ሰዋስው ☘☘☘☘
前往频道在 Telegram
በሰዋስወ ብርሀን ቅዱስ ዻውሎስ ገዳም እና ለተለያዩ ቤተክርስቲያን ለክብረ በአላት ማውጫ ። በተጨማሪም-ዋዜማ ሥርዓተ ማኅሌት - መዝሙራት ስንክሳር - የየእለቱን ምስባክ ቅኔያት ጥያቄዎች እንዲሁም የወቅታዊ ነገር መወያያ በተጨማሪም @eotcww ብለው ይቀላቀሉን ለወዳጅ ዘመድዎ share#Share#Share# ያድርጉ።
显示更多1 161
订阅者
无数据24 小时
无数据7 天
无数据30 天
帖子存档
1 161
🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺
ግንቦት 12 ተክለሃይማኖት ወክርስቶሰ ሰምራ ሥርዓተ ማኅሌት
🍂🍂🍂🍂🍂🍂🍂🍂🍂🍂🌷🍂🍂
ስምዓኒ እግዚኦ ጸሎትየ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ ወይብጻሕ ቅድሜከ ገአርየ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ ወኢትሚጥ ገጸከ እምኔየ በዕለተ ምንዳቤየ አጽምእ እዝነከ ኀቤየ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ አመ ዕለተ እጼውአከ ፍጡነ ስምዓኒ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ ለዓለም ወለዓለመ ዓለም ሃሌ ሉያ ዘውእቱ ብሂል ንወድሶ ለዘሃሎ እግዚአብሔር ልዑል ስቡሕ ወውዱስ ዘሣረረ ኲሎ ዓለመ በአሐቲ ቃል
@EOTCW
@EOTCW
ነግሥ
ሰላም ለአብ ገባሬ ኲሉ ዓለም ለወልድ ሰላም ወለመንፈስ ቅዱስ ሰላም ለማርያም ሰላም ወለመላእክት ሰላም ሰላም ለነቢያት ወለሐዋርያት ሰላም ለሰማእታት ሰላም ወለጻድቃን ሰላም
@EOTCW
ዚቅ
ሰላም ለክሙ ኦ ማኅበራኒሁ ለክርስቶስ እለ ተጋባዕክሙ ውስተ ዝንቱ ቤት ጳጳሳት ቀሳውስት ወዲያቆናት ሰላም ለክሙ ማኅበረ ደናግል ወመነኮሳት እለ ተመሰልክሙ ከመ መላእክት
@EOTCW
@EOTCW
መልክዐ ሚካኤል
ሰላም ለሕፅንከ እንተ በዲቤሁ ሕቁፍ ጸሎተ ቅዱሳን ውኩፍ ሚካኤል ክቡር መስፍነ ትጉሃን አዕላፍ ለረዲኦትየ ከመ ዘይሠርር ዖፍ እንዘ ትሠርር ነዓ በክልኤ አክናፍ
@EOTCW
@EOTCW
ዚቅ
ወሚካኤል አሐዱ እመላእክት እምቅዱሳን ቀደምት እስመ በዲበ ሠናይቱ ለሰብእ ተአዛዚ
ወረብ
ሚካኤል መልአክ አሐዱ አሐዱ እመላእክት
እስመ በዲበ ሠናይቱ ለሰብእ ተአዛዚ
@EOTCW
@EOTCW
ነግሥ
ሰላም ለገቦከ በአክናፈ ብርሃን ግልቡብ: እንተ በዲቤሁ ይጼልል መንፈሰ ኪሩብ: ሚካኤል መልአኩ ለእግዚአብሔር አብ: አጥረየ በረድኤትከ መዓርገ ስብሐት ዕፁብ :ተክለሃይማኖት የዋህ ወብእሲ ጠቢብ
@EOTCW
ዚቅ
ተክለሃይማኖትኒ ይቤ ነዋ ሚካኤል አሐዱ እመላእክት እምቅዱሳን ቀደምት መጽአ ይርድዓኒ አጽንዓኒ ወይቤለኒ ኢትፍራህ ብእሴ ፍትወት አንተ ሰላም ለከ ጽናዕ ወተአገሥ ወእንዘ ይትናገረኒ ጸናዕኩ ወእቤሎ ንግረኒ እስመ አጽናዕከኒ ወይቤለኒ ሶበ ተአምር ዳዕሙ ሚካኤል መልአክክሙ
