ch
Feedback
ሰዋስው ☘☘☘☘

ሰዋስው ☘☘☘☘

前往频道在 Telegram

በሰዋስወ ብርሀን ቅዱስ ዻውሎስ ገዳም እና ለተለያዩ ቤተክርስቲያን ለክብረ በአላት ማውጫ ። በተጨማሪም-ዋዜማ ሥርዓተ ማኅሌት - መዝሙራት ስንክሳር - የየእለቱን ምስባክ ቅኔያት ጥያቄዎች እንዲሁም የወቅታዊ ነገር መወያያ በተጨማሪም @eotcww ብለው ይቀላቀሉን ለወዳጅ ዘመድዎ share#Share#Share# ያድርጉ።

显示更多
1 161
订阅者
无数据24 小时
无数据7 天
无数据30 天
帖子存档
6.44 KB

🔸🔸🔸🔸🔸🔸🔸 ዘመስከረም ፲ ምስባክ ❣❣❣❣❣❣❣ ዘነግህ ወዘሕጎ ያነብብ መዓልተ ወሌሊተ፣ ወይከውን ከመ ዕፅ አንተ ትክልት ኀበ ሙሐዘ ማይ፣ አንተ ትሁብ ፍሬሃ በበጊዜሃ። መዝ ፩፤፪ ማቴ ፲፪፥፴፫-፴፰ ምስባክ ዘቅዳሴ ሮሜ ፫፥፩-ፍ ያዕቆብ ፫፥፲፫-ፍ ግብ.ሐዋ ፩፥፲፪-፲፭ ወንጌል፦ሉቃስ ፩፥፴፮-፶፯ ፦ማቴ ፳፩፥፩-፲፬ ቅዳሴ፦ዘእግዝእትነ ማርያም(ጎሥዐ) ወትቀውም ንግስት በየማንከ፣ በአልባሰ ወርቅ ዑጽፍት ወኍብርት፣ ስምዒ ወለተየ ወርእዪ ወአጽምዒ እዝነኪ። ዓዲ/ምርጫ አዋልደ ንግስት ለክብርከ ወትቀውም ንግስት በይማንከ፣ በአልባሰ ወርቅ ዑጽፍት ወኍብርት።

