ ንጉሥ ዳኬዎስ በነገሠ ጊዜ የጣዖትን አምልኮ አቁሞ የክርስቲያንን ወገኖች አሠቃያቸው። ትእዛዙም ወደ እስክንድርያ አገር ደርሶ ሰዎቿን ሁሉንም አሠቃያቸው የብዙዎች ምእመናንንም ደማቸውን አፈሰሰ። ያን ጊዜ ክርስቲያን እንደ ሆነ ቅዱስ መጥራን በመኰንኑ ዘንድ ወነጀሉት፤ መኰንኑም ወደርሱ አስቀረበው እርሱም ብቻውን እውነተኛ አምላክ እንደ ሆነ ክብር ይግባውና በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ታመነ። ❤ መኰንኑም "ለአማልክት ስገድ እኔም ብዙ ገንዘብን እሰጥሃለሁ ታላቅ ክብርንም አከብርሃለሁ" አለው። እርሱም ቃል ኪዳኑን አልተቀበለም "ኪዳንህና ገንዘብህ ካንተ ጋራ ወደ ጥፋት ይሒድ" አለው እንጂ። መኰንኑም በእርሱ ላይ ተቆጥቶ "እኔ በጽኑዕ ሥቃይ እቀጣሃለሁ" አለው። ❤ ቅዱስ መጥራም ፈርቶ ከበጎ ምክሩ አልተመለሰም እንዲህም አለው እንጂ "እኔ ሰማይና ምድርን ለፈጠረ ለሕያው እግዚአብሔር እሰግዳለሁ። ለረከሱ ጣዖታት ከደንጊያና ከዕንጨት ለተሠሩ ለማያዩ ለማይሰሙ ለማይናገሩ ለማያሸቱ ለማይንቀሳቀሱ እንሰግድ ዘንድ እንዴት ይገባል" አለው። መኰንኑም በሰማ ጊዜ አፈረ። ጽኑ ግርፋትንም እንዲገርፉት አዘዘ። ❤ ከዚህም በኋላ በክንዱ ሰቀሉት በደረቀች ሽመልም ጎኖቹን ሠነጠቁ ቀደዱትም ክብር ይግባውና ጌታ ኢየሱስም አዳነው። ያለ ጥፋትም በጤንነት አስነሣው መኰንኑም ማሠቃየቱን በሰለቸ ጊዜ ራሱን በሰይፍ እንዲቆርጡ አዘዘ። ከከተማውም አውጥተው የከበረች ራሱን ቆረጡ። ሌሎች ብዙዎች ሰማዕታትንም ከእርሱ ጋር ራሶቻቸውን ቆረጡ። የሰማዕትነት አክሊልንም በመንግሥተ ሰማያት ተቀበሉ። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በአባ መጥራ ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን። + + + ❤ ባሕታዊ አባ አጋቶን፦ ይህም አባት ወደ ቲቤያድ ገዳም ሲመጣ ገና ሕፃን ነበር። ያሳደገው ያስተማረው አባ ጴማን ነው። በመቀጠልም ወደ አስቄጥስ ተጉዞ ከአባ እስክድር እና ዞይለስ ጋር ለጥቂት ጊዜ ኖሯል። ገዳመ አስቄጥስ ለመጀመርያ ጊዜ ሲጠፋ አባ አጋቶን ከደቀ መዝሙሩ ከአባ አብርሃም ጋር በመሆን ከደብረ ትሮኤ ሳይርቅ ከዓባይ ወንዝ አጠገብ መኖር ጀመረ። ❤ አንድ ጊዜ ስለ አባ አጋቶን፡ትሕትና የሰሙ መነኰሳት ሊያዩት መጡ። የቁጣ ስሜቱን ወተውንና አለመተውን ለማረጋገጥ ብለው "አመንዝራውና ትዕቢተኛው አጋቶን ማለት አንተ ነህ?" አሉት። አባ አጋቶንም "አዎ ትክክል ነው" አላቸው። ቀጥለውም "ፍሬ የሌለው ነገር ዘወትር የምታወራ አጋቶን ማለት አንተ ነህ?" አሉት "አዎ ነኝ" አላቸው። "መናፍቅ አጋቶን ማለት አንተ አይደለህምን?" ሲሉ ጠየቁት ያን ጊዜ ግን "መናፍቅስ አይደለሁም" ሲል መለሰላቸው። በዚህ ጊዜ "እስካሁን የተናገርንብህን ሁሉ ተቀብለህ የመጨረሻውን ለምን