@EOTCW
@EOTCW
ወረብ
ይቤ ነዋ ሚካኤል አሐዱ እመላእክት እምቅዱሳን ቀደምት እምቅዱሳን
መጽአ ይርድዓኒ ይቤ ተክለሃይማኖት
@EOTCW
@EOTCW
መልክዐ ተክለሃይማኖት
ሰላም ለዝክረ ስምከ ዘጥንተ ፊደሉ መስቀል ስም ክቡር ወስም ልዑል ተክለሃይማኖት ማቴዎስ በዓለ ቀዳማይ ወንጌል ከመ እወድሰከ መጠነ አውሥኦተ እክል ማዕሠረ ልሳንየ ትፍታሕ ማርያም ድንግል
@EOTCW
@EOTCW
ዚቅ
ናሁ ዝክርከኒ ኢይጠፍዕ ወመንፈስከኒ የዓቅቡ መላእክት በሰማያት ኢይትኃጎል ሥጋከ በዲበ ምድር ብጹዕ ብእሲ ዘይፈርሆ ለእግዚአብሔር
@EOTCW
@EOTCW
ወረብ
ናሁ ዝክርከኒ ኢይጠፍዕ ወመንፈስከኒ የዓቅቡ መላእክት
ኢይትኃጎል ሥጋከ ሥጋከ ተክለሃይማኖት
@EOTCW
@EOTCW
መልክዐ ተክለሃይማኖት
ሰላም ለልብከ ቅዱስ ወቡሩክ ዘዐቀበ ሕጎ ለወልደ ማርያም አምላክ ተክለሃይማኖት አሐዱ እምዐሳባውያን ዘሠርክ እምይእቲ ዐስበ ፃማከ ዘኢትትኃደግ በበክ ያስተሣትፈኒ ለፅሩዕ ሚካኤል መልአከ
@EOTCW
@EOTCW
ዚቅ
መላእክት ወሰብእ አሐዱ ማኅበሮሙ በእንተ መስቀሉ ለክርስቶስ አለደ መርዔተ ኮኑ
@EOTCW
@EOTCW
ወረብ
አሐዱ ማኅበሮሙ ክርስቶስ ሠምራ ወተክለሃይማኖት
በእንተ መስቀሉ ለክርስቶስ አሐደ መርዔተ ኮኑ
@EOTCW
@EOTCW
መልክዐ ተክለሃይማኖት
ሰላም ለፍልሰተ ሥጋከ እምውሳጤ ገዳም ዔላመ ወእምነ ዔላምኒ ደብረ ሊባኖስ ዳግመ ተክለሃይማኖት ባህለ ከመ ወንጌላዊ ቀደመ እመ ረከቡ ደቂቅከ በዓለም ሕማመ በኀቤከ አባ ይርከቡ ሰላመ
@EOTCW
@EOTCW
ዚቅ
ትዌድሶ ደብረ ሊባኖስ ገዳሙ ለተክለሃይማኖት ጻድቅ መጠነ በዝኃ ሕማሙ ትዌድሶ ደብረ ሊባኖስ ገዳሙ እስመ በውስቴታ ተገብረ ፍልሰተ ሥጋሁ ወዓፅሙ ትዌድሶ ደብረ ሊባኖስ ገዳሙ እምነ አድባራት ኲሎን ዘተለዓለት በስሙ ትዌድሶ ደብረ ሊባኖስ ገዳሙ ኢየሱስ ክርስቶስ እንተ ቀደሳ በደሙ ትዌድሶ ደብረ ሊባኖስ ገዳሙ ትዌድሶ ደብረ ሊባኖስ ገዳሙ።
@EOTCW
@EOTCW
ዓዲ ዚቅ
ተክለሃይማኖት ድንግል ወንጹሕ ይጸርሕ እንዘ ይብል እስመ አብርሃት ለዛቲ መካን ፈድፋደ እምኮከበ ጽባሕ።
@EOTCW
@EOTCW
መልክዐ ክርስቶስ ሠምራ
ሰላም ለጣዕመ ስምኪ ወለዝክረ ስምኪ በዕሬና አምሳለ ብሩር ወወርቅ እለ ይጼአና ሀላዊተ መቅደስ ክርስቶስ ሠምራ አምሳለ ስምዖን ወሐና እንዘ ትተልዊ ዘተክለሃይማኖት ፍና እፎኑመ ረሰይኪያ በዓተ ለፃና።
@EOTCW
@EOTCW
ወረብ
እንዘ ትተልዊ ክርስቶስ ሠምራ ዘተክለሃይማኖት ፍና ዘተክለሃይማኖት:
እፎኑመ ረሰይኪየ በዓተ ለፃና
@EOTCW
@EOTCW
ወረብ
ኢይፃሙ ዘአፍቀራ ለክርስቶስ ሠምራ ዘአፍቀራ ኢይፃሙ/2/
