Construction Solution- @Consite Media[የግንባታ ሥራ ተቋራጮች]🏗
前往频道在 Telegram
Addis Ababa, Ethiopia Con-Site is a Comprehensive Construction Filed Works and Materials Reference Catalogue for Architects, Engineers, Consultants and Customer service. t.me/ConsitesolutionBot ☜|]Comments Construction Solution Official Service
显示更多3 594
订阅者
+624 小时
+77 天
+4830 天
帖子存档
ስለ ኮንክሪት እና የኮንክሪት ግሬዶች
ኮንክሪት (concrete) ስሙን ያገኘው ከጥንት ሮማኖች ሲሆን ቃሉም የመጣው ኮንክሪተስ (Concretus) ከሚለው የሮማኖች ቃል ነው የቃል በቃል ትርጉሙ ተያይዞ ማደግ / አንድ ላይ ማደግ የሚለውን ይወክላል።
ኮንክሪት በአለም ላይ በብዛት የምንጠቀመው የግንባታ ቁስ ነው።
ኮንክሪት የሲሚንቶ የአሸዋ እና የጠጠሮች ውህድ ነው ።
የኮንክሪት የእመቃ ጥንካሬ (compressive strength)
ሚለካው በግሬዱ ነው (Grade)
የተለያዩ የኮንክሪት ግሬዶች
አሉ C-5 ፣ C-15 C-25 C-30 ወዘተ የኮንክሪት ግሬድ ማለት
ኮንክሪቱ ከሃያ ስምንት ቀን በኋላ የሚኖረው የእመቃ ጥንካሬ
(compressive strength ) ማለት ነው ለምሳላ C-25 የሆነ
ኮንክሪት ግሬድ ከ28 ቀን በኋላ የሚኖረው የእመቃ ጥንካሬ
25N/mm^2 ይሆናል ማለት ነው የC-30 ግሬድ ደግሞ
ጥንካሬው 30N/mm^2 ነው
ለውሃ ስራዎች ብዙን ግዜ ተመራጩ የኮንክሪት ግሬድ ከ C-30 በላይ ነው
አንዳንድ ግዜ የኮንክሪት ግሬዶች በተለያዩ መፅሃፎች በተለያየ
መልክ ይጠቀሳሉ ለምሳሌ አንዳንድ መፅሃፎች C-30 C-15
የሚለውን አጠቃቀስ ሲጠቀሙ አንዳንዶቹ ደግሞ M-30 M-15
የሚለውን ይጠቀማሉ (ከታች በምስሉ እንደተጠቀሰው) ....በ
«C»የሚጠቀሱ የኮንክሪት ግሬዶች በC መጠቀሳቸው የእመቃ ጥንካሬያቸው የተለካው በሲሊንደሪካል ፍተሻ (CYLINDRICAL test ) ስለሆነ ነው በM የሚጠቀሱት ደግሞ ፍተሻው (test) የተደረገው በኪውቢክ ፍተሻ (cubic test) ስለሆነ ነው። በሁለቱ የፍተሻ አይነቶች የሚደረጉ የኮንክሪት ግሬዶች የእመቃ ጥንካሬአቸው ይለያያል። ሲሊንደሪካል ፍተሻ በአንፃራዊነት የኮንክሪትን ትክክለኛ እምቅ ጥንካሬ ይገልፃል ስለዚህ ከኪውቢክ ፍተሻው የተሻለ ነው ማለት ነው።
ILLNESS IN REINFORCEMENT CONCRETE
የባለፌሮ አርማታ በሽታዎች
1. Corrosion in reinforcement bar/ የፌሮ መዛግ - when the rebar is exposed to outer environment other than concrete it will rust /corrode …. As you guys know know reinforcement counters tension as a result of corrosion the tension member fails it’s causes tension failure
የፌሮ መዛግ - ፎሮ ከ አርማታ እቅፍ በወጣ ጊዜ ዝገት ያስከትላል ለምሳሌ አፈር ላይ ረዥም ጊዜ ከተኛ ይዝጋል ወይም ደግሞ ለረዥም ግዜ coloride ያለበት ወይም ጨዋማ ውሀ ከነካው ይሄም tension failure /ውጥረትን መቋቋም የማይችል ባለፌሮ አርማታ መዋቅር(RC structure) ይሆናል።
2. Carbonation of concrete - is the chemical reaction between carbon dioxide in the air and calcium hydroxide and hydrated calcium silicate in the concrete to give mainly carbonates. This slowly changes the PH of concrete.