ተቃወምክ?" አሉት። አባ አጋቶንም "የመጀመሪያያዎቹን ወቀሳዎች ለነፍሴ ተስማሚዎች ናቸውና ተቀበልኳቸው። ኑፋቄ ግን ከእግዚአብሔር መለየት ነው እናም እኔ ከፈጣርዬ መለየት አልፈልግም" አላቸው። በዚህ የተነሣም የርሱ ሕይወት አስደነቃቸው። ❤ አንድ ቀን አባ አጋቶን በእጁ የሠራቸውን ነገሮች ለመሸጥ ወደ ገበያ ሲወጣ በመንገድ ዳር አንድ ሽባ ሰው አገኘ። ሽባውም የት እንደሚሄድ አባ አጋቶንን ጠየቀው። "አንዳንድ ነገሮች ለመሸጥ ወደ ገበያ እሔዳለው" አለው። ሽባው ሰውም "እባክህ ተሸከምህ ወደዚያ ውሰደኝ" ሲል ለመነው። አባ አጋቶንም ያንን ሰው ተሸክሞ ወደ ከተማ ወሰደው። ሽባው ሸውዬ "ዕቃዎችን ከምትሸጥበት ቦታ አጠገብ አኑረኝ" አለው። አባ አጋቶንም እንደዚያው አደረገው። አባ አጋቶን የመጀመርያውን ዕቃ ሲሸጥ "ምን ያህል ሸጥከው?" ብሎ ሽባው ሰው ጠየቀው። እርሱም ዋጋውን ነገረው። ያም ሽባ ሰው "እባክህ ዳቦ ግዛልኝ" ሲል ለመነውና ገዛለት። ❤ አባ አጋቶን ሁለተኛው ዕቃ ሲሸጥ "ምን ያህል ሸጥከው" ሲል ያሰው ጠየቀው። እርሱም ዋጋው ነገረው "እባክህ ይህን ነገር ግዛልኝ" ሲል ለመነው። አባ አጋቶንም ገዛለት። በዚህም መልኩ ሁሉንም ዕቃዎች ሸጦ በጨረሰ ጊዜ ያሽባ ሰው "ወደ በዓትህ ትመለሳለህን?" ሲል ጠየቀው "አዎ" "እንግደውስ እባክ ቀድሞ ወደአገኸኝ ስፋራ አዝለህ መልሰኝ" አለው። አባ አጋቶንም ያን ሽባ ሰው ተሸክሞ ወደ ቀድሞ ቦታው መለሰው። በዚህ ጊዜ ሽባው ሰው "አባ አጋቶን በሰማይና በምድር በረከት ተሞላህ" ብሎ ተናገረው። ወድያው አባ አጋቶን አይኑን አንስቶ ሽባው ቢያየው በቦታው የለም። ሊፈትነው ይህን ያደረገው መልአከ እግዚአብሔር ነበር። ከአባታች ከአባ አጋቶን እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን በጸሎታቸውም ይማረን!። ምንጭ፦ በበረሐው ጉያ ውስጥ ከሚለው መጽሐፍ ዲያቆን ዳንኤል ክብረት ከጻፈው። + + + ❤ "ሰላም ለመጥራ ምስለ ሰማዕታት ማኅበሩ። አመ አሰፈዎ መኰንን ከመ ይጸግዎ ሀብታተ ክቡሩ። ዘኢተመይጠ ምንተኒ እምነ ሠናይ ምክሩ። በሕለት ይቡስ እስከ ገቦሁ ሰቈሩ። ወእስከ በሰይፍ ክሣዶ መተሩ"። ሊቁ አርከ ሥሉስ (አርኬ) የጥቅምት 8። + + + ❤ የዕለቱ ምስባክ፦ "እግዚአብሔር ኢያስተጼንሶሙ እምበረከቱ ለእለ የሐውሩ በየውሀት። እግዚኦ አምላከ ኃያላን። ብፁዕ ብእሲ ዘተወከለ ኪያከ"። መዝ 83፥11-12። የሚነበቡት መልዕክታት ፊሊ 1፥19-ፍ.ም፣ ያዕ 1፥2-7 እና የሐዋ ሥራ 14፥19-ፍ.ም የሚነበበው ወንጌል ሉቃ 21፥12-21። የሚቀደሰው ቅዳሴ የቅዱስ ባስልዮስ ቅዳሴ ነው። መልካም በዓልና የጾም ጊዜ ለሁላችንም ይሁንልን። ❤ በየቀኑ ይህን ቴሌግራም ላይ ማግት ከፈለጉ ከታች ያለውን ሊኩን ይጫኑት። https://t.me/Eotcw

1.51 KB