ሕስዋ ወትልዉ አሠሮ ለተክለሃይማኖት/2/
@EOTCW
@EOTCW
ምልጣን
አባ አቡነ አቡነ መምህርነ እምአዕላፍ ህሩይ ሐውጽ እምሰማይ ብርሃነከ ከመ ንርዓይ አማን ተክለሃይማኖት ፀሐይ።
@EOTCW
@EOTCW
አመላለስ
አማን በአማን
ተክለሃይማኖት ፀሐይ
@EOTCW
@EOTCW
እስመ ለዓለም
በትንሣኤከ እግዚኦ ተዘከረኒ አመ ትመጽእ በመንግሥትከ በትንሣኤከ እግዚኦ ተዘከረኒ ምስለ ኲሎሙ ቅዱሳኒከ በትንሣኤከ እግዚኦ ተዘከረኒ ምስለ አዕላፍ መላእክቲከ በትንሣኤከ እግዚኦ ተዘከረኒ አመ ይረስና ሰማያት ወምድር በትንሣኤከ እግዚኦ ተዘከረኒ አመ ጻድቃን እምዕፁብ ይድኅኑ በትንሣኤከ እግዚኦ ተዘከረኒ በትንሣኤከ እግዚኦ ተዘከረኒ
@EOTCW
@EOTCW
ዓዲ
እስመ ለዓለም
ሊቀ ካህናት ክርስቶስ ተኆለቊ ምስለ ጊጉያን ከመ ይደምረነ ምስለ ነፍሰ ፃድቃን ሐመ በፈቃዱ ወተቀብረ በሥምረቱ ከመ ኪያነ ይርዳዕ ወይቤዝወነ ወልድ ተንሥአ
🇪🇹👇👇👇👇👇👇🇪🇹
👉@EOTCW👈
👉@EOTCW👈
👉@EOTCW👈
🇪🇹👆👆👆👆👆👆🇪🇹
@EOTCW
# Join & share #
1 161
እናገኘወዋለን በደብረ ሐዊ በራስ ዳሽን ተራራ ለ፳፪ ዓመታት በምናኔ መኖሩን ልብ ይሏል
፠ የቅኔ ጀመሪ ነው ስንለው መተርጉም ሁኖ እናገኘዋለን ድጓው ከብሉይ ከሐዲስ የተውጣጣ ነውና
፠ነቢይ ነው ስንል ሐዋርያ ሁኖ እናገኘዋለን ስለዳግም ምጽዐት ስለ መንግስተ ሰማያት የተናገረው ልብ ይሏል
፠ሐዋርያ ነው ስንል ሰማዕት ሁኖ እናገኘዋለን (እግሩን በጦር መወጋቱ ልብ ይሏል)
፠በዓለም አቀፍ ደረጃ የዜማ ምልክቶች ባልታወቁበት ጊዜ ዜማዎቹን በምልክት የቀመረ በዚህም ምክንያት ብዙዎቹ የምዕራባውያን ሀገር የሙዚቃ ባለሙያዎች ቅዱስ ያሬድን የነሱ ሀገር ተወላጅ ለማድረግ ይዳዳቸዋል ፡፡
ይህን ቅዱስ ለኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን መሰረቷ ጉልላቷ ኩለንታዋ ነው፡፡ ግን እሱ እንደሆነላት ቤተክርስቲያኒቱ እና ምዕመኖቿ ውለታውን ረስተው በእሱ ስራ ልክ አልዘከርነውም በርዕደ መዲናዋ በአዲስ አበባም በስሙ የታነጸ ቤ/ክ አንድ ሲሆን ይህም ቅዱሱ የሰራውን ስራ የማይመጥን እና ማቃለል ይመስለኛል ለዚያውም በተወለደበት ሀገሩ አስታዋሽ ማጣት ችግሩን ያከብደዋል፡፡
###እናም እኛ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤ/ክ ካህናት, ዲያቆናት, ምዕመናን እና ምዕመናት ##ለማህሌቱ ##አባት በስሙ በተሰየሙ አብያተ ክርስቲያናት በመሄድ ##ለማህሌቱ አባት ማህሌቱን እናቅርብለት
ሰላም ለዝክረ ስምከ እኩት ወብሩክ
በቃለ ፈጣሪ አምላክ
መዝሙረ በረከት ያሬድ ከመአብርሃም አርክ
አስተበቁዐከ ለለጊዜ ጽባህ ወሰርክ
ከመታድኅነኒ እመንሱት ወሀውክ
ከርዕሰ ሊቀሊቃውን ከቅዱስ ያሬድ ረድኤት በረከት ያሳትፈን