Carbonation - አርማታችን በከባቢያችን(አየር) ካሉ “ካርቦን ዳይ ኦክሳይድ” ፣ “ካልሲየም ሀይድሮ ኦክሳይድ” እና “ሀይድሬትድ ካልሲየም ሲልኬት” ጋር በመዋሀድ ወደ ካርቦኔት ይቀይረዋል ይኼም PH value alter እንዲያረግ ያረጋል
ዲዛይን ቢድ ቢዩልድ(Design bid build)(DBB) እና ዲዛይን ቢዩልድ(Design build)(DB)
1, ዲዛይን ቢድ ቢዩልድ(Design bid build)(DBB)
#በኮንስትራክሽን ጉዳይ በአብዛኛው በሀገራችን የሚሰራበት የፕሮጀክት አይነት ዲዛይኑን አሰሪው በራሱ መንገድ እንዲዘጋጅ ካደረገ በኃላ ግንባታውን በተቋራጭ እንዲከናወን የሚያደርግበት ነው።ይሄውም ዲዛይን ቢድ ቢዩልድ(Design bid build)(DBB) በመባል ይታወቃል፡፡በዚህ የፕሮጀክት አይነት የታቀደውን ግንባታ ዲዛይኑን አሰሪው በራሱ አርክቴክት ወይም በሌላ ሶስተኛ ወገን/ በሌላ አርክቴክት ድርጅት/ እንዲከናወን ያደርጋል፡፡በመቀጠልም በተዘጋጀው ዲዛይን መሰረት ግንባታውን የሚያከናውን ተቋራጭ ወደመምረጥ ሂደት ይገባል፡፡የግንባታው ባለቤት የመንግስት መስሪያ ቤት የሆነ እንደሆነ ግንባታውን የሚያከናውን ተቋራጭ የመምረጡ ስራ የሚከናወነው በግዥ ህግ መሰረት ይሆናል፡፡ይሄ አይነቱ ፕሮጀክት በሀገራችን የተለመደ ነው፡፡
2, ዲዛይን ቢዩልድ(Design build)(DB)
#በሌላ በኩል ደግሞ ተቋራጩ ዲዛይኑን እና ግንባታውን በራሱ የሚያከናውንበት የፕሮጀክት አይነትም አለ።ይሄውም ዲዛይን ቢዩልድ(Design build)(DB) ይባላል፡፡በዚህ የፕሮጀክት አይነት ተቋራጩ የታቀደውን ግንባታ ዲዛይኑን በራሱ አርክቴክት ወይም በሌላ የአርክቴክት ድርጅት አማካይነት ያከናውናል፡፡የአርክቴክት ስራው የሚያስከትለው ሀላፊነት የተቋራጩ ይሆናል፡፡ከዲዛይን ስራው ጋር የተያያዘ ችግር የሚያስከትለው ሀላፊነት አሰሪውን/የግንባታውን ባለቤት አይነካውም፡፡ሆኖም ተቋራጩ ዲዛይኑን ያሰራው በሌላ የአርክቴክት ድርጅት አማካይነት የሆነ እንደሆነ ከአርክቴክቸር ስራው ጋር በተያያዘ ተቋራጩ ለአሰሪው የሚኖርበት ሀላፊነት እንደተጠበቀ ሆኖ አርክቴክቱም ለተቋራጩ በፍትሀብሄር ህጉ ስለእውቀት ስራ ውል በተደነገገው አግባብ ሀላፊነት ይኖርበታል ማለት ነው፡፡በዚህ አይነት ፕሮጀክት የግንባታው ባለቤት/አሰሪው ሙሉ በሙሉ የኮንስትራክሽን ስጋቶችን/risks/ ወደ ተቋራጩ ያስተላልፋል፡፡ይህ ማለት አሰሪው ውጤቱን ማለትም ግንባታውን በመጀመሪያ በቀረበለት ዲዛይን አግባብ በጥራት ተከናውኖለት ከመረከብና በውሉ የተቀመጠውን የግንባታ ዋጋ ከመክፈል ባለፈ ማናቸውም አይነት ሀላፊነት አይኖርበትም ማለት ነው፡፡ለአብነት ለመጥቀስ ያህል የኢትዮጽያ መንገዶች ባለስልጣን(ERA) ዲዛይን ቢዩልድ የመንገድ ፕሮጀክት ሲኖረው ተወዳዳሪ ተቋራጮች