ስት ድንግል ማርያም ጸሎት ይማረን በረከቷም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን። + + + ❤ ሰማዕቷ ቅድስት መጥሮንያ፦ ይቺም የከበረች መጥሮንያ ለአንዲት አይሁዳዊት ሴት አገልጋይዋ ናት። ይችም አይሁዳዊት እመቤቷ ከክርስትናዋ አፍልሳ ትክክል ወደ አልሆነ ሃይማኖቷ ልታስገባት ትሻ ነበር ስለዚህም ታጉሳቁላታለች በላይዋም የአገልግሎት ሥራን ታከብድባታለች ። ❤ ከዚህም በኋላ በአንዲት ቀን አይሁዳዊት እመቤቷን ተከትላ ወደ አይሁድ ምኵራብ ሔደች ተመልሳም ወደ ከበረች ቤተ ክርስቲያን ገብታ ጸለየች። ወደ ቤት በገቡም ጊዜ "ወዴት ሒደሽ ነበር ወደእኛ ምኩራብ ለምን አልገባሽም" ብላ ጠየቀቻት ቅድስት መጥሮንያም "ከእናንተ ምኵራብ እግዚአብሔር ርቋል እኮን እንዴት ወደርሱ እገባለሁ። በውስጧ ልገባባት የሚገባኝ ቦታዬ ግን ክብር ይግባውና ጌታችን ክርስቶስ በከበረ ደሙ የዋጃት ይህች ቤተ ክርስቲያን ናት" ብላ መለሰችላት። እመቤቷም ይህ ነገር በሰማች ጊዜ ተቆጣቻት እጅግም ደብደባ በጨለማ ቤት ውስጥ አሠረቻት ያለ መብልና መጠጥም አራት ቀን ኖረች። ❤ ከዚህም በኃላ ከእሥር ቤት አውጥታ በጅራፍ ታላቅ ግርፋትን ገርፋ ሁለተኛ ወደ እሥር ቤት መልሳ አሠረቻት በዚያም ዐረፈች። እመቤቷም በድኗን አንሥታ ከቤቷ ደርብ ላይ አውጥታ በውጭ ወደታች ጣለቻት። ወድቃ የሚያዩዋት ሰዎች በገዛ ፈቃድዋ እንደወደቀች አድርገው እንዲናገሩ ብላ ነው ስለ መገደሏ ዳኞች እንዳይመራመርዋት ፈርታለች። ❤ በዚያንም ጊዜ በዚያች አይሁዳዊት ሴት ላይ የእግዚአብሔር ቁጣ ወረደ ከደርቧ ላይ ስትወርድም በድንገት ወድቃ ሞተች ወደ ዘላለማዊም እሳት ሔደች ይህች የከበረች መጥሮንያ ግን የሰማዕታትን አክሊል ተቀብላ ወደ ዘላለም ሕይወት ሔደች። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን በቅድስት መጥሮንያ በረከቷም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን። ምንጭ፦ የመስከረም 10 ስንክሳር። + + + ❤ "ሰላምለሥዕልኪ ሀፈ ማኅየዌ። በፄዴንያ ወኢትዮጵያ በአውኀዘት በኢሕሳዌ። ለመፀብሐዊ ማቴዎስ ማርያ እንተረሰይኪዮ ወንጌላዌ። ይኩነነ ወትረ ፀሎትኪ እምዘመነኵሉ ምንሳዌ። ዓቃቤ ዘመዓልት ወዘሌሊት ሀላዌ"። መልክአ ሥዕል። + + + ❤ የዕለቱ የማኅሌት ምስባክ፦ "ወዘሕጎ ያነብብ መዓልተ ወሌሊተ። ወይከውን ከመ ዕፅ እንተ ትክልት ኀበ ሙኃዘ ማይ። እንተ ትሁብ ፍሬሃ በበጊዜሃ"። መዝ1፥2-3። የሚነበበው ወንጌል ማቴ 12፥33-38። + + + ❤ የዕለቱ የቅዳሴ ምስባክ፦ "ወትቀውም ንግሥት በየማንከ። በአልባሰ ወርቅ ዑፅፍት ወኁብርት። ስምዒ ወለትየ ወርእዪ ወአፅምዒ እዝነኪ"። መዝ 44፥9-10። የሚነበቡት መልዕክታት ሮሜ 3፥1-ፍ.ም፣ ያዕ 3፥13-ፍ.ም እና የሐዋ ሥራ 1፥12-15። የሚነበበው ወንጌል ሉቃ 1፥46-57 ወይም ማቴ 25፥1-14። የሚቀደሰው ቅዳሴ የእመቤታች ማርያም ቅዳሴ ነው። መልካም የጴዴንያ ማርያም በዓልና የመስቀሉ በዓል ለሁላችንም ይሁንልን። ❤ በየቀኑ ይህን ቴሌግራም ላይ ማግት ከፈለጉ ከታች ያለውን ሊኩን ይጫኑት። https://t.me/Eotcw