ሠናይ በዓል
1 161
#ግንቦት ፲፩ በዓለ ስዋሬሁ ለቅዱስ ያሬድ
#ልደተ ቅዱስ ያሬድ
ቅዱስ ያሬድ ከአባቱ ከይስሐቅ ከእናቱ ከክርስቲና ሚያዝያ ፭ ቀን በ፭፻፭ ዓ.ም በአክሱም ከተማ ተወለደ፡፡
ያሬድ ማለት እንዚራ መሰንቆ በገና ማለት ነው እነዚህ ባለሙያዎች በባለሙያ ሲመቱ ሁሉን እንደሚያስደስቱ በንጉሰ ነገስቱ በክርስቶስ አደባባይ በቤ/ክ የቅዱስ ያሬድ ጣዕመ ዜማ ሲሰማም መላዕክትን እና ሰውን ያስደስታልና
❀አንድም ያሬድ ማለት ርደት ወሪድ መውረድ ማለት ነው ሰማያውን ዜማ ከሰማይ ወደ ምድር አውርዷልና
✿አንድም ያሬድ ማለት ንብ ማለት ነው ንብ የማይቀምሰው አበባ እንደሌለ ሁሉ ያሬድም የማይቀምሰው መጻሕፍት የለምና
✿አንድም ያሬድ ማለት ረአዬ ምስጢር ነጻሬ ኅብዐት ማለት ነው የመላዕክት ምስጢራት የነበሩትን ጸዋትወ ዜማ አምልቶ አስፍቶ ተናግሯልና ነጻሬ ኅብዐት አለ ኅብዕ(ስውር) የሆነውን ገድለ ሰማዕታ ወጻድቃን ነቢያት ወሐዋርያትን አምልቶ አስፍቶ ተናግሯልና
✿እግዚአብሔር ለቅዱስ ያሬድ ይህንን ሁሉ ጥበብና ትምህርት ለቅዱስ ያሬድ በአንዴ ያልገለጸለት በራሴ አመጣሁት ብሎ በልቡናው መታበይ እንዳያድርበት ብሎ ነው(የሐዊራ የብስድራ እስክንድራን ታሪክ ልብ ይሏል)
★የቅዱስ ያሬድ ድርሰቶች
፩. ምዕራፍ ሲሆን በውስጡ ውዳሴ ማርያም ዜማ, መስተጋብዕ, አርያም, አርባዕት, ሠለስት, ክስተትን ያጠቃልላል
፪. ጾመ ድጓ በዐቢይ ጾም ወቅት የሚባል
፫. ድጓ በአራቱ ክፍላተ ዘመናት የተቀመረ
፬. ዝማሬ በድርገት ሰዓት ለቅዱስ ቁርባኑ ክብር የሚዘመር
፭. መስዋዕት በሞተ ሥጋ ላረፈ ሰው የሚደርስ ጸሎተ ፍትሐት
፮. ፲፬ቱ ቅዳሴትን የደረሱት ፲፬ ሊቃውንት ሲሆኑ ዜማውን ግን የደረሰው ሊቁ ያሬድ ነው
፯. አንቀጸ ብርሃን ንባቡን እና ዜማውን የደረሰው ቅ.ያሬድ ነው፡፡
★የቅዱስ ያሬድ አስደናቂ ነገሮች
፠ መምህር ነው ስንል መናኝ ሁኖ
1 161
ታላቅ የንግስ ጉዞ የፃዲቁ ወዳጅ ሁላ ሼር ሼር
ወደ ደብረ ሊባኖስ አቡነ ተክለሀይማኖት ገዳም
#አባቴ_የሚለኝ_ሁሉ_ይምጣ_በእለተ_ፉልሰቴ
ያኔ እኔና ቅዱሱ ሚካኤል መተን ህዝቡን እንባርካለን
_ የጉዞ ቀን: ግንቦት 12/2014 ዓ.ም በእለተ አርብ
_የጉዞ ሁኔታ :ደርሶ መልስ
_ዋጋ: 350 ብር ብቻ ። የደርሶ መልስ እና ምግብ እና ዉሃን ጨምሮ
አዘጋጅ : ማህበረ ኪዳነ ምህረት ዘ ውሎ በገዳማት
_የጉዞ መነሻ ሠአት : ከጠዋቱ 12 ሠዐት
_መመለሻ : በዕለቱ ከ ንግስ በሃላ
_መነሻ ቦታ : ፒያሳ (አራዳ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን 2, መገናኛ ውሃ ታንከር ጋር
ለመመዝገብ
ፈጥነዉ ይመዝገቡ !
ለበለጠ መረጃ
0942386083
0925939514 ይደዉሉ
የእግዚአብሔር መልካም ፈቃድ ይሁን !