የሰርቨየይንግና ዲዛይን ስራዎችን በራሳቸው ከሰሩ በኋላ በዋጋ ይወዳደራሉ፡፡ተቋራጮቹ ዲዛይኑን ሲሰሩ አሮጌ ድልድዮች ካሉ እና ተጠግነው በአዲስ ድልድይ የጥራት ደረጃ መድረስ የሚችሉ ከሆነ ተቋራጮች እንደየፍላጐታቸውና ሙያዊ ምርመራቸው/ምክንያታቸው ተጠጋኝ ድልድይ እና በአዲስ የሚገነባ ድልድይ እያሉ በዝርዝር በዲዛይን አካተው የሚያቀርቡ ሲሆን ምንም ሆነ ምን በውጤት ደረጃ አሰሪው በሚፈልገው የጥራት ደረጃ/ስታንዳርድ መገንባቱ እና ይሄውም በአማካሪው መረጋገጡ ግን የግድ ነው፡፡ምናልባት ተጠግኖ በሚፈለገው የጥራት ደረጃ ይደርሳል የተባለው አሮጌ ድልድይ በጥገና ወቅት ቢፈርስ እንኳ አሰሪውን ክፍያ የመጨመር ሀላፊነት አያስከትልበትም፡፡ስለዚህ ዲዛይን ቢዩልድ ፕሮጀክት ለአሰሪዎች ሪስክ ፍሪ/ከስጋት ነጻ የሆነ የፕሮጀክት አይነት ነው፡፡
#ሌላው ሁለቱም የፕሮጀክት አይነቶች ለኮንስትራክሽን ውላቸው የሚጠቀሙት ጀኔራል ኮንዲሽን የተለያየ ነው።FIDIC በዚህ ረገድ የግንባታ ውል ዝግጅትን በማቅለል ለአለማችን ትልቅ ስጦታ ነው። አለበለዚያ አሰሪና ተቋራጭ በየአንዳንዱ ውል ዝግጅት ወቅት በሁሉም የውል ሁኔታወች ላይ መደራደርን ይጠይቃቸው ነበር።ዛሬ ላይ ግን ለውሉ ጥቅም ላይ የሚውለውን ጀኔራል ኮንዲሽን አስመልክቶ FIDIC ቨርሽን መረጣ እና በስፔሻል ኮንዲሽን ኦፍ ኮንትራክት በሚካተቱ ነጥቦች ላይ ብቻ መወያየት በቂ ነው።
#በተጨማሪም በዲዛይን ቢዩልድ ፕሮጀክት የኮንስትራክሽን ስጋት/ሪስክ ሙሉ በሙሉ ወደ ተቋራጩ የሚተላለፍ በመሆኑ ልዩ የዋስትና ሽፋን ያስፈልገዋል፡፡ስለዚሁም ተቋራጩ በግንባታው ዋጋ ልክ All risk insurance እንዲገባ እና ለዲዛይን ስህተት፣ለስራው ብልሽትና በተቋራጩ ባለሙያወች የስራ ስህተት ለሚከሰት ጉዳትና ኪሳራ ደግሞ professional indemenity insurance እንዲገባ FIDIC ዲዛይን ቢዩልድ ፕሮጀክት ኮምፖቴብል የሆነው ተርንኪ ጀኔራል ኮንዲሽን ግዴታ ያስቀምጣል።
#በሀገራችን ዲዛይን ቢዩልድ የኮንስትራክሽን ፕሮጀክት ብዙም የተለመደ አይደለም።ሆኖም በመንገድ ግንባታ ውሎች የኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን አልፎ አልፎ ይጠቀምበታል።
#በአጠቃላይ በሀገራችን በኮንሰትራክሽን ዲዛይኒንግ እና የውል አስተዳደር ረገድ ሰፊ የእውቀት ክፍተት ያለ በመሆኑ እና ፕሮጀክቶች በተያዘላቸው ጊዜና ገንዘብ የማይጠናቀቁበት ሁኔታ በሰፊው የሚስተዋል እንደመሆኑ ሙሉ የኮንስትራክሽን ሪስክ/ስጋት ወደ ተቋራጩ በማስተላለፍ መንግስታዊ ግንባታዎችን በዲዛይን ቢዩልድ የፕሮጀክት አይነት እንዲከናወኑ ማድረግ የተሻለ አማራጭ ሊሆን እንደሚችል ለመጠቆም እወዳለሁ።
Via~ጉባኤ አሰፍ
现已上线!2025 年 Telegram 研究 — 年度关键洞察 