7/2/2014 ዓ.ም (፯/፪/፳፻፲፬ ዓ.ም) 🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯 በእለቱ በቅዳሴ ሰዓት የሚባል ምስባክ 🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯 ጸርሑ ጻድቃን ወእግዚአብሔር ሰምዖሙ። ወእምኵሉ ምንዳቤሆሙ አድኅኖሙ። ቅሩብ እግዚአብሔር ለየዋሃነ ልብ፡፡ መዝ. 33፥17 🕯 ትርጉም ጻድቃን ጮኹ፤ እግዚአብሔርም ሰማቸው። ከመከራቸውም ዅሉ አዳናቸው። እግዚአብሔር ልባቸው ለተሰበረ ቅርብ ነው። 🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯

❤ "በስመ አብ ወወልደ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤ ❤ ጥቅምት ፯ (7) ቀን። ❤ እንኳን ለከበረ አባት ጠመው ከሚባል አገር ለሆነ ስለጌታችን ፍቅር ብሎ መከራውን እያሰበ ራሱን ሰባት ጊዜ ለገደለው ለአባ ባውላ ለዕረፍት በዓል በሰላም አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰቡ፦ ከአባ ባውላ ረድእ አባ ሕዝቅኤል ከመታሰቢያቸው፣ ከቅዱሳን ሰማዕታት ከሚናስና ከሐናሲ ከመታሰቢያቸው እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን። + + + ❤ ጠመው ከሚባል አገር የሆነ አባ ባውላ፦ ይህም ቅዱስ ከታናሽነቱ መስተጋድል መነኲሴ ሆነ የሚኖረውም በላይኛው ግብጽ በአለ በእንጽና ገዳም ነው ስሙ ሕዝቅኤል የሚባል ረድእ አለው። እርሱም ስለ ትሩፋቱና ስለ ተጋድሎው ምስክር ሆነ ይህ አባ ባውላ ስለ ክርስቶስ ፍቅር ራሱን ሰባት ጊዜ ገድሏልና። ❤ መጀመሪያው ራሱን በዕንጨት ላይ ዘቅዝቆ በመስቀል አርባ መዓልት አርባ ሌሊት እንደ ተሰቀለ ኖረ። ደሙም በአፍንጫው ፈሰሰ ነፍሱንም አሳለፈ እግዚአብሔርም ከሞት አነሣው። ❤ ሁለተኛው ዓሣዎችና ዓንበሪዎች እንዲበሉት ራሱን ከባሕር ጨመረ እነርሱ ግን አልነኩትም በባሕርም ሠጥሞ ብዙ ወራት ኑሮ ሞተ። ክብር ይግባውና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስም ዳግመኛ ከሞት አስነሣው። ❤ ሦስተኛም ጊዜ ራሱን በአሸዋ ውስጥ ደፍኖ ሞተ ጌታችንም አስነሣው። አራተኛም በውስጡ ስለታሞች ድንጋዮች ካሉት ረጅም ተራራ ላይ ወጥቶ ራሱን ከተራራው ላይ ወደ ታች ወርውሮ ተንከባለለ የተሳሉ ደንጊያዎችም በሥጋው ሁሉ ገብተውበት ሞተ። ረድኡም ያለቅስለት ነበረ ጌታችንም መጥቶ ከሞት አሥነሣው አጽናናውም። ❤ አምስተኛ ከረጅም ዛፍ ላይ ወጥቶ ከስለታም ደንጊያ ላይ ራሱን ወረወረ ከሁለትም ተከፈለና ሞተ ያን ጊዜም ጌታችን አስነሣው። ስድስተኛ ራሱን በእግሮቹ ውስጥ አሥሮ አርባ መዓልትና አርባ ሌሊት እንዲህ ሁኖ ሞተ እግዚአብሔርም መልአኩን ልኮ ከሞት አነሣው አጽናናውም። ❤ ሰባተኛ ከውኃ ጉድጓድ ውስጥ ገብቶ እጆቹን ዘርግቶ አርባ መዓልት አርባ ሌሊት በመቆም ሞተ ክብር ይግባውና ጌታችንም አስነሣው እንዲህም ብሎ አጽናናው "ወዳጄ ባውላ ሆይ ራስህን ሰባት ጊዜ እስከምትገድል ድረስ ሰውነትህን አደከምክ እንግዲህ ድካምህ ይብቃህ"። ❤ አባ ባውላም ለመድኃኒታችን እንዲህ ብሎ መለሰለት "ጌታዬ ሆይ ስለ ከበረው ስምህ እደክም ዘንድ ተወኝ አንተ አምላክ ስትሆን ስለኛ በመከራ ደክመህ ስለ ሰው ወገን ሞትክ ለእኛ ይህ አይገባንም ነበር በቸርነትህ ይህን የማዳንህን ሥራ ሠራህልን እንጂ"። ጌታችንም ከአጽናናው በኋላ ከእርሱ ወደ ሰማይ ወጣ። ❤ ከዚህም በኋላ አባ ብሶይ ወደ እንጽና ገዳም ሒዶ ከአባ ባውላ ጋር ተገናኘ ጌታችንም ለአባ ባውላ ተገልጾለት "ሥጋህ ከአባ ብሶይ ሥጋ ጋር በአንድነት ይኑር" አለው ሁለቱም በዐረፉ ጊዜ ሥጋቸውን በአንድነት አኖሩ። ወገኖቹም የአባ ብሶይን ሥጋ ወደ አስቄጥስ ገዳም ሊወስዱ በወደዱ ጊዜ በመርከብ ጫኑት መርከቢቱ ግን መንቀሳቀስን እምቢ አለች። ❤ ከዚህም በኋላ ተመልሰው የአባ ባውላን ሥጋ አምጥተው በመርከብ ላይ ጫኑት ያን ጊዜ መርከቢቱ ተጓዘች። እንዲህም የቅዱሳኑን ሥጋቸውን ወደ አስቄጥስ ገዳም አድርሰው በአባ ብሶይ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ በአንድነት አኖሩ እስከ ዛሬም በዚያ ይኖራሉ። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳን ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን። ምንጭ፦ የጥቅምት 7 ስንክሳር። + + + ❤ "ሰላም ለርእስከ ዘመንፈስ ቅዱስ አጽንዓ። ከመ ትሰቀል ቍልቍሊተ መጠነ መዋዕል አርብዓ። ባውላ ጻድቅ ዘትጼኑ ቆዐ። ውስተ ገድል ጽኑዕ ዘአልቦ ምምዓ። ወደቀ ስብዐ። ወተንሣ እስከ ሰብዐ"። ሊቁ አርከ ሥሉስ (አርኬ) የጥቅምት 7። + + + ❤ የዕለቱ ምስባክ፦ "ጸርሑ ጻድቃን ወእግዚአብሔር ሰምዖሙ። ወእምኵሉ ምንዳቤሆሙ አድኅኖሙ። ቅሩብ እግዚአብሔር ለየዋሃነ ልብ"። መዝ 33፥17-18። የሚነበቡት መልክታት 2ኛ ቆሮ 11፥23-ፍ.ም፣ ያዕ 1፥12-17 እና የሐዋ ሥራ 21፥12-17። የሚነበበው ወንጌል ማቴ 19፥25-ፍ.ም። የሚቀደሰው ቅዳሴ የሠለስቱ ምዕት ቅዳሴ ነው። መልካም በዓልና የጾም ጊዜ ለሁላችንም ይሁንልን። ❤ በየቀኑ ይህን ቴሌግራም ላይ ማግት ከፈለጉ ከታች ያለውን ሊኩን ይጫኑት። https://t.me/Eotcw

ጥያቄ ፫ ከሰማይ የዘነበው በእሳት የጠፋው ከተማ ምን ይባላል?
Anonymous voting

ጥያቄ ፪  በመስቀል ላይ እያለ፣ በዚያ የቆሙት ሰዎች ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ ማን ይጠራል ነበር ያሉት ?
Anonymous voting

ጥያቄ ፩ የአይኑን ብርሃን ያገኘው እየለመነ በመንገድ ዳር ተቀምጦ የነበረው ሰው ስም ማን ነበር ?
Anonymous voting