❤ "በስመ አብ ወወልደ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤ ❤ መስከረም ፲ (10) ቀን። ❤ እንኳን ለእመቤታች ለቅድስት ድንግል ማርያም በፄዴንያ አገር በማርታ ቤት ሥጋ የለበሠች ከምትመስል ከእመቤታች ሥዕል ከሠሌዳዋ ቅባት እየተንጠፈጠፈ ተአምር ለሠራችበት ቀን መታሰብያ በዓል፣ የጌታችን የአምላካችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ቅዱስ መስቀል ወደ አገራችን ኢትዮጵያ ውስጥ ለገባበት (ተቀጽል ጽጌ) አፄ መስቀል) ቀን ለመታሰቢያ በዓልና ለከበረች ሰማዕትነት ለተቀበለችበት ለቅድስት መጥሮንያ ሰማዕትነት ለተቀበለችበት በዓል ዕረፍት፣ በሰላም አደረሰን። በተጨማሪም በዚች ቀን ከሚታሰቡ፦ አምላክን የወለደች የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም የተወለደችበት ነው የሚሉ አሉ። (ይህም የአስቄጥስ ገዳም የከበረ አባ መቃርስ በጻፈው መጽሐፈ ግጻዌ ተጽፎል እንዲሁም ደግሞ በላዕላይ ግብጽ በሚገኝ መጽሐፈ ግጻዌ የከበረች ድንግል እመቤታችን የከበረች ሐና በታኅሣሥ ወር በዐሥራ ሰባት እንደፀነሰቻትና መስከም በዐሥር ቀን እንደወለደቻት ተጽፍአል)፣ ከከሀዲው ሆሎፎርኒስ እጅ በጥበቧ እስራኤልን ካዳነቻቸው ከጥበበኛ ከከበረች ከዮዲት በዓለ ዕረፍትና ከቅድስት አትናስያና ሦስት ልጆቿ ከመታሰቢያቸው በረከትና ረድኤትን ያሳትፈን። + + + ❤ "መስቀል ጒድበ ሙስና ዲበ ሰይጣን ወሰይፈ ሙቃየ አርእስቲሆሙ ለአጋንንት፤ መስቀል ረምኃ እሳት ዘይረግዞሙ ለመናፍስት ርኵሳን፤ ወሐፀ መብረቅ ዘይደጒፆሙ ለሠራዊተ መስቴማ። መስቀል ፀወን ዘኢይክል በጺሐ ኀቤሁ ዘኢነሥአ ማኅተመ ሥላሴ። መስቀል ወልታ ጽድቅ ዘእምየማን ወእም ጸጋም። መስቀል ንዋየ ሐቅል ለፀብዕ በከመ ይቤ ጳውሎስ ሐዋርያ እስመ ቀትልክሙ ኢኮነ ምስለ ዘሥጋ ወደም። መስቀል ጽርዐ ሃይማኖት ዘኢይክል ሰጢጦቶ ሥጽረተ ሐፀ ወኢደርብዮቶ ኵያንው ወአርማኅ። መስቀል ዘገብረ በአምሳሊሁ ለእደ ሙሴ በገዳም ራፊድ በእንተ ፀብዐ አማሌቅ። መስቀል ዘአጥዐሞ ለማይ መሪር በገዳም ሱር ሶበ ተወድየ ውስቴቱ በእደ ሙሴ። መስቀል ማኅተመ ቅድስና ወንጽሕ። መስቀል አክሊለ መዊዕ ዘመስተጋድላን ወሠርጎ ትርሲት ለእለ ተዓሥሩ ውስተ መርዐ በግዑ። መስቀል ነቅዕ ዘኢይነጽፍ ወአዘቅተ ክብር ዘምሉዕ ረባሐ"።ትርጉም፦ መስቀል ሰይጣንን የሚያጠፋ ምሳር ነው፤ የአጋንንትንም ራሶች የሚቆርጥ ሰይፍ ነው፤ መስቀል ርኩሳን መናፍስትን የሚወጋቸው የእሳት ዘገር ነው፤ የአመስቴማውያንንም (የጠላት፣ የከሳሽ፣ የጠበኛ) ሠራዊት የሚመታ የመብረቅ ጦር ነው። መስቀል ማኅተመ ሥላሴ (የሥላሴ ልጅነት) የሌለው ሰው ወደእርሱ ሊቀርበው የማይቻለው አምባ መጠጊያ ነው። መስቀል ከግራ ከቀኝም ለሚመጣ (ጠላት) የጽድቅ ጋሻ ነው። ቅዱስ ጳውሎስ "ውጊያችሁ ከሥጋና ከደም ጋር አይደለም" እንዳለው መስቀል የጦር መሣርያ ነው። መስቀል የጦር ውጋት ሊቀድደው፤ የቀስትና የዘንግም ጫፍ ሊበሳው የማይችል የሃይማኖት ጥሩር ነው። መስቀል አማሌቃውያንን ለመውጋት በራፊድ በረሐ በዘረጋው በሙሴ እጅ አምሳል የተሠራ ነው። መስቀል በሙሴ እጅ ወደ ውስጥ በተጨመረ ጊዜ መራራውን ውኃ በሱር በረሐ ያጣፈጠ ነው። መስቀል የቅድስናና የንጽሕና ማኅተም ነው። መስቀል ለሚጋደሉ የድል አክሊል፤ ወደ በጉ ሰርግ ለተጠሩትም የሰርግ ልብሳቸው ነው። መስቀል የማይነጥፍ ምንጭ፤ በቁዔትም (ጥቅምም) የሞላበት የክብር ጉድጓድ ነው። ሊቁ አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ በውዳሴ መስቀል ላይ1፥3። + + + ❤ በዚህች ቀን ጼዴንያ በምትባል አገር ሥጋ የለበሰች ከምትመስል ሥዕል ከሠሌዳዋ ቅባት እየተንጠፈጠፈ አምላክን የወለደች የእመቤታችን