1 161
#ምስባክ
መዝ ፫፥፭
አንሰ ሰከብኩ ወኖምኩ
ወተንሣእኩ እስመ እግዚአብሔር እንሥአኒ
ኢይፈርህ እምአእላፍ አሕዛብ
#ትርጉም
እኔ ተኛሁ አንቀላፋሁም፤
እግዚአብሔርም ደግፎኛልና ነቃሁ።
ከሚከብቡኝ ከአእላፍ ሕዝብ አልፈራም።
1 161
❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤
❤ እንኳን ለትንሣኤ አራተኛ ሳምንት በሰላምና በጤና እግዚአብሔር አምላክ አደረሰን።
+ + +
❤ የዚህ ሳምንት መዝሙር፦ "ተንሥአ ወአንሥአ ኵሎ ሙታን ተንሥአ ወአንሥአ ኵሎ ሙታን ወፈትሖሙ ለሙቁሐን፤ አዝ፣ በዐቢይ ኀይል ወሥልጣን ወአግዐዘ ነፍሰ ጻድቃን፤ አዝ፣ ለአልዓዛር ተንሥእ ዘይቤሎ ወዕውርኒ ዘፈወሶ በቃሉ፤ አዝ፣ ትንሣኤሁ ገብረ በሰንበት በሣልስት ዐዕት ተንሥአ ወአንሥአ ኵሎ ሙታን ተንሥአ ወፈትሖሙ ለሙቁሐን"። ትርጉም፦ ተነሣ ሙታንንም አስነሣ እስረኞችን ፈታቸው፤ በታላቅ ኀይልና ሥልጣን ተነሣ፤ የጻድቃንን ነፍስ ነጻ አወጣ፤ አልዓዛርን ተነሥ ያለው፤ ዕውሩንም በቃሉ የፈወሰው አምላክ በታላቅ ኀይልና ሥልጣን ተነሣ፤ ትንሣኤውንም በሰንበት አደረገ፤ በሦስተኛው ቀን ከሞት ተነሣ፤ ሙታንንም አስነሣ፤ እስረኞችንም ፈታ። ሊቁ ቅዱስ ያሬድ በድጓው ላይ።
+ + +
❤ የዕለቱ የማኅሌት ምስባክ፦ "እስመ መምህረ ሕግ ይሁብ በረከተ። ወየሐውር እምኃይል ውስተ ኃይል። ወያስተርኢ አምላከ አማልክት በጽዮን"። መዝ 83፥6-7 ወይም 77፥19-20። የሚነበበው ወንጌል ማቴ 18፥1-12 ወይም ዮሐ 21፥1-15።
+ + +
❤ የዕለቱ የቅዳሴ ምስባክ፦ "አንሰ ሰከብኩ ወኖምኩ። ወተንሣእኩ እስመ እግዚአብሔር አንሥአኒ"። ኢይፈርህ እምአእላፍ አሕዛብ። መዝ 3፥5-6። የሚነበቡት መልዕክታት ቆላ 3፥1-ፍ.ም፣ 1ኛ ጴጥ 3፥15-ፍ.ም እና የሐዋ ሥራ 11፥1-19። የሚነበበው ወንጌል ሉቃ 24፥33-45። የሚቀደሰው ቅዳሴ የቅዱስ ዲዮስቆሮስ ወይም የቅዱስ አትናቴዎስ ቅዳሴ ነው። መልካም የሐዋርያው ቅዱስ አትናቴዎስ የዕረፍት በዓልና የበዓለ ሃምሳ ጊዜ ለሁላችንም ይሁንልን
@eotcw
1 161
❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤
❤ ግንቦት ፯ (7) ቀን።
❤ እንኳን ለአገራች ኢትዮጵያ የመጀመርያውን ሊቀ ጳጳስ አባ ፍሬምናጦስ (አባ ሰላማ ከሳቴ ብርሃንን) ቀብቶ ለሾመው ለእስክድርያ ሃያኛው ሊቀ ጳጳስ ለታላቁ አባት ለሐዋርያዊ ለቅዱስ አትናቴዎስ ለዕረፍት መታሰቢያ በዓል በሰላም አደረሰን።
+ + +