የድንግል ማርያም ተአምር ተገለጠ። ይቺንም ሥዕል የሣላት ወንጌላዊ ሉቃስ ነው ይባላል። ወደ ጼዴንያ አገርም የመጣችበት ምክንያት አንዲት ስሟ ማርታ የሚባል መበለት ሴት ነበረችና ቤቷንም ለእንግዳ ማደሪያ ያደረገች ናት። አምላክን የወለደች እምቤታችን ድንግል ማርያምንም እጅግ ትወዳት ነበር። በሚቻላትም ሁሉ ታገለግላታለች። ❤ በአንዲት ቀንም ስሙ ቴዎድሮስ የሚባል መነኵሴ ከእርሷ ዘንድ እንግድነት አደረ በመልካም አቀባበልም ተቀበለችው በማግሥቱም ስተሸኘው "አባት ሆይ የምትሔደው ወዴት ነው" አለችው። እርሱም "በከበሩ ቦታዎች ውስጥ ልሰግድ ወደ ኢየሩሳሌም እሔዳለሁ" አላት እርሷም "ከእኔ ገንዘብ ወስደህ የእመቤታችን ማርያምን ሥዕል ግዛልኝና በመመለሻህ ጊዜ አምጣልኝ" አለችው። እርሱም በራሴ ገንዘብ ገዝቼ አመጣልሻለሁ አላት። ❤ ከዚህም በኋላ ኢየሩሳሌም በደረሰ ጊዜ ከቅዱሳት መካናት ተባረከና ሥዕሏን ሳይገዛ ወደ ጎዳናው ተመለሰ። ያን ጊዜም "ሥዕል መግዛትን ለምን ረሳህ" የሚል የሚያስደነግጥ ቃልን ሰማ ወደ ገቢያም ተመልሶ ላሕይዋና መልኳ ያማረና የተወደደ የሆነ የእመቤታችን ማርያምን ሥዕል አግኝቶ ገዛት በሐርና በንጹሕ ልብስም ጠቀለላት። በጎዳናውም እየተጓዘ ሳለ ከሚያስፈራ ዱር ውስጥ ወንበዴዎች ተነሡበት ሊሸሽም ወደደ ከዚያቺም ሥዕል "መንገድህን ሒድ የሚል ቃል ወጣ" የተከተለውም ሳይኖር መንገዱን ተጓዘ። ሁለተኛም ነጥቆ ሊበላው አንበሳ ተነሣበት ያን ጊዜም ከዚያች ሥዕል የሚያሥፈራ ድምፅ ወጥቶ አንበሳውን አባረረው። ❤ አባ ቴዎድሮስም ይህን ሁሉ ድንቅ ተአምር ባየ ጊዜ ያቺን ሥዕል ወደ አገሩ ሊወስዳት ወደደ ግዛልኝ ላለችው መበለት ይሰጣት ዘንድ አልፈለገም። ❤ ከዚህም በኋላ በመርከብ ተሳፍሮ በሌላ አቅጣጫ ሲጓዝ ታላቅ ነፋስ ተነሣበት ወደ ማርታ አገር ወደ ጼዴንያም ወሰደው ከመርከቡም ወርዶ ከብዙ እንግዶች ጋር ወደዚያች መበለት ቤት ሔደ ማንነቱንም አልገለጠላትም እርሷም አላወቀችውም። በማግሥቱም ተሠውሮ ወጥቶ ወደ አገሩ ሊሔድ በፈለገ ጊዜ የቅጽሩን ደጃፍ አጥቶ ሲያጥመሰምስ ዋለ በመሸ ጊዜም ወደ ማደሪያው ተመለሰ። ያቺም መበለት በአየችው ጊዜ ታደንቃለች እንዲህም ሁኖ እስከ ሦስት ቀን ኖረ በመሸ ጊዜ በሩን ያየዋል ነግቶ መሔድን ሲሻ የበሩ መንገድ ይሠወረዋል። ያቺም መበለት ያዝ አድርጋ "አባቴ ሆይ አእምሮህ ተነክቷልን ስትቅበዘበዝ አይሀለሁና ምን ሆነህ ነው" አለችው። ❤ ከዚህም በኋላ ከዚያች ሥዕል የሆነውን ሁሉ ነገራት ራሱንም ገለጠላት። ያቺንም ሥዕል ሰጣት ተቀብላም የተጠቀለለችበትን ልብስ ፈታች ወዝ ከሥዕሊቱ ሲንጠፈጠፍ አገኘች። ከደስታዋም ብዛት የተነሣ የዚያን መነኩሴ እጆቹንና እግሮቹን ሳመች። ❤ ከዚህም በኋላ ያቺን ሥዕል ወደ ጸሎት ቤቷ ወስዳ በታላቅ ክብር የምትቀመጥበትን አዘጋጅታ አኖረቻት ማንም እንዳይዳስሳትም የነሐስ መስኮትን ሠራችላት በቀንና በሌሊትም የሚበሩ መቅረዞችን በፊቷ ሰቀለች ከመቅረዞችም ውጭ የሐር መጋረጃን ጋረደች። ከሥዕሊቱ በታችም ከሥዕሊቱ እየተንጠፈጠፈ የሚወርደው የወዝ ቅባት የሚጠራቀምበት ከዕብነ በረድ የተሠራ ወጭት አኖረች ያም መነኰስ እስከሚሞትበት ቀን ድረስ የእመቤታችንን ድንግል ማርያምን ሥዕል እያገለገለ ኖረ። ❤ የሀገሩም ሊቀ ጳጳሳት የዚያችን ሥዕል ዜና በሰማ ጊዜ ከኤጲስቆጶሳትና ከካህናት ከሕዝቡም ሁሉ ጋር መጣ በሠሌዳውም ውስጥ በአዩዋት ጊዜ ሥጋ የለበሰች ሁና አገኙዋት ከዚህ ከአምላካዊ ግብር የተነሣ አደነቁ ከዚህም ቅባት ቀድተው ለበረከት በተካፈሉ ጊዜ ወዲያውኑ በወጭቱ ውስጥ ይመላል። ወደ ሌላ ቦታም ሊወስዷት በፈለጉ ጊዜ ንውጽውጽታ ሆኖ ብዙዎች በድንጋጤ ወደቁ ሥዕሊቱም እስከ ዛሬ በዚያች አገር ትኖራለች። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በእናቱ በእመቤታችን ቅድ

✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨ በእለቱ በቅዳሴ ሰዓት የሚነበብ ወንጌል ✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨ ማቴ. 7፥24-ፍ፡ም፡ "ኩሉኬ ዘይሰምዕ ዘንተ ነገርየ" - "የዚያን፡ጊዜም፦ከቶ፡አላወቅኋችሁም፤እናንተ፡ዐመፀኛዎች፥ከእኔ፡ራቁ፡ብዬ፡እመሰክርባቸዋለሁ። ስለዚህ፥ይህን፡ቃሌን፡ሰምቶ፡የሚያደርገው፡ሁሉ፡ቤቱን፡በአለት፡ላይ፡የሠራ፡ልባም፡ሰውን፡ይመስላል። ዝናብም፡ወረደ፥ጎርፍም፡መጣ፥ነፋስም፡ነፈሰ፥ያንም፡ቤት፡ገፋው፤በአለት፡ላይም፡ስለ፡ተመሠረተ፡ አልወደቀም። ይህንም፡ቃሌን፡ሰምቶ፡የማያደርገው፡ሰው፡ሁሉ፡ቤቱን፡በአሸዋ፡ላይ፡የሠራ፡ሰነፍ፡ሰውን፡ይመስላል። ዝናብም፡ወረደ፥ጎርፍም፡መጣ፥ነፋስም፡ነፈሰ፥ያንም፡ቤት፡መታው፥ ወደቀም፤አወዳደቁም፡ታላቅ፡ሆነ። ኢየሱስም፡ይህን፡ነገር፡በጨረሰ፡ጊዜ፡ሕዝቡ፡በትምህርቱ፡ተገረሙ፤ እንደ ጻፊዎቻቸው፡ሳይሆን፡እንደ፡ባለሥልጣን፡ያስተምራቸው፡ነበርና። ✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨

4.70 KB

9/1/2015 ዓ.ም (፱/፩/፳፻፲፭ ዓ.ም) 🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯 በእለቱ በቅዳሴ ሰዓት የሚባል ምስባክ 🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯 ድምፀ ወተሐምገ ማያቲሆሙ። ወአድለቅለቁ አድባር እምኃይሉ። ፈለገ ዘይኅዋዝ ያስተፌሥሕ ሀገረ እግዚአብሔር፡፡ መዝ. 45፥3 🕯 ትርጉም ውሃዎቻቸው ጮኹ ተናወጡም። ተራራዎችም ከኃይሉ የተነሣ ተናወጡ። የወንዝ ፈሳሾች የእግዚአብሔርን ከተማ ደስ ያሠኛሉ። 🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯

✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨ በእለቱ በነግህ የሚነበብ ወንጌል ✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨ ማቴ.12፥1-9፡ "ወበውእቱ መዋዕል ኀለፈ እእግዚእ" - "በዚያን፡ጊዜ፡ኢየሱስ፡በሰንበት፡ቀን፡በዕርሻ፡መካከል፡ዐለፈ፤ደቀ፡መዛሙርቱም፡ተራቡና፡እሸት፡ይቀጥፉ፡ይበሉም፡ጀመር። ፈሪሳውያንም፡አይተው፦እንሆ፥ደቀ፡መዛሙርትህ፡በሰንበት፡ማድረግ፡ያልተፈቀደውን፡ያደርጋሉ፡አሉት። እርሱ፡ግን፡እንዲህ፡አላቸው፦ዳዊትና፡ከርሱ፡ጋራ፡የነበሩት፡በተራቡ፡ጊዜ፥እርሱ፡ያደረገውን፥ወደእግዚአብሔር፡ቤት፡እንደ፡ገባ፡ካህናትም፡ብቻ፡እንጂ፡እርሱና፡ከርሱ፡ጋራ፡የነበሩት፡ሊበሉት፡ያልተፈቀደውን፡የመሥዋዕቱን፡ኅብስት፡እንደ፡በላ፡አላነበባችሁምን? ካህናትም፡በሰንበት፡በመቅደስ፡ሰንበትን፡እንዲያረክሱ፡ኀጢአትም፡እንዳይሆንባቸው፡በሕጉ፡አላነበባችሁምን? ነገር፡ግን፥እላችኋለሁ፥ከመቅደስ፡የሚበልጥ፡ከዚህ፡አለ። ምሕረትን፡እወዳለሁ፡መሥዋዕትንም፡አይደለም፡ያለው፡ምን፡እንደ፡ሆነ፡ብታውቁስ፡ኀጢአት፡ የሌለባቸውን፡ባልኰነናችሁም፡ነበር። የሰው፡ልጅ፡የሰንበት፡ጌታ፡ነውና። ከዚያም፡ዐልፎ፡ወደ፡ምኵራባቸው፡ገባ።" ✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨

1.00 KB

9/1/2015 ዓ.ም (፱/፩/፳፻፲፭ ዓ.ም) 🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯 በእለቱ በነግህ የሚባል ምስባክ 🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯 እግዚአብሔርኒ ይሁብ ምሕረቶ። ወምድርኒ ትሁብ ፍሬሃ። ጽድቅ የሐውር ቅድሜሁ፡፡ መዝ. 84፥12 🕯 ትርጉም እግዚአብሔርም በጎ ነገርን ይሰጣል። ምድራችንም ፍሬዋን ትሰጣለች። ጽድቅ በፊቱ ይሄዳል። 🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯

❤ "በስመ አብ ወወልደ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤ ❤ መስከረም ፱ (9) ቀን። ❤ እንኳን በሮሜ አገር ፍሩምያ በምትባል ከተማ በመላእክት አለቃ በቅዱስ ሚካኤል በስሙ በተሠራ ቤተ ክርስቲያን ላደረገው ተአምር መታሰቢያ በዓል፣ ከኃላፊው ከዚኽ ዓለም መንግሥቱ መንኖ ተጋድሎውን በዛፍ ላይ ኹኖ ለፈጸመ፤ የደረቀውን ግንድ ላለመለ፣ ለጽጌ፣ ለፍሬ ለአደረሰ ላሳየ እግዚአብሔርን ደስ ላሰኘ ለንጉሥ ለቅዱስ (ለአባ) ያሳይ ለዕረፍት በዓልና ለመጺል ለምትባል አገር ኤጲስቆጶስ ለሆነ ከቅዱስ አባት ለአባ ቢሶራ ሰማዕትነት ለተቀበለበት ለዕረፍቱ በዓል በሰላም አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰቡ፦ ከቅዱስ ፋሲለደስ ጋር ዐሥራ አራት ሺህ ሰባት መቶ ሠላሳ ወንዶችና ሰባት ሴቶችም በሰማዕትነት ከዐረፉ እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን። + + + ❤ በዚህች ቀን በሮም አገር ፍሩምያ በምትባል ከተማ ለሆነው ተአምር መታሰቢያ ሆነ። ይህም እንዲህ ነው የሰማይ ሠራዊት አለቃ በሆነ በከበረ መልአክ በቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን ውስጥ በሚታዩ ድንቆችና ተአምራቶች ምክንያት ዮናናውያን ሰዎች ሰይጣናዊ ቅናትን እንደ ቀኑ ከመቅናታቸውም ብዛት የተነሣ በዚያ አካባቢ የሚወርደውን የወንዝ ውኃ በዚያች ቤተ ክርስቲያን ላይ ሊመልሱትና ከሚጠብቃት መጋቢዋ ጋር በውኃ ስጥመት ሊአጠፉአት ፈልገው መለሱት። ❤ የሰማያውያን ሠራዊት አለቃ ቅዱስ ሚካኤልም ለቤተ ክርስቲያኑ መጋቢ ለናርጢኖስ ተገለጠለት ወደርሱም ቀርቦ "ጽና አትፍራ" አለው ይህንን ብሎ በእጁ ውስጥ ባለ በትር አለቱን መታው አለቱም ተሰንጥቆ እንደ በር ሆነ የዚያ ወንዝ ውኃም በውስጡ አልፎ ሔደ። ❤ ይህንንም ያዩ ምስጉን እግዚአብሔርን አመሰገኑት የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤልንም አከበሩት። ከዚያች ቀን እስከ ዛሬ የወንዙን ውኃ በዚያች በተሠነጠቀች አለት ውስጥ አልፎ ሲሔድ ያዩታል ወደ መላእክት አለቃ ሚካኤል ቤተክርስቲያን ከቶ አይቀርብም። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱስ ሚካኤል አማለጅነት ይማረን ለዘላለሙ አሜን። + + + ❤ "ሰላም ለአባ ያሳይ ብእሴ ሰማይ፤ ለአምላኩ ቀናኢ፤ ሐራይ መዋኢ"። ትርጉም፦ ድል ነሺ ጭፍራ ለአምላኩ ቀናተኛ የሰማይ ሰው ለኾነ ለአባ ያሳይ ሰላምታ ይገባል። ሊቁ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ በተአምኆ ቅዱሳን ላይ። + + + ❤ ንጉሥ ቅዱስ (አባ) ያሳይ፦ ይህም ቅዱስ ከኃላፊው ከዚኽ ዓለም መንግሥቱ መንኖ ተጋድሎውን በዛፍ ላይ ኹኖ የፈጸመ ነው፤ የደረቀውን ግንድ ከልምላሜ፣ ከጽጌ፣ ከፍሬ አድርሶ ያሳየ፤ እግዚአብሔርን ደስ ያሰኘ በቅዱስ ነው። ከንጉሥ ከቅዱስ (አባ) ያሳይ ያሳይ በጸሎቱ የምትገኝ በረከቱ ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን። + + + ❤ የመጺል አገር ኤጲስቆጶስ አባ ቢሶራ፦ ይህም ቅዱስ በግብጽ አገር እግዚአብሔርን በምትወድ መጺል በምትባል ከተማ ኤጲስቆጶስ ሆነ። ዲዮቅልጥያኖስም ነግሦ ክርስቲያኖችን በሚያሠቃያቸው ጊዜ ክብር ይግባውና በክርስቶስ ስም ደሙን ያፈስ ዘንድ ይህ አባት ወደደ። ❤ ሕዝቡንም ሀሉ ሰብስቦ በቤተ መቅደሱ ፊት በዐውደ ምሕረቱ አቆማቸው ሊጠብቁት የሚገባውን ለጽድቅ የሚያበቃቸውን ትእዛዝ ሁሉ አዘዛቸው። ከዚህም በኋላ ክብር ይግባውና በክርስቶስ ስም ደሙን ማፍሰስ እንደሚሻ ነገራቸው ይህንንም በሰሙ ጊዜ ታላቆችም ታናሾችም በላዩ አለቀሱ። "የሙት ልጆች እንሆን ዘንድ የምትተወን ምን ያደርግልሃል እኛስ እንድትሔድ አንለቅህም" አሉት ሊይዙትም ቃጡ ግን አልተቻላቸውም ተውትም እርሱም ወደ ክብር ባለቤት ክርስቶስ አደራ አስጠበቃቸውና ሰላምታ ሰጥቷቸው ከእነርሱ ዘንድ ወጥቶ ተጓዘ። እነርሱም መሪር ልቅሶን እያለቀሱ ሸኙት። ❤ ስማቸው ቢስኮስ ፊናቢክስ ቴዎድሮስ የሚባሉ ኤጲስቆጶሳት አብረውት ሔድ መኰንኑ ወደ አለበት አገርም ደርሰው የክብር ባለቤት በሆነ በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ታመኑ። እርሱም መኰንኑ አሠቃያቸው ኤጲስቆጶሳትም እንደሆኑ አውቆ ሥቃያቸውን አበዛ እሊህ አባቶች ግን በታላቅ ትዕግሥት የጸኑ ናቸው። ክብር ይግባውና ጌታችን ክርስቶስ ያጸናቸዋልና። ❤ ከዚህም በኋላ መኰንኑ ራሶቻቸውን በሰይፍ ይቆርጧቸው ዘንድ አዘዘ የሕይወት አክሊልንም በመንግሥተ ሰማያት ተቀበሉ። የቅዱስ ቢሶራ ሥጋው ግን ንሲል በሚባል አገር እስከ ዛሬ ይኖራል። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳኑ ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን። + + + ❤ "ሰላም ለያሳይ እምነ መንግሥቱ ዘተድህለ። መንግሥተ ሰማያት ያድምዕ ወዘኢየኀልፍ ብዕለ። ውስተ ጒንደ ዕፅ ይቡስ አመ ተለዓለ። በትሩፋቲሁ ከመ ያርኢ ኃይለ። አሥረፀ ሶቤሃ ወአወጽአ ቈጽለ"። ትርጉም፦ የማያልፍ ሀብትንና መንግሥተ ሰማያትን ያገኘ ዘንድ ከምድራዊው መንግሥቱ የኰበለለ ለኾነ ለያሳይ ሰላምታ ይገባል፤ በትሩፋቱ ኃይልን ያሳይ ዘንድ በደረቀ ዕንጨት ግንድ ላይ በወጣ ጊዜ በዚያን ጊዜ ቅጠሎችን አውጥቶ ለመለመ። + + + ❤ "ሰላም እብል ለዓቢይ መንክሩ። ዘተክሥተ ዮም በውስተ ዳቤሩ። ፈለገ ማይ ይሚጡ እንዘ ይመክሩ። ተሠጥቀ ኰኵሕ እንተ ዐላውያን አንበሩ። ሶበ ሚካኤል ዘበጦ በበትሩ"። ሊቁ አርከ ሥሉስ (አርኬ) የመስከረም 9። + + + ❤ የዕለቱ ምስባክ፦ "ምድርኒ ወሀበት (ትሁብ) ፍሬሃ። ወይባርከነ እግዚአብሔር አምላክነ። ወይባርከነ እግዚአብሔር"። መዝ 66፥6-7። የሚነበቡት መልዕክታት 2ኛ ቆሮ 9፥1-ፍ.ም፣ ያዕ 5፥1-10 እና 19፥21-ፍ.ም። የሚነበበው ወንጌል ማር 4፥24-39። የሚቀደሰው ቅዳሴ የቅዱስ ዮሐንስ ወልደ ነጎድጓድ ነው። መልካም የቅዱስ ሚካኤል የተአምራት በዓል፣ የንጉሥ ቅዱስ ያሳይ የዕረፍት በዓልና ዕለተ ሰንበት ለሁላችንም ይሁንልን። ❤ በየቀኑ ይህን ቴሌግራም ላይ ማግት ከፈለጉ ከታች ያለውን ሊኩን ይጫኑ። https://t.me/Eotcw