❤ ሐዋርያዊ አባት ቅዱስ አትናቴዎስ፦ ይህም ቅዱስ ሐናፊ ከሚባል የእስላም ነገድና ከአረማውያን ተወላጅ ነው ይባላል። የተወለደው በ298ዓ.ም በእስክድርያ ነው። እርሱም ከመምህር ከሚማሩ ሕፃናት ጋራ እያለ እርስ በእርሳቸው በመጫወት ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን እየሠሩ ከእነርሱ ውስጥ ዲያቆናትን ኤጲስቆጶሳትንም ሲያደርጉ እሊያን የክርስቲያንን ልጆች አይቶ ጨዋታቸው አንድ ይሆን ዘንድ የክርስቲያንን ልጆች ለመናቸው። እርሱም "አንተ አረማዊ ነህና ከእኛ ጋራ አትደመርም" ብለው ከለከሉት እርሱም "ክርስቲያን እሆናለሁ" አላቸው እነርሱም ደስ ተሰኙበት። ያን ጊዜ ወስደው በሊቀ ጳጳሳት አምሳል አደረጉት ከበታቹም ወንበር አድረሰገው ይሰግዱለት ጀመር። በዚያ ጊዜም ሊቀ ጳጳሳት አባ እለእስክንድሮስ በዚያ አለፈ የክርስቲያን ልጆች ሲጫወቱ በአያቸው ጊዜ አብረውት ላሉ "ይህ ሕፃን ከፍ ከፍ ያለችና የከበረች ሹመትን ይሾም ዘንድ አለው" አላቸው።
❤ አባቱም በሞተ ጊዜ ወደ አባ እለእስክንድሮስ መጣ የክርስትና ጥምቀትንም አጠመቀው። ከዚህም በኋላ የአባቱን ገንዘብ ሁሉ ወስዶ ለድኆችና ለጦም አዳሪዎች ሰጥቶ የቤተ ክርስቲያንን ትምህርት ሕግ ሥርዓትንም ከአባ እለእስክንድሮስ ዘንድ እየተማረ ኖረ እርሱም ተወዳጅ ልጅ አደረገው። ከዚህም በኋላ ዲቁና ሾመው የመንፈስ ቅዱስንም ጸጋ የተመላ ሆነ።
❤ ስለ ቅዱስ አትናቴዎስ ወደ ቤተ ክርስቲያን አጠራር በተመለከተ ሩፊኖስ የተባለው የዚያ ክፍለ ዘመን የቤተ ክርስቲያን ታሪክ ጸሐፊ የሚከተለውን ጽፏል የእስክንድርያ ክርስቲያኖች የእስክንድርያ 17ኛ ፖትርያርክ የነበረውንና በዲዮቅልጥያኖስ ዘመን በሰማዕትነት ያረፈውን የተፍጻሜ ሰማዕት የቅዱስ ጴጥሮስን በዓል በየዓመቱ በታላቅ ሁኔታ ያከብሩ ነበር። በዚያን ጊዜ ፖትርያርክ የነበረው አባት እለእስክንድሮስ ከበዓሉ ፍጻሜ በኋላ በድንገት ወደ ባሕሩ ሲመለከት በዚያ የነበሩ ልጆች ጳጳስ፣ አጥማቂና ተጠማቂ እየሆኑ በባሕሩ ዳርቻ ሲጫወቱ ተመለከተ። መጀመሪያ የሕፃናት ጨዋታ ነው ብሎ አሰበ። ሁኔታቸውን እየቆየ ሲያየው ግን በቤተ ክርስቲያን የሚፈጸመውን መንገድ የተከተለና ከልጆች ጨዋታነት ያለፈ ነገር ሆኖ ታየው። በዚህ ጊዜ በመደነቅ አብረውት የነበሩት ካህናት ጋር በመካከር ልጆቹን ሁሉንም አስጠርቶ ምን እያደረጉ እንደሆነ ጠየቃቸው እርሱም ቅዱስ አትናቴዎስ ጳጳሳቸው ሆኖ ሌሎች ልጆች ደግሞ ተጠማቂዎች ሆነው ወደ እርሱ ሲቀርቡና እርሱ እያጠመቃቸው እንደነበረ ነገሩት።
❤ አባ እለእስክንድሮስ በጨዋታ መልክ ሲያጠምቅ የነበረው "የጨዋታው ካህን" ምን እያለና እንዴት እንዳጠመቃቸው ሲጠይቃቸው የምሥጢራቱ አፈጻጸም መንገድ በትክክል እንደተፈጸመ በመገንዘቡ አብረውት የነበሩትን ካህናት ስለ ጉዳዩ ካማከራቸው በኋላ "እነዚህን ንጹሕ ልባቸው በመለኰታዊ ጸጋ የተጠሩትንና የተጠመቁትን ልጆች እንደገና ማጥመቅ አስፈላጊ አይደለም" ብለው በመወሰን ጥምቀታቸውን በማጽደቅ አስፈላጊ የሆኑ ቀጣይ ምሥጢራትን ፈጸመላቸው።ከዚያም ሌሎችን ሕፃናት ባርኮ አሰናበታቸው። አጥማቂውን ሕፃን አትናቴዎስን ግን ከእርሱ ጋር ይሆን ዘንድ ወደ መንበረ ፖትርያርኩ ወሰደው።
❤ አባ እለእስክንድሮስም አትናቴዎስን በመንበረ ፖትርያርኩ የቤተ ክርሰቲያንን ትምህርትና ሥርዓት እያስተማረ አሳደገው፤ እርሱም ተወዳጅ ልጅ ሆነው። ከዚህም ጋር ሰዋስው፣ ፍልስፍና፣ ክሂሎተ ነቢብና ሌሎች በዘመኑ የነበሩ ትምህርቶችንም በሚገባ ተማረ። ቆይቶም ለመዓርገ ምንኵስና በቃ። በቅድስናው፣ በሞያውና በግብረ ገብነቱ እንከን የሌለው ወጣት አትናቴዎስ በ23 ዓመቱ ሊቀ ዲያቆን ሆነ። በዚያ ዘመኑ መዓርግ "ሊቀ ዲያቆን" ማለት የሊቀ ጳጳሱ አፈ ጉባኤ፣ እንደራሴ እንደ ማለት ነበር። ብዙውን ጊዜ የሊቀ ጳጳሳት ሲያርፉ በመንበራቸው የሚተካው ሊቀ ዲያቆናቸው ነበር።
❤ የከበረ አባት እለእስክንድሮስ በዐረፈ ጊዜ ይህን አባት አትናቴዎስ በእስክንድርያ አገር ላይ ሊቀ ጳጳሳት አድርገው ሾሙት። ከዚህ አስቀድሞ ግን ሦስት መቶ ዐሥራ ስምንት ኤጲስቆጶሳት ስብሰባ በተደረገ ጊዜ አባ እለእስክንድሮስ ከዚህ ዓለም ሳይለይ ይህም አትናቴዎስ ከእርሳቸው ጋራ ተሰብስቧል። የጉባኤውም ጸሐፊ አድርገውት በኒቅያ ከተማ ቀኖና ቤተ ክርስቲያንን ከእርሳቸው ጋራ ሠራ።
❤ ጻድቁ ቈስጠንጢኖስ በሞተ ጊዜ አርዮሳዊ ልጁ ሁለተኛው ቈስጠንጢኖስ ነገሠ አርዮሳውያንም በዙ ይህንንም አባት አርዮሳዊው ንጉሥ ከመንበረ ሢመቱ አሳደደውና በእርሱም ፈንታ ጊዮርጊስ የተባለ ከሀዲ ሰው ሾመ። ከዚህም በኋላ ብዙ ጊዜ ሲያሳድዱትና ሲመልሱት ኖረ። በስደትም በአንዲት ምዕራባዊት አገር በአለ ጊዜ በዚያ የጣዖት ቤት አለች። በዚያቺም የጣዖት ቤት ብዙ ሕዝቦች በውስጧ የሚሠሩ ብዙ የሰይጣን ሥራዎች አሏት። እርሱም የክብር ባለቤት የሆነ ጌታችን ኢየሱስ ክርሰቶስን ለመነው ያቺም የጣዖት ቤት አፍርሶ የአገር ሰዎች ሁሉ እግዚአብሔር ወደማወቅ መለሳቸው።
❤ ይህንንም አባት አምስት ጊዜ አሳደዱት የሹመቱም ዘመን አርባ ሰባት ሲሆን ዐሥራ አምስቱን ዓመት በስደትና በእሥራት ነው ያሳለፈው። ይህም አባት ብዙ መከራና ድካም መሰደደም ስደረሰበት ሐዋርያዊ ተብሎ ተጠራ።
❤ በሚሞትበትም ጊዜ እግዚአብሔር ዘንድ ባለሟልነትን ባገኘ ይህን ጣዖት ቤት ያፈርስ ዘንድ በፊቱ እኔ እየሰገድኩ እለምነዋለሁ። ይህም አባት ከአረፈ በኋላ ንጉሥ ልኮ ያንን የጣዖት ቤት አስፈረሰው። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱስ አትናቴዎስ ጸሎትና ምልጃ ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን። ምንጭ፦ የግንቦት7 ስንክሳርና ቅዱስ አትናቴዎስ ሐዋርያዊ ሕይወቱና ትምህርቱ።
+ + +