ትሕትና ራስን ዝቅ ማድረግ፣ ትዕቢትንና ኩራትን ማስወገድ ማለት ነው። ትሕትና የነፍስ ጸጥታ/እርካታ/፣ ከውዳሴ ከንቱ መዳኛ ናት፡፡ የክርስቲያኖች መታወቂያ ምልከት ትሕትና ናት። የትሕትና መምህራችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። በትሕትና መመላለስ ግዴታችን ነው፡፡ ከዚህ የወጣ የትዕቢት ሕይወት ግን መጨረሻው ውድቀት ነው። ''ትዕቢትሰ ጸሩ ለክርስቶስ'' ይባላል። ስለዚህ ትሕትና የመንግስተ ሰማይ መወጣጫ መሰላል ናት፡፡ ማስረጃ ዘፍ.18 : 28 ፊልጵ 2፡7 1ኛሳሙ.18 ፥ 18 መዝ.38፡3 መዝ.118 ፥141 ሉቃ1፥3 +22 ምሳሌ.14፥30 ማቴ.4፥29 - ዘኑ.12፥3 ምሳሌ.39፥23 ዮሐ. 13፥5 1ኛቆሮ 15፥8 ዮሐ.1፥ 27 1ኛ4 ፥5 1ኛጢሞ.1፥15 2ኛቆሮ.4፥7 ✞ወስብሐት ለእግዚአብሔር✞ ለወዳጅዎ #ሼር ያድርጉ ዲ/ን የአብስራ ጌታሁን

ጥያቄ ፫ በመፅሐፍ ቅዱስ አዲስ ኪዳን ዉስጥ አብዛኛውን መልዕክት የፃፈው ማን ነው?
Anonymous voting

ጥያቄ ፪ ጌታችን ምንን ነበር " ግመል በመርፌ ቀዳዳ ቢያልፍ ከሱ ይቀላል" ያለው ?
Anonymous voting