❤ "ሰላም ለአትናቴዎስ ከመ ላዕሌሁ ተነበዩ። ደቂቀ ክርስቲያን ኵሎሙ እንዘ ይትዋነዩ። ሊቀ ጳጳሳት ዘኮነ ወምእመነ ክርስቶስ ዲበ ንዋዩ። ወበእንተ ዘበጽሖ ስደት እመንበረ ክብሩ ወዕበዩ። ተሰምየ ሐዋርያዌ በኵሉ አያዩ"። ትርጉም፦ የክርስቲያን ልጆች ኹሉ ሲጫዋወቱ በርሱ ላይ ትንቢትን እንደተናሩ የጳጳሳት አለቃ ኾኖ ለተሾመና በክርስቶስ ገንዘብ (ምእመን) ላይ ታማኝ ኾኖ ለተገኘ ለቅዱስ አትናቴዎስ ሰላምታ ይገባል፤ ከፍፁም ክብሩ ዙፋን ላይ ስደት ስለደረሰበትም በግብሩ ኹሉ ሐዋርያዊን ተብሎ ተሰየመ። ሊቁ አርከ ሥሉስ (አርኬ) የግንቦት 7።
❤ በየቀኑ ይህን ቴሌግራም ላይ ማግት ከፈለጉ ከታች ያለውን ሊኩን ይጫኑት።
@Eotcw
1 161
❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤
❤ እንኳን ለትንሣኤ አራተኛ ሳምንት በሰላምና በጤና እግዚአብሔር አምላክ አደረሰን።
+ + +
❤ የዚህ ሳምንት መዝሙር፦ "ተንሥአ ወአንሥአ ኵሎ ሙታን ተንሥአ ወአንሥአ ኵሎ ሙታን ወፈትሖሙ ለሙቁሐን፤ አዝ፣ በዐቢይ ኀይል ወሥልጣን ወአግዐዘ ነፍሰ ጻድቃን፤ አዝ፣ ለአልዓዛር ተንሥእ ዘይቤሎ ወዕውርኒ ዘፈወሶ በቃሉ፤ አዝ፣ ትንሣኤሁ ገብረ በሰንበት በሣልስት ዐዕት ተንሥአ ወአንሥአ ኵሎ ሙታን ተንሥአ ወፈትሖሙ ለሙቁሐን"። ትርጉም፦ ተነሣ ሙታንንም አስነሣ እስረኞችን ፈታቸው፤ በታላቅ ኀይልና ሥልጣን ተነሣ፤ የጻድቃንን ነፍስ ነጻ አወጣ፤ አልዓዛርን ተነሥ ያለው፤ ዕውሩንም በቃሉ የፈወሰው አምላክ በታላቅ ኀይልና ሥልጣን ተነሣ፤ ትንሣኤውንም በሰንበት አደረገ፤ በሦስተኛው ቀን ከሞት ተነሣ፤ ሙታንንም አስነሣ፤ እስረኞችንም ፈታ። ሊቁ ቅዱስ ያሬድ በድጓው ላይ።
+ + +
❤ የዕለቱ የማኅሌት ምስባክ፦ "እስመ መምህረ ሕግ ይሁብ በረከተ። ወየሐውር እምኃይል ውስተ ኃይል። ወያስተርኢ አምላከ አማልክት በጽዮን"። መዝ 83፥6-7 ወይም 77፥19-20። የሚነበበው ወንጌል ማቴ 18፥1-12 ወይም ዮሐ 21፥1-15።
+ + +
❤ የዕለቱ የቅዳሴ ምስባክ፦ "አንሰ ሰከብኩ ወኖምኩ። ወተንሣእኩ እስመ እግዚአብሔር አንሥአኒ"። ኢይፈርህ እምአእላፍ አሕዛብ። መዝ 3፥5-6። የሚነበቡት መልዕክታት ቆላ 3፥1-ፍ.ም፣ 1ኛ ጴጥ 3፥15-ፍ.ም እና የሐዋ ሥራ 11፥1-19። የሚነበበው ወንጌል ሉቃ 24፥33-45። የሚቀደሰው ቅዳሴ የቅዱስ ዲዮስቆሮስ ወይም የቅዱስ አትናቴዎስ ቅዳሴ ነው። መልካም የሐዋርያው ቅዱስ አትናቴዎስ የዕረፍት በዓልና የበዓለ ሃምሳ ጊዜ ለሁላችንም ይሁንልን።
@Eotcw
1 161
ጉባኤ ቃና
ተፈስሐ ሳዶቅ ዕጸ ተሀድሶ ረኪቦ
ዘእንበለ እጽ ሰብዐ እስመ ዘይከውን አልቦ😁
ትርጉም :-
የመታደስ እጽን አግኝቶ ሳዶቅ ተደሰተ
ያለ ዕጽ ሰውን የሚሆን የለምና
ወርቅ:-
ሳዶቅ የኢያቄም ሌላኛ ስሙ ሲሆን ዕጽን አግኝቶ ተደሰተ የተባለው ዕጽ እመቤታችን ስትሆን እመቤታችንን በመውለዱ ተደሰተ ነው
አንቲ ውእቱ ዕጽ ዘርእየ ሙሴ እንዲል ውዳሴ ማርያም ዘሰሉስ
